الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
رفتن به کانال در Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
2 157
مشترکین
-224 ساعت
+367 روز
+41730 روز
آرشیو پست ها
ዱኒያ እና እኛ እንደዚህ ነን⤵️
عْلَمُوا أَنَّمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَزِينَةٌ وَتَفَاخُرٌ بَيْنَكُمْ وَتَكَاثُرٌ فِي الأَمْوَالِ وَالأَوْلَادِ كَمَثَلِ غَيْثٍ أَعْجَبَ الكُفَّارَ نَبَاتُهُ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَاهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَكُونُ حُطَامًا وَفِي الآخِرَةِ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَغْفِرَةٌ مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانٌ وَمَا الحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلاَّ مَتَاعُ الغُرُورِ
ቅርቢቱ ህይወት ጨዋታና ዛዛታ? ማጌጫም! በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መሆንዋን ዕወቁ፡፡ (እርሷ) በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናብ ፣ ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚሆን ብጤ ናት! በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት እና ምህረትና ውዴታ ከአሏህ አለ፡፡ የቅርቢቱም ህይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም⤵️⤵️
ማጌጥ እና መመፃደቅ (زِينَةٌ وتَفَاخُرٌ): አሁን ባለንበት ዘመን ሰዎች በውጫዊ መልካቸው በለበሱት ውድ ልብስ! በሚነዱት መኪና እና በሚኖሩበት ውብ ቤት እርስ በእርሳቸው ይወዳደራሉ ይኩራራሉ። ማህበራዊ ሚዲያ የዚህ መገለጫ ዋና መድረክ ሆኗል።⤵️⤵️
መጫወት እና መዘናጋት ዛዛታ ? (لعِبٌ ولَهوٌ): ዛሬ ላይ የሰው ልጅ ጊዜውን በአብዛሀኛው የምናጠፋው በአላማ ቢስ ነገሮች? መዝናኛዎች እና ከዋናው የህይወት እውነታ ዘና በማለት ነው። ሶሻል ሚዲያ! አላስፈላጊ ውሎዎች እና ከንቱ ነገሮች የዘመኑንሰው ጊዜ ይበሉታል።
⚠️አንዲት ሴት እንዲህ ስትል ጠየቀች፦ "የተከበሩ ሸይኽ ! ለምንድነው ኢስላም እኛን ለባሎቻችን እንድንታዘዝ ያስገደደን፤ ባሎችን ግን ለእኛ እንዲታዘዙ ያላደረገው?"
🌟 ሸይኹም እንዲህ አሏት፦ "ስንት ልጆች አሉሽ?" እርሷም፦ "ሦስት ልጆች አሉኝ" ስትል መለሰችላቸው
🌟 በዚህ ጊዜ ሸይኹ እንዲህ አሏት፦ "አላህ (سبحانه وتعالى) አንቺን ለአንድ ወንድ (ለባልሽ) ብቻ እንድትታዘዢ
አዘዘሽ። ለእነዚያ ለሦስቱ ወንዶች (ለልጆችሽ) ግን አንቺን እንዲታዘዙሽ አዘዛቸው። አንቺን ካልታዘዙሽና ስነ-ምግባራቸውን አሳምረው ካልያዙሽ በስተቀር ጀነት በፍጹም አይገቡም
🌟 ታዲያ ብልጫውና ትርፉ በማን በኩል ሆነ? ስጦታውስ ለማን በዛ?" አሏት። ሴቲቱም በታላቅ እርካታ ተሞልታ፦ "በኢስላም ጸጋ ላይ አላህ (سبحانه وتعالى) ምስጋና ይገባው" በማለት መለሰች
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from قناة ابي حنيفة حسين بن ادريس الوالربابي
.
ያለ መድሀኒት ተኝተን ያለ ህመም ያለ ድካም ከተነሳን አልሀምዱሊላህ በትልቅ ኒዕማ ውስጥ ነን::
الحمدالله 🌸
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
! ፈጥኖ የመለስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
በኢስላም አንድ ወንድ ከቻለ እስከ ስንት ማግባት ይቻላል ?
