fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 317
مشترکین
-324 ساعت
-127 روز
-7530 روز
آرشیو پست ها
🇮🇷🇺🇸⚡️ከዚህ በፊት በትራምፕ ሕይወት ላይ የተቃጡትን ሁለት የግድያ ሙከራዎችን፣ እስራኤሎች፣ አቀናባሪዋ ኢራን እንደሆነች በመንገር፣ ትራምፕን እና በዙሪያው ያሉን በውስን ማሳመን ችለዋል። ትራምፕ ወጥቶ ኢራኖች ሊገድሉት እንደነበር ሲናገርም፣ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም። በአሜሪካ ባለስልጣናት ዘንድ የኢራንን ማስፈራራት እንደ ቀላል አያዩትም። ማስፈራራቷን አክብደው ሲወስዱ ነው የኖሩት። ኢራን፣ እንደ ሌንዚ ግርሃም ያሉ ጦርነቱን የሚያራግቡ ሴኔተሮችን እና ታዋቂ ግለሰቦችን እንደምትገድል ስታስፈራራ፣ ለእነዚህ ግለሰቦች ዋይት ሃውስ ጥበቃቸውን በአንድ ጊዜ ያጠናክራል። ዛሬ ሌንዚ ግርሃም በጥበቃ ተከቦ ነው ያለው። እናም የኢራንን ዛቻ የሚፈሩት በተጨባጭ ነው። ትናንትና በፃፍኩት ዘገባ፣ እስራኤል ለትራምፕ ኢራኖች ሊገድሉት እንደሚፈልጉ "አቃጠረች" ብዬ ነበር። ያንን የእስራኤሎችን ዘገባ ይዞ ነው ትራምፕ ይህን ሊል የቻለው። እስራኤሎች መረጃውን ደርሰውበት ሊሆን ይችላል ወይም ሊያጣሉት በመፈለጋቸውም ይሆናል ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። አንድ እውነት ግን አለ፣ ባለፈው ሳምንት ፣ አሁንም ድረስ፣ በአያቶላው የቀብር ሥነ ስርዓት ወቅት፣ ኢራኖች ትራምፕን ለመግደል ሲዝቱ አይተናል።

🇺🇸🇮🇷 - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በTruth Social ላይ፡ - 1000 ሚሳኤሎች ተቆልፈው ተጭነዋል እና በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ላይም ያነጣጠሩ ናቸው። በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ወዲያውኑ ይከ
🇺🇸🇮🇷 - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በTruth Social ላይ፡ - 1000 ሚሳኤሎች ተቆልፈው ተጭነዋል እና በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ላይም ያነጣጠሩ ናቸው። በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ወዲያውኑ ይከተላሉ። የኢራን መንግሥት በብዙ የዓለም ማዕዘናት የተነገረውን ዛቻቸውን በተግባር ቢተገብሩ እና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትን ለመግደል ቢሞክሩ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ፣ እኔን! ትዕዛዞች ቀድሞውኑ ተሰጥተዋል እናም የአሜሪካ ጦር ለአንድ ዓመት ያህል ጦርነቱን ለማራዘም ዝግጁ እና ፈቃደኛ የሆነ እና ችሎታ ያለው ነው፣ ሁሉንም የኢራን አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት እና ለመደምሰስ! ምስጋና ለአላህ ይገባው! ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕ

🇺🇸🇮🇷⚡ - "በቅርብ ሳምንታት ውስጥ፣ የመግባቢያ ስምምነቱ ከመፈረሙ በፊትም ቢሆን፣ ኦማን ከአሜሪካ እና ከባህረ ሰላጤው አጋሮቿ ጋር፣ ኢራንን ወደ ጎን ብላ፣ በሆርሙዝ ወሽመጥ ዳርቻው አቅራቢያ፣ ሌላ የመርከብ መተላለፊያ ከፍታ ነበር። ኢራን፣ ይህ የኦማን እርምጃ 'የመደራደሪያ ዋና አድቫንቴጄን የሚያዳክምብኝ ነው' በሚል፣ እጅግ ተቆጥታ ነበር። የአሜሪካ ባለስልጣናት 'የኢራን ተደራዳሪዎች 'እንደነገሩን' ባሉት መረጃ መሠረት፣ በገዥው መንግሥት ውስጥ ያሉ አክራሪ አካላት፣ ያጡ የመሰላቸውን የድርድር ኃይል መልሰው ለማግኘት፣ በመርከቦች ላይ ተኩስ እንደከፈቱ ተናግረዋል። በይፋ፣ የኢራን ተደራዳሪዎች፣ የ IRGC አዛዦች እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ቴህራን በባህር ዳርቻው ውስጥ ያለውን አካባቢ በኃይል እንድትቆጣጠር በጠየቁት ጥያቄ ግን፣ አንድ ሆነዋል" - Axios።

