الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
رفتن به کانال در Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
2 151
مشترکین
-224 ساعت
+367 روز
+41730 روز
آرشیو پست ها
ቴሌግራም አዳድ ነገሮችን ስጦታወችን እና እራሳቹህ የሜትፅፏቸውን ማስታወሻ ለመያዝ ስለህነ ይቀመጡ 👑🌸💧
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
➲➢ ትላልቅ ኢስላማዊ
የቴሌግራም ቻነሎች መግዛት ይፈልጋሉ ?
🏷 7600k subscribers
🏷 9300k subscribers
👆በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ👇 አስቾካይ 2 ቻናል ብቻ ነዉ ያለን
ሰላም እና ፍቅር በአቺ ጊዜ ቀረ የኔ አለም
ድሮ ድሮ ጊዜው ደስ ይላል
ሰው ይዋደዳል አቺም ብዙ ነገር ታመጪ ነበር💧
እናተኮ ትረሷት ይሆናል 🕶🕶 ስት ብር ናት ✍️?!
ግቡ ግቡ ድርስ አለ አቡሙሀመድ ገብቷል ተከታተሉ ግቡና ሸርም አድርጉት ለሌሎቹ
https://t.me/merkez_ibnu_kesir?livestream=d1f25cd86c29718744
Repost from ነበእ የቂርአት ሴንተር
ለፍጡር ሱጁድ ማድረግ
~
ሱጁድ (ግንባርን መሬት ላይ ማሳረፍ) ለሁለት ይከፈላል። ንፁህ አምልኮታዊ ሱጁድ እና የሰላምታ (የአክብሮት) ሱጁድ።
1- አምልኮታዊ ሱጁድ:-
የአላህ ብቻ ሐቅ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦
فَاسْجُدُوا لِلَّهِ وَاعْبُدُوا
"ለአላህም ስገዱ፣ ተገዙትም።" [ነጅም፡ 62]
በተጨማሪም አላህ እንዲህ ብሏል፦
{لَا تَسۡجُدُوا۟ لِلشَّمۡسِ وَلَا لِلۡقَمَرِ وَٱسۡجُدُوا۟ لِلَّهِ ٱلَّذِی خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمۡ إِیَّاهُ تَعۡبُدُونَ}
"ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ። ይልቁንም እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደ ሆናችሁ ለእዚያ ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ።" [ፉሲለት፡ 37]
2- የሰላምታ ሱጁድ:-
ይህንንም ቢሆን ለፍጡር መስጠት እንደማይቻል የሚያሳይ ሐዲሥ አለ። ከመሆኑም ጋር ከፊል ሱፍዮች ለሸይኾቻቸው ሲፈፅሙት ይታያል። በርግጥ ቀደሞ የተፈቀደ ነበር። ለዚህም ማስረጃውም የላቀው አላህ እንዲህ ማለቱ ነው:-
{ وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَـٰۤىِٕكَةِ ٱسۡجُدُوا۟ لِـَٔادَمَ فَسَجَدُوۤا۟}
''ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ወዲያውም ሰገዱ።" [አልኢስራእ፡ 61]
እዚህ ላይ የተጠቀሰው ሱጁድ አክብሮትን መግለጫ የሰላምታ ሱጁድ ነው። ይሄ ሱጁድ የአምልኮት ሱጁድ እንዳልሆነ ኢጅማዕ አለበት። [አሕካሙል ቁርኣን፣ ኢብኑል ዐረቢ፡ 1/127] [አልፈስል፣ ኢብኑ ሐዝም፡ 2/129]
የዩሱፍ ታሪክ ላይ የተጠቀሰው የነብዩላህ ዩሱፍ ወላጆች ለዩሱፍ የወረዱት ሱጁድም ይሄው አክብሮትን መግለጫ የሰላምታ ሱጁድ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦
{إِذۡ قَالَ یُوسُفُ لِأَبِیهِ یَـٰۤأَبَتِ إِنِّی رَأَیۡتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوۡكَبࣰا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ رَأَیۡتُهُمۡ لِی سَـٰجِدِینَ}
"ዩሱፍ ለአባቱ፡- 'አባቴ ሆይ! እኔ አስራ አንድ ከዋክብትን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም (በህልሜ) አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው' ባለ ጊዜ (አስታውስ)።" [ዩሱፍ፡ 4]
ከዘመናት በኋላ ይህ ህልማቸው እውን እንደሆነ ሲገልፅ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦
{وَرَفَعَ أَبَوَیۡهِ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ وَخَرُّوا۟ لَهُۥ سُجَّدࣰاۖ وَقَالَ یَـٰۤأَبَتِ هَـٰذَا تَأۡوِیلُ رُءۡیَـٰیَ مِن قَبۡلُ قَدۡ جَعَلَهَا رَبِّی حَقࣰّاۖ}
"ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው። ለእርሱም ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት። 'አባቴ ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው። ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት።' " [ዩሱፍ፡ 100]
ይህንን ፅሁፍ ለመፃፍ ሰበብ የሆነኝ ሰሞኑን እነዚህን አንቀፆች መነሻ በማድረግ ለፍጡር ሱጁድ ማድረግ ይቻላል እያለ የፃፈ ስላየሁ ነው። የሚገርመው ሰዎች ከስር በኮመንት እየገቡ እናንተ አዋቂዎቹ ዝም ብላችሁ ነው የማንም መጫወቻ የምታደርጉት እያሉት ነበር። እንዲህ አይነት ችግር ነው የገጠመን። ቁንፅል ነገር ይይዙና መረጃዎችን በቅጡ ሳይፈትሹ፣ የዑለማእ ንግግሮችን ሳያገላብጡ አሳሳች መልእክት ያስተላልፋሉ። የራሳቸው ጥፋት አልበቃ ብሎ ሌሎችንም ያሳስታሉ። አቀራረቡ ራስን መኮፈስ፣ ሌሎችን መናቅ ሲታከልበት ደግሞ ጥፋቱ እጥፍ ድርብ ይሆናል። ቢገባቸው ይሄ አካሄድ በራሳቸውም ጥፋት፣ በሚያሳስቷቸው ሰዎችም ወንጀል እጥፍ ድርብ ተጠያቂነትን ነው የሚያስከትልባቸው።
ለማንኛውም በቀደምት ሸሪዐዎች የተፈቀደ የነበረው የሰላምታ ሱጁድ በነብዩ መሐመድ ﷺ ሸሪዐ ተሽሯል። ስለዚህ ምንም የማያጠራጥር ሐራም ነው ማለት ነው። ይህንን የሚጠቁመን ተከታዩ ዐብዱላህ ብኑ አቢ አውፋ ያስተላለፉት ሐዲሥ ነው።
ሙዓዝ (ብኑ ጀበል ረዲየላሁ ዐንሁ) ከሻም ሲመለሱ ጊዜ ለነብዩ ﷺ ሱጁድ ወረዱ።
"ምንድነው ይሄ ሙዓዝ?" አሉ።
ሙዓዝም፡ "ሻም በሄድኩኝ ጊዜ (ክርስቲያኖች) ለጳጳሶቻቸውና ለፓትሪያርኮቻቸው ሱጁድ ሲወርዱ አገኘኋቸው። እናም ይህንን ላንተ ልፈፅመው በነፍሴ ወደድኩኝ" አሉ።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ፦
فَلَا تَفْعَلُوا، فَإِنِّي لَوْ كُنْتُ آمِرًا أَحَدًا أَنْ يَسْجُدَ لِغَيْرِ اللَّهِ، لَأَمَرْتُ الْمَرْأَةَ أَنْ تَسْجُدَ لِزَوْجِهَا ...
