cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Dr Zakir Naik

Dr. Zkir Naik ዶ/ር ዛኪር ናይክ አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ይህ ቻናል ዋነኛ አላማው የዶክተር ዛኪርን ስራዎች ለኡማው በማድረስ ኡማው በዲኑ ላይ ጥልቅ ግንዛቤና ይበልጥ ንቃት እንዲኖረው ማድረግ ነው። ኢንሻ አላህ ግቡን ይመታል። ያላቹን ማንኛውንም አይነት ሀሳብ አስተያየት በ @leasteyayetbot @leasteyayetbot @leasteyayetbot በኩል አድርሱን።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
1 984
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

نمایش همه...
5 ደቂቃ ወስዳችሁ እስከ መጨረሻው ተከታተሉት ! በተለይ ሙስሊም ላልሆናችሁ ወገኖቼ ልዩ ግብዣዬ ነው...

55K views, 4.3K likes, 380 loves, 231 comments, 2.6K shares, Facebook Watch Videos from Abdurahim ahmed page: 5 ደቂቃ ወስዳችሁ እስከ መጨረሻው ተከታተሉት ! በተለይ ሙስሊም ላልሆናችሁ ወገኖቼ ልዩ ግብዣዬ ነው የሚገርም አስተማሪ ታሪክ ነው !

"መስከረም" የሚለው ቃል "መዝከር" እና "ዓም" ከሚል ሁለት የግዕዝ ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "የዓመቱ መታሰቢያ" ማለት ነው። ይህ የአይሁዳውያን ሰባተኛ ወር "ኤታኒም" ተብሏል፦ 1 ነገሥት 8፥2 የእስራኤልም ሰዎች ኤታኒም በሚባል በሰባተኛው ወር በበዓሉ ጊዜ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ተከማቹ። וַיִּקָּ֨הֲל֜וּ אֶל־הַמֶּ֤לֶךְ שְׁלֹמֹה֙ כָּל־אִ֣ישׁ יִשְׂרָאֵ֔ל בְּיֶ֥רַח הָאֵֽתָנִ֖ים בֶּחָ֑ג ה֖וּא הַחֹ֥דֶשׁ הַשְּׁבִיעִֽי׃ "ኤታኒም" אֵיתָנִים ማለት "ጥንት" "መሠረት" ማለት ሲሆን ከአደም እስከ ሙሣ ድረስ ሲገለገሉበት የነበረ የወር መጀመሪያ እንደሆነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገፅ 248-249 ላይ ገልጸዋል። በፀሐይ አቆጣጠር የወሩ መጀመሪያ መስከረም ስለሆነ በጽባሓውያን ኦርቶዶክስ"Oriental Orthodox" ሆነ በመለካውያን ኦርቶዶክስ"Estern Orthodox" ዘንድ መስከረም የመጀመሪያው ወር ነው። መስከረምን የመጀመሪያ ወር አርጎ የሚቆጥር የዘመን አቆጣጠር የባዛንታይን የዘመን አቆጣጠር"Byzantine calendar" ይባላል፥ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ከ 691-1728 ድኅረ ልደት የባዛንታይን የዘመን አቆጣጠር ትጠቀም ነበር። ጥር ላይ የሚጀምረው የግርጎሮሳውያን የዘመን