🇮🇱⚡️🇹🇷 ጥያቄ - ለምሳሌ በሶሪያ ውስጥ በቱርክ እና በእስራኤል መካከል ግጭት ቢፈጠር ያ አንቀጽ 5ን ያስነሳል? የኔቶ ፕሬዝዳንት ሩቴ - ኤርዶጋን እጅግ በጣም ጥበበኛ ፕሬዝዳንት ናቸው። በዚህ ሚና ውስጥ ለዓመታት ቆይተዋል እና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ሁኔታ ውስጥ ከመግባት ይቆጠባሉ። ጥያቄ - ኔታንያሁ ግጭትን የማይቀር ቢያደርግስ? ሩቴ- ምን ሊፈጠር እንደሚችል አንገምት። ጥቅምት 7፣ 2023ን መዘንጋት የለብንም። ሐማስ በእስራኤል ላይ ያደረሰው አስከፊ ጥቃት። *-*-* አንቀጽ 5 Article 5 የኔቶ ሕግ ነው። አንድ የኔቶ አባል ከተነካ፣ ሁሉም ይነሳል የሚል ሕግ ነው። ጋዜጠኛዋ እየጠየቀች ያለችው፣ ቱርክ (የኔቶ አባል) ከእስራኤል ጋር ብትገጥም፣ ኔቶ ከቱርክ ጎን ይሰለፋል ወይ? ነው የምትለው። የሩቶ መልስ ግራ የገባው ነው። ሐማስ እስራኤልን እንዳጠቃ መረሳት የለበትም ነው የሚለው። ምን አገናኘው? ቱርክ ከእስራኤል ጋር ተዋጋች ብሎ ኔቶ ከጎኗ የሚቆም ይመስላችኋል? እንደ እኔ፣ በፍፁም አይቆምም! የኔቶ ዋና አባል እና መሪ ማናት? አሜሪካ ናት። የእስራኤል ዋና ወዳጅና ደጋፊ ማናት? አሜሪካ ናት ነው መልሱ። አሜሪካ በእስራኤል (በወዳጅዋ) ላይ ለቱርክ (ለእስላሞች) ብላ ጦር ትመዛለች? አታደርገውም! ስለዚህ ቱርክና እስራኤል የሚገናኙ ከሆነ፣ የሚገናኙት ብቻ ለብቻ ነው። ማን ያሸንፋል?

🇮🇷 በአያቶላህ ኻመኒይ የቀብር ሥነ ሥርዓት ወቅት፣ በመሽሃድ ከተማ ግዙፍ የትራምፕ ሌጎ ችቦ ሆኗል። 'ሞት ለአምሪካ፣ ሞት ለእስራኢል' የሚሉ መፈክሮች ተጩኾዋል።

⚡️🇶🇦🇵🇰🇹🇷🇪🇬🇸🇦🇮🇷🇺🇸 🇮🇱 ከኳታር፣ ፓኪስታን፣ ቱርክ፣ ግብፅ እና ሳዑዲ አረቢያ የተውጣጡ ባለስልጣናት፣ ዕሮብ እለት ብዙ የስልክ ጥሪዎችን አድርገዋል፣ - Axios. ➡️ የተጠናከረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች በቀጥታ ከአሜሪካ እና ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ተካሂደዋል። ➡️ የተቀናጁ ዓለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎች የተደረጉት የቀጠናውን ሁኔታ ለማረጋጋት እና ውጥረቱን ለመቀነስ በታለመ ከፍተኛ ጥረት ነው። ➡️ እስራኤል በበኩሏ ለትራምፕ፣ "ከደህንነት በተገኘ መረጃ መሠረት"፣ ኢራኖች ሊገድሉህ ያስባሉ ስትል አቃጥራለች።

