ዘፀአት ሜዲካል (ZeTse@ Medical)
رفتن به کانال در Telegram
This channel is created for discussion of health related issues in Amharic. ስለጤና/ሕክምና የምንማማርበት ቻናል ነው::
نمایش بیشتر307
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+17 روز
-530 روز
در حال بارگیری داده...
کانالهای مشابه
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
دسامبر '24
دسامبر '24
+3
در 0 کانالها
نوامبر '24
+17
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '24
+53
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '24
+276
در 0 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 14 دسامبر | 0 | |||
| 13 دسامبر | 0 | |||
| 12 دسامبر | +1 | |||
| 11 دسامبر | 0 | |||
| 10 دسامبر | 0 | |||
| 09 دسامبر | 0 | |||
| 08 دسامبر | 0 | |||
| 07 دسامبر | 0 | |||
| 06 دسامبر | 0 | |||
| 05 دسامبر | 0 | |||
| 04 دسامبر | +1 | |||
| 03 دسامبر | +1 | |||
| 02 دسامبر | 0 | |||
| 01 دسامبر | 0 |
پستهای کانال
| 2 | Internal hernia through mesoappendix causing small bowel obstruction: A case report
Eneyew Mebratu Gashey, Sileshi Genetu Tiruneh, Fekadu Wudie Gelaw, Adugna Tasew Tebabel, Litegebew Yitayeh Gelaw
Link: https://doi.org/10.1016/j.ijscr.2024.110590
To send your papers use @HakimAds
@HakimEthio | 152 |
| 3 | Gossypiboma: an unusual presentation as lower urinary tract symptoms
Sileshi Genetu Tiruneh, Eneyew Mebratu Gashey, Adem Ibrahim Aliyi, Litegebew Yitayeh Gelaw
Link: https://doi.org/10.1016/j.ijscr.2024.110377
To send your papers use @HakimAds
@HakimEthio | 153 |
| 4 | To ERMP 2024 applicants
The 2024 ERMP registration will be on Nov 12 - 26, 2024 (Hidar 3 _ 17, 2017).
Visit ( https://www.moh.gov.et/en/ermp-announcements ) for more information. | 192 |
| 5 | Vacancy | 187 |
| 6 | https://www.facebook.com/share/p/18FQNnCkng/ | 175 |
| 7 | #ገጠመኝ
ሰሞኑን ነው
አንድ የማውቀው የ60ዓመት ሰው ለኪንታሮት ህክምና ክትትል ነበረው፡፡ በመሃል ወደ ባህል ህክምና ሄዶ ፊንጢጣው ላይ በመርፌ ተወግቷል፡፡ ከዚያ በኋላ ሰገራ መቆጣጠር እንዳልቻለና መፍትሔ እንድፈልግ ደውሎ ነገረኝ፡፡ ለባህል ሀኪሙ እንዲደውል ነገርኩት፡፡ ደውሎለት ስልክ እንደማይመልስ ነገረን፡፡ በአካልም ሄዶ እንዳያገኘው ከሌላ ቦታ ነው የመጣሁ ብሎ በካምፕ ስላከማቸው ሊያገኘው አይችልም፡፡
እና እኔ ምን ልበለው ወገን? | 215 |
| 8 | የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ
ከ500 አዲስ የሚወለዱ ህፃናት ባንዱ ይከሰታል፡፡ ላንቃና ከንፈር ሁለቱም በጋራ ወይም በተናጠል ተሰንጠቀው ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ በፅንስ ዕድገት ወቅት በ8ኛው ሳምንት ጀምሮ የሚከሰት ነው፡፡
መንስኤዎች፡
ለዚህ ዓይነት ክስተት የሚያጋልጡ ብዙ መንስኤዎች ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
1. የወላጆች እድሜ ከፍ ማለት
2. በእርግዝና ወቅት የሚወሰዱ መድኃኒቶች ፣ አልኮል ፣ ሲጋራ
3. በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግሮች መከሰት
4. በእርግዝና ወቅት በእናቶች የቫይታሚንና ፎሌት እጥረት
ዓይነቶች፡
በተለየዩ መንገዶች ሊከፈል ይችላል፡
1. ከፊልና ሙሉ
2. ባንድ በኩልና በሁለቱም በኩል ፡፡ በመባል ሊከፈል ይችላል፡፡
ከመወለዳቸው ቀድሞ ሊታወቅ ይችላል?
አዎ::
ልጆች ከመወለዳቸው በፊት በባለሙያ በታገዘ አልትራሳውንድ ምርመራ ሊታወቅ ይችላል፡፡
ህክምና፡
ልጆቸ ከመወለዳቸው በፊት ይህን ክስተት ማወቅ ለወላጆች ዝግጁ እንዲሆኑ ስለሚያግዝ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡
ከአመጋገብ (ጡት ከመጥባት) ጋር ተያይዞ የሚያስቸግሩ ሁኔታዎች ስላሉ የባለሞያ ምክር ያስፈልጋል፡፡
ልጆቹ ለቀዶ ህክምና ብቅ እስኪሆኑ ድረስ (ብዙን ጊዜ ከ3 ወራቸው ጀምሮ ብቁ ይሆናሉ) መሰንጠቁ እንዳይሰፋ የሚያግዙ ብሉ መንገዶች አሉ እነሱን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡
ልጆቹ 3 ወር ከሞላቸው በኋላ ቀዶ ህክምና በሚደረግባቸው ተቋማት ክትትል መጀመር አስፈላጊ ነው፡፡ እንደየመሰንጠቁ ዓይነት በተለያዩ መንገዶችና ጊዜያት ቀዶ ህክናምናው ይደረጋል፡፡
ከቀዶ ህክምና በኋላ ደግሞ የጥርስ ፣ የንግግር እንዲሁም የውበት ህክምናዎች በቀጣይነት በክትትል ይደረጋሉ፡፡
መከላከል፡
ሙሉ በሙሉ መከላከል ባይቻልም ክስተቱን በተለያዩ መንገዶች መቀነስ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ መንገዶች መካከል፡
ቅድመ እርግዝና ክትትል ዋናው ነው፡፡
በዚህ ጊዜ በተለይ የቫይታሚና ፎሌት እጥረትን በማከም መቀነስ ይቻላል፡፡
ሌላው በእርግዝና ወቅት ከአልኮል ፣ ከሲጋራና ከተለያዩ መድኃኒቶች በመራቅ ክስተቱን መቀነስ ይቻላል፡፡
ከተከሰተ ደግሞ እንደሚታከም አውቆ ህክምናውን መከታተል ትልቅ ተግባር ነው፡፡
ድህረ ታሪክ (ገጠመኝ)፡
ከዕለታት አንድ ቀን በአባቱ እቅፍ የመጣ የከንፈር መሰንጠቅ ያለው ህፃን ቀዶ ህክምና ከተደረገለት በኋላ ብዙዎች ላይ የምናየው የደስታ ስሜት በዚህ አባት ላይ አላየንም ይልቅም ለቅሶ ነበር የጠበቀን፡፡ ክስተቱ አዲስ በመሆኑ ለምን እንደሆነ ስንጠይቀው የመለሰልን ምላሽ እኛንም አስለቅሶናል፡፡
እንዲህ ለሚስተካከል ነገር እናቱ እራሷን አጥፍታለች ብሎ ነገረን፡፡
መውጫ፡
1. ክስተቱ ከላይ ባነሳናቸውና በሌሎች መንስኤዎች በተፈጥሮ የሚከሰት እንጂ እርማን ወይም ሌላ እንዳለሆነ ማወቅና ማሳወቅ
2. ምንም እንኳን በሀገራችን ህክምና ገና ቢሆንም እንዲህ ያሉ ችግሮች በተለያዩ ረጂ ድርጅቶች ድጋፍ በነፃ የሚታከሙ ስለሆኑ ሲያጋጥም እንደሚታከም አውቆ መፍትሔ መፈለግ፡፡ ያላወቁትንም ማሳወቅ፡፡
ለምክርና ተጨማሪ ማብራሪያ በ 0937044711 መልዕክት ይላኩ::
በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎችም ይወዳጁ
facebook tiktok You tube | 460 |
| 9 | እንደዚህ አይነት ክስተቶች አጋጥሟችሁ ያውቃል?
-መነሻው ምን ይሆን?
-መከላከያ መንገዱ ምን ይሆን?
-ህክምናውስ?
......
ጠብቁ | 325 |
| 10 | بدون متن... | 1 |
| 11 | የሳይነስ በሽታ (SINUSITIS) | 359 |
| 12 | የሳይነስ በሽታ (SINUSITIS)
ሳይነስ በአፍንጫችን አከባ የሚገኙ በአየር የተሞሉ ክፍት ቦታዎች ናቸው፡፡ ሳይነሶች ከስራቸው ባለው የፊት አጥንት ስም ይጠራሉ፡፡ ለምሳሌ፡ ማግዚለሪ ፤ ኢትሞይድ ፤ ፍሮንታል ወዘተ ይባላሉ፡፡ በርካታ ጥቅሞች አሏቸው፡፡ የምተነፍሰው አየር እርጥበታማ እና ሞቅ ለ እንዲሆን ማድረግ ፤ የድምጽ ቅላጼ እዲያምር እና የፊት አደጋን መከላከል ከጠቀሜታዎች ውስጥ ናቸው፡፡
የሳይነስ በሽታ በአብዛኛው አፍንጫን ስለሚያካትት ሪኖሳይንሳይትስ ተብሎ ቢጠራ ይመረጣል፡፡ የበሽታው ስያሜ በተጠቃው ክፍል ላይ በመመስረት ማግዚለሪ ፤ ኢትሞይድ ፤ ፍሮንታል ተብሎ ሲጠራ በመንስኤው ደግሞ የባክቴሪያ ፤ የቫይረስ ፤ የፈንገስ ተብሎ ይጠራል፡፡ በህመሙ ቆይታ ደግሞ አጣዳፊ ዘውታሪ ተብሎ ሊከፈል ይችላል፡፡
አጣዳፊ የሳይነሳይትስ በሽታ በታሪካዊና አካላዊ ምርመራ የሚታወቅ በሽታ ነው፡፡ በዚህም ከአለርጂና ከተለመዱ የላይኛው መተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን መለየት ይቻላል፡፡
አመጣጥ፡
ሶስት ነገሮች አስተዋጽኦ አላቸው፡፡
1. ከሳይነሶች ወደ አፍንጫ ያለው ግንኙነት መስተጓጎል (obstruction of sinus drainage pathway)
2. አፍንጫ ወስጥ ያሉ ፀጉሮች እክል ሲገጥማቸው (ciliary impairment)
3. የአፍንጫ ፈሳሽ መጠንና ባህሪ መለወጥ (altered mucus quantity and quality)
አጣዳፊ የቫይረስ ሳይንሳይትስ
አብዛኛው የሳይነስ ህመም በቫይረስ ኢንፌክሽን ምክንያት ይከሰታል፡፡ rhinovirus, corona virus, Influenza virus, parainfluenza virus, respiratory syncytial virus, adenovirus, interovirus ዋናዎቹ የሳይነስ ህመም አምጭ ቫይረሶች ናቸው፡፡ እነዚህ ቫይረሶች የላይኛው የመተንፈሻ አካልና የሳይነስ ኢንፌክሽን በተያያዠነት ያስከትላሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 5-10% የሚሆኑት የጸረ ተህዋስያን ህክምና የሚያስፈልገው ተደራቪ የባክቴሪያ ሳይነስ ህመም ሊኖራቸው ይችላል፡፡
አጣዳፊ የባክቴሪያ ሳይነስ ህመም
አብዛኛውን ጊዜ ከቫይረሶች ህመም ጋር ይዛመዳል፡፡ Streptococcus pneumonia, Hemophilus influenza, Moraxella catatrrhalis, Staphilococcus aureus ዋናዎቹ ባክቴሪዎች ናቸው፡፡
የፈንገስ የሳይነስ ህመም
አልፎ አልፎ የሚከሰት ሲሆን Aspergillus, Alternaria ከአምጭ ፈንገሶች ዋናዎቹ ናቸው፡፡
የሳይነስ ህመም ምልክቶች፡
በአፍንጫ ዙሪያ ያለ ህመም ፤ ወደ ግንባርና ጥርስ ድረስ ዘልቆ ሊሰማ ይችላል፡፡ በምናጎነብስበትና በምናስነጥስበት ጊዜ ይባባሳል፡፡ የአፍንጫ ፤ የጉንጭ ወይም የዐይን ሽፋሽፍቶች መቅላት ፤ የአፍንጫና የዐይን ዙሪያ መቅላት ፤ የአፍንጫ መደፈን ፤ የፊት ህመም ፤ የማሽተት አቅም መቀነስ ….. ዋናዎቹ ምልክቶች ናቸው፡፡
ከ7-10 ቀናት በላይ የቆየ ጉንፋን ወይም አገግሞ የሚያገረሽ ጉንፋን የሳይነስ ህመም ሊሆን ይችላል፡፡
ምርመራና ህክምና፡
በዋናነት በምልክቶቹ መሰረት ሊታወቅ ይችላል፡፡ በተጨማሪ የደምና የራጅ ምርመራዎች ሊረዱ ይችላሉ፡፡
