(የወጣቶች አለም)🌏 عَالَمُ الشَّبَاب
رفتن به کانال در Telegram
🌟 እንኳን ወደ "የወጣቶች አለም" በሰላም መጣችሁ! 🌟 በኢስላማዊ እሴቶች፣ በአኽላቅ፣ በቁርኣን እና በሐዲሥ ብርሃን የወጣቶችን የዱንያ እና የአኺራ ስኬት ለማጎልበት የተዘጋጀ ልዩ መድረክ። 💡 ኢስላማዊ እውቀት | 🚀 አነቃቂ ምክሮች | 📚 የመልካም ስነ-ምግባር መመሪያዎች💥1ታሪክ 💥2የትዳር ተሞክሮዎች 💥3ኢስላማዊ የእውቀት ፈተና ተቀላቀሉን፤ በእስልምና ብርሃን አብረን እንደግ! 🌙✨
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
334
مشترکین
+424 ساعت
+157 روز
+4530 روز
آرشیو پست ها
💫💥Z ....🥸
💥ከተኛን በኋላ ንጋት ላይ የምንነሳው እኛ መነሳት ስለቻልን ሳይሆን አሏህ ሌላ አድስ ቀን እንድንኖር ስለፈቀደልን ነው።
አልሀምዱሊላህ!!
💥💥 💐 الصلاة خير من النوم
💐 الصلاة خير من النوم
🌺 ሶላት ከእቅልፍ ትበልጣለች ተነሱ
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
💥እይታ 😳 1⃣ 🤓
ጊዜሽን/ህን በምን ላይ እያሳለፍክ ነው? የትውልዱ ትልቁ ፈተና እና የዓላማ ህይወት ⏳✨
በአሁኑ ዘመን በወጣቶች መካከል ያለው ትልቁ ልዩነት የዕድሜ ወይም የእውቀት ልዩነት አይደለም — የጊዜ አጠቃቀም እና የዓላማ ልዩነት እንጂ! 🤔💭
📱 አንዳንዶቻችን ቀናችንን በሙሉ Social Media ላይ ሰዓታት ስክሮል በማድረግ የሰዎችን ህይወት ስንከታተል እና አላስፈላጊ ውይይቶች ውስጥ ስንገባ ውሎአችን ያልቃል። ቀኑ ሲጠናቀቅ ግን በውስጣችን ትልቅ ባዶነት እና የእፎይታ ማጣት ይሰማናል። ምክንያቱም ህይወታችንን የሚመራው የራሳችን ህልም ሳይሆን የሌሎች ሰዎች ድምፅ እና እንቅስቃሴ ስለሆነ ነው! 💔
✨ በተቃራኒው ደግሞ ወጣትነታቸውን ለትልቅ ዓላማ የሚጠቀሙ ብዙ ድንቅ ወጣቶች አሉ፦
📖 ዲናቸውን እና ቁርአናቸውን ለማወቅ በየቀኑ ጥቂት ገፆችን የሚያነቡ
🎯 ራሳቸውን በትምህርት፣ በስራ ወይም በአዲስ ክህሎት (Skill) ለማሳደግ የሚደክሙ፣
🧠 ለአእምሯቸው እና ለጤናቸው የሚጠቅም ነገር ላይ ጊዜያቸውን የሚያስቡ።
ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ከሚጠየቁባቸው ነገሮች አንዱ ወጣትነትህን በምን ላይ ጨረስከው? የሚለው እንደሆነ አስተምረውናል
ወጣትነት ማለት ጉልበት ነፃነት እና እውቀት የሚሰበሰብበት ወርቃማ ዘመን ነው! 🌟
ስኬታማ ወጣት ማለት ህልም ያለው ብቻ ሳይሆን፣ ለህልሙ በየቀኑ ትንሽ እርምጃ የሚራመድ ነው! 🏃♂️💨
🕌 መንፈሳዊ እድገት፦ ከሶላት እና ከዚክር ጋር ያለህን ቁርኝት ማጠናከር።
📚 የግል እድገት፦ መጽሐፍ ማንበብ፣ አዳዲስ ቋንቋዎችን ወይም የቴክኖሎጂ ክህሎቶችን መልመድ።
🕊️ አእምሯዊ ሰላም፦ ከማይጠቅሙና ኃይል ከሚጨርሱ አሉታዊ (Negative) ሰዎችና አካባቢዎች ራስን ማራቅ።
🌱 ወጣትነትህ/ሽ ላይ የምታስቀምጠው ዘር ነው ነገ በዕድሜህ/ሽ የምታጭደው ፍሬ የሚሆነው። ህይወትህን በሌሎች ሰዎች ስክሪን ላይ አትኑረው ሀይ የራስህን ስኬታማ ታሪክ መጻፍ ጀምር/ሪ ሀላስ ! 😉🔥
💭እስኪ ከልምዳቹ ምናምን ሀሳባችሁን በኮመንት አጋሩን 😮💨👇
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
✍️ በ 𝒁𝒆𝒃𝒊𝒃𝒂 የተዘጋጀ 🙃 🌸
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💥﴿من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ، أضاء
له من النورِ ما بين الجمُعتَينِ﴾
“በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሀል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።” ሶሂህ አልጃሚዕ: 2470
KEEP GOING. EVEN SLOW
PROGRESS IS STILL PROGRESS.
ተራመጂ አታቁሚ። ቀስ ብሎ
መሻሻልም ቢሆን እድገት ነው።
💥💜 ዱንያ ውስጥ በጣም ከሚያስፈለጉህ
ነገራቶች ውስጥ አንዱ ጭንቀትህን
ማስወገድ ሲሆን አኺራ ላይ ደግሞ
በጣም ከሚያስፈለጉህ ነገራቶች ውስጥ አንዱ
ለወንጀሎችህ ምህረትን ማግኘት ነው ።
ሁለቱም የሚገኙት በአላህ መልእከተኛ
ላይ ሰለዋት ማውረድን በማብዛት ነው ።በዛለይ ቀኑ ጁመአ🥰🥰
💥*ፈጅር ሶላት የአሏህን* ትእዛዝ ለመተግበር የቀን ውሎህን በደስታ የምትጀምርበት ትልቅ ፀጋ ነው።
*ሰላት ሳይሰግዱ የህይወትን*
ጥፍጥና መቅመስ የማይታሰብ ነው ።
الصلاة خير من النوم 🍇
ሶላተል ፈጅር👉🏻⏰ እየደረሰነው ጀማነው ተነሱሱ😮💨🥰🥰
💥🥳🥳🥳🥳🥳 አስደሳች ዜና 🙈ምን አትሉም እኔ ለናንተ ማሎነው የለ እናንተግን ሪይአክት እንኮን ትቆጥራላቹ 🤧🤧😁 ለማንኛውም ፀዴ የሖነች ቻናል አጊንቼላቹዋለው
✨✨✨✨ ቻናሉ በነፃ የ Turkish English እንዲሁም Amharic ቆንቆዎችን ያስተምራል እና እናንተስ ለምን ይቅርባቹ Join በማለት ተጠቃሚ ሁኑ 👇👇👇👇🏃🏃
https://t.me/languges433
Join 😉
💥ነገ የሳምንቱ ምርጡ
ቀን ነዉ ሰሉ አለ ረሱል ❤️🥰
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّد!🌸🌸🌸
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّد!🌸🌸🌸
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّد!🌸🌸🌸
💥ወላሒ ሳታነቡ እንዳታልፉት 😭 እናት ማለት ለእናንተ በአንድ ቃል ግለፆት ብትባሉ ምን ብላቹ ትገልፆታለቹ ጥያቄው ለሁላችንም ነወ። ታሪኩን ስጀምርላቹ ከእለታት በአንዱ ቀን የወተት ብርጭቆው በድንገት ከእጇ ላይ ወድቆ ተሰበረ ልጇ ጮኸባትና ተናድዶ ከክፍሉ ወጣ። አጭር መልእክት ፅፋ አስቀመጠችለት!
ልጇም ሲመለስ እንደተለመደው ወንበሯ ላይ ተኝታ፣ ደብዳቤውን ጭኗ ላይ አድርጋ አገኛት። ከዛም ወሰደውና አነበበው!
ልጄ ውዴ የዓይኔ ብሌን አዝናለሁ... አርጅቻለሁ እጆቼ ይንቀጠቀጣሉ ምግቤም በደረቴ ላይ ይደፋል።
እና እኔ ከእንግዲህ ቆንጆና ጥሩ መዓዛ ያለኝ አይደለሁም !! አትወቅሰኝ
ልጄ ከዚህ በኋላ ልብሴንና ጫማዬን መልበስ አልችልም!! ስለዚህ እርዳኝ.
እግሮቼም መፀዳጃ ቤት እንኳን ተሸክመው ሊወስዱኝ አይችሉም!! እጄን ያዝ እና መራመድን ላስተምርህ ትንሽ በነበርክበት ጊዜ ምን ያህል እጅህን እንደያዝኩ አስታውስ እና አንድም ቀን ሳለማምድህ ሰልችቼህ አላውቅም ነበር...
ልጄ ሆይ፣ አንተም በእኔ ደካማ የማስታወስ ችሎታ እና የቃላቶች ዝግታ አትሰለች።
አሁን ደስታዬ ሁሉ ካንተ ጋር መሆን ብቻ ነው።
ፈገግታክ ትንሽ እያለክ ያስደስተኝ ነበረ።
አሁንም ፈገግታህን አትንፈገኝ።
እኔ ደግሞ በቀላሉ ሞቴን የምጠብቅ ነኝ ።
ስትወለድ አብሬህ ነበርኩ።
ከኔ ጋር ሁን........
ይህን ፖስት የምታነብ ሆይ ስለ እናትህ ሀቅ የሆነች ነገር ሳትፅፍ አትለፍ እናትህ በህይወት ብትኖርም ባትኖርም ላንተ በጣም ውድ ናት ከ አንድ በላይ ቃል ይገባታል ....
💥ጀነት በእናቶች እግር ስር ናት😢😢 እናቶቻችሁን ላጣችሁንና ቁስላችሁን ለቀሰቀስቁባችሁ በጣም ይቅርታ❤
💥💥💥 ካነበብኩት የወደድኩትን ቀሽት የሖነች😉 ተከታታይ ታሪክ ልጋብዛቹ እንዴትነው ትስማማላቹ 🥰🥰 እስቲ በሪይአክሽን 🤪
💥︎ ︎︎ ︎︎
ጨለማ ባይኖር ኖሮ ጨረቃን እንደማናያት ሁሉ ችግሮች ባይኖሩ የ Allah ፀጋ ባልተረዳን ነበር!
🖤
💥መልካም ጠዋት! ህይወት የጥረታችንን ያህል ፍሬ የምናጭድባት መሬት ናት። ዛሬ የምንዘራው መልካም ስራና ጥረት ነገ ለትልቅ ስኬት ያበቃናል። በርቱልኝ
مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً
"ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ መልካምን የሰራ መልካምን ህይወት በእርግጥ እናኖረዋለን፤"
— (ሱረቱ አን-ነሕል፡ 97)
.መልካምቀን🥰🥰
ትዕግስት ማለት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ሆኖ አላህን ማመስገን መቻል ነው። አላህ ለታገሱት ባሮቹ መላእክትን ልኮ ሰላምታ የሚያቀርብላቸውን ያህል ትልቅ ክብር ሰጥቷቸዋል። ሰላማዊ ቀን ይሁንላችሁ!
سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ
"በታገሳችሁት ነገር ምክንያት ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን፤ የመጨረሻይቱም አገር ፍጻሜ ምን ያማረች ናት! (ይባላሉ)።"
— (ሱረቱ አር-ረዕድ፡ 24)
.ሰናይ ለይል ላጤያንስ🤭
የነቢዩ ﷺ የሚስቶች መካከል የተባለችው “የሰማያት ሰፊ ምጽዋት ባለቤት” በሚል የታወቀችው ማን ናት?
ከሚከተሉት የነቢያት ፈተናዎች ውስጥ በቁርአን በግልጽ የተጠቀሰው የሞት ልጅ ፈተና የትኛው ነው?
