fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 317
مشترکین
-324 ساعت
-127 روز
-7530 روز
آرشیو پست ها
🇺🇸⚡️FBI፣ የሴኔተር ሊኒዝ ግርሃምን አሟሟት እየመረመረ ነው። *-*-* ሰውዬውን ሲጥ አርገውት ይሆን ሩሲያዎች በዩክሬን? ኢራኖችስ፣ ይሆኑ እንዴ እንደዛቱበት? FBI መመርመር የፈለገው ምናልባ
+2
🇺🇸⚡️FBI፣ የሴኔተር ሊኒዝ ግርሃምን አሟሟት እየመረመረ ነው። *-*-* ሰውዬውን ሲጥ አርገውት ይሆን ሩሲያዎች በዩክሬን? ኢራኖችስ፣ ይሆኑ እንዴ እንደዛቱበት? FBI መመርመር የፈለገው ምናልባት በሆነ መንገድ ተገድሏል በሚል ፍራቻ ነው። 'ይመርመርልን፣ ወይ በሩሲያ፣ ወይ በኢራን ተገድሎ ነው' እያለች በአሁኑ ሰዓት የምታለቅሰውን፣ የፕሬዝዳንቱን ልዩ አማካሪ Laura Loomer ን የዛሬ ትዊተር ፖስቶች ተከትሎ እንደሆነ FBI እየመረመረ ያለው ጥርጥር የለኝም። Laura Loomer ራሷ ኢራኖች ሊገድሏት እንደሚፈልጉ ከሊንዚ፣ ከትራምፕ እና ከታቂ ሰዎች ጎን ለጎን የተናገሯት ናት። ትናንት በፖስቴ ኢራኖች ሊገድሏቸው እንደሚፈልጉ አንስቼ ነበር። በዚህ ፖስት በላይ ያለውን ርዕስ እየነካካችሁ ብታነቡት መልካም ነው።

🇺🇸⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙት ሁሉም የአሜሪካ ባንዲራዎች ለሊንዚ ግራሃም ክብር ለሚቀጥሉት ስድስት ቀናት በግማሽ ምሰሶ እንዲውለበለቡ አዘዙ። ለሀገራችን እና ለሚወደው
🇺🇸⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙት ሁሉም የአሜሪካ ባንዲራዎች ለሊንዚ ግራሃም ክብር ለሚቀጥሉት ስድስት ቀናት በግማሽ ምሰሶ እንዲውለበለቡ አዘዙ።
ለሀገራችን እና ለሚወደው የደቡብ ካሮላይና ግዛት ብዙ ያስመዘገበው ውድ ጓደኛዬ እና በእውነት ታላቅ ሰው ለሴናተር ሊንዚ ግራሃም አስደናቂ ህይወት እና ስኬቶች ክብር በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ያሉ ሁሉም የአሜሪካ ባንዲራዎች እስከ ቅዳሜ ምሽት ከቀኑ 6 ሰአት ላይ ወደ ግማሽ ምሰሶ እንዲወርዱ አዝዣለሁ።

 🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ - '
የሆርሙዝ ወሽመጥ ክፍት ነው፣ እሺ? ኢራናውያን ክፉና ጨካኝ ሰዎች ናቸው። ስለ ሆርሙዝ ምንም ተጨማሪ ጥያቄዎችን አልፈልግም፣ ሆርሙዝ እንዲ፣ ሆርሙዝ እንዲያ፣ እኛ እዚህ የመጣነው ሊንዚ ግራሃምን ለመዘከር ነው፣ እሱ ድንቅ ሰው ነበር፣ እኔ ሐዘን ላይ ነኝ፣ ብትችሉ ድረሱኝ፣ ያለበለዚያ ዝም በሉ።

🇮🇷⚡️🇺🇸 በኢራን ካሽም ደሴቶች በደረሰ የአሜሪካ ጥቃት የፔትሮ ኬሚካል ኢንዱስትሪን ጨምሮ በርካታ የኃይል መሠረተ- ልማቶች፣ እንደ አንዳንዶች ዘገባ፣ ከዚህ በፊት በዚህ ጦርነት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እየነደዱ ይታያሉ፣ ብለዋል።

🇮🇷⚡️⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ ኢራን በአሜሪካ መርከቦች ላይ በሚሳዬሎችና በድሮኖች ያልታሰበ ጥቃት መክፈቷን ተከትሎ፣ የአሜሪካ ጦር በተለያዩ የኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ተነገረ።

—❗️🇰🇼/🇮🇷ሰበር ዜና: ኩዌት እንደገለጸችው ኢራን ያልተጠበቀና ድንገተኛ የሰርፕራይዝ ጥቃት በATACMS የመሬት ለመሬት ሚሳዬል ሲስተሞቿ ላይ መክፈቷን ተናገረች። እንደ አንዳንድ ምንጮች፣ ኢ
+2
—❗️🇰🇼/🇮🇷ሰበር ዜና: ኩዌት እንደገለጸችው ኢራን ያልተጠበቀና ድንገተኛ የሰርፕራይዝ ጥቃት በATACMS የመሬት ለመሬት ሚሳዬል ሲስተሞቿ ላይ መክፈቷን ተናገረች። እንደ አንዳንድ ምንጮች፣ ኢራን ከዚህም በተጨማሪ ሊወነጨፉ በዝግጅት ላይ በነበሩ 5 የአሜሪካ HIMARS የሚሳዬል ማስወንጨፊያዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍታ አስወግዳቸዋለች ብለዋል። በኩዌት የኢራን ሚሳዬሎች አርፈውበታል በተባለ ቦታ ትልልቅ ጭሶች ይታያሉ።

🇺🇸 ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሴኔተር ሊንዚ ሞት፡ ከመሞቱ ከደቂቃዎች በፊት ተደዋውለናል። ደህና ነበር፣ ትንሽ ደክሞት ነበር እንጂ (ብዙ ስለሚጓዝ እና ገና ከውጭ ጉብኝት ((ከዩክሬን)) መግባቱ ስለነበር)።

🇺🇸🇮🇷 — የኢራን መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኛ፡
"ፀረ-ኢራኑ ሴኔተር ሊንዚ ግርሃም፣ ወደ ሲኦል መሄዱ ታወቀ። ዜናው ደስ ከማለቱ የተነሳ አንዴ ልድገምላችሁ። ሊንዚ ግርሃም፣ የፀረ ፀረ ኢራኑ ሴኔተር፣ ወደ ሲኦል ሄደ።

🇺🇸 የሚገርመው ሊንዚ ግርሃም ባለፉት 48 ሰዓታት በዩክሬን የድሮን ማምረቻዎችን እየጎበኘ ነበር … ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ ደግሞ፣ ሩሲያ በዩክሬን የድሮን ማምረቻዎችን በስፋት ስትመታ የነበረበ
+1
🇺🇸 የሚገርመው ሊንዚ ግርሃም ባለፉት 48 ሰዓታት በዩክሬን የድሮን ማምረቻዎችን እየጎበኘ ነበር … ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ ደግሞ፣ ሩሲያ በዩክሬን የድሮን ማምረቻዎችን በስፋት ስትመታ የነበረበት ነው …

🇺🇸 ትናንት ደግሞ በዚሁ፣ ኢራኖች ሊገሏቸው ከሚፈልጉት አንዱና ዋነኛው ሊንዚ ግርሃም ነው እያልን ስሙን ስናነሳው … አይ ሊንዚ! ትራምፕ ጉድ ሆነ! በ71 ዓመቱ፣ በአጭር እና ድንገተኛ ሕመም ሄደ
🇺🇸 ትናንት ደግሞ በዚሁ፣ ኢራኖች ሊገሏቸው ከሚፈልጉት አንዱና ዋነኛው ሊንዚ ግርሃም ነው እያልን ስሙን ስናነሳው … አይ ሊንዚ! ትራምፕ ጉድ ሆነ! በ71 ዓመቱ፣ በአጭር እና ድንገተኛ ሕመም ሄደ። በአሜሪካ የፖለቲካ ባሕል የመንግሥት ባለስልጣናት እና ማንኛውም አመራር፣ እሁድ እሁድ በየቴሌቪዝን እና በየሬዲዮ ጣቢያዎች፣ በተጠሩበት ሁሉ (አንዱን ከአንዱ መምረጥ ክልክል ነው) እየዞሩ የሚጠየቁበት እና ለጥያቄዎቹ የሚመልሱበት ቀን ነው። እርግጠኛ ነኝ ዛሬ፣ እንደ ሁሌውም፣ ሊንዚ ግርሃም ለእሁድ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ለመቅረብ እየተዘጋጀ ነበር። ሞቱ፣ በጣም አጭር እና ድንገተኛ በሆነ ሕመም ነውና። ይህ ዜና ለአሜሪካ የፖለቲካ፣ የሚዲያ እና በዚያ ዙሪያ ለሚያቀነቅን ሁሉ፣ ለጥቁሩም፣ ለነጩም፣ ለግራውም፣ ለቀኙም፣ ለዲሞክራቱም፣ ለሪፐብሊካኑም፣ እጅግ አስደንጋጭ ዜና ይሆናል።

🇺🇸 ሰበር ዜና፣ ሰበር ዜና፣ ሰበር ዜና- የሳውዝ ካሮላይናው ሪፐብሊካን፣ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ዋነኛ ደጋፊ፣ የእስራኤል ከፍተኛ ወዳጅ፣ እና የጦርነቱን ዋና ቀስቃሽ እና አሳላጭ፣ ሴኔተር፣ ሊንዚ
🇺🇸 ሰበር ዜና፣ ሰበር ዜናሰበር ዜና- የሳውዝ ካሮላይናው ሪፐብሊካን፣ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ዋነኛ ደጋፊ፣ የእስራኤል ከፍተኛ ወዳጅ፣ እና የጦርነቱን ዋና ቀስቃሽ እና አሳላጭ፣ ሴኔተር፣ ሊንዚ ግርሃም፣ ሞተ!

🇺🇸⚔️🇮🇷 የፔንታጎን አዛዦችን ትዕዛዝ ተከትሎ፣ የኢራን ሚሳኤል ጥቃት እንዳይደርስ በመፍራት የአሜሪካ መርከቦች ወደ ኋላ እያፈገፈጉ ነው ተብሏል። እንደ ዘገባው ከሆነ የአሜሪካ ጦር አዛዥ እና የጦር ሚኒስትሩ፣ በመርከቦች ላይ የሚሳኤል ጥቃቶችን ለማስቀረት፣ የአሜሪካ የባሕር ኃይል መርከቦች እንዲወጡ አዝዘዋል።  በተመሳሳይ ሁኔታ AXIOS እንደዘገበው፣ የአሜሪካ ነዳጅ ጫኝ ወታደራዊ አይሮፕላኖች፣ በቀጠናው፣ በኢራን ጥቃት ፍራቻ፣ እስካሁን ለማረፍ ተቸግረዋል።

🇶🇦 — የቀድሞ የኳታር አሚር/መሪ ሐማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ በ74 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ልፋት ማረፋቸውን ኳታር አስታወቀች። ነፍስ ይማር ጋሽ ሐማድ፣ ነፍስ ይማር ሳትሉ እንዳታልፉ።
🇶🇦 — የቀድሞ የኳታር አሚር/መሪ ሐማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ በ74 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ልፋት ማረፋቸውን ኳታር አስታወቀች። ነፍስ ይማር ጋሽ ሐማድ፣ ነፍስ ይማር ሳትሉ እንዳታልፉ።

🇮🇷⚡️🇺🇸🇦🇪🇶🇦🇧🇭🇴🇲 ባሕሬን፣ ኩዌት፣ ጆርዳን እና ለመጀመሪያ ጊዜ ኦማን፣ እስካሁን ባላባራ የኢራን ሚሳዬሎች እየተቀጠቀጡ ናቸው። ከተኩስ አቁሙ ስምምነቱ በኋላ 'በጣም ከፍተኛው፣ እጅግ መጠነ-ሰፊው እና የመናበብ ትግበራዊ ጥቃት' የተባለው የኢራን ጥቃት፣ አረቦቹን ጨምሮ አሜሪካንም ያልጠበቀችው እንደሆነ ተዘግቧል። ወደቦች፣ የጦር ሰፈሮች፣ የኃይል መሠረተ ልማቶች እና ማንኛውም ወታደራዊ ኢላማዎች እስካሁን በቀጠለው የኢራን አጸፋ ተጠቅተዋል። የአያቶላ ኻመኒይ የቀብር ሥነ-ስርዓት ከመጠናቀቁ ጋር በተያያዘ፣ የኢራን መንግሥት ከሰሞኑ 'የተቆራረጠና አናሳ ምላሽ' እየተባለ ሲኮነንበት የነበረውን የመልስ ምቱን ቀልብሶ፣ ወታደራዊ ምላሾቹን እንደ በፊቱ ያጠናከረው ይመስላል።

🇺🇸🇷🇺🇺🇦⚡️አሜሪካ በዩክሬን ፔትሪዮት ሚሳዬሎችን ለማምረት አስባ የነበረውን እቅድ ሰርዘዋለች። በምትኩ፣ በጀርመን እንዲሆን እየሰራች ነው። በዩክሬን የታሰበው ማምረቻ ምናልባት ጦርነቱ ካለ
🇺🇸🇷🇺🇺🇦⚡️አሜሪካ በዩክሬን ፔትሪዮት ሚሳዬሎችን ለማምረት አስባ የነበረውን እቅድ ሰርዘዋለች። በምትኩ፣ በጀርመን እንዲሆን እየሰራች ነው። በዩክሬን የታሰበው ማምረቻ ምናልባት ጦርነቱ ካለቀ በኋላ ሊሆን ይችላል፣ ተብሏል። አሜሪካ እራሷ የሚሳዬሉ እጥረት ያለባት መሆኑ፣ ዩክሬንን አጣብቂኝ ውስጥ አስገብቷታል።

🇮🇷 49 ሀገሮች በተሳተፉበት በቤጂንግ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የሒሳብ ውድድር፣ የኢራን ብሔራዊ የሒሳብ ቡድን አንደኛ በመውጣት ማሸነፉ ታወቀ።
🇮🇷 49 ሀገሮች በተሳተፉበት በቤጂንግ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የሒሳብ ውድድር፣ የኢራን ብሔራዊ የሒሳብ ቡድን አንደኛ በመውጣት ማሸነፉ ታወቀ።

🇮🇷🇺🇸⚡️የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ፣ ከኢራን ጋር የተያያዙ አዳዲስ በርካታ ማዕቀችን በኢራን ላይ መጣሉን አስታወቀ - The Wall Street Journal

+2
🇷🇺🇺🇦⚡️በአሁኑ ሰዓት ሰባት የሩሲያ ክሩዝ ሚሳዬሎች በኪየቭ ላይ ወርደዋል። ትልልቅ ጭሶች በከተማው ይታያሉ። እንደ አንዳንዶች፣ ፍንዳታዎቹ ከባድ ነበሩ። ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ዩክሬን አንድም የሩሲያን ሚሳዬሎች አክሽፋ ያለመጣሏ አነጋጋሪ እየሆነ ነው። እንደ ብዙዎች ግምት፣ ዩክሬን አሜሪካ ሰራሾቹን ፔትሪዮት አየር መቃወሚያዎቿን አሟጣ ሳትጨርስ አልቀረችም። ይህ ከሆነ በጣም ከባድ ነው። በቀላሉም የሚተካ አይደለም። አሜሪካ እራሷ በኢራን ጦርነት አብዛኛዎቹን ስለተጠቀመች እጥረት አለባት። በዚህም ምክኒያት፣ የሩሲያ ጦር ክፍተቱን ተጠቅሞ የሚሳዬሎችን ድብደባ ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።

🇹🇷 በአንካራ በተካሄደው የኔቶ ስብሰባ ላይ፣ የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ለሁሉም አባል ሀገራት እና ለአውሮፓ ህብረት አመራር፣ የራሱ ስም የተቀረጸበትን የግል ሽጉጥ በስጦታ ሰጥቷል። የተሳተፉት
🇹🇷 በአንካራ በተካሄደው የኔቶ ስብሰባ ላይ፣ የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ለሁሉም አባል ሀገራት እና ለአውሮፓ ህብረት አመራር፣ የራሱ ስም የተቀረጸበትን የግል ሽጉጥ በስጦታ ሰጥቷል። የተሳተፉት ሁሉ በጣም ተገርመው በተለያየ መንገድ ምላሻቸው አንጸባርቀዋል። የሊትዌኒያ ፕሬዝዳንት ወዲያውኑ ስጦታውን ለብሔራዊ ሙዚየም የላከ ሲሆን የቤልጂየም ልዑካን የተቀበሉት ምን እንደሆነ ከፍተው ባለማየታቸው እና ምን እንደተሰጣቸው ባለመረዳታቸው ወደ ብራሰልስ እስኪመለሱ ድረስ ሳጥኑን አልከፈቱትም ነበር። ይህም ማለት ትክክለኛ የሚሰራ መሳሪያ ሳያውጁ በሀገሪቱ ድንበር በኩል በድብቅ አስገብተዋል ማለት ነው።