ar
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

الذهاب إلى القناة على Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

تُعد قناة ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 19 829 مشتركاً، محتلاً المرتبة 1 169 في فئة الطب والمرتبة 1 702 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 19 829 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 08 يوليو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -464، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -25، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 16.43‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 6.66‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 259 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 321 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 5.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 09 يوليو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الطب.

19 829
المشتركون
-2524 ساعات
-777 أيام
-46430 أيام
أرشيف المشاركات
✍️ #የጭንቅላ #እጢ #ምልክቶች 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #አብዛኛዎቹ የጭንቅላት እጢ ቀጥለው ከተዘርዘሩት ውስጥ ቢያንስ ከሁለት በላይ ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላል ነገር ግን ምልክቶቹ ሁሉ የእጢ እና ዕጢ ብቻ የማይሆኑበት አጋጣሚም ይኖራል ስለሆነም በምርመራ የትኛው የአእምሮ ክፍል እና ምን አይነት ዕጢ ነው የሚለውን ነገር መለየት አስፈላጊ ነው፡፡ ⏩ #የንቃት #መቀነስ :- የጭንቅላት እጢ ያለበት ሰው የንቃት ደረጃው መቀነስ በደንብ ካለማውራት እስከ ምንም አለመናገር ሊደርስ የእውቀት ችግር ሊሆን ይችላል። ⏩ #የጭንቅላት #መጠን #መጨመር: - አብዛኛው የአንጎል እና የጭንቅላት አጥንት እድገት የሚኖረው በመጀመርያዎቹ ሁለት የዕድሜ ዓመታት ነው። እጢ ወይም ተመሳሳይ እብጠት እና ከነዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ችግር ያላቸው ልጆች ላይ ከልክ ያለፈ የጭንቅላት እድገት ሊኖር ይችላል፤ብዙ ግዜ ከሁለት ዓመት በታች ያሉ ህፃናት ላይ የሚታይ ምልክት ሲሆን ቀጥታ በእጢው ምክንያት ወይም ከእጢው ጋር ተያይዞ በሚፈጠር ሁኔታ ሊሆን ይችላል። ⏩ #የማስታወስ #ችግር (#መርሳት) ፡- የቅርብ ወይም የረዥም ግዜ ክንውኖችን የማስታወስ ሁኔታ መቀነስ ፤ ሰው ፣ ቦታ ፣ ግዜ ያለማስታወስ ሁኔታም ሊኖራቸው ይችላል። ⏩ #ራስ #ምታት:- በአብዛኛው እጢ ያላቸው ሰዎች የሚኖር ምልክት ሲሆን ረጅም ወይም አጭር ግዜ የቆየ በማስታገሻ በደንብ የማይቀንስ ፣ ጠዋት ከእንቅልፍ ሲነሱ ፣ ወደ ፊት ሲያጎነብሱ ፣ ሲያስሉ የሚጨምር ራስ ምታት ፤በአብዛኛው እጢ ያላቸው ሰዎች የሚኖር ምልክት ይሆናል፡፡ ⏩ #የሚጥል #በሽታ: - ሁሉም የሚጥል በሽታ ያላቸው ሰዎች በእጢ ወይም በተመሳሳይ እብጠት ምክንያት ነው ማለት አይደለም። ሆኖም ግን የሚጥል በሽታ ያለበት ሰው እጢ እና ከእጢ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የአንጎል እብጠት አለመኖሩ በምርመራ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ⏩ #ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች አሉ ማለት የጭንቅላት እጢ አለ ሳይሆን በተደጋጋሚ ለነዚህ ምልክቶች ተጋላጭ መሆንና ቢያንሰ ከነዚህ ምልክቶች የተወሰኑትን በራሳችን ላይ የምናስተውል ከሆነ ጤና ተቋም በመሄድ መታየቱ የተሻለ ነው። ለበለጠ መረጃ ዶክተር አለ 8809 ይደውሉ ማንኛውም የጤና ችግሮች ካጋጠመዎት ይደውሉ ምርጫዎ ያድርጉን !!! ለወዳጆም መረጃዎቻችንን በማጋራት የበኩሎን ያበርክቱ!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)

ውን ደስታ በመንፈጋቸው ሳቢያ ለዘመናት የገነቡትን ትዳር የጠዋት ጤዛ ሲያደርጉት አይተናል፡፡ ምንም እንኳን የስንፈተ ወሲብ ችግር ሳይንሳዊ ምክንያትና መፍትሄ ያለው ቢሆንም፤ ችግሩን በጋራ ለመፍታት መሞከር የተሻለ አማራጭ ነው። ይቀጥላል

#ጤና #ይስጥልኝ #ውድ #የቴሌግራም #ቻላናችን #ተከታታዮቻችን #ለዛሬ #ለእናተ #ይጠቅማል #ያልንውን #ፁሁፍ #እንሆ #ይከታተሉን። በርካታ ባለትዳሮች በግልፅ ለመንገር ባይፈልጉም ከሁለቱ አንደኛው ከወሲብ የሚገኘውን ደስታ በመንፈጋቸው ሳቢያ ለዘመናት የገነቡትን ትዳር የጠዋት ጤዛ ሲያደርጉት አይተናል፡፡ ምንም እንኳን የስንፈተ ወሲብ ችግር ሳይንሳዊ ምክንያትና መፍትሄ ያለው ቢሆንም፤ ችግሩን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል ግልፅነት ባለመኖሩ ትዳሮች ፈርሰዋል፡፡ ቤተሰብ ተበትኗል፡፡ ጥያቄው ያለው መፍትሄ ባለው ችግር ለምን ትዳሮች ይናጋሉ? ለምንስ ፍቅረኞች ወደ መለያየት ያመራሉ? የሚለው ላይ ነው፡፡ በቦስተን አካባቢ ባሉ ነጮች ላይ የተጠና ጥናት እንደሚያመላክተው 30 ሚሊየን የሚደርሱ ወንዶች የስንፈተ ወሲብ ችግር አለባቸው፡፡ ጥናቱ ጨምሮ እንዳረጋገጠው የወንዶች እድሜ በጨመረ ቁጥር ችግሩ የበለጠ እየሰፋ ይመጣል፡፡ ለምሳሌ በጥናቱ ከተካተቱት የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ 40 ዓመት ከሞላቸው ወንዶች 40 በመቶ የሚሆኑት እንደዚሁም 70 አመት ከሞላቸው ደግሞ በ70 በመቶዎቹ ላይ የስንፈተ ወሲብ ችግር ታይቶባቸዋል፡፡ የተለያዩ በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች ተለያይተው ሲጠኑ ደግሞ፤ ለምሳሌ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከሌለባቸው በሶስት እጥፍ የስንፈተ ወሲብ ተጠቂዎች መሆናቸውን በቦስተን በተደረገው ጥናት ተረጋግጧል፡፡ ይህ ጥናት የስነ ልቦና ችግሮችና ውጥረቶች በሚበዛባቸው በአፍሪካና በኤዥያ ሀገሮች ቢሰራ የስንፈተ ወሲብ ችግር ምን ያህል የዓለም ችግር መሆኑን እንደሚያሳይ የአሜሪካዎቹ ተመራማሪዎች ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ በስንፈተ ወሲብ (Sexual Dysfunction) ምንነት፣ መንስኤ፣ ምልክቶችና አማራጭ የህክምና መፍትሄው ዙሪያ የሚያተኩር ትንታኔን ቀርቦበታል በጥሞና በትዕግስት አንብበው ወይም አንብቡት፡፡ የስንፈተ ወሲብን ምንነት ስንፈተ ወሲብ (Sexual Dysfunction) የምንለው በተለያዩ ምክንያቶች በሁለቱም ፆታዎች በኩል ወሲብ ለመፈፀም የሚያስችሉ ችግሮች ሲከሰቱ ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ ደግሞ አግባባዊ (የሚያረካ) የወሲብ ግንኙነት አለመፈፀም አልያም በሚደረገው የወሲብ ግንኙነት አለመርካት (ጥሩ ውጤት አለማግኘት) ማለት ነው የስንፈተ ወሲብ ችግር የሚባለው፡፡ እንዴት ይገለፃል? ለሚለው ለግብረ ስጋ ግንኙነት ስሜት ማጣትና ከግንኙነቱ እርካታ አለማግኘት በሁለቱም ፆታዎች ላይ የሚታይ ችግር ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀሚያ አካላት አለመነሳሳትን በተመለከተ በአብዛኛው በወንዱ ላይ ይታያል፡፡ ፍላጎት ማጣት፣ ከግንኙነት በኋላ እርካታን አለማግኘት (የእርካታ መጨረሻ ላይ አለመድረስ) ብዙውን ጊዜ የሴቶች ችግር ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለችግሩ መፈጠር መንስኤዎች የስንፈተ ወሲብን መንስኤ ስነ ልቦናዊና አካላዊ ብለን በሁለት ትላልቅ ጎራዎች ከፍለን መመልከት እንችላለን፡፡ አካላዊ ስንል ከግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀሚያ አካሎች ለውጥ፣ በደም ውስጥ ካሉ ንጥረ ነገሮች መዛባት፣ ከአዕምሮና ከህብለሰረሰር የሚነሱ ችግር ውስጥ ከመግባታቸው ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ እንደዚሁም ከልብ የሚነሱ ደም ስሮች በአግባቡ ወደ ብልት ሄደው የደም ዝውውሩን ውጤታማ ማድረግ ባለመቻላቸውና ብልትን እንዲቆም የሚያደርጉ ነርቮች ባለመስራታቸው የስንፈተ ወሲብ ችግር ይመጣል፡፡ ሌላውና ከአካላዊ ምክንያት ጋር የሚያያዘው ስሜት ቀስቃሽ ንጥረ ነገሮች (ሆርሞኖች) በሚፈለገው መጠን በሰውነት ውስጥ አለመኖር፣ ስሜት ቀስቃሽ ንጥረ ነገሮች በሚፈለገው መጠን እንዳይሰሩ የሚያደርጉ ሌሎች የሆርሞን አይነቶች በሰውነት ውስጥ በብዛት ሲከሰቱ፣ በብልት ላይ የተለያዩ አደጋዎች ሲደርሱ፣ በብልት አካባቢ በሚሰሩ ቀዶ ህክምናዎች ምክንያት በብልት አካባቢ ያሉ ነርቮችና ደም ስሮች ሲጎዱ ለስንፈተ ወሲብ ችግር መጋለጥን ያመጣሉ፡፡ በተጨማሪም ለሌሎች በሽታዎች መፈወሻ ተብለው የሚሰጡ ለምሳሌ ለደም ግፊት፣ ለጨጓራ፣ ለኮሌስትሮል፣ ለሽንት ማሸኛ፣ ለአዕምሮ ህመሞችና ለሌሎችም በሽታዎች የሚሰጡ መድኃኒቶች ችግሩን የማምጣት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ በአጠቃላይ 25 በመቶ የወንዶች ስንፈተ ወሲብ ለሌሎች በሽታዎች በሚሰጡ መድኃኒቶች የሚመጣ ነው፡፡ ከስነ ልቦና አንፃር ደግሞ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ጫና፣ ውጥረትና ቀደም ሲል በነበረ የወሲብ ታሪክ ጥሩ ያልሆነ ክስተት ከነበረ ለምሳሌ በቅርብ ዘመዶችም ሆነ በሩቅ ሰዎች ተገዶ መደፈር ከነበረ ወሲብን መጥላት ይኖራል፡፡ በወሲብ መፈፀሚያ ቦታዎች አካባቢ ምቾት ማጣት፣ ከማይፈልጉት ሰው ጋር መኖር (ወሲብ መፈፀም) የወሲብ ስሜት አልባነትን ያመጣል፡፡ እንደዚሁም በአንድ ወቅት በሆነ ምክንያት ወሲብ ያለመፈፀም ችግር ገጥሞት ከነበረ ሁል ጊዜም ችግሩ አለብኝ ብሎ መጨነቅ ወደ ስንፈተ ወሲብ ችግር በቀጥታ የሚገፋ ሁኔታ ነው፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ መንስኤዎችን ስናየው አካላዊ ወይም ከበሽታ ጋር ተያይዞ የሚከሰተው ስንፈተ ወሲብ በአብዛኛው ከ40 ዓመት በላይ ባሉ ሰዎች ላይ የሚታይ ነው፡፡ በተለይም ከስነ ልቦና ጋር በተያያዘ ችግር ይበልጥ የሚጠቁት ወጣቶች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ከስነ ልቦናዊ ምክንያቶች ጋር የተያያዘው የስንፈተ ወሲብ ችግር ከ10 እስከ 20 በመቶ የሚደርስ ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን ከ40-80 በመቶ የሚሆነው የስንፈተ ወሲብ ችግር በቂ የሆነ አካላዊ ምክንያት ያለው ነው፡፡ ከላይ በመንስኤነት ከተገለፁ ጉዳዮች በተጨማሪ የሚገልፀው አብዝቶ አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ሐሺሽ እና ለመዝናኛነት ተብለው የሚወሰዱ መድኃኒቶች ችግሩን በማምጣት ረገድ የጎላ ሚና አላቸው፡፡ ስንፈተ ወሲብን በማምጣት ወይም በማባባስ በኩል አስተዋፅኦ ያላቸው የጤና ችግሮች – ኢንፌክሽን – የልብ ህመም – የጉበት ህመም – የኩላሊት ህመም – የስኳር እና – የደም ግፊት በሽታዎች እንደዚሁም – የኮሌስትሮል ከፍ ማለት – የጡንቻ መኮማተር (በተለይ በሴቷ) – የደም ስር ችግሮች – የነርቭ ህመም እና – ሰውነትን የሚያንቀጠቅጥ ህመም (ፓርኪንሰንስ ዲዝዝ) ከላይ የገለፅኳቸው የጤና ችግሮች በአንድ በኩል ስንፈተ ወሲብን ያስከትላሉ፡፡ በሌላም በኩል ቀደም ሲል የተከሰተን ስንፈተ ወሲብ ያባብሳሉ፡፡ ስንፈተ ወሲብ መኖሩን ፍንጭ ከሚሰጡ ምልክቶች ዋና ዋና የሚባሉትን ስናይ – የወሲብ ፍላጎት ማጣት – የወሲብ መፈፀሚያ አካላት ዝግጁ አለመሆን (አለመቆም) – በተለይም ሴቶች ወንድንም ሆነ ወሲብን መጥላት – ብልት ቶሎ ተልፈስፍሶ መውደቅ ወይም መርገብ – ወሲብ በሚፈፀምበት ወቅት ህመም መኖር – የሴት ብልት ጡንቻ መኮማተርና በሁለቱም ላይ ህመም መፍጠር – ሴቶችን ለግንኙነት ዝግጁ የሚያደርግ ፈሳሽ በበቂ መጠን አለመኖር – እርካታ ላይ አለመድረስ ፈጥኖ እርካታ ላይ መድረስ ከሳይንስ አኳያ ስናየው ፈጥኖ የዘር ፍሬን ማፍሰስ ችግር ያለባቸው በቁጥር ቀላል የማይባሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱ ብዙ ነው፡፡ ዋናዋና የምንላቸው ምክንያቶች አንደኛው ለወሲብ ጉጉ ከመሆን የሚመነጭ ችኩልነት፣ ሁለተኛ ከአሁን አሁን የዘር ፍሬዬ ፈሰሰ ብሎ መጨነቅ፣ ሶስተኛ ራሴንም ሆነ ተቃራኒ ፆታዬን ማርካት አልችልም ብለው በተደጋጋሚ ስለሚያስቡ ስሜታቸውን ነፃ አድርገው ለመጋራት መቸገራቸው አራተኛው ከነርቭ ወይም ከብልት አፈጣጠር ጋር የተያያዘ ምክንያት ነው፡፡. በርካታ ባለትዳሮች በግልፅ ለመንገር ባይፈልጉም ከሁለቱ አንደኛው ከወሲብ የሚገኘ

ለኩላሊታችን መልካም ጤንነት ስንል ከእነዚህ ልማዶች ብንርቅስ ኩላሊት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ደም በማጣራት በሰውነታችን ውስጥ የማያስፈልጉ ነገሮችን በሽንት መልክ ማስወገድ አንዱ ነው።በሰውነታችን ውስጥ የተጠራቀመ አላስፈላጊ ውሃን ማስወገድ እና የካልሺየምና የፎስፌት ማዕድናት መጠንን መቆጣጠርም ሌላኛው ስራው ነው። የደም ዝውውርን የሚያፋጥኑና የቀይ ደም ህዋስ መመረት ሂደትን የሚጨምሩ ሆርሞኖችንም ያመርታል። በርካታ ተግባራት የሚከውነው ኩላሊት ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥልና ስራውን በተገቢው መንገድ እንዲያከናውን ታዲያ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ነገሮች መራቅ ይገባል። የሽንት ቀለም መቀየር፣ ማስመለስ፣ የአተነፋፈስ መዛባት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ድካም እና የመሳሰሉት የኩላሊት በሽታ ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋማት መሄድ ይመከራል። 1. ሽንትን ይዞ መቆየት ሽንት ሳይወገድ በፊኛ ለረዥም ጊዜ ከቆየ ለቫክቴሪያዎች መፈጠር ምክንያት የሚሆን ሲሆን፥ ይህም የሽንት ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ይፈጥራል። ስለሆነም በስራ ውጥረትም ይሁን ሌላ የተፈጥሮ ጥያቄን መልስ የሚያዘገዩ ከሆነ ለኩላሊትዎ ሲሉ ከድርጊትዎ ሊቆጠቡ ይገባል እንላለን። 2. በቂ ውሃ አለመጠጣት ኩላሊት አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስወገድ ተግባሩ በቂ ውሃ ስለሚፈልግ በቀን ውስጥ በቂ ውሃ አለመጠጣትም ለኩላሊት ህመም ይዳርጋል። ሰውነታችን አስፈላጊውን ያህል ውሃ ካላገኘ ደም ስለሚረጋ ወደ ኩላሊታችን የሚሄደው ደም መጠን ይቀንሳል። ይህም ኩላሊት ከሰውነታችን የሚያስወግዳቸው መርዘኛ ተህዋሳት በበቂ ሁኔታ እንዳይወገዱ ያሰናክላል ማለት ነው። ስለሆነም በየቀኑ ከ10 እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ኩላሊትዎ ጤናማ እንዲሆን ያግዛል። 3. ጨው አብዝቶ መመገብ በተደጋጋሚ ጨው የበዛበት ምግብ መመገብም ለኩላሊት ጤና ፀር ነው ተብሏል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጨውን አብዝቶ መውሰድ በሽንታችን ውስጥ የፕሮቲን መጠን እንዲጨምር በማድረግ ለኩላሊት ህመም ይዳርጋል። በየቀኑ በአጠቃላይ ከምንወስዳቸው ምግቦች ውስጥ የጨው ድርሻ ከ5 ግራም ባይበልጥ መልካም ነው ይላሉ ባለሙያዎች። 4.መድሃኒቶችን/ ማስታገሻዎችን አዘውትሮ መውሰድ ብዙዎቻችን ጉንፋን አልያም ራስ ምታት ሲያመን በሽታ የመከላከል አቅማችንን የሚያጎለብቱ ምግቦችና መጠጦችን ከመውሰድ ይልቅ ኪኒን ስለመዋጥ ነው የምናስበው። መድሃኒቶች በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ኩላሊታችን አልያም ሌላ የሰውነት ክፍላችን ሊጉዱ እንደሚችሉ ይነገራል። አንዳንድ ጥናቶች ማስታገሻዎችን በተደጋጋሚ መውሰድ ወደ ኩላሊት የሚሄደውን ደም እንቅስቃሴ ሊቀንሱ እንደሚችሉ አመላክተዋል። 5.ፕሮቲን የበዛባቸው ምግቦች ፕሮቲን ለጤና ጠቃሚ ቢሆንም፥ ቀይ ስጋና የፕሮቲን መጠናቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን በተደጋጋሚ መውሰድ ለኩላሊት በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል። 6. አልኮል የአልኮል መጠጦችን አብዝተን በምንጠጣበት ወቅት ዩሪክ አሲድ በኩላሊታችን ቱቦ ይከማቻል። ይህም ኩላሊታችን የተለመደ ተግባሩን እንዳያከናውን እክል ይፈጥራል። ስለሆነም ሁሉም በልኩ ነውና በመጠጡም ለጤናዎ ይወቁበት። 7. ሲጋራ ሲጋራ ማጨስ በሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች የሚያደርሰው አስከፊ ጉዳት አጠያያቂ ባይሆንም ለኩላሊት ህመም እንደሚያጋልጥም ይነገራል። ሲጋራ እድሜ እየገፋ ሲመጣ ለሚከሰተው የኩላሊት ህመም መንስኤ ከመሆኑም ባሻገር የኩላሊት ህመምተኞች አጫሾች ከሆኑ ደግሞ በሽታው እጅግ እንዲባባስ እንደሚያደርግ በጥናት ተረጋግጧል። 8. ቡና (ኮፌይን አብዝቶ መጠቀም) ካፌይን አብዝቶ መጠቀም ለደም ግፊት ከመዳረጉም ባለፈ ኩላሊትንም ይጎዳል። ካፌይንን ካለ ልክ መውሰድ ለኩላሊት ጠጠር መፈጠር ምክንያት የሚሆን ሲሆን፥ የካልሺየም ንጥረ ነገር ከሽንት ጋር በብዛት እንዲወገድም ያደርጋል። 9.ጉንፋንን የመሳሰሉ ህመሞችን ቸል ማለት እንደ ጉንፋን፣ ቶንሲል፣ ኢንፍሊዮንዛ ያሉ ህመሞችን በቸልታ ማለፍ ኩላሊትን ሊጎዱ እንደሚችሉ ይነገራል። እነዚህ ቀላልና የተለመዱ ህመሞችን የሚያመጡ ቫክቴሪያዎችና ቫይረሶች አስፈላጊው ህክምና በወቅቱ ካልተደረገ ኩላሊትን የመጉዳት አቅም አላቸው። 10. እንቅልፍ ማጣት በተጣበበ ጊዜና የስራ ሁኔታ የሚኖሩ ሰዎች እንቅልፍ የሚያስገኘውን የጤና በረከት ይዘነጉታል። በእንቅልፍ ስዓት የአዳዲስ ህዋሳት አሮጌዎቹን የመተካት ተግባር ይከናወናል። በአንፃሩ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት እንደ ኩላሊት ያሉ ሌሎች የሰውነት አካላት ተግባራቸውን በተገቢው ሁኔታ እንዳያከናውኑ ያደርጋል። በተጨማሪም በቂ እረፍት ወይም እንቅልፍ አለመኖር ለደም ግፊት ይዳርጋል።