"እንዲህ አታድርጉ። ከአላህ ሌላ ላለ ሱጁድ እንዲወርድ አንድንም የማዝዝ ቢሆን ኖሮ ሴት ለባሏ ሱጁድ እንድትወርድ አዝ ነበር። ... " [ኢብኑ ማጀህ፡ 1853]
ሐዲሡን ሸይኹል አልባኒይ - ረሒመሁላህ - "ሐሰኑን ሶሒሕ" በማለት ለማስረጃነት የሚያበቃው ጥንካሬ እንዳለው ገልፀዋል። [ሶሒሕ ኢብኒ ማጀህ፡ 1515]
ብዥታ የሚያነሳ ሰው እንዳይኖር የዑለማኦችን ንግግር ላስከትል:-
1- ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
وَأَجْمَعَ الْمُسْلِمُونَ عَلَى: أَنَّ السُّجُودَ لِغَيْرِ اللَّهِ مُحَرَّمٌ
"ከአላህ ሌላ ላለ ሱጁድ መውረድ የተከለከለ እንደሆነ ሙስሊሞች ወጥ ስምምነት አድርገዋል።" [አልመጅሙዕ፡ 4/358]
በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦
فإن نصوص السنة، وإجماع الأمة: تُحرِّم السجودَ لغير الله في شريعتنا، تحيةً أو عبادةً، كنهيه لمعاذ بن جبل أن يسجد لما قدمَ من الشام وسجدَ له سجود تحية
"የሱና መረጃዎችና የህዝበ ሙስሊሙ ወጥ ስምምነት በሸሪዐችን ውስጥ ሱጁድን ከአላህ ውጭ ለሌላ አካል ማድረግን ይከለክላሉ። ሱጁዱ ለሰላምታ (ለማክበር) ይሁን ወይም ለአምልኮም ይሁን ምንም ለውጥ የለውም። ልክ ሙዓዝ ብኑ ጀበል ከሻም ሲመጡ የደረጉትን ሱጁድ እንደከለከሏቸው። (ሙዓዝ) ያደረጉት ሱጁድ የሰላምታ ሱጁድ ነበር።" [ጃሚዑል መሳኢል፡ 1/25]
2- ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል፦
"وَهَذَا السُّجُودُ الْمَنْهِيُّ عَنْهُ : قَدِ اتَّخَذَهُ جُهَّالُ الْمُتَصَوِّفَةِ عَادَةً فِي سَمَاعِهِمْ، وَعِنْدَ دُخُولِهِمْ عَلَى مَشَايِخِهِمْ وَاسْتِغْفَارِهِمْ ، فَيُرَى الْوَاحِدُ مِنْهُمْ إِذَا أَخَذَهُ الْحَالُ ـ بِزَعْمِهِ ـ يَسْجُدُ لِلْأَقْدَامِ ، لِجَهْلِهِ ؛ سَوَاءٌ أَكَانَ لِلْقِبْلَةِ أَمْ غَيْرِهَا ، جَهَالَةً مِنْهُ ، ضَلَّ سَعْيُهُمْ وَخَابَ عَمَلُهُمْ"
"ይህ የተከለከለው ሱጁድ አላዋቂ ሱፊያዎች በዜማቸው ላይ፣ ሸይኾቻቸው ዘንድ ሲገቡ እና ምህረትን ሲለምኑ ልማድ አድርገው ይዘውታል።
ከእነሱ ውስጥ አንዱ - እንደሚሞግቱት - 'ሐሉ' ሲነሳበት ጊዜ በእግራቸው ላይ ሲወድቅ ይታያል። ይህን የሚያደርገው ባለማወቁ ነው። ወደ ቂብላ ቢዞርም ባይዞርም ያደርገዋል፤ ይህ ሁሉ ከእውቀት ማነስ የተነሳ ነው። ጥረታቸው ሁሉ ጠፋ፤ ስራቸውም ከሰረ።" [ተፍሲሩል ቁርጡቢ፡ 1/294]
https://t.me/yehak_mnged
https://t.me/yehak_mnged
⚠️ሰለፊዮች ሆይ ተውሂድ ትልቁ አላማችሁና ጭንቀታችሁ ይሁን!!
🍃 ሰለፊይ ወንድሞቼ ሆይ! ተውሂድን ትልቁ ዓላማችሁ፣ ዋነኛ ጭንቀታችሁና ከምንም በላይ የሚሰቀል አርማችሁ አድርጉት። ማንኛውም ሌላ ጉዳይ ከተውሂድ ጋር እንዲፎካከር ወይም ልቦችን ከእሱ እንዲያርቅ በፍጹም አትፍቀዱ። ተውሂድ የመሠረቶች መሠረት፣ የዲኑ መቆሚያና አላህ (سبحانه وتعالى) መልክተኞችን የላከበት፣ መጻሕፍትን ያወረደበትና የጀነትና የእሳት ሰዎች
የተለዩበት ታላቁ ሐቅ ነውና።
🍃 ተውሂድ የዲን አንዱ ክፍል ብቻ ሳይሆን፤ በሮች የሚከፈቱበት፣ ሥራዎች የሚመዘኑበት፣ ዒባዳዎች ተቀባይነት
የሚያገኙበትና ነጃ መውጫው ዲኑ ራሱ ነው። መሠረቱ (አስሉ) ካመረ ዘርፉ (ፈሩኡ) ያምራል፤ መሠረቱ ከተናወጠ ግን በሰዎች ዓይን የቱንም ያህል ጠንካራ ቢመስልም ሕንጻው ይፈርሳል። አላህን (سبحانه وتعالى) የማላቅ ሐቅ በሌለበት ጥሪ ውስጥ ምንም ዓይነት በረካ የለም።
🍃 በትናንሽና በዳርቻ ንትርኮች ውስጥ እንዳትሰጥሙ፣ ወይም ዕድሜያችሁን ከታላቁ ዓላማ በሚያርቁ ጉዳዮች እንዳታባክኑ ተጠንቀቁ። ሸይጣን ለሰው ልጅ ብዙ የክርክር በሮችን የሚከፍተው አንድን ታላቅ በር—ማለትም ተውሂድን የማላቅና ወደ እሱ የመጣራት በርን—ሊዘጋበት ስለሚፈልግ ነው። ተውሂድን የሁሉም አቋማችሁ ሚዛንና የጥሪአችሁ መንፈስ አድርጉት።
🍃 የተውሂድ አርማ ተሸካሚዎች፣ የጥበብ ጠባቂዎችና በበሲራ (በግልጽ ማስረጃ) ተጣሪዎች ሁኑ። በሰዎች ልብ ውስጥ ሰዎችን ከመገዛትና ከማላቅ ይልቅ አላህን (سبحانه وتعالى) የማላቅን ዘር ዝሩ። ይህች ኡመት በጩኸትና በአርማዎች ብዛት ሳይሆን፤ በነቢዩ (صلى الله عليه وسلم) ፈለግ፣ በተውሂድ ብርሃንና ለጌታዋ ባላት ንጹሕ ታዛዥነት ብቻ ነው ህያው የምትሆነው።
🍃 ጉዳዮች ሲበዙ ተውሂድን በጭንቅላታችሁ ያዙ። አርማዎች ሲበዙ የተውሂድን አርማ አንሱ። መንገዶች ሲለያዩም የተውሂድን መንገድ አጥብቃችሁ ያዙ። ተውሂድን ያላቀ አላህን (سبحانه وتعالى) ያላቀ ነው፤ አላህን ያላቀ ደግሞ ስሙ ከፍ ይላል፣ ጥረቱ ይባረካል፣ እስከሚገናኘው ድረስም በጌታው ፊት በሰላም እንዲቆም በትክክለኛው መንገድ ላይ ይጸናል።
አላህ በተውሒድ ላይ አኑሮ በተውሒድ ላይ የምንሞት ያድርገን
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_AsselfiyRepost from قناة ابي حنيفة حسين بن ادريس الوالربابي
✍ ኡኹቲ አትጨነቂ
የቱንም ያህል አለም ብትጨልምብሽ ማብራቱ ሁሉ ቢጠፋ. ከቁርአን ጋር ተሆንሽ አንች ልዩ በሆነ ብርሀን ዉስጥ ነሽ ።
ያዢዉ ታተርፊያለሽ ። ያዢዉ የቀብር ማብራትሽ የልብሽ ነፀብራራ የፊትሽ ብርሀን ነዉና።
አሏህ ከቁርአን ሰወች ያድርገን 🤲🤲
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris
ኡሙ ዓብዲላህ አልዋዲዒያ እንዲህ ትላለች
አንዳንድ ሴቶች: ‘እኔ እውቀት እወዳለሁ ነገር ግን ቢዚ ነኝ ጊዜ የለኝም’ ይላሉ።
ይሄ በሽተኛ ማመሃኛ ነው። እውቀት የምትወድ ሴት፡ ትጥራለች ትታገሳለች።
ተስፋ መቁረጥ እና መዝቀጥ አያስፈልግም።
[ሰዓደቱል መርኣቲል ሙስሊማ1 (8)]
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
➲➢ ለሽያጭ የቀረቡ ትላልቅ ኢስላማዊ
የቴሌግራም ቻነሎች መግዛት ይፈልጋሉ ? አሁን እጃችን ላይ ያሉ 3 ቻናል
🏷 3200k subscribers
🏷 7600k subscribers
🏷 9200k subscribers
👆በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ👇 አስቾካይ
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #ሶስት_⓷ ፣
✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ
.................. #እራቢያ ................
#ባለቤቱ_የሌለው_ስደት"
.....
ያ ትዳር ተብዬ የፈረሰው ግንብ በአቧራው አፍኖኝ፣ በለጋነት ትከሻዬ የሕይወትን ግርፋት እየቀመስኩ ባለሁበት ወቅት፤ የአላህ እዝነት በእህቴ በኩል መጣች። እህቴ... የወገን አለኝታነቷን በተግባር ልታሳየኝ፣ ከነበርኩበት የጭንቀት ማጥ ሰው ልካ አስወሰደችኝ። በዚህም በሕይወቴ መጽሐፍ ላይ አዲስ ነጭ ገጽ ተገለጠ፤ መዳረሻዬም ወደ እህቴ ቤት ሆነ።
እዚህ ጋር ነው እንግዲህ የታሪኬ እውነተኛው መሠረት የሚጣለው!
እኔ ተወልጄ ያደግኩበት አካባቢ በጅህልና (በድንቁርና) ድቅድቅ ጨለማ የተዋጠ፣ የሽርክና የኩራፋት ሰንሰለት የወጣቱን አእምሮ የቀየደበት ምድር ነበር። ያኔ... እኔም በዚያው የጥመት ድባብ ውስጥ የታጠርኩ፣ የብርሃኑን መንገድ ያልተለማመድኩ ደካማ ወጣት ነበርኩ። ታዲያ ወደ ከተማው ስመጣ፣ ዓይኔ ብቻ ሳይሆን ልቤም አዲስ ዓለም ተመለከተ።
ወደ መስጅድ መመላለስ ጀመርኩ። ቁርኣንን መቅራት፣ የቃላቱን ረቂቅ ምስጢር መበርበር የዕለት ተግባሬ ሆነ። በዚያም ውስጥ ነበር ዛሬም ድረስ በልቤ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸውን፣ የሱና ጀግና የሆኑትን ሼይኼን አሼይኽ አቡ አማር አወል አህመድ አል-ኸሚሴ ያገኘዃቼው። ከተፍሲር ትምህርት እስከ አቂዳ (የእምነት መሠረት) ኪታቦች ድረስ ዘለቅኩ።
ያኔ ነበር እውነተኛው "እኔ" የተፈጠርኩት!
ተውሂድ ምን እንደሆነ፣ ቢድዓ ደግሞ ምን ያህል ጥፋት እንደሆነ መለየት ቻልኩ። ቀድሞ በደመ ነፍስ የምከተላቸው፣ እንደ በግ ጥሬ የነበሩት የአህባሽ፣ የኢኽዋንና መሰል የጥመት አንጃዎች አደጋቸው በግልጽ ታየኝ። ያሳለፍኩት ሕይወት ሁሉ በጅህልና የታጠረ፣ የነፍሴን ረሃብ የማይቆርጥ ምስቅልቅል እንደነበር ተረዳሁ። እንዲህ አልኩ፦
#ጨለማን_ብርሃን_መስሎኝ_ስከተል_ከረምኩኝ፣
#በተውሂድ_ጸዳል_ግን_እውነቱን_አገኘሁኝ።
#የልብን_ዝገት_የሚፍቅ_ዕውቀት_ካልታከለ፣
#ሰው_በምድር_ላይ_ስንት_ዘመን_ባከነ?"
ነገር ግን... ይህ የመንፈስ መታደስ ሌላ ትልቅ ፈተናን ይዞ መጣ። ዕውቀቱ ልቤን ሲያሞቀው፣ አካሌ ደግሞ ወደ ሌላ ዓለም እንዲሰደድ የቀድር ጣት አመለከተኝ።
ከእህቴ ቤት ምቾትና ከዕውቀቱ ማዕድ ተለይቼ፣ በማላውቀው ባዕድ አገር ሌላ ታሪክ ልጽፍ ተነሳሁ።
ያ የስደት መንገድ ግን... እንደ ቀድሞው የለጋነት ፈተና ሳይሆን፣ በቁርኣን የታነጸ ማንነትን የሚፈትን፣ ከባድና አስገራሚ ክስተቶችን የሰነቀ ነበር።
፦ የዲጂታሉ ዓለም ሰንሰለትና የስደት ዋዜማ
.
አንባቢያን ሆይ!! እዚጋ..ልብ በሉልኝ። የሰው ልጅ ዕውቀቱ ጥቂት ቢሆንም፣ ምኞቱ ግን እንደ ባሕር ይሰፋል። እኔም በከተማው ሕይወት ውስጥ "የተውሂድ ጭላንጭል" ብርሃን ቢታየኝም፣ ገና በለጋነት የልብ ትርታና በወጣትነት ስሜት የምታወክ ደካማ ፍጡር ነበርኩ። በዚያ ሰሞን ነበር "አልረፍ ያለች ጣት" በሚዲያው ዓለም (ፌስቡክ) ላይ የታሪክን ክር መተብተብ የጀመረችው።
ትውውቃችን የጀመረው በሁለት መስመር "አስተያየት" (Comment) ነበር። ያኔ... እኔ በፌስቡክ አደባባይ ላይ የሱናን ዕውቀትና የልብን ትርታ ቀላቅዬ በምጽፍበት ወቅት፣ እርሷ ልክ እንደ ንጋት ኮከብ ብቅ አለች። መጀመሪያ አስተያየት ሆነ፤ ከዚያም ያ አስተያየት ወደ "መቀራረብ" አደገ።
ነገሩ እንዲህ ነው... ቃላት ቃላትን እየወለዱ፣ ሐሳብ ሐሳብን እየሳበ፣ "መላመድ" የሚባለው ረቂቅ ሰንሰለት አሰረን።
ያኔ እንዲህ አልኩ፦
*"በቀጭን ሽቦ ተጉዞ የልብ ወሬ፣
አበበ መሰለኝ የትላንቱ ፍሬ፤
ከኮሜንት ጀምሮ እስከ ስልክ ጩኸት፣
ነፍሴ ተሳሰረች በናፍቆት ድርሰት።"
ያ መላመድ ግን እረፍት አልሰጠኝም። ቀስ እያለ ወደ "ፍቅር" ተቀየረ። ፍቅር ስላችሁ... እንደ ዘመኑ በቧልት የሚነደድ ሳይሆን፣ በሰለፎች ጥበብ የታጀበ፣ "ሐላል" የሚል መዓዛ ያለው፣ እስከ ጀነት የሚያዘልቅ ጽኑ ስምምነት ነበር። ታዲያ ያ ፍቅር ለብቻው አልቆመም፤ ወደ "ትዳር ጥያቄ" ተሸጋገረ።
እዚህ ጋር ነው እንግዲህ ለጀሮ "ዱብዳ" የሚሆን መብረቅ የወረደው!
>ታዳ በወቅቱ እንዲህ ነበር መቼም
። በቴሌግራም "ፍቅር እስከ ጀነት"ና ትዳር እና ኢስላም?፣፣ በሚባሉት ቻናል ያልተለከፈ፣ ያንን ትርክት ሰንቆ ለትዳር የማይቸኩል ወጣት አልነበረም። እኛም ካለን ጥቂት ዕውቀት ላይ እየቀነስን፣ ከሰለፎች ንግግር እየኮረጅን፣ በረቂቅ ቃላት "የአዋቂ አጥፊ" ሆነን የልብን ወሬ አቀጣጠልነው።
"በብዕር ተነክቶ የልብ ቁስል ታደሰ፣
የሰለፎች ንግግር ለፍቅር መነሻ ሆነ፤
ዕውቀት ባይኖረኝም ቅኔው ግን ፈሰሰ፣
የሰው ልጅ ተስፋውን በቃላት አፀነሰ።"
ነገር ግን... ይህ በቃላት የተገነባው የፍቅር ግንብ ወደ እውነት እንዲለወጥ፣ የኪስ ባዶነትና የኑሮ ድህነት ትልቅ አጥር ሆኑብኝ። እሷን በሐላል ለማግባት፣ ያቺን ለጋ ሕይወቴን ለማቅናት የግዴታ መሰደድ ነበረብኝ። ስደት! ያ የብዙዎች መቃብር፣ የጥቂቶች ደግሞ የብልጽግና በር።
ጉዞው ተጀመረ። ቀኑ የሳምንቱ ንጉሥ ጁምዓ ነበር። ሰዓቱ ደግሞ ዱዓ ተቀባይነት አለው ተብሎ የሚታሰበው የቀኑ መጨረሻ ነበረች ።አሁን ከቤት ወጣን ጉዞ ሊጀመር ነው ወደ "ኮቻ" የሚወስደውን መኪና ላይ ስወጣ፣ በውስጤ ትልቅ ዐውሎ ነፋስ ይነፍስ ነበር።
ከጅህልና ጨለማ ወደ ተውሂድ ብርሃን የወጣሁባትን ያቺን ውድ መንደሬን።የተቆጣጠሩ አመትን የተቀመጥኩባት ኬሚሴ ፣፣ብርሃን የሆናችኝን እህቴንና ጓደኞቼን ሳልሰናበት "ጠፍቼ" ወጣሁ። መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር፣ ልቤ እንደ ሸማ ይተርተር ነበር። ወደ ኋላ እየቀረች ያለችው አገሬና ወደ ፊት የሚጠብቀኝ ባዕድ ምድር በመሀከላቸው እኔን ጥለውኝ ሲቆራረጡ ታወቀኝ።
አቤት የስደት ነገር! አቤት የናፍቆት እሳት! መኪናው አቧራውን እያቦነነ ሲሄድ፣ እኔ ግን በልቤ ውስጥ የወደፊቱን የትዳር ተስፋና የመንገዱን ስጋት አጭቄ ወደማላውቀው ዓለም ተጓዝኩ።
ቀጣዩ ምዕራፍ፦ "የበረሃው ጋሬጣ"
🔖 #ክፍል_⓸_ይ.ቀ.ጥ.ላ.ል.....~
⤵️

አዋጅ ስሙ
ያልሰማህ ስማ ጆሮ ስጥና ስማ ሁለተኛ ሚስት እኮ የሴቶች ሸክም ችግር ለመሆን ሳይሆን የተፈቀደልህ የሴቶችን ችግር ሸክም ለመቀረፍ ለማቅለል ነው ወድሜ ሆይ✅✅ ሱናን እየተቃወምሽ የሚል ይኖራል ላ ፈፅሞ አልቃወምም የምቃወመው በሴቶች ላይ ሸክምን የሚጨምር እና ግፍየሚሰራን ነው👌👆👏
يَوْمَئِذٍ تُعْرَضُونَ لَا تَخْفَىٰ مِنكُمْ خَافِيَةٌ
በዚያን ቀን ለሂሳብ ትቀርባላችሁ ከእናንተ ምንም የተደበቀ አይደበቅም
ያ ቀን ሁሉም ሰው ያደረገውን በግልፅ ለአላህ ፊት ይቀርባል።
በድርጊት የሰራኸው መልካምም ሆነ ክፉ ሁሉ መዝግቦ ይመጣል
በአሳብ ፡በልብህ የሰውርከው አሳብም ይታወቃል
በሰውነት እጅህ እግርህ ቆዳህ እራሱ ስለሰራው ይመሰክራል 💧💧
ደርስ አለ መከታተል ለምትፈልጉ 💎
ጥያቄ፦ የሰራኋቸውን ወንጀሎችና ሀራም ነገሮች እንዴት ነው መርሳት የምችለው እያለች ለምትጨነቅና የወንጀል ሸክም ለከበዳት ነፍስ የተሰጠ መልስ ?!!
በሸይኽ ሱለይማን አሩሀይሊይ ሀፊዘሁሏህ
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_AsselfiyRepost from قناة ابي حنيفة حسين بن ادريس الوالربابي
🟠 አሁን ቀጥታ ስርጭት ቂራአት
~~
📖 የቁርአን ተፍሲር
🎙 በኡስታዝ አቡ ሐኒፋ ሑሰይን ኢድሪስ ሰዒድ ሐፊዘሁሏህ
ተ
ጀ
መ
ረ
👉 ሸር አድርጉት. ተቀላቀሉ አድም አድርጉ
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris?videochat=59dc0e0734fd48907f
እዳው ያለንበት ወቅት ማሳዘኑ ጪካኔ💦💦 ግን ሰው በሰው ላይ የዚህን ያክል ይጨክናልደ💔
ያአሏህ ያአሏህ ያአሏህ አተ ከሰው እጅ ጠብቀኝ ጠብቀኝ ያረብ
ሰው ግን ምን ጉድ ነን እህህህህህህ ሞት እያለ ወሏሂ በዚህ ልክ ለምን ልባችን ትንሽየ የጎመን ፍሬ ታክል እዝነት እኳ አያደርግም💦 እህህህ ምን ይሻላል ወሏሂ ዛሬ ወድም በወንድሙ የሚጨክንበት ሰአት 💦💦💦 አየ አዱኒያ ይብላኝ