fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
በመዲናዋ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ ተቋማት ቅንጅታቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 30/2017(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ ተቋማት ቅንጅታቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ። ''ወቅታዊ የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ለዘላቂ ደህንነታችንና ዋስትና'' በሚል መሪ ሀሳብ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሒዷል። ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በመዲናዋ ከ378 በላይ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች በጥናት ተለይተዋል። ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ አደጋ ያመጣሉ ተብሎ የተለዩ ከ170 በላይ ለሚሆኑት ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ቀሪዎችን የማጠናቀቅ ስራ ይከናወናል ነው ያሉት። በዋናነትም የተደፈኑ የፍሳሽ መሰረተ ልማቶችን የማጽዳትና የማስተካከል ስራዎችን ማከናወን ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ አስረድተዋል። በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ጎርፍና ሌሎች ተያያዥ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል በትኩረት በመስራት በዘላቂነት ችግሮችን ለመፍታት መረባረብ እንደሚገባም ጠቅሰዋል። በመዲናዋ የተካሔደው የኮሪደር ልማት የአደጋ ስጋት ተጋላጭነትን በእጅጉ የቀነሰ ነው ብለዋል። የመንገድ፣ የመብራት እና የቴሌኮም መሰረተ ልማት ግንባታዎች የጥራት ደረጃቸውን ጠብቀው መገንባታቸውን ለአብነት አንስተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽነር ኮማንደር አሕመድ መሀመድ በበኩላቸው፤ የምክክር መድረኩ ባለድርሻ አካላት በመዲናዋ የተለዩ የአደጋ ስጋት ቦታዎችን ለማሳወቅና በቅንጅት መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። ይሕም አስቀድሞ ለመከላከልና አደጋ ሲከሰት ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ተግባራትን በቅንጅት ማከናወን የሚቻልበትን አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ በዘንድሮው የክረምት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን በመለየት የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ መርክነሕ ያእቆብ በበኩላቸው፤ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ እስካሁን በትብብር ሲሰሩ የቆዩ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል። የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛቸው አበበ የተቋማት በትብብር መስራት ማህበረሰቡ ጉዳት ሳይደርስበት አደጋን መከላከል ያስችላል ነው ያሉት። በዚሁ ጎን ለጎንም ተቋማት አካባቢ የተጠያቂነት ስርዓትም ሊኖር እንደሚገባ ነው ያመለከቱት። #Ethiopia #Ethiopian_News_Agency #ኢ

መንግስት የአዲስ አበባ ከተማን እንደ ስሟ ጽዱና ውብ እያደረገ ያለውን ተግባር ለማገዝ ነዋሪው ፍሳሽም ሆነ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ መያዝና ማስወገድ እንዳለበት ተገለፀ። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዙሪያ በተለያየ መልኩ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መድረክ በማዘጋጀት፣ በቤት ለቤት፣ በሻይ ቡና ፕሮግራም፣ በንቅናቄ እና በተለያዩ ስልቶች ግንዛቤ እየተፈጠረ እንደሚገኝ ጽ/ቤቱ አሳዉቋል። የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በተቀናጀ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት፣መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የከተማ ጽዳትና የጎርፍ መከላከል ንቅናቄ ዕቅድ ዙሪያ ለብሎክ ካውንስል አመራሮች፤ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣አስተባባሪና ቡድን መሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናየ ጫኔ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለጹት የሚሰጠውን ግናዛቤ ወደ ተግባር ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግና በጽዳት ስራው የኃይማኖት ተቋማት፣ዕድሮች፣ድርጅቶችና ተቋማት በንቃት ልትሳተፉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ እንደተናገሩት ቀደም ሲል በመኖሪያ አከባቢ በተቋማትና በብሎክ የጽዳት ንቅናቄ ስናካሄድ የቆየን ሲሆን መጪው ክረምት በመሆኑ የፍሳሽ መውረጃዎችን ማጽዳት ይገባል ብለዋል። በጽ/ቤቱ የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ቡድን መሪ ወ/ሮ እቴነሽ አበራ እና አቶ ጌቱ ኩምሳ የክፍለ ከተማው ጽዳት ስራዎች አስተባባሪ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል። በክፍለ ከተማው በሚፈጠር ግንዛቤ የህብረተሰቡ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንደመጣና ቆሻሻን የመለየትና መልሶ መጠቀም እየተለመደ መምጣቱን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ አያይዘውም መንግስት የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ ውብና ማራኪ እየደረገ ያለውን ተግባር ነዋሪውም በየአከባቢው የፍሳሽም ሆነ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ መያዝና ማስወገድ ይገባል ብለዋል። በተጨማሪም ጨለማን ተገን በማድረግ ቆሻሻ በመነገድ ላይ የሚጥሉና የሚያዝረከርኩ ህገ ወጦችን መከታተልና የወጡ ህግና ደንቦችን ተግባራዊ በማድረግ በቅጣት ማስተማር ያስፈልጋል ብለዋል። ሚያዝያ 24/ 2017 Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ጋር በመሆን ለስራ ጉብኝት ፈረንሳይ ፓሪስ ገብተዋል። በብሔራዊው የጦር ኃይሎች ሙዚየም የአቀባበል ሥነሥርዓት የተደረገላቸው ሲሆን በጉብኝታቸው ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው የሚወያዩ ይሆናል። Prime Minister Abiy Ahmed, accompanied by First Lady Zinash Tayachew and a high-level delegation, arrived in Paris, France earlier today for a working visit whereupon a welcoming ceremony was held for the Prime Minister at the Musée de l’Armée. During the visit, he is scheduled to meet with President Emmanuel Macron.

በመዲናችን አዲስ አበባ ከ2ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ካርድ አግኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ከሰባት አስርት ዓመታት በላይ የነዋሪነት መታወቂያን ለነዋሪዎች በመስጠት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረች ሲሆን ከዚህ ቀደም ለነዋሪዎቿ የምትሰጠውን የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ አሰጣጥ ከህገ-ወጥነት ለመካላከል እና ወደ ዲጂታል በማሸጋገር ታዓማኒነት ያለው የማንነት ስርዓት ለመዘርጋት ከወረቀት ስርዓት ወደ ዲጂታል ለመቀየር ላለፉት ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል። በዚሁ መሰረት ትናንት ግንቦት 13/2017ዓ.ም የወረቀት የነዋሪነት መታወቂያ ወደ ዲጂታል የተቀየረላቸው ነዋሪዎች ቁጥር 2 ሚልየን አልፏል። ይህ የመታወቂያ የዲጂታል ምዝገባ የነዋሪን የባዮሜትሪክ መረጃን ያካተተ ከ35 በላይ ለስታትስቲክሳዊ ጥቅም የሚውሉ የግለሰብ መረጃዎች የሚመዘገቡበት ስርዓት ነው። የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የወረቀት መታወቂያ መስጠትን ለመጨረሻ ግዜ ማብቃቱን ወደ ኋላ ቀርተው የነበሩ 14 ወረዳዎችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል ሽግግር መደረጉን ሰኔ 25/2016ዓ.ም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ኤጀንሲው በቀጣይ ወራት በስራ ላይ ያለውን የነዋሪነት መታወቂያ ይዘት፣ የአገልግሎት ዘመን እና የገፅ ዲዛይን ከተማዋ ያለችበትን ደረጃ በሚመጥን እና ፋይዳን መሰረት አድርጓ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ / Smart Card/ አድርጓ ለማሻሻል ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በኤጀንሲው የወሳኝ ኩነት ምዘገባን ጨምሮ በጠቅላላው ወደ 3 ሚልዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች መረጃ በዲጂታል ምዘገባ የመረጃ ቋት ውስጥ እንዳሉም ተነግሯል።

የህዝባችንን የኑሮ ጫና የሚያቃልለዉ እና ለዉጥ የሚያመጣዉ የሚታይ፣ የሚጨበጥ እና ቀጣይነት ያለዉ ስራ ብቻ ነው! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የተደራጀ ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ፣ የትውልድ ግንባታ መሰረት ነው። በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ የሚዲያና የኮሚዩኒኬሽ ንአመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ከተማዋ ባከናወነቻቸውና እየሰራቻቸው ያሉ ተግባራትን እንዲሁም ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ የሚዲያ አካላት ሊኖራቸው በሚገቡ ሚናዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩ ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎችን ተናቦ ሰርቶ በማጉላት ዜጎች በአስተሳሰባቸው የተሻሉ እንዲሆኑ ለትውልድ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት የኮሚዩኒኬሽን እና የሚዲያ አካላት ትልቅ ድርሻ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ከተማዋ ባለፉት አመታት ሀገሪቱ በፖለቲካ፣በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲው መድረክ ያገኘቻቸው ውጤቶች፣የልማት ስራዎች፣በቴክኖሎጂው ዘርፍ የታዩ እምርታዎች፣ የወጣቱን የስራ እድል ተጠቃሚነት ከማረጋገጥና ከተረጅነት ወደ አምራችነት በማሻገር ሂደት የተሰሩ ስራዎች፣ ከተማዋን ውብ ጽዱና በአረንጓዴ ከማድረግ የተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም በትራንስፖርት፣በጤና፣በትምህርት ዘርፍ በተማሪዎች ምገባ፣በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣በአገልግሎት አሰጣጥና መሰል ተግባራት የተከናወኑ ተግባራት በጥልቀት የተዳሰሱ ሲሆን የሚዲያ አካላት የመረጃ ሚዛናዊነትንና ትክክለኛነትን እንዲሁም የሚዲያ መርህን ተከትሎ መስራት እንዳለባቸውም ተመላክቷል። የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ የሚዳያ አካላት በተለያዩ ዘርፎችና ሃሳቦች ላይ ስለሚሰሩ ለተነሱት ሃሳቦች በቂ ግንዛቤ እንዳላቸውና መድረኩን የሚመጥኑ በሳል ሃሳቦችን ይዘው መምጣታቸውን ገልጸው ሰላምን በተመለከተ መንግስት ሁልጊዜ ለሰላም ትኩረት ሰጥተው እየሰራ መሆኑን በማውሳት የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ አካላት እውነተኛና ተጨባጭ መረጃ በመያዝ ልማትን በሚያጠናክር ሁኔታ መንቀሳቀስ እንዳለበት ተናግረዋል። የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሌማንቾ የሚዲያው አካላት ማንኛውም በዚህች ሀገር ስኬት ላይ የሚጋረጥን ኃይልና አስተሳሰብ በበቂ እውቀትና ልምድ ላይ ተመስርቶ መመከት ይጠበቅበታል ያሉ ሲሆን የመንግስት ጥረቱ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው ብለዋል። የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ በቀለች ጭርቆ በበኩላቸው ሚዲያ የማይዳስሰው ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳይ የለም ያሉ ሲሆን የሚዲያ አካሎቻቸን አጀንዳ ከመቀበል ይልቅ አጀንዳ ወደ መስጠት የተሸጋገርንበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ሃሳብን በሀሳብ የበላይነት መመካት እንደሚገባም ተናግረዋል ። ግንቦት 14/2017

የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ ፤የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው"በሚል መሪ ሀሳብ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ፣የማህበረሰብ አንቂዎች እና የሚኒሚዲያ አባላት ዉይይት እያካሔዱ ይገኛሉ በ 11ዱም ክፍለ ከተሞች ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚሰሩ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የማህበረሰብ አንቂዎች እና የሚኒሚዲያ አባላት በዛሬዉ እለት ዉይይት እያካሔዱ ሲሆን በሁሉም መድረኮች የጋራ መግባባት በመፍጠር የተገኙ ውጤቶችን የሚያፀኑ ፣ ከችግሮች በላይ የሚያቆሙ ፤ ሚዛናዊ አስተሳሰብ የሚያስፍኑ ጠንካራ ሀሳቦች የተነሱበት እና የቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት ዉይይት እንደሚሆን ይጠበቃል። የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ተገኝተዉ ዉይይቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በከተማ ደረጃ በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሠማሩ የከተማችን ነዋሪዎች ጋር ዉጤታማ ውይይቶች መደረጋቸዉን ጠቅሠዉ የዛሬዉ ዉይይትም የዚሁ አንዱ አካል ነዉ ብለዋል። አክለዉም በየደረጃዉ ያሉ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሠራዊት የሀሳብ ልዕልናን በትዉልድ ላይ ለማስረፅ ሚናቸዉ የጎላ መሆኑን ተገንዝበን ለከተማችን ሁለተናዊ እድገት በዘላቂነት ለማስቀጠል ዋጋችን ብዙ ነዉና ለትዉልድ ያለንን ዉድ ስጦታ እናበርክት በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።፡ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከ 4ሺ በላይ የሚሆኑ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ አካላት በዉይይቱ እየተሳተፉ መሆናቸዉ ታዉቋል።

የተሳሳቱ መረጃዎችን መታገል ሃገር ወዳድ ከሆነው የሚዲያ ባለሙያ እንደሚጠበቅ ተገለፀ "የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሃገራዊ መግባባት ካስማ ፤ የትውልድ ግንባታ መሰረት ነው" በሚል መሪ ቃል የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሚዲያ ባለሙያዎችና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የጋራ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። በውይይቱ ላይ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የሚዲያው የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም አጠቃላይ የሚዲያ ባለሙያው ተሳትፈዋል። በውይይቱም ላይም የተሳሳቱ መረጃዎችን መታገል ሃገር ወዳድ ከሆነው የሚዲያ ባለሙያ እንደሚጠበቅ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተናግረዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው በሃገር እና በከተማ ደረጃ ለተመዘገቡ ውጤቶች የሚዲያ ባለሙያው አስተዋፅኦ የላቀ መሆኑን በማውሳትይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። የሚዲያ ባለሙያው የሙያ ሥነ-ምግባርን የጠበቁ ተዓማኒ መረጃዎችን ለህዝቡ ተደራሽ ማድረግ አለበት ያሉት አቶ ካሳሁን ጎንፋ ፤ ከጋዜጠኞች ከወገንተኝነት የፀዳ እንዲሁም ሙያ እና ህዝብን መሰረት ያደረገ ዘገባ እንደሚጠበቅ አጽዕኖት ሰጥተዋል፡፡ "የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሃገራዊ መግባባት ካስማ ፤ የትውልድ ግንባታ መሰረት ነው" በሚል መሪ ቃል የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሚዲያ ባለሙያዎች እና አመራሮች ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። በውይይቱ ላይ በከተማና በሃገር አቀፍ ደረጃ በልማት፣ በሠላም፣ በዲፕሎማሲ፣ በትምህርት፣ በመልካም አስተዳደር እና በሌሎችም ዘርፎች በተመዘገቡ በርካታ ዉጤቶች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ነዉ ።

የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ ፤የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው"በሚል መሪ ሀሳብ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የማህበረሰብ አንቂዎች እና የሚኒሚዲያ አባላት የመዲናችንን የልማት ስራዎች እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡ በጉብኝቱም ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚሰሩ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የማህበረሰብ አንቂዎች እና የሚኒሚዲያ አባላት ተሳታፊ ሲሆኑ ፤ በ11 ዱም ክፍለ ከተሞች የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የተለያዩና በርካታ የልማት ስራዎችን ተዘዋዉረዉ እየጎበኙ መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለስ በጉብኝቱ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባ ለችግር የማይበገሩ አመራሮች እና የኮሙኒኬሽን እና የሚዲያ ሠራዊት ይዛ የነዋሪዎቿን ህይወት ለመቀየር እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ቀን ከሌት እየተጋች መሆኗን የተገኙ ስኬቶች ህያው ምስክር መሆኑን ገልፀዋል ። እንደ ኮሙኒኬሽን እና የሚዲያ ሠራዊት የሀሳብ ምንጭ ሆነን ፤ የከተማችን ብሎም የሀገራችን በሀሳብ የሚያምን እና የሚሞግት ትዉልድ ለመፍጠር ሚናችን የጎላ መሆኑን ልንረሳ እደባም ብለዋል ። ዛሬ በምንጎበኛቸዉ በከተማዋ የተሠሩና እየተሠሩ ያሉ በርካታ እና የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በማስተዋወቅና ህዝባችንን የልማትና የብልፅግና ጉዞ አጋር በማድረግ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ተግተን ኃላፊነታችንን እንድንወጣ በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል። በመጨረሻም ከዚህ ጉብኝት በኋላ ከ 4ሺ በላይ ከሚሆኑ የሚዲያ አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግ የቢሮ ኃላፊዋ ጠቁመዋል። በከተማዋ የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ በርካታና የተለያዩ የህዝብ መዝናኛ አገልግሎቶች እና የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ተርሚናሎች፣ፖርኮች ፣ የተለያዩ የንግድ ዘርፎችን ያቀፉ ማዕከላት ፣ታሪካዊ ቅርሶች እና አደባባዮች፣ የመኪና፣የእግረኛ እና የሳይክል መተላለፊያ መንገዶች ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እና ሠዉ ተኮር ፕሮጀክቶች የፅናት እና የብርታት ምስክሮች በመሆናቸው በጉብኝቱ የተካተቱ ናቸዉ።

በመዲናችን አዲስ አበባ ተጨማሪ ከደረቅ ቆሻሻ ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ (waste to Energy) ግንባታ ለዘመናዊ የቆሻሻ አስተዳደር Addis Ababa Advances Green Future with Landmark Waste-to-Energy Agreement

ቃላችንን በተግባር ለመፈፀም እንድንችል የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን! በአንድ ጊዜ አንድ ሺሕ መኪኖችን የማቆም አቅም ያለውን እና በሾላ ገበያና መገናኛ መካከል ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ የሚያቃልለውን የካ ቁጥር 2 የመኪና ማቆሚያን መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል:: ይህ የመኪና ማቆሚያ ከምድር በላይ ባለ አምስት ወለል እንዲሁም በመሬት ውስጥ ባለ ሁለት ወለል በጥቅሉ 8 ወለል ያለው ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት እንዲሁም የህዝባችንን እንግልት የሚያቃልል ነው:: የመኪና ማቆሚያው የህዝባችን አገልግሎት ምቾትና ክብርን የጠበቀ፣ ተገልጋዮችን ከዝናብና ፀሃይ የገላገለ ፣ የንፅህና መጠበቂያ ያለው፣ የሰው እና የመኪና አሳንሰር ያለው፣ ለአካል ጉዳተኞች አካታች የሆነ አገልግሎት የሚሰጥ፣ ሶስት የመኪና ማጠቢያ ስፍራ ያለው እንዲሁም ለነዋሪዎች የስራ እድል የሚፈጥር ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሆን ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሱቆች እና ቢሮዎች ያሉት የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎትን ለማሳለጥ እንዲሁም የትራንስፖርት ስርአቱን ለማዘመን ትልቅ አስተዋጽዖ ያለው ነዉ። የተሽከርካሪ ማቆሚያው ለመጀመሪያ ጊዜ በህንጻ ደረጃ የተገነባ ሲሆን መሬት እና በጀት በመመደብ የተሰራው ይህ ስራ ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ አበባ የማድረግ አካል ነው:: ከለውጡ በፊት በመንግስት የተገነቡ የፓርኪንግ ቦታዎች ብዛት 2 ሲሆን 500 በላይ መኪኖችን የማቆም አቅም ያልነበራቸው እንዲሁ 1 ተርሚናል ብቻ የነበረዉን ከለውጡ በኃላ በሰራነው ስራ 150 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን የገነባን ሲሆን የዛሬውን ጨምሮ 35 ሺሕ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማቆም የሚችሉ እንዲሁም 49 የሚደርሱ ተርሚናሎችን ገንብተን የትራንስፖርት ስርዓቱን ለማዘመን በመስራት ላይ እንገኛለን:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እናህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager