fa
Feedback
HOP Ministry

HOP Ministry

رفتن به کانال در Telegram

HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
563
مشترکین
+324 ساعت
+217 روز
+5530 روز
آرشیو پست ها
#ምርጥ_ምርጡን_ለእግዚአብሔር! አገልግሎት የእኛን ትጋት፣ ጥረት መጋደል ቢጠይቅም "Content wise" ከመልዕክት ይዘት አንጻር ግን የእኛን ምንም አይፈልግም። የምናቀርበው መልዕክት እግዚአብሔር ራሱ፣ የመልዕክቱ ሰጪም እርሱ ራሱ፣ መልዕክቱ የሚያወራውና የሚሰብከው እርሱን፣ ሥራውን፣  ማዳኑን፣  ፍቅሩን ነውና የእኛ የምንለው ምንም ነገር አያስፈልግም፤ ሊኖርበትም አይገባም። "Presentation wise" ከአቀራረብ አንጻር፣ መልዕክቱን ከምናቀርብበት መንገድ (Technics) አንጻር ግን መማር፣ መሰልጠን አለብን። የእግዚአብሔር የሆነውን ነገር ለማቅረብ ልህቀት (Excellence) ያስፈልገናል። ዘመኑ ያመጣቸውን የተለያዩ መንገዶች (Technologies) በጥበብ መጠቀም፣ በአግባቡ ለእግዚአብሔር ሥራ መዋጀት አለብን። የመልዕክቱ ሰጪ እና መልዕክቱ ዘመን አመጣሽ፣ ደግሞም ዘመን ያለፈበትና ዘመን የሚሽረው አይደለም። የምናዘምነው እግዚአብሔርም የለም። እርሱ ከዘመናት በፊት የነበረ፣ ያለ፣ ለዘላለምም የሚኖር ሕያው አምላክ ነው። ነገር ግን ይሄን ዘላለማዊ አምላክ የምንገልጥበት፣ መልዕክቱንም ለትውልዶች የምናስተላልፍበት መንገድ እንደየ ዘመናቱ ሊቃኝ፣ ዘመን አመጣሽ ነገሮችን ዋጅቶ ሊጠቀም ይችላል። እግዚአብሔርን ለማገልገል ሸክሙ ካለን፣ ጥሪውን እግዚአብሔር ካቀረበልን መልዕክቱንም ይሰጠናል፤ እድል፣ ጊዜ፣ ትውልድና መድረክም ይቸረናል። ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን እኛ ለአገልግሎቱ እንደሚገባ ያልተዘጋጀን፣ ያልታጠቅን፣ ያልተሰራን፣ ያልተገራን፣ ያልሰለጠንን፣ መማር የሚገባንን ነገር ሁሉ ያልተማርን ከሆንን ከእግዚአብሔር አሳብ ጋር እንተላለፋለን፤ የእግዚአብሔርንም አሳብ በልህቀት (Excellence) ለትውልዶች ማቅረብ አንችልም። የእግዚአብሔር መንግሥት፣ ሥራውም ምርጥ የተባለ ነገር ሁሉ ይገባዋል። ምርጥ የተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን፣ መንገዶችን በጥበብ እየዋጀን ለመንግሥቱ ሥራ ልናውል ይገባናል። እኛ የመንግሥቱ አገልጋዮችም የነቃን፣ የበቃን (የታጠቅን፣ የተማርን፣ የሰለጠንን)፣ ከእግዚአብሔር ጋር በመክረም፣ በመሰንበት ከእርሱ፣ ከቃሉ የተማርን፣ በጸሎት የተጋን፣ ከእግዚአብሔር ሥራ በፊት ሕይወታችን በእርሱ የተሰራ ልንሆን ይገባናል። ስለዚህ ሰከን ሳንል፣ ለእግዚአብሔር ሳንገኝ፣ በእርሱ ለመሰራት ፈቃደኛ ሳንሆን፣ በትምህርት እና በስልጠና፣ በዝግጅትም ራሳችንን ሳናበቃ እናገለግላለን ብለን አንጋጋጥ። ለአገልግሎት ያለንን መሻት፣ ትጋት ያህል፤ ለመማር፣ ለመዘጋጀት፣ ለእግዚአብሔር ለመገኘት፣ በእርሱ ለመሰራት፣ ለመገራት፣ ከእርሱ ጋር ለመዋል፣ ከእርሱ ለመቅዳት መሻት፣ ትጋት ይኑረን። ምርጥ ምርጡ ሁሉ ለእግዚአብሔር፣ ለመንግሥቱ ሥራም ያስፈልጋልና በጥበብ እየዋጀን ለመንግሥቱ ሥራ እናውለው። የእግዚአብሔርንም መንግሥት እናስፋበት!! በታጠቁ፣ በተሰሩ፣ በተዘጋጁ ሰዎች መስራት የእግዚአብሔር ደስታው ነውና በእርሱ እንሰራ፣ እንታጠቅ፣ ለአገልግሎቱ እንደሚገባ እንዘጋጅ!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 June 21, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

4_5998844439378793047.mp37.52 MB

ሊያገኘን፣ ከእኛ ጋር ሕብረት ሊያደርግ ናፍቆ እየጠበቀን ነው!! “እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት።” — ኢሳይያስ 55፥6 (አዲሱ መ.ት) #HOPMinistry #HearObey
ሊያገኘን፣ ከእኛ ጋር ሕብረት ሊያደርግ ናፍቆ እየጠበቀን ነው!! “እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት።”   — ኢሳይያስ 55፥6 (አዲሱ መ.ት) #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional t.me/hopministry10

ሊያገኘን፣ ከእኛ ጋር ሕብረት ሊያደርግ ናፍቆ እየጠበቀን ነው!! “እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት።”   — ኢሳይያስ 55፥6 (አዲሱ መ.ት) #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional t.me/hopministry10

#የዘላለም_ሕይወት እውነተኛ አምላክ ከሆነው ከእግዚአብሔር እንዲሁም የሕይወት ምንጭ ከሆነው ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ በምንም አይገኝም። እውነተኛ እና ብቸኛ አምላክ የሆነውን እግዚአብሔርን ፤ እርሱ የላከውንም ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ጊዜያዊ ጉዳይ ሳይሆን የዘላለም ሕይወት ነው። እውነተኛ አምላክ የሆነውን እግዚአብሔር አብን፣ እርሱም የላከውን አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ እንደ ሌሎች የእውቀት አይነቶች አዕምሮን ለማስፋት፣ ለመረጃ ምንጭነት፣ ጠቢብ እና አዋቂ ለመባል፣ የተለያዩ ክህሎቶችን ለማግኘት ማወቅ ያለብን እውቀት ሳይሆን የሕይወት ጉዳይ ነው፤ ያውም የዘላለም ሕይወት ነው። እግዚአብሔር አብን፣ ልጁንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያወቁ እርሱን ያዩ፣ ከእርሱ ሕይወትን የተካፈሉ ሰዎች ምስጉኖች ናቸው፤ የዘላለም ሕይወት አላቸው። የዘላለም ሕይወት የሆነ፣ የዘላለም ሕይወት የሚገኝበት እውቀት እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። እግዚአብሔርን ላለማወቅ ልባችንን ስናደነድን እና ቸልተኞች ስንሆን የዘላለም ሕይወትን ችላ እያልን እንደሆነ እናስተውል!! አስተማሪ የሆነው፣ የእውነት መንፈስ፦ መንፈስ ቅዱስ ዕለት ዕለት እግዚአብሔርን እንድናውቅ፣ ከእርሱ ጋር ይበልጥ እንድንወዳጅ ይርዳን!! “እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”   — ዮሐንስ 17፥3 (አዲሱ መ.ት) ✍️ መክሊት አየለ 📆 January 20 & August 19, 2022 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

#ኢየሱስ_ይወደናል!! 📖 Hear. Obey. Practice. #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional t.me/hopministry10
+5
#ኢየሱስ_ይወደናል!! 📖 Hear. Obey. Practice. #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional t.me/hopministry10

07_Fiker_Neh___ፍቅር_ነህ___Meskerem_Getu(128k).m4a6.37 MB

#እኔ_ምስክር_ነኝ! የእኔ ማንነት፣ የኋላ ታሪኬ፣ ባህሪዬ ታይቶ እና ሚዛን ላይ ተቀምጦ ቢሆን እግዚአብሔር እኔን የመረጠኝ፦ ከክብሩ የጎደልኹ፣ ለመንግሥቱ የማልበቃ፣ ከእግዚአብሔር ሕይወት የተለየሁ፣ ከሙታን መካከል አንዷ ነበርኹ። ነገር ግን በበደሌ እና በኃጢአቴ ሙት በነበርኹ ጊዜ እግዚአብሔር ከወደደኝ ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሰጠኝ፤ በእኔ ሥራ ሳይሆን በጸጋው አዳነኝ፣ የመንግሥቱ ወራሽ አደረገኝ። እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን እንደሚወድ፤ በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩልም ቀርቦ እንደሚታረቃቸው፤ ዳግም ልደት ሰጥቶ አዲስ ፍጥረት እንደሚያደርጋቸው፤ ኃጢአት፣ በደል፣ መተላለፋቸውን ሁሉ በልጁ በኢየሱስ ደም እንደሚያነጻ፣ ልጆቹ እንደሚያደርጋቸው እኔ ማሳያ ነኝ፣ እኔ ምስክር ነኝ። ዛሬ፣ ጌታ ፈቅዶ በሚጨምርልኝም ቀሪ እድሜ ጸጋው ቢበዛልኝና መንፈሱ ቢያግዘኝ የምተጋው፦ እንዲህ ለወደደኝ ኢየሱስ ታማኝ አፍቃሪው ለመሆን፣ ሞቴን ለሞተልኝ ኢየሱስ ሕይወቱን ልኖርለት ነው። #ኢየሱስ_ይወደናል!! ✍️ መክሊት አየለ 📆 June 19, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

#እንደራሴ እንደራሴነቱ ለወከለው አካል እንጂ ለራሱ እና ለግል ጉዳዩ አይደለም። እንደራሴ በላኪው፣ በውክልና ሰጪው ቦታ ሆኖ እርሱ ቢሆን የሚያደርገውን ሁሉ ያደርጋል። የእንደራሴ ስራና ሀላፊነቱን በአግባቡ መወጣቱ በወካዩ (በላኪው) አካል ይገመገማል። አንድ እንደራሴ (አምባሳደር) አገሩን እና የአገሩን መንግሥት ወክሎ ወደ ሌላ አገር ሲሄድ፣ በዚያ በሚኖረው ቆይታ የላከውን መንግሥት ሳይሆን የራሱን አጀንዳ ሲያስፈጽም ቢሰነብት፣ ላኪውንም ባይወክል እንደራሴነቱ (አምባሳደርነቱ) ምን ላይ ነው? 2ኛ ቆሮንቶስ 5 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁸ ይህ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በክርስቶስ አማካይነት ከራሱ ጋር አስታረቀን፤ የማስታረቅንም አገልግሎት ሰጠን፤ ¹⁹ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን። ²⁰ ስለዚህ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ እግዚአብሔርም በእኛ አማካይነት ጥሪውን ያቀርባል፤ እኛም ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን።   ✍️ መክሊት አየለ 📆 February 23, 2025 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

#እንደራሴ እንደራሴነቱ ለወከለው አካል እንጂ ለራሱ እና ለግል ጉዳዩ አይደለም። 📖 Hear. Obey. Practice. #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional t.me/hopministry10

#ከምድሩ_የሚበልጥ_ተስፋ_አለን! ተስፋችን ወንዝ የማያሻግር፣ ወንዝ የማይሻገር አይደለም። ተስፋችን ራሱ የተባረከ ተስፋ ነው፤ የሚዳሰስ የሚጨበጥ አካል ያለው ነው። ተስፋችን በተለምዶው "ተስፋዬ እየመነመነ ሄደ" እንደምንለው አይነት ተስፋ አይደለም። ይልቁንም ተስፋ እያደረግነው እና እየጠበቅነው በሄድን ቁጥር የምንገናኝበት፣ ፊት ለፊት የምንተያይበት ቀን እየፈጠነ ነው። ቀን ሲጨምር ከሚያባብለን፣ ሊያዘገየን ከሚጣጣረው የዓለም ብልጭልጭ እያፈተለክን ወደ ተስፋችን እየተቃረብን ነው። በየመስሪያ ቤቱ፣ በየተቋማቱ የ5፣ የ10፣ የ30፣ የ50....ከዚያም በላይ ዓመት፦ እቅድ፣ ስትራቴጂካዊ ንድፍ እየተባለ የሚነገረን ነገር የምድርን ሕይወት ለማበጃጀት፣ በዚህ ያለንን ቆይታ የተሳካ ለማድረግ ቢጠቅምም፤ ማብቂያ፣ የቁርጥ ቀን፣ ፍጻሜ ግን አለው። ሁሉን እያስጌጥን፣ እያስዋብን እዚህ መኖራችን አይቀጥልም። ከዚህኛው ሕይወት የሚበልጥ ሕይወት፣ ከዚህ ምድር ያለፈ ተስፋ አለን። ክርስቶስም ለዚህች ሕይወት ብቻ ተስፋ አይደረግም። የተባረከውን ተስፋችንን ተስፋ እያደረግን፦ በጽናት፣ በትጋት ነቅቶ መጠበቅ፣ መኖር ይሁንልን!! “ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለዚህች ሕይወት ብቻ ከሆነ፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን።”   — 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥19 (አዲሱ መ.ት) “እኛ ግን አገራችን በሰማይ ነው፤ ከዚያ የሚመጣውንም አዳኝ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በናፍቆት እንጠባበቃለን፤”   — ፊልጵስዩስ 3፥20 (አዲሱ መ.ት) ዮሐንስ 14 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ። ² በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው። ³ ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋር እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ። ✍️ መክሊት አየለ 📆 June 18, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

የተባረከውን ተስፋችንን ተስፋ እያደረግን፦ በጽናት፣ በትጋት ነቅቶ መጠበቅ፣ መኖር ይሁንልን!! 📖 Hear. Obey. Practice. #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional t.me/hopministry10

_የልጅነቴ_ዘማሪ_በረከት_አለሙ_yelejenete_singer_bereket_alemu_vol_2_album128k.m4a5.45 MB

መዝሙር 23 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹  እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤ አንዳች አይጐድልብኝም። ² በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤ በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤ ³ ነፍሴንም ይመልሳታል። ስለ ስሙም፣ በጽድቅ መንገድ ይመራኛል። ⁴ በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ፤ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል። ⁵ ጠላቶቼ እያዩ፣ በፊቴ ማዕድ አዘጋጀህልኝ፤ ራሴን በዘይት ቀባህ፤ ጽዋዬም ሞልቶ ይፈስሳል። ⁶ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በጎነትና ምሕረት በእርግጥ ይከተሉኛል፤ እኔም በእግዚአብሔር ቤት፣ ለዘላለም እኖራለሁ። “ቀድሞ እንደ ጠፉ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።”   — 1ኛ ጴጥሮስ 2፥25 (አዲሱ መ.ት) ዮሐንስ 10 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ በጎቼን ዐውቃለሁ፤ እነርሱም ያውቁኛል፤ ¹⁵ ይህም አብ እኔን እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው ነው። ሕይወቴንም ስለ በጎቼ አሳልፌ እሰጣለሁ። #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional #TheLordIsMyShepherd

📖 Hear. Obey. Practice. #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional t.me/hopministry10

ይሰማኛል_ፓስተር_እንዳለ_ወ_ጊዮርጊስ_Yesemagnale_December_1_2022_128k.m4a9.78 MB

እያንዳንዱን እርምጃችንን ከእርሱ ጋር ለመሄድ፤ በነገሮቻችን ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር ለመመካከር፤ የማያሳስት፣ የእውነት ምክር እና አቅጣጫን ለመቀበል ታድለናል፤ በማስተዋል እንጠቀምበት። 📖 He
እያንዳንዱን እርምጃችንን ከእርሱ ጋር ለመሄድ፤ በነገሮቻችን ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር ለመመካከር፤ የማያሳስት፣ የእውነት ምክር እና አቅጣጫን ለመቀበል ታድለናል፤ በማስተዋል እንጠቀምበት። 📖 Hear. Obey. Practice. #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional t.me/hopministry10

#በማስተዋል_እንጠቀምበት! እግዚአብሔር በሕይወታችን ሲኖር፣ ሞገስ ሲሆነን የሰው Recommendation አያስፈልገንም። ማንም ሰው ከጎናችሁ ሳይኖር፣ ዓለም ሁሉ ፊቱን አዙሮባችሁ፣ ስለ እናንተ እውነት የሚመሰክር አንድ እንኳን ጠፍቶ፤ ለእናንተ ላዘጋጀው፣ ለሚገባው ስፍራ እግዚአብሔር ብቻውን፣ የማንም እርዳታ ሳያስፈልገው Recommend ሊያደርጋችሁ፤ ስፍራን ሊሰጣችሁ ይችላል። ከሕያው አምላክ ጋር የልብ ወዳጅ፣ የቅርብ ጓደኛ የመሆን ዕድል፣ Privilege ተሰጥቶናል፤ በማስተዋል እንጠቀምበት። እያንዳንዱን እርምጃችንን ከእርሱ ጋር ለመሄድ፤ በነገሮቻችን ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር ለመመካከር፤ የማያሳስት፣ የእውነት ምክር እና አቅጣጫን ለመቀበል ታድለናል፤ በማስተዋል እንጠቀምበት። በማንም ሰው ፊት የማንሆነውን ነገር በእግዚአብሔር ፊት ለመሆን፣ ለማንም የማናሳየውን ማንነታችንን ለእግዚአብሔር ለማሳየት፣ ለማንም የማንነግረውን የልባችንን ሸክም ለእግዚአብሔር ግልጥልጥ አድርገን ለመንገር፣ የውስጥ ማንነታችንን፣ ጥልቁን ሳይቀር በእግዚአብሔር ለማስመርመር ታድለናል፤ በማስተዋል እንጠቀምበት። ምንም ያህል ትሁት፣ ታጋሽ፣ ሰው አድማጭ ቢሆኑ የልብ ወዳጅ ያልናቸው ሰዎች እነርሱም የራሳቸው የሆነ ብዙ ሸክም፣ አድማጭና አማካሪ የሚፈልጉበት ብዙ ጉድለት አለባቸውና የሆነ ቀን ተነስተው፦ " ዛሬ ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለሁም፤ ለማውራት፣ ለመስማት ዝግጁ አይደለሁም።" ማለታቸው አይቀርም። ፍጹሙ፣ የዘላለም የልብ ወዳጅ የሆነው፣ ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣ አዳኝ አምላካችን፣ ጌታ እግዚአብሔር ግን ሳይሰለቸን ከእኛ ጋር ሊሆን፣ ሊጸና፣ ሊሸከመን የታመነ ነውና ይህንን ድንቅ ዕድል በማስተዋል እንጠቀምበት። “ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣ አዳኝ አምላካችን፣ ጌታ ይባረክ። ሴላ”   — መዝሙር 68፥19 (አዲሱ መ.ት) "Blessed be the Lord, who daily bears us up; God is our salvation. Selah" Psalm 68: 19 (ESV) ✍️ መክሊት አየለ 📆 June 17, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

ከሕያው አምላክ ጋር የልብ ወዳጅ፣ የቅርብ ጓደኛ የመሆን ዕድል፣ Privilege ተሰጥቶናል፤ በማስተዋል እንጠቀምበት። 📖 Hear. Obey. Practice. #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional t.me/hopministry10

Bereket_Tesfaye‎_ሊቀ_፡_ካህኔ_Liqe_Kahenie_128k.m4a4.79 MB