+5
🇷🇺🇺🇦⚡️ሩሲያ አፍሪካ ለምን መጣች? ምን ፈልጋለች? ኦፊሴላዊ የጉብኝቱን ምክኒያት እርሱት። እሱ ሽፋኑ ነው። ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ፈልጋለች? ይህንን እንደ ምክኒያት ማንም ባያነሳውም፣ ምናልባት ቅጥረኞችን ፈልገዋል። ቅጥረኛ በመቅጠር ዩክሬን ከሩሲያ በላይ ሄዳለች። በተለይ ከላቲን አሜሪካ፣ ከኮሎምቢያ፣ ብራዚል እና ቬኔዝዌላ በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች ከዩክሬን ጎን በገንዘብ ተቀጥረው ይዋጋሉ። የራሳቸው ብርጌድ፣ የራሳቸው ክፍለ ጦር እና መዋቅር ሁሉ አላቸው። ከአውሮፓ ሀገራትም፣ በተለይ ከምሥራቁ ክፍል፣ ብዙ ቅጥረኞች አሏት። በነገራችን ላይ፣ ዩክሬን የራሷን ተዋጊ ዕድሜ ያላቸውን ወንዶች ጨርሳ ነው፣ በስፋት ወደ ቀጠራው የሄደችው። ገሚሱ ተሰዷል። ሩሲያም በበኩሏ፣ ቅጥረኞችን አሰልፋ ትገኛለች፣ እንደ ዩክሬን የበዙ ባይሆንም፣ አሏት። በተለይ ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች የተመለመሉ በዩክሬን ጦር ሜዳዎች በመዋጋት ላይ ናቸው።   ጦርነቱ ከ25-35 ሺ ወታደሮችን በወር ከመጨረሱ ጋር፣ ምናልባት የዚህ የጉብኝቱ ውስጠ ወይራዊ ዓላማ፣ ተዋጊዎችን ፍለጋ ይሆናል። አሁን ላይ፣ ሩሲያ ኢትዮጵያን በዚህ ጉዳይ የምትጠይቃት ከሆነ፣ በስልጣን ያለው መንግሥት ሐሳቡን በደስታ ሊቀበል አያቅማማም። ለምን ቢባል፣ መንግሥታት እንዲህ ያሉ ጦርነቶችን ያስቸገራቸውን ሕዝብ ለመጨረስ ይጠቀሙበታል (አርጀቲና Afro አርጀንቲናዊያንን ወይም ጥቁር አርጀንቲናዊያንን ያጠፋችበትን መንገድ ታሪክ፣ መለስ ብላችሁ አንብቡት። እንደ ፈረንጆች 2022 በWashington Post የወጣውን ጽሑፍ ብታነቡት እመክራለሁ።) በተለይ የሰሜኑ ወጣት ተጠንቀቅ! የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት መልኩን ለውጧል። የሚያልቅ አይመስልም። አሁን ላይ meat grinder ሲሉ ይጠሩታል ጦርነቱን። የሥጋ ወፍጮ ማለታቸው ነው። ሩሲያ ብላችሁ እንዳትቀልጡ! *-

🇷🇺🇺🇦⚡️ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ፈልገው ይሆን ተጨማሪ ከአፍሪካ ሀገራት? ይህንን እንደ ምክኒያት ማንም ባያነሳውም፣ ምናልባት ቅጥረኞችን ፈልገዋል። ቅጥረኛ በመቅጠር ዩክሬን ከሩሲያ በላይ ሄዳለች። በተለይ ከላቲን አሜሪካ፣ ከኮሎምቢያና ብራዚል በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች ከዩክሬን ጎን በገንዘብ ተቀጥረው ይዋጋሉ። የራሳቸው ብርጌድ፣ ክለ ጦር እና መዋቅር ሁሉ አላቸው። ሩሲያም በበኩሏ፣ ቅጥረኞችን አሰልፋ ትገኛለች፣ እንደ ዩክሬን የበዙ ባይሆንም አሉ። በተለይ ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች የተመለመሉ  በዩክሬን ጦር ሜዳዎች በመዋጋት ላይ ናቸው።   ጦርነቱ ከ25-35 ሺ ወታደሮችን በቀን ከመጨረሱ ጋር፣ ምናልባት ተዋጊዎችን ፈልጋ እንዳይሆን። አሁን ላይ፣ ሩሲያ ኢትዮጵያን በዚህ ጉዳይ የምትጠይቃት ከሆነ፣ በስልጣን ያለው መንግሥት ሐሳቡን በደስታ ሊቀበል አያቅማማም። ለምን ቢባል፣ መንግሥታት እንዲህ ያሉ ጦርነቶችን ያስቸገራቸውን ሕዝብ ለመጨረስ ይጠቀሙበታል (አርጀቲና Afro አርጀንቲናዊያንን ወይም ጥቁር አርጀንቲናዊያንን ያጠፋችበትን መንገድ ታሪክ፣ መለስ ብላችሁ አንብቡት። እንደ ፈረንጆች 2022 በWashington Post የወጣውን ጽሑፍ ብታነቡት እመክራለሁ።) በተለይ የሰሜኑ ወጣት፣ ዐማራው፣ ተጠንቀቅ! ጦርነቱ መልኩን ለውጧል። አሁን ላይ meat grinder ሲሉ ይጠሩታል ጦርነቱን። የሥጋ ወፍጮ ማለታቸው ነው። ሩሲያ ብላችሁ እንዳትቀልጡ!

