fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አሰኪያጅ ፅ/ቤት በሀምሌ ወር የተከናወኑ ተግባራትን የያዘ የሀምሌ ወር ዜና መፅሔት ለንባብ በቅቷል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ከሽሮ ሜዳ እስከ ኪዳነ ምህረት ያለው የመንገድ ዳር መብራት የነዋሪዎችን የረጅም ጊዜ ቅሬታ የፈታ እና የመልካም አሰተዳድር ጥያቄዎችምን የመለሰ መሆኑን በም/ከ… See more

የህብረተሰቡን የመንገድ መብራት ጥያቄ ምላሽ መስጠት የሚችል አቅም መፈጠሩ ተገለጸ ከተቋቋመ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከመንገድ መብራት አቅርቦት ጋር ተያይዞ ያሉ የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በየደረጃው ምላሽ መስጠት የሚችል አቅም መፈጠሩን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ የተከበሩ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለፁ፡፡ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ከሽሮ ሜዳ - ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ድረስ ያለውን የመንገድ መብራት በመጠገን ለአገልገሎት ማብቃት መቻሉን በመስክ ላይ ወርደው ተመልክተዋል፡፡ የተከበሩ ኢንጂነር ወንድሙ በጉብኝቱ ማጠቃለያ እንደገለፁት የመንገድ መብራቱ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ባለመስጠቱ በህብረተሰቡ ዘንድ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ መቆየቱን ያስታወሱ ሲሆን ባለስልጣኑ የህብረተሰቡን ጥያቄ ምላሽ መስጠት የሚችል አቅም ፈጥሮ ባከናወነው የጥገና ስራ አካባቢውን በበቂ ብርሀን በመሸፈን ለምሽት ላለው እንቅስቃሴ ምቹና አስተማማኝ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ባለስልጣን መ/ቤቱ ወደ ስራ ሲገባ ከተረከባቸውና በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት የማይሰጡ ከነበሩት ውስጥ በ2017 በጀት ዓመት የዕቅዱን አብዛኛውን ጠግኖ ወደ አገልግሎት ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 15 የሚሆኑ የአዳዲስ የስማርት ፖል የኮንትራት አስተዳደር ስራዎችን መከወን መቻሉንም አስታውቀዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሰረተ-ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ግዛቸው አይካ እንዳሉት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በየደረጃው ባሉ የከተማ አስተዳደሩ መዋቅር ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ቋሚ ኮሚቴው ሰፊ ስራ መስራቱን አንስተዋል፡፡ በዚህ ሂደትም ህብረተሰቡ ምላሽ ካገኘባቸው ውስጥ የሽሮ ሜዳ -ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ድረስ ያለው የመንገድ መብራት ስራ አንዱ ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ግዛቸው አክለውም ባለስልጣኑ የህዝቡን ጥያቄ ምላሽ የመስጠት ስራውን በሌሎችም እያሰፋ መሄድ እንዳለበት አሳስበው፤ በቋሚ ኮሚቴው በኩል አስፈላጊውን የክትትልና ድጋፍ ስራ በማድረግ የህዝቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ኃላፊነት ማከናወኑ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የጥገና ስራውን አፈፃፀም አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን፤ ባለስልጣኑ ገና 9ኝ ወር እድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም በነዚህ ወራት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶችና መንገዱ ለምቶ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የማይሰጡትን በመለየት፤ ብሎም ቅድሚያ በመስጠት የህዝብ ጥያቄዎችን በተሟላ መልኩ መመለስ ተችሏል ብለዋል፡፡ አቶ ሰብስብ በዛሬው ዕለት ስራው የተጎበኘው ፕሮጀክት የጥገና ስራው በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ተከናውኖ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን አስታውሰው ሌሎች ያልተጠናቀቁ ስራዎችን ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሆን እንደሚያጠናቅቁ አስታውቀዋል፡፡ አያይዘውም የመብራት መሰረተ-ልማቱን ከህገወጥ ድርጊት፣ ጉዳትና ብልሽት በመጠበቅና በመከላከል የህብረተሰቡን ሰላማዊ የምሽት እንቅስቃሴ ከማረጋገጥ አኳያ ለታለመለት አላማ እንዲውል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የ90 ቀን የበጎ ፈቃድ ስራዎች የእቅድ አካል የሆነ የህፃናት ድጋፍ አድርጓል። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በተቋም ስር ለሚያሳድጋቸዉ ህፃናት የትህምርት ቁሳቁስና የአልባሳት ድጋፍ በትናንትናው እለት አድርጓል። ጽ/ቤቱ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በማስተባበር በቋሚነት ድጋፍ ለሚያደርግላቸዉ ህፃናት በ90 ቀን እቅዱ አካቶ ተጨማራ የሚያስፈልጋቸውን ግብአቶች በማሰባሰብ እንዲሁም ከተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በፈቃደኝነት ከደሞዛቸዉ ድጋፍ በማሰባሰብ ለህፃናቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ በወቅቱ ተመላክቷል። በመድረኩ በቢሮ ሀላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ እንደገለፁት በተቋም የ90 ቀን እቅድ ዉስጥ አንዱ ፅ/ቤቱ በቋሚነት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ህፃናትን በዚህ መልክ ድጋፍ ማድረጉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አበረታተዋል። እንደ ከተማ በወረደዉ እቅድና አቅጣጫ መሰረት በ90 ቀን ተግባራዊ እንዲሆኑ ከታቀዱ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል አንዱ በዚህ መልክ አቅም ላነሳቸው የህብረተሰብ ክፍል ድጋፍ ማድረግ አንዱና ዋነኛው መሆኑን አመልክተዋል። በዚህ መልካም ተግባር የተሳተፉ የፅ/ቤቱን አካላት በሙሉ አመስግነው በቀጣይም ይህን መሰል ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት እና በ5ቱም ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም በክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጆች መካከል የተካሄደው የ2018 የእቅድ ግብ ስምምነት ፊርማ በምስል ሲቃኝ:- ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት "ስማርት አዲስ አበባ ለላቀ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የ2017 ዓ.ም የሴክተር ማጠቃለያ ጉባኤ የእውቅናና ሽልማት መርሐግብር በምስል ሲቃኝ;- ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን እየመራበት ያለው መንገድ አብነታዊ ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን በበጀት አመት ባደረግነው የክትትልና ድጋፍ ግኑኝነት አግባብ ያረጋገጥነው ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አስታወቁ። የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው ዶ/ር ግዛቸው አይካ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት "ስማርት አዲስ አበባ ለላቀ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የ2017 በጀት አመት የሴክተር ማጠቃለያ ጉባኤ ላይ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ለመዲናችን አዲስ አበባ የስማርት ሲቲ ኢንሼቲብ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሆነገልፀዋል። አክለውም መዲናችንን ጽዱና ውብ በማድረግ፣ የዲጂታል አይደንቲቲ እና የቅድመ አደጋ መከላከል ስርአትን በማጠናከር እንዲሁም ከተማችንን ብርሃናማ በማድረግ ረገድ ፋና ወጊ ስራዎች መከናወናቸውንም ገልፀዋል። በዚሁ ጊዜም የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ መከላከል ሠራተኞች ከተማችን ከአደጋ ስጋት ለመጠበቅ የህይወት ዋጋ እየከፈሉ በመሆኑ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

በበጀት አመቱ ለመዲናችን ነዋሪዎች የሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ፍትሃዊ ተደራሽና የተጋልጋዩን እርካታ የጨመሩ መሆናቸውን በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አመለከቱ። የNBC Ethiopia ዝርዝር ዘገባ በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የ2017 በጀት ዓመት የሕዝባችንን አመኔታ ያተረፍንበት ነው” - ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ +++++++++++++++++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ | የ2017 በጀት ዓመት በከተማ ደረጃ የሕዝባችንን አመኔታ ያተረፍንበት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ። ለስማርት አዲስ አበባ የላቀ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት የተዘጋጀ የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የሴክተር ጉባኤ ተካሂዷል።… See more