1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ፋይዳ ለኢትዮጵያውያን" በሚል መሪ-ቃል የእግር ኳስ ውድድር ዛሬ በይፋ ተጀመረ
የየሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ CUP የሠራተኞች የ2ኛ ዓመት የውድድር ዓመት ዛሬ ግንቦት 16/2017ዓ. ም " ፋይዳ ለኢትዮጵያውያን " የሚል መሪ-ቃል ተሰይሞለት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እንዲሁም የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ምክትል ስራ-አስኪያጅ ወ/ሪት ራሄል አብረሃም በክብር እንግድነት በተገኙበት በድመቀት ተጀምሯል።
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ከንቲባ ምዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስከያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እግር ኳስ አንዱ በመተባበርና በመደጋገፍ የሚሰራ ስፖርት ነው ያሉ ሲሆን ስማርት አዲስ አበባንና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በመተባበር መስራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የህዝባችንን እርካታ ለማረጋገጥ ጠንክረን በአንድነት መስራት ይገባል ያሉት ስራ አስኪያጁ የጀመርነው የስፖርት ውድድር አብሮነትን የምናጠናክርበት መድረክ ይሆናል ሲሉም አክለዋል፡፡
ስፖርታዊ ውድድሩ የተቋሙን የሰራተኞች ቤተሰባዊነት እና የስራ ተነሳሽነት የሚያጠናክር እንዲሁም ጠንካራ የስራ ባህል ያለው ተቋም መገንባት ለማስቻል ሁነኛ ሚና የሚጫወት እንደሚሆን ይታመናል።
በዛሬው የመክፈቻ ጫወታ ዋና መስርያ ቤት ልደታ ክ/ከተማን 3 - 1 በማሸነፍ ተጠናቋል።
በልደታ ክ/ከተማ "የከተማችን የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጅ የቆሻሻ መጠያ አይደሉም" በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ ተከናወነ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ የምትመች ፅዱና ውብ ከተማ እንድትሆን እያንዳንዱ ህብረተሰብ ፅዳትን ባህሉ በማድረግ በባለቤትነት ስሜት አካባቢውን ማፅዳት ይኖርበታል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሁላችን የሆነችውን ከተማ ከብሎክ ጀምረን በማፅዳት የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን በትኩረት መስራት አለብን ያሉት ዶ/ር እሸቱ በ5 ወራት የፅዳት ንቅናቄው የውሃ መውረጃ ቱቦዎችን፣ በወንዝ ዳርቻ የተጣሉ ቆሻሻዎችንና የግንባታ ተረፈ ምርቶችን ማፅዳት ይኖርብናል በማለት ገልፀዋል።
የክ/ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ነፃነት ደረሰ እንደተናገሩት የፍሳሽ ማስተላለፊያ ቱቦዎችን ከቆሻሻ በማፅዳት በክረምት ወቅት ጎርፍ እንዳይከሰት መስራት ይኖርብናል ብለው ፅዳትን ባህል በማድረግ ውብ ምቹና ፅዱ ከተማን እየፈጠርን መጓዝ ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል።
በ5 ወራት የፅዳት ንቅናቄ በባለቤትነት በመስራት አካባቢያችንን ለኑሮና ለስራ ምቹ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል ወ/ሮ ነፃነት።
የልደታ ክ/ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በፍቃዱ ሀይሌ እንደተናገሩት ከተማችንን በሁሉም ዘርፍ የመቀየር እና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ብለው በሁሉም ወረዳዎች የጽዳት ንቅናቄ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።
መንግስት የህዝቡን የልማት ተሳትፎ ያሳየበት፣ በጋራ መልማትንና መጠቀምን ያፀናበት እንዲሁም ያሉንን ፀጋዎች በአግባቡ መጠቀም መቻልን ያረጋገጠበት በመሆኑ እንደሀገር ልንኮራበት የሚገባ ነዉ ። "የንግዱ ማህበረሰብ
'የንግዱ ማኀበረሰብ ሚና ፤ ለሁለንተናዊ ብልፅግና''በሚል መሪ ሀሳብ በከተማ ደረጃ በመዲናችን ያሉ የንግዱ ማህበረሰብ የከተማዋን የልማት ስራዎች ጎበኙ
በከተማችን አዲስ አበባ የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ የልማት ስራዎችን የመዲናዋ የንግዱ ማህበረሰብ በዛሬዉ እለት ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።
ጎብኚዎችም የካዛንቺስ ኮሪደር ልማት ፣አለም አቀፋ ኮንቬንሽን ሴንተር፣አቃቂ የልህቀት ማዕከል፣ገላን ጉራ የተቀናጀ መንደር፣አድዋ መታሰቢያ ሙዘየም፣የቸርቸርና የሜክሲኮ ኮሪደር ልማት፣ልደታ የበጎነት መንደር፣ላፍቶ በራስ አቅም የተሰራ የልማት ስራዎች፣የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲጉለሌ የተቀናጀ ልማት መንደር፣ቦሌ ኤይርፖርት ካርጎ እንዲሁም የነገዋ ሴቶች ማዕከልንና የልበ ብሩህ ትቤት ሠዉ ተኮር ፕሮጀክቶችን እና የመንገድ መሠረተ ልማቶችን መጎብኘታቸዉ ታዉቋል።
ጉብኝቱም ከተማዋ በምታመነጨዉ ገቢ፣ የከተማዋን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚያረጋግጡ የተቀናጁ ዘርፈ ብዙ የልማት ስኬቶች አስመዝግባለች ። ይህም በቀጥታ በንግዱ ማህበረሰብ የላቀ ተሳትፎ ትልቅ ድርሻ እንዲነበረው በተጨባጭ ማሳያ ነው።
በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ የንግዱን ዘርፍ ለማዘመን እየሰራቸው ባሉ በርካታ ተግባራት የንግዱ ማህበረሰብ በዘላቂነት የጀመረዉን የልማት አጋርነት ይበልጥ በማጠናከር ለትዉልድ የሚሻገር የጋራ አሻራን ለማኖር ያለመ መሆኑ ታዉቋል።
ይህም የከተማዋን ገፅታ ከማጉላት ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቷን የሚያጎናፅፍ፤ነዋሪዎቿ የተሻለ እና ትርጉም ያለዉ ህይወት እንዲኖራቸዉ በተጨባጭ እያረጋገጥን የመጣንበት ህያዉ የጋራ ድላችን መሆኑን ለማመላከት ጭምር ስለመሆኑም መገንዘብ ተችሏል።
ነጋዴዎች በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለፁት ባለፍት የለውጥ ዓመታት የተሰሩ የልማት ስራዎች የሰው ልጅን ክብርና ፍላጎት መሰረት አድርገው የተሰሩ መሆናቸውን በጉብኝታችን ማረጋገጥ ችለናል ያሉት ጎብኚዎቹ ይህም መንግስት ለህዝቡ የገባዉን ቃል በተግባር የፈፀመበት ተጨባጭ ሀቅ ነዉ ብለዋል።
አክለዉም መንግስት በሀገር እድገትና በትዉልድ ግንባታ ላይ በሚሠራቸዉ ስራዎች የህዝብን የልማት ተሳትፎ ያሳየበት በጋራ መልማትንና መጠቀምን ያፀናበት እንዲሁም ያሉንን ፀጋዎች በአግባቡ መጠቀም መቻልን ያረጋገጠበት በመሆኑ እንደሀገር ልንኮራበት የሚገባ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም መንግስት የንግዱን ስርዓት ለማዘመን እያደረገ ያለዉን ትጋት አድንቀዉ እንደ ሀገርም ሆነ በከተማ ደረጃ ሁለተናዊ እድገታችንን ለማፋጠን በሚደረጉ ሁለተናዊ እንቅስቃሴዎች የንግዱ ማህበረሰብ በገንዘቡ፣በእዉቀቱ እና በጉልበቱ ድጋፉን ይበልጥ በማጠናከር ለቀጣይ ትዉልድ የምትበጅ ሀገር ለመፍጠር ተቀናጅተን እንሰራለን ሲሉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፈረንሳይ ፣ ፓሪስ ያደረጉት የኢንደስትሪ ጉብኝት በቴክኖሎጂ እና የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ላይ ያተኮረ ነበር። ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን 'ስቴሽን ኤፍ' የተባለውን በአለም ትልቁን የግል የቴክኖሎጂ የስታርት አፕ የቢዝነስ መፍጠሪያ ማዕከልን ጎብኝተዋል። የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ከባቢ ገና በጅምር ደረጃ ያለ ቢሆንም የቴክኖሎጂ እውቀት ጠገብ በሆኑ ወጣቶች የተሞላ እንዲሁም ጠንካራ አቅም እያሳየ በማደግ ላይ ባለ የዲጂታል ትስስር እየተመራ የሚገኝ ነው። መንግሥት እንደ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ያሉ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ፈጠራን ለመደገፍ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። ይኽም ለስታርት አፕ ከባቢ በተለይም በፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ በግብርና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በኢ-ኮሜርስ ግብይት አስቻይ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ ነው። በተጨማሪም የ'ስታርት አፕ' አዋጅ የተሰኘ ሁሉን አቀፍ አዋጅ በማውጣት ለስታርት አፕ እንቅስቃሴዎች የህግ እና ተቋማዊ ማዕቀፎችን በማበጀት ውስን የሆነውን የገንዘብ አቅርቦት የሚያሰፋ፣ የቁጥጥር ተግዳሮቶችን እና መሰል ፈተናዎችን ለማለፍ የሚያስችል ሁኔታ ፈጥሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር በ5G እና 6G ቴክኖሎጂ፣ በሳይበር ደኅንነት፣ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ እና የኦፕቲካል ትስስር ማዕከል የሆነውን የኖኪያ-ፈረንሳይ ዋና መሥሪያ ቤትንም ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ የfiber sensing አቅርቦት፣ የኃይል ቁጠባ ብልሃት እና የ5G ላብራቶሪዎች ምልከታን ያካተተ ሲሆን ይኽም በዘርፉ ፈጠራ፣ መሠረተ ልማት ግንባታ እና ዘርፍ ዘለል ትብብሮች ላይ ለኢትዮጵያ ዋጋ ያላቸው ትምህሮቶች የተገኙበት ነበር።