🇷🇺 ሩሲያ ከአሁን በኋላ ምዕራባውያን ለመደራደር ፍላጎት አላቸው ብላ አታምንም። - ሰርጌ ላቭሮቭ። የሩስያ ዲፕሎማሲ ኃላፊ፣ በአሁኑ ጊዜ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሥራ ጉብኝት አካል በሆነችው ሞዛምቢክ
🇷🇺 ሩሲያ ከአሁን በኋላ ምዕራባውያን ለመደራደር ፍላጎት አላቸው ብላ አታምንም። - ሰርጌ ላቭሮቭ። የሩስያ ዲፕሎማሲ ኃላፊ፣ በአሁኑ ጊዜ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሥራ ጉብኝት አካል በሆነችው ሞዛምቢክ፣ ጉብኝት ላይ ናቸው። *-*-*-

⚡️🇮🇷🇺🇸 Axios: የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ በኢራን ላይ የተደረገ ምንም ዓይነት ድብደባ የለም ብለዋል።

⚡️🇮🇱🇺🇸🇹🇷 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ አመሻሽ ላይ የስልክ ጥሪ ያደረጉ ሲሆን፣ በእስራኤል እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል በበርካታ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የጠበቀ ቅንጅታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ በቅርቡ አሜሪካ በባሕረ ሰላጤው ስላደረገችው እንቅስቃሴዎችም ለኔታንያሁ ገለጻ ሰጥቷል። በውይይቱ ወቅት፣ የኔታንያሁ ጽህፈት ቤት፣ የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋንን በእስራኤል ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የጥላቻ ንግግሮችና ትቢቱን በማንሳት፣ ደውሎ እንዲቆጣው ለፕሬዝዳንት ጥሪ አቅርቧል።

🇬🇷🇹🇷🇺🇸 የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስቴር፡ ኪሪያኮስ ሚቶስታኪስ፡ እኛም እንደ እስራኤል አሜሪካ ለቱርክ F35 አይሮፕላኖችን እንዳትሸጥ የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን። ማንም ምንም አያመጣም።

🇮🇷🇺🇸⚡️ኢራን 10 ባለስቲክ ሚሳዬል ወደ ጆርዳን መተኮሷ አስደንጋጭ መባባስ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሚሳዬሎቹ የተሸከሙት ተቀጣጣይ ፈንጅ ክብደት፣ ከዚህ በፊት ያላሳዩት ነው CNN

