fa
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

رفتن به کانال در Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

کانال ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 19 977 مشترک است و جایگاه 1 154 را در دسته پزشکی و رتبه 1 680 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 19 977 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 25 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -558 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -23 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 22.78% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 5.94% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 556 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 188 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 11 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 26 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته پزشکی تبدیل کرده‌اند.

19 977
مشترکین
-2324 ساعت
-1207 روز
-55830 روز
آرشیو پست ها
የአልኮልና አደንዛዥ እፅ ተፅዕኖ በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ላይ ሁሉም ሰው ከልክ ያለፈ መጠጥና አደንዛዥ እፅ ወሲባዊ ህይወትንና አጠቀላይ ደህንነትን እንደሚጎዳ ያውቃል። እንደ አለመታደል ሆኖ ግን አብዛኛው ሰው የሚያውቀው በአልኮልና በአደንዛዥ እፅ የተነሳ ሊያጋጥመው የሚችለውን የእርካታ ጣርያ ላይ አለመድረስ ብቻ ይመስለናል። ☑️ ይህን ጉዳይ የዘርፉ ባለሙያዎች እንዲህ ይተነትኑታል:- 🦋 ደህንነቱ ያልተጠበቀ ወሲብ አልኮልና አደንዛዥ እፅን በምንጠቀምበት ጊዜ ወሲብ መፈፀም እንደሌለብን በምናምንበት ሁኔታ እንኳን ውስጥ ብንሆን ራሳችንን ለአደጋ አጋልጠን ወሲብ ልንፈፅም እንችላለን። ታዲያ እዚህ ላይ ከቁጥጥር ውጭ ሆነናል ማለት ምናልባትም ኮንዶም መጠቀምን ልንረሳ እንችላለን ማለት ነው፡፡ እንደው እንደምንም ራሳችንን ተቆጣጥረን ኮንዶም ለመጠቀም ብንሞክር እንኳን ወይ ልንቀደው አልያም ከአጠቃቀም መመሪያው በተቃራኒው ልንጠቀመው የምንችልበት እድል ሰፊ ነው። በጥፍራችን ልንቀደው፣ በትክክል በብልታችን ላናጠልቀው አልያም ጫፍ ላይ ምትገኘዋን የኮንዶሙን ክፍል አየር እንዳታስገባ ላንይዛት በኋላም በግንኙነት ጊዜ ልትቀደድ ትችላለች፡፡ ምክንያቱም ሰክረናልና፡፡ ይህ ደግሞ ለአባላዘር በሽታና ላልተፈለገ እርግዝናም ሊያጋልጠን ይችላል። ይህን ሁሉ አልፈን ኮንዶሙን በአግባቡና በመመሪያው መሰረት ብናጠልቀው እንኳን የጠጣነወ አልኮል ከመደበኛው ጊዜ በላይ ወሲብ እያደረግን እንድንቆይ ሊያደርገን ይችላል። ይህ ደግሞ የብልት ማለስለሻ ቅባቶች ድርቀትና ፍትጊያን ያመጣል። በመጨረሻም ኮንዶሙ ሊቀደድ ይችላል። 