1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
በኢትዮጵያ የቲያትር ጥበብ ውስጥ ጉልህ አሻራ ባሳረፈው አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ህልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽኩ፤ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ነብስህን በአጸደ ገነት ታኑረው።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የጥበብ ሰው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
በኢትዮጵያ ቴአትር ታላቅ ዐሻራውን ያሳረፈውና በሃገሩ ጉዳይ በጸና አቋሙ የሚታወቀው ታላቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
አንጋፋው የጥበብ ሰው አርቲስት ደበበ እሸቱ፤ በተለያዩ ታሪካዊና አዝናኝ ፊልሞች እንዲሁም የቴያትር ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ነበረው።
ላለፉት አራት አመታት በላይ ደግሞ የከተማችን የጽዳት አምባሳደር የነበረ ሲሆን ታላቁ የጥበብ ሰው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከሙያ ዘርፉ ጎን ለጎን የከተማዋን ፅዳትና ውበት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በማለዳ እየወጣ በፅዳት ንቅናቄ ስራው ላይ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እየፈጠረ የቆየ ትጉህ የከተማዋ የፅዳት አምባሳደር ነበር።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በአንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ሕልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፁ ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለመላው አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የጽዳት አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን አሰራጨ፡፡
ኤጀንሲው ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ለጽዳት አገልግሎት የሚውል አካፋ፣ ጋሪና የመሳሰሉ ግብዓቶች ርክክብ በተደረገበት ወቅት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ ባስተላለፉት መልዕክት የከተማችንን ጽዳት ለመጠበቅ ግብዓቶቹ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ በመሆኑ በተለይም አሁኑ ወቅቱ ክረምት እንደመሆኑ መጠን በ90 ቀን ዕቅድ በየብሎኩ ለምናካሄደው የፍሳሽ መውረጃ መስመሮች የማጽዳት ስራ መሰል ግብዓቶች እንዲቀርቡ ሲቀርብ ለነበረው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በየደረጃው ያለው መዋቅርም ከመንገድ መጥረጊያ ጀምሮ የከተማችን ጽዳት ለማስጠበቅ የሚረዱ ግብዓቶች በወቅቱ እንዲቀርቡ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ሁሉም ወገን በእኔነት ሊጠብቀው የሚገባው መሠረተ ልማት
ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት፣ አዲስ አበባን ደግሞ የኢትዮጵያ የልማት ማሳያ ለማድረግ የተያዘው ውጥን አንዱ መስታወት ነው - የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት።
ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ ደግሞ የአዲስ አበባን ውበት አጉልቶ ያወጣው ዘመናዊ የመንገድ መብራት ይገኝበታል።
ሆኖም በመንገድ መብራቱ ፖሎች ላይ በግድየለሽነት በሚፈፀሙ ግጭቶች እና በስርቆት ምክንያት ጉዳት እየደረሰ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ይናገራሉ።
በከተማዋ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ በዚህ የመንገድ መብራት ፖሎች ላይ በደረሰ ግጭት እና ስርቆት ምክንያት ከ16.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ጉዳት መድረሱን ኢንጂነር ወንድሙ በተለይ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ገልጸዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ሰዎች በቀን ብቻ ሳይሆን በማታም መሥራት እና የንግድ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችሉባት ንቁ ከተማን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን በማመን የከተማዋን የመንገድ ማብራት በተሻለ ሁኔታ እያስፋፋ ይገኛል።
በተለያየ ምክንያት የማይበሩ ከነበሩ 9 ሺህ 300 የመንገድ ማብራቶች መካከል 9 ሺህ 208 በመጠገን እና 909 አዳዲስ የመብራት ፖሎችን በመሥራት በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከ3 ሺህ 400 በላይ አዳዲስ የመብራት ፖሎችን በመገንባት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ኢንጂነር ወንድሙ ነግረውናል።
