fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
እንኳን ለ2017 የዘመን መለወጫ በአል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም አዲስ ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት

የአዲስ አመት ዋዜማን ከከተማችን ነዋሪዎች ፣ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች እና የከተማችን አመራሮች ፣አምባሳደሮች ፣ዲፕሎማቶች ፣የአለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣የከተማችን ወጣቶች እና ባለሀብቶች በተገኙበት እጅግ በደማቅ ሁኔታ እያከበርን ነው ። በድጋሚ አዲሱ አመት የሰላም ፣የፍቅር፣ የጤና እና የስኬት እንዲሆንልን እመኛለሁ። አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ! ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አመት ዋዜማን ከከተማችን ነዋሪዎች ፣ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች እና የከተማችን አመራሮች ፣አምባሳደሮች ፣ዲፕሎማቶች ፣የአለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣የከተማችን ወጣቶች እና ባለሀብቶች በተገኙበት እጅግ በደማቅ ሁኔታ እያከበርን ነው ። በድጋሚ አዲሱ አመት የሰላም ፣የፍቅር፣ የጤና እና የስኬት እንዲሆንልን እመኛለሁ። አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ! ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በሀገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ፤ እንኳን ለ2ዐ17 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። በሰላም ያደረሰን ፈጣሪ አምላክ የተባረከና የተመሰገነ ይሁን። መልካም አዲስ አመት ! አዲሱን አመት የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የስኬት ያድርግልን፡፡ ባሳለፍነው ዓመት እንደ ሀገር የተጋረጡብንን በርካታ ፈተናዎች በድል የተሻገርንበት፣ ስኬታማ ስራዎችን በመስራት ውጤቶችን ያስመዘገብንብት፤ እና የሕዝባችንን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ያደርግናቸው ጥረቶች ፍሬ ማፍራት የጀመሩበት ነው፡፡ የኢትዮጵያ መልክ የሆነችው፡ መዲናችን አዲስ አበባም በፍቅር የደመቀች እና በህብረ-ብሔራዊነት ያጌጠች ከተማ መሆኗን በተግባር እያሳየች የአብሮነት፣ የመተባበርና የመከባበር እሴትን አጠናክራ ያሳየችበት አመት ነው፡፡ ባለፈ ያሳለፍነው አመት አብሮነታችንን በማጠናከርና የበጎ ተግባር ስራዎቻችንን በማስፋት፡ የበርካታ የከተማችንን አቅመ ደካማ የሀገር ባለውለታዎች እና ለችግር የተጋለጡ ወገኖችቻንን እንባ ያበስንብት፣ ትኩረትና ክብር ተነፍጓቸው የኖሩ ወገኖቻችንን ዝቅ ብለን በማገልገል ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ያጎላንበት አመትም ነው፡፡ ልማታችን ማንንም ወደኋላ የተወ አይደለም፡፡ በመሆኑም ባሳለፍነው ዓመት እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸው የተሻሉ ውጤቶችን በመዘከር በቀጣይ ትልሞቻችን ላይ የሰላምና የልማት ሀይሎችን በማስተባበር በርካታ ሀገር አሻጋሪ ተግባራትን ለማከናወን ተዘጋጅተናል፡፡ በአዲሱ አመት እስከ አሁን በሰራነው ሳንረካ ይልቁንም የዛሬውን ትውልድ ከነገው ትውልድ ጋር በማስተሳሰር የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በብዙ ጥረት፣ በብዙ ትጋትና እና በማያቋርጥ ልፋት እጅ ለእጅ ተያይዘን በመስራት ሕዝባችንን ዝቅ ብለን እናገለግላለን፡፡ አዲሱ ዓመት በአንድነት የምንነሳበት፤ ከማይረቡን አጀንዳዎች ርቀን፡ እጆቻችንን ለስራ በማትጋት የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት በማረጋገት ሰላማችንን ምናፀናበት ከውጭና ከውስጥ የሚተናኰሉንን ሀይሎች በመመከት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አስጠብቀን የምንቀጥልበት እንደዚሁም የነዋሪዎቻችንን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ተግተን የምንሰራበት ፍሬያማ ዓመት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ ፡፡ አመሰግናለሁ መልካም አዲስ ዓመት!! ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለመላው የከተማችን ነዋሪዎች፥ እንኳን ለ2017 አ.ም አዲስ አመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያልኩ አዲሱ አመት የደስታ፣የሰላም፣ የፍቅር፣የአብሮነት እና የብልፅግና ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ ! በአዲሱ አመት ያሰብናቸው ግቦች የሚሳኩበት፣ ህዝባችንን በላቀ ተነሳሺነትና ቁርጠኝነት የምናገለግልበት እና እንዲሁም የከተማችንና የአገራችን እድገትና ብልፅግና በተባበረ ጥረታችን እውን የምናደርግበት እንዲሆንልን እመኛለሁ! በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ

በመጪዉ በዓላት የተሟላ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ በመጪዉ የአዲስ አመት፣የመስቀል ደመራ፣ የኢሬቻና የመዉሊድ በዓላትን በተሟላ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች እንዲከበር ለማስቻል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱን የከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ዛሬ ጳጉሜ 05 ቀን 2016 ዓ.ም በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በመግለጫዉ ላይ እንዳስታወቁት ጽ/ቤቱ ለመጪዉ የአዲስ አመት ፣ የመስቀል፣ የኢሬቻና የመዉሊድ በዓላት ሲከበሩ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች በተሟላ ሁኔታ ለመስጠት እንዲቻል በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣በፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እና በኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የአገልግሎቶች መስተጓጓል እንዳያጋጥምና ባጋጠመም ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ስለመደረጉና የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤትም ስራዉንም እያስተባበረና እየመራ እንደሚገኝ አብራርተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ መጪዎቹ በዓላት ከማንኛውም አደጋ ተጠብቀዉ ያለአደጋ ክስተት እንዲከበሩ አስፈላጊውን የቅድመ አደጋ መከላከልና የግንዛቤ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን ጠቅሰዉ ህብረተሰቡም በኮሚሽን መ/ቤቱ በኩል እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግም አሳስበዋል። የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኘ በበኩላቸዉ በበዓላት ጊዜ ከዕርድና ከመሳሰሉት ተግባራት ጋር ተያይዞ የሚመነጩ ተረፈ ምርቶችን በከተማዉ ገጽታ ላይ የጽዳት መጎደል እንዳያስከትሉ የጽዳት አገልግሎት የሚሰጡ ማህበራት በበቂ ሁኔታ የተዘጋጁ ስለሆነ ህብረተሰቡ ማናቸዉንም ተረፈ ምርቶች በጥንቃቄ በማዘጋጀት የጽዳት አገልገልግሎት ለሚሰጡ ማህበራት እንዲያስረክቡ አስታውቀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሀንስ ገብሬ በበኩላቸው እንደተናገሩት መጪዎቹ በዓላት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ጥቅም ላይ የሚውልባቸዉ በመሆኑ የሚስተዋለዉን የኃይል መቆራረጥ ለመቀነስ አስፈላጊዉ ቅድመ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዉ ለሚያጋጥሙ የሀይል መቆራረጥና የጥገና ስራዎች በሁሉም ማዕከላት ግብረሀይል ተቋቁሞ ወደስራ መግባቱን አብራርተዋል።

መልካም አዲስ ዓመት! ዛሬ የነገ ቀንን “የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት “ብለን ትኩረት ተነፍገው ለነበሩ ትኩረት እና ክብር እየሰጠን በበርካታ ዝግጅቶች እያከበርን ነው። በብርሃን የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ከክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጋር በመሆን አብረናቸው ቆይታ አድርገን እንኳን አደረሳችሁ ብለን ቀጣዩ የትምህርት ዘመን ብረሃናማ እና የተሳካ እንዲሆንላቸው ተመኝተናል። እንዲሁም በነገዋ የሴቶች ተሀድሶና ክህሎት ማጎልበቻ ማዕከል ተገኝተን ነገአቸው ብሩህ እንደሆነ እና አዲሱ ዓመት ወደ የበለጠ ለውጥ የሚመጡበት ዓመት እንደሚሆን ተመኝተን አብረናቸው ቆይታ አድርገናል። በተጨማሪም ከህጻናት ጋር በነበረን ቆይታ በገነባናቸው የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች - በቀዳማይ ልጅነት ማዕከል፣ በወንድማማች 2 እንዲሁም በቦሌ የመደመር ትውልድ ሜዳ ላይ እንኳን አደረሳችሁ ብለን አብረናቸው አሳልፈናል። የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት ብለን! ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እንኳን ለ2017 የዘመን መለወጫ በዓል ዕንቁጣጣሽ በዓል አደረሳችሁ ዘመን ዕድል ነው፡፡ ዘመንን መጠቀም ግን የሥራ ውጤት ነው፡፡ ዘመንን ፈጣሪ ለሁላችንም በእኩልነት ሰጥቶናል፡፡ ልዩነት የሚፈጠረው በዘመን በመሥራትና ባለመሥራት ነው፡፡ በታሪካችን ውስጥ የምንኮራባቸው ምእራፎች አሉ፡፡ በሕይወታችን ውስጥም ደስ የሚያሰኙን ጊዜያት አሉ፡፡ እነዚያ ምእራፎችና ጊዜያት ሌላ ነገር አይደሉም፡፡ የተሰጠንን የዘመን ዕድል በሚገባ ተጠቅመን የሠራንባቸው ወቅቶች ናቸው፡፡ እኛ ብንፈልግም ባንፈልግም ዘመን ይለወጣል፡፡ ጊዜ ወደፊት ብቻ የሚሄድ ማሽን ነውና፡፡ ማንም አያስቆመውም፤ አቅጣጫም አያስቀይረውም፡፡ የሚቻለው በጊዜ መጠቀም ብቻ ነው፡፡ “ክረምት ለሰነፍ ገበሬ መዓት፤ ለጎበዝ ገበሬ ምሕረት ነው” ይባላል፡፡ ምሕረትና መዓቱ ከዝናቡ የሚመጣ ሳይሆን ከገበሬዎቹ ዝግጅትና ሥራ የሚገኝ ነው፡፡ በሰነፍ ገበሬ ላይ ዘመን ይለወጥበታል፤ ብርቱው ገበሬ ግን ዘመንን ራሱን ይለውጠዋል፡፡ በ2016 ለኢትዮጵያ ምን አሳክተናል? በ2017ስ ለኢትዮጵያ ምን ተዘጋጅተናል? የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የዘመን መለወጥን ትርጉም ይቀይረዋል፡፡ ዘመን እየተለወጠብን ነው ወይስ ዘመኑን እየለወጥነው ነው? የሚለውን ያመለክተናል፡፡ ኢትዮጵያን ዘመን እየለወጣት ብዙ ጊዜ ኖራለች፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ በብርታትና በትጋት ዘመኑን ለውጣው ታውቃለች፡፡ ዘመን ሲለውጠን፣ ከተራራ እንደተፈነቀለ ድንጋይ፣ ወዳሰብነው ሳይሆን ወደ ፈለገው ነው የሚወስደን፡፡ 2017 የሚለውጠን ሳይሆን የምንለውጠው ዓመት እንዲሆን ነው ምኞቴ፡፡ ዕቅዶቻችንን ተግብረን፤ ፕሮጀክቶቻችንን በጊዜና በጥራት አጠናቅቀን፤ ግጭቶቻችንን በውይይትና በድርድር ፈትተን፤ የዘመናት ስብራቶቻችንን በምክክርና በሽግግር ፍትሕ ጠግነን፤ በብዙ ነገሮች ራሳችንን ችለን፤ ሪፎርሞቻችንን በብቃት አሳክተን፣ የምንለውጠው ዘመን እንዲሆን ነው ምኞቴ፡፡ 2017ን በኢትዮጵያ ታሪክ የሚጠቀስ ዘመን ለማድረግ እንዘጋጅ፡፡ የዘመናት ዕዳዎቻችን የምናወራርድበት፤ የኖሩ ቁስሎቻችን የምናክምበት፤ የዘመናት ሕልሞቻችንን ሥር መሠረት የምናስይዝበት፤ የታሪክን መኪና መሪና ማርሽ የምንቆጣጠርበት ዘመን ለማድረግ እንነሣ፡፡ ወደፊት የሚመጡት ልጆቻችን “ይሄ ታሪክ የተሠራው፣ የዛሬ ስንት ዓመት በ2017 ነው” እንዲሉን እናድርገው፡፡ በወጀብና በዐውሎ ውስጥ አስገራሚ ሥራዎችን እንድንሠራ የፈቀደ ፈጣሪ ዛሬም ከእኛ ጋር ነው፡፡ ነገም ከእኛ ጋር ነው፡፡ መሥራት የእኛ ማከናወንም የእርሱ ነው፡፡ እኛ ከተነሣን ዘመኑን እንድንለውጠው እርሱ ይረዳናል፡፡ በድጋሚ እንኳን ለ2017 የዘመን መለወጫ በዓል ዕንቁጣጣሽ አደረሳችሁ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ጳጉሜን 5፣ 2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የነገ ቀን ጳጉሜ 5 የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት!
የነገ ቀን ጳጉሜ 5 የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት!

የነገ ቀን ፤ የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት የነገ ቀን ፤ የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት…

በከተማዉ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም እየተገነባ እንደሆነ ተገለጸ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በተጠናቀቀዉ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን አሰመልክቶ ብልጫ ላመጡ ባለሙያዎችና ስራ ክፍሎች እንዲሁም ለተባባሪ ተቋማት የዕዉቅናና ሽልማት መርሀ-ግብር ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም አካሂዷል። በመርሀ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት በከተማዉ በሚያጋጥሙ ማናቸዉም አደጋዎች ለአደጋ ምክንያት የሚሆኑ አሰራሮችን የሚከተሉት ላይ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን አሰራር መተግበር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዉ በዚህ መነሻም የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቀዉ በማይሰሩት ላይም በህግ የሚጠየቁበት አሰራር እንደሚኖር አስታዉቀዋል። ኢንጂነር ወንድሙ አያይዘዉም በከተማዉ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል በተለይም በሰዉ ሀይልና በማሽነሪዎች የኮሚሽኑን አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ጠቅሰዉ ለዚህም በከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠዉ አብራርተዋል። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በተጠናቀቀዉ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በኮሚሽን መ/ቤቱ በሁሉም ዘርፎች ከአምና ተመሳሳይ ጊዜ ሲነጻጸር የተሻለ ዉጤት መመዝገቡን ጠቅሰዉ ለዚህ ዉጤት መመዝገብ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ፣ ሴክተር ተቋማት፣ ህብረተሰቡና የኮሚሽን መ/ቤቱ አመራርና ሰራተኞች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ በተጠናቀቀዉ የ2016 ዓ.ም በጀት በስራ አፈጻጸማቸዉ ብልጫ ላመጡ ሰራተኞች እና ስራ ክፍሎች እንዲሁም ለባለድርሻ ተቋማት ዕዉቅናና ሽልማት የተሰጠ ሲሆን ኮሚሽን መ/ቤቱ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሚያከናዉናቸዉ ተግባራት አብረዉት ከሚሰሩ ተቋማት ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል ። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939*ፈጥነዉ ያሳውቁ። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et