قم صلّ ركعتين في جوف الليل، واخلع هموم الدنيا من قلبك، واقترب من ربك بالخضوع والدعاء؛ فإنه ينزل كل ليلة إلى السماء الدنيا يقول: "هل من داعٍ فأستجيب له؟"⤵️⤵️
በዚህ ምርጥየ ሰአት ተነሱ ወንድም እህቶቸ ጀዋል እንዳያታልለን ግማሽ ሰአት ወደአሏህ አንሾካሽኩ 💦 በዱዓም ውስጥ እስበሳችን እንተዋወስ ✅
ኢላሂ! የሌሊቱ ዝምታና የነፍስ ፀጥታ ባለበት በዚህ ሰዓት አሏህ ይሆ ዱዓችንንም ተቀበል።
ኢላሂ! የዕድሜያችንን ቀናት በፈቃድህ እና በታዛዥነትህ እንድንጨርሳቸው እርዳን ከሰይጣን ወጥመድ እና ከክፉ ምኞትም ጠብቀን።
ኢላሂ! በሥራችን ውስጥ ውብ የሆነ ባረካን አፍስስበት ጥረታችንንም በህዝቦች ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኝ አድርግልን።
ኢላሂ በዙሪያችን ላሉት ለወዳጅ ዘመዶቻችን እና ለምንወዳቸው ሁሉ ሰላምን ጤናን እና የልብ መረጋጋትን ለግስላቸው።
ጌታችን ሆይ! የዱንያን ፈተና አቅልልልን የኣኺራችንን መናኸሪያ ውብ አድርግልን። አንተ መሐሪ ነህና ዛሬም ነገም እኛን ከችሮታህ ለግሰን 💧✨🤲🤲🤲🤲🤲
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አስራ_አምስት(⓯)_ ፣
✍ #ፀሀፊ_ #አቡ_ኹዘይማ
...............☞ #አይከል ................
#ባለቤት_የሌለው_ስደት"
#ምዕራፍ_ሁለት
.....
የቃል ኪዳን ጽናትና የሾርጣው ድንገቴ
ከ"ሙሐመድ ልጅ" ጋር ያለን ግንኙነት ከመላመድ አልፎ ወደ ጥልቅ ቃል ኪዳን ተሸጋገረ።
ያኔ.....ነው እንግዲህ እዝች ልጅ ላይ የወሰንኩት በቃ የትዳር" አጋሬ ይችናት ብዬ ወሰንኩ ታዳ በሚገባ መግባባት ቻልን ነገሮች' ግልፅ ተደራረግን ግንኙነታችን የሚዲያ እንደመሆኑ ከባዱን ጥንቃቄ አደረግን።
ስለ ኒካህ እያለምን፣ ስለ ወደፊት ጎጆአችን እየተመካከርን ወራት ወራትን እየተኩ እንደ ዋዛ ሱዑዲ ምድር ሁለት ዓመታት ነጎዱ። እሷ ጅዳ ናት እኔ ጅዛን ነኝ ተመካርን የጀመረችውን ቤት እንደለና እሱን እስከምጨርስ ግዜ እንድሰጣት ጠዬቀችኝ!! እሷም ቤቷን ለመጨረስ ስትደክም፣ እኔም እሱን እንድጨርስ ልታገሳት ከዛ ጅዛን ሆኜ በናፍቆት እጠብቃት ነበር።
በዚህ መሃል፣ ያቺ በኢትዮጵያ ያለችው ልጅ በትዕግሥት ማጣትና በጭቅጭቅ ሰልችታ "ብሎክ" አድርገኝ ትለኛለች" ሲፈልጋት ደሞ አኩርፋ ትሄዳለች። ያ የድሮው የሐራም ትዝታ እንዲህ ባለ መከፋት ሲደመደም፣ እኔ ግን ለሙሐመድ ልጅ ያለኝን ታማኝነት አጸናሁ። "ደካማ ማንነቴን" አርሜ፣ ለሷ የሚመጥን ወንድ ለመሆን ራሴን ቀረጽኩ። ልብ በሉ እኔ ያለሁት ዛሬላይ ስደት ስለሆነ በምኖርበት ስደት አገር አብራኝ ያለች ጥሩ የትዳር አጋር እዬመረጥኩ እንጂ ሴትልጅ ለማስለቀስ አንዳን መርጬ አንዳን አገባሻለሁ እያልኩ ያጉል ተስፋ ሰጥቼ በሴት ልጅ ላይ የለለ ግፍ ለማድረስ" አይደለም
ለማንኛውም አደራቹሁን ታሪኩን ሳጨርሱ አትፍረዱ!!"ሰው ቢሞት ይረሳል ቢቆይ ይወቀሳል" እንተባለው??ትደርሳሉቹሁ ለወቀሳው
እንቀጥል
አንድ ቀን ድንገት እንዲህ ብዬ ጠየቅኳት፦ "እኔ ብያዝ (ዲፓርት ቢደረግ) እና ወደ ኢትዮጵያ ብገባ ትፈልጊኛለሽ?"አልኳት እሷም በጽናትና በፍቅር እንዲህ አለችኝ፦ "አዎ! የትም ብትሆን አንተ የኔ ነህ፤ ግን እንዳትጎዳኝ አደራ!" ይህ ቃል በልቤ ውስጥ ትልቅ ኃይል ሆነ፤ ለእሷ ያለኝን ታማኝነት በደም አስረገጠው።
ነገር ግን... ቀድሮ (ውሳኔው) ሌላ ነበር።
ገና የንጋቱ ፀሐይ ብቅ ስትል፣ ለሥራዬ ደፋ ቀና እያልኩ፣ ለፍየሎቼ ምግባቸውን ላቀርብ ስል... የሰዑዲ "ሾርጣ" (ፖሊስ) ከኋላዬ ከተፍ አለ። ያ የሁለት ዓመት የስደት ድካም፣ ያ የፍቅር ሕልም እና የናፍቆት ተስፋ በአንዲት ቅጽበት ቆመ።
"ለሕልሜ ስሮጥ - ለፍቅሬ ስተጋ፣
የሾርጣው ጥሪ - መጣ ሳይነጋ፤
አላሁ አክበር! - አልኩኝ በድንጋጤ፣
የስደቱ ማግስት - ሆነብኝ ስርቆቴ።"
ያኔ... የመጀመርያው ትዝታዬ "የሙሐመድ ልጅ" ነበረች። ያ የሰጠችኝ አደራና የገባንበት ቃል ኪዳን በዓይኔ ላይ ብልጭ አለ። በሕግ ቁጥጥር ስር ስውል፣ የነፃነቴ ዋጋ ብቻ ሳይሆን፣ ያ የጀመርነው ትልቅ ተስፋ ምን ይሆን? የሚለው ስጋት ነፍሴን ወረራት።
ከሳዑዲ "ሲጂን" ወደ አገር ቤት ሰማይ ስር......
እንቀጥል
በሾርጣው እጅ ስወድቅ ለማምለጥ የሞከርኩት ሙከራ ከንቱ ሆኖ ቀረ፤ ቀድሮ (ውሳኔው) ጸንቷልና። መኪናው ውስጥ ገብቼ ስልኬ ሳይቀማኝ ለሙሐመድ ልጅና ለአሠሪዬ መያዜን አረዳሁ። ከዚያም ወደ ጅዛን እስር ቤት ተወረወርኩ። የሦስት ቀን አስከፊ ቆይታ በጅዛን ካሳለፍኩ በኋላ፣ እጆቻችን በካቴና ታስረው፣ በባስ ተጭነን ሳዑዲን ልንሰናበት ወደ ጅዳ አመራን።
ጅዳ እስር ቤት ሃያ ስድስት ቀናትን አሳለፍኩ። ያ ስፍራ ግን ለእኔ እስር ቤት ብቻ አልነበረም፤ ልክ በሱማሌ፣ በየመንና በራጎ ምድር እንደነበረው ሁሉ፣ እዚህም የጥያቄና መልስ መድረክ ተከፈተልኝ።
ብዙዎች ስለ ሃይማኖታቸው፣ ስለ ሽርክ ብሎም እኔም የሰከርኩበትን የሀራም፣ፍቅር" የመሳሰሉት ስለ ጫት ሐራምነትና ስለ ሕይወት ምስጢር ይጠይቁኝ ነበር። እኔም ካለኝ ዕውቀት እየቀነስኩ ስመልስላቸው፣ አንዳንዶች እስልምናን እስከመቀበል ደረሱ።አልሃምዱሊላህ በዚያ በስር ቤት ውስጥ ብዙ ታሪኮችን ሰምቻለሁ አይቻለሁ ፣፣ ያኔ....ነበር እዚያ እስር ቤት ውስጥ እንደ "ሙሽራ"ኡስታዝ ኡስታዝ እዬተባልኩ ተከብሬ ሳለሁ ግን፣ ነፍሴ እንዲህ እያለች ትወቅሰኝ ነበር፦
"በመከራው መሃል - አዋቂ ስባል፣
"የጌታዬን ትእዛዝ - ግን ልቤ ጥሷል፤
ሰው ፊት ብከበርም - እንደ ዕውቀት አምባ፣
ውስጤ ግን ፈርቷል - በጸጸት እንባ።"
በመጨረሻም "በረራ" መጣ። ሳዑዲን ተሰናብቼ አዲስ አበባ ገባሁ። አገር ቤት ስደርስ መጀመሪያ የደወልኩት ለዚያች "እንጋባለን" ብላኝ በጭቅጭቅ ስትለበልበኝ ለነበረችው ልጅ ነበር። የምትኖረው አዲስ አበባ ነው።
አሁን እዚህ ጋር ነው ትልቁ የሕይወት እንቆቅልሽ የሚፈታው። ያ ሁሉ የስደት መከራ፣ የራቢያ ፍቅር፣ የጠይባ አደራ፣ የሙሐመድ ልጅ ቃል ኪዳንና የእናቴ ምኞት... አሁን አዲስ አበባ ላይ ተከማችተዋል።