የባከቴሪያ የሳይነስ ህመም እንደአሞክሳሲሊን ባሉ ጸረ ተህዋስያን ሊታከም ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአፍንጫ የሚረጭ ስቴሮይድ ሊሰጥ ይችላል፡፡ አንቲሂስታሚን የሚባሉ መድሃኒቶች ግን ባይሰጡ ይሻላል፡፡
በአፍንጫ ውስጥ የተጠራቀመን ቆሻሻ ለማስወገድ phenylephrine, pseudoephedrine የተባሉ መድሃኒቶች ከ10-14 ቀናት ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡ (እነዚህ መድሃኒቶች የደም ግፊት ላለባቸውና ለአትሌቶች አይሰጡም፡፡)
ተደጋጋሚ የሳይነስ ህመም ጠንቆችን ካስከተለ ቀዶ ህክምና ሊያስፈልገው ይችላል፡፡
ወደ 40% የሚሆኑ የሳይነስ ህመሞች ያለመድሃኒት በራሳቸው ይድናሉ፡፡ በተለይ የቫይረስ ሳይነስ ህመም 98% ያለመድሃኒት ይድናል፡፡ መድሃኒት ተጀምሮ በ48 ሰዓታ ውስጥ መሻሻል ካልታየ ድጋሜ መታየት ያስፈልጋል፡፡ ያልታከመ ወይም በቂ ህክምና ያልተደረገለት የሳይነስ ህመም መጅራ ገትር ፤ የደም ስር ኢንፌክሽን ፤ የዐይን ኢንፌክሽን እንዲሁም የአንጎል መግል ሊያስከትል ይችላል፡፡
(ምንጭ ፡ በለስ፡ በኢትዮጵያ የተለመዱ ተላላፊ በሽታዎች) ለምክርና ተጨማሪ ማብራሪያ በ 0937044711 መልዕክት ይላኩ:: | 317 |
| 13 | ዶ/ር መንሱር ለተማሪዎቹ የተለየ አቀራረብ ነበረው:: ትጉህ እንድንሆን ብዙ መንገዶችን ይጠቀማል:: አንድ ቀን 4ኛ ዓመት ሬዚደንት ሆነን 'delorme procedure' እየሰራን mucosa'ውን ሳትቀዱ ከጨረሳችሁ ምሳ ትጋበዛላችሁ አለን:: እኛም በጣም በትኩረት እየሰራን እየለ አንድ ቦታ ላይ ተቀደደ ሳናውቀው ስሜታዊ ስንሆን አይቶን ይሄኛው ችግር የለውም አይቆጠርባችሁም ብሎን ምሳ ጋብዞናል:: ይህን ለተማሪዎቹ ትጋት ከሚጠቀማቸው መንገዶች አንዱን ለመጥቀስ ነው::
ብዙዎቹ ሀኪሞች በሚጎድላቸው በአስተዳደራዊ ስራዎች ላይም በትኩረት በመሳተፍ ቀዶ ህክምና ት/ክፍልን አስከብሮ የኖረ ሰው ነው::
ዶ/ር መንሱር ሌላው ሊመሠገንበት የሚገባው በትርፍ ሰዓቱ በግል ህክምና አገልግሎት ዘርፍ ከክሊኒክ አንስቶ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል እስከመስራት የደረሰ ታታሪ ሀኪም ነው:: በዚሁም ለጎንደርና አከባቢው ማህበረሰብ ትልቅ ውለታ ውሏል:: ከማህበረሰቡም አልፎ ለጤና ባለሙያው ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ሆኖ እስካሁን እያገለገለ ነው::
ከቸቸላ አድባሮች አንዱ የሆነው ዶ/ር የብዙዎች ቀዶ ህክምና ሐኪሞች ልብ ውስጥ ሁልጊዜም ይኖራል:: የህይወት ጉዞውን በዚህ ሊንክ http://www.youtube.com/@Hakim207?sub_confirmation=1 ይመልከቱ
ዶ/ር እንየው መብራቱ: ጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
@HakimEthio | 317 |
| 14 | በጣም የሚያሳክክ ቁስል ፥ መሃሉ ላይ ድርቅ ያለ ነገር ወይም ክፍተት ካለው 'ዱቅንዱቅ' (myiasis) ሊሆን ይችላል::
Myiasis: ለዚህ ሊያጋልቱ በሚችሉ የዝንብ ዓይነቶች በሚኖር ንክኪ የሚከሰት ሲሆን በተለይ በእንስሳት ላይ ተከስቶ ወደ ሰው የመተላለፍዕድል አለው::
መከላከል: ልብስ የሚሰጣበትንና የምኝታ ቦታዎችን ከዝንብ ንክኪ ነፃ ማድረግ:
ህክምና:
- እንደመጀመሪያ እርዳታ ነፍሳቷ አየር እንዳታገኝና እንዳታድግ ባዝሊን ቀብቶ ማሸግ
- በህክምና በቀላሉ እንዲወጡና እንዲወገዱ ይደረጋል:: | 311 |
