cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የፈትዋ ጉሩፕ በመንሀጅ አሰለፍያ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 813
مشترکین
-324 ساعت
-57 روز
-4130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የቢድዓ ባለቤቶችን ስራ እየሰራ የፈለገውን ጥፋትና ዝንባሌ ካሰራጨ በኋላ ቁርአንና ሀዲስን ነው የምከተለው ብሎ ግግም ካለ . . . በዚህ ዙሪያ የሚናገሩ የደጋግ ቀደምቶችን ንግግሮቻቸውን ለታፔላነት ከተገለገለባቸው ታዝቦ ዝም ከማለት ውጭ ምን ይባላል!? በዚህ ከቀጠለ አህባሹም ከነኩፍሩ ቁርአንና ሀዲስን በሰለፎች አረዳድ በሚል ታፔላ አጉልቶ መነገዱ አይቀርም። ጉዳይ ግምት ውስጥ የሚገባው በተጨባጭ እንጅ በሙግት አይደለም!
نمایش همه...
ባል ሚስቱን አይሰለችም ለምን? አላህ በባል እና በሚስት መካከላ የፈጠረው ተአምር ነው ከአንድ አንጀት የወጣ ነው። ትዳር የሴት ልጅ ክብር  ነው። ባል ሚስቱን አይሰለችም ለእሷ ብቻ የተፈጠረ፤ ሌላ አላማ የሌለው እስከሚመስለው የሚጨነቅ ብዙ ወንድ አለ። እሷም አታውቀው እሱም አያቃት በአንድ ቤት ተገናኝተው በዛው መላመድ ማለት  የአላህ ታአምር ነው። ጥሩ ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት ይባላል☂ https://t.me/UmuAmar_UmuManas
نمایش همه...
كوني قوية🍃🌸🍃

የሰለፊየ እንስቶች ቻነል!!

👍 2
የሂጅራ አቆጣጠር!! 〰 ያነ የስደት ወቅት ከመካ መድና ነብዩ ሙሐመድ የኛ ሀቢቡና ፊት የነበረውን ሊያድሱ እንደገና ብዙ ጉድ ገብቶበት ተበርዟልና እንደቀድሞ እንዲሆን ታላቁ እስልምና መልእክት ሲመጣቸው ከአላህ ረበና ተነሱ ሊያደርሱ ያን ትልቅ አማና በአለም እንዲስፋፋ የተውሒድ ጎዳና!! የሰው ልጅ በምድር የመምጣቱ አላማ አንድ አምላክን ሊያመልክ መሆኑን እንዲሰማ ዘለአለም እንዲድን ወጥቶ ከጨለማ በእምነት አሸብርቃ ምድር እንዲትለማ በጣም ታገሉለት ለተውሒዱ ካስማ እስከ ጥግ ሠሩ አርገው እንዲደማ የታደለ እሺ አለ ያሾፈም አሾፈ ብዙ አይነት ስቆቃ አማኝ ላይ አረፈ ብዙ ተገደለ ብዙ ተገረፈ!! በተለይ የእነኝህ አይወራ ይቅር የያሲር ቤተሰቦች ሱመያና አማር ሌሎችም ልእልቶች ፋጡማና ዘኒር ቢላሉል ሀበሽይ ጀግና የጥቁር ዘር ጅሀድ አልታዘዙ አልገጠሙ በጦር ጥቂትም ነበሩ ትንሾች በቁጥር ያሳለፉት ስቃይ ደም ያስለቅስ ነበር!! ያን ሁሉ መከራ ችለው እያለፉ ይቅርታ እያረጉ ቢበረታም ግፉ ውስን አመታትን ችለው እንደገፉ በስደት ታዘዙ ወደ የስሪብ ሀገር መድና እንዲጎርፉ!! ወጥተው ሲሰደዱ አማኝ በአጠቃላይ አሁንም በረታ ግፉ ሚስኪኖች ላይ አብረው እንዳይሆኑ ከሂጅራው ተካፋይ ሰለማ ኢብኑ ሂሻም ወሊድና ዓያሽ ብዙ ተሰቃዩ በኩፋሩል