በመጨረሻም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ፈረንሳይን የሚገኘውን ታሌ የምርምር እና ቴክኖሎጂ መዐከል ጎብኝተዋል። ይኽ በብዝሃ ዘርፍ የሚንቀሳቀስ የታሌ ግሩፕ የምርምር ተቋም የኩባንያው አለምዓቀፍ የምርምር ጥረት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ የሚያገለግል ማዕከል ሲሆን በኤሮስፔስ፣ መከላከያ እና አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ መስኮች ላይ ያተኩራል።
እነዚህ ጉብኝቶች የአለምዓቀፍ ግንኙነቶችን የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር በማፋጠን ሀገራችንን የአፍሪካ የፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ በማመቻቸት ረገድ የእውቀት ልውውጦችን አስፈላጊነት አስምረው የሚያሳዩ ናቸው።
'የከተማችን የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም'' በሚል መሪ ሀሳብ የክረምት የጽዳት ስራዎች ማስጀመሪያ ንቅናቄ ተደረገ።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በስሩ የሚገኘውን የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በማስተባበር በወረዳ 5 እና 9 አስተደዳር ''የከተማችን የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም'' በሚል መሪ ሀሳብ የክረምት የጽዳት ስራዎች ማስጀመሪያ ንቅናቄ አካሂዷል።
በጽዳት ዘመቻ ንቅናቄው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ታደሰ፣የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙላት ተገኝ ፣የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህር አሜን ጨምሮ የመንገድ ጥርጊያ ባለሙያዎች፣የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች፣የብሎክ ነዋሪዎች፣የሰላም ሰራዊት አባላትና የደንብ ማስከበር አባላት ተገኝተው በጋራ አካቢቢያቸውን አጽድተዋል።
አቶ ወንድማገኝ መጪው ጊዜ የክረምት ወቅት በመሆኑ የውሃ መፍሰሻ ድቾች በቆሻሻ እንዳይዘጉና ለጎርፍ አደጋ ስጋት እንዳይሆኑ ለማድረግ የጽዳት ስራው በንቅናቄ መካሄዱንና ወደፊትም በተቀናጀና ወጥነት ባለው መልኩ እንደሚካሄድ በመግለጽ ሁሉም አካል አካባቢውን በማጽዳት ከተማዋን ውብ ጽዱና አረንጎዴ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል።
"የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የንውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ መሆን አይደሉም "
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር "የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም" በሚል መሪ ቃል ሳምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ ተካሄዷል።
በጽዳት ዘመቻው ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ነጋሽ እንደገለጹት አከባቢያችን ከቆሻሻ ማፅዳት የዘመናዊነት መገለጫ መሆኑንና የማፅዳት ልምድ ከግዜ ወደ ግዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቅሰው ወንዞቻችንን ከብክለት መታዳግ ና ወደ ልማት በመቀየር ሁሉም የጽዳት አምባሳደር መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል ።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀይማኖት እንየው በበኩላቸው ይህ የጽዳት ንቅናቄ ቱቦዎች የንፁህ ውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም በሚል በተለያዬ ጊዜያት እንደሚቀጥል ገልፀው ሀሉም ማህበረሰብ አካባቢያቸውን ያሉትን ቱቦዮችና ቦዎች በማጽዳትና በማስዋብ ምቹ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የጽዳት ንቅናቄ በስነ-ስርዓቱ ላይ የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ የፀጥታ አካላት ፣ የክፍለ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ባለሙያዎች የወረዳው አመራር ፣የጽ/ቤቱ ሠራተኞች እና በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ግንቦት 16/2017 ዓ.ም
"ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ መንስኤ ሊሆን አይገባም"
