cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

YeneTube

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
127 743
مشترکین
-25724 ساعت
-2 2207 روز
-1 97730 روز
آرشیو پست ها
ኔስትሊ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት በሚልካቸው የወተት ምርቶቹ ላይ ስኳር እንደሚጨምር ተሰማ! የስዊዘርላንዱ የምግብና መጠጥ አምራች ኩባንያ ኔስትሊ ወደ አፍሪካ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ በሚልካቸው የጨቅላ ህጻናት ወተት እና ሌሎች ምርቶቹ ላይ ስኳር እና ማር እንደሚጨምር "ፐብሊክ አይ" የተሰኘ ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚገኝ የምርመራ ትቋም አጋልጧል። ቡድኑ ከላይ ወደተጠቀሱት ክፍለ አህጉራት የሚላኩ የኒዶ(Nido) እና ሴሪላክ(Cerelac) ምርቶችን ቤልጄም ወደሚገኝ ላብራቶሪ ልከው ያስመረመሩ ሲሆን በውስጡ በአለም የጤና ድርጅት መመሪያ መሰረት አለቅጥ መወፈርን እና ተያያዝ በሽታዎችን ለመከላከል ለጨቅላ ህጻናት የተከለከለ የስኳር መጠንን ይዞ መገኘቱ ተዘግቧል። በአንጻሩ ኩባንያው ለአውሮፓ ደንምበኞቹ የሚልከው ስኳር የሌለበት እንደሆነ የዘ ጋርዲያን ዘገባ ያመለክታል። ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ በሴሪላክ ምርት ላይ የሚጨመረው ስኳር መጠን ከፍተኛ ከሆነባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ያመለክታል።የመረጃው ይፋ መሆንን ተከትሎ የአለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የተቹት ሲሆን እስካሁን ኩባንያው ያለው ነገር የለም። @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ ነገ ድምፅ ይሰጣል! የፀጥታው ምክር ቤት የፍልስጤምን የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባልነት ላይ ድምጽ ለመስጠት ለመጭው አርብ ቀጠሮ ይዟል።በአሁኑ ጊዜ ከ10 ተዘዋዋሪ አባላት አንዷ የሆነችው አልጄሪያ «የፍልስጤም ግዛት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል እንድትሆን» የሚል ጥያቄ አቅርባለች።የአልጄሪያን ጥያቄ ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ በነገው ዕለት ድምፅ እንደሚሰጥ ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። 15 አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት ነገ ዓርብ ከጠዋቱ 3 ሰአት ላይ፤«የፍልስጤም ግዛት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሆና እንድትገባ”በቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምፅ ይሰጣል ሲል ሮይተርስ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ዘግቧል። እንደ ሮይተርስ ዘገባ የምክር ቤቱ ውሳኔ ቢያንስ ዘጠኝ የድጋፍ ድምጽ የሚያስፈልገው ሲሆን ፤እርምጃው እስከ 13 የምክር ቤት አባላት ድጋፍ ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።ይህም ሀሳቡን በመቃወም ዩኤስ አሜሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንድትጠቀም ያስገድዳል ሲል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል። [DW] @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 26 5
Photo unavailableShow in Telegram
ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ! የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ መፍቀዱ ተሰምቷል፡፡ የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ከትናንት በስቲያ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሒሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ሴኪዩሪቲዎች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለችሎቱ ማቅረቡን ዳጉ ጆርናል ከፋና ዘገባ ተመልክቷል። በዚህ መነሻ መሰረትም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው፤ ይሁን እንጂ ወንጀል አለመፈጸማቸውን አስረድተዋል።ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ፈቅዷል። @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 51😁 23👏 12👀 8 4👎 2🔥 1
የዉጪ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ከነዳጅ በስተቀር በሁሉም የንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ ተፈቀደ! መሰረታቸውን በዉጪ ያደረጉ ባለሃብቶች በችርቻሮ እና በጅምላ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ፍቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ አስታውቀዋል። ከጅምላ ንግድ ጋር ተያይዞ ከማዳበሪያና ከነዳጅ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይችላሉ ተብሏል በዚህም በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላከ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ነዉ የተፈቀደው ። ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች አሁን ደግሞ ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ መደረጉ ነዉ ለማወቅ የተቻለው። Via Capital @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 30😁 12👎 6 2 2
የኮሌራ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ በ8 ክልሎች የሚገኙ ከ41 ሺህ በላይ ዜጎችን ማጥቃቱን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ፡፡ ከፍተኛ ረሃብ እና በሽታ የብዙ ኢትጵያዊያንን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል፡፡የትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች በኢትዮጵያ በተከሰተዉ ጦርነት ምክንያት ከባድ ቀዉስን ያስተናገዱ ናቸዉ፡፡ በእነዚህ ክልሎችም የጤና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እና መሰረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ አልያም በከፊል መዉደማቸዉንም ነዉ ድርጅቱ የገለጸዉ፡፡በኢትዮጵያ 20ኛወሩን ያስቆጠረዉ የኮሌራ ወረርሺኝ 41ሺህ ዜጎችን ያጠቃ እና በ8ወረዳዎች የተከሰተ መሆኑንም ድርጅቱ አስታዉቋል፡፡ የአሁኑ የኮሌራ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛዉ መሆኑን ነዉ ዶ/ር ቴዎድሮስ የተናገሩት፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በወባ ወረርሺኝ 1.1 ሚሊየን ዜጎች መያዛቸዉን አንስተዉ ፤ ባለፈዉ ዓመት ከተመዘገበዉ 4 ሚሊየን ቁጥር አሁን ላይ መቀነሱን ነዉ ያስታወቁት፡፡ በዚህኛዉ ዓመት ብቻ ከ1መቶ በላይ በሚሆኑ አከባቢዎች ከ15ሺህ በላይ ሰዎች በኩፍኝ ወረርሺኝ መያዛቸዉንም አንስተዋል፡፡እነዚህ ችግሮች እየተከሰቱ ያሉት ሚሊየኖች መሰረታዊ የሆነ የህክምና አገልግሎት በሚፈልጉባቸዉ ቦታዎች መሆኑንም ነዉ የገለጹት፡፡ [Ethio FM] @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 15 2
Photo unavailableShow in Telegram
“አንድ ቢሊዮን ዶላር እስክናገኝ ጥሪያችንን እንቀጥላለን” - ዩኤንኦቻ በመጪዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ፣ በኢትዮጵያ የነፍስ አድን ርዳታ ለማቅረብ አንድ ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ ያስታወቀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ለዚሁ ዓላማ ትላንት ማክሰኞ፣ በስዊዘርላንድ - ጄኔቫ በተካሔደ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት፣ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተስፋ ቃል መገባቱን ገለጸ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ወይም በምኅጻሩ ዩኤን-ኦቻ ምክትል ቃለ አቀባይ ጀንስ ላርክ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ከጄኔቫ በሰጡት የስልክ ቃለ መጠይቅ፣ ገቢው የተገኘው ከ20 ለጋሾች መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡ አስቸኳይ ርዳታ የሚያስፈልገው አንድ ቢሊዮን ዶላር እስኪገኝ ድረስም ጥሪ ማቅረባችንን እንቀጥላለን፤ ብለዋል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👎 19👍 13 5😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ወደ ህንድ በትሬኒንግ አማካኝነት ይጓዙ። - Training to India - Work experience 0 years and plus - Both trip tickets is full covered Room and food covered - Daily payment call us on 0946488251 ወይም 0919492435 ይደውሉ
نمایش همه...
👍 11👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
🎉አስደሳች ዜና ለወላጆች🎉          📚Ace Tutors📚     በማንኛውም የት/ት ደረጃ ለሚገኙ ልጆችዎ ብቁ የሆኑ አስጠኚዎች አዘጋጅተናል - ለብሄራዊ እና ለት/ቤት ፈተና እናዘጋጃለን - ብቁ በሆኑ ወንድ እና ሴት አስጠኚዎች - ለሁሉም የት/ት ደረጃ ከ Kg - 12ተኛ ክፍል ለበለጠ መረጃ ☎️በ0943909174 ይደውሉ @acetutorshr @acetutorshr
نمایش همه...
👍 5 2
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ መስጠት እና እድሳት አገልግሎት በቀጣዩ ሳምንት ዳግም ይጀመራል ተባለ! በአዲስ አበባ ከተማ ከአንድ ሳምንት በላይ ተቋርጦ የቆየውን የመታወቂያ መስጠት እና እድሳት አገልግሎትን በሚቀጥለው ሳምንት ለመጀመር የጥገና ስራ እያከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገለጸ። ኤጀንሲ ይሰጣቸው የነበሩ መደበኛ አገልግሎቶች የተቋረጡት፤ ከመረጃ ማከማቻ ቋቱ ጋር በተገናኙ “የቴሌኮም ኬብሎች” ላይ ጉዳት በመድረሱ መሆኑን ገልጿል። በአዲስ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ፤ የመታወቂያ ስርጭት፣ የልደት እና የሞት ምዝገባ፣ ያላገባ የምስክር ወረቀት፣ የማስረጃ የማረጋገጥ ስራን እንዲሁም የጋብቻ እና የፍቺ ምዝገባን የሚከውን ተቋም ነው። ኤጀንሲው በመዲናዋ የሚገኙ 106 ወረዳዎችን “በዲጂታል” ስርዓት” በማስተሳሰር ይሰጣቸው የነበሩ አገልግሎቶች፤ ካለፈው አንድ ሳምንት ወዲህ በመቋረጣቸው በተገልጋዮች ላይ መጉላላትን አስከትሏል። በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት የሚገኝ የነዋሪነት ምዝገባ ጽህፈት ቤትን በትላንትናው ዕለት በአካል ተገኝቶ የተመለከተው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ፤ ለወትሮ በሰው ብዛት ይጨናነቅ የነበረው አገልግሎት መስጪያ ባዶ መሆኑን ታዝቧል። አገልግሎት መቋረጡን ባለመስማት ወደ ጽህፈት ቤቱ የመጡ ሁለት ነዋሪዎችም እምብዛም ሳይቆዩ መመለሳቸውንም ተመልክቷል። [Ethiopia Insider] @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 33 4👏 1😁 1
አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት ኢራን ላይ ማዕቀብ ለመጣል ዝግጅት ጀመሩ! ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ኅብረት፤ እስራኤል ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ኢራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል እየተሰናዱ ነው።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ጃኔት የለን “በሚቀጥሉት ቀናት” እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊስ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ደግሞ ኅብረቱ ማዕቅብ ለመጣል እየሠራ መሆኑን ገልጠዋል።እስራኤል አጋሮቿ የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ጠይቃለች። የተባበሩት መንግሥታት የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ላይ የጣለው ማዕቀብ ባለፈው ጥቅምት ጊዜው አብቅቷል።እኒህ ማዕቀቦች የሚጣሉት የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ለመግታት ነው የሚሉ ሐሳቦች ከፖለቲካ ተንታተኖች ዘንድ ይሰማሉ።አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ኢራን ላይ የተለያዩ ማዕቀቦች ከዚህ ቀደም መጣላቸው አይዘነጋም።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሌተናንት ጄኔራል ሄርዚ ሀሌቪ ባለፈው ሰኞ በሰጡት አስተያየት ኢራን ያደረሰችው ጥቃት ምላሽ ሳያገኝ አያልፍም የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር። ኢራን ባለፈው ቅዳሜ ለመጀመሪያ ጊዜ እስራኤል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ባደረሰችበት ወቅት 300 ሚሳዔሎችና ድሮኖች ከራሷ ክልል፣ ከኢራቅ፣ ሶሪያ እና የመን አስወንጭፋለች።አብዛኛዎቹ ሚሳዔሎች እና ድሮኖች በእስራኤል እና አጋሮቿ ዒላማቸውን ሳይመቱ እንዲከሽፉ ተደርገዋል።ቴህራን እንዳለችው ጥቃቱን የሰነዘረችው እስራኤል፤ ሶሪያ በሚገኘው ቆንስላዋ ላይ ጥቃት አድርሳ 13 ሰዎችን ለገደለችበት ጥቃት አፀፋውን ለመመለስ ነው። እስራኤል ለደረሰባት ጥቃት እስካሁን ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠችም። በምትኩ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኢራንን ለማሽመድመድ እየሠራች ትገኛለች።እስራኤል 30 የሚሆኑ አጋር ሀገሮች የኢራን የሚሳዔል ፕሮገራም ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ጠይቃለች።አልፎም እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ [ኢስላሚክ ሪቮሎሺናሪ ጋርድ ኮር] የተባለው የኢራን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ኃይል ሽብርተኛ ተብሎ እንዲፈረጅ ጠይቃለች። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ቡድኑን ሽብርተኛ ብትልም ዩኬ ይህን ከማድረግ ተቆጥባለች። ማክሰኞ ዕለት ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሚኒስትር የለን “በሚቀጥሉት ቀናት ኢራን ላይ ማዕቀብ እንደምንጥል ይጠበቃል” ብለዋል።ሚኒስትሯ አክለው ኢራን ወደ ውጭ የምትልከው ነዳጅ “ምናልባት የምናየው ይሆናል” ካሉ በኋላ “ኢራንም አሁንም በግልፅ ነዳጅ እየሸጠች ነው፤ ስለዚህ ጉዳይ የምናደርገው ነገር ይኖራል” ሲሉ ማዕቀቡ ምን ላይ እንደሚያተኩር ጠቁመዋል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 61👎 39 5
«ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ህወሓት ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል» ሲል የአማራ ክልል መግለጫ ሰጠ! ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡ ጀንበር ጠልቃ በወጣች ቁጥር ከጦርነት ውጭ ማሰብ የማይችለው የህወሓት ቡድን ከዉጭ እና ከዉስጥ ጠላቶቻችን ጋር ተናቦና ተቀናጅቶ በእርካሽ ፖለቲካዊ ብያኔና ፍረጃ በጊዜያዊ አሥተዳደሩ ካቢኔ አማካኝነት መጋቢት 16/2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት የሆነውን የህወሓት ቡድን ባለፉት ሦስት ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡ ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈፀም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈፀመባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች ስቃይ በተሞላበት ችግር ውስጥም ሆነው በወቅቱ ለነበረው መንግሥት የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መሆኑ በበርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች የተረጋገጥ ጉዳይ ነው፡፡ ተቸንካሪነት ዋና መለያ የሆነው የህወሓት የጥፋት ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመውን አሰቃቂና ታሪክ ምንጊዜም የማይዘነጋው የባንዳነት ተግባር ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት በመላ ኢትዮጵያዊያን እና በጀግኖች የፀጥታ ኀይሎች አማካኝነት የሽንፈት ፅዋን ከመጎንጨቱ ባሻገር የማንነትና የራስ አሥተዳደር ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት ችለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ ያልተመቸው ተቸንካሪው የህወሓት ቡድን በሦስት ዙሮች ከተደረገው ጦርነት ማግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡አሁንም እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የአማራ ክልል መንግሥት ይህን መሰሉን የህወሓትና የግብረ አበሮቹን ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በማክበር በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ እየጠየቅን ይህ የማይሆን ከሆነ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመሆን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል የምንገደድ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ የተከበራችሁ በክልላችን በየደረጃው ያላችሁ የፖለቲካና የጸጥታ መዋቅር አባላት፡- ከሰሜን ዕዝ ጥቃት በኋላ ትህነግ በቀሰቀሰው ጦርነት ሕዝባችን ቀጥተኛ ተጠቂ በመሆኑ ምክንያት ለበርካታ ችግሮች ተዳርጎ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በየደረጃው የሚገኙ የመዋቅር አባላት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ጥምር የጸጥታ ኃይሎችና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሀገር አፍራሽ የጥፋት ኀይሉ ላይ የተቀዳጀው ድል ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ ዛሬም እንደ ትናንንቱ በፅናትና በቁርጠኝነት ሕዝቡን በማደራጀት አካባቢያችሁን በመጠበቅ ታሪካዊ ኀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የተከበርከው የክልላችን ሕዝብ፡- በተደጋጋሚ ጥቃት የፈፀመብህ የጥፋት ኀይል ዛሬም እንደ ትናንቱ ወረራ ፈፅሟል፡፡ በመሆኑም መላ የክልላችን ሕዝብ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ሠርጎ ገቦች ራስህን በመጠበቅ ከክልል መንግሥትና በየአካባቢው ከሚገኙ አሥተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቻችን የከፈቱብንን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የድርሻህን እንድትወጣ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት፡- የፌደራል መንግሥት ህወሓት የቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ ማድረጉን ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተደረገውን ጥረት በሙሉ ልብ በመደገፍ ለውጤታማነቱ የድርሻችንን ስንወጣ ቆይተናል፡፡ ሆኖም ግን ህወሓት በተደጋጋሚ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሲያፈርስ ቆይቷል፡፡ አሁንም በሙሉ አቅሙ ወደ ጦርነት ገብቷል፡፡ ይህን እኩይ ድርጊቱን የአፍሪካ ሕብረትና የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በቦታው ተገኝተው አረጋግጠዋል፡፡በመሆኑም ይህን እብሪተኛ ቡድን በአጭር ጊዜ ከወረራቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ሕዝባችንን ከጥፋት መታደግና የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር ይገባል፡፡ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ህወሓት ከምስረታዉ ጀምሮ ለአማራ ሕዝብ ባለው ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት በአማራ ሕዝብና በመላ ሀገሪቱ ሕዝብ ላይ የማያባራ ደም አፋሳሽ ጦርነትን ሲቀሰቅስ ኖሯል፡፡ ለዚህም ነው ህወሓት የኢትዮጵያም ሆነ የአፍሪካ ቀንድ አለመረጋት ምንጭ ነው የምንለው፡፡ ሆኖም በአሳሳች የፕሮፖጋንዳ ሥራዎቹ ምክንያት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተደጋጋሚ በህወሓት ጉዳይ ላይ የተሳሳተ አቋም ሲይዝ ተስተውሏል፡፡ ዛሬ ግን ለዚህ አሳሳች ፕሮፖጋንዳው ያልተመቼ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በጠራራ ጸሐይ የአፍሪካ ሕብረትና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ወቅት ወረራ መፈጸሙ በገሃድ ታይቷል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ቀደም እንዳደረገው በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ማወናበድ አይችልም፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ህወሓት የፈጸመብንን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝና ከጎናችን እንዲቆም የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሚያዚያ 08 /2016 ዓ‹ም ባሕር ዳር @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 57😁 29 5🔥 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶውን ማስመለስ መቻሉን አስታወቀ! የኢትዯጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚሆነውን ማስመለሱን አስታውቋል።ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተጠቀሰው ዕለት በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊዮን 417 ሺህ 747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር መገለፁ ይታወሳል። ከተወሰደው ገንዘብ 762 ሚሊዮን 941 ሺህ 341 ብር ማስመለስ መቻሉን ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 38 ሚሊዮን 474 ሺህ 938 ብር የማስመለስ ስራ እንደሚቀጥልም ባንኩ ገልጿል። @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
😁 25👍 14👎 5
Photo unavailableShow in Telegram
🎉አስደሳች ዜና ለወላጆች🎉          📚Ace Tutors📚     በማንኛውም የት/ት ደረጃ ለሚገኙ ልጆችዎ ብቁ የሆኑ አስጠኚዎች አዘጋጅተናል - ለብሄራዊ እና ለት/ቤት ፈተና እናዘጋጃለን - ብቁ በሆኑ ወንድ እና ሴት አስጠኚዎች - ለሁሉም የት/ት ደረጃ ከ Kg - 12ተኛ ክፍል ለበለጠ መረጃ ☎️በ0943909174 ይደውሉ @acetutorshr @acetutorshr
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ወደ ህንድ በትሬኒንግ አማካኝነት ይጓዙ። - Training to India - Work experience 0 years and plus - Both trip tickets is full covered Room and food covered - Daily payment call us on 0946488251 ወይም 0919492435 ይደውሉ
نمایش همه...
👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ? ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential Customers) እንዲደርስስ? -ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤ -በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤ -በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን። ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ። ቴሌግራም፡ @adsommar ስልክ፡ 0954260423
نمایش همه...
👍 13 1
00:10
Video unavailableShow in Telegram
⚡️ማስጠንቀቂያ! ቪዲዮውን ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች እንዲያዩት አንመክርም። በሲድኒ፣ አውስትራሊያ የሚገኝ አንድ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ እያለ አንድ ቢላዋ የያዘ ሰው በአንድ ቄስ ላይ በትናንትናው ዕለት ጥቃት ሰነዘረ። ይሄ ሰው በዋኪሊ በሚገኘው የደጉ እረኛ ቤተክርስቲያን ቀርቦ ጳጳስ ማሪ ኢማኑኤልን ደጋግሞ በስለት ወግቷቸዋል። ጥቃት አድራሹ ቄሱን ለመዳን የሞከሩ አራት ምእመናን ላይም ጥቃት ፈፅሟል። ቄስ ማሪ ኢማኑኤል ጉዳት ቢያጋጥማቸውም ከመሞት ተርፈዋል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይሄ ሰው ከአንድ ቀን አስቀድሞ አንድ ሰው በሲድኒ የገበያ ማእከል ውስጥ ገሎ መሰወሩም ተነግሯል።
نمایش همه...
😭 115👍 37👀 7 6
Photo unavailableShow in Telegram
ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለማዛወር እንግሊዝ የነደፈችው ረቂቅ ሕግ ሊጸድቅ ነው! ብሪታንያ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን ተቃርቧል። የዕቅዱ ተቃዋሚዎች በአንጻሩ ስደተኞቹን በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት ጥረት ይዘዋል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና በላይኛው ምክር የቀረበውን ተቃውሞ ለመቋቋም የታለመው ይህ ሕግ በያዝነው ሳምንት በሃገሪቱ ፓርላማ ይድቃል ተብሎ ተጠብቋል። ‘የሩዋንዳ ዕቅድ’ የሚል ቅጽል የተሰጠው ይህ ውጥን ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ‘ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደዚያች አገር የሚያጓጉዙ ጀልባዎች እንቅስቃሴ’ ለማስቆም ለገቡት ቃል ‘ወሳኝ እርምጃ ነው’ ተብሏል። ጉዳዩን አመልክቶ አስተያየት የሰጡት የሱናክ ቃል አቀባይ ዴቭ ፓሬስ ትናንት ሲናገሩ "የእንግሊዝ ፓርላማ በያዝነው ሳምንት በሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ከፍተኛ እንግልት እና ብዝበዛ የሚፈጽምባቸውን ሰዎች ህይወት የሚታደግ ህግ የማጽደቅ እድል ያገኛል" ብለዋል ። “አሁን ባለው አካሄድ መቀጠል እንደማንችል ግልፅ ነው። በመሆኑም ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜው አሁን ነው” ሲሉም አክለዋል። በአነስተኛ ጀልባዎች ተጓጉዘው የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ከዚያ የሚደርሱትን ጥገኝ ነት ጠያቂዎች ወደ ምሥራቅ አፍሪካዊቱ አገር ለማዛወር እና በቋሚነትም ኑሯቸውን ከዚያ እንዲያደርጉ በማቀድ ሁለቱ አገሮች የተፈራረሙት ስምምነት ሁለት ዓመታት አስቆጥሯል። በፍርድ ቤት የታገደው ዕቅድ እንግሊዝን በትንሹ 470 ሚሊዮን ዶላር ሊያስወጣት እንደሚችልም ተገምቷል። Via VoA @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 27😭 7 6
Photo unavailableShow in Telegram
በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2025 ዓመት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 6.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ይፋ አደረገ። IMF ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 8፤ 2016 ይፋ ያደረገው ትንበያ፤ ከዘንድሮው አኳያ ሲነጻጸር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚቀጥለው ዓመት አነስተኛ መነቃቃት እንደሚታይበት የሚጠቁም ነው። በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ6.2 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ድርጅቱ ባለፈው ዓመት ባወጣው ተመሳሳይ ትንበያ ይፋ አድርጎ ነበር። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ትንበያ የኢትዮጵያ መንግስት ከሚጠብቀው ዝቅ ያለ ነው። በኢትዮጵያ መንግስት ትንበያ መሰረት፤ በ2016 ዓ.ም. የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ7.9 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።  (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
😁 72👍 23👎 7👀 3👏 2 1🔥 1
በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምክንያት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጋቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። በዚህም መሰረት፡- •  ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ •  ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር •  ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር •  ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች ምክንያት ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ መከልከሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 25👎 3😁 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያሏት የሚሊየነሮች ቁጥር በአጠቃላይ 2,700 መድረሱን በዘርፉ ላይ የተደረገ አንድ ሪፖርት አመላከተ ኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ ወደ 2,700 የሚጠጉ ሚሊየነሮች እንዳሏት የገለፀዉ ይህ የአፍሪካ ሀብት ሪፖርት ሀገሪቷ በዚህ የስነ ህዝብ እድገት ዉስጥ ጠንካራ እንድገት እንደሚኖረዉ ትንበያውን አስቀምጧል። በ 2024 የወጣዉ የአፍሪካ ሀብት ሪፖርት ዘጠኛ እትሙ ላይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አዳዲስ ገበያዎችን የሚይዘው የአህጉሪቱ ሚሊየነር ህዝቧ በሚቀጥሉት አስርት አመታት ዉስጥ በ 65% ከፍ ሊል እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል ። አሁን ላይ በአፍሪካ ያለዉ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት ሀብት 2.5 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱ የተነገረ ሲሆን ኢትዮጵያ በዚህ ኢኮኖሚ እድገት ዉስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጓ ነዉ ይህ ሀተታ የሚያመላክተዉ። Via:- Capital @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
😁 39👍 31👀 5👎 4 3
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ 56 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ምንም አይነት ቃላት ማንበብ እንደማይችሉ አንድ ጥናት አመላከተ፡፡ የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ አደረጉት ባለዉ ዓመታዊ ጥናቱ ላይ እንደገለፀው በኢትዮጵያ 56 በመቶ የሚሆኑ የ 2ኛ እና የ 3ኛ ክፍል ተማሪዎች ምንም አይነት ቃላት ማንበብ እንደማይችሉ አረጋግጫለሁ ብሏል። የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሲያከናዉን የቆየዉን ጥናት ይፋ አድርጓል ። በዚህም ከትግራይ ክልል በስተቀር በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ 401 ትምህርት ቤቶች እና በ 16 ሺህ ተማሪዎች ላይ በተደረገ ጥናት ዉጤቱ መገኘቱን አስታዉቀዋል። ይህ ቁጥር ከባለፉት አመታት ጋር ሲነፃፀር በመጠኑ መሻሻል አሳይታል የተባለ ሲሆን ከሁለት አመት በፊት የተደረገው ጥናት ምንም ማንበብ የማይችሉት 63 በመቶዎች እንደነበሩ ጥናቱ አመላክቷል።
نمایش همه...
😁 24👍 19😭 11👎 3
Photo unavailableShow in Telegram
🎉አስደሳች ዜና ለወላጆች🎉          📚Ace Tutors📚     በማንኛውም የት/ት ደረጃ ለሚገኙ ልጆችዎ ብቁ የሆኑ አስጠኚዎች አዘጋጅተናል - ለብሄራዊ እና ለት/ቤት ፈተና እናዘጋጃለን - ብቁ በሆኑ ወንድ እና ሴት አስጠኚዎች - ለሁሉም የት/ት ደረጃ ከ Kg - 12ተኛ ክፍል ለበለጠ መረጃ ☎️በ0943909174 ይደውሉ @acetutorshr @acetutorshr
نمایش همه...
👍 11 2
Photo unavailableShow in Telegram
ወደ ህንድ በትሬኒንግ አማካኝነት ይጓዙ። - Training to India - Work experience 0 years and plus - Both trip tickets is full covered Room and food covered - Daily payment call us on 0946488251 ወይም 0919492435 ይደውሉ
نمایش همه...
👍 9 2 1👎 1
01:11
Video unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች ሆን ብለው ቻይናዊ ሯጭ እንዲያሸንፍ በማድረግ ተከሰሱ! አንድ የኢትዮጵያ እና ሁለት ኬንያውያን አትሌቶች ቻይናዊ ሯጭ የቤይጂንግ ግማሽ ማራቶንን እንዲያሸንፍ አድርገዋል ተብለው ምርመራ ተጀመረባቸው። የውድድሩ አዘጋጅ ቤይጂንግ ስፖርትስ ቢሮ ክስተቱን እየመረመርኩ ነው ሲል ለፈረንሳይ የዜና ወኪል - ኤኤፍፒ ተናግሯል። ኢትዮጵያዊው አትሌት ደጀኔ ኃይሉ ቢቂላ እንዲሁም ኬንያውያኑ ሮበርት ኬተር እና ዊሊ ማናንጋት ቻይናዊው አትሌት ሂ ጂ እንዲያሸንፍ ያደረጉበት ሁኔታን የተመለከቱ ቻይናውያን “ስፖርታዊ ሥነ ምግባር የሌለበት አሳፋሪ ተግባር” ሲሉ ገልጸውታል። ሦስቱ አትሌቶች ከውድድሩ መጀመሪያ አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ ቻይናዊውያን አትሌት አጅበው ሲሮጡ ነበር።በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት በተጋራው ቪዲዮ ላይ የውድድሩ መጨረሻ አካባቢ ሦስቱ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች ፍጥነታቸውን በመቀነስ ቻይናዊው አትሌት እንዲያልፋቸው በእጃቸው ሲጠቁሙት ይታያሉ። በመጨረሻም የመላው እስያ ጨዋታዎች የማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው ቻይናዊ አትሌት ሦስቱን የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች አስከትሎ በአንድ ሰከንድ ልዩነት ብቻ ውድድሩን አሸንፏል። የውድድሩ አዘጋጆች ለኤኤፍፒ “ምርመራ እያደረግን ነው። ምርመራችን ሲጠናቀቅ ውጤቱን ይፋ እናደርጋለን” ብሏል። @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
😁 112👍 46 13👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
ታዋቂው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑዔል በቀጥታ የሚተላለፍ ትምህርት እየሰጡ ሳሉ በስለት ተወጉ! በአውስትራሊያ ሲድኒ በቀጥታ በኢንተርኔት እየተላለፈ የነበረ መንፈሳዊ ትምህርት እየሰጡ የነበሩት አቡን እና ሌሎች ምዕመናን በስለት ተወጉ።ይህ የሆነው ዋኬሌ በሚገኘው ክራይስት ዘ ጉድ ሼፐርድ በተሰኘው ቤተ-ክርስቲያን በአውስትራሊያ ሰዓት በቆጣጠር ዛሬ ሰኞ አመሻሽ ላይ በነበረ ሥነ-ሥርዓት ነው። በስለት ጥቃት ከተፈጸመባቸው መካከል የሆኑት አቡነ ማር ማሪ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በእንግሊዝኛ በሚያርቧቸው መንፈሳዊት ትምህርቶቻቸው ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በብዙዎች ዘንድ ተደማጭ ናቸው።ጥቃቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች በስለት ተወግተዋል የሚል ሪፖርት የደረሰው ፖሊስ ወደ ሥፍራው ተሰማርቶ ሁኔታውን ያጣራ ሲሆን፣ የሰዎች ሕይወትን ለአደጋ የሚዳርግ ጉዳት አልደረሰም ብሏል። ፖሊስ አክሎ እንደገለጠው አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሎ አድራሻው ወዳልተገለጠ ሥፍራ ተወስዷል።ከጥቃቱ በኋላ በርካታ ሰዎች የተሰባሰቡ ሲሆን ቢቢሲ ያላጣራቸው የማኅበራዊ ሚድያ ቪድዮዎች እንደሚያሳዩት አንዳንድ ሰዎች በሕንፃው እና በአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መኪናዎችን ላይ ጥቃት አድርሰዋል።ሥፍራው በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠበቀ እንደሆነ የገለጠው ፖሊስ ሰዎች ወደዚያ አካባቢ እንዳይሄዱ አሳስቧል። የአካባቢው ፖሊስ ጥቃት የደረሰባቸው አቡን ስማቸው ማር ማሪ ኢማኑዔል እንደሆነ አሳውቋል። የኢስተርን ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንም ከፖሊስ ዘገባ በኋላ የሃይማኖት አባቱን ማንነት ይፋ አድርጓል።ቤተ-ክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ አባ ኢሳክ የተባሉ ቄስም ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቋል። ሁለቱም የሃይማኖት አባቶች ለሕክምና ወደ ሆስፒታል ተልከዋል። [BBC] @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
😭 71👍 31 8🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸዉ እንደ አልኮል መጠጦች ፣ ሲጋራ እና የታሸገ ዉሃ ላይ ላይ ቴምብር እንዲለጠፍ የሚያስገድደዉ መመሪያ ወጣ! የገንዘብ ሚኒስትር የኤክሳይዝ ቴምብር አስተዳዳር ስርዓትን ለመወሰን የሚያስችለውን መመሪያ ከሰሞኑ አዉጥቷል።በዚህ መመሪያዉ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸዉ እቃዎች ማለትም የአልኮል መጠጦች፤ አልኮልና እና አልኮል አልባ ቢራ፤  ሲጋራ፤ ሲጋሪልስ፤ ትምባሆ ፣ የታሸገ ውሃና ሌሎች ኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸዉ ዕቃዎች ላይ ተግበራዊ ይደርጋል። የኤክሳይዝ ቴምብር  በወረቀት፤ በዲጂታል ወይም ሚኒስቴሩ በሚወስነው መልክ የተዘጋጀና የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው እቃዎች ላይ የሚታተም ወይም የሚለጠፍ ቴምብር ማለት እንደሆነ በዝርዝር ያስቀምጣል። የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣዉ በዚህ መመሪያ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው እቃዎች አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ተሳታፊ የሆነ ማናቸውም ላኪ በእጁ የሚገኙትን የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው እና የኤክሳይዝ ቴምብር ያልተለጠፈባቸው ወይም ምልክት ያልተደረገባቸዉን ዕቃዎችን ለገበያ ማዋል አይችልም። [Capital] @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 27 2
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ የሚታየው የኤሌክትሪክ ሀይል እጥረት የተፈራረምኩትን ስምምነት በድጋሚ እንዳጤነው እየገፋፋኝ ነው ስትል ኬንያ ገለጸች! ኬንያ ከሁለት አመት በፊት ከኢትዮጵያ ጋር ለ25 አመታት የሚቆይ በኤሌክትሪክ ሽያጭ ዙሪያ የተፈራረምኩትን ስምምነት እንደገና ላጤነው ተገድጃለሁ ስትል ገለጸች። ለዚህም እንደምክንያትነት የጠቀሰችው በኢትዮጵያ ያለው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር እየተባባሰ በመሆኑ እና ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ስለሚገኝ፣ ለእኔ በሚቀርበው የኤሌክትሪክ ሀይል ላይ ችግር መፍጠሩ አይቀርም በሚል ስጋት ስላደረብኝ ነው ብላለች። የኬንያ የኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ሃላፊ ዳንኤል ኪፕቶ እንደገለጹለት ስምምነታችንን በመከለስ በቋሚነት ሊቀርብልን ስለሚችለው የሀይል መጠን መፈራረም አለብን፣ እስካሁን የሚቀርብልን የኤሌክትሪክ ሀይል አነስተኛ ነው ሲሉ መናገራቸውም ተካቷል። Via Addis Standard @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 56😁 23 2👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል “ትክክለኛው ሰዓት ላይ” ለኢራን ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እሰጣለሁ አለች! እስራኤል ልክ እንደ ኢራን ሁሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎችን በመተኮስ ‘ትክክለኛው ሰዓት ላይ’ የበቀል እርምጃ እውስዳለሁ አለች።ዓለም አቀፉ ማሕብረሰብ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ከሚያባብስ እርምጃ እንዲቆጠቡ አገራት ቢያሳስቡም እስራኤል ግን ትክክል ሆኖ ሳገኘው የአጸፋ እርምጃ እውስዳለሁ ብላለች። ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል ላይ በፈጸመችው ቀጥተኛ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከ300 በላይ ሚሳኤል እና ድሮኖች ወደ እስራኤል ማስወንጨፏ ይታወሳል።ከ300 በላይ የሚሆኑት ሚሳኤሎች እና ድሮኖች ከኢራን፣ ኢራቅ እና ከየመን ወደ እስራኤል የተተኮሱ ቢሆንም አብዛኞቹ ጉዳት ሳያደርሱ በእስራኤል፣ በአሜሪካ እና በወዳጆቿ አማካይነት እንዲከሽፉ ተደርገዋል። ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን በማምከን ድጋፍ ስታደርግ የነበረችው አሜሪካ እስራኤል የበቀል እርምጃ ብትወስድ ተሳታፊ አልሆንም ስትል አስታውቃለች።አምስት አባላት ያሉት የእስራኤል የጦር ካቢኔ እና የአገሪቱ ፓርላማ አባል ቤኒ ጋንትዝ ትክክለኛው ሰዓት ላይ ኢራን ለፈጸመችው ተግባር እስራኤል ዋጋ ታስከፍላታለች ብለዋል። [BBC] @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 74👎 19 4😁 4
Photo unavailableShow in Telegram
Only 3 days left to apply for the Jimma, Mekelle, and Sheger City Startup Incubation Program. Empower your startup with: • Tailored trainings • Expert consultations • Funding opportunities ( USD2000 Grant and uncollateralized loan) • Investment readiness guidance Don't miss out! Apply now! Link : https://forms.gle/FDYJDrN2zfAdoh4FA #seed #incubation #StartupEthiopia
نمایش همه...
👍 6 3
Photo unavailableShow in Telegram
ከአዲስ አበባ ወደ አርባምንጭ ቤት ለቤት ይላኩ ይቀበሉ። በአዲስ ኤክስፕረስ ይላኩ ይቀበሉ። ዛሬ ከአዲስ አበባ ይላኩ ነገ አርባምንጭ ይቀበሉ። ፓስታዎች የመኪና ስፔር ፓርቶች የጨረታ ሰነዶች አዲስ ኤክስፕረስ የችግሮ መላ 0980526262 አዲስ አበባ 0988627762 አርባምንጭ
نمایش همه...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
🎉አስደሳች ዜና ለወላጆች🎉          📚Ace Tutors📚     በማንኛውም የት/ት ደረጃ ለሚገኙ ልጆችዎ ብቁ የሆኑ አስጠኚዎች አዘጋጅተናል - ለብሄራዊ እና ለት/ቤት ፈተና እናዘጋጃለን - ብቁ በሆኑ ወንድ እና ሴት አስጠኚዎች - ለሁሉም የት/ት ደረጃ ከ Kg - 12ተኛ ክፍል ለበለጠ መረጃ ☎️በ0943909174 ይደውሉ @acetutorshr @acetutorshr
نمایش همه...
👍 5 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
Only 3 days left to apply for the Jimma, Mekelle, and Sheger City Startup Incubation Program. Empower your startup with: • Tailored trainings • Expert consultations • Funding opportunities ( USD2000 Grant and uncollateralized loan) • Investment readiness guidance Don't miss out! Apply now! Link : https://forms.gle/FDYJDrN2zfAdoh4FA #seed #incubation #StartupEthiopia
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
አቶ አብነት ገብረመስቀል በቦሌ ታወርስ ላይ ያላቸውን ድርሻ ለቀው እንዲወጡ ተፈረደባቸው! አቶ አብነት በነሃሴ 2014 ዓም አቅርበውት በነበረው ክስ የቀድሞ የቅርብ ወዳጃቸው እና አጋራቸው የሆኑት ሼክ መሃመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ በቦሌ ታወር ያላቸውን ድርሻ ለቀው እንዲወጡ ወይም ድርጅቱ እንዲፈርስ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም፡፡ ባሳለፍነው ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2016 የዋለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ችሎት በሰጠው ውሳኔ ቦሌ ታወርስ የተባለው እና በወሎ ሰፈር አካባቢ የህንጻ ግንባታ ያለው ድርጅት እንዳይፈርስ የወሰነ ሲሆን፡፡ በተጨማሪም አቶ አብነት የሚገባቸው ድርሻ ተከፍሏቸው ከድርጅቱ ለቀው እንዲወጡ ወስኗል፡፡ቢሊየነሩ ሼክ መሃመድ በቦሌ ታወርስ ላይ የ60 በመቶ ድርሻ ያላቸው ሲሆን ቀሪው በቀድሞ አጋራቸው የተያዘ ነው፡፡ Via Capital @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 81 9😁 8👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
Are you interested in becoming an AI engineer? Join the Kifiya AI Mastery Training Program (Kifiya AIM 1) by Kifiya Financial Technology and 10 Academy. It's a 3-month intensive course beginning on April 29, 2024, focusing on Machine Learning and Data Engineering. Gain fast career advancement in AI and data science through industry-led projects, expert sessions, and explore fintech career opportunities in Addis Ababa, Ethiopia. Special consideration for women and vulnerable groups. Eligibility criteria: - Undergraduates (preferred) aged 22-34 - Has legal right to work in Ethiopia. - Fluent in English (B1 CEFR level), with some background in Python, SQL, and Statistics. - Ready to commit 30-40 hours weekly, with a strong work ethic and community spirit. Submit your application by the deadline of April 17, 2024. Application link: https://apply.10academy.org/login Learn more about the program: https://10academy.org/kifiya/learn-more For any question, contact us at [email protected]
نمایش همه...
👍 17 7👎 2
Register Here
ኢራን በእስራኤል ላይ የምትሰነዝረውን ጥቃት መጀመሯን አስታወቀች! ኢራን ወደ እስራኤል በርካታ ቁጥር ያላቸው ድሮኖችን እና ሚሳዔሎችን መተኮሷን አስታወቀች።እስራኤል ባሳለፍነው ሳምንት በሶሪያ መዲና ደማስቆ በሚገኝ የኢራን ኢምባሲ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ ዘጠኝ ኢራናዊያ መገደላቸው ይታወሳል።ይህንን ተከትሎ በኢምባሲዋ ላይ ለደረሰው ጥቃት እስራኤልን እንደምትበቀል ስትዝት የቆየችው ኢራን በዛሬው እለት መጠነ ሰፊ የድሮን እና ሚሳዔል ጥቃተ ወደ ቴልአቪቭ መክፈቷን አስታውቃለች። የኢራን ሪቮሉሽናሪ ጋርድ ዛሬ ምሽት በሰጠው መግለጫው፤ ወደ እስራኤል ድንበር በርካታ ሚሳዔሎችን እና ድሮኖችን መተኮሱን አስታውቋል።እስራኤል በበኩሏ በርካታ ድሮኖች ከኢራን መተኮሳቸውን ያረጋገጠች ሲሆን፤ ሚሳዔል ስለመተኮሱ ግን እስካሁን ማረጋገጫ አላገኘሁም ብላለች።የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ በሰጡት አስተያየት፤ ኢራን ወደ የተኮሰቻቸው ድሮኖች የእስራኤል ድንበር ላይ ለመድረስ ሰዓታት ይፈጃሉ ብለዋል። ኢራን ወደ እስራኤል ድሮኖችን እና ሚሳዔሎችን እንደተኮሰች ማሳወቋን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁኔታ በፍጥነት እየተቀያየረ ሲሆን፤ መንግስታትም የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛል።ጆርዳን፣ ሊባኖስ እና ኢራቅ የአየር ክልላቸውን መዝጋታቸውን ያስታወቁ ሲሆን፤ እነዚህ ሶስቱ ሀገራት የኢራን ድሮኖች እና ሚሳዔሎች ሊያልፉባቸው የሚችሉ ናቸው ተብሏል።ኢራን እና እስራኤልም ከወታደራዊ አውሮፕላኖች በስተቀር ለሌሎች አውሮፕላኖች የአየር ክልላቸውን መዝጋታቸው ነው እየተነገረ ያለው። ኢራን በእስራኤል ላይ የአየር ወለድ ጥቃትን መጀመሯን የአሜሪካው ነጩ ቤተ መንግስት ወይም ዋይት ሀውስ አስታውቋል።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በብሔራዊ ደህንነት ቡድናቸው አማካኝነት ስለሁኔታው በመደበኛነት እየተከታተሉ መሆኑም ተነግሯል።ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ቡድናቸው ከእስራኤል ባለስልጣናት ጋር በተደጋጋሚ ግንኙነቶችን እያደረጉ እየተወያዩ መሆኑን ዋይት ሃውስ አስታውቋል።አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ኃይል መላኳም ይታወሳል። [Al Ain] @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 53😁 7🔥 3👎 2 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም፣ ቆንጆ ፉድስ ነን!😏 ✅የኢትዮጲያ ባህላዊ ምግቦች በሚገባቸው ክብር እና ደረጃ በማቀናበር ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ቆርጠን ተነስተናል። እርስዎም ይህንን መጠይቅ በመሙላት የሚወዷቸውን ኢትዮጲያዊ ጣዕሞችን በመላው በዓለም ያገኟቸው ዘንድ የበኩልዎን አስተዋፅዎ እንዲወጡ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። 👏ለሚያደርጉት አስተዋፅዎ ያዘጋጀነውን የምስጋና ሽልማት ለመቀበል ስልክ ቁጥሮን መተው እዳይረሱ፣ እናመሰግናለን። የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ወደ ፎርሙ ይግቡ👇👇 https://forms.gle/dZ9qwg2L3bJsX9NR7
نمایش همه...
👍 17 2
በዛሬው ዕለት ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ! በ3ኛው ምዕራፍ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሳኡዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ስራ እየተከናወነ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 71 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል። በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 71 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ዘጠኙ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 20 6