cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Isaiah 48 Apologetics

✟ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✟ "14 The grace of the Lord Jesus Christ, and the love of God, and the communion of the Holy Ghost, be with you all. Amen." (2Corinthians 13:14) 📌 ሌላኛው ቻናላችን:- @ovadiah

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
2 982
مشترکین
-124 ساعت
+57 روز
+4230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

"13-14 እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ #ልጅ መንግሥት አፈለሰን። 15-16፤ እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። #የሚታዩትና #የማይታዩትም፥ #ዙፋናት ቢሆኑ ወይም #ጌትነት ወይም #አለቅነት ወይም #ሥልጣናት፥ #በሰማይና_በምድር ያሉት #ሁሉ #በእርሱ #ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል" (ቆላ 1:13-16) በዚህ ክፍል ላይ ሐዋሪያው ጳውሎስ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሲናገር እንመለከታለን። በቆላ 1:13-16 ላይ ሐዋሪያው ጳውሎስ የተፈጠሩ ፍጥረታትን ሁሉ ይዘረዝራል። የሚታዩትና የማይታዩት (የማይታየው መንፈሳዊው አለም ወይም መንግስተ-ሰማይ (2ቆሮ 4:17-18) እና የሚታየው ቁሳዊ አለምን ይጨምራል) መንፈሳዊ ፍጥረታት ከነ ደረጃቸው፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ (በምድር ያሉት የሰው ልጆችን ጨምሮ) በአጠቃላይ በልጁ በኢየሱስ እንደተፈጠረ ገልጿል። ሐዋርያው ጳውሎስ በቆላሲስ 1 የዘረዘራቸው ፍጥረታት ሁሉ ዕብ 1:1 ላይ ላይ አለማት በሚለው ቃል ተገልጸዋል። ዕብ 1 አለማት ሲል ቆላ 1 ላይ የተዘረዘሩትን ፍጥረታት ሁሉ ማለት ነው። ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው በዕብ 1:1 ላይ አለማት ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል ዕብ 11:3 ላይ በእግዚአብሔር ቃል የተፈጠረውን መላውን ፍጥረት ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ነው። ይህ አለማት ማለት የተፈጠረ ማንኛውም ፍጥረት ማለት እንደሆነ ያረጋግጣል። ስለዚህ የዕብራውያኑ ጸሐፊ አለማት በልጁ እንደተፈጠሩ መናገሩ ከቆላ 1 ጋር ያለውን ውስጠ-ጽሑፋዊ አንድነት ከማረጋገጥ ባሻገር ጸሐፊው ራሱ የቆላሲሱ ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ማሳያ ነው ሌላው ሊስተዋል የሚገባው ነገር በዕብ 1 ላይ እግዚአብሔር አለማትን የፈጠረው በልጁ መሆኑን መገለጹ ነው። ይህ ከቆላሲስ 1 ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው። ምክንያቱም በቆላ 1:15-16 ላይ ሁሉ ፈጠረ የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በቁ.13 ላይ ተገልጿልና፦ "እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ #ልጅ መንግሥት አፈለሰን" (ቆላ 1:13-14) በሁለቱም ቦታዎች ላይ ልጅ የሆነው ኢየሱስ የሁሉ ፈጣሪ መሆኑ መገለጹ ጸሐፊው እራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ሌላኛው ማስረጃ ነው "ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር #ሁሉም_በእርሱ_በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን #አንድ_ጌታ_ኢየሱስ ክርስቶስ አለን" (1ቆሮ 8:6) በዚህ ክፍል ላይ ሐዋሪያው ጳውሎስ ሁሉም ነገር በአንዱ ጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል እንደሆነ ይናገራል። ክፍሉን ሲጀምር ሁሉ ነገር ከእርሱ የሆነ አንድ አምላክ አብ እንዳለን ከገለጸ በኋላ ሁሉ ነገር በእርሱ በኩል የሆነ አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለን ይገልጻል። ሁሉ ነገር በእርሱ በኩል የሆነ ማለት ሁሉ ነገር በእርሱ በኩል ወይም አማካኝነት የተፈጠረ ማለት ነው። ይህ #ሁሉ_በእርሱ_በኩል_የሆነ የሚለው አገላለጽ በሌላ ስፍራ ላይ ፈጣሪነትን ለማመልከት ጥቅም ላይ አገላለጽ ነው፦ " #ሁሉ ከእርሱና #በእርሱ ለእርሱም #ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን" (ሮሜ 11:36) በሮሜ 11:36 ላይ የእግዚአብሔር አብን ፈጣሪነት ለማመልከት ጥቅም ላይ ያዋለውን ቃል በ1ቆሮ 8:6 ላይ ለክርስቶስ ማዋሉ የክርስቶስ ኢየሱስን ፈጣሪነት ያረጋግጣል። 1ቆሮ 8:6 የጌታ ኢየሱስን ፈጣሪነት ከማረጋገጥ ባሻገር ከዕብ 1:2 ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው። በ1ቆሮ 8:6 ላይ "በእርሱ በኩል" ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ሀረግ "ዲያ ኡው/δι οὗ" የሚለው ሲሆን በዕብ 1:2 ላይ እግዚአብሔር አለማትን በልጁ መፍጠሩን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለው ራሱ ሀረግ ነው በ1ቆሮ 8:6 አብ principal መሆኑን #ከ_እርሱ በማለት ከገለጸ በኋላ ልጁ ኢየሱስ ደግሞ ሁሉ በእርሱ አማካኝነት የተፈጠረ agent መሆኑን #በ_እርሱ በማለት ገልጿል። በዚሁ መንገድ በዕብ 1:2 ላይ አለማትን በፈጠረበት በልጁ በማለት እግዚአብሔር principal ልጁ ኢየሱስ ደግሞ እግዚአብሔር አለማትን የፈጠረበት agent መሆኑን ገልጿል። ለዚያ ነው ልክ ከ1ቆሮ 8:6 ጋር አንድ አይነት በሆነ መንገድ #በ_ፈጠረበት የሚለው። በሁለቱ ክፍሎች መካከል ያለው የሰዋሰው (grammar) እና ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) አንድነት የሁለቱም ክፍሎች ጸሐፊ ጳውሎስ መሆኑን ያረጋግጣል በተጨማሪም ልክ በዕብ 1:2 አለማት የተፈጠሩት በልጁ መሆኑን እንደገለጸው ሁሉ ነገር ሁሉ በእርሱ በኩል የሆነ አንድ ጌታ ኢየሱስ እንዳለን በገለጸበት በዚያ በ1ቆሮንቶስ መጽሐፍ ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ገልጿል፦ "ወደ #ልጁ ወደ ጌታችን ወደ #ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው" (1ቆሮ 1:9) በሁለቱም መጻሕፍትና አውዶች ጌታችን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉ በእርሱ አማካኝነት የተፈጠሩበት ፈጣሪ መሆኑ መገለጹ የዕብራውያኑ ጸሐፊ ጳውሎስ ለመሆኑ ማስረጃ ነው። ♦️ ጌታ ኢየሱስ አብ አለማትን የፈጠረበት agent መሆኑ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በዕብ 1:2 እና በ1ቆሮ 8:6 ብቻ ነው የተገለጸው። በሌሎች ቦታዎች የክርስቶስ ኢየሱስ ፈጣሪነት ቢገለጽም (ዮሐ 1:1-3 ቆላ 1:13-17) የአብ agent መሆኑ ግን በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሁለቱ ቦታዎች ብቻ ነው የተገለጸው። ይህ ሁለቱ ክፍሎች ልዩ የሆነ የይዘት አንድነት ያላቸው መሆኑን ከማሳየት ባሻገር የሁለቱም ክፍሎች ጸሐፊ ጳውሎስ መሆኑን በማያሻማ መንገድ ያረጋግጣሉ። 3) በዘመን መጨረሻ በልጁ ተናግሮናል በዕብ 1:2 የዕብራዊያኑ ጸሐፊ እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በብዙ ጎዳና ለአባቶቻቸው በነቢያት ከተናገረ በኋላ በዚህ በዘመን መጨረሻ አለማትን በፈጠረበት በልጁ እንደተናገረ ገልጿል። ይህ ቃል የዕብራውያኑ ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ በብዙ መልኩ ያረጋግጣል። በመጀመሪ ደረጃ የዕብራዊያኑ ጸሐፊ የነበረበትን ዘመን የዘመን መጨረሻ ይለዋል። ይህ ጳውሎስ በመልእክቱ የተናገረው ነገር ነው፦ "ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም #የዘመናት_መጨረሻ_የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ" (1ቆሮ 10:11) ክርስቶስ ኢየሱስ በስጋ ከተገለጠ በኋላ ያለውን ዘመን ሐዋሪያው ጳውሎስ የዘመን መጨረሻ ብሎ ጠርቶታል። ከቁ.1 ጀምሮ እንዴት የጥንት እስራኤላውያን ከግብፅ እንደወጡና በኋላ ላይ ግን እንደተፈታተኑት ከገለጸ በኋላ ይህ በዘመን መጨረሻ ላይ ላለነው ግሳጼ የተጻፈ መሆኑ ይገልጻል። ስለዚህ ልክ እንደ ዕብ 1:2 ሐዋሪያው የነበረበትን ዘመን፥ የዘመን መጨረሻ ብሎ ጠርቶታል። ይህ ጸሐፊው ራሱ ጳውሎስ ለመሆኑ አንድ ማሳያ ነው "ነገር ግን #የዘመኑ_ፍጻሜ_በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ" (ገላ 4:4) በዚሁ ስፍራም ሐዋሪያው ጳውሎስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም የተወለደበትን ዘመን የዘመን መጨረሻ ሲል እንመለከታለን። ወልድ በስጋ ተልኮ የመጣበትን ዘመን (ሮሜ 8:3) ጳውሎስ የዘመን ፍጻሜ ማለቱና በሁለቱም ክፍሎች ላይ የትኩረቱ ማዕከል ልጁ መሆኑ ገላ 4:4 ከዕብ 1:1 ጋር ያለውን የሀሳብ አንድነት ከማሳየት ባሻገር የሁለቱም መልእክታት ጸሐፊ ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ሌላኛው ማሳያ ነው ▶️ ይቀጥላል
نمایش همه...
6👏 2
🚩 የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ (ክፍል 1) ሙስሊሞች ሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስን መለኮታዊ ቃልነት የማይቀበሉ ወገኖች የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ማን እንደሆ አይታወቅም፥ ስለዚህ የአምላክ ቃል አይደለም ሲሉ ይደመጣሉ። ይህ ግን የሀሰት ሙግት ነው። ምክንያቱም የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከምሁራንና ከቤተክርስቲያን ታሪክ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል። ከዚያም ባሻገር በራሱ በዕብራውያን መልእክት ውስጥ ጸሐፊው ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ብዙ ማስረጃዎች አሉ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በተከታታይ ክፍሎች የዕብራውያን ጸሐፊ ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ inter-textual/ውስጠ-ጽሑፋዊ ማስረጃዎችን ለማቅረብ እንሞክራለን። የመጀመሪያው ማስረጃ፦ ✍️ 1) የዕብራውያኑ ጸሐፊ አይሁዳዊ ነው የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ መልእክቱን ሲጀምር አይሁዳዊ መሆኑን በመግለፅ ይጀምራል፦ "ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና #ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ" (ዕብ 1:1) ጸሐፊው መልእክቱን ሲጀምር #ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ በማለት ጥንት እግዚአብሔር በነቢያት ሲናገረው ከነበረው ከአይሁድ ሕዝብ የተወለደ መሆኑን ገልጿል። አባቶቻችሁ ሳይሆን ያለው ራሱን አካትቶ አባቶቻችን ነው ያለው። ስለዚህ ጸሐፊው አይሁድ ያልሆነ አሕዛብ ሳይሆን አይሁዳዊ ነው ማለት ነው። ይህ ጸሐፊው ሐዋሪያው ለመሆኑ አንድ ማስረጃ ነው። ምክንያቱም ሐዋሪያው ጳውሎስ በመልእክታቱ አይሁዳዊ መሆኑን በተደጋጋሚ ይገልጻል፦ "እንግዲህ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸውን? እላለሁ። አይደለም #እኔ ደግሞ #እስራኤላዊና ከአብርሃም #ዘር ከብንያምም ወገን ነኝና" (ሮሜ 11:1) "በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ፥ ከእስራኤል ትውልድ፥ ከብንያም ወገን፥ ከዕብራውያን #ዕብራዊ_ነኝ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ፥ ፈሪሳዊ ነበርሁ" (ፊሊ 3:5) " #ዕብራውያን ናቸውን? #እኔ ደግሞ #ነኝ። የእስራኤል ወገን ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ። የአብርሃም ዘር ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ። የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን?" (2ቆሮ 11:22) "እኔ የኪልቅያ በምትሆን በጠርሴስ የተወለድሁ፥ በዚችም ከተማ በገማልያል እግር አጠገብ ያደግሁ፥ የአባቶችንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ፥ ዛሬውንም እናንተ ሁሉ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ #አይሁዳዊ ሰው ነኝ" (ሐዋ 22:3) " #ጳውሎስ ግን። እኔስ #አይሁዳዊ በኪልቅያ ያለው የጠርሴስ ሰው ሆኜ ስመ ጥር በሆነ ከተማ የምኖር #ነኝ፤ ለሕዝቡ እናገር ዘንድ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ አለ" (ሐዋ 21:39) ▶️ ከሐዋርያው ጳውሎስ መልእክታት ጭብጦች አንዱ ጭብጥ ምንም እንኳ አይሁዳዊ ቢሆንም እግዚአብሔር የክርስቶስ ኢየሱስን ወንጌል ለአሕዛብ እንዲሰብክ እንደላከው መግለጽ ነው። በተደጋጋሚ አይሁዳዊ መሆኑን የሚናገርበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው "ለእናንተም ለአሕዛብ እናገራለሁ። እኔ #የአሕዛብ_ሐዋርያ በሆንሁ መጠን #ሥጋዬ የሆኑትን አስቀንቼ ምናልባት ከእነርሱ አንዳንዱን #አድን እንደሆነ አገልግሎቴን አከብራለሁ" (ሮሜ 11:13-14) በሌሎች ቦታዎችም አይሁዳዊ መሆኑን ገልጾ (2ቆሮ 11:22) የሚያሳስበው ግን አሕዛብም ያሉባቸው አብያተክርስቲያናት መሆናቸውን ይገልጻል (2ቆሮ 11:28) ዕብራዊ መሆኑን ከገለጸ በኋላ (ፊሊ 3:5) በክርስቶስ ኢየሱስ ያመኑ አሕዛብ በክርስቲያናዊ አኗኗር የሚኖሩትን አማኞች እንዲመለከቱ ያዛል (ፊሊ 3:17) ይህ አይሁዳዊ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጹ የተለመደ መሆኑን ያሳያል በሚያስገርም ሁኔታ ዕብ 1:1 ላይ ጸሐፊው "አባቶቻችን" በማለት አይሁዳዊ መሆኑን በገለጸበት በዚያው መንገድ ሐዋሪያው ጳውሎስ በሌላው መልእክቱ ላይ አይሁዳዊ መሆኑን ገልጾ መልእክቱን ጀምሯል፦ "ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። #አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ" (1ቆሮ 10:1) በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋሪያው ጳውሎስ ከግብፅ ምድር ስለወጡት የዘጽአቱ ትውልድ ይናገራል። ምዕራፉን ሲጀምር እንደ መግቢያ የተጠቀመው "አባቶቻችን" በማለት ከግብፅ የወጡት የእስራኤል አባቶች አባቶቹ መሆናቸውን በመግለፅ ነው። አይሁዳዊ ስለሆነ ልክ እንደ ዕብ 1:1 የጥንት አይሁዳውያንን አባቶቻቸው መሆናቸውን በመግለፅ ነው የጀመረው። በሌሎች ቦታዎችም እንዲሁ ሐዋርያው ጳውሎስ ራሱን አካትቶ የጥንት አይሁዳውያን አባቶቹ መሆናቸውን ገልጿል (ሐዋ 13:17 ሐዋ 24:14 ሐዋ 26:6 ሐዋ 28:25) ዕብ 1:1 ከ1ቆሮ 10:1 እና መሰል ምንባባት ጋር ያለው ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ተመሳሳይነት የመልእክቱ ጸሐፊ ራሱ ጳውሎስ ለመሆኑ ጉልህ ማሳያ ነው። ✍️ 2) የዕብራውያን መልእክት ከሌሎች የሐዋርያው ጳውሎስ መልእክታት ጋር ያለው ልዩ የሆነ የአስተምህሮ አንድነት የዕብራውያን መልእክትን በጥንቃቄ ስናጠና የመጀመሪያው የምንረዳው ነገር መልእክቱ ከሌሎች የሐዋርያው ጳውሎስ መልእክታት ጋር ያለውን ልዩ የሆነ የስነ-መለኮታዊ አስተምህሮ አንድነት እናስተውላለን። በዕብራውያን መልእክት ላይ ጸሐፊው በሐዋሪያው ጳውሎስ መልእክታት ውስጥ ብቻ የሚገኙ ሀሳቦችን እና ቃላትን ይጠቀማል። አንድ በአንድ እንመልከተው፦ "1፤ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ 2፤ #ሁሉን_ወራሽ_ባደረገው ደግሞም #ዓለማትን_በፈጠረበት #በልጁ #በዚህ_ዘመን_መጨረሻ_ለእኛ_ተናገረን፤ 3፤ #እርሱም_የክብሩ_መንጸባረቅና #የባሕርዩ_ምሳሌ_ሆኖ፥ #ሁሉን_በስልጣኑ_ቃል_እየደገፈ፥ #ኃጢአታችንን_በራሱ_ካነጻ በኋላ #በሰማያት_በግርማው_ቀኝ_ተቀመጠ" (ዕብ 1፥1-3) 1) እግዚአብሔር ልጁን ሁሉን ወራሽ አድርጎታል የዕብራውያን መልእክት መግቢያው ላይ ጸሐፊው እግዚአብሔር ልጁን ሁሉን ወራሽ እንዳደረገው ይገልጻል። እግዚአብሔር አብ ልጁ ክርስቶስ ኢየሱስን የሁሉ ወራሽ አድርጎታል የሚለው ሀሳብ በሐዋሪያው ጳውሎስ መልእክታት ውስጥ የሚገኝ ሀሳብ ነው፦ "ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል #ከክርስቶስ ጋር አብረን #ወራሾች ነን" (ሮሜ 8:17) "ለገዛ #ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው #ከእርሱ ጋር ደግሞ #ሁሉን_ነገር እንዲያው እንዴት #አይሰጠንም?" (ሮሜ 8:32) " #ሁሉንም_ከእግሩ_በታች_አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።" (ኤፌ 1:22) " #ሁሉን_ከእግሩ_በታች_አስገዝቶአልና። ነገር ግን። ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው" (1ቆሮ 15:27) ወራሽነትን አስመልክቶ የዕብራውያኑ ጸሐፊ በሌሎች የሐዋርያው ጳውሎስ መልእክታት ውስጥ ካሉት ሀሳቦች ጋር አንድ አይነት አስተምህሮ ያለው መሆኑ ጸሐፊው እሱ ራሱ ለመሆኑ ሌላኛው ማሳያ ነው 2) ዓለማት በልጁ እንደፈጠሩ ገልጿል የዕብራዊያኑ ጸሐፊ እግዚአብሔር ዓለማትን በልጁ እንደፈጠረ ገልጿል። ዓለማት ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል "አዮናስ/αἰῶνας" የሚለው ሲሆን መላው ፍጥረትን የሚያመለክት ቃል ነው (ዕብ 11:3) በተጨማሪም በዕብ 1:8-10 ላይ የዕብራዊያኑ ጸሐፊ የእግዚአብሔር ልጅ ሰማይና ምድርን እንደፈጠረ ተናግሯል። ይህ ጸሐፊው ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ሌላ ማስረጃ ነው። ምክንያቱም ሐዋሪያው ጳውሎስ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉ ፈጣሪ መሆኑን አስተምሯልና፦
نمایش همه...
👍 3 1👏 1
New Video፦ Why Four Gospels? ⭐️ በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ መካተት የነበረባቸው ነገር ግን ሳይካተቱ የቀሩ ከሰማንያ የሚበልጡ ወንጌላት አሉን? https://youtu.be/AUtzBU5M2iY?si=4I-xFAC41Sld0VBG ተጭኗል ሼር ይደረግ።🎉
نمایش همه...
👍 5🔥 1
🚩 የቻናላችን አዲሱ የመወያያ ግሩፕ ነው 👇 https://t.me/+lUXgyP0cSCUwYzE0 ተቀላቀሉ!
نمایش همه...
Isaiah 48 Apologetics chat

Samson T invites you to join this group on Telegram.

Photo unavailableShow in Telegram
ይህቺን መጽሐፍ ለ3ኛ ዕትም ለማብቃት እንቅስቃሴ ጀምረናል። በዚህ መልካም ሥራ መሳተፍ የምትፈልጉ ወገኖች ቴሌግራም ላይ ወንድማችን ማሜን ማናገር ትችላላችሁ። ይህንን መልካም ሥራ ከግብ ለማድረስ አንድ ጥራዝ ከማሳተም ጀምሮ ሁላችንም የአቅማችንን እንለግስ። እግዚአብሔር አምላክ ይባርካችሁ! ቴሌግራም t.me/Muhammad_Ewnetlehulu
نمایش همه...
👍 11 6
😢😢
نمایش همه...
نمایش همه...
ክርስቶስ አምላክ ነውን? በሻሸመኔ ከተማ ሺህዎች የታደሙበት የሙስሊም ክርስቲያን ውይይት

👍 9👏 1
🚩 ይህ የወንድማችን የመሐመድ አበባው YouTube ገጽ ነው። ይህ ወንድማችን በእስልምና ዙሪያ የሚያገለግል የተወደደ ወንድም ነው። Subscribe እና Share በማድረግ አግዙት!
نمایش همه...
👍 26 7👏 3🔥 1
🚩 ይህ የወንድማችን የመሐመድ አበባው YouTube ገጽ ነው። ይህ ወንድማችን በእስልምና ዙሪያ የሚያገለግል የተወደደ ወንድም ነው። subscriber እና share በማድረግ አግዙት!
نمایش همه...
نمایش همه...
በእስልምና የድነት ዋስትና አለን?

👍 4 4👏 2🔥 1
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.