አቆጣጠር "ጃንዋሪይ" ግን ባለ ሁለት ፊት ያለው የበሮች እና የመጀመሪያዎች አምላክ ከሚባለው "ጃኑስ" ከተባለው ጣዖት የመጣ ሲሆን የሮማ ካቶሊክ ደግሞ ከጣዖታውያኑ ቀይጦ ያመጣው ሰርጎ ገብ ነው። ምን አለፋችሁ መስከረምን የመጀመሪያ ወር መሠረት ተደርጎ የጨረቃ አቆጣጠር ብታሰሉት የሙሥሊሞች የመጀመሪያ ወር ሙሐረምን ታገኛላችሁ። ባይብል ደግሞ የጨረቃ አቆጣጠርን ዕውቅና ይሰጣል፦ መዝሙረ ዳዊት 104፥19 ጨረቃን ለጊዜዎች አደረገ። መጽሐፈ ሲራክ 43÷6 ጨረቃም ለሁሉም የዘመን መለኪያ ናት። በሰማይ ጠፈር ላይ ያሉት ትልቁ ብርሃን ጸሐይ እና ትንሹ ብርሃን ጨረቃ ለምልክቶች፣ ለዘመኖች፣ ለዕለታት እና ለዓመታት ምልክት እንደሆኑ ዘፍጥረት ይናገራል፦ ዘፍጥረት 1፥14 እግዚአብሔርም አለ፦ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤ ዘፍጥረት 1፥16 እግዚአብሔርም ”ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን አደረገ። በፀሐይ አቆጣጠር አንድ ወር 30 ቀን ብቻ ሳይሆን 28 29 30 31 ይውላል፥ ይህ የፀሐይም የጨረቃም ልዩነት ነው። በፀሐይ አቆጣጠር፦ 1. ሰባት ወራት ጥር፣ መጋቢት፣ ግንቦት፣ ሐምሌ፣ ነሐሴ፣ ጥቅምት እና ታህሳስ 31 ቀናት የያዙ ናቸው። ብዜቱ 31×7= 217 ቀናት ይሆናሉ። 2. አራት ወራት ሚያዚያ፣ ሰኔ፣ መስከረም እና ህዳር 30 ቀናት የያዙ ናቸው። ብዜቱ 30×4= 120 ቀናት ይሆናሉ። 3. አንዱ ወር የካቲት 28 ቀናት የያዘ ነው። በጥቅሉ 217፥120+28= 365 ይሆናል። የኢትዮጵያ ልክ እንደ አይሁድ 1 ወር 30 ቀን ብቻ ነው። የማሶሬቲክ አይሁዳውያን 1 ወር 30 ቀን ይሆንና 12 ወር ብቻ ስለሆነ 360 ቀን ብቻ ነው። 354 ወይም 365 አይቀበሉም። የኢትዮጵያ ከፀሐዩ ጋር ለማመሳሰል 1 ወር 30 ቀን ብቻ ይጠቀሙና 360 ቀን ያመጡታል፥ 5 ቀኗን 13 ወር በማድረግ ከግሪክ ጳጉሜ ብለው ወስደዋል።13ኛ ወር የሚባለው ሰው ሠራሽ እንጂ መለኮታዊ ቅሪት የለውም፥ "ጳጉሜ" የሚለው ቃል "ኤፓጎሜኖን" ἐπᾰγομένων ከሚለው ከግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ “ተጨማሪ” ወይም “የተጨመረ” ማለት ነው። ጳጉሜ የወር ስም ሲሆን በነባሮች 12 ወራት ላይ ከፓጋን ግሪክ የተጨመረ 13ኛ ወር ነው፥ ይህ ሰርጎ ገብ እንጂ መልኮታዊ ቅሪት ያለው አይደለም። ሆነም ቀረ በፀሐይ አቆጣጠር መስከረም እና በጨረቃ አቆጣጠር ሙሐረም የወር መጀመሪያ እና የዓመት መለወጫ ነው፥ ቅሉ ግን መስከረም ሆነ ሙሐረምን ጠብቆ "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት እና በዓል አርጎ መያዝ መለኮታዊ ማስረጃ የሌለው ሰው ሠራሽ በዓል ነውና ጥንቃቄ እናድርግ! ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
نمایش همه...
መስከረም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥር እና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ "ተቅዊም" تَّقْوِيم ማለት "የዘመን አቆጣጠር" ማለት ሲሆን ተቅዊም በሁለት ዐበይት ክፍል ይከፈላል፥ አንደኛው "ተቅዊሙ አሽ-ሸምሢያህ" تَّقْوِيم الشَمْسِيَّة ሲሆን ተቅዊሙ አሽ-ሸምሢያህ 365 ቀናት የያዘ የፀሐይ አቆጣጠር”solar calender” ነው። ሁለተኛው ደግሞ "ተቅዊሙል ቀመርያህ" تَّقْوِيم القَمَرِيَّة ሲሆን ተቅዊሙል ቀመርያ 354 ቀናትን የያዘ የጨረቃ አቆጣጠር”lunar calender” ነው። አምላካችን አሏህ ፀሐይ እና ጨረቃ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ማወቂያ እና መስፈሪያዎችን እንዳደረገ ተናግሯል፦ 10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥር እና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ በጨረቃ አቆጣጠር አዲስ ጨረቃ ሲታይ አዲሱ ወር ሙሐረም የወሮች መባቻ(መጀመሪያ) ሆኖ ይጀምራል፥ "ሙሐረም" مُحَرَّم የሚለው ቃል "ሐረመ" حَرَّمَ ማለትም "ቀደሰ" "አከበረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የተቀደሰ" "የተከበረ" ማለት ነው። ሙሐረም ክብር ያለው የአሏህ ወር ነው፦ ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8 ሐዲስ 59 አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ብለዋል፡- ”ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአሏህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ أَفْضَلُ الصِّيَامِ بَعْدَ صِيَامِ شَهْرِ رَمَضَانَ شَهْرُ اللَّهِ الْمُحَرَّم ሙሐረም "የአሏህ ወር" የተባለበት አሏህ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አንድ ተብሎ ወር የተጀመረበት ወር ስለሆነ ነው። “ወር” የሚለው ቃል በነጠላ “ሸህር” شَهْر ሲሆን በነጠላ ቁጥር በቁርኣን 12 ውስጥ ጊዜ ተጠቅሷል፥ የሚያጅበው የወሮች ቁጥር አሏህ ዘንድ በአሏህ መጽሐፍ አሥራ ሁለት ወር ነው፦ 9፥36 የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ አሏህ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ሲሆን አሏህ ሰማያትን እና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጥሯል፦ 50፥38 ሰማያትን እና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ በግሪክ ኮይኔ "ሄክሳ" ἑξα ወይም "ሔክስ" ἕξ ማለት "ስድስት" ማለት ሲሆን "ሔሜራ" ἡμέρᾱ ወይም "ሄሜሮስ" ἥμερος ደግሞ "ቀን" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "አክሲማሮስ" ማለት "ስድስት ቀናት" ማለት ሲሆን አክሲማሮስ ስለ ስድስት ቀናት አፈጣጠር የሚያወራው ትምህርት ነው። በ4ኛው ክፍለ-ዘመን ከ 367-403 ድኅረ-ልደት የቆጵሮስ ኤጲጵ ቆጶስ የነበረው ኤጲፋንዮስ ያዘጋጀው መጽሐፍ እራሱ አክሲማሮስ ይባላል። ከ 180-222 ድኅረ-ልደት ድረስ ለ 42 ዓመት የአሌክሳንድርያ ፓትርያርክ የነበረው ድሜጥሮስ የቀመረው የዘመን ቀመር “አቡሻኽር” ወይም “ባሕረ-ሐሳብ” ሲባል በዚህ የዘመን ቀመር ላይ ስለ “አዕዋዳት” ይናገራል፥ “አዕዋድ” ማለት “ዖደ” ማለትም “ዞረ” ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን “ዙረት” ማለት ሲሆን በየጊዜው እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው። የፀሐይ አቆጣጠር የሚዞረው 365 ቀናት የያዘው ሲሆን የጨረቃ አቆጣጠር የሚዞረው ደግሞ 354 ቀናት የያዘው ነው፥ የጨረቃ አቆጣጠር 11 ቀናት በመዘግየት ከፀሐይ አቆጣጠር ሲዘገይ "ሙሐረም" ወደ ኃላ ሲሆን ከፊት ለፊቱ ያለው ስሌት "መስከረም" ይሆናል። በአይሁድ የመጀመሪያው ወር ኒሳን ማለትም አቢብ ወር ሲሆን ከዚያ ሰባተኛው ወር ቲሽሬ ነው፦ ዘጸአት 12፥2 ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። ከኒሳን ወር ሰባት ወር ስንቆጥር "ቲሽሬ" የሚባለው ወር መስከረም ነው፥ "ቲሽሬ" תִּשְׁרִי‎ ማለት "መጀመርያ" ማለት ነው። አይሁዳውያን ይህንን ወር "ሮሽ ሀ ሸናህ" רֹאשׁ הַשָּׁנָה ማለትም "የዓመቱ ርእስ፣ ጅማሮ፣ ራስ፣ አውራ" በማለት አዲስ ዓመት ይጀምራሉ። "ቲሽሬ" ወይም "ሮሽ ሀ ሸናህ" በፀሐይ አቆጣጠር "መስከረም" እና በጨረቃ አቆጣጠር "ሙሐረም" መሆኑን ፍንትው እና ቁልጭ አርጎ ያሳያል።
نمایش همه...
Watch "የጀሀነምን እና የጀነትን መኖር ከሳይንስ አንጻር እንዴት ማወቅ ይቻላል? / Dr zakir prove Hell and heaven in two ways" on YouTube https://youtu.be/p_4GdpFj9lY
نمایش همه...
የጀሀነምን እና የጀነትን መኖር ከሳይንስ አንጻር እንዴት ማወቅ ይቻላል? / Dr zakir prove Hell and heaven in two ways

#Terguwami_alimehdi_Tergum_filmoch_zakir_Naik_Kurulus_othman_Ertrg የጀሀነምን እና የጀነትን መኖር ከሳይንስ አንጻር እንዴት ማወቅ ይቻላል ትርጉም - አሊ መህዲ ቤተሰብ ይሁኑ -

https://t.me/alimehdiofficial

ንግድ ባንክ - 100015345058 ዝግጅት እና ትርጉም - አሊ መህዲ ቻናሉን -“ሰብስክራይብ” እና “ሼር” በማድረግ ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ ያድርጉ @

https://youtu.be/rUf9i79u7vI

አሰላሙ አልይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ በጣም በሳል የሆነ እምነቱን በእውቀት ላይ ተመስርቶ የሚረዳ ትውልድ ማነጽ የእያንዳንዱ ሙስሊም ግዴታ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እኛም ያለብንን ኃላፊነት ለመወጣትና በርካታ ሰዎች ጋር ለመድረስ የዶ/ር ዛኪርን የተመረጡ ጥያቄዎችንና የሠጣቸውን ምላሾች ሰብስበን በመጽሐፍ መልክ በማሳተም ለትውልዱ የማድረሱን ጠቀሜታ ተገንዝበናል፡፡ ይህንንም ለማድረግ ከወዲሁ ዝግጅት የጀመርን መሆናችንን ከትልቅ ደስታ ጋር ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የዚህን ድንቅ ምሁር ሥራዎች በተከታታይ ይዘን ለመቅረብም አቅደናል፡፡ ነገር ግን ይህ ያለ እናንተ ተሳትፎና ድጋፍ እንዲሁም ያለ አላህ ፍቃድ የመሆን እድሉ ጠባብ ነው፡፡ በመሆኑም የዚህ ታላቅ ዓላማ አካል በመሆን የራሳችሁን አስተዋጽዖ እንድታበረክቱ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በገንዘብ መደገፍ የምትችሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000153456058 አሊ መህዲ ሙሀመድ በሚል የሒሳብ ቁጥር ላይ የራሳችሁን አስተዋጽዖ አበርክቱ፡፡ በገንዘብ መደገፍ የማትችሉ ወዳጆች ደግሞ ይህ የደዓዋ ሥራ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ለጓደኞቻችሁ ፣ ለቤተሰቦቻችሁ እና ለዘመዶቻችሁ ሼር በማድረግ የዚህ መልካም ሥራ ተቋዳሽ ሁኑ፡፡ ከወደዳችሁትም ‹ላይክ› አድርጉት ፣ ሀሳብ አስተያየት ካላችሁም ‹ኮሜንት› ላይ ጻፉ ፣ ለቻናሉ አዲስ የሆናችሁ ቻናሉን ‹ሰብስክራይብ› በማድረግ ለቻናሉ እድገት የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታበረክቱ በአላህ ሥም እንጠይቃለን፡፡ ሁላችንንም አላህ ይርዳን አሜን አሊ መህዲ . #DrZakirNaik #Terrorism #Atheist #Islamophobia #Music #Dance #Quran #Mistakes #SheikhAhmedDeedat #Jesus #Crucifixion #Hell #Catholic #Zakir #Naik #Drzakirnaik #Fariq #Naik #FariqNaik #FariqZakirNaik #Dr #Drzakirchannel #Allah #Allaah #God #Muslim #Islam #Islaam #Comparative #Religion #ComparativeReligion #Atheism #Atheist #Christianity #Christian #Hinduism #Hindu #Buddhism #Buddhist #Judaism #Jew #Sikhism #Sikh #Jainism #Jain #Lecture #Question #Answer #QuestionsandAnswer #Logic #Reason #Science #Misconception #Misunderstanding #PeaceTV #Dawah #Muhammad #Mohammed #Hadeeth #Hadith #Saheeh #Sahih #Man #Woman #Human #Humanity #Problem #Solution #Rights #Media #War #Peace #Similarities #Debate #Lecture #Quran #Quraan #AlQuran #AlQuraan #Bible #Veda #Gita #Geeta #Baghwat #Upanishad #Purana #Terrorism #Terrorist #Universal #Brotherhood #Word #Purpose #Life #Jihad #Jihaad #Jesus #Christ #Jesuschrist #Church #Mosque #Masjid #Perspective #Ask #AskDrZakir #Seeking #Knowledge #Education #NonMuslim #Fundamentalist #Fundamentalism #Symposium #Dialogue #Salaah #Salah #Shariah #Scripture #Ahmed #Deedat #AhmedDeedat #Daee #Missionary #Concept #West #Family #Global #Ramadhaan #Ramadan #Tauheed #Tawheed #Monotheism #Zakaat #Zakat #Zakah #Hajj #Saum #Fasting #Makkah #Mecca #Madinah #India #Malaysia #Ummah #Unity #Importance #Date #Isamophobia #Understand #Deen #Fardh #Fard #Haraam #Haram #Sunnah #Mustahab #Waajib #Wajib #Compulsory #Prohibited #Encouraged #Permissible #Permitted #Prohibited #Sin #Sinful #Heaven #Hell #Hellfire #Jannah #Jahannum #Paradise Disclaimer Note: we are not the owner of any of the visual shown in this video. We give credit to the respective owners and original producers. Copyright Disclaimer- This video is for educational purpose only. Copyright Disclaimer under Section 107 of the copyright act 1976, allowance is made for fair use for purposes such as criticism, comment, news reporting, scholarship, and research. Fair use is a use permitted by copyright statute that might otherwise be infringing. Non-profit, educational or personal use tips the balance in favor of fair use.

15:22
Video unavailableShow in Telegram
Amazing Answer
نمایش همه...
ዶር_ዛኪር_እና_ግራ_የተጋባው_አሜሪካዊ_Dr_zakir_&_American_Atheist_.mp439.40 MB
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ተክቢር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ወደ ሐሠተኛው ነቢይ ወደ ኢዩ ጩፋ ጋር በመሄድ ከፍሬአለው በማለት ምስክርነት ሰጥቶ የነበረው ሙሰማ ሸዋ በዛ በተከታታይ ሲደረግለት በነበረው ደዕዋህ ወደ አሏህ በተውበት ተመልሷል። በዱዓችሁ አስቡት! ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ! ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
نمایش همه...
ስለዚህ የማይመለከተን ነገር ውስጥ ለመመሳሰል ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያን ማጽዳት፣ የመስቀል ደመራ ቦታ ማጽዳት፣ የጥምቀት ቦታ ማጽዳት፥ ታቦት መሸኘት፣ በዓላቸውን ማክበር፣ መዝሙራቸውን መዘመር ከኢሥላም አጥር ያስወጣል። አንዳንድ ቂሎች፦ “ለመረዳዳት ነው” ይሉናል። በጋራ እሴት ማለትም በልማት፣ በጉርብትና፣ በአስኳላ ትምህርት፣ በሰብአዊነት ወዘተ… ልንረዳዳ እንችላለን፥ ነገር ግን በእምነት ጉዳይ እረዳቶች አድርገን ከያዝናቸው ከእነርሱ እንደ አንዱ ነን፦ 4፥144 *”እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ*፤ ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን? يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَجْعَلُوا لِلَّهِ عَلَيْكُمْ سُلْطَانًا مُّبِينًا 5፥51 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከእነርሱ ነው*፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْيَهُودَ وَالنَّصَارَىٰ أَوْلِيَاءَ ۘ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 2939 ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የሙሽሪክ እርዳታ አያስፈልገንም”* عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّا لاَ نَسْتَعِينُ بِمُشْرِكٍ ‏ ምን ይሁን ብለን ነው ለመስቀል በዓል የምናጸዳው? መስቀል እኮ ስግደት እና ምስጋና ይቀበላል። መስቀል በሃውልት ድንጋይ፣ እንጨት፣ ወርቅ፣ ብር፣ ብረት፣ ነሐስ ወዘተ ነው። ይህ ግዑዝ ነገር ይሰገድለታል፥ ምስጋና ይቀርበለታል፤ ይህ በተግባር ሲሆን በጽሑፍ ደግሞ የዘወትር ፀሎት ላይ እንዲህ ይነበባል፦ ግዕዙ፦ “እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር” ትርጉም፦ “ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው” ግዕዙ፦ “ስብሐት “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በምህረቱ ይዘከረነ” ትርጉም፦ ” “ለ”ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይገባዋል” እንግዲህ ሄደክ ስታጸዳ እንዲያሻርኩ እያመቻቸክላቸው እንደሆነ አትርሳ። ይህንን ድርጊት መተባበር ሺርክ እይደለምን? መከባበር በዚህ ነው እንዴ? ሰዎቹን በሰውነታቸው እናከብራቸዋል እንጂ ለአምልኮታቸው ዕውቅና ሰጥቶ እሹሩሩ ማለት ምን የሚሉት ማሽቃበጥ ነው? መንግሥት ይሉንታ በማስያዝ በሃይማኖት ጣልቃ አይግባብን። ሙሥሊሙ የራሱ ለማጽዳት የሌላ እገዛ አይሻም። መሣጂዶችን እንዲያጸዱልን አንፈልግም። እኛም የእነርሱን ማጽዳት የለብንም፥ የራሳቸውን እራሳቸው ያጽዱ። ኡስታዞች፣ ዐሊሞች፣ መሻይኮች ምነው ዝምታውን መረጡዛ? በዝምታው ምእመኑን በእምነቱ እንዲሸማቀቅ እና እዲሳቀቅ እያረጋችሁት ነው። አብሮነት፣ መከባበር፣ የአገር ልማትና ግንባታ በዚህ አይለካም። አብሮነት፣ መከባበር፣ የአገር ልማትና ግንባታ እናመጣለን በሚል ሽፋን ኡማውን የዝቅተኝነት ስሜት በማከናነብ ከድጡ ወደ ማጡ አትክተቱት። ኢትዮጵያዊነት በመሆን እንጂ በመምሰል አይለካም። ምንም ሳይገባውና ሳያውቀው የሚሳተፈውን ሙሥሊም በትህትና የማስጠንቀቅ የሁላችንም ሃላፍትና ነው። ይህንን መልእክት ለሁሉም በማስተላለፍ ዲናዊ ግዴታዎን ይወጡ! አላህ ለሁላችንም ሂዳያ ይስጠን! አሚን። ✍ከወንድም ወሒድ ዑመር @Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
نمایش همه...
ፖስተር ቄስ ግርማ ዘውዴ 🙏 እውነታውን አፈረጡት https://youtu.be/CRKeUTFUdGg ሂጃብ በደርዘን እያሰፉ 1ሺ ብር እየከፈሉ ነው አሰልጥነው ወደ ጌታ መጣን ሚያስብሏቸው ። እንዲህ እውነታው በራሳቸው ወገን ሲገለጥ ደስ ይላል ቄስ በላይ እውነታውን ስላጋለጡ እናመሰግናለን https://youtu.be/CRKeUTFUdGg
نمایش همه...
ቄስ ግርማ ዘውዴ እውነታውን አፈረጡት ፖስተሮች ሂጃብ እያሰፉ የሚያሰሩት ድራማ

አህዛብ ማን ነው? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። አንዱ ክርስቲያን በውይይት ላይ ሲናደድ አህዛብ ብሎ ተናገረኝ፤ እኔም አህዛብ ምን ማለትና ምን እንደሆነ ብታውቅ ኖሮ ይቺን ቃል አትደፍራትም ነበር ብዬ ምላሽ ሰጠሁት፤ "አህዛብ" ተብሎ በግሪክ ብሉይ ሰፕቱአጀን እና በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ ላይ "ኤትኖስ" ἔθνος የሚለው የግሪኩ ቃል "ኤትኒኮስ" ἐθνικός ከሚለው ገላጭ የመጣ ሲሆን በዕብራይስጡ ደሃራይ እደ-ክታባት ላይ ደግሞ "ጎይ" גוי ተብሎ ተቀምጧል፤ ይህ ቃል እንደየ አውዱ ለተለያየ ትርጉም አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን "ህዝብ" "ብሔር" "አረማዊ" "ይሁዲ ያልሆነ" የሚል ፍቺ እንዳለው የግሪክና የዕብራይስጥ ሙዳየ-ቃላት ያትታሉ፤ ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እዚህ አርስት ላይ "አህዛብ" ብለን የምንመለከተው "አረማዊ"pagan" የሚለው እሳቤ ነው፤ ሰዎች ይህ ስም የአብርሃምን አምላክ ለሚያመልኩ ለሙስሊሞች እንደ ቅፅል ስም ሲጠቀሙ እጅግ ስላስደመመኝ ይህ ስም ማንን እንደሚመለከትና ማንን አህዛብ እንደሚል ለመፅሐፍ ቅዱስ ቦታውን እንልቀቅ፦ ነጥብ አንድ "ርኵሰት" በመፅሐፍ ቅዱስ "የአሕዛብን ርኵሰት" ተብሎ የተቀመጠው ምዋርት፥ ሞራ ገላጭ፥ አስማት፥ መተተት፥ ድግምት፣ ጥንቆላ፥ መናፍስትንም መጥራት፥ ሙታን መሳብ ነው፦ ዘዳግም 18፥9-11 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ ""አሕዛብ"" የሚያደርጉትን "ርኵሰት" ታደርግ ዘንድ አትማር። ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ታዲያ ይህ በኢስላም ትልቁ ሽርክ ነው፤ ከኢስላም አጥርስ የሚያስወጣ አይደለምን? ይህንን ድርጊትስ ማን ነው በዘመናዊ መልክ የሚያደርገው ሙስሊሙ ወይስ ስም ለጣፊው? ነጥብ ሁለት "ግብረ-ሰዶም" አላህ የፈጠረው ተቃራኒ ፃታ"hetro-sexual" እያለ ዛሬ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሆነው ግብረ-ሰዶም"homo-sexual" ማድረግ የአሕዛብን ርኵሰት ነው፦ 1ኛ ነገሥት 14፥24 በምድርም ውስጥ "ሰዶማውያን" ነበሩ፤ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸውን ""የአሕዛብን ርኵሰት" ሁሉ ያደርጉ ነበር። ታዲያ ይህ በኢስላም አይደለም መጋባት ይቅርና ድርጊቱ ሃራም ነው፤ ማን ነው ታዲያ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት የሚያጋባው ቤተክርስቲያን ወይስ መስኪድ? ህሊና ይፍረደዋ። ነጥብ ሶስት "የተቀረፀ ምስል" ነቢያት "የአሕዛብ ልማድ" ብለው ያስቀመጡት ከእንጨት፣ ከብረት፣ ከብር እና ከወርቅ የተሰሩትን የተቀረፁ ምስሎች ነው፤ እነዚህ ምስሎች አፍ አላቸው አይናገሩም፤ ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፤ እጅ አላቸው አይዳስሱም፤ እግር አላቸው አይሄዱም፤ ክፉ መሥራትም አይቻላቸውም ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉም፣ አህዛብ ግን ወደ እነርሱ ይፀልያሉ፣ ይለማመናሉ፣ እጣን ያጨሳሉ፣ ይጎባደዳሉ፣ ያሸረግዳሉ፣ ይሰግዳሉ፣ -ያመልካሉ፦ 2ኛ ነገሥት17፥41 እነዚህም "አሕዛብ" እግዚአብሔርን ይፈሩ ነበር፤ ደግሞም "የተቀረጹ ምስሎቻቸውን" ያመልኩ ነበር፤ 2ኛ ዜና 16፥26 "የአሕዛብ አማልክት" ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። መዝሙር 115፥4-7 የአሕዛብ ጣዖታቶች "የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ" ናቸው፤ አፍ አላቸው አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው አያዩምም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፤ አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤ በጕሮሮአቸውም አይናገሩም። ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ "ከአሕዛብ" ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ "የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት" የሚሸከሙና ያድን ዘንድ "ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ" እውቀት የላቸውም። ኤርምያስ 10፥2-5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና። "የአሕዛብ ልማድ" ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል። እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውማን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው። ማን ነው የተቀረፀ ምስል አድርጎ ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት እና ለሶስቱ አካላት የአምልኮ ስግደት የሚሰግደው? በስዕልና በሃውልት ፊት የሚለማመን፣ የሚያመልክ፣ እጣን የሚያጨስ፣ ስለት የሚሳል? ሙስሊሙ ወይስ እውነተኛው አህዛብ? ኅሊና እያለ ምን ይኮናል። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
نمایش همه...
ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ-አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!