cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Telebirr

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
492
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ውድ ደንበኞቻችን ከኛ ጋር ቢዝነስ በቴሌብር በመስራት ገንዘብ በፐርሰንት ማትረፍ ምትፈልጉ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ መመዝገብ ትችላላችሁ። ለመመዝገብ በ @telebirr_A1 አናግሩን።
نمایش همه...
Repost from telebirr
نمایش همه...
የቴሌክላውድ አገልግሎት (telecloud: IaaS, PaaS & SaaS) ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር

Repost from telebirr
ኩባንያችን ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር የዲጂታል አገልግሎቶችን በማቅረብ የደንበኞቹን የዕለት ተዕለት የቢዝነስ እንቅስቃሴ የሚያዘምን እና የሚያሳልጥ፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ከፍተኛ የመረጃ ክምችት እና አጠቃቀም እንዲሁም ተዛማች የክላውድ አገልግሎት ፍላጎት የሚያሟላ የቴሌ ክላውድ አገልግሎትን ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም በይፋ አስጀምሯል። የቴሌክላውድ ኮምፒዩቲንግ አገልግሎቶች በሶስት አማራጮች የቀረበ ሲሆን Infrastructure as a Service (IaaS) መረጃዎቻቸውን ማስቀመጥ፣ መቀመር የሚያስችል የክላውድ መሰረተ ልማት፣ Platform as a Service (PaaS)- የሶፍትዌር አልሚዎች ካሉበት ሆነው ላበለፀጓቸው ሶፍትዌሮች የተሟላ የዳታቤዝ ማኔጅመንት ሲስተም (MySQL DB) የሚያገኙበት እና Software as a Service (SaaS)- በውጭ ምንዛሪ የላይሰንስ ክፍያ ሳይከፍሉ ሶፍትዌሮችን ከቴሌክላውድ በተመጣጣኝ ክፍያ በብር ማግኘት የሚችሉበት አገልግሎቶች ናቸው። ቴሌክላውድ አገልግሎትን በድረ-ገጻችን https://telecloud.ethiotelecom.et ማግኘት የሚቻል ሲሆን ክፍያውንም ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ በሆነው ቴሌብር ካሉበት በመክፈል ይቻላል። ለበለጠ መረጃ፡ bit.ly/3Wa7eCI #ዲጂታልኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ
نمایش همه...
Repost from telebirr
Repost from telebirr
نمایش همه...
በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኦንላይን ለሚሰጡ አገልግሎቶች ክፍያዎችን በቴሌብር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር

Repost from telebirr
Photo unavailableShow in Telegram
የቴሌብር መላ ብድርዎን ለመክፈል ቀላል መንገዶችን እናጋራችሁ በቴሌብር መተግበሪያ፡ የፋይናንስ አገልግሎትን መርጠው - ቴሌብር መላ ገፅ ላይ የእኔ ቴሌብር መላ የሚለውን በመምረጥ ሂደቶቹን ይከተሉ ወይም *127# በመደወል: (1) ፋይናንሺያል አገልግሎት ላይ ቴሌብር መላ - ቀጥሎም ብድር ለመክፈል የሚለውን መርጠው ሂደቶቹን ይከተሉ #የፋይናንስ_አገልግሎት_ለሁሉም ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሸን ባንክ ጋር በአጋርነት
نمایش همه...
Repost from telebirr
Photo unavailableShow in Telegram
ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በድረ-ገፅ www.etrade.gov.et ለሚያገኟቸው የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ስያሜ እንዲሁም ተያያዥ አገልግሎቶች ክፍያዎን በቀላሉ በቴሌብር ይፈጽሙ! #ቴሌብር ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹና አስተማማኝ
نمایش همه...
Repost from telebirr
ኩባንያችን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባለጉዳዮች ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ለሚያገኟቸው የአገልግሎት ክፍያዎች ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹና አስተማማኝ በሆነው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ቴሌብር በመጠቀም ለመፈጸም የሚያስችል አሰራር በዛሬው ዕለት ተግባራዊ አደረገ! የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለጉዳዮች በድረ ገጽ www.etrade.gov.et ላይ ለሚያገኟቸው የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ስያሜ እንዲሁም ተያያዥ አገልግሎቶች በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ሆነው አገልግሎት በማግኘት እና ክፍያቸውን በቴሌብር በመፈጸም ውጣውረዳቸውን ማስቀረት እና ውድ ጊዜያቸውን መቆጠብ እንዲችሉ ያደርጋል፡፡ ይህ አገልግሎት በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ በሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ 4.8 ሚሊየን ብር የአገልግሎት ክፍያ ለ38 ሺህ አገልግሎቶች ተፈጽሞበታል፡፡ ለበለጠ መረጃ፡ bit.ly/3TQz7xW #ዲጂታልኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ
نمایش همه...
Repost from telebirr
Photo unavailableShow in Telegram
በዌስተርን ዩኒየን ከባህርማዶ የተላከልዎትን ሃዋላ በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ይቀበሉ! የተላከልዎትን ሃዋላ በቀጥታ ወደቴሌብር አካውንትዎ ሲያዘዋውሩ ደግሞ 5 በመቶውን በስጦታ እናበረክትልዎታለን። ቴሌብር - ፈጣን፣ ቀላል፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
نمایش همه...
Repost from telebirr
በአገልግሎቱ ከዚህ ቀደም ደንበኞችን በድምፅና በተወሰኑ የሶሻል ሚዲያ አማራጮች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በተናጠል ያስተናግዱ የነበሩ የጥሪ ማዕከሎችን አሰራር ያዘመነና በልዩ ልዩ አማራጮች ማለትም በድምጽ፣ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፣ በኢሜል፣ በድረ-ገጽ፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች፣ እንዲሁም ቻትቦትን (Chatbot) በመጠቀም የሚቀርቡ የደንበኞች ጥያቄያዎችን በአንድ ላይ አቀናጅቶ ለደንበኞች አገልግሎት ባለሙያዎች ማቅረብ በማስቻሉ ቀልጣፋና ተደራሽ የደንበኞች አገልግሎት ማቅረብ ያስችላል፡፡ ድርጅቶች እና ተቋማትም ይህን አገልግሎት ተጠቅመው የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሳለጥ ብሎም የደንበኞቻቸውን ተሞክሮ እና እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ የሚችሉበት ትልቅ እድል በመሆኑ አብራችሁን ለመስራት ፍላጎቱ ያላችሁ ድርጅቶች እና ተቋማት በድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በመገኘት አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን! ለተጨማሪ መረጃ፡ bit.ly/3gksBRi #ዲጂታልኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ
نمایش همه...