fa
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

رفتن به کانال در Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

کانال ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 19 937 مشترک است و جایگاه 1 156 را در دسته پزشکی و رتبه 1 680 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 19 937 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 28 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -539 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -5 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 25.64% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 7.06% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 5 115 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 408 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 9 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 29 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته پزشکی تبدیل کرده‌اند.

19 937
مشترکین
-524 ساعت
-1197 روز
-53930 روز
آرشیو پست ها
የጌሾ ተክል ለህፃናት ቶንሲል ህመም መፍትሔ እንደሆነ ያውቃሉ? ውድ የኛ ቤተሰቦች ልጆችወን በተደጋጋሚ ቶንሲል እያጠቃብወ ከተቸገሩ በቤትዎ የሚያዘጋጁት ፈዋሽ መድሀኒት ይዘን ቀርበናል። የጌሾ ቅጠል
የጌሾ ተክል ለህፃናት ቶንሲል ህመም መፍትሔ እንደሆነ ያውቃሉ? ውድ የኛ ቤተሰቦች ልጆችወን በተደጋጋሚ ቶንሲል እያጠቃብወ ከተቸገሩ በቤትዎ የሚያዘጋጁት ፈዋሽ መድሀኒት ይዘን ቀርበናል። የጌሾ ቅጠል ጫፍጫፍ ላይ የሚወጡትን ቀንበጦች 7 ቦታላይ በመቁረጥ ትንሽ ውሀ ጠብ እያደረጉ በእጅ በማሸት 1 የሻይ ማንኪያ የጌሾ ጭማቂ በማዘጋጀት ለታመሙት ልጆች ማጠጣት ፍቱን እና የማያዳግም መፍትሔ ነው። ሁሌም ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ ጠቃሚ መረጃችንን ከማካፈል ወድኋላ አንልም አሁንም በድጋሚ ጤናችሁ ይብዛ ለመላው ለአዳም ልጆች የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

ለማመን በሚከብድ አጭር ጊዜ ውስጥ፣ 10ሳሜ በወገብ ዙሪያ የተከማቸ ቦርጭ የሚያጠፋ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ውህድ ጀባ እንበልዎ። Excellent Drink That Melt 10 cm Stomach Fat Waist As If By Magic! **************************************** ይህ አስደናቂ ውህድ ለማዘጋጀት ቀላል ሲሆን፣ 10ሳሜ የሚሆን ቦርጭ ለማጥፋት የሚወስደው ጊዜ አራት ቀን ብቻ ነው። There is a wonderful drink made of just simple ingredients and cleans up 10 cm of waist fat just in four days. ውህዱን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ፣ Ingredients needed for this drink are: -ዝንጅብል /ginger/ -አረንጓዴ ሚንት ቅጠል በተለምዶ ናና የሚባለው ቅጠል /fresh mint leaves/ -ኩኩምበር ወይም ክያር በመባል ይታወቃል /cucumber/ -ሎሚ /lemon/ -8 ብርጭቆ ውሃ /8 glasses of water/ የውህዱ አዘገጃጀት How to prepare the drink በመጀመሪያ ሎሚውን በደንብ ማጠብ እና ለሁለት ቦታ መቁረጥ። ከዛ በጎድጓዳ ሰሃን ውሃ ጨምሮ የተቆረጠውን ሎሚ ውሃው ውስጥ መጨመር ። ኩኩምበሩን መላጥ እና ከታትፎ ውሃው ውስጥ መጨመር ፣ ከዛ ከ 8 እስከ 12 የሚሆኑ አረንጓዴ የሚንት ቅጠል እና ተልጦ በትንንሹ የተከተፈ ዝንጅብል መጨመር ። ሁሉንም ከደባለቅን በኋላ ፍሪጅ ውስጥ ማሳደር፣ (በረዶ ቤት አይደለም ።) በአንዴ መጨረስ ስለሚከብድ ቀስ እያሉ፣ ቁርስ ምሳ መክሰስ ወይም በየተወሰነ ሰዓት ልዩነት ውህዱን መጨረስ ያስፈልጋል። ማሳሰቢያ፣ ውጤቱን በደንብ ለማየት ቢያንስ ለ 4 ቀን መጠጣት ያስፈልጋል። እንዲሁም አመጋገብ ማስተካከል እና የአካል እንቅስቃሴ ብንጨምርበት ደግሞ ገራሚ ለውጥ እናገኛለን። ሰላም ለእናተ ይሁን Wash and do not peel off the lemon, cut into 2 pieces and put them in water in bowl. Peel and chop the cucumber, put in bowl and put washed 8 -12 fresh mint leaves, add them and peeled ginger chopped into slices. Leave it over night in refrigerator. For visible results make this drink at least 4 days. የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

ጥብቅ ማሳሰቢያ 1.አንብበው ላይጨርሱ አይጀምሩት 2.አንብበው ሲጨርሱ ለወገኖ ሼር ያድርጉ ጤና ይስጥልኝ ውድ የዶክተር ቤዛ ተከታታዮች እዴት ዋላችሁ በተደጋጋሚ ግዜ የብዙሃናችሁ ጥያቄ የሆነውን በውስጥ መስመር በተጨማሪ በቴሌግራም ቻላናችን የተጠየቀ ጥያቄ ነው በደንብ ግልፅ እዲሆንላችሁ ስል ፁሁፉ እረጅም አድርጌዋለሁ ሳትሰላችሁ በጥሞና በትግስት ያንብቡት በዚህ ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ በደንብ እደማብራራላች ቃል እገባለሁ ። በወንዶች ሽንት መሽኛ አካባቢ አልፎ አልፎ እየጠፋ የሚመጣ የእብጠት ምልክት ምንድን ነው? የፕሮስቴት እጢ በወንዶች ብቻ የሚገኝ የሰውነት አካል ሲሆን ከወንዶች የስነ ተዋልዶ አካላት ውስጥ አንዱ በመሆን ይጠቀሳል፡፡ ይህ እጢ የሚገኘው ከሽንት ፊኛ በታች ሲሆን የሽንት ትቦ የመሀከለኛውን ክፍል ዙሪያ ከቦ ይገኛል፡፡ ይህ የኦቾሎኒ ያክል መጠን ያለው የፕሮስቴት እጢ ከዕድሜ ጋር መጠኑ እየጨመረ የሚሄድ ሲሆን በተግባሩም ለስፐርም የሚሆነውን ፈሳሽ ከሚያመነጩ የሰውነት አካል ውስጥ አንዱ ሆኖ ይገኛል፡፡ ለዛሬ የምንመለከተው ዋናው ርዕስ የፕሮስቴት እጢ በሚያድግበት ወቅት የሚከተለውን ሁለት አይነት ችግሮች ናቸው ፤ 1. የካንሰር ምልክት/ጠባይ የሌለው የፕሮስቴት እጢ ማበጥ/ማደግ (Benign prostatic Hypertrophy) እና 2. የፕሮስቴት ካንሰር የካንሰር ምልክት/ጠባይ የሌለው የፕሮቴስት እጢ ማበጥ/ማደግ Benign prostatic Hypertrophy ይህ ካንሰር የማያስከትል የፕሮስቴት እጢ ማበጥ ሲሆን መሰረታዊ ምክንያት በውል ባይታወቅም በዕድሜ ለውጥ የሚከተሉ የሆርሞኖችን መለዋወጥ ተከትሎ ሊመጣ እንደሚችል ይገመታል፤ በዚህም ሳቢያ በአብዛኛው የዚህ ችግር ተጠቂዎች የሆኑት ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች ናቸው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው የፕሮስቴት እጢ በሽንት ትቦ ዙሪያ የሚገኝ እንደመሆኑ መጠን መጠኑ በጨመረ ቁጥር ቀስ በቀስ የሽንት ትቦን የመጫንና በዚህም ሳቢያ የማጥበብ ብሎም ጨርሶ የመዝጋት ሁኔታን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በዚህም ሳቢያ የሽንት ፊኛ በዚህ ጠባብ ትቦ ሽንትን ለማስወጣት በሚደረገው ጥረት የሽንት ፊኛ ጡንቻ ማደግና መጠንከር ይከተላል፡፡ ይህም የሽንት ፊኛ ውስጥ ያለው የሽንት መጠን ተሟጦ የመውጣት ስሜት ከማስከተሉም በላይ ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንና ለሽንት ቧንቧ ጠጠር መፈጠር ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ሁኔታዎች እየተባባሱ በመጡ ቁጥርና ጊዜው በረዘመ ቁጥር የኩላሊት መጎዳትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሊከተሉ የሚችሉ ምልክቶች/የህመም ስሜቶች የፕሮስቴት እጢ የማደግ ስሜትን ማስከተል የሚጀምረው የሽንት ትቦ ላይ ጫና በማስከተል ሽንት እንዳይወጣ መከልከል ሲጀምር ነው፡፡ – በመጀመሪያ ደረጃ ሽንት የመሽናት ስሜት ከመጣ በኋላ መሽናት ለመጀመር ጊዜ መፍጀት፣ – ሽንት ጨርሶ ያልወጣ ያልወጣ መስሎ መሰማት፣ – ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣትና ማጣደፍ፤ – በሌሊት ከወትሮው በበለጠ ሁኔታ ከእንቅልፍ ለሽንት መነሳት፤ – ሽንት በሚሸኑበት ወቅት መጠኑ መቀነስና መቆራረጥ እንዲሁም ለመሽናት መታገል፤ – ሽንት ሸንተው ከጨረሱ በኋላ የመንጠባጠብ ሁኔታ፤ – በአንድ አንድ ሁኔታ ሽንት ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ መፍሰስ፤ – በሽንት ትቦና ፊኛ አካባቢ ያሉት ትናንሽ የደም ስሮች ሽንት ለማስወጣት በሚደረገው ግፊት መበጣጠስና በሽንት ውስጥ ደም የመከሰት ሁኔታ፤ – የሽንት ትቦ ከነአካቴው የተዘጋ እንደሆነ ደግሞ ፊኛ ከመጠን በላይ መወጠርና በታችኛው የሆድ ክፍል ከፍተኛ የህመም ስሜት መሰማት፤ – የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የተከሰተም እንደሆነ በመሽናት ወቅት የማቃጠል ስሜት በብልት ላይ መሰማትና እንዲሁም የሰውነት ትኩሳት መከተል ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ግዴታ በአንድ ላይ ይከሰታሉ ማለት ባይሆንም በእነዚህ ጥቂት ስሜቶች ብቻ ቢኖሩም የዚህ ችግር ምልክት ለመሆን ይበቃሉ፡፡ እነዚህ ስሜቶች በሚኖሩን ጊዜ በምን ማወቅና ማረጋገጥ ይቻላል የሚለውን ከታች የምንመለከተው ይሆናል፡፡ ፕሮስቴት ካንሰር የፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ በብዛት የሚታይ ሁኔታ ቢሆንም እንደ አብዛኛው የካንሰር አይነቶች መንስኤው በውል አይታወቅም፡፡ በፕሮስቴት እብጠት ሳቢያ በቀዶ ጥገና ከሚወገዱ የፕሮስቴት እጢዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆነው ዕድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ የሚገኘው የፕሮስቴት እብጠት ካንሰር መሆኑን ያመለክታል፡፡ በአብዛኛው ጊዜ የፕሮስቴት ካንሰር ቀስ በቀስ የሚያድግና የሚሰራጭ እንደመሆኑ መጠን አስከፊ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ምንም አይነት ስሜት ላያስከትል ይችላል፡፡ ሊከተሉ የሚችሉ ምልክቶች/የህመም ስሜቶች ከላይ እንደተጠቀሰው የፕሮስቴት ካንሰር አደገኛ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ በአብዛኛው ጊዜ ምንም አይነት ምልክት ባያስከትልም በፕሮስቴት እብጥት ሳቢያ ሊከተሉ የሚችሉ ምልክቶችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ነገር ግን የፕሮስቴት ካንሰር መሰራጨት ከጀመረ በኋላ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እንደ አጥንት፣ ኩላሊት ብሎም ወደ አንጎል በመሰራጨት የተለያየ አይነት የህመም ስሜቶችና ሁኔታዎችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህንን ችግር በምን ማረጋገጥ ይቻላል? አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች በሚሰሙበት ወቅት ወይም የጤና ባለሙያ ይህንን ሁኔታ በሚጠራጠርበት ወቅት ሊደረጉ ከሚገባቸው ምርመራዎች ውስጥ፤ – በፊንጢጣ በኩል ጣትን በማስገባት የፕሮስቴት እጢው ማበጥ አለማበጡንና፣ ከዚያም በተጨማሪ አስፈላጊ የሆኑ የመለያ ነጥቦችን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ – ከዚህም በተጨማሪ አልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ ችግሩ መኖሩንና ከሆነም ደግሞ ካንሰር የመሆንና ያመሆኑን ሁኔታ በተሻለ ሁኔታ መገመት ይቻላል፡፡ – የፕሮስቴት ዕጢ ማደጉንና እንዲሁም ካንሰር የመሆን ዕድሉን ሊነግረን የሚችልም የደም ምርመራ እንደመኖሩ ይህንን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ እንዲያውም ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች ላይ ይህንን የደም ምርመራ በየዓመቱ ማድረግና አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡ – ከፕሮስቴት ዕጢ ናሙና በመውሰድ የእጢውን ሁኔታ ማረጋገጥም ተመራጭ የሆነውና እርግጠና ሁኔታውን ሊነግረን የሚችል የምርመራ አይነት ነው፡፡ – የፕሮስቴት ካንሰር የተሰራጩ እንደሆነም እንደ የአስፈላጊነቱ የተጠቃውን የሰውነት አካል የተለያዩ ምርመራዎች ማድረግ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ይረዳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ስሜቶች የሌላ ህመም መገለጫ ሊሆኑ እንደመቻላቸው አስፈላጊውን ምርመራ እንደ የአስፈላጊነቱና በደረጃ ማድረግ መሰረታዊ ነው፡፡ ስለዚህም ትንሽ ነው ብለን ጊዜ የሰጠነው የፕሮስቴት ዕጢ ችግር ለባሰ ሁኔታ ሳያጋልጠን በጊዜ ህክምና ብንወስድበት ስለ ህመሙም አውቀን የቅድመ ጥንቃቄ ወይም የመከላከል እርምጃ ብንወስድ መልካም ነው፡፡ መልካም ጤንነት እሁድ ተመኘውሎ በዚች የሒሳብ ጥያቄ ዘና እያላችሁ እሁድን ከኛጋር

#መደንዘዝ .........! 💊ለዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው ጠቃሚ የጤና መረጃችን ከጭን እስከ እግር ጣት ጫፍ ድረስ ስለሚፈጠር #የመደዘዝ፡ #የመጠዝጠዝ፡ #የማቃጠልና #የስሜት መጥፋትን አስመልክቶ ነው። • ይህ ችግር በዋናነት ሁለት ምክናየቶች አሉት። 1. ወደ እግር የሚሰራጨው የደም መጠን መቀነስና 2. እግርን የሚቆጣጠረውና ወደ እግር የተዘረጋው የነርቭ ክፍል ጉዳት ሲደርስበት ነው። #ከነዚህ ዋና ዋና ምክናየቶች በተጨማሪ የሚከተሉት ተጨማሪ ምክናየቶችም አሉ። • የደም መርጋት • ቅዝቃዜ • የአጥንት መሳሳት • የድስክ መሸራተት • ብዙ አልኮል መጠጣት • የቫይታሚን ቢ 12 ማነስ • ኢንፌክሽን • የተለያየ አካላዊ ጉዳት በእግርና ጀርባ ላይ ሲደርስ • የሚሰራጭ የካንሰር አይነት • የተለያዩ በሽታዎች እንደ ደምግፊት፡ ስኳር፡ ሪህ፡ የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን፡ የኩላሊት ችግር፡ የጉበት ችግር፡ ስትሮክ፡ ሌሎችም • ለብዙ ሰአት መቀመጥና እግርን አነባብሮ መቀመጥ #ውድ የኛ ቤተሰቦች የመደዘዝና የመጠዝጠዝ ስሜቱ ጊዜአዊ ከሆነ በቀላሉ የሚለቅና የሚስተካከል ችግር ሲሆን ለረጅም ጊዜ የቆየና እየባሰ የሚሄድ የመደዘዝና የመጠዝጠዝ ስሜት ካለና እየቆየም ሰገራንና ሽንትን መቆጣጠር መቸገር፡ እግርን መቆጣጠርና ማንቀሳቀስ አለመቻል፡ የንግግር መቆራረጥና ግራ መጋባት ጋር ከሆነ ግን አስቸኳይ የጤና ባለሙያ እርዳታ ያስፈልጋል። #የእግር መደንዘዝ ከጀርባ ችግር በተለይ ከታችኛው የወገብ ክፍል ጋር ሊያያዝ ይችላል። • ስለዚህ መደንዘዝ፡ መጨነቅ፡ የማቃጠል ስሜት፡ ቶሎ ቶሎ መሽናት፡ ማሳከክ፡ መጠዝጠዝ፡ የጡንቻ መሸማቀቅና ሽፍታ የእግር የመደንዘዝ ስሜት ጋር የሚያያዝ ነው። በቅንት ሼር

ይህን ያውቃሉ በግንኙነት ወቅት የሚያጋጥሙ ድክመቶች መቅረፍ እንደሚቻል በግብር ስጋ ጊዜ የሚያጋጥሙ ሁሉንም ድክመቶችን መቀርፍ ወዲያዉ መጨረስን የሚያዘገይ የእቃን መጠንና እርዝመትና ውጥረት የሚያስተ
ይህን ያውቃሉ በግንኙነት ወቅት የሚያጋጥሙ ድክመቶች መቅረፍ እንደሚቻል በግብር ስጋ ጊዜ የሚያጋጥሙ ሁሉንም ድክመቶችን መቀርፍ ወዲያዉ መጨረስን የሚያዘገይ የእቃን መጠንና እርዝመትና ውጥረት የሚያስተካክል ያሉበት ቦታ ድረስ ለተጨማሪ መረጃ (0992484672) በአዲስ አመራረት original vimax silver 60 capsual 🤗made in canada ✓ የብልትን መጠን ለመጨመር እንዲጨምር ✓ቶሎ የመጨረስ ችግር ✓ ለወሲብ ፍላጎት ማጣት በዘላቂነት ለመቅረፍ ፈለክ ስመጥር የሆነው new vimax silver 60 capsul እኛ ጋር ይገኛል። መፍትሄው አለ ከጎንዩሽ ጉዳት ነፃ  Tel ፦☎️ 0992484672 ዋጋ ፦3500ብር ብቻ ብዛት ለሚወስዱ ልዩ ቅናሽ እናደርጋለን 🚨በወሲብ ወቅት ብልቶ አልቆም ብሎ ወይም ቶሎ እየረጩ ወይም ቶሎ እየደከሙ ወይም ብልቶ ጥንካሬ በማጣት እየተልፈሰፈሰ ተቸግረዋል? በተጭማሪም ፦ 1) ብልት ውጥር እና ቀጥ ብሎ እንዲቆም 2)የብልትን ጡንቻዎች በማጠንከር የብልት መጠንን መጨመር(4 inch) 3)ቆዳ እንዲለጠጥ በማድረግ በዛው ልክ ውፍረት እንዲጨምር የሚያደርገውን ሁሉንም ግልጋሎት በአንድ ላይ የያዘውን ዘላቂ መፍትሄ   new vimax silver 60 capsul 💯%✓✓ original መሉ በሙኑ ከተፈጥሮ ንጥረነገሮች ብቻ የተሰራ የ ካናዳ ምርት የሆነውን አስመጥተናል ☎️ 0992484672 ላይ ይደውሉ Inbox👉 @bobmarliiii 🚘🚖 ክፉለሀገር ላላችሁ እና ሌሎች ክልል ከተሞች ላላችሁ customers በ ፈጣን ems (posta) እንልካለን 🔴አድራሻ አዲስ አበባ #Free Delivery in AA 📦ለክፍለ ሃገር ደንበኞቻችን በፖስታ እንልካለን 👉ተጨማሪ t.me/Herbal_treatment_end_marketing

ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ቶሎ የመርካት ችግር ወይም ስንፈት ወሲብ እንዴት ሊያጋጥም ይችላል ወይም ቶሎ የመጨረስ ችግ እንዴት ያጋጥማልና እንዴትስ መከላከል እንችላለን 7 ነጥቦችን አንስተን ሰፋ ባለ መልኩ አቅርበናል እና ሴት ልጅ ወሲብ ስትፈልግ የምታሳያቸው ስምንት ምልክቶችንም አንድ ላይ አቅርበናል የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

🚫🚫 attention አሁን ሰሞኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ corona ክትባት ብዙ ሲወራ ሰምቻለሁ like የ lucifer ምልክት ነው የ አውሬው ምናምን አሁን እኛ ከ LuLuciferንብስም እና ነው ዊው ዊው ምትሉት. ይሄም ሆኖ ግን ስለምንከተበው መድሃኒት ማወቅ አለብን አደልም ክትባት ፓራሲታሞልም የ ራሱ side effect አለው ለማንኛውም ስለ ክትባቱ : 📌very common side effects of the vaccine Astrazeneca(ከ አስትራዜኔካ ምንጠብቀው side effect ወይም ጎንዮሽ ጉዳት ) 🔹tenderness, pain, warmth, itching or bruising at the injection site 🔹generally feeling unwell(ጥሩ ስሜት አለመሰማት) 🔹feeling tired (fatigue)(መድከም) 🔹chills or feeling feverish(ብርድ ብርድ ማለት, የ ትኩሳት ስሜት ) 🔹headache(ራስ ምታት ) 🔹nausea( ማቅለሽለሽ) 🔹joint pain or muscle ache(የ መገጣጠምያ ህመም እና የ ጡንቻ ) 📌Common (may affect up to 1 in 10 people)ሚጠበቁ side effect ከ 10 ሰዎች ውስጥ ላይ አንድ ሰው ላይ ሚታይ ምልክት 🔸swelling, redness or a lump at the injection site(የተውጋው ቦታ ላይ እብጠት እና መቅላት 🔸fever(ትኩሳት ) 🔸vomiting or diarrhoea(ማቅለሽለሽ, ተቅማጥ) 🔸flu-like symptoms, such as high temperature, sore throat, runny nose, ( ጉንፋን ሚመስሉ ምልክቶች ጉሮሮ ማሳከክ, ፈሳሻማ ንፍጥ, ትኩሳት ) 🔸cough and chills(ሳል እና ብርድ ብርድ ማለት ) 📌Uncommon (may affect up to 1 in 100 people) ያልተለመዱ ግን ሊታይ ሚችል ምልክቶች 🔻feeling dizzy(መፍዘዝ ) 🔻decreased appetite(የ ምግብ ፍላጎት መቀነስ ) 🔻abdominal pain(የ ሆድ ህመም ) 🔻enlarged lymph nodes(ልምፍ ኖድ እብጠት) 🔻excessive sweating, itchy skin or rash(በጣም ማላብ , ማሳከክ, የቆዳ ሽፈታ ) 📌Not known (cannot be estimated from the available data)(ይሄ ያልታወቀ ምን አልባት ሊያመጣው ይችላል ሚባለው ነው ) ◾️severe allergic reaction (anaphylaxis) (በጣም ከባድ አለርጂክ) በፍጥነት እያደገ ያለዉም የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ። የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን (Vulvovaginal yeast infection) የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምንድን ነው? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ላይ የመቆጣት እና የማሳከክ ስሜት የሚያስከትል ኢንፌክሽን ነው። ይህ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ካንዲዳ(candida) በመባል በሚጠራው የፈንገስ ዝርያ ነው። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶችና የህመም ስሜቶች ምንድን ናቸዉ? ምልክቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ ● የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ማሳከክ ● የሽንት ማቃጠል ● የሴት ብልት እና የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ማቃጠል፣ መቅላት ወይም መቆጣት ● በወሲብ ወቅት ህመም ● የሴት ብልት ፈሳሽ አንዳንድ የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ያላቸው ሴቶች ከሴት ብልት ውስጥ ትንሽ ፈሳሽ ሊኖራቸው ይችላል። ይህ ፈሳሽ በአብዛኛው ነጭና እንደ አይብ የሚበጣጠስ ነው። ነገር ግን ቀጭን እና እንደ ውሃም ሊሆን ይችላል። ምልክቶቼ በፈንገ ኢንፌክሽን ምክንያት መሆኑን እንዴት አውቃለሁ? አብዛኛዎቹ ሴቶች የምልክታቸው መንስኤ የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ይሁን ወይም ሌላ ነገር ይሁን ሊያውቁ አይችሉም ። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶች ከሌሎች የሴት ብልት ኢንፌክሽን ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው ፤ ስለዚህ ምርመራ ሳያደርጉ በዚህ ምክንያት ነው ብሎ ለመናገር በጣም አስቸጋሪ ነው። እርግጠኛ ለመሆን ሃኪም ወይም ነርስጋ ቀርቦ መታየት እና ከማህጸን ፈሳሽ ናሙና ተወስዶ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን እንዴት ነው የሚከሰተው? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚያመጣው ፈንገስ አብዛኛውን ጊዜ በአንጀት ውስጥ እና በሴት ብልት ውስጥ ይኖራል። ይሁንና የፈንገሱ ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የበሽታ ምልክቶች አይኖርም። የተወሰኑ መድሃኒቶች (በተለይም አንቲባዮቲክስ) ፣ ጭንቀትና ሌሎች ምክንያቶች ፈንገሶቹ እንዲባዙ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የማህጸን የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክት መታየት ይጀምራ። ከስር የተዘረዘሩት ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ናቸዉ ●የአንቲባዮቲክስን መጠቀም ●የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠቀም ●የስኳር በሽታ ●እርግዝና ●የተዳከመ የሰውነት የበሽታ መከላከያ ስርዓት (የኬሞቴራፒ ሕክምና፣ኤች አይ ቪ) የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን እንዴት ይታከማል? ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚሆኑ መድኃኒቶች ​​ሊወስዱ ይችላሉ። መድኃኒቶች የሚዋጡ ወይም በሴት ብልት ውስጥ የሚቀመጡ ሊሆኑ ይችላሉ። በሴት ብልት ውስጥ የሚቀመጡት መድሃኒቶች በክኒን ወይም በክሬም መልክ ሊመጡ ይችላሉ። ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚወሰዱ ሁሉም መድሃኒቶች ኢንፌክሽኑን የሚያስከትሉ ፈንገሶችን በመግደል ይሰራሉ። ጥሩ ስሜት የሚሰማኝ መቼ ነው? ሕክምና እንደጀመሩ በጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ ጥሩ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል። ህክምናን ካጠናቀቁ በኋላ ካልተሻለዎት ​​ዶክተርዎን ወይም ነርስዎን እንደገና ማየት አለብዎት ፤ ተጨማሪ መድሃኒት መውሰድ ወይም ሌላ መድሃኒት መውሰድ ይኖርብዎት ይሆናል። ባለቤቴስ ህክምና ማድረግ ይጠበቅበታል? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ አይደለም ። አልፎ አልፎ ከአንዱ ወደ አንዱ የመጋባት ሁኔታ ቢስተዋልም ፤ ባለሙያዎች የወሲብ ጓደኛ ህክምና እንዲያደርግ አይመክሩም። ..................................................... ምንጭ: የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

ለሐኪም ለመንገር የምንቸገራቸው ቀላል ችግሮች ወደ ጤና ባለሙያ ከምንሔድባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ስለ ግል የጤና ችግሮቻችን ለመናገር ነው፡፡ ይሁን እንጅ አንዳንድ የጤና ቸግሮች ከሌሎች የበለጠ ሌሎች ሰዎች ሊያውቋቸው አይገባም የምንላቸው አይነት ናቸው፡፡ ያም ሆኖ የወሲብ ችግር፣ በግልፅ የማይታይ ሽፍታ፣ መጥፎ የአካል ጠረን፣ አሉየም ለከባድ ጠረን የሚያጋልጠን የስሜት ቁስል ቢኖርብንም እንኳን እረዳት ለመፈለግ በሃፍረት መሸማቀቅ የለብንም፡፡ ለምሳሌም፡- የአባላዘር በሽታ ሰዎች የአባላዘር በሽታ እንዳለባቸው ለማወቅ በየጊዜው ወደ ሐኪም ቤት ይሄዳሉ፡፡ የፍቅር ወይም የትዳር ጓደኛችን ለአባላዘር በሽታ መጋለጣችንን ከነገሩንና ምንም አይነት ምልክት ካልታየብን ወደ ሐኪም መሄዱን ትተን ነገሮች ጥሩ ይሆናሉ ብለን እንጠብቃለን፡፡ ዳሩ ግን ለመዳንም ሆነ በሽታውን ወደ ሌሎች ላለማስተላለፍ መመርመሩ ጠቃሚ ነው፡፡ እንደ ጨብጥ ያሉ በሽታዎች በግልፅ የሚታዩ ምልክቶች ሲኖሯቸው ሌሎች መሰል በሽታዎች እንዳለብን እንኳ ለማወቅ እንቸገራለን፡፡ የብልት ሀርፐስ ሲጀመር ቢታወቅም አንዳንድ ጊዜ ምንም አይነት የበሽታው ምልክት ከማይታይበት ሰው ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ከመጠን ያለፈ ላብ በጋለ ፀሐይ ስር ስንቆም ወይም በህዝብ ፊት ንግግር ስናደርግ ሰውነታችን ላብ ማመንጨቱ የተለመደ ነው፡፡ ሊያልበን በማይገባ ጊዜ ካላበን ግን Hyperhidrosis የተሰኘ የጤና ችግር እንዳለብን ሊያመላክት ይችላል፡፡ በላብ ምክንያት ልብሳችንን ቶሎ ቶሎ ከቀየርን፤ በቀን ከአንዴና ሁለቴ በላይ ሻወር ከወሰድን፤ ስንጨነቅ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስንሰራ እጆቻችን ከረጠቡ፤ አሊያም እቃዎችን መያዝ ካቻልን ወደ ጤና ባለሙያ ዘንድ መሄድ ይኖርብናል፡፡ ከመጠን ያለፈ ላብ ለችግሩ ህክምና ስላለው ችግሩን ለጤና ባለሞያ መግለፅ ጠቃሚ ነው፡፡ ችግሩ ያለብን እኛ ብቻ እንዳልሆንን መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ Hyperhidrosis ከሌለብን እንኳ ከመጠን ያለፈ ላብ የሌሎች ጤና ችግሮች የጎንዮሽ ምልክት ሊሆን ስለሚችል መመርመሩ ይመከራል፡፡ ከልብ ድካም በኋላ ወሲብን መፍራት ከልብ ድካም ህመም የሚያገግሙ ሰዎች ብዙ ጊዜ ወሲብ መፈፀም አለመቻላቸው ያሳስባቸዋል፡፡ የልብ ችግር ካብን የጤና ባለሙያው ስለ ወሲብ እስከሚያወራ መጠበቅ የለብንም፡፡ ይልቁንም ስለሚያሳስበን ነገር ራሳችንን መጠየቅ አለብን፡፡ መጠየቅ ካሉብን ጥያቄዎች መካከል ‹‹ቀስ በቀስ ወሲብ መፈፀም የምንችለው እንዴት ነው?››፤ ‹‹ምን አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ እችላለሁ?›› እንዲሁም ‹‹ችግሩን ቀላል ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?›› የሚሉት ይገኙባዋል፡፡ ለምሳሌ የመተንፈስ ችግር ያለበት የልብ ህመምተኛ ወሲብ ቀጥ ብሎ እንደቆመ እንዲፈፅም ሊመከር ይችላል፡፡ አንዳንድ ህሙማን ወሲብ በድጋሚ መፈፀም አልችልም በሚል ይጨነቃሉ፡፡ አብዛኞቹ የልብ ህሙማን ግን ይህ አይነቱ ጭንቀት ሊያሳስባቸው አይገባም፡፡ የብቸኝነት ስሜት በርካታ የስነ ልቡና ባለሞያዎች እንደሚሉት ለአብዛኛዎቹ ታካሚዎቻቸው ስለወሲብ ማውራቱ አያስቸግራቸውም ይልቁንም ይበልጥ የሚያሳስባቸው ከሌሎች ሰዎች ጋር ስሜታዊ ትስስር የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች የማህበረሰቡ አካል እንደሆኑ አይሰማቸውም፡፡ የሆነ አይነት ችግር እንዳለባቸው ያው ቃሉ፡፡ ስለዚህ ህይወታቸው ውስን ነው፡፡ ጥቂት ጓደኛ ቢኖራቸውም እንኳ ጥልቀት ያለው ግንኙነት አይመሰርቱም፡፡ ፍላጎቱ እያላቸውም በብቸኝነት ይጠቃሉ፡፡ ችግራቸውን ለመናገርም ጊዜ ሊወስድባቸው ይችላል፡፡ ቀስ በቀስ ግን ያለባቸውን ችግር ማውጣታቸው አይቀርም፡፡ ለረጅም ጊዜ የብልት መቆም ለረጅም ጊዜ የብልት መቆም (priapism) በህመም ስሜት የታጀበ ከመሆኑም ሌላ በጊዜው ካልታከመ ቀዶ ህክምና ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ስንፈተ ወሲብን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ደግነቱ እንደዚህ አይነት ችግር ሊገጥም የሚችለው በመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ የሚያጋጥመው ለእንቅልፍና እንዲታሹ ጭምር የሚታዘዘው ፀረ- ድብታ ስሜት የሆነው tragadone የተባለውን መድሃኒት ሲጠቀሙ ነው፡፡ ሀኪም መድሃኒት ሲያዝልን ፋርማሲስቱን ስለ አጠቃቀሙ ለመጠየቅ ማፈር የለብንም፡፡ በግልፅ እንዲያብራራልን ካስፈለገ ሰዎች ገለል ሲሉ ጥያቄ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡፡ የብልት ሽፍታ በወንድ ወይም በሴት ብልት እንዲሁም መቀመጫ አካባቢ የሚወጣ ሽፍታ ምቾት የሚነሳ ነው፡፡ ፈንገስ፣ በተባይ መወረር ወይም ሌላ አይነት የቆዳ ችግር በማንኛውም የሰውነታችን ክፍል ላይ ቢታይ በፍጥነት ሀኪም ብናማክር መፍትሄ አግኝተን ችግሩ ሊቆም ይችላል፡፡ የሚያሳፍር ጥርስ በጥርሳቸው የሚያሳፍር የሚመስላቸው ሰዎች ሲስቁ ፈገግታቸውን በእጃቸው መዳፍ የመሸፈን ልማድ አላቸው፡፡ አሊያም ከንፈራቸውን ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ በተፈጥሮም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች የፊት ጥርሳቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ሀፍረታቸውን ገፍፈው ወደ ሀኪም ጎራ ቢሉ መፍትሄ በቀላሉ ያገኛሉ፡፡ መጥፎ የአፍ ጠረን ሁሉም ሰው መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳለውና እንደሌለው ማወቅ ይፈልጋል፡፡ የህክምና ባለሙያው ጭምብል አጥልቆ እንኳ ዘልቆ የሚሰማ የአፍ ጠረን ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ የአንዳንድ ሰዎች የአፍ ጠረን ደግሞ ከሌሎች ይበልጥ አስከፊው ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ባክቴሪ የሚከማችበትን ምላስ በመፋቅ ወይም በመቦረሽ ችግሩን ማስወገድ ይቻላል፡፡ ዶክተር ቤዛ አያሌው ======================= በፍጥነት እያደገ ያለዉም የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ። የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

ጠቃሚ ምክር ሴጋ(Masturbation) እና መዘዙ (ብዙም ስለማናወራው ነገር ግን ስለምናደርገው ጎጂ ልማድ ለምክክር እንዲረዳ በግለጽ ቋንቋ የተጻፈ ነውና ምቾት የሚነሳህ መስሎ ከተሰማህ ያለማንበብ ምርጫው ያንተ ነው) ጀግናው ወንድሜ! ዛሬ ስለ ግለ-ወሲብ ከአሁን በኋላ ሴጋ እያልኩ የምጠራውን ጎጂ ልማድ በአንተ እና በትዳርህም ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ ላወራህ እፈልጋለሁ። ይኽ ጎጂ ልማድ ከሚያመጣው መዘዞች ውስጥ መንፈሳዊ ጉዳቱን ሳይኾን አካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ጠባይዓዊ.. ) ኪሳራውን ላወያይህ ፈልጌያለሁ። ይኼም ጽሑፍ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ጽሑፎቼ ከራሴ ሕይወት የተማርኩትን በንባብም ያዳበርኩትን እውቀት ያማከለ ነው። እነኾ.... ሴጋ (በወንዱም ኾነ በሴቷ) መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ የእድሜ ልክ ክፉና ጎጂ ልማድ ነው። ክፉ አልኩት ይኽ ዐመል አንዴ ከተጠናወተ(ሴቷንም ኾነ ወንዱን) ለመተው እጅግ ከባድ ነውና፤ ጎጂም አልኩት አንተን አለመልቀቁ ሱሰኛም ማድረጉ አንተ ላይ አካላዊ፣ አእምሮኣዊና ስነልቦናዊ ጉዳትን ያመጣልና ነው። ሴጋና ልጆች ሴጋ ከሚያስከትለው ዘለቄታዊ አንዳንዴም(በወቅቱ ካልቆመ) የእድሜ ልክ ችግር ከመኾኑ አንጻር ልጆች ወደ ጉርምስና እድሜያቸው እየተቃረቡ ሲሄዱ ስለወሲብ ጸጋነትና አግባባዊ አጠቃቀሙ መማር አለባቸው። በተለይም አኹን ባለንበት ነባራዊ ዘመን የወንዶች ወንዳወንድነት ባሽቆለቆለበትና አባቶችም ወንዳወንድ ጠባይ በማያሳዩበት በዚህ ወቅት ልጆች በተለይም ሴቶች ልጆች ቶሎ ለመጎርመስና ለተሳሳተ የወሲብ ግንዛቤና ድርጊት ይጋለጣሉ። ከዚህ በተጨማሪም ዘመን በወለዳቸው የቴክኖሎጂ ውጤት በኾኑ መሣሪያዎች የምናገኛቸው የወሲብ ትዕይንቶች(Pornography) ችግሩ ላይ ቤንዚን ያርከፈክፋሉ። ምንም እንኳ ሴጋ በአብዛኛው የወንዶች ክፉ ልማድ ቢኾንም ከወሲባዊው አብዮት ወዲህ ግን የሚለማመዱት ሴቶቹም ቁጥር ጨምሯል። አንተ ታዲያ ሚስትህንና ልጆችህን(ወንዱንም ኾነ ሴቷን) ስለወሲብና ትክክለኛ(አግባባዊ) አፈጻጸሙ፣ ስለሴጋም ጎጂነት ታስተምር ዘንድ አንተ መጀመሪያ አውቀኸው(ጉዳቱንም ጭምር) ራስህንም ጠብቀህ ልትገኝ ይገባል። በዚህም መሠረት ሚስትህም ኾነች ልጆችህ በዚህ ልማድ እንዳይገኙ ሥርዓትን ልትሠራላቸው፣ ልትመክራቸው ፈጽመውት ቢገኙ ደግሞ ልትቀጣቸው ይገባሃል። የሴጋ ጎጂ ልማድነት(ከወንዶቹ አንጻር) ጉዳት ፩ አካላዊ ጉዳት ውዱ ወንድሜ! ሴጋ በቋሚነት የምትመታ ከኾነ የሰውነትህን ፈሳሽ፣ ወዝህን፣ ጉልበትህን አሟጦ ይጨርሰዋል። ይኽም ማለት ከሴጋህ በኋላ ሰውነትህ ይልፈሰፈሳል፣ አይንህ ይፈዛል(ስብር ይላል)። "እንዴዬ ወሲብስ ከሚስቴ ጋር ስፈጽም ይደክመኝ የለ?" ብትለኝ አዎን ወሲብም ከሚስትህ ጋር ብትፈጽም ይደክምሃል። ነገር ግን ከእርሷ ጋር የምትፈጽመው ሰውነትህን የማይመጥ ጉልበትህንም የማይጨርስ ይልቁንስ መታደስ ያለበት ነው። ይኽ የሚኾነው ግን ከእርሷ ጋር የምትፈጽመው ወሲብ ሴጋህን የሚያስረሳ እርካታውም የጋራ መኾን ያለበት እንጂ ዝምብለህ እንደነገሩ ተንደፋድፈህ መነሳት ከኾነ ውጤቱ ከሴጋው ብዙም አይለይም። ጉዳት ፪ አእምሮአዊ ጉዳት በተለይም በዚህ ዘመን ለሴጋ ወሲባዊ ትዕይንቶች(Pornography) ከፍተኛ መንሴዔዎች ናቸው። በስሜት ሕዋሶቻችን የተቀበልናቸውን መልእክቶች ተንተርሶ አስፈላጊው አጸፋዊ ምላሽ በሚመለከተው የሰውነት ክፍል እንዲሰጥ የሚያዘው አእምሮ ነው። በወሲባዊ ትዕይንቶች የተነካው(መልእክት የተቀበለው) የአእመሮአችን ክፍል የልብ ምታችን እንዲጨምር፣ ደምም በፍጥነት እንዲዘዋወር (በተለይም ወደ ብልታችን) ከዚህም የተነሳ እንዲነቃቃ ያደርጋል። ይኽን ልማድ ያደረገው አእምሮህ ታዲያ ሚስትህን ስታይ፣ ጠረኗ ሲሸትህ፣ ሰውነቷን ስትዳብስ(ስትዳብስህ)፣ ለወሲብም ወደምንጣፍህ ስትወጣ አእምሮህ ሰውነትህን ለማዘዝ ይዘገያል(አያዘውም)። ምክንያቱ ደግሞ እርሱ የሚያውቀውና የለመደው ስሜት መቀስቀሻ ሌሎች ወሲብ ሲፈጽሙ ማየት ነውና። ጉዳት ፫ ስነልቦናዊ ጉዳት ሴጋ ስትመታ "ወሲቡ"(ከተባለ) አንተ በራስህ ለራስህ ብቻ የምትፈጽመው የምትወዳትን ሚስትህን ያላሳተፈ ነውና በራስወዳድነት ማዕበል እየተንገላታህ ለሚስትህ ያለህ ናፍቆትና ስስትም እየቀነሰ ይሄዳል። አለባበሷን ማድነቅ፣ የናፍቆትና የፍቅር ቃላትን መናገር፣ ፈቃዷን መፈጸምና ፍላጎቷንም በአግባቡ ማርካት ይሳንሃል። ምክንያቱ ደግሞ የእነዚህ ምንጭ የኾነውን ወሲባዊ ስሜት (መነቃቃት) በሴጋ አድርቀኸዋልና ነው። ጉዳት ፬ ከሴት ያርቅሃል ሴጋን በቋሚነት ለሚመታ ወንድ ሴቶችን መቅረብ(መጥበስ)፣ ማናገር(መጀንጀን) ይሳነዋል። የመጠየቅ፣ የመነጋገርና የመግባባት ብሎም የመፋቀርን ሽልማትና እርካታ በዋዛ በሴጋ ያገኘዋልና(ምንም እንኳ ሴጋ ለወሲብ ምትክ ባይኾንም)። ጉዳት፭ ወኔህን ይሰልበዋል ፈርጀብዙ የኾነ አባወራዊ ሚናህን የምትወጣበትን ወኔ ይገድለዋል። እያደርም ለቤትህ፣ ለሚስትህ፣ ለልጆችህ ግድ የሌለህ በራስወዳድነት ባሕር ሰምጠህ እንድትቀርም ያደርግሃል። ጉዳት ፮ ለስንፈተ ወሲብ ይዳርግሃል ውድ ወንድሜ! እኔ ይኼን ስጽፍልህ ትማርበት ዘንድ በእርሱም ፈጣሪ የሰጠህን ጸጋ በአግባቡ ተጠቅመህ በትዳርህ አንድነትህን ታጠነክርበት ዘንድ ነው። እርግጠኛ ኾኜ የምነግርህ ሴጋ ለስንፈተ ወሲብ እንደሚዳርግህ ነው። እንዴት? .... ይቆየን። የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል እኔን ለማማከር የምትፈልጉ በቴሌግራም ሊንኩን በመንካት ታጉኙኛላቹ https://t.me/DrSofonias

በጊዜ ሂደት የሚመመጡ የወንድ ብልት መጠን መቀነስ ምክንያቶች 👉 ሲጋራ ማጨስ 👉የእድሜ መግፋት 👉የክብደት መጨመር 👉የፕሮስቴት ዖፕራሲዮን 👉ፔይሮኒስ በሽታ 👉መድሃኒቶች ለምሳሌ አንዳንድ ለድ
በጊዜ ሂደት የሚመመጡ የወንድ ብልት መጠን መቀነስ ምክንያቶች 👉 ሲጋራ ማጨስ 👉የእድሜ መግፋት 👉የክብደት መጨመር 👉የፕሮስቴት ዖፕራሲዮን 👉ፔይሮኒስ በሽታ 👉መድሃኒቶች ለምሳሌ አንዳንድ ለድብርት የሚሰጡ መድሃኒቶች 👉መፍትሄዎችን ለምትፈልጉ የቴሌግራም ቻናላችን ተቀላቀሉ የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

በእርግዝና ወቅት የሚመከሩ የወሲባዊ ግንኙነት አቅጣጫዎች **************************************** እንደምን አመሻቹ ዛሬ ልናስገነዝባችሁ የወደድነው ጥንዶች በዕርግዝና ወቅት ሊ
በእርግዝና ወቅት የሚመከሩ የወሲባዊ ግንኙነት አቅጣጫዎች **************************************** እንደምን አመሻቹ ዛሬ ልናስገነዝባችሁ የወደድነው ጥንዶች በዕርግዝና ወቅት ሊጠቀሙት ስለሚገባ የወሲባዊ ግንኙነት አቅጣጫዎች ነው፡፡ ምንም እንኳን በእርግዝና የመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ወሲባዊ ግንኙነት አደገኛ እንደሆነ ቢታወቅም ነገር ግን እነዛ ወራቶች ካለፉ በኋላ ከታች በስእል መልክ በገለጽናቸው መሰረት ተግብራዊ ቢደረጉ ጉዳት እንደሌላቸው ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት በሴቷ ላይ ከፍተኛ የሆነ የሆርሞን ለውጦች ስለሚኖሩ እነዛን ጫንዎች ለመቀነስ እንዲሁም ሰውነቷ ዘና እንዲል ጥንቃቄ የተሞላበት ወሲባዊ ግንኙነት ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረክታል፡፡ ********************** የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

የጀርባ ህመም መነሻ 10 ምክንያቶች 10 Back Pain causes ((((ዶክተር ሶፊ))) መነሻው ምን እንደሆነ በዉል ሳያዉቁት በጀርባ ህመም ተሰቃይተዋል? የጀርባ ህመም በአደጋ ብቻ ላይከሰት ይችላል የአቀማመጥ ሁኔታ፣ የሚጠቀሙት ጫማ፣ ከመጠን ያለፈ ዉፍርትና ከባድ ነገሮችን ማንሳት የላይኛዉና ታችኛው ጀርባ ህመም ያስከትላል። በሴቶችና ወንዶች ላይ የጀርባ ህመም የሚያስከትሉ መነሻ ምክንያቶችን በዝርዝር እንመልከታቸው፦ 1. የቢሮ ወንበር የቢሮ ወንበርዎ ለጀርባ ህመም ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋሉ ሲቀመጡ ጎበጥ የሚሉ ከሆነ ጀርባዎ ላይ ጫና ያደርጉበታል አከርካሪ ሊጋመንታችን ከአቅም በላይ ይለጠጥና ዲስካችን የጀርባ አጥንታችን እንዲወጠር ያደርጋል ከጊዜ ብዛት የጀርባ አጥንታችንን በመጉዳት ለጀርባ ህመም ይዳርገናል። 2. የሚያደርጉት ጫማ ጫማ ለጀርባዎ ጤንነት ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል የማይገባ / ትክክል ያልሆነ ጫማ አቋምዎን በማዛባት ማዕከላዊ የግራቪቲ ቦታን ያዛባል ይህም በታችኛው የጀርባ ክፍልዎ ላይ ህመም ይፈጥራል። 3. የሚተኙበት ፍራሽ የሳሳ ፍራሽ መጠቀም የታችኛዉን የጀርባ ክፍል እንዲሰምጥ ያደርጋል በተጨማሪም የአከርካሪ አጥንቶችን እንዲዛቡ በማድረግ በጡንቻዎች እና የአከርካሪ መገጣጠሚያዎች ላይ ዉጥረት ይፈጥራል። 4. የጀርባ ቦርሳ የሚይዙት የጀርባ ቦርሳ ትልቅ ከሆነ ብዙ እቃዎችን የመያዝ እድል ይኖርዎታል ተጨማሪ ሸክም በጀርባዎ ላይ መጫን ትልቁ የጀርና ህመም ምክንያት ነው። በአንድ በኩል ያለዉ የሰዉነት ክፍልዎ ላይ ሸክም መጨመር የአከርካሪ አጥንቶች እንዲጎብጡ በማድረግ የጀርና ህመም እንዲከሰት ያደርጋል። 5. በሆድ በኩል መተኛት በሆድ በኩል ተደፍተዉ ሲተኙ በጀርባዎና በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ይጨምራል በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ጨመሩ ማለት ደግሞ የሙሉ ሰዉነትዎን ቅርጽ ያዛባዋል ጭንቅላትዎን ወደ ጎን ሲያዞሩት ደግሞ ጭንቅላትዎንና አከርካሪዎት ከመደበኛ አቅጣጫዎ ውጪ አደረጉት ማለት ነው። 6. ትከሻ ወይም አንገት ለረጂም ሰዓት አንገትን አዘንብሎ ( ደፍቶ) መቆየት ወይም መጓዝ በትከሻዎቻችን መሀል ያሉትን ጡንቻዎች እንዲዝሉ በማድረግ የላይኛው ጀርባ ክፍል እና የአንገት ህመም ያስከትላል። 7. ላኘቶኘና ስማርት ስልኮች በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎቻቸው ፍቅር ስለወደቁ በነዚህ ሰዎች ላይ የጀርባ ህመም የተለመደ ነው። በስራ በተጠመድበት ወቅት ስልክዎትን በትከሻዎና በጆሮዎ መሀል በመያዝ ለረጂም ጊዜ ማውራት የአንገት ህመም ያስከትላል። 8. ከመጠን ያለፈ ውፍረት ከሌሎች በሽታዎች በተጨማሪ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለጀርባ፣ መገጣጠሚያ እና ጡንቻዎች ህመም ያጋልጠናል። አብዛኛዎቹ በሚኖራቸው ውፍረት በዳሌና በታችኛው የጀርባ ክፍል ህመም ያጋጥማቸዋል። 9. እግርን አጣምሮ መቀመጥ እግርዎን አጣምረው በሚቀመጡበት ጊዜ የአከርካሪ አጥንትዎ ቀጥ ማለት ይሳነዋል ይህም በዳሌ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ከመጠን በላይ እንዲለጠጡ ያደርጋቸዋል። በተጨማሪም የደም ዝውውር በመስተጓጐሉ ምክንያት ቫሪኮስ ቬይን( Varicose vein ) ለተባለ በሽታ ያጋልጣል። 10 . ሲጋራ ማጨስ በሲጋራ ውስጥ ያለው ኒኮቲን ወደ ዲስክ (Disc) የሚሄደውን የደም ዝውውር በመቀነስ የአከርካሪና ጐን አጥንት ችግር ያስከትላል። በተጨማሪም ካልሲየም በአግባቡ ከሰውነታችን ጋር እንዳይዋሀድ በማድረግ የአጥንት እድገትን ይገታል በመሆኑም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች በአንድ እጥፍ የጀርባ ህመም ችግር ያጋጥማቸዋል። ዶክተር ሶፊ ======================= በፍጥነት እያደገ ያለዉም የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @DrSofonias