የቀጠናው ተመልካች
رفتن به کانال در Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 321
مشترکین
+824 ساعت
-47 روز
-7130 روز
آرشیو پست ها
4 305
🇺🇸🇸🇦 በሪያድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለሳውዲ አረቢያ የጉዞ ማሳሰቢያውን ወደ ደረጃ 3 አሳድጓል፡ ጉዞ ካሰቡ መልሰው ያስቡ፣ ብሏል።
ኤምባሲው፣ በሳዑዲ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን ወታደራዊ ግጭትን፣ የኢራን ድሮኖችን እና የሚሳኤል ጥቃቶችን፣ እንዲሁም የትጥቅ ግጭትን እና የሽብርተኞችን እንቅስቃሴ በመጥቀስ፣ ለመጓዝ ያሰቡ ደግመው እንዲያስቡ ሲል አሳስቧል።
የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምንም በተመለከተ፣ ዜጎቹ፣ የሳዑዲን ሕጎች በመከተል ያልተገቡ የጦርነት ቪዲዮዎችን ከመቅረጽ እንዲታቀቡ እና ከማሰራጨት መራቅ እንዳለባቸው አያይዞ ተናግሯል።
4 305
🇸🇦 ሳዑዲ ዓረቢያ ተሳስታ በየመን በሚገኙ የራሷ ተዋጊዎች ላይ 4200 ኪግ የሚመዝን ቦንብ ታኢዝ አቅራቢያ መጣሏ ተሰማ።
-*-*-
አይ ያይ ያይ … አያ ካራምባ
4 305
⚡️🇮🇷🇺🇸 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰይድ አባስ አራጋቺ፡-
ልቦለድ፡- ኢራን መከላከያ የላትም።
እውነታው፡- በ100 ዎች የአሜሪካ ወታደራዊ ቦታዎች ተደምስሰዋል፤ በርካታ አውሮፕላኖች ተቃጥለዋል። (ምንጭ፡ የዛሬው የፔንታገን ሪፖርት)
ይሄ ገና ኢምንቱ ነው (ብዙ የደበቁት አለ)። ሁሉንም ነገር በጊዜው እንገልፀዋለን።
ስለ ኢራን ውሸት ለሸጡ ሰዎች፣ ጊዜው ጥሩ አይሆንም (ተደበቁ)!
4 305
🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱🇦🇪🇸🇦🇶🇦🇵🇸🇯🇴🇮🇶 በመካከለኛው ምሥራቅ በአስራ ስምንት ሀገሮች ውስጥ ሃያ የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፖች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶች አሉን። እነዚህ በባሕሬን፣ በኢራቅ፣ በዮርዳኖስ፣ በኩዌት፣ በኦማን፣ በኳታር፣ በሳዑዲ ዓረቢያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ውስጥ ይገኛሉ። ከ200 በላይ ሕንፃዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በካምፖቹ ወድመዋል። ካምፖቹን ዳግም መጠቀም በማያስችል ሁኔታ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፔትርዮት ስርዓቶችን፣ THAAD ራዳር ስርዓቶችን፣ ብዙ ፀረ ሚሳዬል ባትሪ ስርዓቶችን፣ ቅድመ-ማስጠንቀቂያ ራዳር ስርዓቶችን (አንዱ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ወጪ) የሚያካትቱ ከ300 በላይ መሳሪያዎችን አጥተናል። ሪፖርቶች እንዲሁ ከ30 በላይ የMQ-9 ድሮኖች እንደወደሙ፣ ሁሉም ዓይነት አይሮፕላኖች እንደ F15s፣ F35s፣ A10s፣ KC135s፣ እንደወደሙ እያሳዩ ነው፣ ሪፖርቶች ከ100 በላይ አውሮፕላኖች ብቻ እንደጠፉ እያሳዩ ነው …… ይህ በ250 ዓመታት ታሪካችን ውስጥ፣ በጣም ውዱ እና ትልቁ ወታደራዊ ስህተት ነው -- የኒውዮርክ ታይምስ ኤዲቶሪያል ቦርድ
*-*-*-
ጎበዝ፣ ጦርነቱ ሲባል ከነበረው በላይ ቀጠናውን ቀይሮታል።
ዛሬ ሳዑዲ የገባችበት ምስቅልቅል፣ ዋናውና አንዱ ሲሆን፣ የአሜሪካ በአካባቢው መሸነፍ ያመጣው ውጤት ነው።
4 305
🇺🇦⚡️🇷🇺 የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ:
የኃይል መሠረተ-ልማቶችን ላለመምታት ቃል ልንገባ እንችላለን፣ ለመቀበልም ዝግጁ ነን፣ ነገር ግን ለእኛ ምን ማለት እንደሆነ መረዳት አለባችሁ። ለፑቲን የኃይል መሠረተ-ልማት ማለት፣ የነዳጅና ጋዝ ሽያጭ ማለት ነው። ለእኛ ኃይል ማለት ለሕዝባችን የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት እና ማቅረብ ማለት ነው።*-*-*- አጭሬ በጣም ሎጂካም ሰው ናት፣ በምላሷ ቀቅላ ትበላሃለች። መላውን አውሮፓና አሜሪካ በምላሷ እያውከበከበች ከጎኗ በማድረግ፣ ተዝቆ የማያልቅ ገንዘብ የምታልብ ሰው ናት። አጭሬ ጦርነት አታቆምም የፈለገ ነገር ቢሆን። የምታቆመው ስትደመሰስ ብቻ ነው። ካልተደመሰሰች ትደመስሳለች። ያንን ለማድረግ ደግሞ ሩሲያ ግዴታ አዲስ አመራር፣ ናሽናሊስት አመራር፣ የሚቆጨው፣ ጊዜውን የዋጀ የጦርነት ጊዜ አመራር፣ ያስፈልጋታል ብዬ አስባለው። አሁን ያላት የኦሊጋርኪዎች ስብስብ አመራር፣ ሩሲያን የሚታደግ ነው ብዬ አላስብም። አራት ዓመት ሙሉ በዩክሬን ያደሟት፣ በሚቀጥለው አራት ዓመትም ሲያደሟት የሚኖሩ ናቸው። እስካሉ ድረስ፣ የተለየ ነገር ይመጣል የሚል ሓሳብ የለኝም፣ ለግብዓተ- መሬት እና ለአስደንጋጭ ሽንፈት ከመቃረብ በስተቀር። በእርግጥ በጦርነት መሃል የመሪ ለውጥ ማሰብ በራሱ አደጋ ነው፣ ግን ደግሞ የማይቻል አይደለም። ምናልባት አሁን ያሉት ኦሊጋርኪዎች ካሉበት ሰመመን ነቅተው፣ ሩሲያ ያላትን እውነተኛ ኃይል ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ከወሰኑ፣ ያኔ ማሸነፍ እና በሥልጣናቸ መቆየት ይችላሉ።
4 305
+1
🇸🇦🇾🇪⚡️
❌ ሳዑዲዎች እያሉ ያሉት ውሸት፡- አንሷረላህ (ሁቲዎች) መካን እና መስጂድ አል-ሐረምን በባለስቲክ ሚሳኤሎች ኢላማ አድርገዋል።
✅ እውነቱ፡ በመካ ጠቅላይ ግዛት ምንም አይነት ሳይረን አልጮኸም፣ እየጮኸምም አይደለም፤ ሳይረኖች እየጮኹ ያሉት በአጎራባች ጣዒፍ እና ጅዳ ጠቅላይ ግዛቶች ውስጥ ብቻ ነው።
4 305
🇺🇸🇩🇪⚡️ — የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ሪቻርድ ግሬኔል፡
የመርዝን ቃል ማመን እንደማንችል ግልጽ ነው። በበርሊን አንድ ነገር እይናገራል፣ በዋሽንግተን ሌላ ነገር ይናገራል።
4 305
🇩🇪🇺🇳⚡️ — የጀርመኑ ፍሬድሪክ መርዝ በሚቀጥለው ሳምንት ለሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ወደ ኒውዮርክ ያቀደውን ጉዞ መሰረዙን አስታወቀ። ይልቅ መንግሥቱ በበርሊን የመቆየቱ ጉዳይ “አንገብጋቢ” ነው ብሏል። በምትኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሃንስ ዋዴፑል ጀርመንን ወክለው በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ይሳተፋሉ።
4 305
🇩🇪🇾🇪🇸🇦⚡️ — የጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ በየመን፡
ሁቲዎች አሁን በባብ አል ማንዳብ ዙሪያ ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ተቆጣጥረዋል። በሳውዲ ዓረቢያ የኃይል ማመንጫዎችን እያጠቁ ነው። ይህ ሁኔታ በኃይል ገበያው ላይ ያለውን ሁኔታ የበለጠ እያባባሰው ሲሆን ጀርመንም ተፅዕኖው እየተሰማት ነው። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁቲዎች ቀይ ባህርን እንዲቀጥሉ መፍቀድ አይችልም።
4 305
🇩🇪🇮🇷⚡️ — የጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ በኢራን ላይ፡
ኢራን በመጨረሻ ይህንን የሆርሙዝ እገዳ ማቆም አለባት። ከምንም በላይ ወታደራዊ የኒውክሌር ፕሮግራሟን ማቆም አለባት። ቴህራን በመላው ቀጣናው ለፕሮክሲዎች የምታደርገው ድጋፍ መቆም አለበት። ውጤቱን በየቀኑ እያየን ነው። በተጨማሪም ኢራን ግጭቱን ወደ ኢራቅ እንዳትወስድ እንጠይቃለን።
4 305
🇸🇦🇪🇺⚡️ — ሳዑዲ ዓረቢያ በሴፕቴምበር ላይ ድፍድፍ ዘይት ለመጫን ከአውሮፓ ነዳጅ ማጣሪያዎች ወስዳ የነበረውን ትእዛዝ መሰረዟን ገለጸች። ይህን ያለችው፣ በድሮን ጥቃቶች የምስራቅ-ምዕራብ የቧንቧ መስመር ላይ ያሉ ሦስት የፓምፕ ጣቢያዎች ከጥቅም ውጭ ከሆኑ በኋላ ነው።
ኤክስፐርቶች፣ የወደመውን ቧንቧ መስመር ለመጠገን ወራቶች ሊወስድ እንደሚችል አሳስበው፣ በዓለም ገበያ ሊፈጠር ለሚችለው እጥረት ሀገራት ከወዲሁ መጠባበቂያቸው እንዲያዘጋጁ መክረዋል።
4 305
🇮🇷/🇺🇸/🇷🇺/🇺🇦 ፕሬዝደንት ትራምፕ ለመገናኛ ብዙኃን ከተናገሩት በተቃራኒ፣ የናፍጣ ነዳጅ ዋጋ የጨመረው የዩክሬን ጥቃት በሩሲያ ኢነርጂ ተቋማት ላይ ስለተደረገ አይደለም።
የናፍጣ ዋጋ ጣሪያ የደረሰው በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ላይ ከተደረገው ጦርነት በኋላ ነው --- The Washington Post
*-*-*-
ናፍጣ፣ ከጋዝ የሚለይ ሲሆን ከባባድ የፋብሪካ ማሽነሪዎች፣ ከባባድ መኪኖች፣ የእርሻ መሳሪያዎች እና በዋናነት ፔትሮኬሚካል ፋብሪካዎች በግብአትነት የሚጠቀሙበት raw material ነው። ፕላስቲክ የሚሰራው ከናፍጣ ነው። እንዲሁም ጋዝ ጋር ተደባልቆ የተጣራ የሚያደርገው ናፍጣ ነው።
የዋጋው መናር፣ አሜሪካ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት፣ በተለይ ገበሬውን እና ከባባድ የጭነት መኪና ባለቤቶችን፣ ያስጨነቀ ጉዳይ ነው።
4 305
🚨 🇸🇦⚡️🇾🇪 ሰበር ዜና: በሳዑዲ አረቢያ ያንቡ፣ ጅዳ፣ ጣኢፍ፣ አብሃ፣ አል-ኡላ እና ኻሚስ ሙሻይት ላይ፣ ከፍተኛ የሆነ የየመን የሚሳኤል ጥቃቶች በመደረግ ላይ ናቸው።
በብዙ የሳዑዲ ግዛቶች ትምህርት ቤቶች፣ አየር ማረፊያዎች እና የመንግሥት ተቋማት ተዘግተዋል።
የባላስቲክ ሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቱ እንደቀጠለ ነው።
*-*-*-
4 305
🇸🇦⚡️ሳዑዲ የመን ላይ የሙጥኝ ያለችው ለምንድነው? በየመን እንዲህ የምትንገበገበው ምን ስላለ ነው? ምን ፈልጋ ነው?
ለምን የመንን አትተዋትም እና መሠረተ-ልማቶቿን ከውድመት አትታደግም?
4 305
🇾🇪❌🇸🇦 — የአንሷረላህ (ሁቲ) የፖለቲካ ቢሮ አባል እና የሹራ ምክር ቤት ሰብሳቢ፣ ሀዛም አል አሳድ፡
ያፋፋመው ላይ አፋፍምበት! የጀመረው የበለጠ ኢፍትሃዊው ነው።
4 305
🇺🇸🇮🇷⚡️ — የአሜሪካ የነዳጅ ዘይት ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የንግድ ምርቶች እየቀነሱ እና ስትራቴጂካዊ ክምችቶች ወደ ገደባቸው በመቃረባቸው በሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ምክንያት የተነበዩት ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ፣ አሁን መድረሱን እያስጠነቀቁ መሆኑን WSJ ዘግቧል።
የቼቭሮን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማይክ ዊርት እንዳለው፣ መጀመሪያ ላይ በኢራን ጦርነት ምክኒያት ገበያዎች እንዳይወድቁ ይከላከሉ የነበሩ ብዙ መጠባበቀቂያዎቻችን፣ አሁን ተጠናቀዋል፣ ብሏል።
ሲፈራ የነበረው ቀውስም፣ ደጃፍ ላይ እንደደረሰ ጨምሮ ተናግሯል።
ከየመን የተነሱ የድሮን ጥቃቶች የሳውዲ ዓረቢያ የምስራቅ-ምዕራብ የቧንቧ መስመርን በአብዛኛው ከመስመር ውጭ ካደረጉ በኋላ፣ ሁኔታው ተባብሷል፣ ያለው ሌላው ሥራ አስፈፃሚ፣ ይህም ቀድሞውኑ ውስን ከሆነው ገበያ ላይ በቀን በግምት 3.5 ሚሊዮን በርሜል አስወግዷል፣ ሲል ተናግሯል።
የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር በበኩሉ፣ ሊፈጠር ጫፍ የደረሰው ቀውስ "ጊዜያዊ" መሆኑን በመግለጽ፣ የቬንዙዌላን ምርት ለማሳደግ እና የዩናይትድ ስቴትስን የማጣራት አቅም ለማስፋፋት እየሞከረ መሆኑን ተናግሯል።
