cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የቀድሞ አበው እና እመት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ጥበብ... 👇👇👇👇👇👇👇👇 👉 @behlateabew 👈 👆👆👆👆👆👆👆👆 https://t.me/+RICJUxY54uwNbPXe

نمایش بیشتر
Advertising posts
10 816مشترکین
-624 ساعت
-97 روز
-7130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

በሰሙነ ሕማማት የካህናት የጸሎት ማሳረጊያ፦ * እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤ ዓመ ከመ ዮም፤ ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም አሜን። ትርጉም:- * ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማ (ሥቃይ፣ መከራ) ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን በደስታና በሰላም ያድርሰኝ ያድርሳችሁ። * አሜን።
نمایش همه...
🥰 5🙏 1
✥✥✥ ዕለት ሰኞ ✥✥✥ - ይህ ዕለት አንጽሖተ ቤተ መቅደስ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለተ ነው፡፡ በቅዱስ ማርቆስ ወንጌል እንደተገለጠልን ጌታችን ከቢታንያ ወጥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ተራበ፡፡ በለስም ከሩቅ ዓየ፣ በለስዋ ግን ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ምንም ኣላገኘባትም ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ፍሬ ኣይገኝብሽ ከአንቺ ፍሬ የሚበላ ኦይኑር አላት ያን ጊዜውንም በለሲቱ ደርቃለች (ማር.11፥12-19/ማቴ.21፥19/ሉቃ.19፥45-46) በለስ የተባለች ኦሪት ናት፡- በለስ አገኘ ማለቱ ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና አገኛት ሲል ነው፡፡ ወደ እርስዋም ሄደ ማለት ፈጻሜ ሕግ ተባለ (ሥርዓተ ኦሪትን ማለት በ8ኛው ቀን መገዘር በ40 ቀን መሥዋዕት ማቅረብን... እየፈጸመ አደገ) ማለት ነው፣ ፍሬ አላገኘባትም አለ ሕግ ከመባልዋ በቀር ድኅነትን አላደረገባትም፣ ፍሬ አይገኝብሽ አላት ሲል፡- ባንቺ ድኅንነት አይደረግ አላት፡፡ ይህም ቅዱ ዳዊት ‹‹መሥዋዕትን ቁርባንን አልወደድሁም ሥጋህን ኣንጻልኝ፣ የሚቃጠለውንና ስለኃጢኣት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም ሲለ የኦሪትን ሕግ (ዐሠርቱ ትዕዛዛትን) አሳለፋቸው ማለት አይደለም፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንደነገረን በመሥዋዕተ ኦሪት ፍፁም ድኅንነት ኣለመገኘቱን አውቆ ማሳለፉን እና ፍፁም ድኅንነት የምናገኝበትን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረቡን ያሳያል፡፡›› አንድም፦ በለስ ያለው ኃጢኣትን ነው፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ኃጢኣትን በዚህ ዓለም ሰፍና ኣገኛት፡፡ ወደ እርሷ ሄደ ፍሬም አላገኘባትም ማለት በአይሁድ አንደበት በሐሰት ኃጢኣተኛ ተባለ እንጂ (ስለ እኛ መተላለፍ እንደበደለኛ ተቆጠረ እንጂ) ኃጢኣትን አልሠራም ሲል ነው፡፡ ፍሬ አይገኝብሽ ሲል፡- ባንቺ በመጣ ፍዳ የሚያዝ አይኑር አላት ማለት ነው፡፡ ➕ ከዚህ በመቀጠል ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡ ቤተ መቅደሱም ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ በዚያ ያሉትን ሁሉ አስወጣቸው፡፡ ይኸም በጠቅላላው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ለጆች ኃጢኣት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢኣታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ (ማቴ.21፥12-17/ማር.11፥15-24/ሉቃ.19፥4)
نمایش همه...
5
"ከመድኃኒትነቱ የተነሳ ከቤቱ መሠረት ሳይናወጥ ከልዑል መንበሩ ወረዶ ጸጋንና ኃይልን አሳየ ። ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም። "           ቅዳሴ ጎርጎርዮስ እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ። አምላከ ቅዱሳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም ያድርሰን!!!
نمایش همه...
".......እግዚአብሔርን ቃል ወደ ምድር ይወርድ ዘንድ ከድንግል ማርያም ሰው ይሆን ዘንድ በጨርቅ ይጠቀለል ዘንድ በበረት ውስጥ ይጣል ዘንድ ከሴት ልጅ ጡቶች ወተትን ይጠጣ ዘንድ ምን አተጋው? ለእኛ ለጠፋናው አይደለምን?" ሃይማኖተ አበው ንባብና ትርጓሜው፤ ዘቅዱስ እለእስክንድሮስ ፲፮÷፪
نمایش همه...
👍 5 2
نمایش همه...
ሚያዝያን ለመቄዶንያ!

በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለመቄዶንያ አረጋዊያን እና ህሙማን መርጃ ማዕከል እንለግሳለን! እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ! ቴሌግራም (

https://t.me/ethio_telecom)

ፌስቡክ (

https://www.facebook.com/ethiotelecom)

ኢንስታግራም (

https://www.instagram.com/ethiotelecom/)

ሊንክዲን (

https://www.linkedin.com/company/ethio-telecom)

ዩትዩብ (

https://www.youtube.com/c/EthiotelecomETH)

ቲክቶክ (http://www.tiktok.com/@ethio_telecom?lang=en) ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ! #MatchingFundForSustainableFuture #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

በድንግልና መኖር የሚችሉ መጋባትም መውለድም የለባቸውም በሌላ በኩል ደግሞ በድንግልና መኖር የማይችሉ ቢኖሩ ነውር በሆነ መንገድ እንዳይወልዱ ወይም ለመውለድ ሳይፈልጉ ይበልጥ ነውር በሆነ መንገድ ከሌላይቱ ሴት ጋር እንዳይተኙ በሕጋዊ መንገድ ጋብቻን ይፈጽሙ ልጅ ላለመውለድ የጽንስ መከላከያን የሚጠቀሙ ባለትዳሮች ሁሉ ሥራቸው ነውር እና ስህተት ነው፡፡ ልጆች መውለድን በመከላከል ድክመታቸውን በመሸፈን መመከር አይኖርባቸውም፡፡ ቅዱስ አውጉስጢን
نمایش همه...
9👍 1