cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

AbuTolhaAhmedmusa

ከቻናሉ ይቀላቀሉ በአላህ ፍቃድ ጠቃሚነጥቦችንያገኛሉ ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ https://t.me/joinchat/SBf-mUs1ixjO31Gc ”ሙብተዲዕ (መጀመሪያ) ቤቱን ከውስጥ ያበላሻል። ከዛም ለጠላት በሩን ከፍቶ ግባ ይለዋል” ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሃዲ አልመድኸሊ [المجموع صـ (።

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
470
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-27 روز
-1730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

👉 ሐቅና ባጢል እስኪለይ ከኣል ኢምናን የቁርኣን ትርጉም ደርስ ላይ ተቀንጭቦ የተወሰደ – ሐቅና ባጢል እስኪለይ የባጢል ሀይሎችን ባጢል ግልፅ ማድረግ ግድ ነው ። – የሱፍዮች ባጢል – የኢኽዋኖች ባጢል – የሙመዪዓዎች ባጢል የሁሉም ባጢል ይነገራል የተመራ ሰው በመረጃ ላይ ሆኖ ሊመራ የጠመመ ሰው መረጃው ከደረሰው በኋላ ሊጠም የጣፈጠው ቢጣፍጠውም የመረረው ቢመረውም ባጢል ግልፅ ይደረጋል ። – በሕይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም ። ባህሩ አላህ በሐቅ ላይ ያፅናው ካልሆ በጥቅም ምላሱ ሳይያዝ አላህ ወደርሱ ይወሰደው ብላችሁ ዱዓእ አድርጉለት ። አላህ ሁላችንንም በሐቅ ላይ ፅናቱን ይሰጠን ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ሐቅና ባጢሉ እስኪለይ.mp33.05 MB
📖 የኢማሙ አሕመድ ኡሱል አስ-ሱንና ኪታብ ደርስ ክፍል 4 🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አል-ሐበሺ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ) 🕌 በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል 🕰 ከጁምዓ እስከ እሁድ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ የሚሰጥ ት/ት የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
نمایش همه...
ኡሱል አስ-ሱንና ክፍል 4.mp313.74 MB
🟢ከሴረኞች ቂጂ  ማስጠንቀቅ السَّعِيدُ مَنْ وُعِظَ بغَيْرِهِ ከአሸይኽ ሙሀመድ ሰዒድ ረስላን ማብራሪያ 👉 https://t.me/Abuhemewiya/2410 🔊አቡ ሀመዊየህ https://t.me/Abuhemewiya
نمایش همه...
የሴረኞች ቂጂ .mp323.39 MB
