cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🍃بالقرآن نحي {በቁርአን እንኖራለን

የተለያዩ ቁርኣናዊ አስተምህሮ’ዎች፣ ጣፋጭ ቲላዋዎች፣ ቁርኣንን የሚመለከቱና በቁርኣን ዙሪያ የሚሽከረከሩ መልዕክቶች የሚተላለፍበት ቻናል join ይበሉ ! ቁርኣን የወረደው ለሰው ልጅ መመሪያ፣ እንድናስተነትነውና እንድንገሰፅበት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦ (ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡ {Q 38:29}

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 017
مشترکین
-124 ساعت
-27 روز
-830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ኢላሂ! የማይወድቅ ዱዐ ስጠን። ሁኔታችንን አስተካክል። ልጆቻችንን አብጅልን። ያማረ አደብ ስጠን። በረካ ስጠን። ቀልባችንን አርጥብልን። ጭንቀታችንን ገላግለን። ጉዳያችንን አግራልን። በሽተኞችን አሽርልን። ለሟቾቻችን እዘን። ወንጀላችንን ማርልን። ነውራችንን ሽፍንልን። መከራን አቅልልልን። ከፈተና ጠብቀን። አሚን!
نمایش همه...
👏 2
#ሪዝቅ_ሰፊ_ነው በሲሳይ (ሪዝቅ) የተደራጀ እምነት መያዝ ከተውሒድ ግንዛቤዎች መካከል አንዱ ነው። በርካቶቻችን በሚታዩ ቁሳዊ ነገሮች በተለይም በገንዘብ ላይ ብቻ የሚታይ ሲሳይ ላይ እናተኩራለን።  ኢማሙ ሸዕራዊ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) ስለሪዝቅ ሲመክሩ የተሟላ ሪዝቅ ማለት የልጆች መስተካከል ነው፣ አስፈላጊ የሚባለው ደግሞ የጤንነት ሪዝቅ ነው ዝቅተኛው ሪዝቅ የገንዘብ ነው። በማለት የሪዝቅ እሳቤን እንድናሰፋው ይጠቁማሉ። አንዳንዴ የምታወራው ነገር የሚገባው ጓደኛ ማግኘት ትልቅ ሪዝቅህ ነው፣ በኪስህ ብር ሞልቶ በቁስ ሀብት ተንበሻብሸህ ሰው ይጠርብህ ይኾናል ስታገኘው የምትደሰትበት ሰውም ማግኘት ሪዝቅህ ነው። የምትደሰትበት ሥራህ፣ የሚያዝናኑህ ልጆችህ፣ ሕይወትን የምታቀልልህ ባለቤትህ ሪዝቆች ናቸው። መስጂድ የመቀመጥ ዕድልህ፣ ለብቻህ የመዝናናት፣ የማንበብና በመንገድ ላይ እየተራመድክ የምታገኘው አየርህ ኹሉ የአላህ ጸጋና ሪዝቅ ናቸው። ምን የርሱ ያልኾነ አልለ። የሚያስቅ ብዙ ነገር እያለህ መሳቅ ሊከብድህ ይችላል፣ መተኛት ፈልገህ መኝታ ላይ ብትገኝም ዕንቅልፍ እምቢ ብሎህ ይኾናል። ብዙ የሚያስለቅስ ገጠመኝ ይኖርሀል ግና ማልቀስ ተስኖሀል ከእነዚህ ነገሮች መጠበቅ በራሱ ከአላህ ጸጋዎች ናቸው። « እነሆ እርሱም አስሳቀ፣አስለቀሰም።» አልነጅም፤43 ሳቃችን ከርሱ የተሰጠን ጸጋ ነው፣ ለቅሶኣችንም ከርሱ የተሰጠን ሪዝቅ ነው። እንባ ከስንት ውስጣዊ ንዳድ ያድናል?! እንባ የደረቀበት ሰው ንዳዱ በምን ይበርዳል። ፈገግታ ሲሰለብ የሰው ልጅ በምን ሀይል ያገኛል። አላህ ጥልቅና ደቂቅ በኾኑ ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ፍጡራኑን በእዝነቱ የሚያካብ አምላክ ነው። የሰው ልጅ ከላዩ ላይ ያለውን ዝንብ እንኳን ለማባረር ከጌታ የእዝነት እርዳታ ፈላጊ ነው። ያሉንን ጸጋዎችና ሪዝቆች እንዳንመለከት የሚያደርገው እርጉሙ ሰይጣንና የገዛ ነፍስያችን ነው። አላህ ያለንን ያሳየና ♥ አላህ ይህን ባርነት ያስረዳን ♥ Best kerim 💚
نمایش همه...
ዐይንህ ሲደርቅ በቁርአን አርሰው፣ ወገብህ ሲገር በሱጁድ አለስልሰው፣ ቀልብህ ሲደርቅ በሞት አስታውሰው። . ከቁርአን ጋር ያረጀች ዐይን አቤት ማማሯ! ከቁርአን ጋር የኖረች ዐይን አቤት ብርሃኗ! በቁርአን የተኳለች ቅንድብ አቤት ዉበቷ! . https://t.me/MuhammedSeidAbx
نمایش همه...