🦋 ያልተፈለገ ወሲብና ፀፀት የአልኮልና የአደንዛዥ እፅ አንዱና ዋነኛው ችግር አእምሯችንን ማገናዘብ ወደማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በመክተት በሚቀጥለው ቀን የምንፀፀትበትን ጉዳይ ዛሬ እንድንፈፅም ሊያደርጉን ይችላሉ። በአልኮልና በአደንዛዥ እፅ ምክንያት የጓደኝነት ህይወትዎን አያበላሹ አልያም በሚቀጥለው ቀን ከማያውቁት እንግዳ ሰው ጎን ራስዎን ምንእንደተፈጠረ እንኳን ማስታወስ በማይችሉበት ሁኔታ ተኝተው እንዲያገኙት አይፍቀዱ፡፡ 🦋 መደፈር የወሲባዊ ብዝበዛና መደፈር መቼም ቢሆን የሰለባው ጥፋት ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን አልኮልና አደንዛዥ እፅ መጠቀም ወሲባዊ ብዝበዛ እንዲፈፀምብዎ፣ እንዲደፈሩ ተጋላጭ ሊያደርግዎት አልያም የከፋ አደጋ እንዲደርስብዎ የሚያደርግ ሁኔታ ውስጥ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ 🦋 ደካማ ወሲባዊ ብቃት አልኮልና በተለይ እንደ ኮኬይን፣ ሄሮይን እና ስዳቲቭስ ያሉ አደንዛዥ እፆች በወሲባዊ አካላቶቻችን ላይ የሚገኙ የነርቭ ሴሎችን ሊያደነስሷቸውና ከጥቅም ውጭ ሊያደርጓቸው ይችላሉ፡፡ ይሄ ደግሞ እርካታን ለማግኘት እጅግ አዳጋች ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ እንዲሁም ለወሲባዊ ግንኙነት ሳቢ ሆነን እንድንታይ ላያደርጉን ስለሚችሉ ደስ የማይል ወሲብ ልንፈፅም እንችላለን፡፡ በተጨማሪም ወንዶችን ብልታቸው እንዳይቆም ሴቶችን ደግሞ በቂ የብልት ማለስለሸ ቅባት እንዳያዘጋጁ ሊያደርጓውም ይችላሉ። በነገራችን ላይ ከመጠን ያለፈ መጠጥ መጠጣት ከድብርት ጋር ስለሚያያዝ የወሲብ ፍላጎትዎን ጭራሹንም ሊገድለው ይችላል። @DrSofonias

የልጆች አዕምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው የሚያደርጉ 7 ምግቦች 1️⃣ እርጎ አእምሮ ላይ መልዕክት በተገቢው እንዲላክ እና እንዲቀበል ይረዳል፣ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ ይይዛል፤ ይህ ደግሞ የአእምሮ ህብረ ህዋሶች እና መልእክት አስተላላፌዎች በተገቢው እንዲያድጉ ይጠቅማል። 2️⃣ አትክልቶች አትክልቶች አንቲ ኦክሲደንትነት አላቸው ይህ ደግሞ የአዕምሮ ህዋሶች ጤናማ እንዲሆኑ ይረዳል። ለምሳሌ እንደ ስኳር ድንች፣ ዱባ፣ ካሮት ያሉትን መስጠት፣ እንደባሮ ሽንኩርት፣ እስፒናች፣ ቆስጣ ያሉት ደግሞ በፎሌት የበለፀጉ ስለሆኑ ልጆችን ከመርሳት በሽታ ይከላከላሉ። 3️⃣ ብሮኮሊን ካንሰር ተከላካይነት ባህሪ አለው በተጨማሪም የነርቭ ስርዐት በተገቢው የተያያዘ እንዲሆን ያግዛል። 4️⃣ አቮካዶ አስፈላጊ ቅባት ይይዛል ይህም በቂ ደም ወደ ጭንቅላት እንዲዘዋወር ይረዳል። ኦሊክ አሲድ በመያዙ ምክንያት ማይሊን የተባለውን የአዕምሮ ክፍል ከመጥፎ ነገር ይከላከለዋል (ማይሊን በሰዐት በ200 ማይል ፍጥነት መልዕክት እንዲተላለፍ ያደርጋል)። በቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ መሆኑ ልጆች በግፌት የመያዝ እድላቸውን ይቀንሳል። 5️⃣ አሳ አሳዎች ኦሜጋ 3 የበለፀጉ በመሆናቸው የልጆች አእምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው ይረዳሉ። 