ይህም በከተማዋ ያለውን የመንገድ መብራት ፖሎችን ቁጥር ወደ 34 ሺህ 800 በማድረስ የመብራት ሽፋን በመጨመሩ ሰዎች ያለምንም ስጋት መንቀሳቀስ እንዲችሉ፣ የመንገድ ትራፊክ አደጋ እንዲቀንስ እና የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ በተሻለ ሁኔታ እንዲካሄድ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።
ከዚህ በፊት “ከመጨለሙ በፊት ወደ ቤት ካልገባሁ ወንጀል ይፈፀምብኛል፤ ጉዳት ይደርስብኛል” የሚል ስጋት የነበረው የከተማዋ ነዋሪ አሁን ግን አምሽቶ መሥራት እና መንቀሳቀስ እንዲችል ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።
ሰዎች ምሽት ታክሲ ከመጠበቅ በእግር እንዲሄዱ እና ጤናቸውን እንዲጠብቁ የራሱን አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑንም አክለዋል።
በከተማዋ በዋና ዋና የመንገዶች አካባቢ የንግድ ተቋማት እና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማ አስተዳድሩ ግዴታ እንዲሆን መወሰኑን የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፣ ይህ የተሳካ እንዲሆን የመንገድ መብራቶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው ብለዋል።
ይሁን እንጂ በከተማዋ በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የመንገድ መብራት መሠረት ልማቶች በግድየለሽ አሽከርካሪዎች በሚከሰት የመንገድ ትራፊክ አደጋ ፖሎች በግጭት እየወደቁ እና በስርቆት ምክንያት ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለአብነትም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ71 ፖሎች ላይ ጉዳት በመድረሱ 16.5 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ሀብት ላይ ውድመት ማስከተሉን ጠቁመዋል።
አብዛኛዎቹ ጉዳቶች በተሽከርካሪ የሚደርሱ ግጭጦች ቢሆንም የመብራት መሠረተ ልማት መቆጣጠሪያ ሳጥኖችን፣ ገመዶችን፣ ሽቦዎችን ቆርጠው እና ነቅሎ መውሰድ፤ በግንባታ ወቅት ለነባር መሠረተ ልማቶች አስፋላጊውን ጥንቃቄ አለማድረግ ሌሎች ተጠቃሽ መንሥኤዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለሕዝብ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ የተገነቡ የመንገድ ዳር መብራት መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ያደረሱ አካላት በሕጉ መሠረት ወጪውን እንዲከፍሉ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
እስካሁንም በመብራት ፖሎች ላይ ግጭት ያደረሱ አሽከርካሪዎች 4.8 ሚሊዮን ብር በኢንሹራንስ እንዲከፍሉ ተደርጓል ብለዋል።
በስርቆት የተዘረፉ ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት በፖሊስ ተይዞ በሕግ ተጠያቂነት ለማስፈን እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በመብራት መሠረት ልማቶች ላይ በግጭትም ሆነ በመስረቅ ያወደመ አካል የጠፋውን ንብረት መተካት ብቻ ሳይሆን በወንጀል ድርጊት ተጠያቂ ይሆናልም ብለዋል።
ነዋሪው ሁሉ በመሠረተ ልማቱ ላይ የሚደርስ ጉዳት በእኔ ሀብት ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው የሚል እምነት መፍጠር፣ የመከላከል፣ የመጠበቅ እና አደጋ በሚደርስት ወቅት ለሚመለከተው አካል መረጃ መስጠት ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል።
https://www.ebc.et/Home/NewsDetails...
በመዲናዋ በዚህ ዓመት በመንገድ መብራት ላይ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ውድመት ደርሷል
****************
ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት፣ አዲስ አበባን ደግሞ የኢትዮጵያ የልማት ማሳያ ለማድረግ የተያዘው ውጥን አንዱ መስታወት ነው - የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት።
ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ ደግሞ የአዲስ አበባን ውበት አጉልቶ ያወጣው ዘመናዊ የመንገድ መብራት ይገኝበታል።
ሆኖም በመንገድ መብራቱ ፖሎች ላይ በግድየለሽነት በሚፈፀሙ ግጭቶች እና በስርቆት ምክንያት ጉዳት እየደረሰ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ይናገራሉ።
በከተማዋ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ በዚህ የመንገድ መብራት ፖሎች ላይ በደረሰ ግጭት እና ስርቆት ምክንያት ከ16.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ጉዳት መድረሱን ኢንጂነር ወንድሙ በተለይ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ገልጸዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአስተያየት መስጫ ውስጥ ያለውን ሊንክ ይጫኑ
#EBC #ebcdotstream #AddisAbaba #Corridordevelopment
በፈተና በመፅናት፣በማያቋርጥ ትጋት ፣ ለማገልገል ሁሌም በታማኝነት፣በስኬት ላይ ስኬትን ለሰጠን ፈጣሪ አምላክ ምስጋና ይሁንለት!!…
See more
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባዉን አካሄዷል::
ካቢኔዉ በዛሬዉ ውሎዉ በቀረቡት 4 የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ የተለያዩ ዉሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
1ኛ ራስን ችሎ የሚለማ ቦታ ዝቅተኛው ስፋትና የፊት ለፊት ገፅታ ርዝመት ( set back) አተገባበር ጥናት ላይ ተወያይቶ የከተማዋን እድገት ታሳቢ ያደረገ እና የአተገባበር ምቹነት ታሳቢ ባደረገ የቀረበዉ ጥናት ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
2ኛ በኮሪደር ልማት የለሙ ልዩ ልዩ መሰረተ ልማቶች እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ለማቋቋም የቀረበዉ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ የማስተዳደር ፣ አገልግሎት የመስጠት፣የመጠበቅ ፣የማስተባበር እና የማቀናጀት ኃላፊነት እንዲኖረው ሆኖ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል፡፡
3ኛ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ አስተዳደር አግባብነት ያለዉ አካል ሳይፈቅድ ፤ የተያዙ ይዞታዎች አገልግሎት የመስጠት ጊዜን ለማራዘም በቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
4ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች እና የኢንዱስትሪ ልማት ተቋማት ላይ ለመሳተፍ የቀረበ የመሬት ጥያቄ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የተጠሪ ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጣቸዉን ለማዘመን እና ብሎም ለማሻሻል የተጠኑ ጥናቶች የሰነድ ርክክብ የተካሄደበት…
See more
በ2018 የበጀት አመት በመዲናችን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የመጡ ለውጦችን በማጠናከር ስማርት የመንግስት አገልግሎት የማስፋፋት ስራዎች በልዩ ትኩረት ተፈፃሚ እንደሚሆን በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የ2018 በጀት አመት የማዘጋጃ ቤታዊ ስትራቴጂክ የትኩረት መስኮችን አሰመልክተው ያዘጋጁትን ሰነድ ለተጠሪ ተቋማት፣ ከማእከል እስከ ወረዳ ላለው የዘርፉ መዋቅርና ለባለድርሻ አካላት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በፅዳት አስተዳደር ረገድ በመዲናችን የተመዘገቡ ውጤቶችን በይበልጥ የሚያጎለብት የአሰራር ስርአት የማሻሻልና በቅድመ አደጋ መከላከል ዝግጁነት በኩልም ትላልቅ የገበያ ማእከላት፣ ባለኮከብ ሆቴሎች፣ ትላልቅ የመኖሪያ አፓርታማዎች፣ እና ኢንዱስትሪዎችን የአደጋ ተጋላጭነት የመቀነስና አደጋን የመከላከል አቅም የመፈተሽ፣ የማስተካከልና የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬሽን እንዲያገኙ የማድረግ ስራ እና የግንባታ ቦታዎች ለአደጋ አጋላጭ የሆኑ ሁኔታዎችን የመለየትና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ ስራ ኮሚሽኑ በስፋት ትኩረት ሰጥቶ የሚያከናውነው ይሆናል።
አክለውም የመሠረተ ልማቶችን ከአደጋ፣ ከስርቆት እና ከብልሽት መከላከልና ህብረተሰቡን ባለቤት የማድረግ ስራ በስፋት እንደሚሰራ ገልፀው በሲቪልና ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ስራዎችም ረገድ በይበልጥ አገልግሎቱን የሚያሻሻል የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን እና የፋይዳ ምዝገባን የማጠናቀቅ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንደሚፈፀምም አስታውቀዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አያይዘውም በ2018 በጀት አመት ከተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር የብሎክ ስታንዳርዳይዜሽን እና ውበት፣ የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ፈጠራ ስራዎች በወጥነት የሚከናወኑ ስራዎች እንደሆኑም አስረድተዋል።
ከከተማችን ፅዳት ጋር በተያየዘም ባለፉት አመታት የመጡ ውጤቶችንና ለውጦችን የሚያጠናክሩ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አስተዳደር ስርአትን የሚያሻሽሉ ቆሻሻን የመለዬትና የመልሶ መጠቀም ስራዎች ማጠናከር፣ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርት አያያዝና አወጋገድ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።
በተጠናቀቀው 2017 በጀት አመት የተሳለጠና የተቀናጀ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ማሳካት እና የህብረተሰብ ተሳትፎ በማረጋገጥ ረገድ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ የተቻለበት እንደነበር ኢንጅነር ወንድሙ በዚሁ ወቅት አንስተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የ2017 በጀት አመት ዋና ዋና የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎች በምስል ሲቃኝ:-…
See more
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አሰኪያጅ ፅ/ቤት በሀምሌ ወር የተከናወኑ ተግባራትን የያዘ የሀምሌ ወር ዜና መፅሔት ለንባብ በቅቷል።
