cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

YeneTube

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

نمایش بیشتر
Advertising posts
129 672مشترکین
+28024 ساعت
+1 0117 روز
+2 18230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች እንደአዲስ ሊዋቀሩ ነው ተባለ! በቅርብ ጊዜያት በርካታ ቅሬታዎችን ያስተናገደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉምሩክ የስራ ክፍል፤ ሰራተኞች በአዲስ መልክ እንደሚደራጁ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በ2016 ስምንት ወራት ውስጥ 49 የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከፍተኛ አመራሮች ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል። ኮሚሽኑ በሰራተኝኞቹ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለመቅረፍ "ረጅም ጊዜ" የወሰደ ጥናት መካሄዱ ታውቋል።በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞን ለመቀየር፣ ለማሸጋሸግ እና በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል። በመጋቢት መጀመሪያ "በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ አሉባልታዎችና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ከእውነት የራቁ ናቸው" በማለት የብሔራዊ የአየር ትራንስፖርት ፋሲሊቲ ኮሚቴ መግለጫ ቢሰጥም አየር መንገዱ በበኩሉ በቅሬታዎቹ ላይ ምርመራ መጀመሩ አይዘነጋም። @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
በድሬዳዋ ከተማ ትናንት መጋቢት 18 ማታ አካባቢ ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ በከተማዋ ድንገተኛ ጎርፍ ተከስቶ የንብረት ጉዳት ደርሷል። ለጉልት ገበያ ሲያገለግሉ የነበሩ በሸራ የተሰሩ ቤቶች በጎርፉ ተወስደዋል። እስካሁን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም። የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል የዝናቡ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ድንገተኛ ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል ብሏል።
نمایش همه...
👍 13👀 2👏 1
የአማራ ክልል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለአገሪቱ ቋሚ የቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ ሲል አስጠነቀቀ፡፡ የአማራ ክልል የትግራይ ክልል ግዜያዊ አሥተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ ሲል ያስጠነቀቀው ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነው፡፡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የአማራ ክልል ተማሪዎች መፃህፍትን ምክንያት በማድርገ ጠብ አጫሪ የሆነ መግለጫ ያስታወሰው የአማራ ክልል፣ጊዜያዊ አስተዳደሩ አውጥቶት የነበረው መግለጫ ‹‹አሳሳችና ጠብ አጫሪ ፍላጎት የተሸከመ ነው›› ብሏል፡፡ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መግለጫውን ከወጣ ከሦስት ቀናት በኋላ ማለትም መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደልና በማሰቃየት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ በመማሪያ መፃህፍቶቹ ተካተዋል የተባሉ አካባቢዎች ካለፉት 30 አመታት በፊት ጀምሮ የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎች ሲቀርቡባቸው የነበሩ መሆናቸውንም አክሏል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት በእነዚህ አካባቢዎች የተማሪዎች የመማር መብት እንዲከበር ግዴታውን መወጣቱን ሰበብ አድርጎ የወጣ ነው ያለው የጊዜያዊ አስተዳደሩን መግለጫ፣ ድርጊቱ የሚያሳየው ከድርብርብ ውድቀቶቹ ትምህርት አለመውሰዱን ነው ሲል አጣጥሎታል፡፡ በአገሪቱ እነዲሁም በሁለቱ ክልሎች መካከል ቀውስ ከሚፈጥሩ ተግባራት በመቆጠብ ‹‹ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣ›› አሳስቦ፣ ለዘላቂ ሠላምና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር አሳስቧል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 8😁 5 1😭 1
ዜጎች የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ በኦንላይን ተመዝግበው ባሉበት እንዲመጣላቸው የሚያስችል አገልግሎት ተጀመረ ብሔራዊ መታወቂያ ካርድን በኦንላይን ተመዝግቦ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ካርዱን ካሉበት ሆነው በማዘዝ ባሉበት የማድረስ ሥራ መጀመሩን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ። የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ የሕትመት ሥራ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ሲከናወን የቆየ ሲሆን የብሔራዊ መታወቂያ ካርዱን ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎችም አገልግሎቱን ለማግኘት በአካል መገኘት ይኖርባቸው ነበር። አሁን ግን ዜጎች አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ የኦንላይን ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን የክፍያ ሥርዓቱም በቴሌ ብር እና በባንክ መክፈል እንደሚቻል ተጠቁሟል። የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች card-order.fayda.et ድረ ገጽ ላይ በኦንላይን መመዝገብ እንደሚችሉ ሲገለፅ ፥ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ካርዱን ባሉበት ቦታ እንዲመጣላቸው ማዘዝ ይችላሉ ተብሏል። ዜጎች ምዝገባ ከማድረጋቸው በፊት የፋይዳ ቁጥራቸውን የሚገልጽ የጽሑፍ መልዕክት በስልካቸው ስለመላኩ ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸውም ነው የተገለፀው። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
👍 29 3
በአዳባ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ! በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ኤጀርሳ ቀበሌ ትናንት ምሽት 2 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ። የምዕራብ አርሲ ዞን ትራፊክ ክፍል ሃላፊ ኮማንደር ከማል አማን እንዳሉት፤ አደጋው የደረሰው ከጉብሳ ወደ አዳባ እህል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ከባድ ተሽከርካሪ ፍሬን በጥሶ በመገልበጡ ነው። በአደጋው ሹፌሩ፣ ረዳቱን እና ከላይ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል።በሁለት ሰዎች ላይም ከባድ ጉዳት እንደደረሰ ሃላፊው ተናግረዋል። Via FBC @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👍 3😁 3😭 3
የኬንያ አየር መንገድ ከሰባት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ 80 ሚሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱ ተነገረ የኬንያ አየር መንገድ በ2018 የማስፋፊያ ፕሮጀክት በመጀመር የብድር እዳ ውስጥ ከገባ በኋላ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2023 አመት ለመጀመሪያ ጊዜ 80 ሚሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱ ተነግሯል። አየር መንገዱ 178 ሚሊዮን ሽልንግ አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱ ሲነገር ይህም በ 2022 ከነበረው አጠቃላይ ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ53 በመቶ ጭማሪ ያለው ነው ተብሏል። የተጓዦች ቁጥርም 35 በመቶ መጨመሩ ሲነገር በቀጣይ ወደ ለንደን ከተማ የበረራ አድማሱን እንደሚያሰፋ ተገልጿል። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
👍 6🔥 6
ሜልኮን የተባለ የግል ድርጅት እያስገነባ ባለዉ ህንፃ ሰራተኞች አርማታ እየሞሉ ተደርምሶ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰባቸው ትላት በደረሱ ሁለት የእሳት አደጋዎችም የአንድ ትምህርት ቤት ስድስት ክፍሎች እና አንድ ፕላስቲክ ጫማ ፋብሪካ ተቃጥለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ትላንት መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 5:55 ሰዓት ቦሌ ክፍለ -ከተማ ወረዳ 3 ቲኬ ህንፃ አካባቢ ሜልኮን የተባለ የግል ድርጅት እያስገነባ ባለዉ ህንፃ ሰራተኞች አርማታ እየሞሉ በነበረበት ሰዓት አንዱ ወለል ተደርምሶ ከተደረመሰዉ ወለል ስር የነበሩ ሁለት ሠራተኞች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናሩት ከተደረመሰዉ ወለል ስር የነበሩትን ሁለቱን ሰዎች የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፈጥነዉ በመድረስ ህይወታቸዉን መታደግ ችለዋል። ጉዳት የደረሰባቸዉን ሰዎች በኮሚሽኑ  አምቡላንስ ወደጤና ተቋም ተወሰደዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል። በአዲስ አበባ መሰል የስራ አደጋዎችን ለመከላከል አሰሪዎችና የዘርፉ ባለሞያዎች የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቀዉ እንዲሰሩ ኮሚሽኑ አሳስባል በሌላ በኩልም ትላንት በአዲስ አበባ ሁለት የእሳት አደጋዎች ደርሰዋል፡፡ @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
👍 9😭 9
በአዲስ አበባ ከተማ የደንበኞችን እንግልት ለመቀነስ  ምስልን እና ንግግርን የሚቆጣጠር ካሜራ በሁሉም ወረዳዎች እና ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ ሊሆን ነዉ! በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በወረዳዎች እና በክፍለ ከተማ ደረጃ እየተስተዋለ ያለውን የደንበኛ መጉላላት እንዲሁም ስልጣንን በመጠቀም ያልተገባ ተግባር የሚፈጽሙ ሰራተኞችን ለመቆጣጠር በ11 ክፍለ ከተማዎችና 119 ወረዳዎች የካሜራ ቁጥጥር ስራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡ በቀጣይ ከካሜራ በተጨማሪ የቃላት ንግግራቸውንም ለመስማት የሚያስችል አሰራር እንደሚገባ ይህም ምንም አይነት ያልተገባ እና ስነምግባር የጎደለው አሰራር እንዳይፈጠር የሚያደርግ መሆኑንም አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪም ለዓቅመ ደካማዎች የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን ኤጀንሲዉ ገልጿል።ጊዜው ያለፈበት ወይም የአገልግሎት ጊዜው ሊያበቃ ቀኑ የተቃረበ  የወረቀት መታወቂያ አቅመ ደካማ የሆኑ ነዋሪዎችን ቤት ለቤት በመሄድ አሻራ እና የሚያስፈልገውን መስፈርት በማሟላት አገልግሎት መስጥት እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። [ዳጉ ጆርናል] @YeneTube @FikerAssefa
نمایش همه...
👏 43😁 19👍 10 1
ጋምቤላ ከላሬ ተርፋም ተነስተው ወደ ጋምቤላ በመምጣት ላይ እያሉ ለአቦል ከተማ 10ኪሎ ሜትር ሲደርስ በታጣቂዎች በጠብመንጃ ተመቶ ይህ የህዝብ ማመላለሻ እስካሁን ሁለት ስዎች ሲሞቱ ከመጠን በላይ ሰው ስለተጎዳ ሁሉም ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ። አሁን ላይ ከተማው በጣም ውጥረት ነግሷል። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
😭 14👍 2👏 2😁 1
አሚባራ ፒሮፕርትስ /Amibara properties 👉ከ30ዓመት በላይ  ልምድ ያካበተ ድርጅት 🌟🌟""የምስራች ለ ቤት ፈላጊዎች """ አሚባራ ፕሮፐርቲስ በከተማችን ውብ ገፅታ በታላላቅ ፓርኮችና ሆቴሎች ታጅቦ በመሀል ከተማ ፍልውሀ 👉ከወዳጅነት ፓርክ አጠገብ ላይ በ35,751 ካሬ ላይ እያስገነባ ያለውን መንደር ለሽያጭ አቅርበናል: 👉ባማረው መንደራችን ላይ የመዝናኛ ማእከላት መኖሪያ ነው ሆቴል ያስባሉ የኪነ ሕንፃ ጥበባት ሲሲዲ ካሜራ ሪሴፕሽን ፕሬዠራይዝድ ስቴር ዶርስ ያማሉ አፓርትመንቶችን ከባለ 1 -4መኝታ ያላቸው ለእይታ ማራኪ የሆኑ ፔንት ሀውሶችን ለመኖሪያ ምቹ በሆነ ስፍራ ቀርቧል ። ☎️ 0925776480 👉በ10% ቅድመ ክፍያ ለአጭር ጊዜ በሚቆይ የዋጋ ቅናሽ ጋር ለሽያጭ አቅርበናል። 👉ከ1.4 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ። ❇️ሸራተን ፊት ለፊት ኮምፓውንድ አፓርትመንት 35,751 ካሬ ላይ ያረፈ የመኖርያ መንደር። 🙏ግንባታቸው 50%የደረሰ ##ባለ 1 ምኝታ 101m2 &91M2 ##ባለ 2 ምኝታ 160m2 & ##ባለ 3 ምኝታ 172m2& 178m2 ##ባለ 4 ምኝታ 211m2 & 221m2 ##ፔንታወስ 👉SWIMMING POOL 👉Compounded 👉Green Area 👉GYM Room 👉POOL BAR 👉PARKING ይደውሉ 📞0925776480
نمایش همه...
👍 2🔥 1
وارد شوید و به اطلاعات مفصل دسترسی پیدا کنید

ما این گنجینه ها را پس از تأیید هویت به شما نشان خواهیم داد. ما وعده می‌دهیم که سریع است!