ቁረይሽ ስደቱ ቀጥሏል መድና ተመሙ በፊት የወጡ አሉ ቀድመው የተመሙ የአለሙ መብራት ነብዩ ሊያዘግሙ ሊወጡ መሆኑ ቁረሾች ሲሰሙ በመኝታቸው ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ ሴራ ጠነሰሱ በሂስድ ምቀኝነት በጣሙን ታመሙ ጅብሪልን ላከና አላህ ሲነግራቸው ሴራ ጠንስሰዋል አትተኛ አላቸው ሲመጡ ጊዜና አንድ ጊዜ ከበው ለአንድየ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሽተው ሊያጠፏቸው ተአምር ሠሩና የዛን ጊዜ እሳቸው ዓልይን ተክተው እሱን አስተኝተው በላያቸው ላይ አፈር እየረጩ ወጡ በጎናቸው ከአቡበክር ጋራ “ጋሩ ሰውር” አመሩ—አቤት—ሲያምርባቸው ቁረይሾቹ መጥተው ዙሪያ ቢከቧቸው ታላቅ ሀያሉ አምላክ አላህ ጠባቂያቸው በማይታይ ዘማች ጥበቃ አርጎላቸው ከዋሻው ቆይተው ምንም ሳይነካቸው ጉዞ ወደ የስሪብ ቀጠለ እርምጃቸው ቁረይሾች በገኑ ቁጭት ጠናባቸው ሊከፍሉ ወሰኑ ለደረሰባቸው እነሱን ላመጣ መቶ ግመል አለው ብለው አሳወጁ በየ ጉባኤአቸው "ሱራቃ” ሞከረ ጋለበ ለብቻው ሲቀርብ ጊዜና ደርሶ ከኋላቸው ዱዓ አደረጉበት መሬትም ዋጠችው ይቅርታ ጠይቆ ተመለሰ በዛው!! ብዙም ዝርዝር ያለው አስገራሚም ታምር የሆነ ሆነና አልፎ ያ-ሁሉ አሳር ሀ"ብለው ጀመሩ መድና በመስፈር ከዛ ተይዞ ነው የሂጅራ አቆጣጠር!! ✍ አብዱረህማን ዑመር http://t.me/Abdurhman_oumer
نمایش همه...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ « ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡ » [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

👍 1
የጁሙዓ ኹጥባ (ምክር) ➴➴➴➴➴ ========= 🖇 ርዕስ፦«ትክክለኛው/እውነተኛው ስኬት»በሚል ርዕስ ⤵️العنوان: "الفوز الحقيقية". ➴➴➴➴➴ ======== ከተዳሰሱ ነጥቦች መካከል:- 👉 ትክክለኛ/እውነተኛ የሆነው ስኬታማነት፣ 👉 ስኬታማ ባለቤቶች እነማን እንደሆኑ፣ 👉ትልቁ ስኬታማነት ምን እንደሆነ፣ 👉 በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ የሆነው ምንድነው ትክክለኛ/እውነተኛው ስኬታማነት መተዋወስ አስፈላጊ ስለመሆኑ፣ 👉ለቀጣዩ ህይወታችን ለአኼራችን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ፣ 👉ሁላችንም እንደምንሞት እያወቅን ለዚህ ለምንሞትለት ዝግጅት አለማድረጋችን፣ መዘጋጀት አለብን፣ 👉 ትክክለኛው ስኬት ምን እንደሆነ፣ 👉 የስኬት ባለቤቶች መገለጫዎች/ባህሪያት ምን እንደሆነ፣ 👉እነዚህ የትከክክለኛ ስኬት ባለቤቶች ደመወዝ/ምንዳ ምን እንደሆነ፣ 👉 የዱኒያ ጥፍ ጥና ሳያታልልህ ትክክለኛ/እውነተኛ ከሆነውን ስኬት እንዳያታልልህ መዘጋጀት፣ 👉 ለትክክለኛው ስኬት/ለጀነት መዘጋጀት እንዳለብን፣ 👉ዘላለማዊ የሆነውን ፀጋ ለማግኘት መዘጋጀትእንዳለብን፣ 👉ይህንን ፈውዝ/ስኬት ለማገኘት በዱዓዕ፣ከሽርክና ከሙሽሪክ፣ከቢዲዓናከሙብተዲዕ መራቅ እንደሚኖርብን፣ ➴➴➴➴➴ ============== 🎙በኡስታዝ ሰዓድ ዓብዱለጢፍ ሀፊዘሁሏህ 🎙لآستاذ سعد بن عبد الطيف -حفظه الله- ➴➴➴➴➴ ይ ደ መ ጥ =============== 🗓ሰኔ‐ 07‐ 10 - 2016E.C 🕌ባህር ዳር ከተማ 🕌 بمدينة بحردار [إثيوبيا]؛ في مسجد البخاري #size መጠን 30.28 MB #length 30:24 min ➴➴➴➴➴ ========= 🕌መስጂደል ቡኻሪ 🌎ባህር ዳር፣ ኢትዮጲያ ➴➴➴➴➴ ======== የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصير
نمایش همه...
AudioCutter_ኡስታዝ_ሰዓድ_አብዱል_ለጠፍ_ጁሙዓ_ኹጥባ_21‐cutted.m4a28.88 MB
👍 1
01:47
Video unavailable
https://t.me/+IoVJ6kUVmLowYzQ0 ይህንን ቻነል ሼር ጆይን አድርጉት
نمایش همه...
5.16 MB
Photo unavailable
🔵ጣፋጩ ገዳይ መርዝ! ✅️በሰሜን አንታርቲካ ላይ የሚኖሩ እስኪሞ የተባሉ ጎሳዎች ተኩላ ለመግደል ሲፈልጉ የሚዘይዱት ዘዴ አለ፡፡ በበረዶ ውስጥ ጫፉ በጥቂቱ የወጣ ቢላ ይደብቃሉ፤ በላዩ ላይ ጥቂት የበግ ደምን ያደርጉበታል:: ተኩላው ደሙን አሽትቶ ይመጣል፡፡ በረዶው ላይ ያለውን ደም መላስ ይጀምራል።   ደሙ ይጣፍጠዋልና ፍጥነቱን እየጨመረ መላስ ይጀምራል፡፡ በዚህ ፍጥነት ውስጥም  እያለ ሳያስበው ደም የተቀባው ቢላዋ ምላሱን ይቆርጠዋል፡፡ ነገር ግን ደም መላሱን አያቆምም፡፡ አሁን ላይ ይህ ተኩላ ባለማወቅ ከራሱ ምላስ የሚፈሰውን ደም እየላሰ ነው፣ ሆኖም ጣፍጦታል እና በፍጥነት መላሱን ይቀጥላል። ከመጠን በላይ ደምም ይፈሰዋልና በነጋታው ተኩላው ሞቶ ይገኛል። የራሱን ደም እየጠጣ እንደነበረም አልታወቀውም። ይህ ተኩላ ከእኛ ታሪክ ጋር ይቆራኛል፡፡ ብዙዎቻችን ጊዜያችንን የምናሳልፈው ወሬ፣ስልክ የመሳሰሉ ምንም በማይጠቅመን   ነገር ላይ ነው። ይባስ ሲል አሏህን በማመፅ ላይ ላይ ነው ወቅታችን የሚያልፈው።... ጊዜያችንን ሳንጠቀምበት እንዲሁ ያልቃል... ይጣፍጣልና፤ ጥቂት ብቻ አይበቃንም፤ በፍጥነት እና በኃይልም ህይወታችንን፣ ጊዜያችንን ልሰን እየጨረስነው ነው። በፍጥነት በላስን ቁጥር በፍጥነት ወደ አዘቅት  እንየወረደን መሆኑን አውቀን ከወንጀልና ከመዕሲያ ልንርቅ የግድ ነው።   አስታዋይ ሰው ለደቂቃ ደስታ ብሎ የዘለዓለም ሕይወቱን አያበላሽም!!    #ወንጀል_ሐጢዓት_ጣፋጭ_ገዳይ_መርዝ!! https://t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
نمایش همه...
👍 4
ረድ (ምላሽ መስጠት) ምንድን ነው ጥቅሙ???? 〰〰 ولتكن منكم أمة يدعون إلى الخير ويأمرون بالمعروف وينهون عن المنكر وأولئك هم المفلحون « ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡» [ ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 104 ] በሌላ አንቀጽ ላይ  لعن الذين كفروا من بني إسرائيل على لسان داوود وعيسى ابن مريم ذلك بما عصوا وكانوا يعتدون كانوا لا يتناهون عن منكر فعلوه لبئس ما كانوا يفعلون  « ከእስራኤል ልጆች እነዚያ የካዱት በዳውድና በመርየም ልጅ በዒሳ ምላስ ተረገሙ፡፡ ይህ  ትእዛዝን በመጣሳቸውና ወሰንን የሚያልፉ በመኾናቸው እንድሁም  (አንዱ አንዱን) ከሠሩት መጥፎ ነገር አይከላከሉምና ነበር፡፡ ይሠሩት የነበሩት ነገር በእርግጥ ከፋ! » (ሱረቱ አል-ማኢዳህ: 78 - 79) عن أَبي سعيدٍ الخُدْريِّ رضي اللَّه عنه قال : سمِعْتُ رسُولَ اللَّه صَلّى اللهُ عَلَيْهِ وسَلَّم يقُولُ : « مَنْ رَأَى مِنْكُم مُنْكراً فَلْيغيِّرْهُ بِيَدهِ ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطعْ  فبِلِسَانِهِ ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبقَلبهِ وَذَلَكَ أَضْعَفُ الإِيمانِ » رواه مسلم .  የአላህ መልእክተኛ  ﷺ  የሚከተለውን ብለዋል፦ {{መጥፎ ሲሰራ ያየ በእጁ ያስቁመው ያልቻለ በምላሱ (ይናገር) ያልቻለ በልቡ ይጥላ (ከቦታው ተነስቶ ይሂድ) በልብ መጥላት የእምነት ደካማው ነው}}  (ሙስሊም ዘግቦታል) እንዲሁ ከጥቅሞቹ ውስጥ . . .   ➖ለተናጋሪው ከጅሀድ የበለጠ ነው! የመናገር ሱስም ሆነ፤ ሰዎችን ዝቅ የማድረግ የመበቀል የቂመኝነት፤ የእልኸኝነት፤ የህሜት ሱስ ሳይኖርበት በጥሩ ንያ የአላህን ዲን ለመጠበቅ ብሎ ከሙኻሊፎች የሚያስጠነቅቅና ሱናን የሚጠብቅ ሙጃሂድ ነው። ከዛም እንደሚበልጥ ደጋግ ቀደምቶች እንደት እንደሚያስቀምጡት የሚከተሉትን ንግግሮቻቸውን በአንድነት እንመልከት! قال يحيى بن يحيى شيخ الإمام البخاري ومسلم الذب عن السنة أفضل من الجهاد نقض المنطق  ص:12) የቡኻሪና የሙስሊም ሸይኽ የሆኑት የህያ ኢብኑ የህያ እንዲህ ይላሉ፦ "ከሱና መከላከል፣ ከጅሃድ  ይበልጣል።" قال ابن تيمية – رحمه الله تعالى "فالراد على أهل البدع مجاهد   الفتاوى  ( 4/13 )     ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላሁ እንዲህ ይላል፦ "በቢድዓ ባለ-ቤቶች ላይ ረድ የሚያደርግ (ምላሽ የሚሰጥ)፣ ሙጃሂድ ነው። (አልፈታዋ ( 4/13 ) ) قال ابن القيم والجهاد بالحجة واللسان مقدم على الجهاد بالسيف والسنان مقدمة منظومته الكافية الشافية ص/ 19 ኢማም ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ፦ በማስረጃና በአንደበት የሚደረግ ጅሃድ፣ በሰይፍና በጦር ከሚደረግ ጅሃድ ይቀድማል። (አልካፊየቱ አሻፊያህ: 19) ይሄውላችሁ እንግዲህ ጅሃድ ማለት አንድ ሰው ደይን (የሰዎች እዳ) ብቻ ከሌለበትና በአላህ ላይ ትክክለኛ ጥሩ እምነት (ተውሒድ) ኖሮት በጅሀድ ከሞተ ሌሎችን ማንኛውንም ወንጀሎች የሚያሰርዝ ጀነት የሚያኖር ነገር ነው። ከመሆኑም ጋር በኢኽላስ የሚደረግ ረድ ከጅሀድ ይበልጣል። ➖ለሰሚው ህዝብ፤ በሽተኛውን ከደህናው የሚለይበት ነው! ህዝብ ያም ሲናገር እውነት ይመስለዋል፤ ያም ሲናገር እውነት ይመስለዋል። ጥፋት የሚያሰራጨው ስም ተጠቅሶ በበቂ መረጃ እገሌ ተሳስቷል እንደሁኔታውም ተጠንቀቁት ሲባል፤ ያኔ በሽተኛውን ከደህነኛው መለየት ይችላል። قيل لأحمد بن حنبل: الرجل يصوم ويصلي ويعتكف، أحبّ إليك أو يتكلم في أهل البدع؟ فقال: إذا قام وصلى واعتكف فإنما هو لنفسه، وإذا تكلم في أهل البدع فإنما هو للمسلمين؛ هذا أفضل»  زكره ابن تيمية -رحمه الله في مجموع الفتاوى، ص 231/28. {{ ከፊሎች ለኢማም አህመድ ቢን ሀንበል እገሌ እንዲህ ነው እገሌ ደግሞ እንዲህ ነው እገሌም እንዲህ ነው ብየ (ሥለ ሰው ለመናገር) ይከብደኛል አሏቸው እርሳቸውም፡- አንተ ዝም ካልክ እኔም ዝም ካልኩ መቼ ነው አላዋቂው ጤነኛውን ከሕመምተኛው ለይቶ የሚያውቀው? ብለው መለሱ}} (መጅሙዑል ፈታዋ) ➖ጥፋተኛውንም ራሱ መጥቀም ነው! ጥፋተኛው አጉል እልህ፤ ሹብሀ፤ ጥቅማ-ጥቅም፤ ወገንተኝነትና ሌሎችም እዚሁ ዱንያ ላይ የሚያበቁ ነገሮች ሸንግለውት ለመመለስ ቢከብደውም፤ ማንኛዋንም ትክክል ያልሆነች ነገር ባሰራጨ ቁጥር ምላሽ ሲሰጠው፤ በርካታ ጥቅሞች ሲኖሩት፤ ከነሱም ውስጥ፦ 1.የሱን ንግግር ሰምተው ተደናድነው ጥፋት ላይ የሚወድቁትን የነዛን ሁሉ ወንጀል እንዳይሸከም ወንጀሉን ማቃለል ነው። 2.ምላሽ ሲሰጥበት ምናልባት ከእለታት አንድ ቀን አላህ ልቡን ለሀቅ ከፍቶለት ቢቶብት፤ ዲንን በማጥፋቱ ከአላህ ፊት እንዳይጠየቅ ምክንያት እንሆንለታለን! ይሄም ወንድምን መርዳት ከሚለው ነው የሚገባው። የአላህ ባሮች ሆይ ታዲያ እንደዚህ ርዕስ የተባረከ ነገር ምናለ በአላህ!? ሆኖም ግን ሁሉም ሊጠነቀቅ የሚገባው አንገትን ከማስሞሽለቅ ከጅሃጅ ጋር የሚወዳደር ያውም የሚበልጥ የሆነ ጉዳይ እንዲህ በዋዛ የሚገኝ አይደለምና የ ኢ ኽ ላ ስ ን ነገርን ትልቅ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል። ረድ አድራጊው የሱና ወንድሙ ላይም ሆነ የሌላ አካሄድ ባለቤት ላይ ምላሽ ሲሰጥ ረድ የተደረገባቸው በግልፅ ከተመለሱም እሰየው በግልፅ መመለስ ተስኗቸው ረድ አድራጊው ላይ ቂም ይዘው ቀድሞም ምንም አይነት ጥፋት እንደሌለ ለማስመሰል ቢጥሩም ራሳቸውን ይጎዳሉ እንጅ ዋናው ጉዳዩ መስተካከሉ ነውና በኢኽላስ እስካደረገው ድረስ ከአላህ ዘንድ አጅር መጠበቅ ነው ያለበት። ሌላው ረድ የሚደረገው ዛሬ እንደሚታየው ሌሎች እኛ ላይ ስለሚናገሩ ጥፋታችንን ስላጋለጡ ዘመቻ መክፈት አይደለም። ይህ ከሆነ ዛሬ ላይ ኢኽዋኖችና ሙመይዓዎች እንዲሁም ሀጃዊራዎችም ሁሉም የጥመት ቡድን የገቡበት ችግር ውስጥ መግባት ይሆናል። ከነሱ ዘንድ በአጥፊዎች ላይ ረድ ምላሽ መስጠት የለም። ነገር ግን እነሱን የነካቸው ላይ ዘመቻ ይከፍታሉ። ይሄ ሁሉ ኢኽላስን የሚፃረር አደገኛ ነገር ነው። ረድ ለቡድንተኝነት ከዋለና ኢኽላስ ከሌለው ህሜት ነው የሙስሊሞችን ነውር መከታተል ከሚለው ነው የሚካተተው። http://t.me/Abdurhman_oumer
نمایش همه...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ « ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡ » [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

#የሱና_ባለ-ቤት! የቢድዓ ሰዎች አየሩን እያዩ አንድ ሁለት ንግግር ተናግረውና የሆነ ሁኔታ አንፀባርቀው የሚሸውዱት ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ከጥመታቸው እስከ-ሚመለሱ ድረስ ጆሮ የማይሰጥ ነው። وقال مفضل بن مهلهل: لو كان صاحب البدعة إذا جلست إليه يحدثك ببدعته حذرته وفررت منه، ولكنه يحدثك بأحاديث السنّة في بدو مجلسه ثم يدخل عليك بدعته فلعلها تلزم قلبك فمتى تخرج من قلبك. 📚 [الإبانة (2/ 444) አላህ ይዘንላቸው ሙፈዶል ብን ሙሐልሐል - የሚከተለውን ብለዋል :- "ከቢድዓ ባለቤት ዘንድ ከተቀመጥክ ፣ በቅድሚያ ቢድዓውን ቢነግርህ ኖሮ ትጠነቀቀው ነበር ፣ ከርሱም ትርቅ ነበር። ነገር ግን በቅድሚያ የሱና ሐዲሶችን ነው የሚነግርህ። ከዚያም ቢድዓውን ያስገባልሀል። ልብህም ትይዛታለች። ከዚያ በኋላ ከልብህ መቸ ነው የምትወጣው?" 📚 አል-ኢባና (2/ 444)] t.me/Abdurhman_oumer
نمایش همه...
Photo unavailable
كما يقال من لم يعظه القرآن والسنة فلا واعظ له እንዲህ ይባላል “ቁርኣንና ሱንና ያልገሰፀው (ያልመከረው) ሰው መካሪ የለውም።”
نمایش همه...
Photo unavailable
ወንድ ልጅ ለሚስቱ መህር ግዴታ እንደሆነው ሁሉ ሴት ልጅም ለባሏ ከና ክብሯ መገኛት ግዴታዋ ነው። https://t.me/UmuAmar_UmuManas
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.