🚫 እውነትም እንቁ – ጣጣሽ እንቁ የሚለው ቃል እኔ የማውቀው የከበረ ማእድን መሆኑን ነው ። እኛ ሀገር ግን ዘመን መለወጫ ላይ የሚወጣን አበባ ለመግለፅ ይጠቀሙበታል ። በእነርሱ እይታ አበባዋና ጣጣዋ ምን እንደሆነ ባላውቅም በኔ እይታ ግን የዘመን መለወጫን ተክትላ የምትመጣው እንቁ ብዙ ጣጣ አላት ። በሌላ አባባል ዘመን መለወጫው ብዙ ጣጣ አለው ። ከሁሉም በፊት ይህ ባአል ከክርስትና እምነት ጋራ የተገናኘ ስለሆነ ሙስሊሞችን አይመለከትም ። ሙስሊሞች በአመት ሁለት ዒድ ( ባአል አላቸው) እነርሱም ዒደል አድሓና ዒደል ፊጥር ናቸው ። የዘመን አቆጣጠራቸውም የአላህ መልእክተኛ ወደ መዲና ሂጅራ ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ በሂጅሪያ ነው የሚቆጥሩት ። በዚህ አቆጣጠር መሰረት አመቱ አልቆ አዲሱ የሚጀምርበት ወር ሙሐረም ይባላል ። ይሁን እንጂ ይህን የዘመን መለወጫ ቀን እንደ ባአል አያከብሩትም ። እንቁጣጣሽ የሚባለው ግን ከክርስትና እምነት ጋር የተገናኘ ባአል ነው ። ዘመኑንም ዘመነ ዮሐንስ, ማቲዮሰ, ሉቃስና ዻውሎስ ብለው ይሰይሙታል ።‼ ታዲያ ይህንን እንዴት ሙስሊሞች ያከብሩታል ? በጣም የሚገርመው የኢኽዋን መሪዎች አብሮነት በሚል ይህን ባአል የጋራ ለማድረግ ሲታትሩ ይታያል ። አልፎም በዚህና በጥምቀት ባአል ላይ በክብር እንግድነት ሲሳተፉና መግለጫ ሲሰጡም ሊታይ ይችላል ። ይህ የዲናቸውን ክብር ማስነካትና ራሳቸውንም ከማዋረድ ውጪ ጥቅም የለውም ። የሀገረችን ሙስሊም በሱፍይ መሪዎች አማካይነት ታቦት ሲሸኝና ጥምቀት አብሮ እየጨፈረ ሲያከብር ኖራል ። ተራው የኢኽዋን ሆነና በተራቸው ጭራሽ እየሱስ ፍቅር ያስተማረ ጌታ ነው ‼ ብለው አረፉት ። ይህም ለሙስሊሙ ወላእና በራእ የሚለው የዐቂዳ ውድቀት ሰበብ ሆነ ። የአላህ መልእክተኛ ለኡመቴ የምፈራው አጥማሚ መሪዎችን ነው ያሉት ይህ ነው ። ወደ ርእሴ ስመለስ እንቁ – ጣጣሽ እውነትም ብዙ ነው ጣጣሽ እላለሁ ። በመርህ ላይ ያልተመሰረተ ዐቂዳ ሁሌም ኮተት አያጣውም ። ዘመን መለወጫ ሲመጣ ሰዎች ካለፈው አመት ድክመታቸውና ስህተታቸው ታርመው የበለጠ ለመስራት ከመዘጋጀት ይልቅ የህይወታቸውን አቅጣጫ ለመቀየር ወደ መተት ኮተት ያማትራሉ ። በመሆኑም ከምን ጊዜውም በላይ በዚህ የእንቁ–ጣጣሽ ባአል ላይ መተትና ድግምት ይሰራል ጠንቋዮች በጣም ቢዚ ይሆናሉ ። ይህ መተትና ድግምት የእነርሱ ህይወት ሊለውጥ የሌላው ህይወት ማጥፋት አለበት ብለው ነው የሚያስቡት ። በመሆኑም በአብዛኛው የሚሰሩ ድግምትና መተቶች በሰዎች ላይ ይሆናል ። አላህ ከፈቀደው ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ። መጠንቀቁና ሰበብ ማስገኘቱ መልካም ነው ። በዘመን መለወጫው ማለዳ ( ጠዋት) ላይ የተለያዩ ዶሮዎች በተለያየ መንገድ ተገለው በሰዎች መውጫና መግቢያ ላይ ወይም መንገድ ላይ ሊጣሉ ይችላሉ ። በሌላ መልኩ መሬት ተቆፍሮ ሊቀበሩም ይችላሉ ። ሙስሊሞች በተለይ በዚህ ቀን ጠዋትም ሆነ ቀኑ ላይ ከቤታቸው ሲወጡ " ቢስሚላህ ተወከልቱ ዓለላሂ ላ ሐውለ ወላ ቁወተ አልላ ቢላህ " ብለው መውጣት ይኖርባቸዋል ። ለልጆቻቸው ይህን ዚክር ማስተማርና መንገድ ላይ የሚያገኙትን ነገር እንዳይረግጡ ፣ እንዳያነሱና እንዳይጫወቱበት መንገር ይኖርባቸዋል ። ይህን ዚክር አድርገው ሰበብ ካስገኙ በአላህ ይጠበቃሉ ። በእንቁጣጣሽ ጣጣ እንዳይገቡ ይረዳቸዋል ። በመጨረሻም ይህን ኮተት ተሸክሞ የሚመጣውን ዘመን መለወጫ የሁሉም ነው ከማለት መቆጠቡና ይዞት ከሚመጣው ጣጣና ኮተት በአላህ መጠበቅ ያስፈልጋል አላህ ሙስሊሞችን ከሸረኛች ተንኮል ይጠብቅልን ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🎤 የመርከዙ ሰዎች ኢኽዋኖች አይደሉም የሚል ስለ ኢኽዋን የማያውቅ ነው ። ኢኽዋኖች ሰለፍይ የሚለውን መጠሪያ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ቢችሉ ኖሮ የትኛውንም ዋጋ ይከፍሉ ነበር ። በህይወታቸው የማይፈልጉት ነገር ሐዲሱል ኢፍትራቅና ሰለፍይ የሚለው መጠሪያ ነው ። ሐዲሱል ኢፍትራቅ ( " ኢፍተረቀቲል የሁዱ ዐላ ኢሕደ ወሰብዒነ ፊርቀተን ወፍተረቀቲ አንነሷራ ዐላ ስንተይ ወሰብዒነ ፊርቀተን ወሰተፍተሪቁ ኡመቲ ኢላ ሰላሲን ወሰብዒነ ፊርቀተን ኩሉሃ ፊናር ኢላ ዋሒዳህ " ) የሚለው ሲሆን የዚህ ኡማ መከፋፈልን የሚያመለክት ሐዲስ ነው ። በጣም የሚገርመው ኢኽዋኖች ኡማውን የከፋፈለው ይህ ሐዲስ ይመስላቸዋል ። በመሆኑም ሐዲሱን ደዒፍ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ። በዚህም ኡማውን አንድ የሚያደርጉት ይመስላቸዋል ።‼ ልክ እንደዚሁ ሰለፍይ የሚለው መጠሪያም ኡማውን የከፋፈለ ስለሚመስላቸው ይህን መጠሪያ ለማጠልሸትና በሙስሊሞች አእምሮ ላይ እንዲጠላ ለማድረግ ሲዳክሩ ይታያሉ ። በተቃራኒው ደግሞ አዲሶቹ ኢኽዋኖች ( የመርከዙ ሰዎች) ኢኽዋንዮች መሆናቸው እንዳይታወቅና በሰለፍያ ስም ለመነገድ እኛ ነን ሰለፍዮቹ ሌሎቹ ወሰን አላፊዎች ናቸው ይላሉ ። ነገር ግን ስራቸውን ለሚያይና ኢኽዋንን ለሚያውቅ የእነርሱ ኢኽዋንይነት በጣም ግልፅ ነው ። በተለይ በአሁኑ ጊዜ ፕሮግራማቸው ሁሉ ከኢኽዋኖች ጋር ነው ። ከዚህም ሲያልፍ ከአሕባሽና ሱፍይ ጋር ሁሉ አላቸው ። በቋሚነት ከኢኽዋን ጋር የሚሰሩባቸው መስጂዶች :– – ሜዳ መስጂድ ( ኢማሙ አሕመድ መስጂድ ) በተራ ነው ፕሮግራም ያላቸው ። ይህ የሆነው የመርከዙ ሰዎች ከስምምነቱ በኋላ አህሉል ቢዳዓን ማውገዝ በመተዋቸው ነው ። ረድ ፣ ተሕዚር የሚባል ነገር የለም ። ወይም ኢኽዋንይ ፣ ሱፍይ ፣ ተብሊጝይ ማለት በስምምነቱ መሰረት ወንጀል ነው ። የመርከዙ ሰዎች ዘንድ ዶክተር ጀይላን ፣ ሙሐመድ ሓሚዲን ፣ ያሲን ኑሩ ፣ አቡበከር አሕመድ ካሚል ሸምሱና የመሳሰሉ የኽዋን መሪዎች ሰለፍዮች ናቸው ። እነርሱን ሙብተዲዕ ማለት እንደ ከባድ ወንጀል የሚታይ ይመስላል ። ሜዳ መስጂድ የመርከዙ ሰዎች ፕሮግራም ሲኖር የውጭ እስፒከር አይዘጋም ። ምክንያቱም በእነርሱ ላይ በጣም እርግጠኛ ስለሆኑ ። በተቃራኒው ከኢኽዋኖች የሚፈሩዋቸው ለሙሐደራ ከገቡ የውጪ እስፒከር ይዘጋል ። ለምሳሌ ካሚል ሸምሱን የመሰለ ። – ዒባዱራሕማን መስጂድ ይህም በጋራ የሚሰሩበት መስጂድ ነው ። እዚህም ከእንጀራ አባቶቻቸው ጋር ተስማምተው ነው የሚሰሩት ። – ከአሕባሽ ጋር በጋራ የሚሰሩበት መስጂድ ደግሞ የላፍቶ ትልቁ መስጂድ ነው ። ይህ መስጂድ የአሕባሾች መርከዝ መሆኑ ሁሉም ያውቀዋል ። የመርከዙ ሰዎች በእነዚ መስጂዶች ላይ ማስተማራቸው ሳይሆን ችግሩ የተፈቀደላቸው ከነበሩበት አቋም ወደ እነርሱ ስለመጡ ነው ። ይህ ባይሆን ኖሮ ያሲን ኑሩ ሸኽ ሆጀሌ መስጂድ ላይ እንዳለው ሁሉ ለኢብኑ መስዑዶች አድርሱላቸው ይሉ ነበር ። የመርከዙ ሰዎች የጥመት አንጃዎችን ስም እየዘረዘሩ ችግራቸውን በግልፅ ቢያስተምሩ ኖሮ እንኳን እኩል ፕሮግራም ሊሰጣቸው አይደለም እርግማን ነበር ድርሻቸው የሚሆነው ። ይህ አ/አ ላይ ያለው ነው ። ክ/ሀገር ላይ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ የኢኽዋኖች መስጂድ እነርሱ ናቸው ፕሮግራም የሚያደርጉበት ። ምን አይነት ካላችሁ የእንቅልፍ መርፌና ክኒን የሆነ ፕሮግራም ። ለዚህ ማሳያ ደግሞ ብዙ ለፍተው የሱዳን ኢኽዋንዮችን ሰብስበው ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ኡስታዞችንና ዱዓቶችን ሰብስበው የሰጡት የአንድ ሳምንት ኮርስ ነው ። የተመረጡ ኪታቦችን ያየ ሰው የሰዎቹን ሚንሀጅ ምንነት ያውቃል ። የእነዚህ ሰዎች ምሳሌ የዛሬ 18 አመት አካባቢ ዶክተር ጀይላን ከየክፍለሀገሩ መሻኢኾችንና ኢማሞችን ሰብስቦ ኪታቡ ጦሃራና ኪታቡ ኒካሕ እያስተማሩ ከቆዩ በኋላ ሸይኽ ዐ/ከሪም እነዚህ እኮ ኩቱቡ ሲታ የሚያስተምሩ ናቸው ለምን አመጣችዋቸው ሲሉት አላማችን ውስጣቸው ያለውን ( ወሰን አላፊነት ) አውጥተን እኛ ጋር ያለውን ( ለዘብተኝነት ) ለሞምላት እንጂ እነርሱን ለማስተማር አይደለም እንዳለው ነው ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

📖 የኢማሙ አሕመድ ኡሱል አስ-ሱንና ኪታብ ደርስ ክፍል 3 🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አል-ኢትዮጲ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ) 🕌 በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል 🕰 ከጁምዓ እስከ እሁድ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ የሚሰጥ ት/ት የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
نمایش همه...
ኡሱል አስ-ሱንና ክፍል 3.mp313.02 MB
👉 ውልባረግ ላይ የሚነዛው ቅጥፈት በስልጤ ዞን ውልባረግ ወረዳ ቢሎዋንጃ ቀበሌ ላይ አላማቸው ምን እንደሆነ የማይታወቁ አካላት አንድ ልጅ ከሞተ ከሶስት አመት በኋላ መጥቷል ‼ ብለው በሙስሊሞች ታሪክ ተሰምቶ የማይታወቅ ቅጥፈት እያሰራጩ ነው ። የዚህ ቅጥፈት ተዋናይ የሆነ አንድ ወጠምሻ መጀመሪያ ጉዳዩን በሚዲያ ለቆት ውግዘት እንደገጠመውና ከዛም ማረጋገጫ ብሎ ሞቶ የተነሳው ልጅ ዘንድ ሄዶ ልጁን በማሳየት እንዳረጋገጠ ያወራል ። ይህ ወጠምሻ ይህን ቅጥፈት ምናልባት እርጥብ እሳት ( ጫት ) እየበላ ያወጣው እቅድ ሊሆን ይችላል አለያም ከአክፍሮት ሀይላት የተሰጠው ሚሽን ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው ሊሆን የሚችለው ። ምክንያቱም ማረጋገጫ ብሎ የሚያሳየው በቢሎዋንጃ ቀበሌ ውስጥ ባለች ጎጆ ቤት መስኮት ላይ አንድ የአእምሮ ዘገምተኛ የሆነ ታማሚን ነው ።‼ ይህ ልጁ ሞቶ መነሳቱን ሳይሆን የወጠምሻውን ቅጥፈት ነው የሚያረጋግጠው ። ምክንያቱም እንዲህ አይነት በኢስላምና ሙስሊሞች ላይ የተቀጠፈን ትልቅ ውሸት ለማረጋገጥ አንድ የአእምሮ ዘገምተኛን ይህ ነው ብሎ ማሳየቱ በምን ሒሳብ ነው ማረጋገጫ የሚሆነው ? ምናልባት ከሆነም ለአእምሮ ዘገምተኞች ነው የሚሆነው ። ይህ የቅጥፈት ተዋናይ ወጠምሻ በእርጥብ እሳት ሰክሮ ያወጣውን እቅድ ወደ ተግባር ለመቀየር የሰራቸው ስራዎች መኖራቸውን ለመረዳት ነግግሮቹን ማዳመጡ በቂ ነው ። ይህ የቅጥፈት ተዋናይ እቅዱን ካወጣ በኋላ የዘገምተኛውን ቤተሰብ ቀድሞ ማዘጋጀት እንዲሁም ይህን የሚያራግቡ ቡድኖች መፍጠር ለዚህ ድራማ በፀጥታ ሀይሎች መታገዝ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል ። ይህ ወጠምሻ በምርቃና በምናቡ ያየውን እውን ለማድረግ እየቋመጠ ሲያወራ እንዲህ ይላል : – ይህን ጉዳይ በሚዲያ ለቀነው ውግዘት ገጥሞን ነበር አሁን እውነት መሆኑን ለማሳየት በአካል ተገኝተናል ።‼ የጎጆ መስኮት እንዲከፈት ካደረገ በኋላ ይህ ልጅ ነው ብሎ ያስተዋውቃል ። በመቀጠልም ይህ የአላህ ተአምር ነው የፈጣሪ ስራ ነው ይላል ። ይህ ነው ከአክፍሮት ሀይላት የተሰጠው ሚሽን ነው እንድል ያደረገኝ ። ምክንያቱም የሱን ድራማ የአላህ ተአምር ነው ብሎ ሙስሊሞች ለማክፈር ያቀደ ይመስላልና ። ቀጥሎ በአላም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ተአምር ይላል ።‼ አው በሙስሊሙ ዐለም ላይ ተሰምቶ የማይታወቅ ቅጥፈት ነው ። ከዛ በምርቃናው አለም በምናቡ ያየውን የመክበር ስሜት በስሜት ሰክሮ እንዲህ ብሎ ገለፀው : – ይህን ተአምር ለማየት ከስልጤ ዞንና እንዲሁም ከአ/አበባም ህዝብ እየጎረፈ ነው ይላል ።‼ የሚያሳዝነው በምናቡ ያያቸው የመክበሪያ መንገዶችን አለመቻቸም ። ሱቅ አልከፈተም ፣ ሻይቤት የሚከፍት አላዘጋጀም ፣ ለመሸበት የሚያከራየው ትናንሽ ጎጆ አልሰራም ፣ ለሚጎርፈው ህዝብ የሚበቃ ባጃጆችን ታሪፍ አውጥቶ አላሰማራም ። ብዙ ጊዜ ሰዎች ተአምር አለ ሲሉ በዚህ መንገድ ለመክበር አስበው ነው ። ሌላው የአእምሮ ዘገምተኛ የመረጠበት ምክንያት ፈጣንና መናገር የሚችል ቢመርጥ እውነቱን ተናግሮ ሊያዋርደው ስለሚችል ነው ። አንድ የረሳው ነገር አለ እሱም ማረጋገጫ ነው ብዬ ዝም ብዬ ይህን የአእምሮ ዘገምተኛ ሳሳይ ሰው ላያምነኝ ይችላል የሚለውን ነው ። ምን ማድረግ ነበረበት የሚለው ለሱ አይነት ቀጣፊዎች ትምህርት እንዳይሆን ትቼዋለሁ ። ለማንኛውም እኛ ሙስሊሞች ከሞት በኋላ መነሳትን አስመልክቶ መለኮታዊ የህይወት መመሪያ በሆኑት ቁርኣንና ሐዲስ ትልቅ መርህ ተቀምጦልናል ። ይኸውም በሚከተለው የአላህ ቃል እናገኘዋለን : – وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن سُلَالَةٍ مِّن طِينٍ በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው ፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاهُ نُطْفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው ፡፡ ثُمَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ ۚ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን ፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን ፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን ፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው ፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው ፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ ፡፡ ثُمَّ إِنَّكُم بَعْدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ ። ثُمَّ إِنَّكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ تُبْعَثُونَ ከዚያም እናንተ በትንሣኤ ቀን ትቀሰቀሳላችሁ ፡፡ المؤمنون ( 12– 16 ) ከእነዚህ የቁርኣን አንቀፆች የምንረዳው ከነብዩ ኡመት ውስጥ አንድ ሰው ከሞተ በኋላ የሚነሳው የቂያማ ቀን መሆኑን ነው ። የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – የቂያማ ቀን መጀመሪያ መሬት የምትከፈትላቸውና ከቀብር የሚወጡ የመጀመሪያ ሰው መሆናቸውን እንዲህ ብለው ይነግሩናል : – عن أبي سعيد الخدري – رضي الله عنه – قال: قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم – "  أنا سيدُ ولدِ آدمَ ولا فخر وأنا أولُ من تنشقُّ الأرضُ عنه يومَ القيامةِ ولا فخر وأنا أولُ شافعٍ وأولُ مشفَّعٍ ولا فخر ولواءُ الحمدِ بيدي يومَ القيامةِ ولا فخرَ " صححه الألباني كما في صحيح ابن ماجه 🔹 አቡ ሰዒድ አል ኹድርይ ባወሩትና ኢብኑ ማጃህ በዘገቡትና ኢማሙል አልባኒ ባሉት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል : – " እኔ የኣደም ልጆች አለቃ ነኝ ኩራት የለም ። የቂያማ ቀን መጀመሪያ መሬት የምትከፈትለት ነኝ ኩራት የለም ። እኔ የመጀመሪያ ምልጃ ጠያቂና አማላጅ ነኝ ኩራት የለም ። የቂያማ ቀን የምስጋናው ባንዲራ በእጄ ነው ኩራት የለም ። " እነዚህ ከሰባት ሰማይ ከዐርሽ በላይ የመጡ ወሕዮችን ነው እኛ የምናምነው ። እንጂ የአንድ ተራ ወጠምሻ ድራማን አይደለም ። በመጨረሻም እነዚህ አካላት የሙስሊሞችንና የእስልምናን ክብር የነኩና የደፈሩ ስለሆኑ በህግ ሊጠየቁ ይገባል ። በተለይ የስልጤ ዞን የፀጥታ ሀይል እነዚህን አካላት ይዞ ለፍርድ ማቅረብ ህዝባዊ ሀላፊነቱ ነው ። የስልጤ ዞን ሙስሊሞች ባጠቃላይ የውልባረግ ከተማ ሙስሊሞች በተለይ የአክፍሮት ሀይላትን ተልእኮ ለማስፈፀምና ሙስሊሙን ወደ ሽርክ ለመንዳት የሚንቀሳቀሱ አካላትን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ። አላህ ቀጣፊዎችን አዋርዶ ዲኑን የበላይ ያድርገረልን ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

قال الشيخ العلّامة الدكتور ربـيـــع بـن هـــادي الـمـــدخـلـــي -حفظه الله تعالى ورعاه-: « كثير من المنتسبين للمنهج السلفي حينما عاشروا الأحزاب و الطوائف الضالة، ضلوا وتاهوا وأصبحوا من أشد الناس حرباً على أهل السنة ». 📚 المجموع (301/14). وهذا الذي نراه ظاهرا باديا في بلدناالحبشة على المميعة القديمة والجديدة الله المستعان
نمایش همه...
