🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
1 137
مشترکین
+5524 ساعت
+1447 روز
+41030 روز
آرشیو پست ها
ሁሌም እውነተኛ ሁን
◃ አዛኙ ውዱ ነብያችን እንዲህ በማለት ይመክሩናል፦
➭አደራ እውነተኛ በመሆን ላይ!
➭እውነት ወደ መልካም ተግባር ይመራል!
➭መልካም ተግባር ደሞ ወደ ጀነት ይመራል!
Repost from الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
👆✅✍ ሶሂህ
ዘረኝነት ሲባል አማራ ኦሮሞ ብቻ አይደለም ። የግሩፕ፣ የቻናል ፣ የዳእዋ የብዙነገር ዘረኝነት ተስፋፍቶብናል💧 አሏህ ልባችንን ካለበት መጣበብ ካረፈበት ክፉ ጠባሳ ያንፃልን ያስተካክለን ጀሊሉ
🪴ማራኪ ቲላዋ🪴
የጌታችን የአላህን ቁርዓን እንቅራው📖
ከልቻልን እናዳምጠው 🎧
🎤ቃሪእ ኡመር ሂሻም🍃
ሱረቱል~ አረህማን
http://t.me/UmuAbais
አንዳድ እህቶቻችን ዘረኝነት ተጠናዉቷቸዉ ይታያል አኡዙቢላህ ሚን ዛሊክ እኛን አንድ የሚያደርገን ተዉሂድ እጅ ቢሄር ፡ጎሳ ፡ቆንቆ ፡ከለር ፡አይደለም ሀቢብቲ ራስሽን ከዚህ ተግባር አርቂ የተማርሽውን ትምህርት ተግባር ላይ ካላዋልሽዉ ምን አለፋሽ አርፈሽ ተቀመጪ አተረፍኩ ብለሽ አታክስሪ ዘረኝነት ጥንብ ናት ብለዋል ዉዱ ነብያችን አሁን ላይ አላህ ያዘነለት ሲቀር የከሌ ጀመአ ግሩፕ የከሌ ሀገር ግሩፕ ግሩፑ ላይ ያለው ሰው ደግሞ የሚገርመው ከየሀገሩ የተሰበሰበ ነው ሀገሩ ብቻ ነው ስሙ የተለየው ከዚህ የበለጠ ዘረኝነት አለደ ተቆጠቡ መክፈት ካለብን የሱና እህቶች ጀመአ ብለን እንክፈት መተዋወስ መተዋወቅ ከፈለጋችሁ በተለይ አንድ ግሩፕ ላይ የአንድ ሀገር ልጆች አንድ ግሩፕ ላይ ተቀምጣችሁ አንድ የሌላ ሀገር ልጅ የሆነ ነገር ስትናገር መተባበር ምን አመጣው ከዚህ የበለጠ ዘረኝነት አለደ እረ እባካችሁ አቅል ተሰቷናል እናስብ
Repost from N/a
🚨ፈጥኖ ማን ይመልስ ‼️🏃➡️🏃➡️
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው
ምርጥ እና ጠቃሚ ቻናልያገኛል ።
👉ጥያቄ፦ ቁርዓን ስንት ምዕራፍ አለው⁉
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
ተስሒሑ ቲላዋ
በሙሐመድ ሲራጅ አል ከሚሴ
https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie?livestream=73a70d82ed2818e2fc
▶️የመጀመሪያዉ ፕሮግራም▶️
🎙ኡስታዝ አቡል ሁበይብ
ርዕስ አጠቃይ ምክር ለጧሊበል ዒልሞች
ተ⭐️
ጀ🔴
መ⭐️
ረ🔴
ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም!
ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት
📥📥📥📥📥📥📥📥
▶️ https://t.me/sobabilelmesjide
⚠️ ዘረኝነት በሰለፊዮች መካከል ቦታ የሌለው የጃሂሊያ ባህሪ ነው⁉️
♦️አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ በዘሩ፣ በጎሳው፣ በቤተሰቡ፣ በአገሩ፣ በቋንቋው ወይም በቀለሙ ምክንያት ሲበልጥ እና ሲያንስ ማድረግ ሲጀምር፣ ይህ የእስልምና መለኪያ አይደለም።
አላህ ለሰዎች የሰጠው የዘርና የጎሳ ልዩነት ራሱ ችግር አይደለም። ችግሩ የሚጀምረው ይህንን ልዩነት ለመኩራራት፣ ለመናቅና ለመከፋፈል መጠቀም ስንጀምር ነው።
📖 የአላህ መለኪያ ልንከተል ይገባል።
አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ይላል፦
﴿يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُمْ مِنْ ذَكَرٍ وَأُنْثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِنْدَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ﴾
“እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፤ እርስ በርሳችሁ እንድትተዋወቁም ሕዝቦችና ጎሳዎች አደረግናችሁ። ከእናንተ በአላህ ዘንድ የተከበረው በጣም የሚፈራው ነው።”
(ሱረቱል ሑጁራት 49፥13)
ተመልከቱ፤ አላህ “ልትበላሉ ልትከፋፈሉ” አላለም፤ “لِتَعَارَفُوا — እርስ በርሳችሁ እንድትተዋወቁ” ነው ያለው።
ከዚያም የክብር መለኪያውን ግልጽ አደረገ፦
﴿إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِنْدَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ﴾
“በአላህ ዘንድ ከእናንተ የተከበረው በጣም የተቀደሰው (ተቀዋ ያለው) ነው።”
ስለዚህ አንድ ሰው ከየት እንደመጣ ከመጠየቅ በፊት፣ ከአላህ ጋር ያለው ግንኙነቱ ነው የሚመዘነው።
🌿ነቢዩ ﷺ የጃሂሊያ ጥሪ ብለው የገሰጹት
አንድ ጊዜ ከሙሐጂሮች አንዱ ከአንሷሮች አንዱን ተጣሉ። ከዚያም እያንዳንዱ ቡድን ወገኑን ለመጥራት ጀመረ፦
⚠️“ያሙሐጂሮች ሆይ!”
⚠️“የአንሷሮች ሆይ!” ብለው ሁሉም ዘሩን ተጣራ። ይህ ለነቢዩ ﷺ ሲደርስ፣ እንዲህ ብለው ገሰጹ፦
«دَعُوهَا فَإِنَّهَا مُنْتِنَةٌ»
“ተዉት፤ እርሷ የሚያስጠላ ቆሻሻ ነገር ናት!”አሉ
ከዚያም፦
«أَبِدَعْوَى الْجَاهِلِيَّةِ وَأَنَا بَيْنَ أَظْهُرِكُمْ؟»
“እኔ በመካከላችሁ እያለሁ የጃሂሊያን ጥሪ ትጠራላችሁን?”ብለዋል። በጣም ተቆጡ ፊታቸው አስከሚቀያየር ድረስ።
ይህ በጣም ትልቅ ትምህርት ነው።
♦️ሙሐጂር የሚለው እንኳ የክብር የእስልምና ስም ነው።
♦️አንሷሪ የሚለውም እንዲሁ የክብር ስም ነው።
ነገር ግን እነዚህ ስሞች የቡድን ጥላቻና የጭፍን ወገንተኝነት መሣሪያ ሲሆኑ፣ ነቢዩ ﷺ የጃሂሊያ ጥሪ ብለው ገሰጹት።
🌿 ሰለፊይ ነን ካልን ይህን እንማር
የሰለፎች መንገድ በኪታብና ሱና ላይ መቆም ነው።
ስለዚህ የሱና ሰው ከእውነት ጋር ይቆማል፤ እውነት ከማንም ጋር ቢሆን። የራሳችን ዘር ስለሆነ ብቻ በደልን አንደግፍም።
◆ የራሳችን አገር ስለሆነ ብቻ ስህተትን አንከተልም።
◆ የራሳችን ቡድን ስለሆነ ብቻ አንደግፍም።
እና ከሌላ ዘር የመጣ ሰው ስለሆነ ብቻ አንንቅም።
🔹መለኪያው እውነት ነው።
🔹መለኪያው ተቀዋ ነው።
🔹መለኪያው ሱና ነው።
🔹መለኪያው እስልምና ነው።
አንድ ሰው ከእኛ የተለየ ዘር ቢሆንም የእምነት ወንድማችን/እህታችን ነው።
⚠️ በተለይ ሰለፊይ ለእህቶቻችን የምታሳዩት የዘር መከፋፈል መጣም የሚያሳዝን ነው።
እህቶቼ ሆይ፣ በዘር ምክንያት እርስ በርሳችሁ እንዳትጣሉ።
“እኔ ከዚህ ነኝ፣ እሷ ከዚያ ናት” እኔ አማራ ነኝ እሷ ኦሮሞ ናት እኔ ትግሬ ነኝ እሷ ስልጤ ናት" ብሎ በመከፋፈል የሙስሊምን የእህቶቻችሁን ልብ አትስበሩ።
⚠️አንዲት እህት ከሌላ ዘር መሆኗ ከእኛ ያነሰች አያደርጋትም።
⚠️አንዲት እህት ቋንቋችንን በደንብ ስለማትናገር ያነሰች አይደለችም።
⚠️አንዲት እህት ከሌላ ጎሳ ስለሆነች ከእኛ ያነሰች አይደለችም።
⚠️እኛ ሁላችንም የአደም ልጆች ነን፤
⚠️ አደምም ከአፈር ነው።
የትኛዋ እህት ከአላህ ዘንድ የተሻለች እንደሆነች የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው።
ምናልባት እኛ የምንንቃት እህት ከእኛ የበለጠ በአላህ ዘንድ ክብር ያላት ሊሆን ይችላል።በዘር ከማንቋሽሽ ተጠንቀቁ።
⚠️ የሰለፊያ እህትነት ከዘር በላይ ነው
አንዲት እህት ከእኛ ጋር በተውሒድ፣ በሱና በሰለፊያ መንሐጅ በመልካም አምልኮ ላይ ከቆመች፣ የሚያገናኘን ነገር ከሚለየን በጣም ይበልጣል።
🔸እኛ አንድ ጎሳ ስላልሆንን አንጠላላም።
🔸አንድ ቋንቋ ስላልተናገርን አንከፋፈልም።
🔸አንድ አገር ስላልሆነች አንናቃትም።
🔸የሚያገናኘን ላ ኢላሃ ኢለላህ ነው።
🔸የሚያገናኘን ኪታቡ ነው።
🔸የሚያገናኘን ሱናው ነው።
🔸የሚያገናኘን ነቢዩ ﷺ ነው።
ይህ ከሁሉም የበለጠ የሚያስተሳስር ነው።
⚠️ ዘረኝነት በአንድ ቀን አይጀምርም
መጀመሪያ፦ “የእኛ ሰዎች ናቸው” ይላል።
ከዚያ፦ “እነሱ እንደኛ አይደሉም” ይላል።
ቀጥሎ፦ “እነሱን አትቀርቧቸው” ይላል።
በመጨረሻም የሙስሊም ልብ በሌላ ሙስሊም ላይ በጥላቻ ይሞላል።
እንዲህ ያለው መንገድ የሚያስፈራ ነው።
ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ የጎሳ ወይም የቡድን ድጋፍ በደልን ለመደገፍ ሲሆን የጃሂሊያ ባህሪ መሆኑን ገልጸዋል።
⚠️ ስለዚህ እህቶቼ ሆይ…
●እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
●እርስ በርሳችሁ ተሳሰቡ።
●እርስ በርሳችሁ ተሸፋፈኑ።
●እርስ በርሳችሁ ዱዓ አድርጉ።
●አንዲት እህት ስትሳሳት በዘርዋ አትውቀሷት፤ በስህተቷ ምክር ስጧትጅ።
●አንዲት እህት ስትበረታ በዘርዋ አትቀኑባት፤ በመልካምነቷ ደስ ይበላችሁ።
●አንዲት እህት ስትወድቅ አትገፏት፤ እጇን ያዙ።
ሰለፊይ ማለት የራሳችንን ወገን በተሳሳተ ነገር ላይ መደገፍ አይደለም፤ እውነትን መደገፍና በመመካከር ነው።
የእውነት ወገንተኝነት ከጎሳ ወገንተኝነት ይለያል።
🌿 ጎሳችን ለመተዋወቅ ነው፤ ለመኩራራት አይደለም።
🌿 ዘራችን ለመለያየት ነው፤ ለመናቅ አይደለም።
🌿 ልዩነታችን የአላህ ፍጥረት ነው፤ የጥላቻ ምክንያት አይደለም።
🌿 መለኪያችን ዘር ሳይሆን ተቀዋ ነው።
ኢላሒ...! በሙስሊሞች ልቦች መካከል ፍቅርንና አንድነትን ስጥ፤ የጃሂሊያ ዘረኝነትንና ጭፍን ወገንተኝነትን ከልቦቻችን አስወግድ።
اللَّهُمَّ أَلِّفْ بَيْنَ قُلُوبِنَا، وَأَصْلِحْ ذَاتَ بَيْنِنَا، وَاهْدِنَا سُبُلَ السَّلَامِ.
አላህ ሆይ፣ ልቦቻችንን አቀራርብ፣ መካከላችንን አስተካክል፣ ወደ ሰላም መንገዶችም ምራን።
🤍 እኛ የተለያዩ ጎሳዎች ልጆች ልንሆን እንችላለን፤ ግን አንድ ቂብላ፣ አንድ ኪታብ፣ አንድ ነቢይ ﷺ እና አንድ ዲን አለን። ይህን የሚያህል ትልቅ አንድነት ለትንሽ የዘር ልዩነት አንሸጠው።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት ሀሰት በማለት መልሱ ።
ነቢዩሏህ ኢብራሂም ለመጀመሪያ ጊዜ በሰይፍ የተዋጉ ነቢይ ናቸው ፡፡
ታላቅ የሙሓደራ ፕሮግም🖱የዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን፦💡 🇸🇦. ኡስታዝ አቡል ሁበይብ🌟 ⬅️ርዕስ🔴 አጠቃይ ምክር ለጧሊበል ዒልሞች➡️ 🇸🇦. ወንድም አቡ ኢምራን🌟 👈 ርዕስ🔴 ሞት➡️ 🇸🇦. ወንድም አቡ ሹራ አህመድ🌟 ⬅️ርዕስ🔴 በሰአቱ➡️ 🙁☹️😭🙁😭🙁☹️ 🔘 ፕሮግራሙ አቡ ሹራ ይመራል 🕰 የፕሮግራም ሰዓት ፡ 😴 ጅሙዓ ምሽት √ 🔻2:00 ~ በኢትዮ 🔺8:00 ~ በሳዑዲ 🔻9:00 ~ በዱባይ 🛜 ፕሮግራሙ የሚካሄደው 🔽 📥📥📥📥📥📥📥📥 ▶️https://t.me/sobabilelmesjide
╔═════════════════════════╗
✨ 1,000 SUBSCRIBERS ✨
╚═════════════════════════╝
🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحاتውድ የቻናላችን ተከታዮች፤ ዛሬ 1,000 (1K) አባላት ደርሰናል! ከጎናችን ሆናችሁ ሀሳቦቻችንን ለምታበራቱልንና አብራችሁን ላላችሁ በሙሉ የላቀ ምስጋናችን ይድረሳችሁ። «መልካም ነገርን ያመለከተ እንደሰራው ይቆጠራል» እና መልካም ነገሮች ለሌሎችም እንዲደርሱ ቻናላችንን SHARE በማድረግ አብራችሁን ተጓዙ! ✨ 🔗 [https://t.me/Asselefiyah_Channel] 🔗 [https://t.me/Asselefiyah_Channel] ──────── ──────── ────────
السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكاتُهُ
ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው የተስሒሑ ቲላዋ ፕሮግራማችን በአላህ ፍቃድ ዛሬ እንጀምራለን ኢንሻአሏህ🎙በወንድማችን ሙሐመድ ሲራጅ አል ኬሚሴ 🔴የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ 🌟https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie
Repost from 🎁የሀርቡ እና አካባቢዋ ሰለፊዮች መገናኛ🛍
•••♕❀
وَتَشهَدُ كُلَّ يَومٍ دَفنَ خِلٍّكَأَنَّكَ لا تُرادُ بِما شَهِدتا وَلَم تُخلَق لِتَعمُرها وَلَكِن لِتَعبُرَها فَجِدَّ لِما خُلِقت.
