cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ምክር ለወዳጅ @

@yandebet_mikr @yandebet_mikr @yandebet_mikr @yandebet_mikr እግዛብሄር ለሁሉም ጥያቄ መልስ አለው ። @e7968nig #join #share #share @yandebet_mikr @yandebet_mikr @yandebet_mikr

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
198
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

+ በአምልኮት ስግደት ዙሪያ ጥርት ያለ መረጃ + ከአራቱ የስግደት አይነቶች ውስጥ ቀዳሚው የሆነው የአምልኮት ስግደት፤ እግዚአብሔርን አመልካለው የሚል ሰው ሁሉ ሊሰግደው የሚገባው ስግደት ነው፡፡ ይሄ ስግደት፤ ለልዑል እግዚአብሔር ብቻና ብቻ የሚቀርብ ሲሆን፤ በሰማይም በምድርም ያሉ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ፍጥረታት ሁሉ ይሰግዱት ዘንድ የተገባ እጅግ አስደናቂ ስግደት ነው፡፡ "በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥ ለአንተም ይዘምራሉ፥ ለስምህም ይዘምራሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 66፥4) የአምልኮት ስግደት የሰማይ መላእክትና ቅዱሳን ሁሉ ሳያቋርጡ በመስገድ አምልኮትን የሚገልጹበት ሰማያዊ ስግደት ነው፡፡ የቅዱሳንን መልክአ ጸሎት ብትመለከቱ፤ ቅዱሳኑ ለእግዚአብሔር እንደሚሰግዱ በግልጽ ይናገራል፡፡ ለምሳሌ እንመልከት፥ ➊• ፳፪. ለአቁያጺከ። ገብርኤል ሆይ፤ በሰማያዊ አምላክ ፊት ዘወትር ተንበርክከው ለሚሰግዱ ጉልበቶችህና አቁያጾችህ ሰላም እላለሁ። (መልክአ ገብርኤል) ➋• ፳፩. ለአብራኪከ። ሩፋኤል ሆይ፤ ለሰግደት ለአስተብርኮ ለተፈጠሩ ጉልበቶችህ ሰላም እላለሁ። (መልክአ ሩፋኤል) ➌• ፲፯፤ ለአቍያጺከ። ዑራኤል ሆይ፤ በአንድነቱና በሦስትነቱ ለሚሰገድለት አምላክ ስግደትና ለሚያስቀድሙ ለሁለቱ አብራኮችህና እሳታውያን አቍያጾችህ ሰላም እላለሁ። (መልክአ ዑራኤል) ➍• ፵፩፤ ለአብራኪከ፡፡ ተክለ ሃይማት ሆይ፤ ከላይ ከሰማይ ለወረደው እግዚአብሔር አምላክ ስግደትን ለአዘወተሩ አብራኮችህ ሰላም እላለሁ፡፡ (መልክአ ተክለሃይማኖት) ➎• ፴፩፤ ለአቍያጺከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ለመቅደስ ሰውነትህ ዓምድ ለሆነው አቍያጽህና ስግደት የዘወትር ግብራቸው ለሆነ አብራኮችህ ሰላም እላለሁ፡፡ (መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ) ➏• ፴፩፤ ለአብራክኪ፡፡ እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ሆይ፤ በስግደትና በማማለድ ጊዜ ከእግሮችሽ ጋር ለሚተባበሩ አብራኮችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ (መልክአ ኪዳነ ምሕረት) ➐• ፴፰፤ ለአብራኪክሙ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ የፍጥረታትን ሁሉ አብራክ ለሚያሰገድ አብራካችሁ ሰላምታ ይገባል። (መልክአ ሥላሴ) ከላይ የተዘረዘሩት ስድስቱ እንዲሁ ለምሳሌ የቀረቡ እንጂ፤ በጠቅላላ የቅዱሳንን መልክአ ጸሎት ብትመለከቱ፥ መልክአ አብራካቸውን(ጉልበታቸውን) በሚያመሰግንበት ክፍል ላይ ለእግዚአብሔር እንደሚሰግዱ ይናገራል፡፡ ለእግዚአብሔር ብቻ መስገድ ደግሞ የአምልኮት ስግደት ይባላል፡፡ የመጨረሻው ምሳሌ መልክአ ሥላሴም፤ ፍጥረታት #ሁሉ ለእግዚአብሔር እንደሚሰግዱ ያስረግጣል፡፡ የአምልኮት ስግደት እጅግ እጅግ ኃያል የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ሁሉም ፍጡራን በአንድነት የሚገዙበት መለኮታዊ ኃይልን የሚስብ ስግደት በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ስግደት የማይሰግድ ማንኛውም፥ በየትኛውም ሃይማኖታዊ ማዕረግ ያለ ክርስቲያን እግዚአብሔርን አያመልክም፡፡ የክርስቲያኖች እናት ድንግል ማርያም በአርያም ዘወትር የምትሰግደውን ስግደት ሳይሰግድ ክርስቲያን ነኝ የሚል ሰው ሁሉ ከአንደበት የዘለለ ክርስትና የለውም፡፡ ይህንን ስግደት መቼውኑ በፍቃዳቸው የማይሰግዱ ብቸኛ ፍጡራን ርኩሳን መናፍስት ናቸው፡፡ ምክንያቱም መጀመሪያውኑ እግዚአብሔርን አናመልክም ብለው የካዱ ፍጡራን ስለሆኑ፤ በምንም ፈቃደኝነት የማመልኪያውን ስግደት አይሰግዱም፡፡ አንተም ዛሬ ይህን ስግደት በአንድም በሌላም ምክንያት የማትሰግደው ይህ የዲያብሎስ መንፈስ ልብህ ውስጥ፣ ጊዜህ ውስጥ፣ ኑሮ ውስጥ ስላለ ነው፡፡ ለአንድ ሳምንት የአምልኮት ስግደትን በቤትህ ጸሎት ስፍራ ላይ በእምነት ኃይል ጠዋትና ማታ ስገድ፡፡ ተመሳስሎህ የኖረው አጥፊ መንፈስ ስለመኖሩ በአጭር ቀናት ውስጥ ምልክት ታገኛለህ፡፡ እስከ አሁን ይሄን ስግደት መስገድ ጀምሮ፤ በባሕሪይው ውስጥ አድፍጦ የመሸገበትን ጠላት ያላወቀ ሰው እኔ በበኩሌ አንድስ እንኳ አልገጠመኝም፡፡ + የአምልኮት ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገደው? + የአምልኮት ስግደት ለእግዚአብሔር አምላክ የሚሰግድ ስግደት ነውና፤ በስግደቱ ጊዜ ላይ የሚጠሩትም ቃላት ይህንን የእግዚአብሔርን አምላክነት የሚያሳዩ መሆን አለባቸው፡፡ "ይቅር በለኝ፥ ማረኝ" እየተባለ የሚሰገደው ስግደት የንስሐ ነው፡፡ የአምልኮት ስግደት "ለአብ እሰግዳለው፥ ለወልድ እሰግዳለው፥ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለው" የሚሉ የማምለኪያ ቃላትን ይይዛል፡፡ እስከዛሬ ድረስ ይህን ስግደት ሰግዳችሁ ለማታውቁ ሁላችሁ፣ ይህንን ከበታች ያለውን 28 ስግደት ጠዋትና ማታ ያለማቋረጥ ከመስገድ ጀምሩ፡፡ ✝ 28 የአምልኮት ስግደት ✝ ለአብ እሰግዳለሁ ለወልድ እሰግዳለሁ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ ምስጋና ይሁን ለአብ ምስጋና ይሁን ለወልድ ምስጋና ይሁን ለመንፈስ ቅዱስ ሃሌሉያ ለአብ ሃሌሉያ ለወልድ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ በረከቱን ለሰጠን ኃይሉን ላበዛልን በዚህ ሰዓት ላቆመን በቸርነቱ መንገድ ለመራን በዚህ ሰዓት በጸጋው ለጠበቀን በብርሃኑ መንገድ ለመራን ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ቅዱስ ኤልሻዳይ ቅዱስ አዶናይ ቅዱስ ያሕዌ ቅዱስ ጸባኦት ቅዱስ ኢየሱስ ቅዱስ ክርስቶስ ቅዱስ አማኑኤል የድንግል ማርያም ልጅ ክብር ምስጋና ይግባው ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ ይሄ አዲስ ገና መስገድ ለጀመሩ የሚሆን የአምልኮት ስግደት ነው፡፡ ይህን ሰግደት በየጊዜው እያሳደጉ መሄድ አስፈላጊ ነው፡፡ ከ28 ወደ 41 ከዛ 64 ከዛ እያለ ብዙ የመስገድ አቅምን መጨመር ያስፈልጋል፡፡ ስግደት በጨመርን ቁጥር የሚሰጠው ኃይልም ይጨምራል፡፡ ስግደት በጨመርን ቁጥር የመናፍስት መድከምም ይጨምራል፡፡ ስግደት በጨመርን ቁጥር ወደ እምነት መንገድ የምናደርገውም ጉዞ ይጨምራል፡፡ + የአምልኮት ስግደት የሚሰጠው ጥቅሞች ምንድነው? + ሰዎች ስንባል ራስ ወዳዶች ነን፡፡ ለእግዚአብሔር መስገድ የበለጠ የሚያጓጓን ጥቅም እንዳለው ስናውቅ ነው፡፡ ርኩሳን መናፍስትን እንደምናሸንፍበት ስንማር ነው፡፡ እንጂ ፍቅሩ አሸንፎን፣ አባትነቱን ለማክበር፣ አምላክነቱን ለማግነን፣ ቸርነቱን ለማድነቅ፣ ምስጋናን ለመሠዋት፣ የዋህነቱን ለማሰብ ከልብ ለእርሱ ተገዝተን አንሰግድለትም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔርን ቁስ ነገርን በምንውድበት የተግባር ፍቅር ልክ እንኳን አንወደውም፡፡ ይሄንን ሁላችንም በውስጣችን እናውቃለን፡፡ እርሱ ግን ፍቅር ነውና፥ ብንወድውም ባንወደውም በአምልኮት ስግደት በኩል ሊያካፍለን የሚፈልጋቸው መፍቅደ ስጦታዎቹ እነዚህ ናቸው፡፡ 1. ሰላም 2. ኃይል 3. ደስታ 4. በረከት 5. ጸጋ 6. እረፍት 7. እፎይታ 8. የዲያቢሎስ መንፈስ ስለማድፈጡ የሚሰጥ ምልክት 8. ከምልክቱ በኋላ ዲያቢሎስን የመጣያ ጉልበት 9. የማስተዋል አቅም 10. የእግዚአብሔርን ቃል የማገናዘቢያ ልቦና መከፈት + የአምልኮት ስግደት መቼ መቼ ይሰገዳል? + አስቀድሞ የተመለከትነው መልክአ ገብርኤል ይህንን መቼ መቼ መልስ ይሰጣል እንዲህ በማለት፤ "ገብርኤል ሆይ፤ በሰማያዊ አምላክ ፊት #ዘወትር ተንበርክከው ለሚሰግዱ ጉልበቶችህና አቁያጾችህ ሰላም እላለሁ፡፡" ቅዱስ ገብርኤል የአምልኮትን ስግደት ዘወትር ሳያቋርጥ እንደሚሰግድ መልክአው ይናገራል፡፡ የሌሎቹም እንዲሁ፡፡ ይህ ግልጽ ቋንቋ የሚነግረን የአምልኮት ስግደት በሰባቱም ቀናት ከዓመት እስከ ዓመት የሚሰገድ ስግደት መሆኑን ነው፡፡ የአምልኮት ስግደት ለአንድም ቀን አይቋረጥም፡፡ ለአንድም!
نمایش همه...
#ስምና_ትርጉኖቻቸው 1መልከጼዴቅ =#የፅድቅ ንጉስ 2ኑሀሚን =#ደስታ 3ምናሴ =#ማስረሻ 4ዮሴፍ =ይጨመርልኝ ,ይደገመኝ 5ሰሎሞን =#ሰላማዊ 6መክብብ =#ሰባኪ 7ኢሳይያስ =እግዚአብሔር ፈራጅ ነው 8ኤርሚያስ =እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል 9ሕዝቅኤል =ብርታትን ይሰጣል 10ዳንኤል =#ዳኛ ነው 11ሚክያስ =የሚመስለው ማን ነው 12ሶፎንያስ =#ከለላ ነው 13ኢዩኤል =#አምላክ ነው 14ዘካርያስ =(ያስታውሳል 15ሚልክያስ =#መልዕተኛ 16ዮናስ =#ርግብ 17ናሆም =#መፅናናት 18እንባቆም =#ማቀፍ 19ሀጌ =#የኔ ደስታ 20ማቴዎስ =#ስጦታ 21ማርቆስ =ካህን ,ልዑክ 22ሉቃስ =#ብርሀን 23ዮሐንስ =#ፍስሀወሀሴት 24ያሬድ =ርደት, መውረድ 25በርተሎሜዎስ =አትክልተኛ 26ሕርያቆስ =ረቂቅ ብርሀን 27እስጢፋኖስ =#ፋኖስ 28ባስልዮስ =#መዕቶት 29ማትያስ =#ምትክ 30ዳዊት =#ብላቴና 31ጴጥሮስ =#ዐለት 32 ያዕቆብ =ተረከዝ ያዥ 33 ኢያሱ =#መድሀኒት 34ይሁዳ =#ታማኝ 35አርዮስ =#ፀሀይ 36ሙሴ =#የዋህ 37አብርሀም =የብዙዎች አባት 38ሳሙኤል =ፀሎቴን ሰማኝ 39ኢዮብ =#አበባ 40ሲራክ =#ፀሀፊ 41ጳውሎስ =ምርጥ ዕቃ 42ኢየሱስ =(መድሀኒት 43 ክርስቶስ =#ንጉስ 44 ኤልሻዳይ =ሁሉን ቻይ 45. ዮሐንስ = የእግዚአብሔር ፀጋ (ሀሴት፣ ፍስሀ) 45. ዳንኤል = እግዚአብሔር ፈራጅ ነው 46. ኤልሳዕ =እግዚአብሔር ደህንነት 47. አሞን =#የወገኔ ልጅ 48. እስራኤል =የእግዚአብሔር ህዝቦች 49 ማርያም = የእግዚአብሔር ስጦታ 50. ሀና =#ፀጋ 51. ሩሀማ =ምህረት የሚገባት 52. ኢ ያሱ =እግዚአብሔር አዳኝ ነው፣ መድሃኒት 53. ጌርሳም=ከሌላ ምድር ስደተኛ ነኝ 54. እዮሳፍጥ=እግዚአብሔር ፈርዷል 55. እዮአም =#አዳኝ 56. ኢዮሲያስ= ከፍ ከፍ አለ 57. ኤልሳቤጥ= እግዚአብሔር መሀላዬ ነው 58. አብርሃም = የብዙሃን አባት 59. ኢሊዲያ ( ይድድያ ) = በእግዚአብሔር የተወደደ 60. ኤዶንያስ =እግዚአብሔር ጌታዬ ነው 61. ኦዶኒራም= ጌታየ ከፍ ያለ ነው አለ 62. ሆሴዕ= እግዚአብሔር መድኃኒት ነው 62. ሕ ዝቅያዝ = እግዚአብሔር ሀይሌ ነው 63. ጴጥሮስ=# መሰረት 64. ሴት =#ምትክ 65. ሳሙኤል =እግዚአብሔርን ለምኜዋለው 66. አቤል =የህይወት እስትንፋስ 67. ጎዶሊያስ =እግዚአብሔር ታላቅ ነው 68. ስጥና =# ተዘጋ 69. ማቴዎስ =#ሞገስ 70. ፌቨን=# የእግዚአብሔር አገልጋይ 71. ሚኪያስ =እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ 72 ይሁዳ= አማኝ ( የአማኝ ልጅ) 73. ወንጌል = የምስራች 74. ኤርሚያስ=እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደርጋል 75. ህዝቅኤል = እግዚአብሔር ብርታት ይሰጣል 76. ማራናታ= እግዚአብሔር ቶሎ ና 77.ሆሴዕ =እግዚአብሔር ያድናል 78. አሞፅ =#ሀይል 79. ኤሴቅ =#የተጣላሁብሽ 80. ሚኪያስ =እግዚአብሔር የሚመስል ማን ነው 81. ኢ ዮኤል=እግዚአብሔር አምላክነው 82. አብድዩ=የእግዚአብሔር አገልጋይ 83. ዮናስ =#ርግብ ( የዋህ፣እሩሩህ ) 84.እምባቆም = እቅፍ 85. ሶፎኒያስ =እግዚአብሔር ጠብቋል 86.ሀጌ=በሀላዊ ወይም በበዓል የተወለደ 87. ዘካርያስ =እግዚአብሔር ያስታውሳል 88. ሚልክያስ ፡- መልክተኛዬ 89. ናታኔም ፡ - የእግዚአብሔር ጠራጊ 90. አቤኔዘር ፡ - እግዚአብሔር እረድቶኛል 1. ~ሆሴዕ - እግዚአብሔር ያድናል 2. ~ሐና - ጸጋ 3. ~ሔዋን - የሕያዋን ሁሉ እናት 4. ~ሕዝቅኤል- እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል 5. ~ሕዝቅያስ - እግዚአብሔር ኃይል ነው 6. ~መልከ ጼዴቅ - የጽድቅ ንጉሥ 7. ~ሚልክያስ - መልእክተኛየ 8. ~ሚክያስ - እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው 9. ~ምናሴ - ማስረሻ 10. ~ሣራ - ልዕልት 11. ~ሩሐማ - ምህረት 12. ~ሮቤል - እነሆ ወንድ ልጅ 13. ~ሰሎሞን - ሰላማዊ 14. ~ሳሙኤል - አምላካዊ ስም (የአምላክ ስም) 15. ~ሳኦል - ከእግዚአብሔር የተለመነ 16. ~ሴዴቅያስ - የእግዚአብሔር ጽድቅ 17. ~ሶፎንያስ - እግዚአብሔር ሰውሯል 18. ~ቃዴስ - ቅዱስ 19. ~በርተለሜዎሰ - የተለሜዎስ ልጅ 20. ~በንያስ - እግዚአብሔር አዳነኝ 21. ~ባሮክ - ቡሩክ 22.~ ቤተልሔም - የእንጀራ ቤት 23. ~ቤተል - የእግዚአብሔር ቤት 24. ~ብንያም - የቀኝ እጄ ልጅ (የደቡብ ልጅ) 25. ~ቶማስ - መንታ 26. ~ናሆም - መጽናናት 27. ~ናታን - እግዚአብሔር ሰጥቷል 28. ~ንፍታሌም - የሚታገል 29. ~አልዓዛር - እግዚአብሔር ረድቷል 30. ~አማኑኤል - እግዚአብሔር ከእኛጋር 31. ~አርኤል - የእግዚአብሔር ምድጃ 32. ~አሴር - ደስተኛ 33. ~አስቴር - ኮኮብ 34. ~አብርሃም - ታላቅ አባት (የብዙዎች አባት) 35. አቤሴሎም - አባቴ ሰላም ነው 36. ~አቡ - አባት 37. ~አብዱዩ - የእግዚአብሔር አገልጋይ 38.~ አቢያ - እግዚአብሔር ወንድሜ ነው 39. ~ኢሳይያስ - እግዚአብሔር ደህንነት ነው 40. ~አቤኔዘር— እግዚአብሔር እረድቶኛል 41.~ ኢዩኤል - እግዚአብሔር አምላክ ነው 42. ~ኢያሱ - እግዚአብሔር አዳኝ ነው 43. ~ኢይዝራኤል - እግዚአብሔር ይዘራል 44.~ ኢዩሣፍጥ - እግዚአብሔር ፈርዷል 45. ~ኢዩራም - እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ 46. ~ኢዩርብአም - ሕዝቡ እየበዛ ሄደ 47. ~ኢዮስያስ - እግዚአብሔር ይደግፋል 48.