✍ #የወንድ #መካንነት #ምልክቶች #እና #ህክምናው 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ 👉 #ለመካንነት መፈጠር ወንድ እና ሴት እኩል የሆነ ድርሻ አላቸው። ይህ ማለት ምንም እንኳን ጥንዶቹ ያለ ምንም የ እርግዝና መከላከያ በተደጋጋሚ ለ 1 ዓመት ያህል ግንኙነት ቢፈፅሙም ማርገዝ አይችሉም፡፡ 👉 #አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ነፍሰጡር ለማድረግ ጤናማ የሆነ የወንድ የዘር ህዋስ ወይም ስፐርም እንዲኖረው ያስፈልጋል። ይህም መደበኛ የስፐርም ቁጥር ተብሎ ይጠራል። የማስረገዝ ችግር ያላቸው ወንዶች በዘር ህዋሳቸው ማለትም በስፐርማቸው ውስጥ የሚከተሉት ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ ዝቅተኛ የሆነ የወንድ ዘር ህዋስ መመረት፡- ወንዶች ያልተለመዱ የወንድ የዘር ህዋስ ቁጥር እንዲኖራቸው የሚያደርጋቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ 🔹በተለያዩ ምክንያቶች (ኢንፈክሽ ፣ ጨረር፣ወዘተ) በደማቸው የሚዘዋወረው የቴስቴስትሮን መጠን ዝቅተኛ መሆን በጄኔቲክ ችግር ምክንያት በቂ የወንድ የዘር ህዋሳት ማምረት አለመቻል ስፐርም የሚያፈልቁ ፍሬዎች ሲጎዱ። በዚህም ምክኒያት ምንም እንኳን በወሲብ ጊዜ ማፍሰስ ቢችሉም የወንዴ ፈሳሽ ውስጥ ስፐርም አይኖርም በመሆኑም ማስረገዝ አይችሉም ። 👉 #አጥጋቢ የሆነ እንቅስቃሴ የሌላቸው ወይም ትክክል ያልሆኑ ቅርፆች ያላቸው የወንድ ዘር ህዋሶች መኖር 🔹 ስፐርም ከብልታቸው መፍሰስ ሳይችል ሲቀር የዚህ ምክንያት በአባላዘር በሽታዎች ወይንም በቀዶ ጥገና (ቫሴክቶሚ) የወንድ የዘር ህዋስ መተላለፊያ ቱቦዎች በመጎዳት ሊሆን ይችላል። ምልክቶች 🔹 የወንድ መካንነት ዋነኛው ምልክት ልጅን ለማፀነስ አለመቻል ነው። ሌላ ግልጽ ምልክቶች ወይም ላይኖሩ ይችላሉ። 🔹 በአንዳንድ ሁኔታዎች ግን እንደ ሥር የሰደደ ችግር በዘር የሚተላለፍ በሽታ የሆርሞን መዛባት በወንድ ዘር ዙሪያ የተስፋፋ ደም መላሽ ቧንቧዎች ወይም የወንዱ የዘር ፍሬን የሚያግድ ሁኔታ ምልክቶችን ያስከትላል። እርስዎ ሊያስተውሏቸው የሚችሉ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ 🔹 በግኑኝነት ጊዜ ችግሮች ለምሳሌ ፣ ቶሎ የመፍሰስ ችግር ወይም አነስተኛ መጠን ያለው ፈሳሽ ፣ የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ፣የብልት መነሳት ችግር ( erectile dysfunction) 🔹 በወንድ ዘር አካባቢ ህመም 🔹 እብጠት 🔹 ተደጋጋሚ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች 🔹 ማሽተት አለመቻል 🔹 ያልተለመደ የጡት እድገት (gynecomastia) 🔹 የፊት ወይም የሰውነት ፀጉር ወይም ሌሎች የክሮሞሶም ወይም የሆርሞን መዛባት ምልክቶች 🔹 ከመደበኛ የወንድ የዘር ያነሰ (በወንድ የዘር ፈሳሽ ከ 15 ሚሊዮን ያነሰ የወንዱ የዘር ፈሳሽ ወይም በአንድ የዘር ፈሳሽ ከጠቅላላው ከ 39 ሚሊዮን በታች 👉#ህክምና 🔹 ለወንዶች መካንነት ሕክምናዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ 🔹 ቀዶ ጥገና 🔹 ኢንፌክሽኖችን ማከም 🔹 በግንኝነት ጊዜ ግንኙነት ጋር ተያይዘው ላሉ ችግሮች ሕክምናዎች 🔹 የሆርሞን ሕክምናዎች እና መድኃኒቶች 👉👉 #ይህን እና ተያያዥ የሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ያሎትን ጥያቄዎች ለማቅረብ ወደ 8809 ይደውሉ ከባለሙያ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ !! (#በጤና #ባለሙያ #ትዕግስት)

#ጥያቄ:እናቴ 55 አመቷ ነው፣ሀኪሞች አጥንቷ ሳስቷል አሉኝ፣ምን አልባት ትንሽ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጡኝ የወንድማችን ጥያቄዎ ተቀባይነት ያለው ነው፣ስለዚህ ትነሽ ነገር ልበል የአጥንት መሳሳት(Osteoporosis)ምንድን ነው? -Osteoporosis የምንለው የሰውነታችን የአጥንት መሳሳት ችግር ሲሆን የአጥንት የሚነራል ክምችት(Bone mineral density) በእጅጉ እንዲቀንስ የሚያደርግ ችግር ነው። -አጥንቶቻችን ያለማቋረጥ ሊሰባበሩ የሚችሉ ከዛም የሚተካ አካል ነው።ነገር ግን አዲስ አጥንት መተካት ሳይችል ሲቀር የአጥንት መሳሳት ሊያመጣ ይችላል። ማንን ያጠቃል? -የአጥንት መሳሳት ሴቶችም ወንዶችም ላይ ሊከሰት የሚችል በተለይም እድሜያቸው ገፋ ያሉ ሴቶች ላይ እና ከማረጥ በዃላ(post menopause) ፣ እድሜ እየገፋ ሲሄድ የ Estrogen hormone እየቀነሰ ስለሚሄድ ፣ወንዶች ላይ ደግሞ የ testesretone hormone ማነስ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ ምክንያቱ ደግሞ እነዚህ hormones ለ አጥንት መጠንከር አስፈላጊ ስለሆኑ ነው። ለ አጥንት መሳሳት የሚያጋልጡን ተጨማሪ ነገሮችስ? -የተመጣጠነ ምግብ እጥረት(Malnutrition) -መድሀኒቶች ለምሳሌ Corticosteroid የምንላቸው ለቀላሉም ለከባዱም ህመም በተደጋጋሚ የምንወስዳቸው ማስታገሻዎች፣ለአስም የሚወሰዱ,በተጨማሪ Anticonvulsant የምንላቸው የሚጥል በሽታ መድሀኒቶች -ሲጋራ ማጨስ፣አልኮል መጠጥ -የኩላሊት፣የጉበት ችግር፣የአንጀት መቆጣት ችግር ምልክቶቹስ? -በአብዛኛው ጊዜ የአጥንት መሳሳት ስበራት እስኪኖር ድረስ ምልክት ላያሳይ ይችላል ። -ምልክት የሚያሳይ ከሆነ አጥንት አካባቢ የህም ስሜት፣የቁመት መቀነስ(height loss) የሚያመጣውስ ችግር? -በመውደቅ ወይም በግጭት አንዳንዴ ጎንበስ ስንል እንኳን የአጥንት መሰበር በተለይም የጀርባ አከርካሪት እና የዳሌ አጥንት ስብራት በቀላሉ መሰበር(Hip fracture) እሰከ የእለት ከእለት አንቅስቃሴ ማገድ ድረስ፣ሊያደርስ ይችላል።