—❗️🇮🇷/🇮🇶 ኢራን፣ በሺ የሚቆጠሩ ልዩ ኃይሎቿን፣ በኢራን ኢራቅ/ኩርድ ድንበር ላይ ማሰለፏ ታውቋል። የIRGC ኮማንደር እንደገለጸው፣ ኩርዶች በማንኛውም መንገድ ከአሜሪካና እስራኤል ጋር ተባ
—❗️🇮🇷/🇮🇶 ኢራን፣ በሺ የሚቆጠሩ ልዩ ኃይሎቿን፣ በኢራን ኢራቅ/ኩርድ ድንበር ላይ ማሰለፏ ታውቋል። የIRGC ኮማንደር እንደገለጸው፣ ኩርዶች በማንኛውም መንገድ ከአሜሪካና እስራኤል ጋር ተባብረው ትንኮሳ ቢያደርጉ፣ ግዛታቸው ድረስ በመግባት "የፀጥታ ዞን" እንደሚመሰርቱ ተናግሯል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 በባግዳድ እና በጆርዳን አሜሪካ ጦር ሰፈሮች አቅራቢያ፣ የአደጋ ጊዜ ደውሎች ዋይ ዋይ እያሉ ናቸው። በቁጥር ብዙ የኢራን ሚሳዬሎች ወደነዚህ ሥፍራዎች ተተኩሰዋል። በጆርዳን የሚገኝ የአሜሪካ ፔትሪዮት አየር መቃወሚያ ሲስተም በቀጥታ ምት መውደሙን የሚያሳዩ ዘገባዎች እየወጡ ናቸው። የኢራን ጦር ኃይሎች "ከፍተኛ የጦርነት ንቃተ-ሕሊና ውስጥ" እንዲሆኑ እና እንዲዘጋጁም ትዕዛዝ ወርዷል።

🇮🇷🇺🇸⚡️ይህ፣ ትናንት ኢራን መርከቦች ላይ ለፈፀመችው ጥቃት የተወሰደ አፀፋዊ እርምጃ ነው። የሚደገም ከሆነ፣ እርምጃችን የባሰ ይሆናል።
🇮🇷🇺🇸⚡️ይህ፣ ትናንት ኢራን መርከቦች ላይ ለፈፀመችው ጥቃት የተወሰደ አፀፋዊ እርምጃ ነው። የሚደገም ከሆነ፣ እርምጃችን የባሰ ይሆናል።

+6
🇪🇹🇷🇺🇲🇱🇧🇯🇳🇪 የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ሰርጌ ላቭሮቭ፣ ትናንትና ወደ ምዕራብ አፍሪካ እየተጓዘ ሳለ መንገድ ላይ ሽንቱ መጥቶበት አዲስ አበባ ወርዶ እንደነበር ሰምተናል። እንደወረደም በቀጥታ፣ "ሽንት ቤቱን አሳዩኝ፣ የቱ ጋ ነው" ሲል እንደነበር ምንጮቼ ነግረውኛል። ምሽት ላይ ስለነበር ያረፈው፣ እዚሁ እደር፣ ቡና ጠጣ፣ ራትም ብላና ነገ ትሄዳለህ ብለውት፣ በመነጋታው ተነስቶ ወደ ጉዳዩ እንደሄደ ነው የማውቀው። ሰርጌ ላቭሮቭ፣ ከቡርኪና ፋሶ፣ ከኒጀር፣ ከማሊ እና ከሌሎች ሀገር መሪዎች ጋር መገናኘቱን እና ጉብኝቱ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑ ታውቋል። *-*-*-

🇮🇷🇺🇸⚡️IRGC: አታላይዋ አሜሪካ፣ በድጋሚ የገባችውን ቃል በመጣስ፣ በኢራን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ አውራጃዎች በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝራለች። 🔺 በሌላ ፀረ-ሲቪል ድርጊቷም፣
🇮🇷🇺🇸⚡️IRGC: አታላይዋ አሜሪካ፣ በድጋሚ የገባችውን ቃል በመጣስ፣ በኢራን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ አውራጃዎች በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝራለች። 🔺 በሌላ ፀረ-ሲቪል ድርጊቷም፣ በሀገሪቱ ምስራቃዊ አውራጃዎች ወደ ቅድስት ከተማ ማሽሃድ የሚወስዱ ሁለት ድልድዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሰነዘረች ሲሆን ይህም የሰማዕቱን መሪ የስንብት ሥነ ሥርዓት ለመሸፈን የተሞከረ ነበር። 🔺 እንደነዚህ ያሉት ወንጀሎች በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን የበለጠ እንደሚያነቃቁ እና "ከታላቁ ሰይጣን" ጋር በሚደረገው ትግል ውስጥ የበለጠ ሚና ለመጫወት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያጠናክር ሊገነዘቡ አልቻሉም። 🔺 የእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን ተዋጊዎች፣ ሕጻናትን ለሚገድል የአሜሪካን ጦር ጥቃት፣ ምላሽ ሳይሰጥ አይተዉም!