ch
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

前往频道在 Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

显示更多

📈 Telegram 频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias 的分析概览

频道 ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 19 856 名订阅者,在 医学 类别中位列第 1 159,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 699

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 19 856 名订阅者。

根据 06 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -486,过去 24 小时变化为 -2,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 16.16%。内容发布后 24 小时内通常能获得 6.83% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 210 次浏览,首日通常累积 1 357 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 6

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

凭借高频更新(最新数据采集于 07 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 医学 类别中的关键影响点。

19 856
订阅者
-224 小时
-737
-48630
帖子存档
የወንዶች ብልት መጠን ጉዳይ፤ እድገቱና አማካይ መጠኑ በዚህ ጉዳዩ ዙሪያ ባሰናዳነው የመጀመሪያው ክፍል ጽሁፋችን የወንድ ልጅ ብልት እድገት መቼ ጀምሮ መቼ እንደሚጠናቀቅ፣ እንዲሁም አማካይ የሚባለው የወንድ ልጅ የብልት መጠን ምን ያክል እንደሆነ የሳይንሳዊ ምርምር ውጤቶችን ዋቢ አድርገን ለማየት ሞክረናል። የብልት መጠንን ማሳደግ ይቻል እንደሆነም ጥያቄዎችን አንስተን፣ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ብልትን ለማሳደግ የሚደረጉ ሙከራዎችን አይተናል። እንቀጥል…. ☑️ ስለብልት መጠን የሚነገሩ አፈታሪኮች (Myths) ስለ ብለት መጠን እና ቅርጽ የሚነገሩ ብዙ አፈታሪኮች አሉ። እነዚህ አፈታሪኮች ብዙ ሰዎችን ለጭንቀት ሲዳርጉም ይስተዋላል። በስፋት ከሚነገሩት አፈታሪኮች መካከል የሚከተሉት በተደጋጋሚ የሚሰሙ ናቸው። 🍀 የእግር መዳፍ እርዝመትና የብልት እርዝመት እኩል ናቸው:- ይህ አፈታሪክ በሰፊው ሲነገር ቢሰማም ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው። የብልት መጠን ከዬትኛውም የሰውነታችን ክፍል ጋር እንደሚመጣጠን በጥናት የተረጋገጠ ነገር የለም። 🍀 ለግንኙነት ዝግጁ ያልሆነ (@flaccid state) እና ለግንኙነት ዝግጁ የሆነ (@erection state) ብልት በመጠን እኩል ናቸው:- ይህም ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ሚት ነው። ለግንኙነት ዝግጁ ያልሆነ ብልት መጠኑ በአየር ጠባይ ምክንያት ተለዋዋጭ ሊሆን ይችላል። 🍀 ሴቶች ትልቅ ብልት ያለው ወንድ ይመርጣሉ:- ብዙ ወንዶች የፍቅር አጋራቸው ብልታቸው ትልቅ ቢሆን እንደሚመርጡ ያስባሉ። ይሁንና በፈረንጆቹ 2006 ዓ.ም. የተደረገ አንድ ጥናት እንዳመለከተው በጥናቱ ከተሳተፉ ሴቶች 85% የሚሆኑት በፍቅር አጋራቸው የብልት መጠን ደስተኞች መሆናቸውን አመልክቷል። 🍀 ትልቅ ብልት የወሲብ እርካታን ይጨምራል:- ይህ ብዙ ወንዶችን የሚያስጨንቅ ሚት ነው። ከርዝመቱ ይልቅ የብልት ውፍረት ነው የወሲብ እርካታን የሚጨምረው የሚሉም አሉ። ያም ሆነ ይህ ግን ከብልት መጠን ይልቅ የሁለቱ መነጋገር እና እርስ በእርሳቸው አንዳቸው ለአንዳቸው የሚኖራቸው ስሜት የበለጠ የወሲብ እርካታን እንደሚጨምር ነው ጥናቶች የሚያመለክቱት። ☑️ ትንሽ ብልት (Micro penis) ምንድነው? ህክምናውስ? ማይክሮ ፒነስ (micro Penis) አንድ ህጻን ሲወለድ ብልቱ ምንም እንኳን ትክክለኛ ቅርጽና ይዘት ቢኖረውም መጠኑ ከሚገባው በታች የሆነ ሁኔታን የሚገልጽ የህክምና ቃል ነው። የአንድ ወጣት ወንድ ልጅ ብልት ለግንኙነት ዝግጁ በሆነበት (@erection state) ጊዜ ርዝመቱ ከ9.3 c.m. በታች ከሆነ የህክምና ባለሞያዎች ሁኔታውን micro Penis ነው ሲሉ ይገልጹታል። ይህ ችግር በጊዜ ከተደረሰበት (በልጅነት እድሜ) በሆርሞን ቴራፒ ህክምና የብልቱ እድገት እንዲነቃቃ የሚደረግበት እድል አለ። ማይክሮ ፒነስ (Micropenis) በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ሁኔታ ነው። ከ10,000 ወንድ ህጻናት 1.5 ቱ ብቻ ናቸው በዚህ ሁኔታ የመጠቃት እድል ያላቸው። ይሁንና ይህን ሁኔታ መገንዘብና አጠራጣሪ ነገር ስናስተውል ቶሎ ሀኪም ማማከሩ መልካም ነው። 👉 ማጠቃለያ:- ከብልት መጠንና ቅርጽ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ብዙ የሚነገሩ ከእውነትና ከሳይንስ የራቁ ነገሮች መኖራቸውን መገንዘብ ተገቢ ነው። ብልት የተፈጥሮ እድገቱን ካጠናቀቀ በኋላም የብልት መጠንን ለማሳደግ ሲባል ሰው ሰራሽ ዘዴዎችን መጠቀም የቆጡን አወርድ ብሎ የብብቱን ጣለ እንዲል የሀገሬ ሰው ለሌላ አላስፈላጊ ችግር ሊያጋልጥ እንደሚችል የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ። ስለዚህ እንዲህ ዓይነት አደገኛ ውሳኔ ከመወሰን በፊት የህክምና ባለሞያ ማማከሩ ተገቢ ነው። @DrSofonias

የአእምሮ ጤና እና ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ በብዙ የህይወት መንገዶች አዕምሯችንን መጠቀም በምንፈልግበት ቦታ በትምህርት ቤት፣ በስራ ቦታ፣ በፈተና እና በተለያዩ ቦታዎች መቀመጥን እናዘወትራለን፡፡ በአንድ ወቅት የወጣ ጥናት ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ የአእምሮ ነዳጅ አቅርቦት ላይ ተጽኖ ከማሳደር ባሻገር በአእምሮም ጤና ላይ አሉታዊ ተጽኖ ሊያመጣ እንደሚችል አመላክቷል፡፡ አዕምሯችን ጉሉኮስ የተራበ አካል ነው፡፡ ምንም አንኳን የሰውነታችንን ክብደት 2% ብቻ የሚሸፍን ቢሆንም 20% የኛን ሀይል አልያም ኢነርጂ የሚጠቀመው እርሱ ነው፡፡ ይህ ሀይል ደግሞ በአብዛኛው የመጀመሪ ደረጃ የአዕምሮ ነዳጅ በሆነው ጉሉኮስ መልክ የሚገኝ ነው፡፡ የዚህ ሀይል ስርጭት ከተቋረጠ የአዕምሯችንን ሴሎች ሊጎዳ ይችላል፡፡ ስለዚህ የጉሉኮስ በበቂ ደረጃ መኖር ከአይምሮ ጤንነት ጋር ቀጥተኛ ዝምድና አለው፡፡ አዕምሯችን ለከፍተኛ ጉሉኮስ መጠንም ይሁን ለአነሰተኛ ጉሉኮስ መጋለጥ ዲሜንሺያ ለተሰኘው ህመም የመጋለጥ አደጋን ይጨምርበታል፡፡ ይህም የሚጠቁመው በተገቢው መንገድ ጉሉኮስን መቆጣጠር ለአእምሮ ጤና እጅግ አስፈላጊ አስፈላጊመሆኑን ነው፡፡ ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ ከሚያመጣቸው የጤና እክሎች መካከል ጥቂቶቹ 💎 በለጋ ዕድሜ ለሞት የመጋለጥ (early death) አደጋን ከፍ ያደርገዋል፡፡ በግምት 60-75 መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በቀን ስምንት ሰዓት በመቀመጥ የሚመጣን በለጋ አድሜ ለሞት የመጋለጥ አደጋን ለማጥፋት ይረዳል፡፡ 💎 ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ የጉሉኮስ መጠንን በማዛባት ለአእምሮ ጤና ችግር ያጋልጥል፡፡ 💎 ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ በአእምሯችን የደም ስርጭትን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ከመቀመጥ ይልቅ መራመድ በአእምሯችን የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖር ይረዳል፡፡ የአእምሮ የደም ዝውውር ለአእምሮ የሚቀርበውን የጉልኮስ መጠን በመቆጣጠር አእምሮ ጤና ላይ አወንታዊ ተጽኖ ይፈጥራል፡፡ በአእምሮ የደም ዝውውር መቀነስ የአእምሮ ስራ በፍጥነት እንዲቀንስ የማድረግ እና ከመርሳት በሽታ ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ ☑️ መፍትሄ 🍀 ከምግብ በኋላ የመቀመጥ መጠናችንን መቀነስ 🍀 ከምሳ በኋላ የእግር ጉዞ ማድረግ 🍀 ከእራት በኋላ በተለያየ መንገድ እንቅስቃሴ ማድረግ 🍀 ጠዋት ወደ ስራ ስንሄድ ወይም ከስራ በኋላ በእግር መጓዝ። @DrSofonias

ሀንግኦቨር ሀንግኦቨር ለበርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የጤና እክሎች የሚያጋልጥ ከልክ በላይ የአልኮል መጠጥ በመጠጣት ምክንያት የሚከሰት ህመም ነው። ☑️ ምልክቶች 💎 ድካም 💎 ከመጠን በላይ ጥማት እና የአፍ መድረቅ 💎 ራስ ምታት እና የጡንቻ ህመም 💎 ማቅለሽለሽ ማስታወክ ወይም የሆድ ህመም 💎 በቂ እንቅልፍ አለመተኛት 💎 በብርሃን እና በድምፅ ቶሎ መረበሽ 💎 ማዞር 💎 የማተኮር ችሎታ መቀነስ 💎 እንደ ድብርት ጭንቀት እና ብስጭት ያሉ የስሜት መቃወስ 💎 ፈጣን የልብ ምት። ☑️ አጋለጭ ሁኔታዎች 🔹 በባዶ ሆድ መጠጣት 🔹 እንደ ኒኮቲን ይዘት ያላቸው ሌሎች ነገሮችን ከአልኮል ጋር መጠቀም ለምሳሌ ሲጋራ ማጨስ 🔹 ከጠጡ በኋላ በደንብ እንቅልፍ አለመተኛት። ☑️ ውስብስብ ችግሮች 🦋 የመርሳት ችግር 🦋 ለማተኮር መቸገር 🦋 ከስራ መቅረት 🦋 ተግባሮችን ማጠናቀቅ ላይ ችግር 🦋 ከሌሎች ጋር ግጭት 🦋 በትምህርት ቤት ወይም በሥራ ቦታ መተኛት። ☑️ መከላከያ መንገዶች ሀንግኦቨር ለመከላከል ብቸኛው የተረጋገጠ መንገድ የአልኮል መጠጥን ማስወገድ ነው። ነገርግን አልኮል የሚጠቀሙ ከሆነ የሚከተሉትን ቢያደርጉ ለውጥ ማየት ይችላሉ:- 💥 ከመጠጣትዎ በፊት እና ሲጠጡ ይበሉ 💥 የሚጠጡትን መጠጥ በጥንቃቄ ይምረጡ 💥 በመጠጥ መካከል ውሃ ይጠጡ 💥 ገደብዎን ይወቁ እና በመጠኑ ብቻ ይጠጡ 💥 ቀስ ብለው ይውሰዱት 💥 በአንድ ሰዓት ውስጥ ከአንድ በላይ የአልኮል መጠጥ ከመጠጣት ይቆጠቡ 💥 ገደብዎ (ወይም ከዚያ በፊት) ሲደርሱ ሙሉ በሙሉ መጠጣትዎን ያቁሙ። 👉 ከሀንግኦቨር ለመውጣት የሚረዱ የቤት ውሰጥ መፍትሄዎች 💥 ብዙ ውሃ ማጠጣት 💥 ቁርስ መብላት 💥 አንቲኦክሲደንት ይዘት ያላቸውን ምግቦች ይጠቀሙ። 👉 ጥሩ የአንቲኦክሲደንት ምንጮች የሚከተሉትን ያካትታሉ:- 🍀 ስትሮቤሪ 🍀 የወይን ፍሬ 🍀 ሮማን 🍀 ካሮት 🍀 ሙዝ 🍀 ስፒናች 🍀 ዝንጅብል 🍀 ጥቁር ቸኮሌት 🍀 ለውዝ 🍀 አረንጓዴ እና ጥቁር ሻይ ናቸው።

ዝንጅብል እንዳይጠቀሙ የሚመከሩ ሰዎች ዝንጅብል በርካታ የጤና በረከቶች እንዳሉት ተደጋግሞ የተነገረ ሀቅ ነው። ይሁን እንጂ ዝንጅብል ለሁሉም አይነት የጤና ችግር መፍትሄ ይሆናል ማለት አይደለም። ☑️ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዝንጅብል መጠቀም የማይኖርባቸው ወይም የሌለባቸው ሰዎች ናቸው:- 👉 ነፍሰ ጡር ሴቶች! ዝንጅብል በውስጡ የያዘው ሀይለኛ አነቃቂ ንጥረ ነገር ከመደበኛው ጊዜ አስቀድሞ መውለድን ሊያስከትል ይችላል። በተለይም መውለጃዋ የተቃረበ እንስት ዝንጅብል ባትወስድ ይመከራል። 👉 ክብደት መጨመር የሚፈልጉ ሰዎች! ዝንጅብል ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ሰዎች ተመራጭ ነው። በአንፃሩ ክብደት መጨመር ለሚፈልጉ ሰዎች ምኞታቸውን ገደል የሚከት ነው ተብሏል። ዝንጅብል ከሻይ ጋር ቀላቅለንም ሆነ በሌላ መንገድ ስንወስድ የጥጋብ ስሜት እንዲሰማን ከማድረጉም ባለፈ በሰውነታችን ውስጥ የተከማቸ ስብን ለማቅለጥ ያግዛል። በመሆኑም ክብደትዎን ለመጨመር ከፈለጉ ከዝንጅብል ራቁ ተብላችኋል። 👉 ከደም ጋር የተያያዘ ችግር ያለባቸው ሰዎች! ዝንጅብል የደም ዝውውርን ያፋጥናል። የደም ማነስ፣ የደም መፍሰስ ችግር (ሄሞፊሊያ)፣ የደም መርጋት፣ የተለያዩ የደም ካንሰሮች (ሊኩሚያ፣ ሊምፎማ እና ሚይሎማ) ያሉባቸው ሰዎች ዝንጅብል ቢጠቀሙ የተለየ ተፅእኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል። 👉 የደም ግፊት እና ስኳር ህመምተኞች! የደም ግፊት አልያም የስኳር ህመምን ለመቆጣጠር መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎችም ዝንጅብል በጭራሽ መውሰድ የለባቸውም ተብሏል። ይህም ዝንጅብል የህክምና ክትትሉን ሊያዛባባቸው ስለሚችል ነው። በተለይ ከፍተኛ የደም ግፊትን እና ደም መርጋትን ለመቀነስ ከሚወሰዱ መድሃኒቶች ጋር ዝንጅብል አብሮ መውሰድ አደገኛ መሆኑን ባለሙዎች ይናገራሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት አካላት ዝንጅብል መመገብ ቢያምራቸው እንኳን በአቅራቢያ የሚገኝ የህክምና ባለሙያ አማክረው ቢሆን ይመከራል፡፡ @DrSofonias

የዋና መሠረታዊ የጤና ጥቅሞች ዋና ሙሉ ሰውነትን እና የ ካርዲዮ-ቫስኩላር ስረዓታችንን የሚያሰራ ስፖርት ነው። ለአንድ ስዓት ያክል መዋኘት ለተመሳሳይ ሰዓት የመሮጥን ያክል ካሎሪን የማቃጠል አቅም አለው። ያውም አጥንታችንን እና መገጣጠሚያዎቻችንን ደህንነታቸው ተጠብቆ። ☑️ ለመሆኑ ውሃ ዋና የሚሰጠን ዋና ዋና ጥቅሞች ምንድን ናቸው? 1️⃣ ሙሉ ሰውነታችን እንዲንቀሳቀስ ያደርጋል በምንዋኝበት ጊዜ ከእግር ጣታችን እስከ ጭንቅላታችን ያሉ የሰውነት ክፍሎቻችን በሙሉ ይንቀሳቀሳሉ። በዚህም እንቅስቃሴ የሰውነታችን ጫናን የመቋቋም አቅም (Endurance) ይጨምራል። አካላችንም ይጠነክራል። የተለያዩ አይነት የዋና ስልቶች የተለያዩ ጡንቻዎቻችንን በመገንባት ጥሩ ቁመና እንዲኖረንም ይረዳል። 2️⃣ ሳንባና ልብን ያጎለብታል ዋና ለላይኛው (ለሚታየው) የሰውነት ክፍላችን ከሚሰጠው የጤና ጥቅም በተጨማሪ ለውስጠኛው የሰውነት ክፍሎቻችን ጤንነትም ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ አለው። ልብን እና ሳንባን በማጎልበት ረገድ ከሚሰጠን ጥቅም በተጨማሪ ውሃ ዋና የደም ግፊት እና ስኳርን ከመሳሰሉ የጤና ምስቅልቅሎች እራስን ለመጠበቅ ሁነኛ መላ መሆኑን በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ውጤት ያመለክታል። 3️⃣ ለአስም ታማሚዎች የአስም በሽታ ተጠቂ ለሆኑ ሰዎች ዋና እጅግ ተመካሪ ስፖርት ነው። ሰዎች በሚዋኙበት ወቅት ረዘም ላለ ሰዓት ትንፋሻቸውን ውጠው መቆየት ስለሚለማመዱ የአተነፋፈስ ሥርዓታቸውን የመቆጣጠር ብቃትን ያዳብራሉ። ይህም አስም ለሚያሰቃያቸው ሰዎች አንዱ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ባለሞያዎቹ ይመክራሉ። 👉 ጥንቃቄ:- አንዳንድ ጊዜ የመዋኛ ገንዳ ለማጽዳት ጥቅም ላይ የሚውሉ ኬሚካሎች በራሳቸው አስምን የማባባስ እድል አላቸው። ስለዚህ ከመዋኘቶ በፊት ስለመዋኛ ገንዳው ንጽህና ግንዛቤ ሊኖሮት ይገባል። 4️⃣ ለጥሩ እንቅልፍ ኤንሲቢአይ ላይ የወጣ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ውሃ ዋና ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት የሚመከር እንቅስቃሴ ነው። በእንቅልፍ ማጣት (Insomnia) የሚቸገሩ ሰዎች ዋና በመዋኘት ጥሩ እንቅልፍ የማግኘት እድላቸውን ከፍ ማድረግ ይችላሉ። 5️⃣ ስሜትን ለማነቃቃት ሳይንቲስቶች የመርሳት በሽታ (Dementia) ባለባቸው ሰዎች ላይ ለ12 ወራት በዋና ላይ ተመስርተው ባደረጉት ጥናት ውጤት መሰረት ዋና በሰዎች ስነ ልቦና እና የስሜት መነቃቃት ላይ አዎንታዊ ሚና እንዳለው ተገልጿል። በተጨማሪም ጭንቀትን በመቆጣጠር ረገድ የዋና ጥቅም ከፍተኛ መሆኑን ጥናቶች አመልክተዋል። 6️⃣ ለጤናማ እርግዝና ኔቸር ዶት ኮም ላይ የወጣ አንድ ጥናት እንዳመለከተው እናቶች በእርግዝና ወራት የሚያደርጉት የዋና እንቅስቃሴ በጽንሱ የአዕምሮ እድገት ላይ አዎንታዊ የሆነ ተጽዕኖ አለው። የሚዋኙ እርጉዝ ሴቶች አካላዊ ጉዳት ያለበት ልጅ የመውለድ እድላቸውም የቀነሰ ይሆናል። እርጉዝ ሴቶች በዬትኛውም የእርግዝናቸው ወቅት ላይ መዋኘት ይችላሉ። @DrSofonias

የአልኮልና አደንዛዥ እፅ ተፅዕኖ በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ላይ ሁሉም ሰው ከልክ ያለፈ መጠጥና አደንዛዥ እፅ ወሲባዊ ህይወትንና አጠቀላይ ደህንነትን እንደሚጎዳ ያውቃል። እንደ አለመታደል ሆኖ ግን አብዛኛው ሰው የሚያውቀው በአልኮልና በአደንዛዥ እፅ የተነሳ ሊያጋጥመው የሚችለውን የእርካታ ጣርያ ላይ አለመድረስ ብቻ ይመስለናል። ☑️ ይህን ጉዳይ የዘርፉ ባለሙያዎች እንዲህ ይተነትኑታል:- 🦋 ደህንነቱ ያልተጠበቀ ወሲብ አልኮልና አደንዛዥ እፅን በምንጠቀምበት ጊዜ ወሲብ መፈፀም እንደሌለብን በምናምንበት ሁኔታ እንኳን ውስጥ ብንሆን ራሳችንን ለአደጋ አጋልጠን ወሲብ ልንፈፅም እንችላለን። ታዲያ እዚህ ላይ ከቁጥጥር ውጭ ሆነናል ማለት ምናልባትም ኮንዶም መጠቀምን ልንረሳ እንችላለን ማለት ነው፡፡ እንደው እንደምንም ራሳችንን ተቆጣጥረን ኮንዶም ለመጠቀም ብንሞክር እንኳን ወይ ልንቀደው አልያም ከአጠቃቀም መመሪያው በተቃራኒው ልንጠቀመው የምንችልበት እድል ሰፊ ነው። በጥፍራችን ልንቀደው፣ በትክክል በብልታችን ላናጠልቀው አልያም ጫፍ ላይ ምትገኘዋን የኮንዶሙን ክፍል አየር እንዳታስገባ ላንይዛት በኋላም በግንኙነት ጊዜ ልትቀደድ ትችላለች፡፡ ምክንያቱም ሰክረናልና፡፡ ይህ ደግሞ ለአባላዘር በሽታና ላልተፈለገ እርግዝናም ሊያጋልጠን ይችላል። ይህን ሁሉ አልፈን ኮንዶሙን በአግባቡና በመመሪያው መሰረት ብናጠልቀው እንኳን የጠጣነወ አልኮል ከመደበኛው ጊዜ በላይ ወሲብ እያደረግን እንድንቆይ ሊያደርገን ይችላል። ይህ ደግሞ የብልት ማለስለሻ ቅባቶች ድርቀትና ፍትጊያን ያመጣል። በመጨረሻም ኮንዶሙ ሊቀደድ ይችላል። 🦋 ያልተፈለገ ወሲብና ፀፀት የአልኮልና የአደንዛዥ እፅ አንዱና ዋነኛው ችግር አእምሯችንን ማገናዘብ ወደማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በመክተት በሚቀጥለው ቀን የምንፀፀትበትን ጉዳይ ዛሬ እንድንፈፅም ሊያደርጉን ይችላሉ። በአልኮልና በአደንዛዥ እፅ ምክንያት የጓደኝነት ህይወትዎን አያበላሹ አልያም በሚቀጥለው ቀን ከማያውቁት እንግዳ ሰው ጎን ራስዎን ምንእንደተፈጠረ እንኳን ማስታወስ በማይችሉበት ሁኔታ ተኝተው እንዲያገኙት አይፍቀዱ፡፡ 🦋 መደፈር የወሲባዊ ብዝበዛና መደፈር መቼም ቢሆን የሰለባው ጥፋት ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን አልኮልና አደንዛዥ እፅ መጠቀም ወሲባዊ ብዝበዛ እንዲፈፀምብዎ፣ እንዲደፈሩ ተጋላጭ ሊያደርግዎት አልያም የከፋ አደጋ እንዲደርስብዎ የሚያደርግ ሁኔታ ውስጥ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ 🦋 ደካማ ወሲባዊ ብቃት አልኮልና በተለይ እንደ ኮኬይን፣ ሄሮይን እና ስዳቲቭስ ያሉ አደንዛዥ እፆች በወሲባዊ አካላቶቻችን ላይ የሚገኙ የነርቭ ሴሎችን ሊያደነስሷቸውና ከጥቅም ውጭ ሊያደርጓቸው ይችላሉ፡፡ ይሄ ደግሞ እርካታን ለማግኘት እጅግ አዳጋች ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ እንዲሁም ለወሲባዊ ግንኙነት ሳቢ ሆነን እንድንታይ ላያደርጉን ስለሚችሉ ደስ የማይል ወሲብ ልንፈፅም እንችላለን፡፡ በተጨማሪም ወንዶችን ብልታቸው እንዳይቆም ሴቶችን ደግሞ በቂ የብልት ማለስለሸ ቅባት እንዳያዘጋጁ ሊያደርጓውም ይችላሉ። በነገራችን ላይ ከመጠን ያለፈ መጠጥ መጠጣት ከድብርት ጋር ስለሚያያዝ የወሲብ ፍላጎትዎን ጭራሹንም ሊገድለው ይችላል። @DrSofonias

የልጆች አዕምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው የሚያደርጉ 7 ምግቦች 1️⃣ እርጎ አእምሮ ላይ መልዕክት በተገቢው እንዲላክ እና እንዲቀበል ይረዳል፣ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ ይይዛል፤ ይህ ደግሞ የአእምሮ ህብረ ህዋሶች እና መልእክት አስተላላፌዎች በተገቢው እንዲያድጉ ይጠቅማል። 2️⃣ አትክልቶች አትክልቶች አንቲ ኦክሲደንትነት አላቸው ይህ ደግሞ የአዕምሮ ህዋሶች ጤናማ እንዲሆኑ ይረዳል። ለምሳሌ እንደ ስኳር ድንች፣ ዱባ፣ ካሮት ያሉትን መስጠት፣ እንደባሮ ሽንኩርት፣ እስፒናች፣ ቆስጣ ያሉት ደግሞ በፎሌት የበለፀጉ ስለሆኑ ልጆችን ከመርሳት በሽታ ይከላከላሉ። 3️⃣ ብሮኮሊን ካንሰር ተከላካይነት ባህሪ አለው በተጨማሪም የነርቭ ስርዐት በተገቢው የተያያዘ እንዲሆን ያግዛል። 4️⃣ አቮካዶ አስፈላጊ ቅባት ይይዛል ይህም በቂ ደም ወደ ጭንቅላት እንዲዘዋወር ይረዳል። ኦሊክ አሲድ በመያዙ ምክንያት ማይሊን የተባለውን የአዕምሮ ክፍል ከመጥፎ ነገር ይከላከለዋል (ማይሊን በሰዐት በ200 ማይል ፍጥነት መልዕክት እንዲተላለፍ ያደርጋል)። በቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ መሆኑ ልጆች በግፌት የመያዝ እድላቸውን ይቀንሳል። 5️⃣ አሳ አሳዎች ኦሜጋ 3 የበለፀጉ በመሆናቸው የልጆች አእምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው ይረዳሉ። 6️⃣ እንቁላል የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል ለምሳሌ ኦሜጋ 3፣ ዚንክ፣ ኮሊን (አሴታይል ኮሊን) እንዲመረት የሚረዳ ሲሆን የማስታወስ ችሎታን ለማዳበር ያግዛል። 7️⃣ የተፈጨ አጃ በተለይ ለቁርስ ብንመግባቸው ጥሩ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖራቸው ይረዳል፤ በተጨማሪም በቫይታሚን ኢ፣ ዚንክ፣ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ ነው። ከፍተኛ ፉይበርነት ስላለው ሀይልን እንዲያገኙም ያደርጋል። @DrSofonias

🎯ኩላሊት የሚጎዱ ልማዶች አሳሳቢ የሆነው የኩላሊት ህመም ቀድሞ መከላከያ መንገዶችን ያውቃሉ ? ብዙ ልማዶች ለኩላሊት ህመም ምክንያት ናቸው እነዚህም 🔹ሽንትን መቋጠር ሽንት በፊኛ ውስጥ ረጅም ሰአት ሲቆይ በውስጡ የሚያድጉት ባክቴሪያዎች ይበራከታሉ። እንዚህ ባክቴሪያዎች የሽንት ቧንቧ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊያመጡ ይችላሉ። ሽንትን መያዝ ኩላሊት ላይ በሚያደርሰው ጫናም ኩላሊት ተጎድቶ ሽንትን የመቆጣጠር ችሎታችንን ሊያጠፋ ይችላል። 🔹በቂ ውሃ አለመጠጣት አንድ ሰው በቀን ቢያንስ ከ10 እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት አለበት። 🔹ጨው ማብዛት ብዙ ጨው መመገብ ኩላሊታችን ላይ ከፍተኛ ጉ በምንመገበው ጨው የሚገኘውን ሶዲየም 95% ያህሉ በኩላሊታችን ነው የሚቀየረው። ጨው ስናበዛ ኩላሊታችን ጨውን ለማጣራት ይበልጥ መስራት ይኖርበታል። 🔹የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ማዘውተር የኩላሊት ህመም ካለብዎ ዶክተርዎን ሳያማክሩ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን አይጠቀሙ። 🔹ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች ማብዛት 🔹መጠጥ ማብዛት መጠጥ ሲበዛ ኩላሊታችን አደጋ ላይ ይወድቃል ። መጠጥ ኩላሊታችን እና ጉበታችን ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። 🔹ሲጋራ ማጨስ 🔹ቀላል ኢንፌክሽኖችን በግዜው አለመታከም። @DrSofonias

ሙዝ ለጤና የሚኖረው 15 ጠቀሜታዎች 1. ጥርስን ያነጣል!! ጥርስዎን ሁልጊዜ ሲቦርሹ ለሁለት ደቂቃ ያህል በሙዝ ልጣጭ/ልጫ ጥርስዎን ይሹት ከዚያም አስደናቂ ለውጥ ያገኙበታል። 2. በተለያዩ ነፍሳቶች ሲነከሱ ቁስልዎን ያስታግስልዎታል!! ነፍሳቱ የነከስዎት ቦታ ላይ በሙዝ ልጫ በማሸት የሚኖረውን እብጠትና ህመም መቀነስ ይቻላል። 3. የተጎዳን የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል!! ሙዝ የተበላሸ ወይም የተጐዳ የፊት ቆዳን በሚያምር አዲስ የፊት ቆዳ የመተካት ምትሀታዊ ሀይል አለው። 4. ለእፅዋት ማዳበሪያነት ያገለግላል!! ደረቅ የሙዝ ልጫ ተወዳዳሪ የሌለው የአትክልትና እፅዋት ማዳበሪያ ነው። 5. የፊት መሸብሸብ ወይም መጨማደድን ይከላከላል!! ሙዝ ከፍተኛ የክሬምና የተፈጥሮ ማር ካላቸው ምግቦች የሚመደብ ሲሆን አንዳንድ ሴቶች የፊት መሸብሸብን ለመከላከል ሲሉ ከሙዝ የተሰሩ የፊት ክሬሞችን በሳምንት ለ3 ጊዜ ያህል ይጠቀማሉ። 6. የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል!! የሰውነት ቆዳዎ እያሳከክዎትና እየተሰነጣጠቀ ተቸግረዋል? ህመምዎ(ችግርዎ) ይገባኛል፤በጣም እድለኛ ነዎት!! እንደዚህ ያድርጉ የተሰነጠቀውን የሰውነትን ቆዳ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) ይሹት እንደዚያ ሲያደርጉ በሙዙ ልጫ ላይ ያለው ተፈጥሮአዊ ኢንዛይም በተሰነጠቀው ቆዳዎ ላይ በመግባት ስራውን ይሰራል ማለት ነው። 7. ጥሩ የአይስክሬም መስሪያ ነው!! በጣም ጣፋጭ ነገር ይወዳሉ? ነገር ግን ለማዘጋጀት ጊዜ ወይም ገንዘብ የለዎትም? እንግዲውስ እንዲህ ያድርጉ በጣም የቀዘቀዘ ሙዝ ቆራርጠው ወደ አይስክሬም መስሪያ ያስገቡት ከዚያም አስደናቂ ጣዕም ያለው አይስክሬም ይመገባሉ። 8. ክንታሮትን ያድናል!! ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ነው። ይህ ንጥረ ነገር ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው ስለዚህ ሙዝ ተፈጥሮአዊ የክንታሮት መድሀኒት ሆኖ ያገለግላል። 9. ሰውነታችን በስለት ሲቆረጥ ወይም ሲያብጥ የማዳን ሀይል አለው!! ሙዝ ሰውነታችን በግጭት ወይም በሌላ ምክንያት ሲያብጥ ወይም ስለት ነገር ሲቆርጠን በውስጡ ፓታሲየም የተባለ ንጥረ ነገር ስላለው ሰውነታችን ለማገገም የሚያደርገውን ሂደት ያግዛል ወይም ያፋጥነዋል። 10. ሙዝ ወፎችንና ቢራቢሮዎችን የመሣብ ሀይል አለው!! ወፎችንና ቢራቢሮዎች ልክ እንደሠው ልጅ ሁሉ የሙዝን ቃና በጣም ይወዱታል።ስለዚህ ሙዝ ይህን ያህል የመሣብ አቅም ስላለው ወፎችን የመመልከት ፍላጎት ካለዎት በአካባቢዎ ሙዝ ይጣሉላቸው ከዚያም በአስደናቂው ቃና ወደርስዎ ይስባሉ። 11. የቆዳ ውጤቶችንና የብር ጌጣጌጦችን (silver) ያፀዳል!! የቆዳ ዉጤቶችንና ከብር የተሰሩ ጌጣጌጦችን ለማፅዳት ለመርዛማ ኬሚካሎችን ለመግዛት ገንዘብዎን አያጥፉ በምትኩ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) በደንብ ካሹት በኋላ በጨርቅ ይጥረጉት። 12. ሙዝ በፀረ-ተባይ መድሀኒትነት ያገለግላል!! ማንም ሰው ቢሆን እፅዋት ተጎድተው ማየት አይፈልግም!! የሙዝ ልጫን ቆራርጠው በእፅዋቱ አካባቢ ከ6-7 ሳ.ሜ አርቀው ይቅበሩዋቸው ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአካሎቹ ላይ ያሉት ተባዮች ይሞታሉ። 13.የውሻን በሽታ ይከላከላል!! በፍቅር የሚወድዎትን ውሻዎ በቀላሉ ጤናውን ይጠብቅልዎታል። 14. ውሀን ያጣራል!! የተለያዮ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሙዝ ልጫ/ልጣጭ በወንዝ ውሀ ውስጥ የሚገኙትን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን መጦ የመያዝ አቅም አለው። 15. በሽታ የመከላከል አቅምዎን ይጨምራል። @DrSofonias

የልብ ድካም ማስጠንቀቂያ ምልክቶች 1.ድካም፦ ከተለመደው የተለየ ድካም መሰማት፤ ልብ ሰውነት እና አንጎል የሚፈልገውን በቂ ኦክሲጅን ባለማድረሱ የሚከሰት ምልክት ነዉ። 2. የእንቅስቃሴ ገደብ፦ብዙውን
የልብ ድካም ማስጠንቀቂያ ምልክቶች 1.ድካም፦ ከተለመደው የተለየ ድካም መሰማት፤ ልብ ሰውነት እና አንጎል የሚፈልገውን በቂ ኦክሲጅን ባለማድረሱ የሚከሰት ምልክት ነዉ። 2. የእንቅስቃሴ ገደብ፦ብዙውን ጊዜ የልብ ድካም ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ ስለሚደክሙ እና የትንፋሽ እጥረት ስለሚሰማቸው መደበኛ ተግባራቸውን ማከናወን አይችሉም። ይህ ከ 60 ዓመት እድሜ በኋላ በሰዎች ላይ በጣም ስለሚከሰት ይህንን የማስጠንቀቂያ ምልክት በማሰናከል "እርጅና" እንደሆነ ያስባሉ። 3.ሰዉነት ማበጥ ( edema)፦ ጥቅም ላይ የዋለው ደም ከታችኛው ዳርቻ ወደ ላይ እንዲመለስ ለማስገደድ ልብ በቂ የፓምፕ ሃይል ከሌለው ፈሳሽ በቁርጭምጭሚት ፣ እግሮች ፣ ጭኖች እና ሆድ ውስጥ ሊሰበሰብ ይችላል። ከመጠን በላይ ፈሳሽ በውሃ ክብደት መልክ ፈጣን ክብደት እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል። 4.የትንፋሽ እጥረት፦በሳምባ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ጥቅም ላይ የዋለውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ አዲስ ኦክሲጅን ለመለወጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል። በእንቅስቃሴ ላይ ብቻ ሳይሆን ተቀምጦም ሆነ ተኝቶ መተንፈስ ከባድ ይሆናል። ከእነዚህ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች አንዱን ስለተሰማዎ፣ የልብ ድካም አለቦት ማለት አይደለም። ነገር ግን 2 ወይም ከዚያ በላይ ከሆኑ ዶክተር ጋር መሄድ አለብዎት። https://t.me/DrSofonias