ውድ አንባቢያን ሆይ! የሰው ልጅ ጉዞው ረጅም ቢሆንም፣ መዳረሻው ግን ሁሌም ወደ ራሱ ማንነት ነው። እኔም ያንን ሁሉ አቀበትና ቁልቁለት አልፌ፣ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ቆሜ ቀጣዩን የሕይወት መስመር ለመዘርጋት ስልኬን አነሳሁ።
ቀጣዩ ክፍል ⓰
የሚከተለው ነው
የመካ መንገድ ትዝታና የወሎው ንጋት
ይ ቀ ጥ ላ ል
▫
ስለገለልተኛነትህ ምክንያት ከጠየቁህ እድህ በላቸው! የማይታዩትን ቀዳዳዎች እየሰፋሁ ነው !
የልብ ስብራት ውጭ ላይ ፀጥ ያለ ቢመስልም ከውስጥ ግን ማንም የማይሰማው ጥልቅ እና የሚያንገበግብ ድምፅ አለው።
Repost from N/a
ሶብር ድልብ ነው አላህ እሱ ዘንድ ክብር ላለው እንጂ አይሰጠውም
አል ሐሰኑል በስርይ የተባለ ታላቅ ሊቅ እንዲህ ይላል
" ሶብር ከኸይር ነገሮች ድልብ አንዱ ነው ። አላህ እሱ ዘንድ ክቡር ለሆነ ባሪያው እንጂ አይሰጠውም
https://t.me/abuhureyrahmedresa
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
🚨አዲስ ቻሌንጅ ለቻነል ባለቤቶች በሙሉ 🚨
🛜 ቻናላቺሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ ማሳደግ የምትፈልጉ ብቻ አናግሩኝ 🔽
👉 1k+ subscribers 🟢
👉 2k+ subscribers 🟢
👉 4k+ subscribers 🟢
👉 6k+ subscribers 🟢
👉 10k+ subscribers 🟢
⚠️ ከ1000 ጀምሮ እንቀበላለን ℹ️
💎ቻናል በነፃ ለመሳደግ ያናግሩን ፍጠኑ🔽
ጉዳያችን በዝቶ ለመዘርዘር አፋችን ይተሳሰራል ኢላሂ አንተደግሞ የውስጥ አዋቂ ነህ እርዳታህን ያአሏህ💧🤲🤲🤲⤵️⤵️
اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ خَيْرَ الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ. اللَّهُمَّ أَصْلِح لي دِينِي الَّذِي هُوَ عِصْمَةُ أَمْرِي، وَأَصْلِح لي دُنْيَايَ الَّتِي فِيهَا مَعَاشِي، وَأَصْلِح لي آخِرَتِي الَّتِي فِيهَا مَعَادِي.
اللَّهُمَّ يَا مُحَوِّلَ الْأَحْوَالِ، حَوِّلْ حَالِي إِلَى أَحْسَنِ الْحَالِ، وسَهِّلْ لِي كُلَّ عَسِيرٍ، واقْضِ عَنِّي الدَّيْنَ، واغْنِنِي مِنَ الْفَقْرِ.
اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنَ الْخَيْرِ كُلِّهِ عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ، مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ الشَّرِّ كُلِّهِ عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ، مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ.
اللَّهُمَّ حَقِّقْ لِي أَحْمَامِي وَأَحْلَامِي، واجْعَلْ فِيهَا خَيْرًا لِي فِي دِينِي ومَعَاشي وعَاقِبَةِ أَمْرِي، ولا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طَرْفَةَ عَيْنٍ، وَارْزُقْنِي التَّوْفِيقَ وَالْبَرَكَةَ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ
"አላህ ሆይ! የዱንያንና የአኼራን መልካም ነገር ሁሉ እለምንሃለሁ። አላህ ሆይ! ጉዳዮቼ ሁሉ መጠበቂያ የሆነውን ሃይማኖቴን አቀናጅልኝ፤ መተዳደሪያዬ የሆነችውን ዱንያዬንም አቀናጅልኝ? መመለሻዬ የሆነችውንም አኼራዬን አቀናጅልኝ።"
"ሁኔታዎችን ቀያሪ የሆንክ አላህ ሆይ! ሁኔታዎቼን ወደ ተሻለና ውብ ሁኔታ ለወጥልኝ፤ የሚከብዱኝን ነገሮች ሁሉ አግራኝ? እዳዬንም ክፈለው፤ ከድህነትም አብቃኝ።"
"አላህ ሆይ! ካለፈውም ሆነ ከወደፊቱ፣ ካወኩትም ሆነ ካልዐወኩት መልካም ነገር ሁሉ ፈጥነው ከመጡትም ዘግየው ከሚመጡትም እለምንሃለሁ። ከክፉ ነገር ሁሉ! ካለፈውም ሆነ ከወደፊቱ! ካወኩትም ሆነ ካልዐወኩት በአንተ እጠበቃለሁ።
"አላህ ሆይ! የናፍቆት ህልሞቼንና ምኞቶቼን እውን አድርግልኝ፦ በእነሱም ውስጥ ለሃይማኖቴ፣ ለኑሮዬና የነገ ፍጻሜዬ መልካም ነገርን አድርግልኝ። ለአፍታ ያህልም ቢሆን ለራሴ አትተወኝ፤ በዱንያም በአኼራም ስኬትንና በረከትን ለግሰኝ።🤲🤲🤲
ያልተኛቹህ ወድም እህቶቸ ረከኣቴን ስገዱና ዱዓላይ ተጣዱ ምርጥ ሰአት ላይ ነን ፣💦💦 " እስኪ በዱዓ እንተዋወስ አሏህ ይዘንልን እና
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
يَنْزِلُ رَبُّنَا تَبَارَكَ وَتَعَالَى كُلَّ لَيْلَةٍ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا حِينَ يَبْقَى ثُلُثُ اللَّيْلِ الْآخِرُ، يَقُولُ: مَنْ يَدْعُونِي فَأُسْتَجِيبَ لَهُ؟ مَنْ يَسْأَلُنِي فَأُعْطِيَهُ؟ مَنْ يَسْتَغْفِرُنِي فَأَغْفِرَ لَهُ؟
(رواه البخاري ومسلم
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አስራ_አራት⓮_ ፣
✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ
.................. #እራቢያ ................
#ባለቤቱ_የሌለው_ስደት"
.....
የበቀል ፍጻሜና የንስሐ ብርሃን
-
የእራቢያን "የበቀል በሽታ" ለማከም ቆርጬ ተነሳሁ። ነገር ግን ምክሬና ተግሣጼ ሰሚ ሲያጣ፣ የመጨረሻውን የፈተና መንገድ መረጥኩ። ከጓደኛዬ ጋር ሆኜ በስልክ እንድትፈተን አደረግን።
ያኔ... ያቺ በበረሃው ድንጋይ ስር በንፅህና ያየኋት ልጅ፣ በሁለት ቀን ወሬ ብቻ ክብሯን የእርቃን ፎቶ አሳልፋ ስትሰጥና ለብልግና ቀጠሮ ስትይዝ ሳያት፣ ልቤ በሐዘን ተሰበረ።
ጓደኛዬ ማንነቱን ገልጦ ሲነግራት፣ እራቢያ በድንጋጤና በሐፍረት ተዋጠች። በእንባ ታጅባ "ለምን እንዲህ አደረግክ?" ስትለኝ፣ እኔም እንዲህ አልኳት፦ "አየሽ እራቢያ? ሰውን ለመበቀል የምታደርጊው ጥረት የሚጎዳው አንቺኑ ነው።
ወንድ ልጅን በዚህ መንገድ አትበቀዪውም፤ ይልቁንም የገዛ ሕይወትሽን ነው የምታጠፊው!"
ያኔ ነበር... የእራቢያ ልብ የተሰበረው። የልጅነት ሰቆቃዋንና የበቀል ጥማቷን ተፋችው። አልሐምዱሊላህ! ያ መራራ ፈተና ለእሷ የንስሐ በር ሆነላት። ቶበተች (ተመለሰች)፤ "አሁን እረፍት አገኘሁ" እያለች በምስጋና ትደውልልኝ።ጀመር
አዬው ኒቃብ እኮ ለበስኩ ብላ ደስ የሚለኝንም ተስፋ መገበችኝ
ቀናቶች እንደ ጉድ ይሄዳሉ ታዳ እራቢያም ደጋግማ እዬደውለች አመሰግንሀለው ትለኛለች"
እኔም የራሴን ድርሻ ተወጥቼ፣ ያንን በስሜትና በመከራ የተተበተበ ታሪካችንን እዚያው ላይ የመዝጊያ ነጥብ አኖርኩበት።
"በቀል የልብ እሳት - ነፍስን የሚያነድ፣
በፍቅር ስም መጥቶ - ሕይወትን የሚገዳድ፤
እራቢያ ስትመለስ - ወደ እውነተኛው ብርሃን፣
ታሪካችን አበቃ - በድልና በሰላም።"
አሁን... ወደዚያች በኢትዮጵያ ወደምትጠብቀኝ ልጅ ተመለስኩ። "ገንዘብ አምጥቼ አገባሻለሁ" ያልኳት፣ በስደት መከራዬ ሁሉ ስሟን የጠራኋት ልጅ። ነገር ግን... ያ በሐራም መንገድ የጀመርነው ወሬ፣ አሁን ፍሬ አልባ ጭቅጭቅና ሰበብ ፍለጋ ሆነ። የሐራም ፍቅር መዳረሻው እንዲህ ነው፤ ልክ ውኃ እንዳጣችና ምንጯ እንደደረቀባት አትክልት፣ መጀመሪያ አማረ መስሎ ይታያል፣ ኋላ ግን ይደርቃል፣ ይጠወልጋል።
ውድ አንባቢያን ሆይ! የዚህ ረጅም የታሪክ ዋና ...ነጥቡና ጉዞ ትልቁ ቁምነገር የሚከተለው ነው፦
የሐራም ፍቅር ውጤት፦ ፍቅር በአላህ መንገድ ካልሆነ፣ መጨረሻው ፀጸት፣ ጭቅጭቅና የልብ መድረቅ ነው። እንደ እራቢያ ያለው የበቀል መርዝ፣ እንደ ኢትዮዋ ልጅ ያለው የቃላት ውጋት ሁሉ የዚሁ ውጤት ነው።
▫▫▫▫#መዕራፍ_ሁለት▫▫▫▫
የተውበት ኃይል፦ ሰው ምንም ያህል ቢቆሽሽ፣ አላህ የሚመልስበትን መንገድ ካዘጋጀለት ንጹህ ይሆናል። እራቢያን ከጥፋት መንገድ ማውጣቴ ለኔ ትልቅ የሕሊና እረፍት ነው።
የእውነት ጽናት፦ በበረሃው ጥይት፣ በባሕሩ ማዕበልና በደላላው ጅራፍ መሃል አላህ ያወጣኝ፣ ወደ ቀድሞ ማንነቴና ወደ ቂርዓቴ እንድመለስ ነው።
የንጋት ኮከብና የጽናት ፈተና
በሳዑዲ ምድር ሆኜ ከእናቴ ጋር በምደውልበት ወቅት፣ የእናትነት ምኞቷ ሁሌም አንድ ነው— "ልጄ አግባ፣ ሚስት ላምጣልህ!" ትለኛለች። እናቴ የምትመርጥልኝ ከዘመድ አዝማድ ቢሆንም፣ እኔ ግን ልቤ አልቀበል አለው። ምክንያቱም እኔ ያደግኩበት አካባቢ የአለባበስና የዲን ግንዛቤው ከሸሪዓው መስመር የራቀ ነበር፤ እኔ ደግሞ ከጥፋት ሸለቆ ወጥቼ በተውሂድ አምባ ላይ ቆሜያለሁ። እንዴት ብዬ በባሕል የታሰረች፣ የዲን ብርሃን ያልነካት እንስት የቤቴ ምሰሶ አደርጋለሁ?
በዚህ የሐሳብ ውቅያኖስ ውስጥ ሳለሁ ነው... እንደ ንጋት ኮከብ ድምቅ ያለች፣ በዕውቀቷና በጽናቷ የምትታወቅ አንዲት "የሰለፍያ እንስት" የተዋወቅኩት። ስሟን ልደብቃቹሁ እና "የሙሐመድ ልጅ" እላታለሁ። እሷን ለመቅረብ የበረሃውን ጉዞ ያህል ከባድ ፈተና አሳለፍኩ። በትዕግሥትና በጊዜ ሂደት ግን ወደ ልቧ ቀረብኩ።
እሷ... ከእኔ በዕውቀትና በግንዛቤ የምትሻል፣ ለሥነ-ምግባርና ለዲን ክብር ያላት ድንቅ ዕንቁ ነች። እሷን ሳያት "የልጆቼ እናት፣ የቤቴ መሠረት ይህች ነች!" ብዬ በልበ ሙሉነት ተናገርኩ። በመካከላችን ግልጽነት ነገሠ፤ የስደት ሕይወት ቢሆንም፣ ግንኙነታችንን በአላህ ጥበቃና በጥንቃቄ መራነው። የትዳር ጥያቄዬን በአክብሮት ተቀበለችኝ።
"በአንድ በኩል እናቴ - በባሕል ትጣራለች፣
በአንድ በኩል ልቤ - ዕውቀትን ይመርጣል፤
የሙሐመድ ልጅ መጣች - ብርሃን ሆና፣
የቤቴን ምሰሶ - በእምነት ልታጠና።"
ነገር ግን... ያ የድሮው የሐራም ትዝታና ያቺ በኢትዮጵያ ያለችው ልጅ አሁንም ጥላ ሆና ትከተለኛለች። ለእሷ ያለኝን ክብርና የታማኝነቷን ጥልቀት ባውቅም፣ አስተሳሰባችን ግን እንደ ሰማይና ምድር ተራራቀ። በየደቂቃው የሚፈጠረው ጭቅጭቅ፣ "ካልፈለግከኝ ንገረኝ" የሚለው ፉከራዋ... የልጅነት ማንነቷ ገና እንዳልበሰለ ምስክር ሆነ።
እዚህ ጋር ነው እንግዲህ የታማኝነትና የመርህ ግጭት የመጣው። ለ"ሙሐመድ ልጅ" ስል ታማኝ ለመሆን ወሰንኩ። በስሜትና በልማድ ከታሰረ ትዳር ይልቅ፣ በእውነትና በዲን ላይ የተመሠረተ ትዳር እንደሚበልጥ ተረዳሁ። እንዲህ አልኩ፦
"ከጭቅጭቅ ማዕበል - ወደ ሰላም ወደብ፣
ከሐራም ትዝታ - ወደ ሐላል ጥርብ፤
የሙሐመድ ልጅ ሆይ - የልቤ ንግሥት፣
አንቺን መረጥኩሽ - ለነገው ሕይወት።"
ውድ አንባቢያን ሆይ! ልብ በሉ። ትዳር ማለት መውደድ ብቻ አይደለም፤ ትዳር ማለት አብሮ መጓዝ የሚቻልበት የዕውቀትና የእምነት መጣጣም ነው።
[የታሪኩ ማሳረጊያ]
በ"ሙሐመድ ልጅ" እና በዚያች በኢትዮጵያ ባለችው ልጅ መካከል የመጨረሻውን ውሳኔ እንዴት አሳረግከው? እናትህስን
ይ
......ቀ
...........ጥ.
.................ላ.......ል.✍️
የቃል ኪዳን ጽናትና የሾርጣው ድንገቴ
፨
እኮ ጠብቁ🕶🕶 ቀጣይ ክፍል 14 እየመጣነው ወፈር ደመቅ ያለሻይ እየጠጣቹ ጠብቁ ቋቋ እድታደርጉት በደቂቃ 🤝🤝 በውስጥጥ ላኪ የምትሉ በዚሁ አብራቹህ ጠብቁ እሺ
ሪጃሎች ሰሚዕና ወአጧዕና ብለዋል ያሸይኽ ባረከሏሁ ፊክ
እህታችን ግን ጧ ጧ ማለት ነው የቀራት የኔናት 💦💦 ክው ብላለችኮ ?!
ቀጥታ ስርጪት ተጀምሯል ግቡ📢📢📢
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris
