ar
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

الذهاب إلى القناة على Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

تُعد قناة ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 19 795 مشتركاً، محتلاً المرتبة 1 170 في فئة الطب والمرتبة 1 705 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 19 795 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 12 يوليو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -406، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -4، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 17.59‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 6.21‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 484 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 230 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 6.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 13 يوليو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الطب.

19 795
المشتركون
-424 ساعات
-617 أيام
-40630 أيام
أرشيف المشاركات
#የጥርስ_መቦርቦር ========== #ምንነት፡- የጥርስ መቦርቦር ማለት ጥርስ በተለያዩ ባክቴሪያዎች አማካኝነት በቀላሉ ሲሰበር ወይንም ሲሸራረፍና የተፈጥሮ ቀለሙንና ቅርፁን ሲቀይር ማለት ነው፡፡ ምግብ ከበላን በኋላ ካላፀዳነው በጥርሳችን የሚቀር ቅሪት (debris) ለተለያዩ ባክቴሪያዎች መራባት ምክንያት ይሆናል፡፡ እንደ አለም ጤና ድርጅት ጥናት ከሆነ በአለም ላይ ወደ ሁለት ነጥብ ቢሊዮን ህዝብ (የአለም 36 በመቶ) በጥርስ መቦርቦር የተጠቃ ነው፡፡ #መንስኤዎች፡- አጋላጭ ነገሮች፣ጣፋጭነት ያላቸው ምግቦችን መመገብ ፣የአፍ (የጥርስና የድድ) ንጽህናን አለመጠበቅ፣ጫት መቃም፣ሲጋራ ማጨስ፣የአፍ መድረቅ ወይም ምራቅ በበቂ አለመመረት (dry mouth)፣በሽታ የመከላከል አቅም መቀነስ፣ስኳር በሽታ መኖር #ምልክቶች፡- ጥርስ ነጭ ወይም ቢጫ በመሰለ ልጥፍ ነገር መሸፈን፣ነጭ የነበረው የጥርስ አካል ወደ ቡናማ ቀለም መቀየር፣መጥፎ የአፍ ሽታ መኖር፣ሞቃት፣ቀዝቃዛና ጣፋጭ ምግቦችን ወይም መጠጦችን ስንበላና ስንጠጣ የህመም ስሜት መኖር፣ምግብ በምንበላ ጊዜ የጥርስ መሰንጠቅ ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ጤና ተቋም ሄደን ብንታይ

5ቱን የጉበት ገዳይ በሽታዎች እናስተዋውቃችሁ ሂፐታይተስ የጉበት ብግነት ነው፡፡ የብግነቱ ሁኔታ በጉበት ላይ ጠባሳ ሊፈጥር ወይም ጉበትን ሊያኮማትር ወይም ደግሞ ካንሰር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ለሂፐታይተስ መፈጠር ሂፐታይተስ ቫይረስ ዋነኛ ምክንያት ሲሆን ሌሎች ኢንፌክሽኖች እና መርዛማ ነገሮች ማለትም አልኮልና የተወሰኑ መድኃኒቶች እንዲሁም የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከያ አቅም አዳካሚ በሽታዎች ለሂፐታየተስ መፈጠር ተጠቃሽ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት አምስት ዓይነት የሂፐታየተስ ቫይረሶች እያንዳንዳቸው አምስት የሂፐታየተስ በሽታዎችን ያስከትላሉ፡፡ ሂፐታየተስ ኤ፣ቢ፣ሲ፣ዲ እና ኢ በሽታዎች በመላው ዓለም ለብዙዎች ሕመምና የሞት ምክንያት ናቸው፡፡በተለይ ሂፐታየተስ ቢ እና ሲ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች በጉበት መኮማተርና ካንሰር ተጠቅተው ወደ ሞት የሚወስዱ አደገኛ በሽታዎች ናቸው፡፡ ሂፐታይተስ ኤ ቫይረስ ( ኤች ኤ ቪ) 1. ሂፐታይተስ ኤ ቫይረስ የሚገኘው በተበከለ ሰው አይነምድር ውስጥ ሲሆን ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በአይነምድር የተበከለ ምግብ ወይም ውሀ በምንወስድበት ጊዜ ነው፡፡ 2. የተወሰነ የግብረስጋ ግንኙነት ይህን ቫይረስ ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ 3. የንፅህና ጉድለት ባለባቸው የዓለም ክፍሎች በስፋት ይህ ቫይረስ የሰዎችን ሕይወት እየነጠቀ ይገኛል፡፡ 4. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት በየአገሩ ይሰጣል፡፡ ሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ (ኤች ቢ ቪ) 1. ቫይረሱ የሚተላለፈው በደም፣በስፐርም እና በሌሎች ፈሳሽ ነገሮች ነው፡፡ 2. ሌላው የቫይረሱ መተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተጠቃች እናት በምትወልድበት ጊዜ ወይም ህፃናት በልጅነት ጊዜያቸው በቫይረሱ ከተጠቃ የቤተሰብ አባል ሊሆን ይችላል፡፡ 3. በቫይረሱ የተበከለ ደምና የደም ተዋሀፆ በመስጠት ወይም በማስተላለፍ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 4. በሕክምና ወቅት በቫይረሱ የተበከ መርፌ በመጠቅም አንዱ መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡ 5. በመርፌ በሚወሰዱ አድገኛ መድኃኒቶችና እፆች አጠቃቀም ወቅት ሌላው መተላለፊያ መንገድ ሲሆን በተለይ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጥንቃቄ ንቅሳት (ታቱ) የሚሰሩ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡ 6. የጤና ባለሙያዎች በሕክምና ወቅት መርፌ ሊሰበርባቸውና ራሳቸውን ሊወጉ ይችላሉ በዚህም ለብክለት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ 7. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት በየአገሩ ይሰጣል፡፡ ሂፐታይተስ ሲ ቫይረስ (ኤች ሲ ቪ) 1. አብዛኛው ጊዜ የሚተላለፈው በተበከለ ደም አማካኝነት ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በቫይረሱ የተበከለ ደምና የደም ተዋሀፆ በመስጠት ወይም በማስተላለፍ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 2. በሕክምና ወቅት በቫይረሱ የተበከ መርፌ በመጠቅም አንዱ መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡ 3. በመርፌ በሚወሰዱ አድገኛ መድኃኒቶችና እፆች አጠቃቀም ወቅት ሌላው መተላለፊያ መንገድ ሲሆን በተለይ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጥንቃቄ ንቅሳት (ታቱ) የሚሰሩ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡ 4. በግብረስጋ ግንኙነት ሊተላለፍ ይችላል ነገር ግን ዝቅተኛ ነው፡፡ 5. ይህን ቫይረስ ለመከላከል ምንም አይነት ክትባት የለም፡፡ ሂፐታይተስ ዲ ቫይረስ (ኤች ዲ ቪ) 1. በዚህ ቫይረስ የሚጠቁት በሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ ብቻ የተጠቁ ሰዎች ናቸው፡፡ 2. በሁለቱ ቫይረሶች የሚጠቁ ሰዎች ለአደገኛ በሽታ የሚጋለጡ ሲሆን ውጤቱም እጅግ መጥፎ ሊባል የሚችል ይሆናል፡፡ 3. የሂፐታይተስ ቢ ክትባት በዚህ ቫይረስ ለሚጠቁ ሰዎች መከላከያ በመሆን ያገለግላል፡፡ ሂፐታይተስ ኢ ቫይረስ (ኤች ኢ ቪ) 1. ብዙን ጊዜ የሚተላለፈው የተበከለ ምግብ ወይም ውሃ በምንጠቀምበት ጊዜ ነው፡፡ 2. በተዳጊ አገሮች በስፋት ለሚታየው የሂፐታይተስ ስርጭት ይህ ቫይረስ ግንባር ቀደም ነው፡፡ 3. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት ቢኖርም በስፋት ማግኘት ያዳግታል፡፡

💔በየትኛው የእድሜ ክልል ውስጥ ወሲብ መጀመር ጥሩ? ✅በጥናት የተረጋገጠ ማብራሪያ 👌እንግሊዝ ውስጥ ስለ ግብረ ሥጋ ግንኙነት የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ በለጋ ዕድሜያቸው ድንግልናቸውን ያጡ ወጣቶች የኋላ ኋላ ይቆጫሉ። 🧩በጥናቱ ከተሳተፉት በአፍላ ዕድሜ የሚገኙ አንድ ሦስተኛ ሴቶችና አንድ አራተኛ ወንዶች፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ የፈጸሙት በትክክለኛው ዕድሜ እንዳልነበር ይናገራሉ። በእንግሊዝ ሕግ መሠረት በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረት ወሲብ መፈጸም የሚቻለው ጥንዶቹ 16 እና ከዚያ በላይ ሲሆኑ ብቻ ነው። በየአሥር ዓመቱ የሚከናወን ጥናት ግን በዚህም ዕድሜ ለወሲብ ዝግጁ መሆን አይቻልም ይላል። ውጤቱ በቅርቡ ይፋ ለተደረገው ጥናት መረጃ የተሰበሰበው ከ3000 ወጣቶች ሲሆን፤ እ.አ.አ ከ2010 እስከ 2012 ባለው ጊዜ ለንደን ባሉ ሳይንቲስቶች የተሰራ ነው። የጥናቱ ውጤቱ ከጥናቱ ተሳታፊዎች 40% የሚሆኑት ሴቶችና 26% የሚሆኑት ወንዶች ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ሲፈፅሙ በተገቢው ዕድሜ ላይ እንዳልነበር ተናግረዋል። ተሳታፊዎቹ ትንሽ ዘግይተው ቢሆን ኖሮ ደስ ይላቸው እንደነበረም ገልፀዋል። አብዛኛዎቹ ወሲብ ማድረግ የጀመሩት 18 ዓመት ሳይሞላቸው ሲሆን፤ ቢያንስ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ደግሞ 16 ዓመት ሳይሞላቸው የግብረ ሥጋ ግንኙነት አድርገዋል። ፈቃደኝነት ጥናቱ ግብረ ሥጋ ግንኙነት የማድረግ አቅምና ዝግጁነትንም ጭምር ተመለከተ ነው። ማለትም አንድ ሰው አመዛዝኖ፣ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ማድረግ ይችላል ወይ? የሚለው ከግምት ገብቷል። የማመዛዘን ብቃት ሲለካ፤ ከአሥር ሴቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑትና ከወንዶቹ ደግሞ አራቱ ሳይልፉ ቀርተዋል። ከአምስት ሴቶች አንዷና ከአስር ወንደች አንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያደረጉት ብዙም ፈቃደኛ ሳይሆኑና በፍቅረኛቸው ተገፋፍተው እንደነበረ ይናገራሉ። የ'ናትሳል' ጥናት መሥራች የሆኑት ፕሮፌሰር ካዬ ዌሊንግስ እንደሚሉት፤ ለግብረ ሥጋ ግንኙነት ሕጋዊ ተብሎ የተቀመጠው ዕድሜ አንድ ሰው ለግብረ ሥጋ ግንኙነት ዝግጁ ወይም ብቁ ነው ማለት አይደለም ይላሉ። "ሁሉም ወጣት የተለያ ነው። አንዳንድ የ15 ዓመት ወጣቶች ዝግጁ ቢሆኑም አንዳንዶች ደግሞ በ18 ዓመታቸው ብቻ ዝግጁ እንደሆኑ ሊሰማቸው ይችለላል" ሌላዋ አጥኚ ዶ/ር ሜሊሳ ፓልመር፤ "ግኝታችን እንደሚያሳየው አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች ከወንዶች በበለጠ በፍቅረኛቸው ግፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረጋቸውን ነው" ይላሉ። በጥናቱ መሰረት፤ ከአሥር ወጣቶች ዘጠኙ መከላከያ ቢጠቀሙም፤ "ለወደፊትም ወጣቶች ከበሽታ እንዲጠበቁ ለጤናቸው ትኩረት መሰጠት አለበት" ብለዋል። በተጨማሪም የወጣቶች የመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ጤናማ እንዲሆን ትምህርት ቤቶች ተገቢውን የጤና ጥበቃ አገልግሎት እንዲሁም ትምህርት መስጠት አለባቸው ብለዋል። የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ያለብን መቼ ነው? የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሊያደርጉ ከሆነ ለራስ ✅እነዚህን ጥያቄዎች መሰንዘር ያሻል፡ ✅የሚሰማኝ ትክክለኛ ስሜት ነው? ✅አብሬው ከምተኛው ሰው ፍቅር ይዞኛል? ✅ያፈቅረኛል/ታፈቅረኛለች? ✅ከኤችአይቪና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎች ራሳችንን ለመከላከል ኮንዶም ስለመጠቀም ተነጋግረናል? ✅ካልተፈለገ እርግዝና ለመጠበቅ የወሊድ መከላከያ አዘጋጅተናል?።። ✅ሃሳቤን መቀየር ብፈልግ በማንኛውም ሰዓት እምቢ የማለት አቅም አለኝ? ፍቅረኛዬስ ይህን ውሳኔ ያከብራል? ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሹ አዎ ከሆነ ወሲብ ለመፈጸም ትክክለኛው ጊዜ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ከዚህ በታች ላሉት ጥያቄዎች መልሱ አዎ ከሆነ ትክክለኛው ጊዜ ላይሆን ይችላል፡ ❌ከጓደኞቼ ወይም ከፍቅረኛዬ ግፊት እየተሰማኝ ነው? ❌በኃላ ሊቆጨኝ ይችላል? ❌አሁን ወሲብ ማድረግ የፈለኩት ከጓደኞቼ እኩል ለመሆን ወይም እነሱን ለማስደሰት ነው? ❌ግንኙነት ለማድረግ ፈቃደኛ የሆንኩት ከፍቅረኛ ጋር ላለመለያየት ብዬ ነው? ኢዛቤል ኢንማን ስለ ወሲብ ትምህርት በሚሰጥ መጽሐፍ ይህን ብለዋል፡ "ወሲብ ለመፈጸም ተገቢ ስለሆነው ዕድሜና ጊዜ ለወጣቶች ትምህርት መሰጠት አለበት። ሲያድጉ የሚበጃቸው ውሳኔ ላይ ለመድረስ አይቸገሩም። ትምህርቱ በትምህርት ቤቶች መሰጠት ቢጀመርም ጠቃሚ ነው። የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

ክፍል 2 የእንስላል ቅጠል ወይም ፍሬን አፍልቶ መጠጣት የኩላሊት ጠጠርን በሽንት መልክ እንደሚያሶግድ ያውቃሉ?? ቶሎ ቶሎስ ሽንት ለመሽናት እንደሚጠቅምስ?? እንስላል (Pimpinella anisum) ለባህል መድኃኒትነት ከሚውሉ የአረም ዓይነቶች አንዱ ነው፡፡ መድኃኒትነቱ በሀገራችን ቢታወቅም ብዙ ሰው አይጠቀምበትም፣ በጓሮው አያበቅለውም፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ይቆጫል፡፡ እንስላል በሌላው ዓለም ለምግብነትም ሆነ ለመድኃኒትነት በደንብ ጥቅም ላይ የዋለ የተክል ዓይነት ነው፡፡ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ ዲፓርትመንት አንድ ተማሪ የማስተርስ ዲግሪው ማሟያ ይሆን ዘንድ በእንስላል ላይ ጥናት ሰርቶ ነበር፡፡ ከተማሪው “ቴሲስ” ያነበብሁትን ላካፍላችሁ፡፡ የሜዲትራሊያን አካባቢ ምግብ ሥርዓት በዓለም ካሉ ምርጥ የምግብ ሥርዓቶች(አንደኛ ሳይሆን አይቀርም) አንዱ፡፡ በሚዲትራሊያን የምግብ ሥርዓት ውስጥ አንስላልን መጠቀም የተለመደ ነው፤ የምግባቸው ዋና አካል ነው፡፡ በኢጣሊያ ቀንበጡን በማኜክ የአፍ ቁስለትን ለማዳን ይጠቀሙበታል፡፡ በማዕከላዊ ሰርቪያ ፍሬው፣ ዘሩ ለአፍ መጉመጥመጫነት ይወላል፡፡ በብራዚል እንደ ሻይ በማፍላት የእንቅልፍ እጦትን ይከላከሉበታል፡፡ በህንድና በካሽሚር ዘሩን እንደ ሻይ በማፍላት ከስኳር ጋር በመጨመር ለሆድ ድርቀት መከላከያነት ይጠቀሙበታል፡፡ በኢኳዶር አበባውንና ቅጠሉን በመጭመቅ ለካንሰርና ለዓይን ህመም መድኃኒትነት ይጠቀሙበታል፡፡ በሚያሚና ፍሎሪዳ በተባለው የአሜሪካ ግዛት ስሩንና ፍሬውን በመጭመቅ ብዙ ሽንት ለማሸናት ይጠቀሙበታል (ብዙ የሚያሸኑ እጾች እንደ መድኃኒት(diuretics) ይወሰዳሉ፡፡ ሳማ እና ጌሾ በዚህ ጥቅማቸው ይታወቃሉ) ፡፡ በኢጣሊያ፣ በቱርክና በዮርዳኖስ እያንዳንዱን ክፍል በመጭመቅና እንደ አጥሚት በመጠቀም የሆድ ቁርጠትን ለመከላከል ይጠቀሙበታል፡፡ ሮም ውስጥም ለጉንፋን፣ ነቃ ለማለት፤ ለተነፋ ሆድ፣ ለቁርጥማትና ለሌሎችም ፈውስ የተክሉን የተለያዩ ክፈሎች በፈላ ውሃ በመጭመቅ ይጠቀሙበታል፡፡ በደቡብ አፍሪካ የቅጠሉ ጭማቂ ለቁርጥማት ማስታገሻነት ይውላል፡፡ በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎችና በሶማሌ ስሩን በመጭመቅ ለወባ በሽታ ይጠቀሙበታል፡፡ በፍሬው ጭማቂ በተደረገ ጥናት ፀረ ባክቴሪያነቱን በተለይም “ስትሬፕቶ ኮከስ ሙታንስ” የተባለውን የጥርስ መበስበስ የሚያስከትል ባክቴሪያ የማጥፋት ሀይል እንዳለው ተረጋግጧል፡፡ለዚህ ይሆን ብዙ ሰዎች ጥርሳቸውን በእንስላል ሲፍቁ የሚታዩት፡፡ በሀገራችን አንስላልን ለመድኃኒትነት እንጂ ለምግብነት የሚፈልገው የለም፡፡ እረ ምን ይሻለናል? ቦታ ያለችሁ ሰዎች ትከሉት፣ ተጠቀሙበት፡፡ እንስላል እንዴት ደስ ይላል፡፡

መጥፎ የአፍ ጠረንን ወይም ሃሊቶስስን የሚያመጣዉ ምንድነዉ? መጥፎ የአፍ ጠረን(ሃሊቶስስ) የአፍን ንፅህና በደንብ ካለመጠበቅ የሚከሰት ችግር ቢሆንም ሌሎች የአፍና የጥርስ ንፅህና ቢጠበቅም ለህክምና አስቸጋሪ የሆኑ መንስኤዎችም አሉት፡፡ ይህ ሁኔታ ሲከሰት ከማስጨነቁም በላይ የታማሚዉን ሁለንተናዊ ግንኙነት (በትዳርም ይሁን በሌሎች ግንኙነቶች፤በስራ ቦታ) ሊጎዳ ይችላል፡፡ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጡ ከሚችሉ መንስኤዎች ዉስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ፡፡ • የአፍ ንፅህናን ያለመጠበቅ • የድድ ህመም መኖር • ሽታ ሊያመጡ የሚችሉ ባክቴሪያዎች በአፍና የአንጀት ክፍሎች ዉስጥ መራባት • እንደ ካንዲዲያስስ ያሉ የፈንገስ ህመሞች መከሰት • የሳይነስ እንፎክሽን • መድኃኒቶች(በተለይ አፍን የሚያደርቁ መድሃኒቶች) • ሲጋራ ማጨስ • የተወሱ የምግብ አይነቶች(ነጭ ሽንኩርት፤ሽንኩርት፤ሰርዲን፤ከፍተኛ የገንቢ ምግብ(ፕሮትን) ያላቸዉ ምግቦች) • የምግብ ያለመፈጨት ችግርና የጉበት ችግር • የሆድ ድርቀት መጥፎ የአፍ ጠረን መኖሩን እንዴት ሊያዉቁ ይችላሉ? • መጥፎ ወይም የሚመር የአፍ ጣዕም ሲሰማዎት • በጣም የሚመከረዉ ዘዴ ግን የሚያምኑት ሰዉ መጥፎ የአፍ ጠረን እንደአለዎትና እንደሌለዎት እዉነቱን እንዲነግሮት መጠየቅ ናቸዉ፡፡ መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል የሚመከሩ ነገሮች/ምክሮች • ምግብ ከተመገቡ በኃላ ጥርስዎትን መታጠብ(መቦረሽ) • ቢያንስ በቀን አንዴ በጥርስ መካከል ያሉትን የምግብ ተርፍራፊ በጥርስ መጎርጎርያ ወይም ፍሎስ ማዉጣት • ምላስዎትን መቦረሽ • አርትፊሽል ጥርስ ወይም ድድ ካለዎት ማፅዳት • የአፍ ድርቀትን መከላከል፡ ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቆም፤ዉሃ በብዛት መጠጣት(ቡና፣ለስላሳ መጠጦችና አልኮል የአፍን መድረቅ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ስለዚህ አያዘወትሩ)፤ማስቲካ ማኘክ ወይም ከረሜላ መምጠጥ የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን በቴሌግራም ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

የጌሾ ተክል ለህፃናት ቶንሲል ህመም መፍትሔ እንደሆነ ያውቃሉ? ውድ የኛ ቤተሰቦች ልጆችወን በተደጋጋሚ ቶንሲል እያጠቃብወ ከተቸገሩ በቤትዎ የሚያዘጋጁት ፈዋሽ መድሀኒት ይዘን ቀርበናል። የጌሾ ቅጠል
የጌሾ ተክል ለህፃናት ቶንሲል ህመም መፍትሔ እንደሆነ ያውቃሉ? ውድ የኛ ቤተሰቦች ልጆችወን በተደጋጋሚ ቶንሲል እያጠቃብወ ከተቸገሩ በቤትዎ የሚያዘጋጁት ፈዋሽ መድሀኒት ይዘን ቀርበናል። የጌሾ ቅጠል ጫፍጫፍ ላይ የሚወጡትን ቀንበጦች 7 ቦታላይ በመቁረጥ ትንሽ ውሀ ጠብ እያደረጉ በእጅ በማሸት 1 የሻይ ማንኪያ የጌሾ ጭማቂ በማዘጋጀት ለታመሙት ልጆች ማጠጣት ፍቱን እና የማያዳግም መፍትሔ ነው። ሁሌም ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ ጠቃሚ መረጃችንን ከማካፈል ወድኋላ አንልም አሁንም በድጋሚ ጤናችሁ ይብዛ ለመላው ለአዳም ልጆች የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

ለማመን በሚከብድ አጭር ጊዜ ውስጥ፣ 10ሳሜ በወገብ ዙሪያ የተከማቸ ቦርጭ የሚያጠፋ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ውህድ ጀባ እንበልዎ። Excellent Drink That Melt 10 cm Stomach Fat Waist As If By Magic! **************************************** ይህ አስደናቂ ውህድ ለማዘጋጀት ቀላል ሲሆን፣ 10ሳሜ የሚሆን ቦርጭ ለማጥፋት የሚወስደው ጊዜ አራት ቀን ብቻ ነው። There is a wonderful drink made of just simple ingredients and cleans up 10 cm of waist fat just in four days. ውህዱን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ፣ Ingredients needed for this drink are: -ዝንጅብል /ginger/ -አረንጓዴ ሚንት ቅጠል በተለምዶ ናና የሚባለው ቅጠል /fresh mint leaves/ -ኩኩምበር ወይም ክያር በመባል ይታወቃል /cucumber/ -ሎሚ /lemon/ -8 ብርጭቆ ውሃ /8 glasses of water/ የውህዱ አዘገጃጀት How to prepare the drink በመጀመሪያ ሎሚውን በደንብ ማጠብ እና ለሁለት ቦታ መቁረጥ። ከዛ በጎድጓዳ ሰሃን ውሃ ጨምሮ የተቆረጠውን ሎሚ ውሃው ውስጥ መጨመር ። ኩኩምበሩን መላጥ እና ከታትፎ ውሃው ውስጥ መጨመር ፣ ከዛ ከ 8 እስከ 12 የሚሆኑ አረንጓዴ የሚንት ቅጠል እና ተልጦ በትንንሹ የተከተፈ ዝንጅብል መጨመር ። ሁሉንም ከደባለቅን በኋላ ፍሪጅ ውስጥ ማሳደር፣ (በረዶ ቤት አይደለም ።) በአንዴ መጨረስ ስለሚከብድ ቀስ እያሉ፣ ቁርስ ምሳ መክሰስ ወይም በየተወሰነ ሰዓት ልዩነት ውህዱን መጨረስ ያስፈልጋል። ማሳሰቢያ፣ ውጤቱን በደንብ ለማየት ቢያንስ ለ 4 ቀን መጠጣት ያስፈልጋል። እንዲሁም አመጋገብ ማስተካከል እና የአካል እንቅስቃሴ ብንጨምርበት ደግሞ ገራሚ ለውጥ እናገኛለን። ሰላም ለእናተ ይሁን Wash and do not peel off the lemon, cut into 2 pieces and put them in water in bowl. Peel and chop the cucumber, put in bowl and put washed 8 -12 fresh mint leaves, add them and peeled ginger chopped into slices. Leave it over night in refrigerator. For visible results make this drink at least 4 days. የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

ጥብቅ ማሳሰቢያ 1.አንብበው ላይጨርሱ አይጀምሩት 2.አንብበው ሲጨርሱ ለወገኖ ሼር ያድርጉ ጤና ይስጥልኝ ውድ የዶክተር ቤዛ ተከታታዮች እዴት ዋላችሁ በተደጋጋሚ ግዜ የብዙሃናችሁ ጥያቄ የሆነውን በውስጥ መስመር በተጨማሪ በቴሌግራም ቻላናችን የተጠየቀ ጥያቄ ነው በደንብ ግልፅ እዲሆንላችሁ ስል ፁሁፉ እረጅም አድርጌዋለሁ ሳትሰላችሁ በጥሞና በትግስት ያንብቡት በዚህ ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ በደንብ እደማብራራላች ቃል እገባለሁ ። በወንዶች ሽንት መሽኛ አካባቢ አልፎ አልፎ እየጠፋ የሚመጣ የእብጠት ምልክት ምንድን ነው? የፕሮስቴት እጢ በወንዶች ብቻ የሚገኝ የሰውነት አካል ሲሆን ከወንዶች የስነ ተዋልዶ አካላት ውስጥ አንዱ በመሆን ይጠቀሳል፡፡ ይህ እጢ የሚገኘው ከሽንት ፊኛ በታች ሲሆን የሽንት ትቦ የመሀከለኛውን ክፍል ዙሪያ ከቦ ይገኛል፡፡ ይህ የኦቾሎኒ ያክል መጠን ያለው የፕሮስቴት እጢ ከዕድሜ ጋር መጠኑ እየጨመረ የሚሄድ ሲሆን በተግባሩም ለስፐርም የሚሆነውን ፈሳሽ ከሚያመነጩ የሰውነት አካል ውስጥ አንዱ ሆኖ ይገኛል፡፡ ለዛሬ የምንመለከተው ዋናው ርዕስ የፕሮስቴት እጢ በሚያድግበት ወቅት የሚከተለውን ሁለት አይነት ችግሮች ናቸው ፤ 1. የካንሰር ምልክት/ጠባይ የሌለው የፕሮስቴት እጢ ማበጥ/ማደግ (Benign prostatic Hypertrophy) እና 2. የፕሮስቴት ካንሰር የካንሰር ምልክት/ጠባይ የሌለው የፕሮቴስት እጢ ማበጥ/ማደግ Benign prostatic Hypertrophy ይህ ካንሰር የማያስከትል የፕሮስቴት እጢ ማበጥ ሲሆን መሰረታዊ ምክንያት በውል ባይታወቅም በዕድሜ ለውጥ የሚከተሉ የሆርሞኖችን መለዋወጥ ተከትሎ ሊመጣ እንደሚችል ይገመታል፤ በዚህም ሳቢያ በአብዛኛው የዚህ ችግር ተጠቂዎች የሆኑት ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች ናቸው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው የፕሮስቴት እጢ በሽንት ትቦ ዙሪያ የሚገኝ እንደመሆኑ መጠን መጠኑ በጨመረ ቁጥር ቀስ በቀስ የሽንት ትቦን የመጫንና በዚህም ሳቢያ የማጥበብ ብሎም ጨርሶ የመዝጋት ሁኔታን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በዚህም ሳቢያ የሽንት ፊኛ በዚህ ጠባብ ትቦ ሽንትን ለማስወጣት በሚደረገው ጥረት የሽንት ፊኛ ጡንቻ ማደግና መጠንከር ይከተላል፡፡ ይህም የሽንት ፊኛ ውስጥ ያለው የሽንት መጠን ተሟጦ የመውጣት ስሜት ከማስከተሉም በላይ ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንና ለሽንት ቧንቧ ጠጠር መፈጠር ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ሁኔታዎች እየተባባሱ በመጡ ቁጥርና ጊዜው በረዘመ ቁጥር የኩላሊት መጎዳትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሊከተሉ የሚችሉ ምልክቶች/የህመም ስሜቶች የፕሮስቴት እጢ የማደግ ስሜትን ማስከተል የሚጀምረው የሽንት ትቦ ላይ ጫና በማስከተል ሽንት እንዳይወጣ መከልከል ሲጀምር ነው፡፡ – በመጀመሪያ ደረጃ ሽንት የመሽናት ስሜት ከመጣ በኋላ መሽናት ለመጀመር ጊዜ መፍጀት፣ – ሽንት ጨርሶ ያልወጣ ያልወጣ መስሎ መሰማት፣ – ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣትና ማጣደፍ፤ – በሌሊት ከወትሮው በበለጠ ሁኔታ ከእንቅልፍ ለሽንት መነሳት፤ – ሽንት በሚሸኑበት ወቅት መጠኑ መቀነስና መቆራረጥ እንዲሁም ለመሽናት መታገል፤ – ሽንት ሸንተው ከጨረሱ በኋላ የመንጠባጠብ ሁኔታ፤ – በአንድ አንድ ሁኔታ ሽንት ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ መፍሰስ፤ – በሽንት ትቦና ፊኛ አካባቢ ያሉት ትናንሽ የደም ስሮች ሽንት ለማስወጣት በሚደረገው ግፊት መበጣጠስና በሽንት ውስጥ ደም የመከሰት ሁኔታ፤ – የሽንት ትቦ ከነአካቴው የተዘጋ እንደሆነ ደግሞ ፊኛ ከመጠን በላይ መወጠርና በታችኛው የሆድ ክፍል ከፍተኛ የህመም ስሜት መሰማት፤ – የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የተከሰተም እንደሆነ በመሽናት ወቅት የማቃጠል ስሜት በብልት ላይ መሰማትና እንዲሁም የሰውነት ትኩሳት መከተል ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ግዴታ በአንድ ላይ ይከሰታሉ ማለት ባይሆንም በእነዚህ ጥቂት ስሜቶች ብቻ ቢኖሩም የዚህ ችግር ምልክት ለመሆን ይበቃሉ፡፡ እነዚህ ስሜቶች በሚኖሩን ጊዜ በምን ማወቅና ማረጋገጥ ይቻላል የሚለውን ከታች የምንመለከተው ይሆናል፡፡ ፕሮስቴት ካንሰር የፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ በብዛት የሚታይ ሁኔታ ቢሆንም እንደ አብዛኛው የካንሰር አይነቶች መንስኤው በውል አይታወቅም፡፡ በፕሮስቴት እብጠት ሳቢያ በቀዶ ጥገና ከሚወገዱ የፕሮስቴት እጢዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆነው ዕድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ የሚገኘው የፕሮስቴት እብጠት ካንሰር መሆኑን ያመለክታል፡፡ በአብዛኛው ጊዜ የፕሮስቴት ካንሰር ቀስ በቀስ የሚያድግና የሚሰራጭ እንደመሆኑ መጠን አስከፊ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ምንም አይነት ስሜት ላያስከትል ይችላል፡፡ ሊከተሉ የሚችሉ ምልክቶች/የህመም ስሜቶች ከላይ እንደተጠቀሰው የፕሮስቴት ካንሰር አደገኛ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ በአብዛኛው ጊዜ ምንም አይነት ምልክት ባያስከትልም በፕሮስቴት እብጥት ሳቢያ ሊከተሉ የሚችሉ ምልክቶችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ነገር ግን የፕሮስቴት ካንሰር መሰራጨት ከጀመረ በኋላ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እንደ አጥንት፣ ኩላሊት ብሎም ወደ አንጎል በመሰራጨት የተለያየ አይነት የህመም ስሜቶችና ሁኔታዎችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህንን ችግር በምን ማረጋገጥ ይቻላል? አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች በሚሰሙበት ወቅት ወይም የጤና ባለሙያ ይህንን ሁኔታ በሚጠራጠርበት ወቅት ሊደረጉ ከሚገባቸው ምርመራዎች ውስጥ፤ – በፊንጢጣ በኩል ጣትን በማስገባት የፕሮስቴት እጢው ማበጥ አለማበጡንና፣ ከዚያም በተጨማሪ አስፈላጊ የሆኑ የመለያ ነጥቦችን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ – ከዚህም በተጨማሪ አልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ ችግሩ መኖሩንና ከሆነም ደግሞ ካንሰር የመሆንና ያመሆኑን ሁኔታ በተሻለ ሁኔታ መገመት ይቻላል፡፡ – የፕሮስቴት ዕጢ ማደጉንና እንዲሁም ካንሰር የመሆን ዕድሉን ሊነግረን የሚችልም የደም ምርመራ እንደመኖሩ ይህንን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ እንዲያውም ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች ላይ ይህንን የደም ምርመራ በየዓመቱ ማድረግና አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡ – ከፕሮስቴት ዕጢ ናሙና በመውሰድ የእጢውን ሁኔታ ማረጋገጥም ተመራጭ የሆነውና እርግጠና ሁኔታውን ሊነግረን የሚችል የምርመራ አይነት ነው፡፡ – የፕሮስቴት ካንሰር የተሰራጩ እንደሆነም እንደ የአስፈላጊነቱ የተጠቃውን የሰውነት አካል የተለያዩ ምርመራዎች ማድረግ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ይረዳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ስሜቶች የሌላ ህመም መገለጫ ሊሆኑ እንደመቻላቸው አስፈላጊውን ምርመራ እንደ የአስፈላጊነቱና በደረጃ ማድረግ መሰረታዊ ነው፡፡ ስለዚህም ትንሽ ነው ብለን ጊዜ የሰጠነው የፕሮስቴት ዕጢ ችግር ለባሰ ሁኔታ ሳያጋልጠን በጊዜ ህክምና ብንወስድበት ስለ ህመሙም አውቀን የቅድመ ጥንቃቄ ወይም የመከላከል እርምጃ ብንወስድ መልካም ነው፡፡ መልካም ጤንነት እሁድ ተመኘውሎ በዚች የሒሳብ ጥያቄ ዘና እያላችሁ እሁድን ከኛጋር

#መደንዘዝ .........! 💊ለዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው ጠቃሚ የጤና መረጃችን ከጭን እስከ እግር ጣት ጫፍ ድረስ ስለሚፈጠር #የመደዘዝ፡ #የመጠዝጠዝ፡ #የማቃጠልና #የስሜት መጥፋትን አስመልክቶ ነው። • ይህ ችግር በዋናነት ሁለት ምክናየቶች አሉት። 1. ወደ እግር የሚሰራጨው የደም መጠን መቀነስና 2. እግርን የሚቆጣጠረውና ወደ እግር የተዘረጋው የነርቭ ክፍል ጉዳት ሲደርስበት ነው። #ከነዚህ ዋና ዋና ምክናየቶች በተጨማሪ የሚከተሉት ተጨማሪ ምክናየቶችም አሉ። • የደም መርጋት • ቅዝቃዜ • የአጥንት መሳሳት • የድስክ መሸራተት • ብዙ አልኮል መጠጣት • የቫይታሚን ቢ 12 ማነስ • ኢንፌክሽን • የተለያየ አካላዊ ጉዳት በእግርና ጀርባ ላይ ሲደርስ • የሚሰራጭ የካንሰር አይነት • የተለያዩ በሽታዎች እንደ ደምግፊት፡ ስኳር፡ ሪህ፡ የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን፡ የኩላሊት ችግር፡ የጉበት ችግር፡ ስትሮክ፡ ሌሎችም • ለብዙ ሰአት መቀመጥና እግርን አነባብሮ መቀመጥ #ውድ የኛ ቤተሰቦች የመደዘዝና የመጠዝጠዝ ስሜቱ ጊዜአዊ ከሆነ በቀላሉ የሚለቅና የሚስተካከል ችግር ሲሆን ለረጅም ጊዜ የቆየና እየባሰ የሚሄድ የመደዘዝና የመጠዝጠዝ ስሜት ካለና እየቆየም ሰገራንና ሽንትን መቆጣጠር መቸገር፡ እግርን መቆጣጠርና ማንቀሳቀስ አለመቻል፡ የንግግር መቆራረጥና ግራ መጋባት ጋር ከሆነ ግን አስቸኳይ የጤና ባለሙያ እርዳታ ያስፈልጋል። #የእግር መደንዘዝ ከጀርባ ችግር በተለይ ከታችኛው የወገብ ክፍል ጋር ሊያያዝ ይችላል። • ስለዚህ መደንዘዝ፡ መጨነቅ፡ የማቃጠል ስሜት፡ ቶሎ ቶሎ መሽናት፡ ማሳከክ፡ መጠዝጠዝ፡ የጡንቻ መሸማቀቅና ሽፍታ የእግር የመደንዘዝ ስሜት ጋር የሚያያዝ ነው። በቅንት ሼር

ይህን ያውቃሉ በግንኙነት ወቅት የሚያጋጥሙ ድክመቶች መቅረፍ እንደሚቻል በግብር ስጋ ጊዜ የሚያጋጥሙ ሁሉንም ድክመቶችን መቀርፍ ወዲያዉ መጨረስን የሚያዘገይ የእቃን መጠንና እርዝመትና ውጥረት የሚያስተ
ይህን ያውቃሉ በግንኙነት ወቅት የሚያጋጥሙ ድክመቶች መቅረፍ እንደሚቻል በግብር ስጋ ጊዜ የሚያጋጥሙ ሁሉንም ድክመቶችን መቀርፍ ወዲያዉ መጨረስን የሚያዘገይ የእቃን መጠንና እርዝመትና ውጥረት የሚያስተካክል ያሉበት ቦታ ድረስ ለተጨማሪ መረጃ (0992484672) በአዲስ አመራረት original vimax silver 60 capsual 🤗made in canada ✓ የብልትን መጠን ለመጨመር እንዲጨምር ✓ቶሎ የመጨረስ ችግር ✓ ለወሲብ ፍላጎት ማጣት በዘላቂነት ለመቅረፍ ፈለክ ስመጥር የሆነው new vimax silver 60 capsul እኛ ጋር ይገኛል። መፍትሄው አለ ከጎንዩሽ ጉዳት ነፃ  Tel ፦☎️ 0992484672 ዋጋ ፦3500ብር ብቻ ብዛት ለሚወስዱ ልዩ ቅናሽ እናደርጋለን 🚨በወሲብ ወቅት ብልቶ አልቆም ብሎ ወይም ቶሎ እየረጩ ወይም ቶሎ እየደከሙ ወይም ብልቶ ጥንካሬ በማጣት እየተልፈሰፈሰ ተቸግረዋል? በተጭማሪም ፦ 1) ብልት ውጥር እና ቀጥ ብሎ እንዲቆም 2)የብልትን ጡንቻዎች በማጠንከር የብልት መጠንን መጨመር(4 inch) 3)ቆዳ እንዲለጠጥ በማድረግ በዛው ልክ ውፍረት እንዲጨምር የሚያደርገውን ሁሉንም ግልጋሎት በአንድ ላይ የያዘውን ዘላቂ መፍትሄ   new vimax silver 60 capsul 💯%✓✓ original መሉ በሙኑ ከተፈጥሮ ንጥረነገሮች ብቻ የተሰራ የ ካናዳ ምርት የሆነውን አስመጥተናል ☎️ 0992484672 ላይ ይደውሉ Inbox👉 @bobmarliiii 🚘🚖 ክፉለሀገር ላላችሁ እና ሌሎች ክልል ከተሞች ላላችሁ customers በ ፈጣን ems (posta) እንልካለን 🔴አድራሻ አዲስ አበባ #Free Delivery in AA 📦ለክፍለ ሃገር ደንበኞቻችን በፖስታ እንልካለን 👉ተጨማሪ t.me/Herbal_treatment_end_marketing

ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ቶሎ የመርካት ችግር ወይም ስንፈት ወሲብ እንዴት ሊያጋጥም ይችላል ወይም ቶሎ የመጨረስ ችግ እንዴት ያጋጥማልና እንዴትስ መከላከል እንችላለን 7 ነጥቦችን አንስተን ሰፋ ባለ መልኩ አቅርበናል እና ሴት ልጅ ወሲብ ስትፈልግ የምታሳያቸው ስምንት ምልክቶችንም አንድ ላይ አቅርበናል የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

🚫🚫 attention አሁን ሰሞኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ corona ክትባት ብዙ ሲወራ ሰምቻለሁ like የ lucifer ምልክት ነው የ አውሬው ምናምን አሁን እኛ ከ LuLuciferንብስም እና ነው ዊው ዊው ምትሉት. ይሄም ሆኖ ግን ስለምንከተበው መድሃኒት ማወቅ አለብን አደልም ክትባት ፓራሲታሞልም የ ራሱ side effect አለው ለማንኛውም ስለ ክትባቱ : 📌very common side effects of the vaccine Astrazeneca(ከ አስትራዜኔካ ምንጠብቀው side effect ወይም ጎንዮሽ ጉዳት ) 🔹tenderness, pain, warmth, itching or bruising at the injection site 🔹generally feeling unwell(ጥሩ ስሜት አለመሰማት) 🔹feeling tired (fatigue)(መድከም) 🔹chills or feeling feverish(ብርድ ብርድ ማለት, የ ትኩሳት ስሜት ) 🔹headache(ራስ ምታት ) 🔹nausea( ማቅለሽለሽ) 🔹joint pain or muscle ache(የ መገጣጠምያ ህመም እና የ ጡንቻ ) 📌Common (may affect up to 1 in 10 people)ሚጠበቁ side effect ከ 10 ሰዎች ውስጥ ላይ አንድ ሰው ላይ ሚታይ ምልክት 🔸swelling, redness or a lump at the injection site(የተውጋው ቦታ ላይ እብጠት እና መቅላት 🔸fever(ትኩሳት ) 🔸vomiting or diarrhoea(ማቅለሽለሽ, ተቅማጥ) 🔸flu-like symptoms, such as high temperature, sore throat, runny nose, ( ጉንፋን ሚመስሉ ምልክቶች ጉሮሮ ማሳከክ, ፈሳሻማ ንፍጥ, ትኩሳት ) 🔸cough and chills(ሳል እና ብርድ ብርድ ማለት ) 📌Uncommon (may affect up to 1 in 100 people) ያልተለመዱ ግን ሊታይ ሚችል ምልክቶች 🔻feeling dizzy(መፍዘዝ ) 🔻decreased appetite(የ ምግብ ፍላጎት መቀነስ ) 🔻abdominal pain(የ ሆድ ህመም ) 🔻enlarged lymph nodes(ልምፍ ኖድ እብጠት) 🔻excessive sweating, itchy skin or rash(በጣም ማላብ , ማሳከክ, የቆዳ ሽፈታ ) 📌Not known (cannot be estimated from the available data)(ይሄ ያልታወቀ ምን አልባት ሊያመጣው ይችላል ሚባለው ነው ) ◾️severe allergic reaction (anaphylaxis) (በጣም ከባድ አለርጂክ) በፍጥነት እያደገ ያለዉም የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ። የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን (Vulvovaginal yeast infection) የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምንድን ነው? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ላይ የመቆጣት እና የማሳከክ ስሜት የሚያስከትል ኢንፌክሽን ነው። ይህ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ካንዲዳ(candida) በመባል በሚጠራው የፈንገስ ዝርያ ነው። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶችና የህመም ስሜቶች ምንድን ናቸዉ? ምልክቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ ● የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ማሳከክ ● የሽንት ማቃጠል ● የሴት ብልት እና የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ማቃጠል፣ መቅላት ወይም መቆጣት ● በወሲብ ወቅት ህመም ● የሴት ብልት ፈሳሽ አንዳንድ የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ያላቸው ሴቶች ከሴት ብልት ውስጥ ትንሽ ፈሳሽ ሊኖራቸው ይችላል። ይህ ፈሳሽ በአብዛኛው ነጭና እንደ አይብ የሚበጣጠስ ነው። ነገር ግን ቀጭን እና እንደ ውሃም ሊሆን ይችላል። ምልክቶቼ በፈንገ ኢንፌክሽን ምክንያት መሆኑን እንዴት አውቃለሁ? አብዛኛዎቹ ሴቶች የምልክታቸው መንስኤ የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ይሁን ወይም ሌላ ነገር ይሁን ሊያውቁ አይችሉም ። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶች ከሌሎች የሴት ብልት ኢንፌክሽን ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው ፤ ስለዚህ ምርመራ ሳያደርጉ በዚህ ምክንያት ነው ብሎ ለመናገር በጣም አስቸጋሪ ነው። እርግጠኛ ለመሆን ሃኪም ወይም ነርስጋ ቀርቦ መታየት እና ከማህጸን ፈሳሽ ናሙና ተወስዶ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን እንዴት ነው የሚከሰተው? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚያመጣው ፈንገስ አብዛኛውን ጊዜ በአንጀት ውስጥ እና በሴት ብልት ውስጥ ይኖራል። ይሁንና የፈንገሱ ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የበሽታ ምልክቶች አይኖርም። የተወሰኑ መድሃኒቶች (በተለይም አንቲባዮቲክስ) ፣ ጭንቀትና ሌሎች ምክንያቶች ፈንገሶቹ እንዲባዙ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የማህጸን የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክት መታየት ይጀምራ። ከስር የተዘረዘሩት ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ናቸዉ ●የአንቲባዮቲክስን መጠቀም ●የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠቀም ●የስኳር በሽታ ●እርግዝና ●የተዳከመ የሰውነት የበሽታ መከላከያ ስርዓት (የኬሞቴራፒ ሕክምና፣ኤች አይ ቪ) የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን እንዴት ይታከማል? ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚሆኑ መድኃኒቶች ​​ሊወስዱ ይችላሉ። መድኃኒቶች የሚዋጡ ወይም በሴት ብልት ውስጥ የሚቀመጡ ሊሆኑ ይችላሉ። በሴት ብልት ውስጥ የሚቀመጡት መድሃኒቶች በክኒን ወይም በክሬም መልክ ሊመጡ ይችላሉ። ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚወሰዱ ሁሉም መድሃኒቶች ኢንፌክሽኑን የሚያስከትሉ ፈንገሶችን በመግደል ይሰራሉ። ጥሩ ስሜት የሚሰማኝ መቼ ነው? ሕክምና እንደጀመሩ በጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ ጥሩ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል። ህክምናን ካጠናቀቁ በኋላ ካልተሻለዎት ​​ዶክተርዎን ወይም ነርስዎን እንደገና ማየት አለብዎት ፤ ተጨማሪ መድሃኒት መውሰድ ወይም ሌላ መድሃኒት መውሰድ ይኖርብዎት ይሆናል። ባለቤቴስ ህክምና ማድረግ ይጠበቅበታል? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ አይደለም ። አልፎ አልፎ ከአንዱ ወደ አንዱ የመጋባት ሁኔታ ቢስተዋልም ፤ ባለሙያዎች የወሲብ ጓደኛ ህክምና እንዲያደርግ አይመክሩም። ..................................................... ምንጭ: የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias