የጥበብ እመቤት 📜
رفتن به کانال در Telegram
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
271
مشترکین
-124 ساعت
+77 روز
+15230 روز
آرشیو پست ها
271
የወንድነት ግርማ እንዲኖርህ ና ተከተለኝ ...
🔹 ቃልህ አጥብቀህ አክብር
🔹 አቋምህ ቀጥ አድርግ
🔹 ድክመትህ በሚስጢር ያዝ
🔹 ንፅህና ዘወትር ጠብቅ
🔹 ፁኑ አቋም ይኑርህ
🔹 ደንበርህን ለሰው አሳውቅ
🔹 በትህትና መሪ ሁን
🔺 ለምትፈልገው ነገር ይ ላመንክበት መስወአቲ ክፈል
🔹 በራስህን ብቃት ተማመን
271
“ፍቅር ደስ የሚል ነገር አይደለም ሳሊ... የምትወደውን ስታገኝ ጅል ትሆናለህ። የምትወደውን ስታጣ ደግሞ እብድ ነው የምትሆነው፡፡ ገባህ? በሁለቱም መንገድ ፍቅር የአንተ የሆነውን ሁሉ ይነጥቅሃል፡፡ እኔ የምትለው አንዳችም ነገር እስካይኖርህ ድረስ ሥሩን ይሰድብሃል፡፡ ፍቅር በሰዎች ላይየሚጥለውን ጥላ ከጊዜ በቀር ማንም አያነሣውም፡፡''
271
ግን ባለፀጋ ነኝ!!!
በሀብቴ እንዳትቀኑ ሀብት የለ ከቤቴ፣
ገብታችሁ ፈትሹት ባዶ ነው ማጀቴ፣
ሙሉ ጤና ያለኝ ምንም ያልጎደለኝ!!!!
ፈጣሪ ይመስገን ግን ባለፀጋ ነኝ።
271
271
" መፍትሔ አልባ ተስፋዎች !
የተስፋውን መንገድ ጎዳና ሳይመሩ፣
ተስፋ አትቁረጥ ቢሉት ስሙን እየጠሩ፣
የምላስ ወጌሻ ሳይደርብ ተግባርን፣
አሽቶ መች ሊፈውስ ተስፋ ያጣ ልብን፣
ከልብ ባልመነጨ እውነት አልባ ምክር፣
በማስመሰል ቅኔ ቢሉት በርታ ጠንክር!
ተስፋን የተራበ መንገድ ለጠፋው ሰው፣
በተግባር ተከብሮ መንገዱን ማን ይምራው?
የመካሪ ምክሩ ከልብ ካልፈለቀ፣
በፍቅር ውቂያኖስ ተግቶ ካልጠለቀ!
አሉ! ለመባሉ ተስፋ አትቁረጥ ቢሉ፣
መች ተስፋን ሊመልስ ተስፋ የለሽ ቃሉ።
271
psychological tricks to gain respect
♻️ Speak less say mor
♻️ Hold eye contact longer
♻️ Don't rush your words
♻️ Pause before replying
♻️ Stop seeking approval
♻️ Stand straight always
♻️ Be comfortable in silence
♻️ Set clear boundaried
♻️ Walk like you belong
♻️ Mean what you say
271
ጠንካራ ሴት ለመሆን...
♻️ ሰበብ አቁሚ
♻️ በዝምታ ስሪ
♻️ ትችትን አትፍሪ
♻️ ቂም አትያዢ
♻️ ዛሬን ተጠቀሚ
♻️ለውጥን ውደጂ
♻️ በራስሺን ተማመኚ
♻️ ተስፋ አትቁረጪ
♻️ የማይመጥንሽ ቦታ አትገኚ
271
በእርግጠኝነት ይሄ አጋጥሟችኋል።አንዳንድ ሰዎች ጥፋት ያጠፉና፣ ያንን ጥፋታቸውን አምነው ከመቀበል ይልቅ እራሳቸውን እንደ ተበዳይ አድርገው ያቀርባሉ።ከዛ እናንተ ጨካኝና ተሳዳቢ እንደሆናችሁ፤ እነሱ ደግሞ ንጹህና ተጎጂ እንደሆኑ ያስመስላሉ። ይህንን የሚያደርጉት ጥፋታቸውን ለመሸፈንና እናንተ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቷችሁ ይቅርታ እንድትጠይቋቸው ለማድረግ ነው።ስለዚህ በጥፋታቸው ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ እራሳቸውን ተበዳይ የሚያደርጉ ሰዎችን በጥንቃቄ ተመልከቱ!
ርዕስ፦ ዳርክ ሳይኮሎጂ
✍️ ደራሲ፦ ዊሊያም ኩፐር
271
" ሰው ለሆኑ ሰዎች ❤
በፍቅር ለተጉ ለታታሪ ልቦች፣
በሰውነት ውበት ለሚፈኩ ቅኖች፣
የትኛው ቃል ይሆን? ገላጭ ቃል ምጣኔ?
ማነው? ጥበበኛ ? እውነት ባለቅኔ?
ለቅን ሰዎች ምግባር ለልባቸው ሞገስ፣
መጣኝ ቃል ተዋቅሮ የልብን የሚያደርስ፣
እኔ ነኝ ባይ ምሁር እኔ ነኝ ባይ ሊቅ፣
በሽህ አመታት ትውልድ በዘመን ቢራቀቅ፣
ሰው ለሆኑ ሰዎች በቅንነት ማገር፣
የቱም ቃል አይመጥን ከስራቸው በቀር ።
የልባቸው ቅኔ ምስጢር ማህደሩ፣
መነሻ መድረሻው ፍቅር ነው ሀገሩ።
271
"የሰው ልጅ ውበት በፊቱ ሳይሆን በልቡ ውስጥ ባለው የፍቅር መጠን ይለካል። ልብህን ለሚያደንቅህ ሳይሆን፣ ለሚያከብርህ እና በነፃነት እንድትበር ክንፍ ለሚሆንህ ሰው ስጥ።" 🕊️🔗
271
"ዓለም ጨካኝ ናት" ይባላል። ግን ለመሆኑ የጨከነችው ዓለም ናት ወይስ ሰው? 🤔
ዓለምስ ማለት ምን ማለት ናት? ተፈጥሮአዊቷ ምድር ወይስ እኛው የምንፈጥረው ማህበራዊ ግንኙነት? ብዙ ጊዜ ዓለምን የምንከሰው በሰዎች ድርጊት ምክንያት በደረሰብን ጠባሳ ነው። ዓለም ግን እንደ መስታወት ናት፤ የፊታችንን ነው የምታሳየን።
እኛ ደግ ስንሆን ዓለም ለስላሳ ትሆናለች፤ እኛ ስንጨክን ደግሞ ዓለም ፊቷን ታጠቁራለች። ዓለምን መለወጥ ባንችል እንኳ፣ እኛ ለዓለም የምንሰጠውን ትርጉም እና በውስጧ የምናሳየውን ደግነት መምረጥ እንችላለን።
እናንተስ ምን ትላላችሁ? ዓለም ናት የጨከነችው ወይስ ሰው?
271
!ልባም ሴት አድርገኝ😘
መልክም ረጋፊ ደምግባትም ከንቱ
ልባም ሴት አድርገኝ ሳይመሽ በጥዋቱ
በጎነት እንዳስብ ክፋት የሌለበት
በቃልኪዳን መንገድ ምራኝ ባለህበት
ከፍሬህ ልመገብ ከፅዋህ ልጠጣ
ባጉል መንገድ ሄጄ ፍቅርህን እዳላጣ
በዉጪ ማንነት በመልኩዋ ማትኮራ
አስተዋይ አድርገኝ ፈጣሪን ምትፈራ
🍎ሄዋን
271
ሳቄን መልሱልኝ
ተጨዋች ነበርኩኝ ሲበዛ ቀልደኛ
ሳቂተኛም ነበርኩ ሆኘ ደስተኛ
አሁን ግን ከፍቶኛል ነገሩን ሳላውቀው
እስቲ መልሱልኝ ሳቄን ማን ሰረቀው
ግን ምን አጠፍሁኝ እኮ ምን ሰርቸ
ደስ ብሎኝ እዳልኖር ስቄ ተደስቸ
ኸረ ምን ሰርቸ ምን አደረኮችሁ
የምወደውን ሳቄን ለምን ሰረቃችሁ
አልችልም ያለሳቄ መኖር ተደስቸ
አልጠግብም እርቦኝ በልቸ ጠጥቸ
አንተ ትሁን እሶ እኔ ምን አውቄ
አልገባኝም እኔ ሳቄን መሰረቄ
ሳቄ ትርጉም አለው ለኔ ትልቅ ቅኔ
መልሱልኝ ይቅር አልግባ ኩነኔ
በትንሽ ትልቁ መናደድ ስራየ
ከወይትስ መጣ እድህ አይነት ፀባየ
ሳቄን መልሱልኝ ልኑር እደበፊቱ ሁኘ ደስተኛ
ሳላውቀው ሳቄን ተሰርቄአለሁ እናንተ መልሱ
እህህህህህህ ሳቄን መልሱልኝ!!!🤗🤭🌸
https://t.me/artladyart
271
🔑ሰዎች ብዙ ጊዜ የሰሩትን ስህተት እያሰቡ ጊዜያቸውን ያጠፋሉ።
🔑ነገር ግን ስህተት የህይወትህ ፍጻሜ አይደለም፤ ትምህርት የምትማርበት መንገድ ነው።
🔑ዛሬ ያደረግከው ስህተት ነገ የተሻለ ውሳኔ እንድትወስን ያስተምርሃል።
🔑ሁሉም ስኬታማ ሰዎች ስህተት ሰርተዋል፤ ልዩነቱ ግን ከስህተታቸው ተምረው መቀጠላቸው ነው።
🔑ስለዚህ ያለፈውን አትቀይር ላይ አትቆይ፤ ትምህርቱን ውሰድ እና ወደፊት ቀጥል።
271
" ጎጅሽን በማፍቀር "
ልብ ሳትመዝኝ በምላስ እያመንሽ፤
ከሰው ተራ ወጣሽ ስታምኝ ሲከዱሽ፣
ወደንሻል ሲሎሽ በምላስ ጋጋታ፣
ቆመሽ ማገናዘብ አቅቶሽ ለአንድ አፍታ፣
በስሜት ገስግሰሽ በህልም ዓለም ስካር፣
አፍቃሪሽን ጎድተሽ ጎጅሽን በማፍቀር፣
በከንቱ ባከነ ምድራዊ ውበትሽ፣
ልብ ቀርቶ ምላስ እሺ በማለትሽ፣
271
ሄዋኔ ላንቺ ስል
በልሳኔ እሾህ አንቺን ከምጎዳ ቃል በምጥ ልጣ ልመደብ ከዱዳ መቼስ ታውቂው የለ ቃልና አቅሙ ምድር እንዲ የረጋው ሰማይም መቆሙ ከቶ አይደለም ሌላ ቃል ነው ሚስጥሩ የመኖሩ ምክንያት የፍጡር ቀመሩ እናም ቃል ተፍቼ አንቺን ከማደማ ልሳኔ ተጣብቆ ያንቺን ቅኝት ልስማ፡፡
271
ከትናንት እና ከነገ የቱ ይቀርባል ? አልኩት
እሱም.... ❝እንደመንገዱ ነው።❞ አለኝ
እንዴት ? አልኩት
እሱም.......
❝በትዝታ መንገድ ከተጓዝክ ትናንት፤ በተስፋ መንገድ ከሄድክ ነገ❞ አለኝ።