| 15 | https://www.tiktok.com/@dr.eneyew/video/7420841203752619270
https://www.tiktok.com/@dr.eneyew/video/7420841203752619270 | 230 |
| 16 | ወደ ውስጥ የገባ ጥፍር ከቀዶ ህክምና በፊትና በኋላ
(Ingrown nail before and after surgery! ) | 672 |
| 17 | አርቲሜተር የተባለው በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል ታገደ
****
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አርቲሜተር የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡
በተደረገ የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡
በመሆኑም ይህን መድኃኒት የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት እና በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡
መድኃኒቱ ሻይንፋርም በተባለ የቻይና የመድሃኒት አምራች የተመረተ ሲሆን፤ አርቲሜተር (Artemether 80mg/1ml) የሚል ስያሜ ያለው እና በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት መሆኑን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መረጃ አመልክቷል፡:
Source: EBC | 249 |
| 18 | የቆዳ ካንሰር:
ከካንሰር ዓይነቶች በብዛት የሚታይ ካንሰር ነው::
በተለይ ለፀሐይ ተጋላጭ በሆኑ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ ተደጋግሞ ይታያል:: በቁስል ወይም በእብጠት መልክ ሊከሰት ይችላል::
የቆዳ ካንሰር ምልክቶች!
1. ለረጅም ጊዜ የማይድን ቁስል
2. ከቆዳች የተለየ የጠቆረ ዕብጠት (ቁስል)
3. መሃሉ ጎድጉዶ ዳር ዳሩ ከቆዳ ከፍ የሚል ቁስል
4. የተለየ ጠረን ያለው ቁስል
5. በቀላሉ የሚደማ ቁስል
6. በየጊዜው እየሰፋ የሚሄድ ቁስል
ምርመራ (diagnosis)
1. በሃኪም ዕይታ (physical diagnosis)
2. በፓቶሎጂ ምርመራ (ከእብጠቱ ወይም ከቁስሉ ናሙና በመውሰድና በማይክሮስኮፕ በማየት)
ህክምና፡
የቆዳ ካንሠር አብዛኛውን ጊዜ በቀዶ ህክምና ይታከማል:: በጨረርና ኬሞቴራፒም ሊታከም ይችላል::
ለምክርና ተጨማሪ ማብራሪያ በ 0937044711 መልዕክት ይላኩ:: | 204 |
| 19 | በመሃል አናት ላይ ለአንድ አመት የቆየ ቁስል
ምን ሊሆን ይችላል?
መልሳችሁን በአስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡ | 187 |
| 20 | ፊንጢጣ አከባቢ ያለ ህመም ሁሉ ኪንታሮት አይደለም::
1. በፊንጢጣ ዙሪያ ጠረን ያለው ወይም የሌለው ፈሳሽ ካለዎት - የፊንጢጣ ፊስቱላ
2. ሰገራ በሚወጡበት ጊዜ ከፍተኛ ህመም የሚሰማወት ከሆነ - የፊንጢጣ መሰንጠቅ
3. ፊንጢጣ ዙሪያውን የሚገባና የሚወጣ ከሆነ - የአንጀት መውጣት
4. ሰገራ በሚወጡበት ጊዜ ማስጨነቅ ፣ አብሮ ተቀላቅሎ ደም መውጣት ካለዎት - የፊንጢጣ ካንሰር
5. በፊንጢጣ ዙሪያ ማሳከክ ከለዎት - ኢንፌክሽን (ብክለት)
6. ህመም የሌለው ደም መድማት ወይም በጎን የሚገባና የሚወጣ እብጠት - የፊንጢጣ ኪንታሮት ሊሆን ይችላል::
(በፊንጢጣ አከባቢ ላለ ህመም ምክር ከፈለጉ በ 0937044711 በቴሌግራም መልዕክት ይላኩ) | 220 |