🔷 የአክፍሮት ሀይላት ሴራ በምእራባዊያን ባጀት የሚንቀሳቀሰው የአክፍሮት ሀይላት የማክፈር ዘመቻ በአሁኑ ጊዜ ባለ በሌለ ሀይሉ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ። ለዚህ እንደምክንያት የሚጠቀሰው ስርኣቱ ለእነዚህ አካላት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ነው ። በአሁኑ ጊዜ በዋነኝነት የሚንቀሳቀሱት የሀድያ ታሪክ ስልጤ ዞንና ጉራጌ ዞን ላይ መድገም በሚል መሪ ቃል ነው ።‼ ይህን ቅዠት ወደ ሕልምና ከዛም ወደ እውን ለመቀየር የነደፉት ስልት በመጀመሪያ አሕባሽንና ሱፍያን በመደጎም ወሀብይ የሚሉትን ትክክለኛውን እስልምና ማዳከም ሲሆን ለዚህ ደግሞ ለሁለቱም ባጀት በመመደብ የቀብር አምልኮትን ወልዮችን መውደድ በሚልና ቅርሳቸውን ጠብቆ ታሪካዊ ቦታ ነው በሚል እንዲጎበኙ ( እንዲመለኩ) ማድረግ ናቸው ። የራሳቸውን እምነት ለማስፋፋትና እስልምናን ለመምታት ቁርኣንና ሐዲስ ለሀገራችን አይበጅም ወሀብዮች ያመጡት ነው ብለው እምነቱን ወደ ባህል መቀየር ዋነኛ ትኩረታቸው ነው ። እነዚህ የአክፍሮት ሀይላት ይህን ቅዠታቸውን ለማሳካት ከላይ ከተጠቀሰው እስትራቴጂ ጎን ለጎን በተቻለ መጠን አመራሮችን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ እንዲሆኑ ማድረግ ካልተቻለ እምነታቸውን በማያውቁና ዲናቸውን ልማድ አድርገው በያዙ ግለሰቦችን በማድረግ በእነርሱ መታገዝ ነው ። በዚህም ሙስሊሙን በሙስሊም እየመቱ እነርሱ እምነታቸውን ሊያስፋፉ ቀና ደፋ እያሉ ነው ።‼ እኛ ሙስሊሞች በተለይ ወደ ተውሒድ ተጣሪዎች በአሁኑ ሳአት ኢኽዋንና ሙመዪዓ ዲኑን ልክ ሞቶ የሱ ፎቶ ግድግዳ ላይ እንደተሰቀለ የታሪክ ሰው ትተውት በፖለቲካና ራስን ማበልፀግ በሚል መሪ ቃል እንቅልፍ አጥተው ሲሯሯጡ ሀላፊነታች መወጣት ካልቻልን አላህ ፊት መልስ የለንም ። የአክፍሮት ሀይላት ታርጌት ያደረጉት ድንጋይና ጉቶን አይደለም ቀብር እያመለኩ ያሉ የኔና የናንተ ቤተሰቦችን ነው ። ቤተሰቦቻችን ቀብር ማምለክ ኩፍር መሆኑን በመግለፅ ነብዩና ሶሐቦች ዋጋ የከፈሉለት አላህ በብቸኝነት እንዲመለክ እንጂ ለቀብር አምልኮ አለመሆኑን አስረድተን ካሉበት የኩፍር ተግባር ካላወጣናቸው ጉዳዩ ከባድ ነው ። ጠላት ለሊት ቤተሰቦችህን ለማክፈር የቤትህን ግድግዳ ከውጭ በኩል ከስር ሲምስ አንተ ከተኛህ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አስበው ። ዛሬ እነዚህ አካላት ለቤተሰቦችህ ኒቃብ የኛ ባህል አይደለም ። ሱሪ ማሳጠር የኛ ባህል አይደለም ። ፂም ማሳደግ የኛ ባህል አይደለም ብለው በባህል ስም ኢስላምን የሚያጠፋ መርዝ ሲግቱዋቸው ለእስልምና አስበው ወይም ለአብሮነት አስበው እንዳይመስልህ ። ዲንህን ለመናድ ጉድጓድ ሲምሱ ነው ። በመሆኑ እየአንዳንዱ የአላህ ዲን ላኢላሀ ኢልለላህ የበላይ እንዲሆን የሚፈልግ የቤተሰቦቼ ዲን ያሳስበኛል የሚልና ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስብ ዛሬ ከቤተሰቦቹ ይጀምር ። በመልካም ስነምግባር ቤተሰቦቹን ከቀብር አምልኮ ያውጣ ። ህፃናት ትክክለኛው እስልምና በቁርኣንና ሐዲስ መረጃነት ያስተምር ። አንተ ልጆችህ ቀርኣንና ሐዲስ እንዳይማሩ ልጆች ናቸው ትላለህ ምእራባዊያን ለህፃናት