fa
Feedback
የእናቶችና የህፃናት ጤና በዶ/ር ትዕግስት አርጋው

የእናቶችና የህፃናት ጤና በዶ/ር ትዕግስት አርጋው

رفتن به کانال در Telegram
1 870
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-57 روز
-1630 روز
آرشیو پست ها
ተወዳጅ ተፈላጊ እና የረጅም አመት ልምድ ያካበቱ የህፃናት ህክምና ባለሙያዎችን በ አንድ ማእከል! - የጨቅላ ህፃናት ህክምና - የህፃናት የተመላላሽና የ24 ሰአት የድንገተኛ ህክምና - የህፃናት ከአ
ተወዳጅ ተፈላጊ እና የረጅም አመት ልምድ ያካበቱ የህፃናት ህክምና ባለሙያዎችን በ አንድ ማእከል! - የጨቅላ ህፃናት ህክምና - የህፃናት የተመላላሽና የ24 ሰአት የድንገተኛ ህክምና - የህፃናት ከአንገት በላይ ህክምና - የህፃናት የካንሰር ህክምና - የህፃናት የነርቭ እና የአእምሮ ህክምና - የህፃናት የኩላሊት ህክምና - የህፃናት የቆዳ ህክምና - የህፃናት ቀላል እና ከባድ ቀዶ ህክምና - የህፃናት የአጥንት ህክምና - የህፃናት የልብ ህክምና - የህፃናት ተላላፊ በሽታዎች ህክምና - የህፃናት የሳምባ እና የመተንፈሻ ኣካላት ህክምና - የክትባት አገልግሎት - የህፃናት የደምና ተያያዥ ህምሞች ህክምና - የህፃናት ፅኑ ህሙማን ህክምና... Contact Us +251946888883 / 011 553 2760 t.me/LANCETMCH Signal to 22 road, 200m before reaching the flyover bridge ከሲግናል ወደ 22 በሚወስደው መንገድ ድልድዩ ጋር ከመድረሶ በፊት Lancet Women & Children Hospital ላንሴት የሴቶችና የልጆች ሆስፒታል

Exceptional Pediatric Care at Lancet Women and Children Hospital! Our Pediatric team is composed exclusively of top pediatric specialists and subspecialists - the best of the best in their fields. From general pediatrics to advanced subspecialties like Cardiology, Neurology, Pulmonology, Nephrology, Neonatology, Orthopedics, ENT, Dermatology, Hematology and Oncology, our doctors have extensive expertise to handle even the most complex cases. Our advanced Neonatal intensive care units, ICU, Pediatric emergency services, and Pediatric surgery capabilities ensure we can meet all of your child's healthcare needs. As a leading pediatric destination, Trust your child's care to our exceptional team at the Lancet Pediatric Department. Contact Us +251946888883 https://t.me/LANCETMCH 📍Signal to 22 road, 200m before reaching the flyover bridge 📍ከሲግናል ወደ 22 በሚወስደው መንገድ ድልድዩ ጋር ከመድረሶ በፊት Lancet Women & Children Hospital ላንሴት የሴቶች እና የልጆች ሆስፒታል

ከወሊድ በሁዋላ የጨቅላ ህፃናት እንክብካቤ፣ ህይወት ማዳን እና እርዳታ ላይ ውጤታማ ስልጠና ለማእከላችን ነርሶች እና አዋላጅ ነርሶች ያዘጋጁልን የማእከላችን የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት እና የጨቅላ
+9
ከወሊድ በሁዋላ የጨቅላ ህፃናት እንክብካቤ፣ ህይወት ማዳን እና እርዳታ ላይ ውጤታማ ስልጠና ለማእከላችን ነርሶች እና አዋላጅ ነርሶች ያዘጋጁልን የማእከላችን የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት እና የጨቅላ ህፃናት ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ገስጥ መታፈርያ እንዲሁም የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ትዕግስት አርጋውን ልናመሰግን እንወዳለን።

Our skilled team and specialized facility at Lancet Women and Children Hospital's NICU department excels in advanced & compli
+4
Our skilled team and specialized facility at Lancet Women and Children Hospital's NICU department excels in advanced & complicated surgeries. This is Baby-X, Twin B Female, Born via C/S, Preterm (32 weeks) with low birth weight (1.5kg). Findings after delivery were distended abdomen & inactive bowel sound. After proper evaluation and confirming with abdominal Xray, our Pediatric surgical team was consulted and Laparatomy was done for the indication of spontaneous gastric perforation. Findings were 0.5cmx0.5cm gastric perforation at the lesser curvature for which repair was done. Post Surgery she was intubated for 24hrs & put on mechanical ventilation. Currently baby is 16days old, stable & improving. 📸 Posted with consent April 7,2024 - World Pediatric Surgery Day "Let's create awareness on Pediatric Surgeries" Contact Us +251946888883 https://t.me/LANCETMCH 📍Signal to 22 road, 200m before reaching the flyover bridge 📍ከሲግናል ወደ 22 በሚወስደው መንገድ ድልድዩ ጋር ከመድረሶ በፊት Lancet Women & Children Hospital

Discover Lancet Women and Children Hospital's Pediatric Surgical Department, where we specialize in advanced pediatric and neonatal surgeries. Our experienced surgeons & exceptional facilities set us apart, making us a leading institution in pediatric surgical care. Our areas of specialization encompass advanced surgeries & treatment of cases like: •  Esophageal atresia/Tracheoesophageal fistula •  Duodenal Atresia •  Intussusception/Hydrostatic reduction & Surgical reduction/ • HSD •  Short bowel syndrome •  Infantile Hypertrophic Pyloric Stenosis •  Omphalocele & Gastroschisis •  Imperforate anus/Anorectal malformation correction •  Congenital Diaphragmatic Hernia •  Undescended Testes •  Hypospadia & Epispadia Correction •  Hernia Repair •  Gastrostomy •  Pediatric Urology Surgeries •  Pediatric Oncology Surgeries... & more. We are dedicated to providing the highest standard of care for our pediatric patients! Contact Us +251946888883 https://t.me/LANCETMCH https://maps.google.com/?cid=17345188147198467565&entry=gps Lancet Women & Children Hospital

Dr. Tigist Argaw is an exceptional Pediatrician who is highly regarded for her expertise and loved by children under her care
Dr. Tigist Argaw is an exceptional Pediatrician who is highly regarded for her expertise and loved by children under her care. As a pediatric specialist, Dr.Tigist offers a comprehensive range of services to address the diverse healthcare needs of children of every age from growth & developmental assessments to diagnosing & treating a wide array of acute and chronic disorders that affect children and thereby ensuring optimal health for your little ones. Dr. Tigist is now available at Lancet Women and Children Hospital Monday to Friday on regular working hours & Saturday half day until 6:00LT. ዶ/ር ትዕግስት አርጋው በሙያዋ የረጅም አመት ልምድ ያካበተችና በልጆች የምትወደድ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ስትሆን በየትኛውም እድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ህፃናት ህክምና ትሰጣለች። ዶ/ር ትዕግስትን በላንሴት የሴቶች እና የልጆች ሆስፒታል ከሰኞ እስከ አርብ በመደበኛ የስራ ሰዐት እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት እስከ 6:00 ማግኘት ይችላሉ። Contact Us +251946888883 https://t.me/LANCETMCH 📍Signal to 22 road, 200m before reaching the flyover bridge 📍ከሲግናል ወደ 22 በሚወስደው መንገድ ድልድዩ ጋር ከመድረሶ በፊት Lancet Women & Children Hospital ላንሴት የሴቶች እና የልጆች ሆስፒታል

የህፃናት #ጉንፋንን የቤት ውስጥ እንዴት አርገን ማከም እንቺላለን❓️❓️ ወደ #ሆስፒታል መውሰድ ያለብንስ መቼ ነው❓️ 👉 ጉንፋን ከ 200 በላይ በሚሆኑ የተለያዩ እና ራሳቸውን በሚቀያይሩ ቫይረሶች የሚመጣ በሺታ ነው:: 👉 በዝህም ምክንያት በአለም ላይ ለጉንፋን ተብሎ የተዘጋጀ ፈዋሽ መድሃኒት የለም ❗️ ሆኖም ቤት ውስጥ በማከም ለውጥ ማምጣት እና ማገገም ይቻላል 👉 የህፃናትን የጉንፋን የቤት ውስጥ ሕክምና ለሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን እነሱም 📌 ከአንድ ዓመት በታች (ለአራስ እና ጨቅላ ህፃናት) እና ከአንድ ዓመት በላይ 1. ለአራስ እና ጨቅላ ህፃናት የጉንፋን ቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው❓️ 👉 አራስ/ጨቅላ ህፃናት የሚተነፍሱት በዋናነት በ አፍንጫቸው ነው:: በጉንፋን ምክንያት አፍንጫቸው ከተደፈነ በ አፋ መተንፈስ ስላለመዱ በጣም ይጨናነቃሉ:: 👉 ስለዚህ አፍንጫቸው ከተደፈነ እንዴት መክፈት/ማፅዳት አለብን ❓️ 📌 መጀመርያ በጀርባ ማስተኛት እና ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 3-4 ጠብታ ማድረግ 40 - 60 ሰከንድ ጠብቀን ከተኙበት አንስተን ወደ ታች ዘቅዘቅ አርገን መያዝ እና የአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ (Nasal suction bulb) ማጽዳት ወይም መምጠጥ ✔️ የጡት ወተት ረጅም ሰአት ማጥባት (#አስተውሉ: የጡት ወተት ዉስጥ በሽታ ተከላካይ ንጥረ ነገሮች አሉ) ✔️ የጣሳ ወተት የሚወስዱ ከሆነ ለብ እያርጉ መስጠት ከሌላው ጊዜ መጠኑን ጨመረ አርጎ መስጠት ✔️ ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት(ከ 7 ወር በላይ) ለምሳሌ ሾርባ የብርቱካን ሻይ እና የመሰሳሰሉት ✔️ ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ ✔️  የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት እና ማናፈስ ✔️ ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን ✔️ በቂ እረፍት/እንቅልፍ እንዲያገኙ ማድረግ ✔️ ስናስተኛቸው ቢያንስ 30 ዲግሪ ከፍ ማድረግ (አንገታቸውን ብቻ አይደለም) ✔️ የአፍንጫ ፈሳሽ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል :: ✔️ ነጭ ሽንኩርት በመጠኑ ከምግባቸው ጋር እየጨመሩ አብስሎ መስጠት ✔️  ትኩሳታቸው ለመቀነስ መጀመርያ ልብሳቸውን መቀነስ ከዛም ለብ ያለ ዉሃ ውስጥ ፎጣ እየነከሩ ግንባራቸው እና ሰውነታቸው ላይ ማድረግ ✔️ ከላይ ባለዉ ዘዴ ሰውነታቸው ካልቀዘቀዘ ባለሙያ አማክሮ በ ፊንጥጣ የሚደረግውን ወይም በሺሮፕ ያለውን ፓራሴታሞል መጠቀም 👨‍⚕️ #ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎችስ የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው❓️ 📌 ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ራስን በአንድ ክፍል ማግለል 📌 ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን ደጋግሞ መውሰድ 📌 ነጭ ሽንኩርት ማር እና ዝንጅብል መጠቀም 📌 በቂ እረፍት ማድረግ 📌 የትኩሳት እና ራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ ለምሳሌ ፓራሴታሞል 🔊 እነዚህን መፍትሄዎች እያረጋችሁ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የመቆራረጥ ምልክት በህፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል‼️ 🔊 ጨቅላ ህፃናት ላይ ጉንፋን በቀላሉ ወደ ኒሞንያ ሊሻገር ስለሚችል ⚠️ ጡት አልጠባም ካሉ ⚠️  ትኩሳታቸው 38.5 በላይ ከሆነ ⚠️ ኃይለኛ ሳል እና ተደጋጋሚ ትውከት ካላቸው ⚠️ እንደ ማንቀጥቀጥ ወይም እንደ መንዘር የሚመስሉ ምልክቶች ካስተዋሉ ⚠️ በጣም መደካከም ካለ ⚠️ ተቅማጥ  ካለ ⚠️ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ እና ማቃሰት ካለ ⚠️ እንቅልፍ ለመተኛት የሚቸገሩ ከሆነ ⚠️ ረጅም ሰአት ማልቀስ ካለ ⚠️ ከ አንድ ዓመት በላይ ሆነው ከዝህ ቀደም በትኩሳት ራሳቸው ስተው መንቀጥቀጥ (Febrile seizure) አጋጥሟቸው የሚያውቅ ከሆነ 🔊🔊 ከላይ ያሉትን ምልክቶች ካዩ ልጅዎን ባፋጣኝ ወደ ሆስፒታል መውሰዱ እና ቶሎ ማሳከሙ የተሻለ ነው❗️ 🔊 #ማሳሰቢያ ⚠️ የፀረ ባክቴርያ (Antibiotics) መድሃኒቶች ለምሳሌ :አሞክሳሲሊን አዝትሮማይሲን ...ለጉንፋን በሺታ መስጠት በፍፁም አይመከርም‼️ አዘጋጅ: ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ረዳት ፕሮፌሰር እና የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም) ❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ ለሌላውም እንዲደርስ #share ያድርጉት

🌟ስለ ሾተላይ (Rh-isoimmunization) ማወቅ ያለብን ነጥቦች🌟 💥 ሾተላይ የሚባለው በሽታ ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን ይህም በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት አለመጣጣም(Rh incompatability) ምክንያት የሚከሰት ነው።  💥 ሾተላይ የሚከሰተዉ  የሴቲቱ የደም አይነት Rh negative ፣ የባል የደም አይነት Rh positive እና የፅንሱ ደግሞ Rh positive ከሆነ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች Rh positive ደም ወደ ሴቲቱ ደም ከገባ ወይም ከወሰደች ነው። 🌟 ነጥብ 💥 ሚስት Rh negative መሆን ይኖርባታል እና ፅንሱ Rh positive መሆን ይኖርበታል 💥 ባል Rh negative ከሆነ ሾተላይ አይከሰትም 🌟 ሾተላይ ለምን ይከሰታል?   👉 የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም 1. “A” 2. “B” 3. “AB” 4. “O”  ተብለው ይጠራሉ። 👉 በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው። ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና  ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል። 👉 አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም  ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ። 👉 እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive  የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል። 👉 ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል ፤ እነኚህም ☘️ በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር - Fetal hydrops ☘️ በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ - Miscarriage ☘️ የፅንሱ የደም ማነስ - Fetal anemia ☘️ ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ ☘️ ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ(phototherapy) ☘️ በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ 🌟 ሾተላይ እንዴት ይታከማል? 👉 Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት ☘️ ባለቤቷ Rh positive ከሆነ ☘️ ውርጃ ካጋጠማት ☘️ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት ☘️ ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ(Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት ☘️ በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤ ☘️ በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ 👉👉 Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል። 💥☘️ በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር(28 ሳምንት) ላይ እና ህፃኑ በተወለደ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል። 👉 Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል። 👉 ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል። በዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት -  @HakimEthio

Repost from TIKVAH-MAGAZINE
ልጆች የስክሪን ጊዜ ልጆች እንዳይረብሹ ስልክ፡ ታብሌት መስጠት፡ ቴሌቪዥን መክፈት እከንደመፍትሄ የሚታየው በሁሉም ሰው ቤት ሆኗል።የስክሪን ጊዜ በልጆች በእድገታቸው ላይ ያለው ተፅዕኖ ምንድን ነው?
ልጆች የስክሪን ጊዜ ልጆች  እንዳይረብሹ ስልክ፡ ታብሌት መስጠት፡ ቴሌቪዥን መክፈት እከንደመፍትሄ  የሚታየው በሁሉም ሰው ቤት ሆኗል።የስክሪን ጊዜ በልጆች በእድገታቸው ላይ ያለው ተፅዕኖ ምንድን ነው? ጥቅሙስ ምንድን ነው? በምን አይነት መልኩ እንፍቀድላቸው? የስክሪን ጊዜ ምን ማለት ነው? የስከክሪን ጊዜ ማለት ህፃናት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ማለትም እንደ ቴሌቪዥን ስልክ ታብሌት ኮምፒውተር ላይ የሚያሳልፉት ጊዜ ማለት ነዉ ። ለምን ያህል ሰአት ይጠቀሙ? - ከ 2አመት በታች ለስክሪን መጋለጥ የለባቸውም! - ከ2-5 አመት ከ1 ሰአት ያልበለጠ በወላጅ የተመረጠ ! - ከ6-17አመት  ከ2 ሰአት ያልበለጠ በወላጅ የተመረጠ! የስክሪን ጊዜ ሲጨምር ጉዳቱ ምንድን ነዉ ? - የቋንቋና የንግግር ብቃታቸው ይቀንሳል - የትምህርት አቀባበል ብቃታቸው ይቀንሳል - ጨረሩ የአይን ጉዳት ሊያመጣ ይችላል - የእንቅልፍ ሰአት መዛባት - ስሜትና እራስን መቆጣጠር አለመቻል - ወጣ ያለ ባህሪ ማሣየት - የአመጋገብ ስርአት መስተጓጐል - የሰውነት እድገትና ክብደት ላይ ተፅእኖ ይፈተጠራል - አእምሮአቸው ላልዳበረበትና መረዳት ለማይችሉት የተለያዩ ነገሮች ይጋለጣሉ። በቂ የስክሪን ጊዜ ጥቅም ምንድን ነው? - ለትምህርታቸው እንደ አጋርነት ያገለግላል። - ለወደፊቱ በ ቴክኖሎጂ ላይ ፍላጎት ላላቸው ልጆች ብዙ እውቀት ያስጨብጣል። - በአንዳንድ "Game" ጫዋታዎች የተለያዩ ችሎታዎችን እንዲያዳብሩ ይረዳል። እንዴት እንቆጣጠራቸው? 1)  ወላጆች ለ Digital and Electronic ያላቸውን እውቀት ማሳደግ አለባቸው። ከልጆቻቸው በተሻለ ወይም ቢያንስ የነሱን ያህል ሊያውቁ ይገባል። 2)  ወላጆችረ ለልጆች ጥሩ ምሳሌ ሊሆቸው ይገባል። 3)  እንዴትና ምን ማየት እንዳለባቸው አስቀድመው አይተው ሊወስኑላቸው ይገባል። 4)  የአጠቃቀም ህጎችን ለልጆች ማውጣት አለባቸው 5)  ጥቅሙንም ጉዳቱንም በደንብ በግልፅ መነጋገር አለባቸው:: 6) ሌላ ጫዎታዎችን የሚጫወቱበት መንገድ ማዘጋጀት ለምሳሌ በቤት ውስጥ የስእል፡ የሙዚቃ ፡ የተለያዩ  ክሂሎት ሊያዳብሩ የሚችሉበትን መጫወቻዎች በማዘጋጀት : የሰውነት እንቅስቃሴዎችን በማሰራት የስክሪን ጊዜን መቀነስ ይቻላል። ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው ( ጠቅላላ ሀኪምና ሁለንተናዊ የህፃናት እድገት ባለሞያ) [ ይኽ መልዕክት @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ዘወትር #ሐሙስ ለወላጆች የሚያቀርብ ትምህርት ነው። ] ❤ t.me/tikvahethmagazine

ዶ/ር ትግስት አርጋው በሙያቸው የካበተ ልምድ ያላቸው የህጻናት ስፔሻሊስት ሃኪማችን ለህጻናት ፣ ለጨቅላ ህጻናት እና ለታዳጊ ልጆች የተሟላ አጠቃላይ ህክምና አገልግሎቶችን ይሰጣሉ ፡፡ ዶ/ር ትግስት
ዶ/ር ትግስት አርጋው በሙያቸው የካበተ ልምድ ያላቸው የህጻናት ስፔሻሊስት ሃኪማችን ለህጻናት ፣ ለጨቅላ ህጻናት እና ለታዳጊ ልጆች የተሟላ አጠቃላይ ህክምና አገልግሎቶችን ይሰጣሉ ፡፡ ዶ/ር ትግስት አርጋው (የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ) ዘወትር ሰኞ ከ1፡00 እስከ 10፡00 ማክሰኞ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 ዕረቡ ከ1፡00 እስከ 10፡00 ሃሙስ ከ1፡00 እስከ 10፡00 አርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከ1፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት ላይ ያገኙዋቸዋል፡፡ facebook: https://www.facebook.com/teklehaimanothospital Instagram: https://www.instagram.com/teklehaimanotgeneral Telegram: https://t.me/teklehaimanothospital1 LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/teklehaimanot-general-hospital/ Twitter: https://twitter.com/TeklehaimanotG4 Website: www.teklehaimanothospital.com E-mail: Info@teklehaimanothospital.com #health #service #teklehaimanothospital #teklehaimanotgeneralhospital #hospital #addisababa #Ethiopia

Who is a good candidate for HydraFacial? HydraFacial is suitable for all skin types and concerns, as it can be customized to
Who is a good candidate for HydraFacial? HydraFacial is suitable for all skin types and concerns, as it can be customized to address your specific needs. Whether you have dry, oily, sensitive, or acne-prone skin, HydraFacial can help you achieve your skin goals. It is also safe for pregnant and breastfeeding women, as it does not use any harsh chemicals or lasers. ለHydraFacial ጥሩ እጩ ማን ነው? HydraFacial የእርስዎን ልዩ ፍላጎቶች ለማሟላት ሊበጅ ስለሚችል ለሁሉም የቆዳ አይነቶች እና ስጋቶች ተስማሚ ነው። ደረቅ፣ ቅባት፣ ሚስጥራዊነት ያለው ወይም ለብጉር የተጋለጠ ቆዳ ካለዎት HydraFacial የቆዳ ግቦችዎን እንዲያሳኩ ሊረዳዎት ይችላል። በተጨማሪም ለነፍሰ ጡር እና ለሚያጠቡ ሴቶች ምንም አይነት ኃይለኛ ኬሚካል ወይም ሌዘር ስለማይጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። ዛሬውኑ ወደኛ ይምጡ! Abed Dermatology and Venereology clinic +251902709999 +251902650909 #HydraFacial #SkinCare #Beauty #Glow#abed#dermatology#beauty#foryoupage#addisababa#ethiopia