ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
رفتن به کانال در Telegram
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
نمایش بیشتر1 676
مشترکین
-124 ساعت
-17 روز
-1730 روز
آرشیو پست ها
ትሑት ምህላ
=========
አቤቱ ጌታ ሆይ ፣
የኢትዮጵያውያንን እምነት
የግሪክን ጥበብ መሻት
የአይሁድን ምልክት ጥማት
የፈሪሳውያንን የአመክንዮ ሙግት-
ልክፍት
የሱፊን ተደሞ
የዜንን አርምሞ
የተመሥጦ መገለጥን ምትሐት ፣
......አጣምረህ ለነብሴ ሥጣት!
በዚህ፣ኃይሏ ግርማ
እንደ ጨለማ ፣ ቀለም ድንበርን ታሥማማ.....።
አሜን።
ዲበኩሉ ጌታ
ሰኔ ፳ ፳፻፰ ዓ.ም
-----------//----------
የምድር ዘላለም ድንቅ መፅሀፍ ነው በተገኘበት ይነበብ!! ያነበበ ብዙ ያተርፋል
#
@sufafel
@sufafel
@sufafel
Abstract
Utter silence
I listen
Whooshing sound of
cars
Some how it makes me calm
The moon lighting the darkness
Some how it heals
Some how the beauty
Puts me in trance
Some how it is easier
To bare my soul
To people I barely know
It is okay to be bare
And sometimes
it is okay
To wallow in pain
I want to live here
Here is just me
Here is just me alone
Here is my home
Do we have a meaning?
Do you have a meaning?
Do I?
We work, sleep and eat
Wake up to do it all again
What if this is hell?
What if hell is just like a broken
Record
Repitition of the same thing over and over
Suddenly you wouldn't know when it will be over
I say all this while I am sober
When you pause
Only eyes can see
Ears can hear
Fears dissapear
life reappear
And you exist
I crave this pause
The one that closed the door
Is my shadow
who likes to to oppose
He is in control
I suppose
Somehow they misunderstood
It is he who is talking
Not me
It is he who you seeing
Not me
"Me" is a misconstruction
Made by the perception of what I think is others perception of me
I really don't know what "Me" is
I don't know "I"
As soon as the word "I" exist
We perish
This abstract mind
Science couldn't decode
History couldn't record
This isn't my mind speaking
This isn't my body your witnessing
Just the formation of DNA
Manifestation of information
That lived for decade
-Anima
#Existence
Can't get enough poetry in your life?! Come on down to Pallet (near "Yugo Church", Bole) on Thursday for a night of connection with our friends at Spittoon!
https://facebook.com/events/s/spittoon-poetry-reading-night/591908678309967/?ti=as
አባ ዳኘው-አጤ ምኒልክና ባዕታ ማርያም
Jan 21, 2020
| Written by
ታመነ መንግስቴ
|
ታሪክ/ history
"አለ ወልድ አልነሳኝ
ስለቴን በከንቱ
የተገፋን ሰሚ
ባዕታ አለች እናቱ።"
ይች ስንኝ በወጣቱ የሙዚቃ ባለሙያ ዳን አድማሱ ዳምጠው "አራት ኪሎ" የተሰኘች አነጋጋሪ እና ቅኒያም ነጠላ ዜማ ውስጥ ያለች ናት።
ታዕካ ነገስት ባዕታ ለማርያም ገዳም እዚያው አራት ኪሎ ከግቢ ገብርኤል ከፍ ብላ ለእምየ ምኒልክ መታሰቢያ ትሆን ዘንድ በልጃቸውና በዘመኗ ኢትዮጵያን ንግስተ ነገስት ሆና ባስተዳደረቻት ዘውዲቱ ምኒልክ የተሠራች ናት።
የታላቁ ንጉስ ዓጤ ምኒልክ እና ባለቤታቸው የኢትዮጵያ ብርሃን -እቴጌ ጣይቱ ብጡል መቃብርም በዚችው ገዳም ነው።
ለዚህም ይመስላል ለዛሬው ትውልድ እንደ ማንቂያ ደወል የሚሆኑ፣እንደ ወይን ጠጅ የሚጣፍጡ የአባ ዳኘው-አጤ ምኒልክና ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ መልዕክቶች በአፀደ ገዳሟ በጉልህ ተፅፈው መነበባቸው።
እነሆ እንደ መነሻ፦አባ ዳኘው ጣሊያንን አፈር አስግጠው ካባረሩት በሗላ ስለ ህዝባቸው መዘመን አብዝተው ይጨነቁ ጀመር።ጠላታቸውን ያሸነፉት በበዛ የፈጣሪያቸው ድጋፍና በህዝባቸው ቀናኢነት እንጅ በተጠና የጦር ስልት፣በተለካ ጥበብ አለመሆኑን አሰቡ።እናም ዘመናዊ ትምህርትን ማስፋፋት የማይታለፍ ተግባራቸው መሆኑን አመኑ።እንዲህም አሉ።
"በጣም ወደ ሗላ የቀረን ህዝቦች ነንና፤ገና የምንሰራው ብዙ ስራ ስላለ ወጣቶቻችንን ማስተማር አለብን።"
ይሁንና አባ ዳኘውን እንዲህ ያሳሰባቸው የትምህርት ጉዳይ ከድፍን ምዕተ ዓመት(100ዓመት) በሗላም እንደነበረ አለ። ይሄን ያስተዋለው ዳን አድማሱ "በአራት ኪሎ" ዘፈኑ፦
"የአውራ ዶሮ ቁንጮ ስሙ ነው ኮኮን
ስንቱ ቆቡን ጫነ ያልተማረውን።"
እያለ የትምህርታችንን ውድቀት ያሽሟጥጠዋል።
እምየ ምኒልክ ተዓምር በሰሩባት አገር ያላቸው የህይወት ገመድ መመንመኑን እየተረዱ ነው።ሞት ብዙ ጊዜ ድል ያደረጉትን ንጉስ ሊወስዳቸው እየመጣ ይመስላል።እሳቸውም በዓለም የሚፀፀቱበት የለምና በፀጋ ተቀብለውታል ፤ግን በተጋደሉላት አገራቸው ኢትዮጵያ ከእሳቸው ህልፈት በሗላ የሚመጣው የስልጣን ሽኩቻ ለዳግም አድዋ ዳርጓት ኢትዮጵያን እንዳያሳጣ ይሰጋሉ።ስለሆነም መኳንንቱን ሰብስበው እንዲህ ሲሉ የመሰናበቻ መልዕክታቸውን አደረሡ፦
"እኔ እስካሁን በፍቅር እንዳኖርሗችሁ እናንተም በፍቅር ተስማምታችሁ እንድትኖሩ እለምናችሗለሁ።"
የምኒልክ ልጅ ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱም ምንም እንኳን ታሪካቸው በብልጣብልጡ እንደራሴያቸውና የሗላው ንጉሰ ነገስት ተፈሪ መኮነን የተጋረደ ቢመስልም በአገራቸው ጉዳይ የዋዛ ሴት አይደሉም።
በታዕካ ነገስት ባዕታ ለማርያም ገዳም ያለው ነፍስ አለምላሚ መልዕክታቸው ይሄን ይመስላል፦
"መሪዎች በቤተ-መንግስት ቢቀመጡ፣ህዝቡም በየግል ቤቱ ቢቀመጥ መጠለያ ይባላል፤እንጅ የጋራ ቤታችን ኢትዮጵያ ናት!"
ሁሉንም መልዕክቶች አራት ኪሎ ከቤተ-መንግስቱ በስተ ምስራቅ ካለችው የታዕካ ነገስት ባዕታ ለማርያም ገዳም ቅጥር ግቢ አገኘሗቸው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ይቆየን!
Copyright ©2020 All rights reserved | This site is owned by NConsults
ብርዕ – በደም ዕንባ / ሙሉጌታ ተስፋዬ
በኔው ‘ኔ ጥራና
በኔው ‘ኔ ጥራና
ባፅሜ ቀሰም ብርዕ
በህይወት ማቅለሚያው
ጠርቤ ስለቁጥ
የኑሮን ሽቁጥቁጥ
የራሴ ጉልቻ … አንገቴ አለ ዘምበል
የደም ወዜ ጠለል … እንባዬ አለ ከምበል
በሞት ሞት ጣረሞት … <በልቤ ልብ በል!>
ሥጋት አንድውጋት
ነፍሴን ሲሰንጋት
በቅኔ እንቆቅልሽ … ቁልቁል ተቆልፌ
በእምነት … እምም እመ-እዝነት
በህልም ዓለም ሽምጥ ግልቢያ ተሰልፌ
ለሥጋ ታርቄ
ለገላ መርቄ
እርቃኔን ወጥቼ – ግቤኔን አስጥቼ
የጎኔን ጨረስኩት – ሆዴን ስሸነግል
ለነገ ራሴ ስንቅ – ልቃንጣዬ አገልግል።
ካምና ከታች አምናው
የጉልበት የጤናው
ቢታይ ሁለንተናው – <ሁሉ> ሁለመናው
የልቤ ልብ በል – ለልቤ ሲጠናው
ብቻ ላይኔ ብቻ – ላይኔ ለብረቱ – ላይኔ ብቻ ቀናው!
ለታይታ ለዝናው …
በሰው ፊት በሸንጎ ለወግ ማ’ርግ ዝናው!!
አዎ! በኔው ‘ኔ ጥራና
በኔው ‘ኔ ብራና
በብርዔ ስለቁጥ
የኑሮን ሽቁጥቁጥ
ደም እንባ – ደም እንባ – እንበለ እንባ ደም
ሕይወት እንጉርጉሮ – በአትም አይታደም።
(ለሚንቁኝ – ለማያውቁኝ)
29/7/84
ባለቅኔ ሙልጌታ ተስፋዬገ(አያ ሙሉ የወሎ አበጋር ወድ አለቃ ጅብ አይበላሽ)
🦋🦋👇🦋🦋
https://telegram.me/sufafel
✅🦋👆🦋✅
✍🦋 ሙሌዋ ✍ 🦋
🦋
እኛ ቤት ሴት አለ
በአባዎች አለም እነ እማ ባቆሙት
መኩሪያዋ እልፍ ነው የሶስት ወንዶች እናት
የሶስት ወንዶች እናት
በወንዱም በሴቱም አለም እየገባች
ጾታዋን ተሻግራ ሁሉን እያሳየች
ወንድ ልጆችዋ ውስጥ ሴትነትን አየች
እኔ ትንሹ ነኝ የመጨረሻው ልጅ
ቃጭሌን አንቃጭላ ዱብ ያደረገችኝ
ይህ ቃጭል ሲንቃጨል
አባቴ ደስ አለው ወንድ ልጅ ሲደገም
እነ እማ ባጸኑት በዚህ የእኛ ቤት አለም
ሴታሴት ልብ እንጂ ሴት አልተወለደም
ሴትነት ውስጤ አለ
ተፈጥሮ ከእናቴ ተማክረው የዘሩት
ቤተሰብ ከመንደር ተባብረውም ቢያጥሩት
በሰብዓዊ ለዛ የማሰቢያ ጥጌ
አጼ ሆኜ ሳለሁ ያረገኝ እቴጌ
ሴትነት ውስጤ አለ
የአንደበቴ አራሚ የኔነቴ አንዱ መልክ
የጉልበቴ ሚዛን የሰውነቴም ልክ
እወቀው አባቴ እወቀው ወንድሜ አንተም ውስጥ እኔም ውስጥ ሴትነት አለልክ
ይህን እጹብ ጸጋ ወንድሞቼ ስተው
እማዎች ባጸኑት መኖሪያ አለማቸው
አባ ሆነው ቀሩ ልክ እንደአባታቸው (የት አባታቸው)
እኔ ግን ‘ወንድ ነኝ!’ . . .
እኔ ግን ‘ወንድ ነኝ’ ብዬም የማልፎክር
በሴታዊ ገጼም ከቶም የማላፍር
ሴትነት ወንድነት ቅኝቴ ውስጥ የለም
ሰው መሆን ዜማዬ ለሁለቱም ቀሰም
እነ እማ ባጸኑት በዚህ የእኛ ቤት አለም
ሴታሴት ልቤ እንጂ ሴት አልተወለደም
እነ እማ ባጸኑት በዚህ የእኛ ቤት አለም
ወንዳወንድ ቀልቧ እንጂ ወንድ እናት አልሆነም
የተገደበ እንባ ኤሌትሪክ አልሰጠም
በአባቴ አዛኝነት ቤታችን አልሞተም
በኔ ቡና ማፍላት ጎረቤት አልሳቀም
ምክንያቱም . . .
የሶስት ወንዶች እናት ወንዶች ውስጥ ሴት እንጂ ሴት አልወለደችም
እነ እማ ባቆሙት በአባዎች አለም
እኛ ቤት ሴት አለ እኛ ቤት ሴት የለም
ሰይፈ ተማም 2011
በልብ የቀበሩት
አይኖቿ ሲሰርቁኝ፤ እኔም ሰርቄያቸዉ፣
ምኞቴን አርግዤ፤ ትግል ገጠምኳቸዉ፣
የሚሸነፍ ጠፍቶ፤ ተዉ ሺሸኝ…! አልሸሽም…!
እንዳዉ ስንባባል፣
የጊዜ መቁጠሪያ፤ ለካ ጥሎን ሄዷል፡፡
በሱለይ አደም
ጦቢያ ግጥምን በጃዝ
📅 102ኛውን ፕሮግራም ዛሬ ረቡዕ ጥር 6/2012 በ11፡30
📍 ራስ ሆቴል
🙏 @Ribki
መግቢያ 100 ብር ብቻ
@eventsethiopia
Day 1 of our 31 Days of Poetry! Check out Rob Haile's beautiful piece, "Living Tribute"! https://youtu.be/rE06WYe4uPM
አደረች አራዳ አደረች አራዳ
የኔ ብርቱካኔ የኔ ፅጌረዳ
(የጌታነህ ልጅ ©)
አደረች አራዳ አደረች አራዳ
የኔ ብርቱካኔ የኔ ፅጌረዳ
አንቺ የኔ አበባ የብርቱካን ፍሬ
ማደሩን እደሪ
ብትከርሚም ክፍት ነው አይዘጋም በሬ
እኔ ጌታ አይደለሁ
ዘይትሽ አልቋል ብዬ ፊቴን አላዞርም ፊትሽን እያየሁ
እጠብቅሻለሁ
ባደርሽበት ነግቶ ማለዳን እያየሁ
አበባዬ ፅጌ
እሾህ የወረረሽ ከቀለምሽ ግርጌ
እንዴት ዓይኔን ልክደን
ያደርሽበት ወዳጅ እሱ እኔን አይደለ
በቀለምሽ ድምቀት...
አይገባው ይሆናል እንደተታለለ
አሳዘነኛ
አንድ እኔ አለሁ አይደል?
በቀለምሽ ድምቀት...
አውቄ 'ምታለል!?
የብርቱካን ልጣጭ ውስጡን ግጬ በላሁ
አዳርሽ አስግቶኝ ደጅ ደጁን እያየሁ
አዳርሽ እንዴት ነው አንቺ ፅጌረዳ
ደስ ብሎሽ አነጋሽ? ንገሪኝ ልረዳ
እ?
ተይ ተይ
ተይ አትመልሺልኝ አትበይኝ ስ**
ነገ እንድጠብቅሽ ደጅ ደጁን እያየሁ
ይቅር አትንገሪኝ ይቅር ብዬሻለሁ
እስክትመለሺ
ድንግዝግዙ ጠዋት ሌቱ ከሰዓት ነው!
----_----_----_----_----_----_----_----
ታህሳስ 19: 2012