6️⃣ እንቁላል የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል ለምሳሌ ኦሜጋ 3፣ ዚንክ፣ ኮሊን (አሴታይል ኮሊን) እንዲመረት የሚረዳ ሲሆን የማስታወስ ችሎታን ለማዳበር ያግዛል። 7️⃣ የተፈጨ አጃ በተለይ ለቁርስ ብንመግባቸው ጥሩ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖራቸው ይረዳል፤ በተጨማሪም በቫይታሚን ኢ፣ ዚንክ፣ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ ነው። ከፍተኛ ፉይበርነት ስላለው ሀይልን እንዲያገኙም ያደርጋል። @DrSofonias

🎯ኩላሊት የሚጎዱ ልማዶች አሳሳቢ የሆነው የኩላሊት ህመም ቀድሞ መከላከያ መንገዶችን ያውቃሉ ? ብዙ ልማዶች ለኩላሊት ህመም ምክንያት ናቸው እነዚህም 🔹ሽንትን መቋጠር ሽንት በፊኛ ውስጥ ረጅም ሰአት ሲቆይ በውስጡ የሚያድጉት ባክቴሪያዎች ይበራከታሉ። እንዚህ ባክቴሪያዎች የሽንት ቧንቧ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊያመጡ ይችላሉ። ሽንትን መያዝ ኩላሊት ላይ በሚያደርሰው ጫናም ኩላሊት ተጎድቶ ሽንትን የመቆጣጠር ችሎታችንን ሊያጠፋ ይችላል። 🔹በቂ ውሃ አለመጠጣት አንድ ሰው በቀን ቢያንስ ከ10 እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት አለበት። 🔹ጨው ማብዛት ብዙ ጨው መመገብ ኩላሊታችን ላይ ከፍተኛ ጉ በምንመገበው ጨው የሚገኘውን ሶዲየም 95% ያህሉ በኩላሊታችን ነው የሚቀየረው። ጨው ስናበዛ ኩላሊታችን ጨውን ለማጣራት ይበልጥ መስራት ይኖርበታል። 🔹የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ማዘውተር የኩላሊት ህመም ካለብዎ ዶክተርዎን ሳያማክሩ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን አይጠቀሙ። 🔹ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች ማብዛት 🔹መጠጥ ማብዛት መጠጥ ሲበዛ ኩላሊታችን አደጋ ላይ ይወድቃል ። መጠጥ ኩላሊታችን እና ጉበታችን ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። 🔹ሲጋራ ማጨስ 🔹ቀላል ኢንፌክሽኖችን በግዜው አለመታከም። @DrSofonias

ሙዝ ለጤና የሚኖረው 15 ጠቀሜታዎች 1. ጥርስን ያነጣል!! ጥርስዎን ሁልጊዜ ሲቦርሹ ለሁለት ደቂቃ ያህል በሙዝ ልጣጭ/ልጫ ጥርስዎን ይሹት ከዚያም አስደናቂ ለውጥ ያገኙበታል። 2. በተለያዩ ነፍሳቶች ሲነከሱ ቁስልዎን ያስታግስልዎታል!! ነፍሳቱ የነከስዎት ቦታ ላይ በሙዝ ልጫ በማሸት የሚኖረውን እብጠትና ህመም መቀነስ ይቻላል። 3. የተጎዳን የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል!! ሙዝ የተበላሸ ወይም የተጐዳ የፊት ቆዳን በሚያምር አዲስ የፊት ቆዳ የመተካት ምትሀታዊ ሀይል አለው። 4. ለእፅዋት ማዳበሪያነት ያገለግላል!! ደረቅ የሙዝ ልጫ ተወዳዳሪ የሌለው የአትክልትና እፅዋት ማዳበሪያ ነው። 5. የፊት መሸብሸብ ወይም መጨማደድን ይከላከላል!! ሙዝ ከፍተኛ የክሬምና የተፈጥሮ ማር ካላቸው ምግቦች የሚመደብ ሲሆን አንዳንድ ሴቶች የፊት መሸብሸብን ለመከላከል ሲሉ ከሙዝ የተሰሩ የፊት ክሬሞችን በሳምንት ለ3 ጊዜ ያህል ይጠቀማሉ። 6. የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል!! የሰውነት ቆዳዎ እያሳከክዎትና እየተሰነጣጠቀ ተቸግረዋል? ህመምዎ(ችግርዎ) ይገባኛል፤በጣም እድለኛ ነዎት!! እንደዚህ ያድርጉ የተሰነጠቀውን የሰውነትን ቆዳ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) ይሹት እንደዚያ ሲያደርጉ በሙዙ ልጫ ላይ ያለው ተፈጥሮአዊ ኢንዛይም በተሰነጠቀው ቆዳዎ ላይ በመግባት ስራውን ይሰራል ማለት ነው። 7. ጥሩ የአይስክሬም መስሪያ ነው!! በጣም ጣፋጭ ነገር ይወዳሉ? ነገር ግን ለማዘጋጀት ጊዜ ወይም ገንዘብ የለዎትም? እንግዲውስ እንዲህ ያድርጉ በጣም የቀዘቀዘ ሙዝ ቆራርጠው ወደ አይስክሬም መስሪያ ያስገቡት ከዚያም አስደናቂ ጣዕም ያለው አይስክሬም ይመገባሉ። 8. ክንታሮትን ያድናል!! ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ነው። ይህ ንጥረ ነገር ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው ስለዚህ ሙዝ ተፈጥሮአዊ የክንታሮት መድሀኒት ሆኖ ያገለግላል። 9. ሰውነታችን በስለት ሲቆረጥ ወይም ሲያብጥ የማዳን ሀይል አለው!! ሙዝ ሰውነታችን በግጭት ወይም በሌላ ምክንያት ሲያብጥ ወይም ስለት ነገር ሲቆርጠን በውስጡ ፓታሲየም የተባለ ንጥረ ነገር ስላለው ሰውነታችን ለማገገም የሚያደርገውን ሂደት ያግዛል ወይም ያፋጥነዋል። 10. ሙዝ ወፎችንና ቢራቢሮዎችን የመሣብ ሀይል አለው!! ወፎችንና ቢራቢሮዎች ልክ እንደሠው ልጅ ሁሉ የሙዝን ቃና በጣም ይወዱታል።ስለዚህ ሙዝ ይህን ያህል የመሣብ አቅም ስላለው ወፎችን የመመልከት ፍላጎት ካለዎት በአካባቢዎ ሙዝ ይጣሉላቸው ከዚያም በአስደናቂው ቃና ወደርስዎ ይስባሉ። 11. የቆዳ ውጤቶችንና የብር ጌጣጌጦችን (silver) ያፀዳል!! የቆዳ ዉጤቶችንና ከብር የተሰሩ ጌጣጌጦችን ለማፅዳት ለመርዛማ ኬሚካሎችን ለመግዛት ገንዘብዎን አያጥፉ በምትኩ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) በደንብ ካሹት በኋላ በጨርቅ ይጥረጉት። 12. ሙዝ በፀረ-ተባይ መድሀኒትነት ያገለግላል!! ማንም ሰው ቢሆን እፅዋት ተጎድተው ማየት አይፈልግም!! የሙዝ ልጫን ቆራርጠው በእፅዋቱ አካባቢ ከ6-7 ሳ.ሜ አርቀው ይቅበሩዋቸው ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአካሎቹ ላይ ያሉት ተባዮች ይሞታሉ። 13.የውሻን በሽታ ይከላከላል!! በፍቅር የሚወድዎትን ውሻዎ በቀላሉ ጤናውን ይጠብቅልዎታል። 14. ውሀን ያጣራል!! የተለያዮ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሙዝ ልጫ/ልጣጭ በወንዝ ውሀ ውስጥ የሚገኙትን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን መጦ የመያዝ አቅም አለው። 15. በሽታ የመከላከል አቅምዎን ይጨምራል። @DrSofonias

የልብ ድካም ማስጠንቀቂያ ምልክቶች 1.ድካም፦ ከተለመደው የተለየ ድካም መሰማት፤ ልብ ሰውነት እና አንጎል የሚፈልገውን በቂ ኦክሲጅን ባለማድረሱ የሚከሰት ምልክት ነዉ። 2. የእንቅስቃሴ ገደብ፦ብዙውን
የልብ ድካም ማስጠንቀቂያ ምልክቶች 1.ድካም፦ ከተለመደው የተለየ ድካም መሰማት፤ ልብ ሰውነት እና አንጎል የሚፈልገውን በቂ ኦክሲጅን ባለማድረሱ የሚከሰት ምልክት ነዉ። 2. የእንቅስቃሴ ገደብ፦ብዙውን ጊዜ የልብ ድካም ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ ስለሚደክሙ እና የትንፋሽ እጥረት ስለሚሰማቸው መደበኛ ተግባራቸውን ማከናወን አይችሉም። ይህ ከ 60 ዓመት እድሜ በኋላ በሰዎች ላይ በጣም ስለሚከሰት ይህንን የማስጠንቀቂያ ምልክት በማሰናከል "እርጅና" እንደሆነ ያስባሉ። 3.ሰዉነት ማበጥ ( edema)፦ ጥቅም ላይ የዋለው ደም ከታችኛው ዳርቻ ወደ ላይ እንዲመለስ ለማስገደድ ልብ በቂ የፓምፕ ሃይል ከሌለው ፈሳሽ በቁርጭምጭሚት ፣ እግሮች ፣ ጭኖች እና ሆድ ውስጥ ሊሰበሰብ ይችላል። ከመጠን በላይ ፈሳሽ በውሃ ክብደት መልክ ፈጣን ክብደት እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል። 4.የትንፋሽ እጥረት፦በሳምባ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ጥቅም ላይ የዋለውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ አዲስ ኦክሲጅን ለመለወጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል። በእንቅስቃሴ ላይ ብቻ ሳይሆን ተቀምጦም ሆነ ተኝቶ መተንፈስ ከባድ ይሆናል። ከእነዚህ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች አንዱን ስለተሰማዎ፣ የልብ ድካም አለቦት ማለት አይደለም። ነገር ግን 2 ወይም ከዚያ በላይ ከሆኑ ዶክተር ጋር መሄድ አለብዎት። https://t.me/DrSofonias

ቡና መጠጣት ጥቅሙ ወይስ ጉዳቱ ያመዝናል? በየቀኑ የምንወስደው ቡና ☕️ የሚሰጣቸው የጤና ጥቅሞች፣ ☕️ የሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳቶች፣ ☕️ መውሰድ የሚከለከሉ ሰዎች እነማን እንደሆኑ እንዲሁም በቀን ምን ያህል መውሰድ እንደሚመከር ያውቃሉ? ከሚሰጣቸው የጤና ጥቅሞች ስንጀምር ከማነቃቃት ባሻገር የተለያዩ ሥር የሰደዱ በሽታዎችን ይከላከላል። ከነዚህም ውስጥ ተጠቃሾቹ 👉አይነት ሁለት የስኳር በሽታ፣ 👉የጉበት በሽታ፣ 👉የፓርኪንሰንስ ህመም እንዲሁም የመርሳት (አልዛይመርስ) በሽታ ናቸው። በአንጻሩ ደግሞ ቡናን ከሚመከረው በላይ አዘውትሮ መጠቀም 👉ከፍተኛ የደም ግፊት ፣ 👉የልብ ምት መዛባት እና የኮሌስትሎር መጠን መጨመር ያስከትላል። የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ተጓዳኝ በሽታ የሌለባቸው ጤናማ ሰዎች ቡናን በመጠኑ ቢወስዱ የሚያገኙት የጤና ጠቀሜታዎች ያመዝናሉ። ለመሆኑ በቀን እንድንወስድ የሚመከረው የቡና መጠን ምን ያህል ነው? በህክምናው በቀን ከ300ሚግ ያለፈ የካፊን መጠን መውሰድ አይመከርም። እንደ ቡናው አይነት እና አሰራሩ ላይ በመመስረት አንድ ባለ 150ሚሊ ሰኒ ቡና ከ 30 እስከ 175 ሚግ ካፊን ሊኖረው ይችላል። ይህም ማለት በቀን በአማካኝ ከሁለት ወይም ሶስት ስኒ በላይ መውሰድ አይመከርም። ቡና አንዳይወስዱ የሚከለከሉ ሰዎች እነማን ናቸው? 👉ቡና ሰውነታችን ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከሰው ሰው ስለሚለያይ በአስተነኛ የካፊን መጠን አካላዊ እና ባህሪያዊ የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያዩ ሰዎች ቡና እንዲያቆሙ ይመከራሉ። ይህ ህፃናትንም ያካትታል። 👉 በተጨማሪም ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ፣ የልብ ህመም እና የኮሌስትሮል መጨመር ያለባቸው ሰዎች ቡና ከመውሰድ ይከለከላሉ። 👉 ለነፍሰጡር ሴቶች የሚወስዱትን የቡና መጠን በአግባቡ መቀነስ፤ከተቻለ ፈጽሞ ማቆም ያስፈልጋል። @DrSofonias