ይህ ሲሆን ደግሞ የሰውነት ክብደት መጨመር ከዛም ከውፍረት መጨመር ጋር ተያይዞ ለስኳር፣ለልብ በሽታ ተጋላጭነት ይጨምራል። -የ አከርካሪ እና የዳሌ አጥንት ስብራት እሰከ ሞትም ሊያደርስ ይችላል። እንዴት መከላከል እንችላለን? -በቂ የሆነ የፀሀይ ብርሀን ማግኘት Vitamin D የምናገኝበት ስለሆነ እና Vitamin D ደግሞ ለአጥንት ጥንካሬ በጣም ወሳኝ እና ዋነኛው ነገር ነው -የተመጣጠነ በካልሽየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ለምሳሌ ወተት እና የወተት ተዋፅኦ፣ የአሳ ምርቶች እንዲሁም በzinc፣magnesium፣የበለፀጉ ምግቦች፣የብርቱካን ጭማቂ -በቂ የአካል በቃት እንቅስቃሴ ማድረግ -ተመጣጣኝ የሰውነት ክብደት እንዲኖረን ማድረግ -ቡና እና ጨው አለማብዛት ምክንያቱም ካልሽየም በብዛት በሽንት እንዲወጣ ስለሚያደርጉ የአጥንት መሳሳት እንዴት ማረጋጋጥ እንችላለን? -የአጥንት ሚንራል ክምችት በ central dual-energy x-ray absorbitometry(DXA) ታይቶ መረጋገጥ ይችላል። ህክምናውስ? -አጥንት እንዲደራጅ እና የስብራት ተጋላጭነት አንዲቀንስ የሚያደርጉ መድሀኒቶች መስጠት የአጥንትን የሚነራል ክምችት ሙሉ በሙሉ መመለስ ባይቻልም በተወሰነ መለኩ መመለስ ይችላል። -ያረጡ ሴቶች ላይ Estrogen የመተካት ህክምና -ስብራት ካለ ስብራቱን መጠገን ነገር ግን በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ስብራት ከተከሰተ በዃላ መጠገን እና ወደነበረበት መመለስ ጊዜ የሚወስድ እና ትንሽ ከበድ ስለሚል መጠንቀቅ ይገባል። ጤና ይብዛይሎ ዶ/ር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ

✅ የኪንታሮት መንስኤና መፍትሄዎች (ህክምና) ✅ ይህ መረጃ በዚህ ችግር ለሚሰቃዩ ሰዎች ይደርስ ዘንድ በቅድሚያ ሼር ብታደርጉትና ወደ ንባብ ብትገቡ ደስ ይለናል፡፡ መልካም ንባብ… የቂጥ ኪንታሮት ሠገራን በምናስወገድ ጊዜ ከማማጥ ወይንም በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት የደም ስሮች ላይ የሚገኝ ግፊት ምክንያት የሚመጣ ሲሆን በሁለት መልኩ ይከፈላል፡፡ 🌀👉1, ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoid) በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ 🌀👉2, ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoid) በላይኛው ቆዳ ላይ የሚገኝ ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰት ሲሆን በተለይ ዕድሜያቸው 50 ዓመት የሞላቸው ሰዎች ላይ በስፋት (ግማሽ በሚሆን ደረጃ) የኪንታሮት ምልክቶች እንደሚያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ በቤት ውስጥ ሕክምና እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ በማድረግ ይድናሉ፡፡ ✅ ኪንታሮትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች 👉 ሠገራን ሲያስወግዱ ለረጅም ጊዜ ማማጥ 👉 ለረጅም ሰዓታት በመፀዳጃ ቤት መቀመጥ 👉 የሆድ ድርቀት (ለረጅም ጊዜ የቆየ) 👉 ከመጠን ያለፈ ውፍረት 👉 ዕርግዝና 👉 የፋይበር መጠኑ የቀነሰ ምግብ መመገብ ናቸው 👉 በዕድሜ መጨመር ቬይኖችን የሚደግፉ የሰውንት ክፍሎች እንዲደክሙ ስለሚያደርግ ለሄሞሮይድ ያጋልጣል፡፡ ✅ የኪንታሮት ምልክቶች 👉 ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደም 👉 በሰገራ መውጫ አካባቢ ማሳከክ 👉 ሕመም ወይንም አለመመቸት 👉 በፊንጢጣ አካባቢ እብጠት ናቸዉ፡፡ ✅ ሃኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው? 👉በፊንጢጣ የሚወጣ ደም የኪንታሮት የተለመደ ምልክት ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎች የሕመም ዓይነቶች እንደ ኮሎሬክታል ካንሰር እና ሌሎች የህመም አይነቶች ጋር ተመሳሳይ ምልክት ሊኖረው ስለሚችል ሄሞሮይድ ነው በሚል ግምት ችላ ሊባል አይገባም፡፡ ስለዚህም ወደ ሐኪም በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ 👉ከፍተኛ ሕመም የሚሰማዎ ከሆነ እና በቤት ውስጥ የሕክምናዎች ለውጥ የማያገኙ ከሆነ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይገባዎታል፡፡ 👉ከፍተኛ መጠን ያለው ደም መፍሰስ ካጋጠምዎ እና እንዲሁም ራስ የማዞር የመሳሰሉት ስሜት ከተሰማዎ ወደ ሐኪም እንዲሄዱ ይመከራል፡፡ ✅ ኪንታሮት የሚያስከትለው ተያያዥ ጉዳቶች ምንድን ናቸዉ? 👉 አኒሚያ (የደም ማነስ) ከፍተኛ የሆነ ደም በሚፈስ ጊዜ በሰውነታችን ውስጥ ኦክስጂን ተሸካሚ ቀይ የደም ሴሎች መጠን ስለሚቀንስ የድካምና ራስ የመሳት ሁኔታዎችን ያስከትላል፡፡ 👉 ለውስጣዊ ሄሞሮይድ የሚደርሰው የደም ፍሰት መጠን ሲቀንስ ከፍተኛ የሆነ ሕመምን ያስከትላል፡፡ ይህም ለሴሎች መሞት እና ለጋንግሪን ይዳርጋል፡፡ ✅ በቤት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎችና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች 👉 ለብ ባለ ውሃ ከ10 – 15 ደቂቃ በቀን በቀን ሁለትና ሶስት ጊዜ መዘፍዘፍ 👉 ሁሌም ከተፀዳዱ በኋላ በሚገባ በንፁህ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ 👉 ደረቅ የሆነ የመፀዳጃ ወረቀትን አለመጠቀም 👉 እብጠት እንዲቀንስ በረዶን መጠቀም 👉 ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መጠቀም ከላይ የተጠቀሙትን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሄሞሮይድን ማጥፋት የሚቻል ሲሆን ሕመም የሚያብስ ከሆነ እና ምንም ዓይነት ለውጥ በሳምንት ውስጥ ካላገኙ ወደ ሕክምና ቦታ እንዲሄዱ ይመከራል፡፡ ✅ ሄሞሮይድን ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባል? 👉 በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር - አትክልት፣ፍራፍሬዎችን መመገብ ሠገራን በማለስለስ ማስማጥ እንዳይኖር ያድርጋል፡፡ 👉 ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ - በቀን ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃን ወይም ጭማቂን መውሰድ 👉 ማስማጥን ማስወገድ - ሠገራን ለማስወጣት በምናምጥ ጊዜ በደም ስሮቻችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ግፊትን ስለምንፈጥር ለሄሞሮይድ/ለኪንታሮት/ ተጋላጭንት ይጨምራል፡፡ 👉 ሠገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያልፉ ወደ መፀዳጃ ቤት በመሄድ ያስወግዱ፡፡ አለዚያ ሠገራዎ ስለሚደርቅ ለማስወገድ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ 👉 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያዘውትሩ - የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ጤናማ እንድንሆን ያደርጋል፣ 👉 ለረጅም ሰዓታት መቀመጥን ያስወግዱ፡፡ በተለይም በመፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ለሄሞሮይድ መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

✍ #በተደጋጋሚ #ሽንቶ #እየመጣ #ተቸግረዋል? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ማለት ጤናማ ከሚባለዉ ከሽንት መምጫ ጊዜ በበለጠ በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ሲኖር ማለት ነዉ፡፡በተድጋጋሚ ሽንት መሽናት ስራዎን እንቅልፍዎን እና አጠቃላይ ሰላምዎን ሊያስተጓጉል ይችላል፡፡ ስለዚህም የዚህን ችግር መነሻ እና ህክምናዉን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነዉ፡፡ 👉 #መንስኤ 📌 የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን 📌 የስኳር ህመም 📌 እርግዝና 📌 የፕሮስቴት እጢ ችግር 📌 ሽንት የሚያሸኑ መድሀኒቶች መጠቀም 📌 የነርቨ ችግር 📌 የኩላሊት በሽታ 📌 አንዳንድ ለካንሰር የሚሰጡ ህክምናዎች 📌 የሽንት መጠንን የሚጨምሩ ንጥረ ነገሮች እና መጠጦች 👉 #መፍትሄ 📌 በቀን ከ 8-10 ብርጭቆ ውሀ መጠጣት 📌 የሽንት መጠንን የሚጨምሩ እንደ ካፌን እና አልኮል ያሉ ንጥረ ነገሮችን መቀነስ 📌 ሽንቶዎን አለመቋጠር 📌 ወደ መኝታ በሚሄዱ ጊዜ ፈሳሽ ነገሮችን አለመጠቀም 📌 ለዳሌ አጥንት የሚረዱ እንቅስቃሴዎችን መስራት 👉👉#በተደጋጋሚ ሽንቶ እየመጣ ተቸግረዋል!! ይህን እና ተያያዥ የሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ያሎትን ጥያቄዎች ለማቅረብ ወደ 8809 ይደውሉ ከባለሙያ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ! (#በጤና # ባለሙያ# ስጦታ )

ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት በራሳችን ልናደርግ የምንችላቸዉ፡፡ 👇 ማድረግ የሚገባ -------------------- #ቋሚ የመተኛ ሰዓት መመደብ #ቋሚ የመነሻ ሰዓት መመደብ (አእምሮአችን መደበኛ የሆነ የእንቅልፍ ፕሮግራም እንዲይዝ ያደርጋሉ ፡፡) #የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ (ጠዋት ጠዋት ቢሆን ይመረጣል ) #እራት በጊዜ መመገብ ( ከመተኛት ሶስት-አራት ሰዓት ቀደም ብሎ ) #መኝታ ክፍልን ብርሀን ያልበዛበት፣ ጸጥተኛና ቀዝቀዝ ያለ ማድረግ ማድረግ የሌለብን 👇 #አልጋ ላይ ሆኖ ስልክ ማወራት፤ ቻት ማደረግ #አልጋ ላይ ሆኖ ቲቪ ማየት፣ ሬዲዮ ማዳመጥ #አነቃቂ ነገሮች አመሻሽ ላይ መጠቀም #አልኮል መዉሰድ (ለአጭር ጊዜ የሚረዳ ቢመስልም ከጊዜ በኃላ የተቆራረጠ እንቅልፍ ያስከትላል ፡፡) ከላይ የተዘረዘሩት ቀላል ዘዴዎች ስለሆኑ የማይሰሩ ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ የእንቅልፍ ችግር ያለባቸዉን ሰዎች ያለ መድኃኒት ጥሩ እንቅልፍ እንድተኙ ረድተዋል፡፡ ከእንቅልፍ ጋር ተያይዞ ህክምና የሚያስፈልጋቸዉ 👇 -ከላይ የተጠቀሱትን አድርገን አሁንም በቂ እንቅልፍ የማናገኝ ከሆነ - ተያያዞ የድብርት ስሜት የሚሰማ ከሆነ -ተያይዞ ጭንቀት ካለ -በአጠቃላይ የእንቅልፍ ችግሩ በሥራችን ወይም በማህበራዊ ህይወታችንን ላይ ተፅኖ ካሳደረ። አንድ ሶስተኛ ስንንከባከብ ሁለት ሶስተኛው ላይ የበለጠ ውጤታማ መሆን እንችላለ ለምን የሙከራ ስራውን ዛሬ አንጀምርም።መልካም አዳር

መካንነትን እንደት መከላከል ይቻላል? በተለይ በሴቷ በኩል? • ጤናማ የአኖኖር ዘይቤን መከተል • ከፍተኛ የአካል እንቅስቃሴን መተው • አነቃቂ መጠጦችን መቀነስ • አልኮልን መተው ወይም መቀነስ • አለማጤስ • የተመጣጠነ ምግብ • አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ • ክብደትን ማመጣጠን • የተለያዩ በሽታዎች ካሉ መታከም • ስኳር ህመም ካለ መታከም • የታይሮድ መጠን አነስተኛ ወይም ከፍተኛ መሆነ ለማስተካከል መሞከር • እራስን ከአባላዘር በሽታ መጠበቅ። ካለ ፈጥኖ መታከም • ሳይዘገዩ ለማርገዝ መሞከር • የጤና ምርመራ በየጊዜው ማድረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ስለመካንነትና ህክምናው ማወቅ ይፈልጋሉ? እንግዳውስ ይሄው ብለናል። ግን ግን ሸር ማድረጉን አደራ! (መካንነት ወይም መፀነስ አለመቻል) • ይህ ችግር Infertility ከፍ ሲልም sterility እየተባለ ይጠራል። Infertility በተለያየ ምክናየት መፀነስ ማርገዝ አለመቻል ቢሆንም የተለያዩ ህክምናዎችን በማግኝት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል። Sterility ግን ፈፅሞ የመፀነስ እድል አለመኖርም ሲሆን ይህ አይነት ችግርም የመፈጠር እድሉ በጣም አነሳ ነው። ውድ ስለጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀት ቤተሰቦችና ተከታታዮች ዛሬ ካላይ የጠቀስኩትን ርዕስ ጠቅለል አድርጌ መካንነት በሚል እርስ ዙሪያ ይጠቅማል ያሉኩትን አጠር ያለ፡ ግልፅና አስተማሪ የሆነ መረጃ እንሆ ብያለሁ። ይህን መረጃ ከወደዱት ቢያጋሩት የብዙዎችን ጭንቀት እንደሚቀርፍ አልጠራጠርም። • አንድት እናት እድሚዋ ከ35 አመት በላይ ከሆናትና ለአድ አመት ያህል የመውለድ ሙከራ አድርጋ ካልተሳካ መከነች (ማርገዝ አትችልም) እንላለን። መፀነስ እንኳ ብትችል እድገት መጀመርና መቀጠል ካልቻለም እንድሁ የማርገዝ ችግር እንዳለባት ይቆጠራል። • እንደሚታወቀው እርግዝና ሂደት ነው። ደረጃ በደረጃ የሚከወን። ሴቷ ካሏት ሁለት ኦቫሪ (እንቁላል መፈጠሪያና ማደጊያ ክፍል) በየወሩ እንቁላል ትለቃለች። ይህ የሚሆነው የወር አበባ ማየት በጀመረች በ14ኛው ቀን ነው። በመቀጠል የምትለቀቀው እንቁላል ፊምብሪያ (የማህፀን ጣት) በሚባል የማህፀን ከፍል በመነጠቅ fallopian tube (የማህፀን ክንፍ) በሚባለው የማህፀን ክፍል ላይ ማለፍ ይጠበቅባታል። እዚሁ ክፍል ላይም የወንድ የዘር ፍሬ ደርሶ ውህደት መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። በመቀጠል እቡጡ(zygote) ወደ ማህፀን ዋና ክፍል ወይም ሆድ ክፍሉ Endometrium (የማህፀን የውስጠኛ ክፍል) ላይ መቀመጥና እድገት መጀመር ይጠበቅባቸዋል። • እንግድህ መካንነት(ማርገዝ አለመቻል) የሚፈጠረው ከላይ ከዘረዘርናቸው ሄደቶች ወይም ክንውኖች አንዱ ወይም ሁለት ሶስቱ ሳይካሄድ ሲቀር ነው። በአጭሩ ችግሩ ከእንቁላሏ ጤንነት ወይም ከዘር ፍሬ ጤንነት አለያም ከጉዞአቸው መደናቀፍ ወይም ከቦታው አለመመቸት ጋር የተያያዘ ነው። • የመካንነት ምክናየት ከሴቷ ወይም ከወንዱ ችግር ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሁለቱም። 1/3ኛ የሴቷ፡ 1/3ኛ የወንዱ፡ ቀሪው 1/3ኛ የሁለቱም ወይም የማይታወቅ ምክናየት ነው። በወንዶች በኩል የሚመጣው ችግር ከምን ጋር ሊያያዝ ይችላል? • Varicocele የሚባል ችግር ቀዳሚ ነው። ይህ ችግር ቀጫጭን የደም ቱቦዎች ተፈጥረው(viens) ከዘር ፍሬ የሚነሱ ስለሆኑ ያብጡና ትላልቅ ይሆናሉ። ይህም የዘር ፍሬ ለከፍተኛ ሙቀት ያጋልጠውና ውጤታማ እንዳይሆን ያደርገዋል። • የዘር ፍሬ ቅርፅ መበላሸት፡ በቁጥርና መጠን ማነስ • እንቅስቃሴው ዘገምተኛ ወይም ደካማ መሆን • የተለያዩ አካላዊ ጉዳት ወይም አደጋ ማጋጠም • አልኮል ጠጭ መሆን • የተለያዩ መድሀኒቶችን ተጠቃሚ መሆን • መርዛማ ለሆኑ ነገሮች መጋለጥ • ማጤስ • የኩላሊት ችግር • የሆርሞን መዛባት • የካንሰር ህክምና • እርጅና በሴቶች በኩል የሚመጣ ችግር ከምን ጋር ሊያያዝ ይችላል? • ብዙ ጊዜ በሴቶች በኩል የሚፈጠረው ችግር በኦቩሌሽን ወቅት የሚፈጠር ነው። እንቁላልን መልቀቅና አለመልቀቅ ጋር ይያያዛል።ኦቩሌሽን ፔሪድ ማለት የወር አበባ ማየት ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ሲቆጠር 14ኛዋ ቀን ነች። ይች ቀን እንቁላል የምትለቀቅባትና ለፅንስ ዝግጁ የምትሆንባት ቀን ነች። ስለዚህ በዚህ ቀን እንቁላል ካልተለቀቀ ፅንስ አይፈጠርም። የዚህ ምልክቱ ደግሞ የወር አበባ መዛባት አንዳንድ ጊዜም ፈፅሞ አለመኖር ነው። • እንቁላል ካለችበት ቦታ (ከኦቫሪ) እንዳትወጣ የሚያደርጋት ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ዋናዋናዎቹ ግን ትናንሽ እጢ መሳይ ነገሮች በኦቫሪ ውስጥ መፈጠራቸውና ኦቫሪ ከ40 አመት ቀድሞ ስራውን ሲያቆም ነው። • ሌላው ብዙ የተለመደ ባይሆንም የማህፀን ቀኝና ግራ ክፍሉ (ክንፍ) በተለያየ መንገድ በመዘጋቱ እንቁላሏ ከዘር ፍሬ ጋር እንዳትገናኝ በማድረጉ ሊሆን ይችላል። ይህ ችግር የዳሌ አጥንት ዙሪያ ኢንፌክሽን፡ ኢንዶሜትሪዎሲስና ከማህፀን ውጭ በተፈጠረ ፅንስ ሊከሰት ይችላል። • በተጨማሪም ማንኛውም በማህፀንና በኦቫሪ ውስጥ የሚፈጠር ችግርና የሚያድግ እጢ ምክናየት ይሆናል። ሴቶች እርግዝናቸውን እንድያጡ ወይም መካን ሆነው እንድቆዩ የሚያደርጉ ሌሎች አጋላጭ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው። • እድሜ • ጭንቀትና ውጥረት • ያልተመጣጠነ ምግብ • የሩጫ ልምምዶች • ከመጠን በላይ መወፈር • ከመጠን በታች መቅጠን • ማጤስ • ከመጠን ያለፈ መጠጥ • የአባላዘር በሽታ • የተለያዩ የጤና ችግሮን ለምሳሌ እጢ፡ የኦቫሪ ስራ ማቆም፡ የሆርሞን ችግርና ሌሎችም። • እርጅና/ እድሜ መጨመር ይህም በቂ እንቁላል አለማምረት፡ አነሳ እንቁላል መልቀቅ፡ ጤናማ እንቁላል አለመኖርና ሌሎችም ናቸው። ®በነገራችን ላይ አንድት ሴት እድሜዋ 30ን ካለፈ በየአመቱ የማርገዝ እድሏ በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል። ስለዚህ ሴቶች እድሜአችሁን ሳትገድሉ እንድትወልዱ ይመከራል። እድሜ አሳልፎ የመጣ ርግዝና ሌላም ሌላ ችግር አለውና። ይህ ማለት ግን ማንኛዋም በእድሜ የገፋች ሴት ለመውለድ ትቸገራለች እያልን አይደለም። የመካንነት ህክምና ምንድን ነው? • ነፃ ሆኖ ጊዜ መስጠት ይጠበቃል። ውጤታማ ህክምናም አለው። 1. የመጀመሪያው ለእርግዝና ወሳኝ በሆኑ ወቅቶች የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ እንድችሉ ማድረግ ነው። ይህም ችግሩ ከምን እንደሆነ ለማወቅ ያግዛል። ለምሳሌ የማይዛባ የወር አበባ ኡደት ላላት ሴት የሚከተለውን ምሳሌ እንይ። ለምሳሌ ወይዘሮ ከበቡሽ የወር አበባዋ በ18/09/12 መምጣት ቢጀምር ዛሬ ማለት ነው። ደግሞም በየ28 ቀኑ የሚመጣ ወጥ ከሆነ፡ 02/10/12 ቀን ኦቩሌሽን ፔሬድዋ ነው። ከበቡሽ ማርገዝ ከፈለገች በሚከተሉትን ቀናት የግብረስጋ ግንኙነት መፈፀም ይኖርባታል። 29/09/12, 30/09/12, 01/10/12, 02/10/12, 03/10/12, 04/10/12 እና 05/10/12 ዓ.ም. ከበቡሽ ምንም አይነት ችግር ከሌለባት የትዳር አጋሯም ጤናማ ከሆነ እነዚህን ቀናት ሳትፀንስባቸው ልታልፍ አትችልም። በተለይ 02/10/12 ዓ.ምን። 3እጅ መካንነትም ከዚህ አለመመጣጠን ጋር የተያያዘ ነው። 2. የተለያዩ መድሀኒቶችን በመጠቀም መካንነትን ማከም ይቻላል። ለምሳሌ Clomphene እና Serophene ውጤታማ ናቸው። መካን ነን ከሚሉ ግማሽ ያህሎቹ ሴቶች በClomphene መድሀኒት ውጤት ያመጣሉ። (እንድያረግዙ ያደርጋቸዋል)። ይህን መድሀኒት የተጠቀመች ሴት መትያ ልጆችን የመውለድ እድሏን ይጨምራል። 3. የተዘጋ የማህፀን ክፍልን በቀዶ ጥገና በመክፈት እንቁላሏና የዘር ፍሬ በቀላሉ እንድገናኙ በማድረግ ይታከማል። 4. የዘር ፍሬ እንቅስቃሴ ደካማ ከሆነ ከወንዱ ወስዶ ሴቷ ውስጥ በመሳሪያ በመጨመር የዘር ፍሬዎቹ በራሳቸው እንድገናኝ በማድረግ ይታከማል። 80% ውጤታማ ነው። 5. ከላይ ያለው ካልተሳካ በኦቩሌሽን ወቅት ስፐር ሴሉን በመውሰድ ከእንቁላሏ አጠገብ በማስቀመጥ ይታከማል። እጅግ ውጤታማ ነው። 6. ከላይ ባሉት እንደ አጋጣሚ ባይሳካ በውጮቹ ዘንድ እንቁላልንና የዘር ፍሬን ውጭ ላይ በማሽን ውስጥ በማገናኝት ውህደቱን በመፍጠር የመጨረሻው ህክምናም ይሞከራል።

5ቱን የጉበት ገዳይ በሽታዎች እናስተዋውቃችሁ ሂፐታይተስ የጉበት ብግነት ነው፡፡ የብግነቱ ሁኔታ በጉበት ላይ ጠባሳ ሊፈጥር ወይም ጉበትን ሊያኮማትር ወይም ደግሞ ካንሰር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ለሂፐታይተስ መፈጠር ሂፐታይተስ ቫይረስ ዋነኛ ምክንያት ሲሆን ሌሎች ኢንፌክሽኖች እና መርዛማ ነገሮች ማለትም አልኮልና የተወሰኑ መድኃኒቶች እንዲሁም የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከያ አቅም አዳካሚ በሽታዎች ለሂፐታየተስ መፈጠር ተጠቃሽ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት አምስት ዓይነት የሂፐታየተስ ቫይረሶች እያንዳንዳቸው አምስት የሂፐታየተስ በሽታዎችን ያስከትላሉ፡፡ ሂፐታየተስ ኤ፣ቢ፣ሲ፣ዲ እና ኢ በሽታዎች በመላው ዓለም ለብዙዎች ሕመምና የሞት ምክንያት ናቸው፡፡በተለይ ሂፐታየተስ ቢ እና ሲ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች በጉበት መኮማተርና ካንሰር ተጠቅተው ወደ ሞት የሚወስዱ አደገኛ በሽታዎች ናቸው፡፡ ሂፐታይተስ ኤ ቫይረስ ( ኤች ኤ ቪ) 1. ሂፐታይተስ ኤ ቫይረስ የሚገኘው በተበከለ ሰው አይነምድር ውስጥ ሲሆን ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በአይነምድር የተበከለ ምግብ ወይም ውሀ በምንወስድበት ጊዜ ነው፡፡ 2. የተወሰነ የግብረስጋ ግንኙነት ይህን ቫይረስ ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ 3. የንፅህና ጉድለት ባለባቸው የዓለም ክፍሎች በስፋት ይህ ቫይረስ የሰዎችን ሕይወት እየነጠቀ ይገኛል፡፡ 4. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት በየአገሩ ይሰጣል፡፡ ሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ (ኤች ቢ ቪ) 1. ቫይረሱ የሚተላለፈው በደም፣በስፐርም እና በሌሎች ፈሳሽ ነገሮች ነው፡፡ 2. ሌላው የቫይረሱ መተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተጠቃች እናት በምትወልድበት ጊዜ ወይም ህፃናት በልጅነት ጊዜያቸው በቫይረሱ ከተጠቃ የቤተሰብ አባል ሊሆን ይችላል፡፡ 3. በቫይረሱ የተበከለ ደምና የደም ተዋሀፆ በመስጠት ወይም በማስተላለፍ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 4. በሕክምና ወቅት በቫይረሱ የተበከ መርፌ በመጠቅም አንዱ መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡ 5. በመርፌ በሚወሰዱ አድገኛ መድኃኒቶችና እፆች አጠቃቀም ወቅት ሌላው መተላለፊያ መንገድ ሲሆን በተለይ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጥንቃቄ ንቅሳት (ታቱ) የሚሰሩ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡ 6. የጤና ባለሙያዎች በሕክምና ወቅት መርፌ ሊሰበርባቸውና ራሳቸውን ሊወጉ ይችላሉ በዚህም ለብክለት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ 7. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት በየአገሩ ይሰጣል፡፡ ሂፐታይተስ ሲ ቫይረስ (ኤች ሲ ቪ) 1. አብዛኛው ጊዜ የሚተላለፈው በተበከለ ደም አማካኝነት ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በቫይረሱ የተበከለ ደምና የደም ተዋሀፆ በመስጠት ወይም በማስተላለፍ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 2. በሕክምና ወቅት በቫይረሱ የተበከ መርፌ በመጠቅም አንዱ መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡ 3. በመርፌ በሚወሰዱ አድገኛ መድኃኒቶችና እፆች አጠቃቀም ወቅት ሌላው መተላለፊያ መንገድ ሲሆን በተለይ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጥንቃቄ ንቅሳት (ታቱ) የሚሰሩ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡ 4. በግብረስጋ ግንኙነት ሊተላለፍ ይችላል ነገር ግን ዝቅተኛ ነው፡፡ 5. ይህን ቫይረስ ለመከላከል ምንም አይነት ክትባት የለም፡፡ ሂፐታይተስ ዲ ቫይረስ (ኤች ዲ ቪ) 1. በዚህ ቫይረስ የሚጠቁት በሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ ብቻ የተጠቁ ሰዎች ናቸው፡፡ 2. በሁለቱ ቫይረሶች የሚጠቁ ሰዎች ለአደገኛ በሽታ የሚጋለጡ ሲሆን ውጤቱም እጅግ መጥፎ ሊባል የሚችል ይሆናል፡፡ 3. የሂፐታይተስ ቢ ክትባት በዚህ ቫይረስ ለሚጠቁ ሰዎች መከላከያ በመሆን ያገለግላል፡፡ ሂፐታይተስ ኢ ቫይረስ (ኤች ኢ ቪ) 1. ብዙን ጊዜ የሚተላለፈው የተበከለ ምግብ ወይም ውሃ በምንጠቀምበት ጊዜ ነው፡፡ 2. በተዳጊ አገሮች በስፋት ለሚታየው የሂፐታይተስ ስርጭት ይህ ቫይረስ ግንባር ቀደም ነው፡፡ 3. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት ቢኖርም በስፋት ማግኘት ያዳግታል፡፡