اللهم صلِّ على سَيِّدنا مُحَمَّدٍ النبي الأمي وعلى آله وصحبه وسلم تسليما، صلاة دائمة بدوامك، باقية ببقائك، لامنتهى لها دون عرشك💚
نمایش همه...
1
#ሪዝቅ አላህ ፍጡራኑን ከፈለገ በሰበብ ይረዝቃል፣ ያለሰበብም መረዘቅ ይችላል። ከሰበብ ተቃራኒም ኾኖ ይረዝቃል፣ ምንም በማይቻልበት ሁኔታዎች ውስጥም ይረዝቃል። እርሱ (አላህ) ጥራት የተገባውና  ራዚቅ ነው ♥ የለገሰን ሐብት፣ ዕውቀት፣ አምልኮ፣ ውበት፣ ወዘተ የርሱ ሪዝቅ ሲኾኑ እነዚህ ነገሮች በራሳቸው ዋና ነገሮች አይደሉም ሰበቦች ቢኾኑ እንጂ! ሰበብ ላይ መኩራራት ሺርክ (ማጋራት) ነው። ገንዘቤ ያድነኛል፣ አምልኮዬ ነው ነጻ የሚያወጣኝ፣ ዕውቀቴ፣ ዝናዬ ማለት አላህን የሚያስረሱ ናቸው። እነዚህ ሰበቦች ላይ መቆየት ግን በራሱ የታዘዝንበት ጉዳይ ስለኾኑ ዋጂብ (ግዴታ) ናቸው። ሰበቦችን ከማድረስ መዘናጋት ወይም መተው ደግሞ ወንጀል ነው። ሰበብ ለማድረስ ስንታገል ካለመኮፈስ ጋር እንዲሁም ከእኛ ውጭ ያለውን ታሳቢ ከማድረግ ጋር እንዲኾን ይመከራል። አላህ ለፈለገው ባርያው የፈለገውን አይነት ሪዝቅ (ኢማን፣ ሐብት፣ ዝና፣ ...) ሊሰጥ ስለሚችል ሁሌም ልብ ሌሎችን ከመመለከት ራሷን እንድትመለከት ብቻ መጣር ያስፈልጋል። የተባረከ ሪዝቅ የምናገኝበት ጁምዓ ይኹንልና ♥
نمایش همه...
ጤናን የሚጠብቁ ወጪ የማይጠይቁ መድሀኒቶች። 💊 ንግግር ዋጋ በሌለው ቦታ አለመናገር። 💊 ከጃሂል(አላዋቂ) ጋር አለመከራከር። 💊 ሰዎች ላይ አስተሳሰብን ለመጫን አለመሞከር፣ ይልቁንስ በመልካም ስብዕና ልባቸውን ማናገር። 💊 የሰዎችን ፍፃሜ አውቃለሁ ብሎ አለመፍረድ! 💊 በአንድ ህመም ሰዎችን ሁሉ አለመዳኘት። 💊 መሄድ የፈለገን መሸኘት፣ አዲስ ህይወትን ለመልመድ አለመጠየፍ። 💊 በቀደር መረጋጋት። 💊 ጥሩ አድማጭ መሆን! ካደመጡት ውስጥ መርጦ መውሰድ። 💊 ሁሉንም ነገር ለማስረዳት አለመሞከር። 💊 ሰበቡን አድርሶ መቀጠል። 💊 ስለ ሰዎች በአደባባይ ለማውራት አለመጣደፍ፣ ከልክ ባለፈም አጓጉል አለመቀደስ። 💊 መጠበቅን መቀነስ፣ ኡዝር(ምክንያት) መስጠት። 💊 መተናነስ ማብዛት፣ መተናነስ ለማይገባቸው መተናነስን አለማባከን። 💊 ሰዎችን በሚገባቸው መንገድ ማውራት። 💊 አላዋቂነት አምኖ ለማወቅ መፍጨርጨር። 💊 የሀሳብ ልዩነቶችን ማክበር። 💊 መለየትን ፈርቶ ለማፍቀር አለመሰሰት። 💊 ባለፈ ታሪክ የሰዎችን የአሁንና የወደፊት ታሪክ አለመደምደም። 💊 ለተውበት ክብር የሚሰጥ ልብ ለመጎናፀፍ መጣር። 💊 አላህን መጠየቅ አለማቆም። 💊 ሰለዋት ማብዛት። 💊 በሌሎች ሰዎች ህይወት ጣልቃ አለመግባት። 💊 መስጠት፣ መለገስ ማብዛት። 💊 ወላጆችን፣ ትላልቅ ሰዎችን፣ ዓሊሞችን መኻደም። [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13
نمایش همه...
سورة الكهف ❤️ قراءتها نور ورحمة وبركة ❤️ ابداع الشيخ البلوشي ❤️ قمة الروعة من أمتع ماتسمع في حياتك كلها❤️ الهدوء والسكينة ❤️ وراحة القلب والنفس وعلاج كل أمراض العصر ❤️ ممتعة جداا ❤️❤️❤️❤️❤️❤️
نمایش همه...