የአራዳ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት "ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ መንስኤ ሊሆን አይገባም" በሚል መሪ ቃል ከአራት ኪሎ ስድስት ኪሎ የመንገድ ኮሪደር ልማት ስራ ተረፈ ምርት ማስወገድና ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ አካሄደ። በፅዳት መርሐ ግብሩ ላይ የክ/ከተማው የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ ፣ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፀጋነሽ ታምራትን ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የወጣት ማህበር አመራርና አባላቶች ፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና የፅዳት አምባሳደሮች እንዲሁም ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የአራዳ ክ/ከተማው የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ እንዳሉት ከአራት ኪሎ ስድስት ኪሎ የመንገድ ኮሪደር የልማት ስራ የከተማዋን ገፅታ ከፍ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን አንስተው በዚህ የልማት ስራ ያሉ ተረፈ ምርቶችን በማንሳትና ኮሪደሩ ውበቱን ጠብቆ ምቹ ገፅታን እንዲፈጥር ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም ወንዞች እና የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎችን በቆሻሻ እንዳይዘጉ ማድረግና ፅዱ ከተማን መፍጠር እንደሚገባ ገልፀው በከተማችን የተጀመረውን የልማት ጉዞ ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ ፅዱ ከተማን መፍጠር ይገባል ብለዋል።
ወ/ሮ ፀጋነሽ ታምራት የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ የፀዳ ከተማ ለሁለንተናዊ የሀገር ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው መጭው የክረምት ወቅት እንደመሆኑ በየአካባቢያችን የሚገኙ የቆሻሻ መውረጃ ቱቦዎችን በማፅዳት ደረቅ ቆሻሻን ሀብት እንዲሆን ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
የአራዳ ክ/ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ተስፋዬ እንዳሉት ፅዳትን ባህል በማድረግ አካባቢን ማፅዳትና በተለይም መጭው የክረምት ወቅት እንደመሆኑ የመንገድ ኮሪደር ስራው በፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎችን መዘጋት እንዳይበላሹ ተረፈ ምርቶቹን በማንሳት እና በማፅዳት ውብ ከተማን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በሳምንታዊ የፅዳት መርሐ ግብር ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች ማምጣት መቻሉንና ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ተፈጥሯል ያሉት የክ/ከተማው የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንየው ዘላለም በመጭዎቹ የክረምት ወራት የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች በደረቅ ቆሻሻ እንዳይዘጉ ማድረግና የመንገድ ኮሪደር ስራ ውበቱን ማስጠበቅና ማስቀጠል ብሎም ወንዞችን እንዳይበከሉ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
የዛሬው የፅዳት ንቅናቄ መርሐ ግብር በክ/ከተማው በሁለት ክላስተር "ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ መንስኤ ሊሆን አይገባም" በሚሎ መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን ንቅናቄው ለሁለት ወራት የሚቆይ መሆኑ ተመላክቷል።
ግንቦት 16/2017
ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ግንኙነታችንን እና ትብብራችንን በሚያጠናክሩ ሰፋ ያለ መጠነ ርዕይ ባላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መወያየት ምንግዜም አስደሳች ነው። ለተደረገልን ደማቅ አቀባበል እና በታኅሳስ ወር በአዲስ አበባ ከነበረን ውይይት ቀጥለን ስላካሄድነው ፍሬያማ ውይይት ምስጋናዬን እገልጣለሁ። ትብብራችን በብዙ ጠቃሚ ዘርፎች የቀጠለ ሲሆን የንግድ ትስስሮቻችንን የበለጠ ማሳደግ ከቅድሚያ የትኩረት ማዕከሎቻችን አንዱ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
