ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

iCareMC የእናቶች እና የህፃናት ጤና

iCareMC የእናቶች እና የህፃናት ጤና

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 431
المشتركون
-424 ساعات
-67 أيام
-1130 أيام
أرشيف المشاركات
#ከአንድ ቀን እስከ 18ዓመት ያለውን የልጃችሁን እድሜ በiCare MC application ላይ install አድርጋትሁ ያገልግሎት ከከፈላችሁ በኃላ የልጆቻችሁን -#አካላዊ, -#ቋንቋ -#አስተሳሰብ እና -#ተግባቦት እድገት ይከታተሉ #iCare MC ለጤናዎ የሚተጋ።!!#viral ይህንን link ተጭነው application ኑን ያውርዱ Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icaremc.app iPhone: https://apps.apple.com/jp/app/icare-mc/id6782706843?l=en-US https://vt.tiktok.com/ZSbgsRFcX/

በiCare MC application ከታች ባለው link ተጭነው የእርግዝናውን የግፊት መጠን ይከታተሉ ሐኪም ያማክሩ #0964407777 Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icaremc.app iPhone: https://apps.apple.com/jp/app/icare-mc/id6782706843?l=en-US

የግፊት ህመምና እርግዝና ✳ባደጉ ሀገራት ከእርግዝና ጋር ተያይዘው ከሚከሰቱ ሞቶች ቀዳሚውን ሥፍራ የሚይዘው በግፊት ምክንያት የሚመጣ ነው(በታዳጊ ሀገራት ከወሊድ በኋላ የሚከሰት የበዛ ደም መፍሰስና ጥንቃቄ የጎደለው ውርጃ ሊቀድሙት ይችላሉ)። ከመቶ ወላዶች 16ቶቹ የግፊት ህመም ሊያጋጥማቸው ይችላል(ከእርግዝና በፊት የነበረ ወይም በእርግዝና ወቅት የሚጀምር)። ✳ጥቁሮች (Black race)፣ እድሜ 35 ዓመትና ከዛ በላይ የሆኑ፣ ከልክ ያለፈ የሰውነት ውፍረት (Obesity) ያለባቸው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው። እነዚህ አጋላጭ ሁኔታዎች በሌሉበትም ሊከሰት ይችላል። ✳በእርግዝና ጊዜ ግፊት ህመም አለ የሚባለው የደም ግፊት በ4 ሰዓታት ልዩነት 2 ጊዜ ተለክቶ >/=140/90 ሲሆን >=160/110 ከሆነ ደግሞ በ15 ደቂቃዎች ደግሞ ማየትና በዚያው ከቆየ ደግሞ ወዲያው ግፊት መቀነሻ መድኃኒት መስጠትና <140/90 በታች ማድረግ የሚያሻው (Severe Hypertension) ይሆናል። ✳ግፊት በእርግዝና ወቅት በ4 ይከፈላል፡ 1. ከእርግዝና በፊት የነበረ ወይም የእርግዝና ዕድሜ ከ 20 ሳምንት በፊት እያለ የሚከሰት(Chronic Hypertension) 2. እርግዝናው 20 ሳምንትና ከዛ በላይ ሆኖ የሚከሰት ግን    የሌሎች አካላት(ጉበት፣ ኩላሊት፣የደም ሕዋሶች፣ የአንጎልና የሳምባ) ጉዳት ያላስከተለና በሽንት ፕሮቲን የማይባክንበት(Gestational Hypertension) 3. አደገኛ የእርግዝና ጊዜ ግፊት(Preeclampsia/Eclampsia): ከላይ በተራ ቁጥር እንደተገለጸው ሆኖ ግን የተዘረዘሩ አካላት ጉዳቶች የሚታዩበትና እንደሚጥል ህመም አይነት ያለ የሰውነት መንቀጥቀጥ ወይም ራስን መሳት የሚስተዋልበት(Eclampisa) 4. ቁጥር 1  በተገለጸው ላይ ቁጥር 3 የተገለጸው ሲደረብ(Preeclampsia Superimposed on Chronic Hypertension) ✳እነዚህ ክፍፍሎች ህክምናቸውን ለማመልከት ይረዳሉ። 1. Chronic Hypertension ያለባቸው ሴቶች ከማርገዛቸው በፊት ግፊታቸው ከ140/90 በታች ለማድረግ መታከም አለባቸው፤ ማርገዝ ሲፈልጉ ወይም ድንገት ሳያውቁ አርግዘው ከሆነ የሚወስዱት መድኃኒት ጽንስ የማይጎዳ መሆኑን ሐኪም ጋር ሄደው ማጣራት አለባቸው፤ እየወሰዱ ያሉት ጽንሳቸውን የሚጎዳ ከሆነ ወደማይጎዳው ማስቀየር አለባቸው። ግፊታቸው ላይ ሌላ ግፊት እንዳይደረብ(ቁጥር 4 ላይ እንደተገለጸው) እርግዝናቸው 12 ሳምንት ሲሆነው አስፕሪን(Aspirin 81mg daily) መውሰድ አለባቸው(የአስፕሪን አለርጂ ካለባቸው በስተቀር) 2. Gestational Hypertension ያለባቸው ደግሞ ግፊታቸው >/=160/110(Severe Hypertension) ከሆነ ወዲያው ግፊት መቀነሻ መድኃኒት መጀመር አለባቸው፤ ከዛ በታች ከሆነ ግን መድኃኒት ሳይጀምሩ ክትትል ላይ ይቆያሉ። 3 እና 4. አስቸኳይና ነፍስአድን ህክምና በብዙ ባለሙያዎች ስብጥር ያስፈልጋቸዋል፤ እንደህመሙ ደረጃ በመድኃኒት ግፊትን መቀነስ፣ ጽንስ ከማቋረጥ ወይም ከደረሰ ከማዋለድ እስከ ጽኑ ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል። ✳ይህ አደገኛው አይነት ግፊት ምልክት/ስሜት አልባ ሊሆን ቢችልም በዋናነት ሊሰሙ የሚችሉ ስሜቶች/የህመም ምልክቶች: ከ20 ሳምንት ያለፈ እርግዝና ባላት ነፍሰጡር የሚሰማ ሌላ ምክንያት የሌለውና ለህመም ማስታገሻ ምላሽ የሌለው ራስምታት፣ ከቀኝ ጡት ሥር ወይም በላይኛው ሆድ የሚሰማ ማቃጠል/ውጋት፣ የሽንት መጠን መቀነስ፣ የፊትና እጅ እብጠት (50-80% በሚሆኑ ነፍሰጡሮች የሚከሰተውንና በሽታ ያይደለውን የእግር እብጠት አይመለከትም) ፣ ድንገት ራስን መሳት ወይም የሚጥል በሽታ እንዳለው ሰው መንቀጥቀጥ/መንፈራገጥ ...እና ከእነዚህ ምልክቶች ጋር ተያይዞ የደም ግፊት ጨምሮ ሲገኝ። ለማረጋገጥ የሚሠሩ የላቦራቶሪ ምርመራዎች ህመሙን ለመለየት ያግዛሉ። ✳በእርግዝና ወቅት የግፊት ህመም ያጋጠማቸው እናቶች  ወደፊት ለሚዘልቅ ግፊት፣ለልብ ህመም፣ ለኩላሊት ህመምና ለስትሮክ የመጋለጣቸው ዕድል ከፍ ያለ ስለሆነ ከወለዱ በኋላም ግፊታቸውን መለካትና አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ መድኃኒታቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋል። ይህም ክትትል ወልደው ከሆስፒታል ከወጡ 3-10 ቀን ጀምሮ መሆን ይገባል። በዚህ የክትትል ወቅት መዳናቸው የታወቀ ደግሞ ከዚያ በኋላ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ግፊታቸውን መታየት አለባቸው። ✳ስለዚህ በእርግዝና ጊዜ ስለሚከሰት አደገኛ ግፊት (Preeclamsia/Eclampsia) ለእናቶችና ለቤተሰቦቻቸው ይህችን አጭር የጤና መረጃ ላጋራ ስጽፍ በዚህ በሽታ በወጣትነት ዕድሜያቸው ያጣናቸውን እናቶችን በሙሉ እና ሁለት እጅግ የምወዳቸው ቤተሰቦቼን 1. መምህርት ሰናይት ሰማያት፡ ጭምቷ እህቴ (የአጎቴ ልጅ) 2. ሚሚ (ትዕግሥት ደረሰ): እውነትም እናት የሆነች ደጓ ዘመዴን እያሰብኳቸው ነው💔 ❤ለእነርሱ መታሰቢያ በሕይወት ላሉ እናቶች ደግሞ ትምህርት ይሁንልኝ። References: - 2025 AHA/ACC Guideline for the Prevention, Detection, Evaluation, and Management of High Blood Pressure in Adults. - ACOG Guidelines for the Diagnosis and Management of Gestational Hypertension and Preeclampsia, 2020 - Harrison's Principles of Internal Medicine, 22nd Edition.               Dr. Esayas Sada: Internist Bele General Hospital @HakimEthio

🌟 አዲስ ልጅ የወለደች እናት ልጇ ላይ ማየት እና በትኩረት መከታተል ያለባት 10 ወሳኝ ነገሮች 1. ልጁ በስንት የእርግዝና ሳምንቱ እንደተወለደ እና ሲወለድ የነበረውን የክብደት መጠን ማወቅ 2. የሽንት መስመር እና የካካ መስመር የተለያየ እና ጤናማ መሆን አለመሆኑን ማየት አዲስ የተወለደ ህፃን ሽንት የሚሸናው እና ካካ የሚያደርገው ጤናማ በሆነ ተፈጥሮአዊ አካሉ መሆን አለመሆኑን ሲፀዳዳ በማየት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ይህም ጥቅሙ አንዳንድ ጊዜ ህፃናት ሲወለዱ በተፈጥሮ የሚከሰቱ የካካ መውጫ ቀዳዳ አለመኖር ወይም የካካ መውጫ እና የሽንት መውጫ ቀዳዳ አንድ መሆን ሊከሰት ስለሚችል ነው ። ይህ ችግር ደግሞ በጊዜ ተገቢውን ህክምና እና ክትትል ካላገኘ የልጁን ሂወት አደጋ ላይ የሚጥል የጤና እክልን ያስከትላል። 3. ከተወለደ በኋላ ካካ ያደረገበትን ሰአት እና ካካ በየስንት ሰአት እንደሚያደርግ ማየት አንድ አዲስ የተወለደ ጤናማ ህፃን በ 24 ሰአት ውስጥ አረንጓዴ ወይም ጠቆር ያለ ካካ ያደርጋል። ነገርግን በ 24ሰአት ውስጥ ካካ ካላደረገ ወይም ካካ ሲያደርግ የሚጨናነቅ ከሆነ እንዲሁም ሆዱ እየተነፋ የሚመጣ ከሆነ ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ በዋነኝነት የአንጀት ጡንቻ ነርቮች ላይ ችግር  ወይም ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ሊሆን ስለሚችል የልጅዎን ሀኪም በጊዜ ማማከር ያስፈልጋል። 4. ወንድ ልጅ ከሆነ ሁለቱም የዘር ፍሬዎች ከረጢት ውስጥ መሆናቸውን  ማረጋገጥ አንዳንድ ጊዜ የወንድ ህፃናት ሲወለዱም ሆነ ከተወለዱ በኋላ ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ የዘር ፍሬያቸው ጤናማ በሆነ መንገድ የዘር ፍሬ ከረጢት ውስጥ ሳይወርድ እዛው የታችኛው የሆድ ክፍል ውስጥ ወይም የዘር ፍሬ መውረጃ መስመሩ ላይ ሊቀር ይችላል ። ይህ ደግሞ በጊዜ ካልታወቀ በጊዜ ሂደት ህፃኑ ላይ አደገኛ የሆኑ የጤና እክሎችን ያስከትላል። ሌላው የሽንት መሽኛ ቀዳዳው  ጤናማ  እና ተፈጥሮአዊ ቦታ ላይ መሆን አለመሆኑን ማየት ማለትም የመሽኛ አካሉ ላይ የሚኖረው የሽንት መውጫ ቀዳዳ ከጤናማው ቦታው በተለየ ከጫፉ ላይ ሳይሆን ከስር ወይም ከላይ ከሆነ ከመገረዙ በፊት በጊዜ ታይቶ ችግሩ መታከም ያስፈልገዋል። 5. የሆድ የታችኛው ክፍል በግራ ወይም በጎን በኩል እንዲሁም ወንድ ህፃን ከሆነ የዘር ፍሬ ከረጢት እብጠት መኖር አለመኖሩን ማየት ይህ ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ የታችኛው የግራ ወይም የቀኝ የሆድ ግድግዳ በመሳሳት የአንጀት ክፍል ወደ ዉጪ መውጣትን ያስከትላል። ወንድ ህፃን ከሆነ ደግም የሆድ እቃ ክፍሉ ከዘር ፍሬ ከረጢት ጋር ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት በመፍጠር የዘር ፍሬ ከረጢት ማበጥን ሊያስከትል ይችላል። ይህ ደግሞ በጊዜ መታከም ያስፈልገዋል። 6. እምብርት አካባቢ እብጠት መኖር አለመኖሩን ማየት አንዳንድ ጊዜ በተፈጥሮ የእትብት መነሻ የነበረው የእንብርት አካባቢ የሆድ እቃ ግድግዳ በመሳሳቱ ምክንያት አንጀት ወደውጪ በመውጣት የእንብርት እብጠትን ያስከትላል። ይህን ካስተዋሉ የልጅዎን ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል። 7. ልጁ ጡት ሲጠባ የሚያልበው እና ትንፋሽ የሚያጥረው መሆን አለመሆኑን ማየት አንድ ጨቅላ ህፃን ጡት ሲጠባ የሚያልበው ፣ ትንፋሽ እያጠረው መጥባቱን የሚያቋርጥ ከሆነ እና ከንፈሩ የሚጠቁር ከሆነ ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ የልብ ወይም የአፍንጫ ውስጥ ችግር ሊሆን ስለሚችል በጊዜ የልጅዎን ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል። 8. የጠባው በሙሉ የሚያስመልሰው ከሆነ እና ምራቁ (ለሀጩ ) ከመጠን በላይ በአፉ በኩል የሚዝረበረብ ከሆነ አዲስ የተወለደ ህፃን በተወለደ በ 30 ደቂቃ ውስጥ ጡት መጥባት መጀመር አለበት። ነገር ግን ከጠባ በኋላ የጠባው ሁሉ የሚመለስ እና የሚወጣ ከሆነ ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ የሚከሰት የጨጓራ ወይም የአንጀት መስመር ችግር ሊሆን ስለሚችል ሂወቱ አደጋ ላይ ከመውደቁ በፊት በጊዜ የልጅዎን ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል። 9. የጠባው ሲያስመልሰው ቢጫ ወይም አረንጓዴ ፈሳሽ የሚቀላቀል ከሆነ አንድ ጨቅላ ህፃን ሲያስመልሰው ሀሞት የመሰለ አረንጓዴ ወይም ቢጫ ከሆነ ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ የሚከሰት የአንጀት መዘጋት ፣ መጥበብ ወይም መታጠፍ ችግር ሊሆን ስለሚችል ጊዜ ሳይሰጡ በቶሎ የልጅዎን ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል። 10. በተወለደ በመጀመሪያ 24ሰአት ውስጥ ምንም ዳይፐር የማያረጥብ ከሆነ ወይም በጊዜ ሂደት የሚያረጥበው የዳይፐር ቁጥር ትንሽ ከሆነ ይህ ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ የሽንት መስመር ችግር ወይም የኩላሊት አፈጣጠር ችግር ሊሆን ስለሚችል ኩላሊቱ ላይ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ጊዜ ሳይሰጡ የልጅዎን ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል። ✍️ ዶ/ር ዮናታን ከተማ በቅዱስ ፓውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ቀዶ ህክምና ሬዚደንት ሀኪም ምንጭ : ሀኪም page

iCare MC የማህጸን እና ጽንስ ሐኪም ከህጻናት ሐኪም ጋር በመሆን ያዘጋጁት አስተማማኝ መረጃ #0964407777 Android: https://play.google.com/store/apps/details?
iCare MC የማህጸን እና ጽንስ ሐኪም ከህጻናት ሐኪም ጋር በመሆን ያዘጋጁት አስተማማኝ መረጃ #0964407777 Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icaremc.app iPhone: https://apps.apple.com/jp/app/icare-mc/id6782706843?l=en-US

🔢የእርግዝናን ሳምንት እንዴት ማስላት ይቻላል? iCare MC የማህጸን እና ጽንስ ሐኪም ከህጻናት ሐኪም ጋር በመሆን ያዘጋጁት አስተማማኝ መረጃ #0964607777 የመውለጃ ቀን ግምት እንዴት ማስላት ይቻላል የሚለውን መልስ በዚሁ መተግበሪያ ያገኛሉ Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icaremc.app iPhone: https://apps.apple.com/jp/app/icare-mc/id6782706843?l=en-US

🤰👶🧒 iCare MC – ከእርግዝና እስከ ጉርምስና! 💚 ልጆቻችን በትክክል እያደጉ ነው? የሚለውን ጥያቄ በጊዜው መልስ እናገኝ። 📏 ክብደትና ቁመት 🗣️ የንግግር እድገት 🧠 የአስተሳሰብ እድገት 🤝 የተግባቦትና ማህበራዊ ክህሎት 🌱 የጉርምስና ደረጃ የልጅዎን የትውልድ ቀን በማስገባት እና የልጅዎን መረጃ በየጊዜው በመመዝገብ፣ እድገቱን በተከታታይ ይከታተሉ። 🔐 💉 ከክትባት በኋላ የተለካውን ክብደትና ቁመት ይመዝግቡ። 👨‍👩‍👧‍👦 በአንድ መተግበሪያ ከአንድ በላይ ልጆችን ይከታተሉ። 👩‍⚕️ ሲያስፈልግዎት ስፔሻሊስት ሐኪሞችን ያማክሩ! የማህፀንና የጽንስ፣ የሕፃናት ሕክምና፣ የሕፃናት ኩላሊት፣ ልብ፣ ሳንባ እና የነርቭ ሥርዓት ስፔሻሊስቶችን በiCare MC ማማከር ይችላሉ። 📱 iCare MC በGoogle Play Store እና App Store ላይ ያግኙ! 💚 የiCare MC ቤተሰብ ይሁኑ! እድገትን በጊዜው እንከታተል፤ ልዩነትን በጊዜው እንወቅ፤ ተገቢውን እርምጃ እንውሰድ። 📞 0964 407 777 / 0964 507 777 📲 Download Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icaremc.app iPhone: https://apps.apple.com/jp/app/icare-mc/id6782706843?l=en-US

#iCare MC በዚህ link https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icaremc.app አይ ኬር ኤም ሲ መተግበሪያ (iCare MC app) ከplay store አውርዳችሁ ወይም install አድርጋችሁ የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም ካላችሁበት ሆናችሁ አሁኑኑ ማማከር ትችላላችሁ # ብልህ ወላጅ ለልጁ ጤና ቅድሚያ ይሰጣል!! # iCare MC ለተሻለ ጤና!!

👉ባዲሱ አመት ለልጆ ምን ሊያደርጉ አስበዋል!! እድገታቸውን ማረጋገጥ ካሉ ትክክለኛ ውሳኔ ወስነዋል!! ጤናማ እድገት የሚጀምረው የልጆን ጤና በማወቅ ነው!!! ካሉበት ሆነው የልጆን አካላዊ እድገት፤ቋንቋ፤ አስተሳሰብ፤ ማህበራዊ እና የተግባቦት እድገት ደረጃ ይገምግሙ  https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icaremc.app ይህንን ሊንክ በመጫን መተግበሪያውን ያውርዱ  አባል ይሁኑ! የልጆን የተወለዱበትን ቀን ያስገቡ ፤ ለእድሜያቸው የሚጠበቀውን መድረሳቸውን ይገምግሙ በአጭር ፅሁፍ እኛን ያማክሩ ክብደት እና ቁመት ይመዝግቡ መግበሪያው ውስጥ ያስቀምጡ ከሳምንት ከወር፤ ከዓመት፤ በኃላ ያለውን ልዩነት ይመዝግቡ ይገምግሙ ያማክሩ ልጆን ክትትል ከIcare Mc እስፔሻሊስት ሃኪሞች ጋር ያድርጉ ጤናማ እድገት የሚጀምረው የልጆን ጤና በማወቅ ነው!!! ከ0-18ዓመት ላሉ ልጆች እስፔሻሊስት ሃኪሞች በጥምረት!! ለበለጠ መረጃ 0964407777 https://t.me/DRPGO

🔥የተባባሰው እጥረት እና እጦት የሚያስከትለው የጤና ችግር ቤት ውስጥ ቤንዚን ወይም ናፍጣ ማስቀመጥ በተለይ ለእርጉዝ እናቶች፣ ለአዲስ የተወለዱ ህፃናት፣ ለልጆች ከፍተኛ የጤና ችግር ያመጣል። እነዚህ ነገሮች ቢዘጉም እንኳ ጎጂ ጭስ (vapors)  በመልቀቅ አየሩን ይበክላሉ። 1. እርጉዝ እናቶች -የፅንስ መጥፋት (miscarriage) ወይም -ዝቅተኛ  ክብደት ሊያመጣ ይችላል 2. ለአዲስ የተወለዱ ሕጻናት እና ልጆች -የመተንፈሻ ችግር፣ -የደም ካንሰር -በስህተት መጠጣት (poisoning) አደጋ 3. አጠቃላይ አደጋ -እሳትና ፍንዳታ አደጋ -በየትኛውም እድሜ ክልል -ረጅም ጊዜ ተጋላጭነት የደም ችግርና የደም ካንሰር (leukemia ) ያመጣ  እንዲሁም የቤት ውስጥ አየርን በመበከል የመተንፈሻ አካል ችግር ያስከትላል  👉የደህንነት ምክር ቤንዚን እና ናፍጣ በቤት ውስጥ በምንም ምክንያት መቀመጥ የለባቸውም:: 👉በአሁኑ ጊዜ የተባባሰውን የነዳጅ እጦት ተከትሎ አግባብነት የሌለውን ትርፍ ለማግኘት ቦታውን ትቶ በየቤቱ የገባውን ቤንዚን እና ናፍጣ ለጤና ጠንቅ መሆኑ ለህብረተሰቡ በማስተማር ጤናውን እንዲመርጥ እና ከዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩትን የሚመለከተው አካል እንዲቆጠቡ በማድረግ የህዝቡንም ደህንነት ለመጠበቅ ዘላቂ እርምጃ ቢወሰድ መልካም ነው እላለሁ :: አመሰግናለሁ ቸር እንሰንብት ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት share ያድርጉ በዶ/ር ትዕግስት አርጋው የህፃናት ህክምና እስፔሻሊስት የእናቶችንና የህፃናትን ጤናን  ከታች ባለው link ይቀላቀሉ ! ቤተሰብ ይሁኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ቴሌግራም- t.me/DRPGO 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 Facebook- fb.me/drtigist

አዲስ የወለድሺውን ልጅ ገላውን አትጠቢዉ:: ጥያቄ: አዲስ የወለድኩትን ልጅ መቼ ማጠብ ልጀምር? ✅️መልስ: ከተወለደ 24 ሰዓት ሲሞላው ምክንያት:- የሰውነቱን ሙቀት ለመጠበቅ ይረዳዋል:: 🟢vernix caseosa (አዲስ የተወለደ ህፃን ቆዳ ላይ የሚገኝ ነጭ ለስላሳ ሽፋን) ሳይለቅ አንዲቆይ ይረዳል:: 🟢አንቺም ቢሆን 24ሰዓት ሳይሞላዉ ለማስለቀቅ አትሞክሪ:: ጥያቄ : መቼ መቼ ልጄን ልጠብ? ✅️መልስ: አንድ ቀን እያለፍሽ እጠቢ ምክንያት: ቶሎ ቶሎ ማጠብ የሚያመጣውን የቆዳ መድረቅ እና የቆዳን በሸታ የመከላከል አቅም ከመቀነስ ይከላከላል:: ጥያቄ : ልጄን እንዴት አድርጌ ልጠብ? ✅️መልስ: ልጅሽ እትብቱ አስኪወድቅ ድረስ sponge bath (በገላ ማጠቢያ ስፖንጅ/ምቹ ጨርቅ) ከወደቀ በኈላ ደሞ Tub bath(በገንዳ ዉስጥ) አድርገሽ እጠቢው:: 🟢አንገቱን እና ጭንቅላቱን መደገፍ አትርሺ ጥያቄ : ልጄን በምን ልጠበው? ✅️መልስ: በዉሃ ብቻ ማጠብ ብዙ ጊዜ በቂ ነው 🟢የልጅሽ ቆዳ ደረቅ ሚባለው አይነት ከሆነ ግን: ሸታ የሌለው እና ለልጅሽ ሚስማማውን ሳሙና (እንደቆዳው አይነት ስለሚለያይ) መርጠሽ ተጠቀሚ:: Dr. Habtamu S. Mengistu,Pediatrician Telegram: t.me/HakimEthio

ተወዳጅ ተፈላጊ እና የረጅም አመት ልምድ ያካበቱ የህፃናት ህክምና ባለሙያዎችን በ አንድ ማእከል! - የጨቅላ ህፃናት ህክምና - የህፃናት የተመላላሽና የ24 ሰአት የድንገተኛ ህክምና - የህፃናት ከአ
ተወዳጅ ተፈላጊ እና የረጅም አመት ልምድ ያካበቱ የህፃናት ህክምና ባለሙያዎችን በ አንድ ማእከል! - የጨቅላ ህፃናት ህክምና - የህፃናት የተመላላሽና የ24 ሰአት የድንገተኛ ህክምና - የህፃናት ከአንገት በላይ ህክምና - የህፃናት የካንሰር ህክምና - የህፃናት የነርቭ እና የአእምሮ ህክምና - የህፃናት የኩላሊት ህክምና - የህፃናት የቆዳ ህክምና - የህፃናት ቀላል እና ከባድ ቀዶ ህክምና - የህፃናት የአጥንት ህክምና - የህፃናት የልብ ህክምና - የህፃናት ተላላፊ በሽታዎች ህክምና - የህፃናት የሳምባ እና የመተንፈሻ ኣካላት ህክምና - የክትባት አገልግሎት - የህፃናት የደምና ተያያዥ ህምሞች ህክምና - የህፃናት ፅኑ ህሙማን ህክምና... Contact Us +251946888883 / 011 553 2760 t.me/LANCETMCH Signal to 22 road, 200m before reaching the flyover bridge ከሲግናል ወደ 22 በሚወስደው መንገድ ድልድዩ ጋር ከመድረሶ በፊት Lancet Women & Children Hospital ላንሴት የሴቶችና የልጆች ሆስፒታል

Exceptional Pediatric Care at Lancet Women and Children Hospital! Our Pediatric team is composed exclusively of top pediatric specialists and subspecialists - the best of the best in their fields. From general pediatrics to advanced subspecialties like Cardiology, Neurology, Pulmonology, Nephrology, Neonatology, Orthopedics, ENT, Dermatology, Hematology and Oncology, our doctors have extensive expertise to handle even the most complex cases. Our advanced Neonatal intensive care units, ICU, Pediatric emergency services, and Pediatric surgery capabilities ensure we can meet all of your child's healthcare needs. As a leading pediatric destination, Trust your child's care to our exceptional team at the Lancet Pediatric Department. Contact Us +251946888883 https://t.me/LANCETMCH 📍Signal to 22 road, 200m before reaching the flyover bridge 📍ከሲግናል ወደ 22 በሚወስደው መንገድ ድልድዩ ጋር ከመድረሶ በፊት Lancet Women & Children Hospital ላንሴት የሴቶች እና የልጆች ሆስፒታል