fa
Feedback
Eneho Books እነሆ መጻሕፍት

Eneho Books እነሆ መጻሕፍት

رفتن به کانال در Telegram

እነሆ መጻሕፍት | ዘወትር በልዮ ቅናሽ 0912735000 / 0905222224 ➍ኪሎ ምኒሊክ ት/ቤት ፊት ለፊት ሮሚና ዝቅ ብሎ

نمایش بیشتر
8 642
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+107 روز
-3330 روز
آرشیو پست ها
ከአሁን መሸሽ- መበለጥ! በጊዜ ለሚስካ ሥርዓት ውስጥ እየኖርሁ ጊዜ ቅዠት ነው ብል ምን እጠቀማለሁ የሚል ጥያቄ አለህ አይደል? ልብ በል! ጥያቄህ ምሁራኑ ካበጁት የእውቀት ግኝት አንደኛው ነው፡፡ ይ
ከአሁን መሸሽ- መበለጥ! በጊዜ ለሚስካ ሥርዓት ውስጥ እየኖርሁ ጊዜ ቅዠት ነው ብል ምን እጠቀማለሁ የሚል ጥያቄ አለህ አይደል? ልብ በል! ጥያቄህ ምሁራኑ ካበጁት የእውቀት ግኝት አንደኛው ነው፡፡ ይህም ከእውቀቶቹ ሁሉ አንድ መገለጫ ነው፡፡ እነሱ ያሉትን ማለትህ ባንተ ላይ የረባ ለውጥ ላይኖረው ይችላል፤ እነሱ ያለፉበትን ምቹ ህይወት አንተ እስካላለፍህበት ድረስ፡፡ ስለዚህ ነገሩ ያለው ከአንተ እና ከራስህ ጋር ብቻ ነው:: ቁመናህን የፈጠሩት የሰውነት አባለ-አካሎችህ ንቁ በሆኑ ጊዜ አንተም እንደ አንተ የነቃህ ትሆናለህ፡፡ ይሄን ቅልጥፍና ከታጠቅህ ነው ከሚሄደው «ጊዜ› ጋር መሄድ የምትችለው፡፡ THE POWER OF NOW Eckhart tolle

ዕውቁ የአፍሪካ የሥነ-ጽሑፍ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ዕውቁ የአፍሪካ የሥነ-ጽሑፍ ሰው ንጉጊ ዋቲዮንጎ በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ እስር፣ ግዞት እና ህመም ያላንበረከካቸው ኬ
ዕውቁ የአፍሪካ የሥነ-ጽሑፍ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ዕውቁ የአፍሪካ የሥነ-ጽሑፍ ሰው ንጉጊ ዋቲዮንጎ በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ እስር፣ ግዞት እና ህመም ያላንበረከካቸው ኬንያዊው ጉምቱ ደራሲ ፤ የአፍሪካዊ ዘመናዊ ሥነ-ጽሑፍ ምልክት ተደርገው ይቆጠሩ ነበር፡፡ ደራሲው ሥድስት አሥርት ዓመታት በተሻገረው የሥነ-ጽሑፍ ጉዟቸው ፤ በዋነኛነት ሀገራቸው ኬንያ ከቅኝ ግዛት እስከ ዴሞክራሲዊ ሥርዓት የነበራትን ጉዞ በመሰነድ ይታወቃሉ፡፡ ንጉጊ ዋቲዮንጎ ለበርካታ ጊዜያት የኖቤል ሽልማት የአሸናፊነት ቅድሚያ ግምት ተሰጥቷቸው ሳይሳካላቸው መቅረቱ አድናቂዎቻቸውን ሲያሳዝን ቆይቷል፡፡ ደራሲው ከምስጉን ጸሐፊነታቸው ባሻገር የአፍሪካዊያን የአፍ መፍቻ ቋንቋዎችሥነ-ጽሑፍ እንዲጎለብት ከፍተኛ ድጋፍ በማድረጋቸው ይታወሳሉ፡፡ ንጉጊ ዋቲዮንጎ እ.አ.አ በ1938 በወቅቱ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት በነበረችው ኬንያ ውስጥ ነበር የተወለዱት፡፡

አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በተዘጋጀው ዓውደ የመጻሕፍት ርእይ ያገኙታል። የፓውሎ ኮሊሆ አዲስ መጽሐፍ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል። ተርጓሚ፦ ዘላለም ንጉሤ The Witch Of Portobello የፖርቶቤሎዋ
አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በተዘጋጀው ዓውደ የመጻሕፍት ርእይ ያገኙታል። የፓውሎ ኮሊሆ አዲስ መጽሐፍ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል። ተርጓሚ፦ ዘላለም ንጉሤ The Witch Of Portobello የፖርቶቤሎዋ ምትኃተኛ መብራትንም አብርቶ በስውር ወይም በእንቅብ በታች የሚያኖረው የለም፤ የሚገቡ ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል እንጂ። ሉቃስ፦11:13 ይህ ጽሑፍ ጠረጴዛዬን ለቅቆ ወዳለምኩለት ዕጣ ፈንታው ከመሄዱ በፊት የተለመደውን አይነት እውነተኛ ታሪክን የሚተርክ፣ በጥንቃቄ ጥናት የተደረገበት የአንድ ግለሰብ የሕይወት ታሪክ ለማዘጋጀት እንደመሠረት ልጠቀምበት አስቤ ነበር:: ለዚሁ ሥራ ይጠቅሙኛል ብየ በማሰብ የተለያዩ ግለሰቦችን የሕይወት ታሪኮች ባነብም የአንድ የሕይወት ታሪክ ጸሐፊ የግል እመለካከቶች በሚያደርገው የምርምር ውጤት ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖራቸው ምንም ጥርጥር እንደሌለው እንድገነዘብ ብቻ ነበር የረዳኝ። እኔም የራሴን እመለካከቶች በአንባቢው ላይ የመጫን ዓላማ የለኝምና 'The Witch Of Portobello' "የፖርቶቤሎዋ አስማተኛ" ታሪክን ከዋነኞቹ ባለታሪኮች ዕይታ አኳያ እንዳለ ለመተረክ ወሰንኩ። ማለትም በቀጥታ የሕይወት ታሪኳን የመጻፍ ሃሳቤን ወዲያው በመተው ከሰዎች አንደበት ያገኘሁትን ሃሳብ ሳልጨምርና ሳልቀንስ ማቅረብን እንደቀዳሚ አማራጭ ወሰድኩ። ሥልክ፦ 0912735000             0905222224 ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks

አዲስ መጽሐፍ ርእስ፦ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም አዘጋጅ! በደመወዝ ጎሽሜ “ለሌዊ ነገድ ግን ሙሴ ርስት አልሰጠም፤ የእሥራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳላቸው ርስታቸው እርሱ ነው"45 ይህ አሥራ ሦስተኛው ነ
አዲስ መጽሐፍ ርእስ፦ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም አዘጋጅ! በደመወዝ ጎሽሜ “ለሌዊ ነገድ ግን ሙሴ ርስት አልሰጠም፤ የእሥራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳላቸው ርስታቸው እርሱ ነው"45 ይህ አሥራ ሦስተኛው ነገድ በአሥራ ኹለቱ ነገዶች መካከል ርስት እንዲኖረው የተደረገው፣ የኹሉም አገልጋይ ስለኾነ ነው፡፡ ተወዳጁ ይህ የብሉይ ምሳሌ የተነገረለት ሊቀ ካህን እና ባለ አሥራ ኹለት ከዋክብትም መኾኑ ነው የዚህ ምዕራፍ ሀሳብ። በዚህ ምእራፍ ኢየሩሳሌማችንን ከእርሱ ሊቀ ካህንነትጋ እያሰናሰልን ካህናት ተኮር መንፈሳዊ ጉዳዮችንና ማሳያዎችን ቀጥለን እናያለን፡፡ ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌምን ምሳሌዋ በኾነው በተጨባጩ መቅደስ በኩል ልያት፡፡ ከበዓለ አምሳ ጥቂት ዓመታት በኋላ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በኹለት መልክ እንዲቀጥል ተደረገ። የአገልግሎቱ ግብ አንድ ቢኾንም የማገልገያው መንገድ እንደ ቦታው፣ እንደ ሕዝቡና እንደ መምህሩ ፀጋ የሚወሰን ነው፡፡ ለምሳሌ ተወዳጁ አሥራ ኹለቱን ተማሪዎቹን፤ በሚከተለው መንገድ ለአገልግሎት ሲልካቸው እናነባለን፡ መጽሐፉን በብዛት ለምትፈልጉ ነጋዴዎች 5ኪሎ አበራ መጻሕፍት መደብር ታገኛላችሁ።

ዓለማየሁ ዋሴ በቅርብ ቀን ገበያ ላይ የሚውል መጽሐፍ ፍካሬ
ዓለማየሁ ዋሴ በቅርብ ቀን ገበያ ላይ የሚውል መጽሐፍ ፍካሬ

ሰላም የእነሆ መጻሕፍት ወዳጆች እንዴት አላችሁ። ዓቢይ ጾም እንደመሆኑ መንፈሳዊ መጻሕፍት የምታገኙበትን ቦታ እንጠቁማችሁ። ግዮን መጻሕፍት መደብር ይባላል አድራሻው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይገኛል ነባርና አዳዲስ መንፈሳዊ መጻሕፍትን በብዛትና በቅናሽ ያገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ገድላት የተለያዩ የጸሎት መጻሕፍ ትርጓሜ መጻሕፍት የውጪ ትርጉም መጻሕፍት መዝሙረ ዳዊትና ሌሎች መንፈሳዊ መጻሕፍት ያገኛሉ። ለበለጠ መረጃ ቻናሉን Join ያድርጉ። በ0913083816 ይደውሉ። እንዲሁም በመላው ዓለም ለምትኖሩ ውድ አንባቢዎች በDhl እና በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት መጽሐፍትን እንልካለን ይዘዙን። t.me/GhionBookStore1623

እነዚህ 4መጻሕፍት የሰዋሰውና የስነ ጽሑፍ መመርያ ሲሆኑ ኅምሌት የጸጋዬ ገብረ መድኅን ተውኔት ከእያንዳንዱ አንድ አንድ ቅጂ እኛ ጋር ማግኝት ትችላላችሁ። እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። 091
+4
እነዚህ 4መጻሕፍት የሰዋሰውና የስነ ጽሑፍ መመርያ ሲሆኑ ኅምሌት የጸጋዬ ገብረ መድኅን ተውኔት ከእያንዳንዱ አንድ አንድ ቅጂ እኛ ጋር ማግኝት ትችላላችሁ። እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። 0912735000/ 0905222224

አዲስ የትርጉም መጽሐፍ ኑዛዜ ቶልስቶይ ትርጉም፦ አሌክስ ዘፀአት ይህ መጽሐፍ አንድ ታላቅና ጒምቱ የሥነ ጽሑፍ ሰው በዕድሜው አጋማሽ ላይ የተፈጠረበትን ነውጥ የሚተርክ ነው። ይኹን እንጂ የትርክቱ እ
አዲስ የትርጉም መጽሐፍ ኑዛዜ ቶልስቶይ ትርጉም፦ አሌክስ ዘፀአት ይህ መጽሐፍ አንድ ታላቅና ጒምቱ የሥነ ጽሑፍ ሰው በዕድሜው አጋማሽ ላይ የተፈጠረበትን ነውጥ የሚተርክ ነው። ይኹን እንጂ የትርክቱ እርሾ በነፍሱ ውስጥ መሟሸት የጀመረው ከወጣትነቱ ጀምሮ ነው። ቶልስቶይ የሕይወትን ምንነትና እውነተኛ ትርጒም በሳይንስና በፍልስፍና ውስጥ ለማግኘት ያደርግ የነበረው ፍለጋና የደረሰበት ድምዳሜ አመለካከቱንና አኗኗኑሩን ብቻ ሳይኾን፣ የሥነ ጽሑፍ አቅጣጫና ይዘቱን ጭምር ይቀይራል። በመኾኑም እ.አ.አ ከ1880 ጀምሮ የቶልስቶይ ትኲረት ሙሉ ለሙሉ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት፣ በተለይም የጭሰኞች ሕይወት፣ እምነትና ኑሮ ላይ ይኾናል። እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። አዲሱ አድራሻችን ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት የባቡር ትኬት መቂረጫው ላይ ያገኙናል ። ሥልክ፦ 0912735000             0905222224 ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks

አዲስ የትርጉም መጽሐፍ How to stop worrying start living ርእስ፦ ሕይወት ቀላል ናት ትርጉም! ኤፍሬም ዓለሙ ስለዚህ በጥልቀት ተነፍስ... ከመጠን በላይ ማሰብ አቁሞ... ቀደሞ ሲ
አዲስ የትርጉም መጽሐፍ How to stop worrying start living ርእስ፦ ሕይወት ቀላል ናት ትርጉም! ኤፍሬም ዓለሙ ስለዚህ በጥልቀት ተነፍስ... ከመጠን በላይ ማሰብ አቁሞ... ቀደሞ ሲል የሆነወነ ነገር ስመተንተን መሞከር አቁሞ... ገና ያልመጣውንም መተነበይ +ው! ያከበደከወን እንድታቀለው፣ ያወሳሰብከወን እንድታረግበው የዝነኛው ዴል ካሬኔን 'ሕይወት ቀላል ናት፡ አታወሳስባት' መጽሐፍ በጥንቃቄ ተርጉሞና በጥራት ታትሞ መጥቶልሃል። መጽሐፋን ያዝና ቡናህን ፋት እያልክ ሕይወትህን አሳሞር... እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። አዲሱ አድራሻችን ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት የባቡር ትኬት መቂረጫው ላይ ያገኙናል ። ሥልክ፦ 0912735000             0905222224 ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks

አዲስ መፅሐፍ በጋዜጠኛ ተስፋ ፈሩ የተፃፈው "አንሶላ ውስጥ ሟች እና ሌሎችም ወጎች" ለንባብ በቃ። መጽሐፉ 57 ወጎች እና ሽሙጦች የተካተቱበት ሲሆን በ 207 ገፆች ተቀንብቧል። ደራሲው ጋዜጣ ላይ
አዲስ መፅሐፍ በጋዜጠኛ ተስፋ ፈሩ የተፃፈው "አንሶላ ውስጥ ሟች እና ሌሎችም ወጎች" ለንባብ በቃ። መጽሐፉ 57 ወጎች እና ሽሙጦች የተካተቱበት ሲሆን በ 207 ገፆች ተቀንብቧል። ደራሲው ጋዜጣ ላይ በሚጽፋቸው ቁምነገር አዘል አዝናኝ ጽሑፎች ይታወቃል። የተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ  ጉዳዮችን የሚዳስሱ ወጎች በተካተቱበት መፅሐፍ ጀርባ ላይ አቶ ሙሼ ሰሙ፣ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን እና ዶክተር መስፍን ፈቃዴ አስተያየታቸውን አስፍረዋል። ስልክ፦ 0913145214

ከታተመ  32 ዓመት የሞላው የፍልስፍና መጽሐፍ በእነሆ መጻሕፍት ያገኙታል። ይህ የፍልስፍና መጽሐፍ በብዙ ፍልስፍና ለሚወዱ ለሚማሩ የሚጠቅም መጽሐፍ ነው ጥቂት ቅጂዎች እጃችን ላይ አሉ በአዱሱ መገኛችን ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት የባቡር ትኬት መቁረጫው ላይ ያገኙናል። *የምዕራባውያን ፍልስፍና ሥልጣኔ ታሪክ* በቀለ ተገኝ መኰንን (በውስጥ ገጾቹ የያዙት) * የግሪኮች ሥልጣኔ ከመሬት አነሣሱ * ሚሊጦሳዊው ትምህርት ቤት * ጲፃጐራስ * ሔራቅሊጦስ * ጳርሜኒዲስ * ኤምጲዶቅሊስ * የአቴና ባህላዊ ሥልጣኔ * አናግዛጐራስ * አቶሚስቶቹ * ጵሮታጐራስ ክፍል ሁለት:- ሶቅራጥስና ፕሌቶ (አ ፍ ላ ጦን ) * ሶቅራጥስ * በጥንቱ ሥልጣኔ የስፓርታ ፈንታ * ፕሌቶ የፍልስፍና ተአምኖቱን የቀዳባቸው ምንጮች * የፕሌቶ ተምኔተ ዓለም (ዩቶፒያ) * የፕሌቶ ጽርሓ አርአያዊ አሚነህላዌ * የፕሌቶ ዘለዓለማዊት ሕይወት * የፕሌቶ መድበላተ ዓለማት * በፕሌቶ ፍልስፍና የገሐዳዩና የጽሩዩ ሐሊዮት ዕውቀት. እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። አዲሱ አድራሻችን ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት የባቡር ትኬት መቂረጫው ላይ ያገኙናል ። ሥልክ፦ 0912735000             0905222224 ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks

የእናት ምድር ኅዘን ዶ/ር ብርሃኑ ኪዳኔ ትኩረቱን መልክአ ምድር የተፈጥሮ ልምላሜ የብዝኅ ሕይወት ስለሰው ልጅና እንስሳት የተጻፈ የልብወለድ ትረካ ነው ይወዱታል። ሥልክ፦ 0912735000 090522
የእናት ምድር ኅዘን ዶ/ር ብርሃኑ ኪዳኔ ትኩረቱን መልክአ ምድር  የተፈጥሮ ልምላሜ የብዝኅ ሕይወት  ስለሰው ልጅና እንስሳት የተጻፈ የልብወለድ ትረካ ነው ይወዱታል። ሥልክ፦ 0912735000             0905222224 ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks

ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት አዲሱ መገኛችን። የባቡር ትኬት መቁረጫው ላይ ያገኙናል ። እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። አዲሱ አድራሻችን ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት የባቡር
ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት አዲሱ መገኛችን። የባቡር ትኬት መቁረጫው ላይ ያገኙናል ። እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። አዲሱ አድራሻችን ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት የባቡር ሥልክ፦ 0912735000 0905222224 ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks

https://www.ethioeyewitness.com/book-review-%E1%88%B8%E1%88%99%E1%8A%94-shemune/ ሸሙኔ ብዙ የሥነጽሑፍ ሰው የወደዳት መጽሐፍ ናት።(እስቲ አንብቧት)

***ሁለቱ የቢዝነስ መጻሕፍት በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ ለገበያ ቀርበዋል።*** ታላቅነትህን አትጠራጠር ታላቅነትህን እንድትገልጥ የሚረዳ መጽሐፍ!!! YOU are a BADASS በዓለም ላይ አንተ ማለም ብቻ የምትችለውን አይነት ሕይወት የሚኖሩ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ከእነዚያ ሰዎች አብዛኞቹ የአንተን ያህል ተሰጥኦ ያላችው አይደሉም፡፡ የስኬታቸው ቁልፍ የሚፈልጉትን ለማግኘት መወሰናቸው፣ አሮጌ _ ሰበቦቻቸውን ማዳማጥ ማቆማቸው፣ መጥፎ ልማዶቻቸውን መተዋቸው እና ማድረግ ያለባቸውን ማድረጋቸው ነው፡ ጄን ሲን ሴሮ ትርጉም:- ሀኒም ኤልያስ ከቅጥር፣ ከባለህበት እርገጥ እና ከድህነት ራስን ነጻ ማውጣት THE 4-HOUR WORKWEEK አንድን ችግር በአንድ መንገድ ለመፍታት ሞክራችሁ ያገኛችሁት ውጤት ዝቅተኛ ከሆነ፣ በተቃራኒው ቢሆንስ ኖሮ የሠራሁት? ብላችሁ መጠየቅ ይገባችኋል፡፡ ውጤታማ ያልሆነ አርአያና ከውጤት የማያደርስን መንገድ አትከተሉ፡፡ የምትጠቀሙባቸው ግብዐቶች የማይጠቅሙ ከሆኑ የቱንም ያህል ባለሙያዎች ብትሆኑ የምትሠሩት ምግብ ሊጣፍጥ አይችልም፡፡ ተርጓሚ ብርሀኑ በላቸው እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። አዲሱ አድራሻችን ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት የባቡር ትኬት መቂረጫው ላይ ያገኙናል ። ሥልክ፦ 0912735000             0905222224 ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks

ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት የከፈትነው አዲሱ መገኛችን ይጎብኙን። እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። አዲሱ አድራሻችን ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት የባቡር ትኬት መቂረጫው ላይ ያገኙናል ። ሥልክ፦ 0912735000             0905222224 ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks

አሐቲ ድንግል በአዲሱ መደብራችን። በአዲሱ መገኛችን ሜክሲኮ ተግባረዕድ ፊት ለፊት በሚገኝው  የባቡር ትኬት መቁረጫው ጋር ያገኙናል። የአባ ገብረ ኪዳን ግርማ ለአንባብያን አንዳንድ ጥቆማዎች፦ » ይህ መጽሐፍ ስለ እመቤታችን የተጻፈ ሆኖ ሳለ ነገረ ክርስቶስም በብዛት አለበት። ለዚህም ምክንያቱ ጌታ በእመቤታችን እንደሚሰበክ ለመግለጥ እንደሆነ አንባቢው ያስተውል "ዳግመኛም እመቤታችንን እንዲህ ናት ስንል እንዲህማ የሚባል ጌታ አይደለምን? የሚል ጥያቄ ለሚነሣባቸው ወገኖች ለይቶ ለማሳየት ነው፡፡ ➢ አንዳዳንድ ሀሳቦች ከርእሰ ጉዳዩ ርቀው የሔዱ ይመስላሉ።የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በእያንዳንዱ ሐሳብ እንድናተርፍ ከመፈለጌ የተነሣ ምክሮችንና ማብራሪዎችን በተጓደኝ ማስቀመጤ ነው። ታግሠው የጨረሱት የመጽሓፉን ልብ ለማግኘት ይችላሉ የተንሸዋረረ መረጃ ጨልፎ ከመወሰንም ይድናሉ።የመጽሐፉን ከፊል ሳይሆን ሙሉ እውነት ያገኙ ዘንድ ሙሉውን ቢያነቡት ያስመሰግናቸዋል። ➢ በመካከል ያሉት የግዕዝ ኃይለ ቃላት አንባቢውን ላለማስቸገር ጎላ ባለ ጥቁር ቀለም ተቀምጠዋል።ግዕዙን ቢያነቡት የቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት ቋንቋ በመሆኑ ግዕዝ ለማወቅ ትርፍ በቁዔት ይሆናቸዋል።የሚችሉትን አማርኛ ያለ መቆራረጥ ቶሎ አንብበው መረዳት ለሚፈልጉ ደግሞ ግዕዙ ጎልቶ ስለ ተጻፈ እያለፉ ከጭረቱ በኋላ ያለውን አማርኛ ፍቹን ማንበብ ይችላሉ። ➢ የዚህ መጽሐፍ መልካም ትምህርት ሁሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነው።በፊደልም ሆነ በምሥጢር የሳትኩት ካለ ደግሞ የእኔ ብቻ ነው እንጅ ነውር የሌለባት የክርስቶስ ሙሽራ የቤተ ክርስቲያን አይደለም። ቢኖርብኝ ደግሞ አቤት ወዴት ብዬ በእናቴ ለመታረምም ዝግጁ ነኝ። እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ። አዲሱ አድራሻችን ሜክሲኮ ተግባረዕድ ት/ቤት ፊት ለፊት የባቡር ትኬት መቂረጫው ላይ ያገኙናል ። ሥልክ፦ 0912735000             0905222224 ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል። https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks https://t.me/enhobooks