#ጤናመረጃ ሙቅ ውሃ መጠጣት የሚያስገኛቸው የጤና ጥቅሞች!! በቂ ንፁህ ውሃ መጠጣት ለቆዳ፣ ለጡንቻና ለመገጣጠሚያ ክፍሎች ጤንነት ያለው ጥቅም የላቀ ነው። ውኃ የሰውነት ሕዋሳት ንጥረ ነገሮችን እንዲመገቡና በሽታን እንዲከላከሉም ይረዳቸዋል። ሙቅ ውሃ መጠጣት ደግሞ ጤናን ለማሻሻል የሚረዳ ቀላል ዘዴ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፥ ከሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች መካከል፦ 1. ውሃን አሙቆ መጠቀም የሽንት ችግር እና ኪንታሮትን እና የሆድ በሽታን ከመከላከል ይረዳል በተጨማሪ የሆድ ድርቀትን ይቀንሳል ሲሉ ባለሙያዎች ገልፀዋል። 2. ምግብ በሆዳችን ውስጥ ቶሎ እንደዲዋሃድ! አንድ ሰው በቂ ውሃ ካልጠጣ ትንሹ አንጀት በምግብ እና በመጠጥ የሚወስደውን ፈሳሽ መጠቀምን ይመርጣል። 3. መርዛማ ነገሮችን ከሰውነት ለማስወገድ!! ጥናቶች ሙቅ ውሃ መጠጣት መርዛማ ነገሮችን ከሰውነታችን እንዲወገዱ ያግዛል። የሰውነት ሙቀት መጠን በመጨመር በላብ እንዲወጣ ያደርጋል። 4. የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖር!! የሞቀ ውሃ መጠጣት የደም ቧንቧን ወይም ሥሮችን በማስፋት የደም ዝውውርን ያሻሽላል። ይህ ደግሞ ጡንቻዎች እንደፈለጉት እንዲንቀሳቀሱ እና ህመምን ለመቀነስ ይረዳል። 5. የሰውነት ክብደት ለመቀነስ! ሁል ጊዜ ውሃን መጠጣት ሰውነታችን ንጥረ ነገሮችን እንዲመገብ እና ውፍረት እንዲቀንስ ይረዳል። 6. የህመም ስሜት ይቀንሳል! ለተጎዱ ጡንቻዎች የደም ዝውውርን እና ፍሰትን ያሻሽላል፤ የህመም ስሜታትን ሊቀንስ እንደሚችል ተረጋግጧል። 7. ጉንፋንን በመዋጋት የአፍንጫ ጤንነትን ያሻሽላል እንዲሁም የአፍንጫ መቆጣት ጫና ለመቀነስ ይረዳል። 8. ጭንቀትን ለመቀነስ:- የሞቀ ውሃ መጠቀም የአእምሮ ጭንቀት እና ውጥረት ይከላከላል። @DrSofonias

የጥርስ መቦርቦር በጥርስ የላይኛው ክፍል ላይ የሚመጡ ክፍተቶች ሲሆን በአብዛኛው በባክቴሪያ ምክንያት ይከሰታል።ባክቴሪያዎቹ ስኳር በመመገብ በሚያመርቱት አሲድ ምክንያት ጥርስን ይቦረቦራል። የባክቴሪያ ክምችት በጥርስ ሽፍን ላይ እንደ ቅርፊት አይነት ነገር በመስራት የጥርስ መበስበስ ያስከትላሉ። እነዚህን በተፈጥሮአዊ መንገድ እንዴት መከላከል እንደምንችል ጥቂት ነገሮችን እናጋራችሁ። ፨፨፨እርድ፨፨፨ እርድ ተፍጥሮአዊ የሆነ የፀረ ባክቴሪያ ባህሪው የድድ ኢንፌክሽንን ይከላከላል እንዲሁም የባክቴሪያ ቅርፊት እንዳይከሰት ይረዳል። ሌላው ጥቅም እንደ ጥርስ ማንጫ መንገድ ልንጠቀምበት ይቻላል። አንድ ማንኪያ ከ ኮኮናት ዘይት ጋር በመቀላቀል ጥርስ ከቦረሽን በኃላ ለ3-5 ከጠበቅን በኃላ አፍን መታጠብ ከላይ የጠቀስናቸውን ጥቅሞች ሊያመጣ ይችላል። ፨፨፨ሻይ፨፨፨ ጥቁር እና አረንጓዴ ሻይ ውስጥ ካትችንስ የሚባል ንጥረነገር ያለ ሲሆን ይህ ንጥረነገር የባክቴሪያ ክምችትን የሚከላከል ብቻ ሳይን የአሲድ ምርቱንንም ይከላከላል። አንድ ኩባያ ሻይ የጥርስ ጤንነትን ሊጠብቅ ይችላይ።ስኳር ግን መቀላቀል አያስፈልግም። ፨፨፨እሬት፨፨፨ እሬት ከፍተኛ ፀረ ባክቴሪያ ባህሪው የሚታወቅ ሲሆን ለድድ ኢንፌክሽን እና የጥርስ ቅርፊት ለመከላከል ይጠቅማል። እሬት የአፍ ማጠብያ የተጠቀሙ ከላይ የተጠቀሱትን ጥቅሞች እንደተገኙባቸው ታውቋል። በቀላሉ አሎ ቬራን ከውሀ ጋር በማቀላቀል ልክ እንደ የአፍ ማጠቢያ እንደምንጠቀመው ማድረግ በቂ ነው። ፨፨፨የኮኮናት ዘይት፨፨፨ የኮኮናት ዘይት ባክቴሪያን ስቦ በመውጣት የጥርስን ጤንነት ይጠብቃል። የድድ ኢንፌክሽን፣ቅርፊትን፣መጥፎ የአፍ ጠረንና የጥር መቦርቦርን ይከላከል እንዲሆም ጥርስ የማንጣት አቅምም እንዳለው ታውቋል። ኦርጋኒክ ኮኮናት ዘይት ለ5 ደቂቃ በሞግሞጥሞጥ ለውጡን ማየት እንችላለን። የሞግሞጥሞት ጊዜው ባረዘምን ቁጥር የተሻለና ፍጣን ለውጥ ልናገኝ እንችላለን። ምን አይነት ነገሮችን ማራቅ ያስፍልጋል ፨፨፨ስኳር፨፨፨ ስኳር የጥርስ ቅርፊት መከሰቻ ዋናው ምክንያት እንደሆነ ይታወቃል። ከስኳር ካላቸው ምግቦች መቆጠብ የተሻለ የጥርስ ጤንነት እንደሚያመጣ ይታወቃል። ፨፨፨ሪፋይንድ ካርቦሀይድሬት፨፨፨ ነጭ ዳቦ፣ፓስታ፣የተጠበሰ ድንች እና ብስኩቶች ልክ እንደ ስኳር ተመሳሳይ ጉዳት ያመጣሉ። ፨፨፨ለስላሳ መጠጦች፨፨፨ ለስላሳ መጠጥ ስኳር ብቻ ሳይን ፎስፍረስ ያላቸው ሲሆን ይህም ለጥርስ መሸርሸር ምክንያት ይሆናሉ ስለዚህ ራሳችንን ከነዚህ መቆጠብ ጠቃሚ ነው። ፨፨፨አሲዳማ ባህሪ ያላቸው ምግቦች፨፨፨ ይህ ባህሪ ያላቸው ምግቦች በተለይ አትክልቶች እንደ ሎሚ አፍ ውስጥ ለከፍተኛ ጊዜ መቀመጥ የለባቸውም። ጥሩ የጥርስ አጠባበቅ ቢኖረንም የጥርስ መቦርቦር ያጋጥመናል። ለዚህ ችግር ቀንደኛ መፍትሔ ቶሎ ህክምና ማግኝት ነወ። @DrSofonias

እረጅም ሳት የመቀመጥ ጉዳት በዶ/ር ሶፎነለያስ

የሆድ ድርቀት እራሳችን ላይ የሚከሰት እስካልሆነ ድረስ ጎዳዩ ሊናቅ ይችላል። በተከሰተ ጊዜ ግን የሆድ መነፍትና ማስማጥን በማምጣት ከፍተኛ ጭንቀት ይፍጥርብናል። የሆድ ድርቀት 40-60% የሚሆነውን አረጋውያን የሚያጠቃ ሲሆን ካልታከመ ወደ ኪንታሮት በሽታ መለወጡ አይቀርም። ባለሁበት የክፍለ ሀገር ሆስፒታል ዋና ምክንያት ለአረጋውያን አንጀት መታጠፍ ወይም መቆለፍ ምክንያት የሚሆነው የሆድ ድርቀት ነው። ምክንያቶቹ አመጋገብ ላይ እንደሆነ ብዙ ሰው ቢመሰክርም ሌሎች ምክንያቶች መኖራቸውም ግልፅ ነው። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የሆድ መድረቅ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ በከፊል ፨በቀን ውስጥ በቂ ፈሳሽ ባለመውሰድ ፨በቂ እንቅስቃሴ ባለማድረግ ፨በማስመለስ ምክንያት የሰውነት ፈሳሽ ማነስ ፨በሰውነት ትኩሳት ወይም በቂ ፈሳሽ በሰውነት ውስጥ አለመኖር ፨ፋይበር ያላቸው ምግቦችን በበቂ ለመመገብ ፨በአንዳንድ በሽታዎች ምክንያት ፨በትክክል ያልተደባለቀ የህጻናት ፎርሙላ ወተት ፨የእንቅርት እና ስኳር በሽታ ፨ሰገራ በሚገፍበት ጊዜ አለመጠቀም ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ መፍትሔው ምንድን ነው? ፨ፋይበር ያለው ምግብ መጠቀም አስፈላጊ ነው... ፨ማድቀቅ የማንችለው የምግባችን ክፍል ስለሆነ የሆድ ድርቀት ለመከላከል ይጠቅማል ፨ሰገራ የሚያለሰልስ መድኃኒቶች ፨የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፨ቡና መጠጣት ፨ሽንት ቤት በየጊዜው መጠቀም እነዚህን ሰገራ ለስላሳ የሚያረጎ መንገዶች ሞክረው ለውጥ እያሳዩ ካልሆነ ሀኪም ማየት ይኖርበታል። @DrSofonias

ቶሎ የመጨረስ ችግር የሚባለው የወንዶች የወሲብ ችግር ሲሆን ሁለቱም ባለፍለጎበት ጊዜ ቀደም ብሎ የወንዱ የመጨረስ ችግር ነው። መንስኤው የተለያየ ስለሆነ በትክክል በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚፍጠር ብሎ ማስቀመጥ ልንቸገር እንችላለን። በአጠቃላይ ዘላቂ መንስኤ ከሆነ ከ1 ደቂቃ በታች ሲሆን ዘላቂ ያልሆነ መንስኤዎች ከሆነ ከ3 ደቂቃ በፊት መጨረስ ብለን ልናስቀምጠው እንችላለን። ስለዚህ ችግር ማውራት እንደ ህፍረት ስለሚቆጠር ብዙ ወንዶች ችግራቸውን ተሸክመው ሲጨናነቁ ይስተዋላል። በኢትዮጵያ ጥናት ባይደረግበትም በአሜሪካ ከ40 አመት በታች የሆኑ ወጣቶች ከ30-70% ይህ ችግር እንዳለባቸው ታውቋል። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ምንስኤዎቹ ምንድን ናቸው? መንስኤዎቹ ዘላቂ እና የአጭር ጊዜ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ፨፨፨፨፨ዘላቂ መንስኤዎች፨፨፨፨፨ ፨በዘር ፨በትምህርት ወይም ስራ ፨የልጅነት የወሲብ ጥቃት ወይም ጉዳት ፨ተመሳሳይ ፆታ የሆነች የፍቅር ጓደኛ ፨የተቃራኒ ፆታ ወይም አጠቃላይ የወሲብ አመለካከት ፨ያለፉ የአይምሮ ጉዳቶች ወይም ችግሮች ሲሆኑ ዘላቂ ያልሆኑ መንስኤዎች ፨የአደንዛዥ ዕፅ መጠቀም ፨ሌላ የስንፍተ ወሲብ ችግሮች ፨ራስን ማርካት(በሳምንት ከ5 በላይ) በሁለቱም መንስኤዎች ከታች የጠቀስኳቸው ሁኔታዎች ወሳኝነት አላቸው። ፨፨የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት(ያገባ ወይስ ያላገባ) ፨፨ሌሎች ተጓዳኝ የሆኑ የፍቅር ግንኙነት ሁኔታ ፨፨ያለፍ የፍቅር ታሪክ ፨፨የተቃራኒ ፆታ የወሲብ ስሜት ምላሽ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ መፍትሔው ምንድን ነው? ለችግሩ ቀዳሚ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው ከፍቅር ጓደኛ ጋር መነጋገር ነው። ይህ የሁለቱንም ጭንቀትና አለመግባባትን ይፍታል። ትክክለኛውን መፍትሔ ማግኝት የሚቻለው በህክምና ሲሆን መንስኤው ዘላቂ ህመም ምክንያት ሊሆን ስለሚችል እነዚህ መለየት አለባቸው። በቤት ሆነን ልንሞክር የምንችለው መፎትሔዎች መካከል፦ 1. የዳሌ ጡንቻ የሚያጠነክሩ እንቅስቃሴዎች ማለትም የታፍ እና የመቀመጫ ጡንቻዎች የሚያጠነክሩ እና ሽንት መሀል ላይ የማቋራት እንቅስቃሴ ቶሎ የመጨረስ ወይም መርካትን ይቀንሳል። 2. ከኃልዝ ላይን ካገኝነው የ ጥናት ምንጭ ዚንክና ማግኒዥየም ሰፕሊመንቶች ቴስቴስትሮንን በመጨመር ቶሎ የመርካትን ባህሪ ይቀንሳሉ። እነዚህንም ንጥረነገሮች ልናገኝባቸው የምንችላቸው ምግቦች መካከል፦ • እርጎ • ቀይ ስጋ • ጥቁር ቸኮሌት • ነጭ ሽንኩርት • ጎመን • ማር በጥቂቱ ናቸው። 3. ወፍራም ኮንዶም ማረግ ስሜትን ስለሚቀንስ እንደ አንድ መፍትሔ ሊቆጠር ይችላል። 4. ሌላው እንዲቆይ ለማላመድ የምንጠቀምበት መንገድ ነው ይህም በግንኙነት ጊዜ የመጨረስ ስሜት ከመምጣቱ በፊት ግንኙነት ማቆም። ከእረፍት በኃላ ደግሞ እንደገና መሞከር። ይህ ሁኔታ አካል እየለመደ ይሄድና ከጊዜ በኃላ ስሜትን መቆጣጠር ያስችለናል። እነዚህ የጠቀስኳቸው መፍትሔ እንደሚሆናችሁ እገምታለሁ። መዘንጋት የሌለበት ከፍቅር ጋደኛ አልፎም ከሀኪም ጋር ችግሩን መወያየት ለችግሩ ፍጣን መፍትሔ ይሆናል እላለሁ። @DrSofonias