~ ኢዮአስ - እግዚአብሔር ሰጥቷል 49.~ ኢያቄም - እግዚአብሔር አቆመ 50. ~ኢዮአብ - እግዚአብሔር አባቴ ነው 51.~ ኢዮአታም - እግዚአብሔር ፍጹም ነው 52. ~ኢዮአካዝ - እግዚአብሔር ይዟል 53. ~ኤሊዔዘር - እግዚአብሔር ረዳቴ ነው 54.~ ኤልሳዕ - እግዚአብሔር ደህንነት ነው 55.~ ኤልያቄም - እግዚአብሔር ያስነሳል 56. ~ኤርምያስ - እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል 57. ~እስማኤል - እግዚአብሔር ይሰማል 58. ~ኬልቅያስ - እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ነው 59. ~ኤድን - ደስታ 60. ~ኬብሮን - ኅብረት 61.~ ዘካርያስ - እግዚአብሔር ያስታውሳል 62. ~ይሳኮር - ዋጋየ 63. ~ይዲድያ - በእግዚአብሔር የተወደደ 64. ~ዮሐናን - እግዚአብሔር ጸጋ ሰጭ ነው 65. ~ዮናስ - ርግብ (የዋህ) 66. ~ዮናታን - እግዚአብሔር ሰጥቷል 67. ~ዮአኪን - እግዚአብሔር ያቆማል 68.~ የካብድ - እግዚአብሔር ክብር ነው 69. ~ዮዳሄ - እግዚአብሔር ያውቃል 70. ~ዮፍታሔ - እግዚአብሔር ይከፍታል 71. ~ጋድ - መልካም ዕድል 72.~ ጎዶልያስ - እግዚአብሔር ታላቅ ነው ©ምንጭ:- @gbw_dan
نمایش همه...
📎ይሄ መፅሃፍ በውስጡ እስከ 10000 የሚደርሱ የጠቅላላ እውቀት 📘📗ጥያቄዎች በእንግሊዘኛ ከነ መልሱ ይዟል፡፡ ያንብቡ! እውቀቶን ያዳብሩ! ማጋራት አይዘንጋ! @ETHIO_PDF_BOOKS @ETHIO_PDF_BOOKS @ETHIO_PDF_BOOKS
نمایش همه...
ፍትሐ ነገሥትን ዳግም ወደ ተግባር ስለመመለስ (መጽሐፋ በተመረቀበት ቀን የቀረበ) በመምህር ዲ_ን ዮርዳኖስ አበበ ሁሉም ያልፋል: ለመቀላቀል 👇👇👇 🇪🇹https://t.me/sibketOrthodox 🇪🇹https://t.me/sibketOrthodox 🇪🇹https://t.me/sibketOrthodox
نمایش همه...
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀 በጣም የሚዋደዱ ባለትዳሮች ነበሩ። በፍቅራቸውም ሆነ በታማኝነታቸው ተወዳዳሪ አልነበራቸውም!! በአጋጣሚ ከእለታት እንድ ቀን ሰይጣን ከመሀላቸው በመግባት ፍቅራቸውን እንዳልነበር አድርጎ አጣላቸው። አቶ ባል~ንዴት በተሞላ ቃላት "የኔ እህት ትሰሚያለሽ? ጧት ሲነጋ እዚህ ቤት እንዳላገኝሽ የምትፈልጊውንና የምትወጂውን ዕቅ በመያዝ ከቤቴ ውልቅ እንድትይ አሳስብሻለሁ። ሁለተኛ ዓይንሽን ማየት አልፍልግም!! " ወይዘሮ ሚስት ~"እንዴት የኔ እህት እባላለሁ ሚስትነቱ ቀርቶብኝ" ብላ ኡኡታዋን አቀለጠችው። ሆኖም ግን ወደ ወላጆችዋ ቤት እንድትሄድ የፈቀደላት ንጋት ስለነበር ምሽቱን ቤቷ በመቀመጥ አሳለፈችው። አቶ ባል ከተኛ የማይነቃ ሰው ነበርና መኝታ ክፍል በመግባት እንቅልፉን ላሽ ብሏል። የሚገርመው ከእንቅልፉ ጧት ሲነቃ እሱነቱን ያገኘው ከሚስቱ ቤተሰቦች ጋር ነበር። እሱም በመደንገጥ ይህን ሲል ጠየቃት "የተኛሁት ከቤቴ ነበር። ለመሆኑ ማነው እዚህ ያመጣኝ ?" ሚስትም አለች " ሲነጋልሽ የምትውጂውንና የምትፈልጊውን እቃ ይዘሽ ውጭ አልከኝ። እኔ ደግሞ የምፈልገውና የምወደው አንተን ስለሆነ እንቅልፍ ከተኛህበት አንስቼ በመሸከም ወደ ቤተሰቦቼ ቤት ይዠህ መጣሁ" ስትል መለሰችለት። ባል "በመገረምም በመደሰትም የኔ ፍቅር ማታ የተናገርኩት ተናድጄ ነው ይቅርታ አድርጊልኝ ብሎ የኔ ባትሄኚ እንዴት ይቆጨኝ ነበር በማለት ግንባሯን ሳማት።☹️ በሉ ሰላም እደሩልኝ😒 🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
نمایش همه...
+ የጴጥሮስ ጥላ + አንድ አባት በተመስጦ ሆኖ እየጸለየ ነው:: ድንገት ሌላ አባት መጣና በቁጣ ጸሎቱን አስቆመው:: "አንተ ደፋር እንዴት ወደ ፀሐይ መውጫ (ምሥራቅ) ሳትዞር ትጸልያለህ?" አለው ያ አባት መለሰ "አንተ ፀሐይህን ፈልግ:: የኔ ፀሐይ ክርስቶስ መውጫ መግቢያ የለውም":: በእውነትም ክርስቶስ በነቢዩ ሚልክያስ እንደተነገረለት ለሚፈሩት የሚወጣ እውነተኛ ፀሐይ ነው:: ወደ ፀሐይ ዞረን ስንጸልይም አባ ጊዮርጊስ እንዳለው ወደ ፀሐይ ሳይሆን ፀሐይን ወደሚያወጣው እንጸልያለን:: (አኮ ዘንጼሊ በቅድመ ፀሐይ አላ ለዘያሠርቆ ለፀሐይ") ክርስቶስ ፀሐይ ነው:: አናት የሚበሳ ኃይል የሚያደክም ለሕመም የሚዳርግ ሳይሆን ኃይል ፈውስ የሚሠጥ ፀሐይ ነው:: ቅዱስ ጴጥሮስ በሐዋርያት ሥራ እንደተጻፈልን ሕሙማንን በጥላው ይፈውስ ነበር:: በዚህ ምክንያት በሽተኞችን በሚያልፍበት መንገድ አሰልፈው ጥላውን ብቻ እንዲያሳርፍ ያደርጉ ነበር:: የሰው ጥላ ጥሩ አይደለም ለበሽታ ይዳርጋል በሚል ማኅበረሰብ ውስጥ ሆነን ይህን ስንሰማ ምን እንል ይሆን? የጴጥሮስ ጥላ ግን ይፈውስ ነበር:: ሐዋ. 5:15 የጴጥሮስ ጥላ ምን የተለየ ነገር አለው? ምንም የለውም:: እንዲያውም በአሣ አጥማጅነቱ ጊዜ ከወንድሞቹ ጋር በቀን ዓሣ ሲያጠምዱ ጥላቸው በውኃው ላይ አርፎ አሣ እንዳያሸሽባቸው በሌሊት ማጥመድ ይመርጡ ነበር:: አሁን ግን ዓሣ የሚያሸሸው የጴጥሮስ ጥላ መድኃኒት ሆኖ ከዓሣ አልፎ ምእመናን ማጥመድ ጀመረ:: የጴጥሮስ ጥላ ከቀድሞው ጥላው በምንም አይለይም:: ያንን ሁሉ በሽተኛ መፈወስ የቻለው ጥላው ተቀይሮ ሳይሆን ያረፈበት ፀሐይ ተቀይሮ ነው:: ፈዋሹ ጥላ የተፈጠረው እውነተኛው ፀሐይ ክርስቶስ በጴጥሮስ ላይ ስላረፈ ነው:: እውነተኛው ፀሐይ በእኛ ላይ ሲያርፍ እኛ ተፈውሰን ሌላ እንፈውሳለን:: የእርሱ ብርሃንና ሙቀት ሲያርፍብህ የኃጢአት ቆፈን ቀስ በቀስ ይለቅህና ትፍታታለህ:: ከዚያም ሐሙስ ማታ ብርድ ፈርተህ እሳት ለመሞቅ ሦስቴ የካድከውን ፀሐይ ስትሞቀው ሦስት ሺህ ሰው ፊት ትመሰክርለታለህ:: እሱን ሞቀህ በጥላህ ደግሞ ለሌሎች ትተርፋለህ:: ክርስቶስ እንዴት ያለ ፀሐይ ነው? ፀሐይን ያጨለመ ፀሐይ! ፈረቃ የማያውቅ ፀሐይ! ፀሐይ ራስዋ የምትሞቀው ፀሐይ እርሱ ክርስቶስ ነው:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሰኔ 10 2012 ዓ ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
نمایش همه...
🌀" ሁሉም ሰው በሌላው ሰው አይን ስህተት ሊሆን ይችላል ። በራሱ አይን ግን ሁሉም ሰው ልክ ነው ። አንድን ነገር ስለተቃወምነው ስህተት ነው ማለት አይደለም ። ስለደገፍነውም ትክክል ነው ማለት አንችልም ። በስሜት ከደገፍነው ይልቅ በሀሳብ የሞገትነው በብዙ ሺ እጥፍ ፍሬ ያፈራል ። 🔴አለም የተሰራችው በሀሳብ ነው ፣ ሀሳብ የሁሉ ነገር አልፋ ነው ። ሁሉም ሀሳቦች ግን መልካም ናቸው ማለት አይደለም ። መልካሞቹ ግን በህሊና ቅኝት የተቃኙት ናቸው ። ጥበብ ማስተዋል ነች ፣ ማስተዋል ደግሞ ከእርጋታ ( ከስክነት ) ትወለዳለች ። የሰላ አይምሮ በተጨባጭ ማስረጃ ተነጋግሮ መደማመጥን ይከጅላል ። 🔵በውይይት መግባባትም አለመግባባትም የሀሳብ ብዛሀነትን ማስተናገድ መቻል ነው ። በሃሳብህ፣ በንግግርህና በተግባርህ ላይ ለሚነሳ ለማንኛውም ጥያቄ ደግሞ ሙሉ ሃላፊነት በመውሰድ ለማስረዳት፣ ለመከላከልና ለማስከበር፤ ስህተት ከሆነ ደግሞ ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ ሁን፡፡ 🌀ሰው ስትሆን የሰው ችግር ይገባሀል..ሰውን ለማጥቃት ሳይሆን ለማዳን ትዘጋጃለህ ለራስህ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ሀላፊነት ይሰማሀል ለተበደሉና ለተጎዱ ትቆማለህ ..ከዘረኝነት ወጥተህ ሁሉንም በእኩልነት መመልከት ትጀምራለህ አዎ ሰው ሰትሆን አይደለም የሰው ልጅ የእንሰሳት ህመምና ስቃይን ትረዳለህ እናም ሰው ሁን ..ሰው እንሁን !!! ውብ አሁን ❤️
نمایش همه...
#የእመቤታችን 120 ስሞች ! ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም 120 ስሞችን እንዲህ በማለት ትጠራታለች። 1. ሰአሊተ ምሕረት 2. ድንግል 3. እመ ብዙሃን 4. አቁራሪተ መዓት 5. የገብርኤል ብስራት 6. ንፅህተ ንጹሐን 7. ሃገረ እግዚአብሔር 8. ቅድስተ ቅዱሳን 9. ማህደረ ሰላም 10. መዓርገ ሕይወት 11. ማኅደረ ስብሐት 12. ማኅደረ ትፍስሕት 13. ቤተ ሃይማኖት 14. ብጽዕት 15. ሕሪት 16. ክብርት 17. ልእልት 18. ውድስት 19. የሰማዕታት እናት 20. የመላዕክት እህት 21. የነቢያት ትንቢት 22. የሐዋርያት ሞገስ 23. እመ ብርሃን 24. ርሕርሕተ ልብ 25. እመ አምላክ 26. የሲና እፀ ጳጦስ 27. የአዳም ተስፋ 28. የአብል ይውሕና 29. የሴት ቸርነት 30. የሔኖክ ደግነት 31. ሙጻአ ፀሐይ 32. ታቦት ዘዶር 33. እግዝትነ ማርያም 34. የቅዱስ ኤፍሬም ባራኪ 35. ምልዕተ ውዳሴ 36. ቡርክት 37. የደስታ መገኛ 38. ምእራግ 39. አዳም ቆማ 40. ጽርሕ ንጽሕት 41. ማሕደረ መለኮት 42. እሕቱ ለሙሴ 43. ገራሕቱ ለአብርሃም 44. ወለቱ ለዳዊት 45. እሙ ለአማኑኤል 46. ነያ ሰናይት 47. እምነ ጽዮን 48. መዝገበ ብርሃን 49. ጽጌ ሃይማኖት 50. ደብተራ ፍጽምት 51. ማርያም ቅድስት 52. አክሊለ ንጹሐን 53. ብርሃነ ቅዱሳን 54. ወለተ ሐና ወኢያቄም 55. መድኃኒተ ይእቲ 56. ሐመልማለ ገነት 57. ሙዳዬ መና 58. ርግበ ጸአዳ 59. ሐመልማላዊት 60. መንፈሳዊት ሃገር 61. የኖህ መርከብ 62. የሴም ምርቃቱ 63. የሴም እድል ፈንታዉ 64. የአብርሃም ዘመድ 65. ሶልያና 66. እሙ ለፀሐይ ጽድቅ 67. ምስራቀ ምስራቃት 68. በትረ አሮን 69. የገነት ኮል 70. የይስሐቅ ሽቱ 71. የያዕቆብ መሰላል 72. የዮሴፍ አረጋጊ 73. ቤዛዊተ ዓለም 74. የእሴይ ሥር 75. ወለተ ዳዊት 76. የሙሴ ጽላት 77. የአሮን ካህን ጸናጽል 78. የኢያሱ የምስክር ሐውልት 79. የጌዴዎን ጸምር 80. የሳሙኤል ሽቱ 81. የአሚናዳብ ሰረገላ 82. የዳዊት መሰንቆ 83. የሰሎሞን ቀለበት 84. የኤልያስ መሶበወርቅ 85. የኤልሳዕ ልሕኩት 86. የኢሳይያስ ትንቢት 87. የሕዝቅኤል አዳራሽ 88. ዕፀ ሕይወት 89. የሚኪያስ ኤፍራታ 90. የናሆም ፈዋሽ 91. የዘካርያስ ደስታ 92. ወለተ ጽዮን 93. ንጽሕት ጸምር 94. ደብተራ ዘትዕይንት 95. ሀገረ ክርስቶስ 96. ኪዳነ ምሕረት 97. በአታ 98. መሰረተ ሕይወት 99. ናዛዚተ ሕዙናን 100. እሕትነ ነያ 101. አንቀጸ አድሕኖ 102. መዓዛ እረፍት 103. ርግብየ ሠናይት 104. ሐረገወይን 105. አንቀጸ ብርሃን 106. ተቅዋም ዘወርቅ 107. መቅደስ 108. ሐመልማለ ወርቅ 109. ብርሃነ ሕይወት 110. ሆሕተ ምስራቅ 111. መዝገቡ ለቃል 112. ፍኖተ ሕይወት 113. ምስጢረ ስብሐት 114. መዝገበ ብርሃን 115. ምልእተ ክብር 116. ምልእተ ፍስሐ 117. ምልእተ ፀጋ 118. ጽላተ ኪዳን 119. ጽላተ ሕግ 120. ዳግሚት ሰማይ #ክብር_ለእናታችን @dnzema @dnzema @dnzema
نمایش همه...
"ዛሬም ፣ነገም፣ሁሌም እግዚአብሔር ይመስገን "~ ፈጣሪ ሆይ፦ "ወጥተን የገባነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ ፈጣሪ ሆይ፦ "ሠርተን ያገኘነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "ጤናን ያገኘነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "ተርበን የጠገብነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "ተጠምተን የረካነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ ፈጣሪ ሆይ፦ "ታርዘን የለበስነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "ዕድሜ የተጨመረልን" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ ፈጣሪ ሆይ፦ "ቀን የተጨመረልን" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "የሚያስጨንቁ ለሊቶች ያለፉት" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "የቆምነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "በእግራችን የተራመድነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "በአይናችን ያየነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "በጆሯችን የሰማነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "በእጆቻችን የሰራነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "በአንደበታችን የተናገርነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "በአይምሯችን ያሰብነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "የምንተነፍሰውን አየር አስገብተን ያስወጣነው" በአንተ ነው፤ ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "ሁሉም ነገር ያለፈው፤ በአንተ ነው፤ተመስገን። ~ አባት ሆይ፦ "ከቃላት በላይ ነህ፥ከአእምሮ በላይ ነህ፥ ከግምት በላይ ነህ፤ ተመስገን። ~ ፈጣሪ ሆይ፦ "ያልጠፋነው ከምህረትህ የተነሳ ነው"፤ ተመስገን። "ዛሬም ተመስገን" "ነገም ተመስገን" "ለዘላለምም ተመስገን።አሜን።
نمایش همه...
❍●●◦─━━━⊱🌹⊰━━━─◦●●❍ ●●◦ ምክር ◦●● ደመና ሲያይ መስሎት የጨለመ አለ ቂል ሰው 'ሁሉም አከተመ' ደቂቅ ተስፋን ካየናት አርቀን ነገ ሌላ ይሆናል ጥሩ ቀን! ጨለማው በብርሀን ይለወጣል! ሕይወት በብርሀን ጊዜ ብቻ የምንደሰትባትና የምንፈነጥዝባት አይደለችም። ይልቁኑም በጨለማውና ግራ በገባን ጊዜ ጭምር ከጨለማውና ከውጥንቅጡ ለመውጣት በምናደርገው ጥረት ይበልጥ ህይወታችንን ወደ በለጠ ደስታ ውስጥ እንጨምረዋለን። በጨለማው ጊዜ በውጥንቅጡ ጊዜ በችግሩ ጊዜ ተስፋ የቆረጡ፣ህይወታችን አበቃላት ብለው ጉዟቸውን ያቆሙና ህመሙ በዛብኝ ብለው ህልማቸውን ያቋረጡት ሁሉ አስደናቂዋን የብርሀን ፍንጣቂ ለማየት አይታደሉም። የብርሀኗን ፍንጣቂ ለማየት በህመሙ ጊዜ መጠንከር፣ በስቃዩ ጊዜ መበርታት በጨለማው ጊዜ መታገስ ያስፈልጋል፤ ያኔ ህመሙ ወደ መዳን፣ ማጣቱ ወደ ማግኘት፣ ጨለማውም ወደ ብርሀን ይለወጣል! በጨለማው ጊዜ ጥርስህን ንከስና ጉዞህን ቀጥል ወደ ስኬትህ መጨረሻ የሚያደርስህን ትግል በፍጹም አታቁም። አዎ ፈተናው ምን ያህል ቢበዛና ሊጥልህ ቢያንገዳግድህም አንተ ግን በፍጹም አትውደቅ። ብትወድቅም እንኳ እየተንፏቀቅ መሄድህን ቀጥል። ያኔ ብርሀን ከፊትህ ይመጣል! ይፈትናል እንጂ ድሉ ያንተ ነው! አስተውል! አበቃ የሚባል ነገር የለም ሕይወት ይቀጥላል...
نمایش همه...