fa
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

رفتن به کانال در Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

کانال ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 19 949 مشترک است و جایگاه 1 157 را در دسته پزشکی و رتبه 1 681 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 19 949 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 27 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -557 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -23 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 26.07% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 6.79% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 5 203 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 354 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 10 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 28 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته پزشکی تبدیل کرده‌اند.

19 949
مشترکین
-2324 ساعت
-1257 روز
-55730 روز
آرشیو پست ها
✅ የኪንታሮት መንስኤና መፍትሄዎች (ህክምና) ✅ ይህ መረጃ በዚህ ችግር ለሚሰቃዩ ሰዎች ይደርስ ዘንድ በቅድሚያ ሼር ብታደርጉትና ወደ ንባብ ብትገቡ ደስ ይለናል፡፡ መልካም ንባብ… የቂጥ ኪንታሮት ሠገራን በምናስወገድ ጊዜ ከማማጥ ወይንም በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት የደም ስሮች ላይ የሚገኝ ግፊት ምክንያት የሚመጣ ሲሆን በሁለት መልኩ ይከፈላል፡፡ 🌀👉1, ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoid) በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ 🌀👉2, ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoid) በላይኛው ቆዳ ላይ የሚገኝ ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰት ሲሆን በተለይ ዕድሜያቸው 50 ዓመት የሞላቸው ሰዎች ላይ በስፋት (ግማሽ በሚሆን ደረጃ) የኪንታሮት ምልክቶች እንደሚያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ በቤት ውስጥ ሕክምና እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ በማድረግ ይድናሉ፡፡ ✅ ኪንታሮትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች 👉 ሠገራን ሲያስወግዱ ለረጅም ጊዜ ማማጥ 👉 ለረጅም ሰዓታት በመፀዳጃ ቤት መቀመጥ 👉 የሆድ ድርቀት (ለረጅም ጊዜ የቆየ) 👉 ከመጠን ያለፈ ውፍረት 👉 ዕርግዝና 👉 የፋይበር መጠኑ የቀነሰ ምግብ መመገብ ናቸው 👉 በዕድሜ መጨመር ቬይኖችን የሚደግፉ የሰውንት ክፍሎች እንዲደክሙ ስለሚያደርግ ለሄሞሮይድ ያጋልጣል፡፡ ✅ የኪንታሮት ምልክቶች 👉 ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደም 👉 በሰገራ መውጫ አካባቢ ማሳከክ 👉 ሕመም ወይንም አለመመቸት 👉 በፊንጢጣ አካባቢ እብጠት ናቸዉ፡፡ ✅ ሃኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው? 👉በፊንጢጣ የሚወጣ ደም የኪንታሮት የተለመደ ምልክት ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች የሕመም ዓይነቶች እንደ ኮሎሬክታል ካንሰር እና ሌሎች የህመም አይነቶች ጋር ተመሳሳይ ምልክት ሊኖረው ስለሚችል ሄሞሮይድ ነው በሚል ግምት ችላ ሊባል አይገባም፡፡ ስለዚህም ወደ ሐኪም በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ 👉ከፍተኛ ሕመም የሚሰማዎ ከሆነ እና በቤት ውስጥ የሕክምናዎች ለውጥ የማያገኙ ከሆነ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይገባዎታል፡፡ 👉ከፍተኛ መጠን ያለው ደም መፍሰስ ካጋጠምዎ እና እንዲሁም ራስ የማዞር የመሳሰሉት ስሜት ከተሰማዎ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡ ✅ ኪንታሮት የሚያስከትለው ተያያዥ ጉዳቶች ምንድን ናቸዉ? 👉 አኒሚያ (የደም ማነስ) ከፍተኛ የሆነ ደም በሚፈስ ጊዜ በሰውነታችን ውስጥ ኦክስጂን ተሸካሚ ቀይ የደም ሴሎች መጠን ስለሚቀንስ የድካምና ራስ የመሳት ሁኔታዎችን ያስከትላል፡፡ 👉 ለውስጣዊ ሄሞሮይድ የሚደርሰው የደም ፍሰት መጠን ሲቀንስ ከፍተኛ የሆነ ሕመምን ያስከትላል፡፡ ይህም ለሴሎች መሞት እና ለጋንግሪን ይዳርጋል፡፡ ✅ በቤት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎችና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች 👉 ለብ ባለ ውሃ ከ10 – 15 ደቂቃ በቀን በቀን ሁለትና ሶስት ጊዜ መዘፍዘፍ 👉 ሁሌም ከተፀዳዱ በኋላ በሚገባ በንፁህ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ 👉 ደረቅ የሆነ የመፀዳጃ ወረቀትን አለመጠቀም 👉 እብጠት እንዲቀንስ በረዶን መጠቀም 👉 ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መጠቀም ከላይ የተጠቀሙትን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሄሞሮይድን ማጥፋት የሚቻል ሲሆን ሕመም የሚያብስ ከሆነ እና ምንም ዓይነት ለውጥ በሳምንት ውስጥ ካላገኙ ወደ ሕክምና ቦታ እንዲሄዱ ይመከራል፡፡ ✅ ሄሞሮይድን ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባል? 👉 በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር - አትክልት፣ፍራፍሬዎችን መመገብ ሠገራን በማለስለስ ማስማጥ እንዳይኖር ያድርጋል፡፡ 👉 ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ - በቀን ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃን ወይም ጭማቂን መውሰድ 👉 ማስማጥን ማስወገድ - ሠገራን ለማስወጣት በምናምጥ ጊዜ በደም ስሮቻችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ግፊትን ስለምንፈጥር ለሄሞሮይድ/ለኪንታሮት/ ተጋላጭንት ይጨምራል፡፡ 👉 ሠገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያልፉ ወደ መፀዳጃ ቤት በመሄድ ያስወግዱ፡፡ አለዚያ ሠገራዎ ስለሚደርቅ ለማስወገድ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ 👉 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያዘውትሩ - የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ጤናማ እንድንሆን ያደርጋል፣ 👉 ለረጅም ሰዓታት መቀመጥን ያስወግዱ፡፡ በተለይም በመፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ለሄሞሮይድ መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

✍ #በተደጋጋሚ #ሽንቶ #እየመጣ #ተቸግረዋል? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ማለት ጤናማ ከሚባለዉ ከሽንት መምጫ ጊዜ በበለጠ በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ሲኖር ማለት ነዉ፡፡በተድጋጋሚ ሽንት መሽናት ስራዎን እንቅልፍዎን እና አጠቃላይ ሰላምዎን ሊያስተጓጉል ይችላል፡፡ ስለዚህም የዚህን ችግር መነሻ እና ህክምናዉን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነዉ፡፡ 👉 #መንስኤ 📌 የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን 📌 የስኳር ህመም 📌 እርግዝና 📌 የፕሮስቴት እጢ ችግር 📌 ሽንት የሚያሸኑ መድሀኒቶች መጠቀም 📌 የነርቨ ችግር 📌 የኩላሊት በሽታ 📌 አንዳንድ ለካንሰር የሚሰጡ ህክምናዎች 📌 የሽንት መጠንን የሚጨምሩ ንጥረ ነገሮች እና መጠጦች 👉 #መፍትሄ 📌 በቀን ከ 8-10 ብርጭቆ ውሀ መጠጣት 📌 የሽንት መጠንን የሚጨምሩ እንደ ካፌን እና አልኮል ያሉ ንጥረ ነገሮችን መቀነስ 📌 ሽንቶዎን አለመቋጠር 📌 ወደ መኝታ በሚሄዱ ጊዜ ፈሳሽ ነገሮችን አለመጠቀም 📌 ለዳሌ አጥንት የሚረዱ እንቅስቃሴዎችን መስራት 👉👉#በተደጋጋሚ ሽንቶ እየመጣ ተቸግረዋል!! ይህን እና ተያያዥ የሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ያሎትን ጥያቄዎች ለማቅረብ ወደ 8809 ይደውሉ ከባለሙያ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ! (#በጤና # ባለሙያ# ስጦታ )

ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት በራሳችን ልናደርግ የምንችላቸዉ፡፡ 👇 ማድረግ የሚገባ -------------------- #ቋሚ የመተኛ ሰዓት መመደብ #ቋሚ የመነሻ ሰዓት መመደብ (አእምሮአችን መደበኛ የሆነ የእንቅልፍ ፕሮግራም እንዲይዝ ያደርጋሉ ፡፡) #የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ (ጠዋት ጠዋት ቢሆን ይመረጣል ) #እራት በጊዜ መመገብ ( ከመተኛት ሶስት-አራት ሰዓት ቀደም ብሎ ) #መኝታ ክፍልን ብርሀን ያልበዛበት፣ ጸጥተኛና ቀዝቀዝ ያለ ማድረግ ማድረግ የሌለብን 👇 #አልጋ ላይ ሆኖ ስልክ ማወራት፤ ቻት ማደረግ #አልጋ ላይ ሆኖ ቲቪ ማየት፣ ሬዲዮ ማዳመጥ #አነቃቂ ነገሮች አመሻሽ ላይ መጠቀም #አልኮል መዉሰድ (ለአጭር ጊዜ የሚረዳ ቢመስልም ከጊዜ በኃላ የተቆራረጠ እንቅልፍ ያስከትላል ፡፡) ከላይ የተዘረዘሩት ቀላል ዘዴዎች ስለሆኑ የማይሰሩ ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ የእንቅልፍ ችግር ያለባቸዉን ሰዎች ያለ መድኃኒት ጥሩ እንቅልፍ እንድተኙ ረድተዋል፡፡ ከእንቅልፍ ጋር ተያይዞ ህክምና የሚያስፈልጋቸዉ 👇 -ከላይ የተጠቀሱትን አድርገን አሁንም በቂ እንቅልፍ የማናገኝ ከሆነ - ተያያዞ የድብርት ስሜት የሚሰማ ከሆነ -ተያይዞ ጭንቀት ካለ -በአጠቃላይ የእንቅልፍ ችግሩ በሥራችን ወይም በማህበራዊ ህይወታችንን ላይ ተፅኖ ካሳደረ። አንድ ሶስተኛ ስንንከባከብ ሁለት ሶስተኛው ላይ የበለጠ ውጤታማ መሆን እንችላለ ለምን የሙከራ ስራውን ዛሬ አንጀምርም።መልካም አዳር

መካንነትን እንደት መከላከል ይቻላል? በተለይ በሴቷ በኩል? • ጤናማ የአኖኖር ዘይቤን መከተል • ከፍተኛ የአካል እንቅስቃሴን መተው • አነቃቂ መጠጦችን መቀነስ • አልኮልን መተው ወይም መቀነስ • አለማጤስ • የተመጣጠነ ምግብ • አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ • ክብደትን ማመጣጠን • የተለያዩ በሽታዎች ካሉ መታከም • ስኳር ህመም ካለ መታከም • የታይሮድ መጠን አነስተኛ ወይም ከፍተኛ መሆነ ለማስተካከል መሞከር • እራስን ከአባላዘር በሽታ መጠበቅ። ካለ ፈጥኖ መታከም • ሳይዘገዩ ለማርገዝ መሞከር • የጤና ምርመራ በየጊዜው ማድረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ስለመካንነትና ህክምናው ማወቅ ይፈልጋሉ? እንግዳውስ ይሄው ብለናል። ግን ግን ሸር ማድረጉን አደራ! (መካንነት ወይም መፀነስ አለመቻል) • ይህ ችግር Infertility ከፍ ሲልም sterility እየተባለ ይጠራል። Infertility በተለያየ ምክናየት መፀነስ ማርገዝ አለመቻል ቢሆንም የተለያዩ ህክምናዎችን በማግኝት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል። Sterility ግን ፈፅሞ የመፀነስ እድል አለመኖርም ሲሆን ይህ አይነት ችግርም የመፈጠር እድሉ በጣም አነሳ ነው። ውድ ስለጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀት ቤተሰቦችና ተከታታዮች ዛሬ ካላይ የጠቀስኩትን ርዕስ ጠቅለል አድርጌ መካንነት በሚል እርስ ዙሪያ ይጠቅማል ያሉኩትን አጠር ያለ፡ ግልፅና አስተማሪ የሆነ መረጃ እንሆ ብያለሁ። ይህን መረጃ ከወደዱት ቢያጋሩት የብዙዎችን ጭንቀት እንደሚቀርፍ አልጠራጠርም። • አንድት እናት እድሚዋ ከ35 አመት በላይ ከሆናትና ለአድ አመት ያህል የመውለድ ሙከራ አድርጋ ካልተሳካ መከነች (ማርገዝ አትችልም) እንላለን። መፀነስ እንኳ ብትችል እድገት መጀመርና መቀጠል ካልቻለም እንድሁ የማርገዝ ችግር እንዳለባት ይቆጠራል። • እንደሚታወቀው እርግዝና ሂደት ነው። ደረጃ በደረጃ የሚከወን። ሴቷ ካሏት ሁለት ኦቫሪ (እንቁላል መፈጠሪያና ማደጊያ ክፍል) በየወሩ እንቁላል ትለቃለች። ይህ የሚሆነው የወር አበባ ማየት በጀመረች በ14ኛው ቀን ነው። በመቀጠል የምትለቀቀው እንቁላል ፊምብሪያ (የማህፀን ጣት) በሚባል የማህፀን ከፍል በመነጠቅ fallopian tube (የማህፀን ክንፍ) በሚባለው የማህፀን ክፍል ላይ ማለፍ ይጠበቅባታል። እዚሁ ክፍል ላይም የወንድ የዘር ፍሬ ደርሶ ውህደት መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። በመቀጠል እቡጡ(zygote) ወደ ማህፀን ዋና ክፍል ወይም ሆድ ክፍሉ Endometrium (የማህፀን የውስጠኛ ክፍል) ላይ መቀመጥና እድገት መጀመር ይጠበቅባቸዋል። • እንግድህ መካንነት(ማርገዝ አለመቻል) የሚፈጠረው ከላይ ከዘረዘርናቸው ሄደቶች ወይም ክንውኖች አንዱ ወይም ሁለት ሶስቱ ሳይካሄድ ሲቀር ነው። በአጭሩ ችግሩ ከእንቁላሏ ጤንነት ወይም ከዘር ፍሬ ጤንነት አለያም ከጉዞአቸው መደናቀፍ ወይም ከቦታው አለመመቸት ጋር የተያያዘ ነው። • የመካንነት ምክናየት ከሴቷ ወይም ከወንዱ ችግር ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሁለቱም። 1/3ኛ የሴቷ፡ 1/3ኛ የወንዱ፡ ቀሪው 1/3ኛ የሁለቱም ወይም የማይታወቅ ምክናየት ነው። በወንዶች በኩል የሚመጣው ችግር ከምን ጋር ሊያያዝ ይችላል? • Varicocele የሚባል ችግር ቀዳሚ ነው። ይህ ችግር ቀጫጭን የደም ቱቦዎች ተፈጥረው(viens) ከዘር ፍሬ የሚነሱ ስለሆኑ ያብጡና ትላልቅ ይሆናሉ። ይህም የዘር ፍሬ ለከፍተኛ ሙቀት ያጋልጠውና ውጤታማ እንዳይሆን ያደርገዋል። • የዘር ፍሬ ቅርፅ መበላሸት፡ በቁጥርና መጠን ማነስ • እንቅስቃሴው ዘገምተኛ ወይም ደካማ መሆን • የተለያዩ አካላዊ ጉዳት ወይም አደጋ ማጋጠም • አልኮል ጠጭ መሆን • የተለያዩ መድሀኒቶችን ተጠቃሚ መሆን • መርዛማ ለሆኑ ነገሮች መጋለጥ • ማጤስ • የኩላሊት ችግር • የሆርሞን መዛባት • የካንሰር ህክምና • እርጅና በሴቶች በኩል የሚመጣ ችግር ከምን ጋር ሊያያዝ ይችላል? • ብዙ ጊዜ በሴቶች በኩል የሚፈጠረው ችግር በኦቩሌሽን ወቅት የሚፈጠር ነው። እንቁላልን መልቀቅና አለመልቀቅ ጋር ይያያዛል።ኦቩሌሽን ፔሪድ ማለት የወር አበባ ማየት ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ሲቆጠር 14ኛዋ ቀን ነች። ይች ቀን እንቁላል የምትለቀቅባትና ለፅንስ ዝግጁ የምትሆንባት ቀን ነች። ስለዚህ በዚህ ቀን እንቁላል ካልተለቀቀ ፅንስ አይፈጠርም። የዚህ ምልክቱ ደግሞ የወር አበባ መዛባት አንዳንድ ጊዜም ፈፅሞ አለመኖር ነው። • እንቁላል ካለችበት ቦታ (ከኦቫሪ) እንዳትወጣ የሚያደርጋት ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ዋናዋናዎቹ ግን ትናንሽ እጢ መሳይ ነገሮች በኦቫሪ ውስጥ መፈጠራቸውና ኦቫሪ ከ40 አመት ቀድሞ ስራውን ሲያቆም ነው። • ሌላው ብዙ የተለመደ ባይሆንም የማህፀን ቀኝና ግራ ክፍሉ (ክንፍ) በተለያየ መንገድ በመዘጋቱ እንቁላሏ ከዘር ፍሬ ጋር እንዳትገናኝ በማድረጉ ሊሆን ይችላል። ይህ ችግር የዳሌ አጥንት ዙሪያ ኢንፌክሽን፡ ኢንዶሜትሪዎሲስና ከማህፀን ውጭ በተፈጠረ ፅንስ ሊከሰት ይችላል። • በተጨማሪም ማንኛውም በማህፀንና በኦቫሪ ውስጥ የሚፈጠር ችግርና የሚያድግ እጢ ምክናየት ይሆናል። ሴቶች እርግዝናቸውን እንድያጡ ወይም መካን ሆነው እንድቆዩ የሚያደርጉ ሌሎች አጋላጭ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው። • እድሜ • ጭንቀትና ውጥረት • ያልተመጣጠነ ምግብ • የሩጫ ልምምዶች • ከመጠን በላይ መወፈር • ከመጠን በታች መቅጠን • ማጤስ • ከመጠን ያለፈ መጠጥ • የአባላዘር በሽታ • የተለያዩ የጤና ችግሮን ለምሳሌ እጢ፡ የኦቫሪ ስራ ማቆም፡ የሆርሞን ችግርና ሌሎችም። • እርጅና/ እድሜ መጨመር ይህም በቂ እንቁላል አለማምረት፡ አነሳ እንቁላል መልቀቅ፡ ጤናማ እንቁላል አለመኖርና ሌሎችም ናቸው። ®በነገራችን ላይ አንድት ሴት እድሜዋ 30ን ካለፈ በየአመቱ የማርገዝ እድሏ በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል። ስለዚህ ሴቶች እድሜአችሁን ሳትገድሉ እንድትወልዱ ይመከራል። እድሜ አሳልፎ የመጣ ርግዝና ሌላም ሌላ ችግር አለውና። ይህ ማለት ግን ማንኛዋም በእድሜ የገፋች ሴት ለመውለድ ትቸገራለች እያልን አይደለም። የመካንነት ህክምና ምንድን ነው? • ነፃ ሆኖ ጊዜ መስጠት ይጠበቃል። ውጤታማ ህክምናም አለው። 1. የመጀመሪያው ለእርግዝና ወሳኝ በሆኑ ወቅቶች የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ እንድችሉ ማድረግ ነው። ይህም ችግሩ ከምን እንደሆነ ለማወቅ ያግዛል። ለምሳሌ የማይዛባ የወር አበባ ኡደት ላላት ሴት የሚከተለውን ምሳሌ እንይ። ለምሳሌ ወይዘሮ ከበቡሽ የወር አበባዋ በ18/09/12 መምጣት ቢጀምር ዛሬ ማለት ነው። ደግሞም በየ28 ቀኑ የሚመጣ ወጥ ከሆነ፡ 02/10/12 ቀን ኦቩሌሽን ፔሬድዋ ነው። ከበቡሽ ማርገዝ ከፈለገች በሚከተሉትን ቀናት የግብረስጋ ግንኙነት መፈፀም ይኖርባታል። 29/09/12, 30/09/12, 01/10/12, 02/10/12, 03/10/12, 04/10/12 እና 05/10/12 ዓ.ም. ከበቡሽ ምንም አይነት ችግር ከሌለባት የትዳር አጋሯም ጤናማ ከሆነ እነዚህን ቀናት ሳትፀንስባቸው ልታልፍ አትችልም። በተለይ 02/10/12 ዓ.ምን። 3እጅ መካንነትም ከዚህ አለመመጣጠን ጋር የተያያዘ ነው። 2. የተለያዩ መድሀኒቶችን በመጠቀም መካንነትን ማከም ይቻላል። ለምሳሌ Clomphene እና Serophene ውጤታማ ናቸው። መካን ነን ከሚሉ ግማሽ ያህሎቹ ሴቶች በClomphene መድሀኒት ውጤት ያመጣሉ። (እንድያረግዙ ያደርጋቸዋል)። ይህን መድሀኒት የተጠቀመች ሴት መትያ ልጆችን የመውለድ እድሏን ይጨምራል። 3. የተዘጋ የማህፀን ክፍልን በቀዶ ጥገና በመክፈት እንቁላሏና የዘር ፍሬ በቀላሉ እንድገናኙ በማድረግ ይታከማል። 4. የዘር ፍሬ እንቅስቃሴ ደካማ ከሆነ ከወንዱ ወስዶ ሴቷ ውስጥ በመሳሪያ በመጨመር የዘር ፍሬዎቹ በራሳቸው እንድገናኝ በማድረግ ይታከማል። 80% ውጤታማ ነው። 5. ከላይ ያለው ካልተሳካ በኦቩሌሽን ወቅት ስፐር ሴሉን በመውሰድ ከእንቁላሏ አጠገብ በማስቀመጥ ይታከማል። እጅግ ውጤታማ ነው። 6. ከላይ ባሉት እንደ አጋጣሚ ባይሳካ በውጮቹ ዘንድ እንቁላልንና የዘር ፍሬን ውጭ ላይ በማሽን ውስጥ በማገናኝት ውህደቱን በመፍጠር የመጨረሻው ህክምናም ይሞከራል።