ግብረሶዶማዊነትና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ከዚህ በላይ ፆታ ስለመቀየር ያስተምራሉ ። ‼ ተመልከት እስልምናን ለማዳከም ባንተ አእምሮ ላይ ምን እንደተሰራ ። አንተ ለእስልምና የሰጠኸውን ቦታ ማየትህ ለአክፍሮት ሀይላት ሁኔታዎችን እያመቻቸህ መሆኑን ለማቅህ በቂ ነው ። አንተ የተውሒድ ባንዲራ የያዝከው ዳዒ ሆይ ባንዲራውን ምን ያክል ከፍ አድርገኸዋል ? ጥሪህ እነማን ጋር ደርሷል ? የት ምን ሰርቷል ? ማንን ከቀብር አምልኮ አውጥቷል ? በጉዞህስ የት ደርሰሀል ወይስ ደክሞህ ቆመሀል ? የተውሒድ ጠላት ሰራዊት አልደከመውም ። ሀይልም አላነሰውም ። ማኔጅ የሚያደርግም አላጣም ። የተውሒድን ከተማ ወሮ ህዝቦቹን ጨርሶ ከተማዋን ለማፍረስ እየገሰገሰ ነው ። የሚገርመው ግን ተውሒድ ሰራዊቶቹ ቢደክሙም ራሱ ሀይል አለው የጠላትን ሰራዊት የሚማርክበት በቁጥጥሩ ስር የሚያደርግበት መለኮታዊ ስውር አቅም አለው ። ለዚህ ነው የተውሒድ ጠላቶች ለዘመናት እቅድ አውጥተው ይህ ነው የማይባል ባጀት መድበው ሰራዊት አሰማርተው አመራር እየሰጡ ልፋታቸው ከንቱ የሚሆነው ። አንተ ግን ለራስህ ስትል ተንቀሳቀስ የክብሩ ከፍታ ለራስህ ነው ። ካልሆነም የውርደቱ ቁልቁልም አንገትህን አስደፍቶ እንድታይ ያደርገሀል ። በመጨረሻም የተውሒድ ሚስጢራዊ ተአምር በአንድ የአክፍሮት ሀይላት ክስረት ባሳየ ክስተት ላሳያችሁ ። ክስተቱ ኢንዶኔዢያ ላይ ነው ። የአክፍሮት ሀይላት ለ20 አመት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ቀንና ማታ በማክፈር ስራ ላይ ተጠምደው ኖሩ ። ከሀያ አመት በኋላ 90% የሚሆነው የኢንዶኔዢያ ህዝብ ከፈረ ። የአክፍሮት ሀይላትም የቤት ስራቸውን ስለጨረሱ ሊወጡ ሽር ጉድ ማለት ጀመሩ ። የ20 አመት የስራ ውጤትታቸውን ሪፖርት ለማቅረብና ሽልማት ለሚገባቸው ለመሸለም የመዝጊያ ፕሮግራም አዘጋጁ ። በፕሮግራማቸው ማጠቃለያ ላይ ለተሰበሰበው ህብረተሰብ ያዘጋጁት የገንዘብ ስጦታ ነበርና ሰጡ ። መጨረሻ ላይ ህብረተሰቡ እነርሱን አወድሶ የሚሰራበትን ነገር እንዲነግራቸው ብለው በዚህ ገንዘብ ምንድነው የምታደርጉበት ብለው ጠየቁ በእውናቸው ሳይሆን በህልማቸውም ያለሰቡትና ኪሳራቸውን የሚያረጋግጥ መልስ አገኙ ። ህዝቡም በአንድ ድምፅ ሐጅ ነው የምናደርግበት አላቸው ። !!!!!!! አላህ ባጢልን አዋርዶ ሐቅን የበላይ ያድርግልን ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

📖 የኢማሙ አሕመድ ኡሱል አስ-ሱንና ኪታብ ደርስ ክፍል 2 🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አል-ኢትዮጲ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ) 🕌 በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል 🕰 ከጁምዓ እስከ እሁድ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ የሚሰጥ ት/ት የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
نمایش همه...
ኡሱል አስ-ሱንና ክፍል 2.mp312.79 MB
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.