5ቱን የጉበት ገዳይ በሽታዎች እናስተዋውቃችሁ ሂፐታይተስ የጉበት ብግነት ነው፡፡ የብግነቱ ሁኔታ በጉበት ላይ ጠባሳ ሊፈጥር ወይም ጉበትን ሊያኮማትር ወይም ደግሞ ካንሰር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ለሂፐታይተስ መፈጠር ሂፐታይተስ ቫይረስ ዋነኛ ምክንያት ሲሆን ሌሎች ኢንፌክሽኖች እና መርዛማ ነገሮች ማለትም አልኮልና የተወሰኑ መድኃኒቶች እንዲሁም የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከያ አቅም አዳካሚ በሽታዎች ለሂፐታየተስ መፈጠር ተጠቃሽ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት አምስት ዓይነት የሂፐታየተስ ቫይረሶች እያንዳንዳቸው አምስት የሂፐታየተስ በሽታዎችን ያስከትላሉ፡፡ ሂፐታየተስ ኤ፣ቢ፣ሲ፣ዲ እና ኢ በሽታዎች በመላው ዓለም ለብዙዎች ሕመምና የሞት ምክንያት ናቸው፡፡በተለይ ሂፐታየተስ ቢ እና ሲ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች በጉበት መኮማተርና ካንሰር ተጠቅተው ወደ ሞት የሚወስዱ አደገኛ በሽታዎች ናቸው፡፡ ሂፐታይተስ ኤ ቫይረስ ( ኤች ኤ ቪ) 1. ሂፐታይተስ ኤ ቫይረስ የሚገኘው በተበከለ ሰው አይነምድር ውስጥ ሲሆን ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በአይነምድር የተበከለ ምግብ ወይም ውሀ በምንወስድበት ጊዜ ነው፡፡ 2. የተወሰነ የግብረስጋ ግንኙነት ይህን ቫይረስ ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ 3. የንፅህና ጉድለት ባለባቸው የዓለም ክፍሎች በስፋት ይህ ቫይረስ የሰዎችን ሕይወት እየነጠቀ ይገኛል፡፡ 4. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት በየአገሩ ይሰጣል፡፡ ሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ (ኤች ቢ ቪ) 1. ቫይረሱ የሚተላለፈው በደም፣በስፐርም እና በሌሎች ፈሳሽ ነገሮች ነው፡፡ 2. ሌላው የቫይረሱ መተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተጠቃች እናት በምትወልድበት ጊዜ ወይም ህፃናት በልጅነት ጊዜያቸው በቫይረሱ ከተጠቃ የቤተሰብ አባል ሊሆን ይችላል፡፡ 3. በቫይረሱ የተበከለ ደምና የደም ተዋሀፆ በመስጠት ወይም በማስተላለፍ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 4. በሕክምና ወቅት በቫይረሱ የተበከ መርፌ በመጠቅም አንዱ መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡ 5. በመርፌ በሚወሰዱ አድገኛ መድኃኒቶችና እፆች አጠቃቀም ወቅት ሌላው መተላለፊያ መንገድ ሲሆን በተለይ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጥንቃቄ ንቅሳት (ታቱ) የሚሰሩ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡ 6. የጤና ባለሙያዎች በሕክምና ወቅት መርፌ ሊሰበርባቸውና ራሳቸውን ሊወጉ ይችላሉ በዚህም ለብክለት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ 7. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት በየአገሩ ይሰጣል፡፡ ሂፐታይተስ ሲ ቫይረስ (ኤች ሲ ቪ) 1. አብዛኛው ጊዜ የሚተላለፈው በተበከለ ደም አማካኝነት ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በቫይረሱ የተበከለ ደምና የደም ተዋሀፆ በመስጠት ወይም በማስተላለፍ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 2. በሕክምና ወቅት በቫይረሱ የተበከ መርፌ በመጠቅም አንዱ መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡ 3. በመርፌ በሚወሰዱ አድገኛ መድኃኒቶችና እፆች አጠቃቀም ወቅት ሌላው መተላለፊያ መንገድ ሲሆን በተለይ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጥንቃቄ ንቅሳት (ታቱ) የሚሰሩ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡ 4. በግብረስጋ ግንኙነት ሊተላለፍ ይችላል ነገር ግን ዝቅተኛ ነው፡፡ 5. ይህን ቫይረስ ለመከላከል ምንም አይነት ክትባት የለም፡፡ ሂፐታይተስ ዲ ቫይረስ (ኤች ዲ ቪ) 1. በዚህ ቫይረስ የሚጠቁት በሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ ብቻ የተጠቁ ሰዎች ናቸው፡፡ 2. በሁለቱ ቫይረሶች የሚጠቁ ሰዎች ለአደገኛ በሽታ የሚጋለጡ ሲሆን ውጤቱም እጅግ መጥፎ ሊባል የሚችል ይሆናል፡፡ 3. የሂፐታይተስ ቢ ክትባት በዚህ ቫይረስ ለሚጠቁ ሰዎች መከላከያ በመሆን ያገለግላል፡፡ ሂፐታይተስ ኢ ቫይረስ (ኤች ኢ ቪ) 1. ብዙን ጊዜ የሚተላለፈው የተበከለ ምግብ ወይም ውሃ በምንጠቀምበት ጊዜ ነው፡፡ 2. በተዳጊ አገሮች በስፋት ለሚታየው የሂፐታይተስ ስርጭት ይህ ቫይረስ ግንባር ቀደም ነው፡፡ 3. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት ቢኖርም በስፋት ማግኘት ያዳግታል፡፡

ግለ ወሲብ (ራስን በራስ ማርካት) ===================== ከሴክስ ጋር ከተያያዙ ጉዳዮች እንደ ግለ ወሲብ በብዛት ውይይት የተደረገበት፣ ባጠቃላይ የተወገዘ ነገር ግን በአለምአቀፍ ሁኔታ የሚደረግ ድርጊት የለም፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሁሉም ወንዶችና ሰባ አምስት ከመቶ ሴቶች ግለ ወሲብ ፈጽመው እንደሚያውቁ ነው፡፡ ግለ ወሲብ የሚጀምረው በጣም በህፃንነት ሲሆን ህፃናት የእጃቸውን ወይም የሌሎች አካላቸውን ተግባር እንደሚረዱ በተመሳሳይ ስለ ብልቶቻቸውም ይረዳሉ፡፡ ከ15 እስከ 19 ወር ሁለቱም ፆታዎች ላይ ብልቶቻቸውን ሲነኩ የሚሰማቸው ደስታ ባጠቃላይ አካላቸውን ከመረዳት ፍላጎታቸው ጋር ተዳምሮ ግለ ወሲብ እንዲያደርጉ ይገፋፋቸዋል፡፡ ጉርምስና ሲመጣ እሱን ተከትለው የሚከሰቱት የሆርሞንና የአካል ለውጦች ስለ ሴክስ የሚኖረውን የማወቅ ጉጉትና ግለ ወሲብን ይጨምረዋል፡፡ ግለ ወሲብ በጉርምስና ጊዜ ስነ ህይወታዊ በሆነው የሴክስ ፍላጎትና በማህበረሰብ በሚደረገው የሴክስ ክልከላ መሀል የሚፈጠረውን ውጥረት ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ ለማርገብ ያግዛል፡፡ ግለ ወሲብ እስከ ጉልምስና እድሜ የሚቀጥል ሲሆን በሂደት በሴክስ እየተተካ ይሄዳል፡፡ በትዳር/የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ያሉ ሰዎች ግለ ወሲብን ሙሉ በሙሉ አይተውም፡፡ የሴክስ ህይወታቸው አጥጋቢ ሳይሆን ሲቀር ወይም አጋራቸው በህመም ምክኒያት በቅርብ ከሌሉ ከሴከስ የሚገኘውን ደስታ ለማግኘትና ውጥረትን ለማርገብ ግለ ወሲብ ይፈፅማሉ፡፡ ግለ ወሲብ በማህበረሰብ ደረጃ ነውር በመሆኑ የአእምሮ ህመም እንደሚያመጣ ወይም የሴክስ አቅምን እንደሚቀንስ የሚገልፁ አባባሎች ይሰማሉ፡፡ እንዚህ ግን በሳይንሳዊ ጥናቶች ምንም ድጋፍ የላቸውም፡፡ ግለ ወሲብ የአእምሮ ህመም የሚሆነው ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ላይ ጣልቃ በሚገባ መልኩ ሲሆን ነው፡፡ የአእምሮ ህመም ሲሆንም ከሴክስ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ሳይሆን ስሜትን የመቆጣጠር ችግር በመሆኑ ነው፡፡

በግል ልታወሩኝ የምትፈልጉ እንዳላቹ አውቃለው የሁላቹንም በግል የማወራ ከሆኔ በጣም ቢዚ ስለሚያደርገኝ የሁላቹንም ጥያቄ አንድ በአንድ ልመልስላቹ አልችልም። ነገር ግን በዛት የሚነሱ ችግሮችን እያየው
በግል ልታወሩኝ የምትፈልጉ እንዳላቹ አውቃለው የሁላቹንም በግል የማወራ ከሆኔ በጣም ቢዚ ስለሚያደርገኝ የሁላቹንም ጥያቄ አንድ በአንድ ልመልስላቹ አልችልም። ነገር ግን በዛት የሚነሱ ችግሮችን እያየው በቻናሌ በኩል ለሁላቹም እለቅላችዋለው በስልክ ልታወሩኝ የምትፈልጉ ደሞ ለግዜው በስልክ ልታገኙኝ እንደማትቹሉ ነው የምነግራቹህ ፈጣሪ ፈቅዶ አንድ ቀን ነገሮች ሲመቻቹልኝ ሁላቹንም በቅርበት ተገናኝተን ያቅሜን እንደማደርግ እርግጠኛ ነኝ ከመደበኛ ስራዬና ከትምህርት በተረፈኝ ሰዐት አሁንም ሰውን ለመርዳት እየጣርኩ እንዳለው ነው ሚሰማኝ በ YouTube በ Facebook በ TikTokም በ Telegramም ጥረት እያደረኩ ነው ጊዜው እስኪደረስ በዚው እቀጥላለው አመሰግናለሁ መልካም ጤና ዶ/ር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ

ስነ ልቦናዊ የብልት አለመቆምና ህክምናው-ገጠመኝ1 ================================== አእምሮ በተለያዩ ሀሳቦች ሲወጣጠር የብልት አለመቆም ሊከሰት ይችላል። በተጨማሪም ሶስት አይነት ስሜቶች ማለትም ፍርሀት፣ ፀፀትና ሀፍረት ተመሳሳይ ችግር ሊያመጡ ይችላሉ። በእንግሊዘኛ አንድ ባለሁለት ስንኝ ግጥም አለች። When your mind is iffy You can not get a stiffy አንድ 30 አመት መልከ መልካም ወጣት ወደ 'የሴክስ ክሊኒክ' ክፍል ገባ። ቀጥ ብሎ መቀመጡ በራስ መተማመኑን ያሳያል። "በስራዬ ደስተኛ ነኝ። ቆንጅዬ ሚስት አለችኝ። የፍቅር ግንኙነታችን ጥሩ ነው። ምንም አይነት የአእምሮ ህመም የለብኝም።" አለ። ሀኪሟ "ዛሬ እንዴት መጣህ?" ብላ ጠየቀችው። "ከሶስት ወር ወዲህ ብልቴ አይቆምም።" አለና ትከሻውን ሰብቆ አንገቱን ደፋ። ሀኪሟ ከ40 አመት በታች የሚከሰት የብልት አለመቆም በአብዛኛው ስነ ልቦናዊ እንደሆነ ስለምታውቅ እርግጠኛ ለመሆን "ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ይቆማል?" አለችው። "አዎ" ብሎ መለሰ። እንደገመተችው ስነልቦናዊ ነው። ምክኒያቱን ለማወቅና መፍትሄ ለመፈለግ ረጅም ንግግር አደረጉ። ችግሩ የጀመረው ከ3ወር በፊት ነበር። ከወንድ ጓደኞቹ ጋር በምሽት እየተዝናና ነበር። ጓደኞቹ ወደየቤታቸው ሄዱ። ኪሱ ውስጥ በቂ ብር ስላልነበር ከኤቲኤም ለማውጣት ሄደ። አውጥቶ እንደጨረሰ ድንገት አራት ጎረምሶች ከበቡት። አንዱ ጩቤ ይዟል። የያዘውን ብርና ተጨማሪም አውጥቶ እንዲሰጣቸው ጠየቁት። እንዳሉት አደረገ። ትተውት ከሄዱ በኋላ ግን ከነከነው። "እኔ ወንድ አይደለሁም እንዴ? እንዴት የገዛ ገንዘቤን ለማንም እሰጣለሁ?" የሚል ሀሳብ መጣበት። ሀኪሙ ስነልቦናዊ ምክኒያቱ በተፈጠረው ክስተት የተሰማው ፀፀት እንደሆነ ስለገመተች "አራት ጩቤ የያዙ ዱርዬዎች በምሽት ብር ሲጠይቁ መስጠት ወንድ አለመሆን ሳይሆን ብልህ መሆንን ነው የሚያሳየው።" አለችው። የተሰበቀው ትከሻው ቀጥ አለ። ከአንገቱም ቀና አለ። ከዛ በኋላ አልተቸገረም። ከIntroduction to Psychosexual Medicine መፅሀፈ የተወሰደ ለወዳጅዎ ያጋሩ ጤና ይብዛሎ! ዶ/ር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ

✍ #በሴቶች #ላይ #የሚከሰት #የብልት #ማሳከክ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የሴት ብልት ማሳከክ ብዙውን ጊዜ በሚያስቆጡ ንጥረ ነገሮች ፣ ኢንፌክሽኖች ወይም ማረጥ ምክንያት የሚከሰት ምቾት የሚነሳ እና አንዳንድ ጊዜ ህመምን የሚያስከትል ነው። ⏩ #እንዲሁም በተወሰኑ የቆዳ መታወክ ወይም በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች (አባላዘር) ምክንያት ሊከሰት ይችላል። አልፎ አልፎ ፣ በውጥረት (ጭንቀት) ወይም በሴት ብልት ካንሰር ምክንያት የሴት ብልት ማሳከክ ሊከሰት ይችላል። 👉 #መንስኤዎቹ 🔺 ብልትን የሚያስቆጡ ነገሮች፡- ሳሙና፣ በአረፋ መታጠቢያዎች ወስጥ በተደጋጋሚ መዘፍዘፍ፣ ወደ ማህፀን ዉሃ እየከተቱ መታጠብ፣ አንዳንድ ክሬሞችና ቅባቶች፣ ብናኝ ያላቸዉ ማደራረቂያዎች፣ መዓዛ ያላቸዉ የሽንት ቤት ወረቀቶች 🔺 አንዳንድ የቆዳ ህመሞች 🔺 የፈንገስ ኢንፌክሽን 🔺 የባክቴሪያ ኢንፌክሽን 🔺 የስኳር ህመም 🔺 ሽንት መቆጣጠር አለመቻል 🔺 ብልት ላይ የሚገኙ ጥሩ እና መጥፎ ባክቴሪያዎች አለመመጣጠን 🔺 የአባላዛር ህመም 🔺 ማረጥ 🔺 ጭንቀት 👉 #ህክምናዎቹ ⏩ #ህክምናዎቹ የሚሰጡት እንደ መንስኤዎቹ አይነት ነዉ፡- 🔺 በሳሙና እና በምንጠቀመው አማካኝነት የሚፈጠርን ማሳከክ የምንጠቀመው ነገር ማስተካከል በንፁህ ውሀ መታጠብ 🔺 የፈንገስ መድሀኒቶችን መጠቀም 🔺 የባክቴሪያ መድሀኒት መውሰድ 🔺 የሆርሞን መድሀኒቶችን መጠቀም 👉 #መከላከያዎቹ 🔺 የብልት አካባቢዎን ለማጠብ ሞቅ ያለ ውሃ እና ለስላሳ ማጽጃ ይጠቀሙ። 🔺 ሽታ ያላቸውን ሳሙናዎችን ፣ ቅባቶችን እና የአረፋ መታጠቢያዎችን ያስወግዱ። 🔺 ዉሃን ወደ ማህጸን እየከተቱ ከመታጠብ ይቆጠቡ። 🔺 ከመዋኛ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በኋላ ወዲያውኑ የዉስጥ ልብሶችን ይለውጡ። 🔺 ኮተን የውስጥ ልብስ ይልበሱ እና በየቀኑ የውስጥ ልብስዎን ይለውጡ። 🔺 በፈንገስ የመያዝ እድልን ለመቀነስ አዘዉትረዉ እርጎ ይብሉ። 🔺 ኮንዶም መጠቀም። 🔺 ሰገራ ከተጠቀሙ በኋላ ሁል ጊዜ ከፊት ወደ ኋላ ይጥረጉ። 👉 #እነዚህን #ምልክቶች #ካዩ #ወደ #ጤና #ተቋም #መሄድ #አለብዎት? 🔺 በብልት ላይ ቁስሎች፣ እብጠቶች ወይም መቅላት 🔺 በብልት አካባቢ ህመም ወይም ሲነካ ህመም መሰማት 🔺 ለመሽናት መቸገር 🔺 ያልተለመደ ከብልት የሚወጣ ፈሳሽ 🔺 በጾታዊ ግንኙነት ወቅት ምቾት ማጣት 👉👉 #ይህን መሰል እና ማንኛዉም ተያያዥ የጤና ጥያቄ ካሎት ወደ ጥሪ ማዕከላችን በመደወል ከጤና ባለሙያ ጋር ይማከሩ! ለመማከር 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ስጦታ)

በአለም ላይ እንዲሁም በአገራችን የብዙ ሰው ሂወት እየቀጠፈ ስላለው "ስትሮክ"(stroke) በሽታ ትንሽ ነገር ልበል ድምፅ አልባው ገዳይ "ስትሮክ ምንድን ነው? -ወደ አእምሯችን ክፍል በተለያየ ምክንያት የደም አቅርቦት ሲስተጓጎል ይህ ደግሞ ወደ አእምሮ የሚደርሰው ኦክስጅን እነዲቋረጥ ያደርጋል።አንድ መኪና ነዳጅ እንጀሚያስፈልገው ሁሉ ጭንቅላታችን ያልተቆራረጠ ኦክስጅን የያዘ የደም አቅርቦት ያስፈልገዋል። ያለ ኦከስጅን አእምሮ ውስጥ ያሉ ሴሎች ይጎዳሉ ፣ይሞታሉም። ስለዚህ በተለያየ ምክንያት የሚፈጠረው አእምሯችን በቂ ደም ሳያገኝ ሲቀር ስትሮክ እንለዋለን ። መንስኤውስ? -ስትሮክን በደም ስር መደፈን ወይም መዘጋት ምክንያት የሚመጣ(Ischemic stroke) እና በመድማት ምክንያት(hemorahgic stroke) ብለን ልንከፍለው እንችላለን። 1.Ischemic stroke የምንለው አእምሯችን ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮች በረጋ ደም አንዳንዴም Atheroscleorsis በተባለ ነገር ሲዘጋ ወይም ሲደፈን፣ይህም Embolic የሚባል ስትሮክ ሲሆን ሌላኛው ከአእምሮ ውጪ ከሌላ የሰውነታችን አካል በተለይ ከልብ፣ከአንገት አካባቢ በደም ቧንቧ አማካኝነት ወደ አእምሯችን ሲሄድ እና አእምሯችን በቂ የሆነ ኦክስጅን የያዘ ደም እንዳያገኝ ሲያስተጓጎለው የሚፈጠር thrombotic የሚባል ስትሮክ እንለዋለን። 2.Hemorrhagic stroke የምንለው አእምሮ ውሰጥ የደም ስር በተለያየ ምክንያት ሲፈነዳ እና ደም ወደ ጭንቅላታችን ሲፈስ ነው ይህም የሚፈሰው ደም ተጠራቅሞ አእመሮ ላይ በሚፈጥረው ጫና ምክንያት ጫናው የደረሰበት የአእምሮ ክፍል ኦክስጅን እንዳያገኝ ሲሆን የሚከሰት የስትሮክ አይነት ነው። ለስትሮክ የሚያጋልጡን ነገሮችስ? -እድሜ እየገፋ ሲሄድ፣ስኳር፣ደም ግፊት፣ከመጥን በላይ የሰውነት ዉፍረት፣የኮሌስትሮል ክምችት፣ሲጋራ ማጨስ፣አልኮል መጠጥ፣የደም መርጋት ችግር፣የወሊድ መቆጣጠሪያ በተደጋጋሚ የሚጠቀሙ ሴቶች፣ደም ለማቅጠን የምንጠቀምባቸው መድሀኒቶች፣እርግዝና፣በፊት የነበረ ያልታከመ ስትሮክ፣አደንዛዥ እፆች፣የአእምሮ እጢዎች ይጠቀሳሉ። ምልክቶቹስ? -ድንገተኛ እና ሀይለኛ የእራስ ምታት፣እራስን መሳት ፣ትውከት፣የማጅራት መገተር፣ሚዛንን ለመቆጣጠር መቸገር፣የፊት በአንድ በኩል ማዘንበል፣የእጅ እና የእግር ሰንፈት ወይም አለመታዘዝ በተለይ በአንድ በኩል ፣መናገር ማቃት፣መንተባተብ፣ግራ መጋባት ሊኖር ይችላል። የሚያመጣውስ ችግር? -የአእምሮ እብጠት፣የሳንባ ምች፣የሚጥል በሽታ፣የልብ ድካም፣ሽንት ያለመቆጣጠር ችግር፣የአልጋ ቁስል፣ለመዋጥ መቸገር፣የህመም ስሜት ፣ጭንቀት፣የመግባባት ችግር፣ሽባነት(paralysis)፣ሞትን ያስከትላል። በምን ማረጋገጥ ይቻላል? -በፍጥነት የህክምና እርዳታ ማግኘት ከማገገማችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስላለው ቶሎ መታከም እጅግ ወሳኝ ነው። -በህክምና እርዳታ ወቅት የጤና በላሙያው ጥርጣሬ ካለው አካላዊ ምርመራ አድርጎ ከዛም ተጨማሪ ምርመራዎችን ለምሳሌ የደም ስኳር መጠን፣ሙሉ የደም ምርመራ፣የደም መርጋት ምርመራ፣የልብ ምርመራ፣በመጨረሻም CT scan እንደ አስፈላጊነቱ MRI በማዘዝ ትክክለኛውን የስትሮክ አይነት ማረጋገጥ ይቻላል። ህክምናውስ? -ከምንም በላይ በፍጥነት የህክምና እርዳታ ማግኘት እጅግ ወሳኝ ነው። -ህክምናው እንደየ ስትሮክ አይነት የሚወሰን እና ጊዜ የሚፈልግ ሲሆን በአብዛኛው የሚታዘዙ መድሀኒቶች የደም ግፊት መቀነሻ ፣የረጋ ደም መቀነሻ፣የኮሌስትሮል መቀነሻ፣አልፎ አልፎም በደም መፍሰስ ምክንያት ከሆነ የረጋውን ደም ለማውጣት ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግ ይችላል። -የመናገር እና የመግባባት ህክምና ፣physical እና occupational ህክምና፣ፊዚዮቴሬፒ እና የሀኪም ክትትል ማድረግ ሌላው እጅግ ወሳኝ የህክምና አካል ነው። -ስለዚህ በየቀኑ ያሉ የጤና መሻሻሎችን በትግስት መከታተል ተገቢ ነው። ለወዳጅዎ ያጋሩ ጤና ይብዛሎ! ዶ/ር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ በዉስጥ ልታወሩኝ ምትፈልጉ ቴሌግራም ላይ ከስር ሊንኩን ነካ በማረግ ታገኙኛላቹ https://t.me/DrSofonias

#አለርጂክ ምንድነው ?፨፨፨ አለርጂ የሰውነት የመከላከያ ስርአት ከሰውነት ወጪ ባእድ ለሆኑ ነገሮች የሚሰጠው ምላሽ ነው።እነዚህ ባእድ ነገሮችም(Allergens) በተፈጥሮ ጉዳት የማያደርሱ ሲሆኑ አንዳንድ የምግብ ዓይነቶች፣ ለማዳ እንሰሳት ፣የአበባ ፖለንና ፍግ የመሳሰሉ ሊሆኑ ይችላሉ ። የሰውነት የመከላከያ ስርአት ሚናው ሰውነትን ሊጎዱ የሚችሉ ባእድ ነገሮችን መዋጋት ነው። ይህን የሚያደርግው ጎጂን ከማይጎዳ ነገር በመለየት ነው። አለርጂ ያለበት ሰው ግን የማይጎዳን ባእድ ነገር እንደ ጎጂ አድርጎ በመተርጎም ምላሽ ይሰጣል።በዚህ ባልተገባ ምላሽም አለርጂ ያለበት ሰው ይታመማል ። #የአይን የአለርጂ ምልክቶች ፨፨፨ *የአፍንጫ መዘጋት ኮንጀስሽን *ውሃ አይነት ፈሳሽ ከአፍንጫ መውጣት *የአይን ማበጥና ማሳከክ *ማስነጠስ *የቆዳ ሽፍታና ማሳከክ *የጉሮሮ ህመም #አለርጂን የሚቀሰቅሱ ነገሮች ፨፨፨ *የቤት እንሰሳት፣በረሮ፣ጉንዳን ፣ፋንዲያ *መድኃኒት፦ በተለይ ፔንሲሊንና ሰልፋ መድኃኒቶች *ምግቦች ፦ወተት ፣ለውዝ አሳ የመሳሳሉ *በነፍሳት መነደፍ ፥ ንብ፣ተርብ ፣ቢንቢ *የአበባ ብናኝ *ግላቭና ኮንዶም ውስጥ ያሉ ኬሚካሎች እነዚህን ነገሮች አውቆ ራስን መከላከል አስፈላጊ ሲሆን ከታመሙ በኋላ ግን የህክምና አማራጮች አሉ። #የህክምና አማራጮች *አንቲሂስታሚን መድሀኒቶች፦ ዳይፌነሃይድራሚን፣ሲትሪዚንሎራቲዲን *ስቴሮይድ የተባሉ የተለያዩ መድኃኒቶች *ኢሚኖቴራፒ *ኢፒኔፍሪን *ሌሎችም አለርጂ አንዳንድ ጊዜ የትንፋሽ ማጠር፣ ሾክ ውስጥ መግባት ፣ራስ መሳትን በማስከተል ለህይወት አስጊ ደረጃ ሊደርስ ይችላል ። ይህ በሚከሰትበት ጊዜ ፈጥኖ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።