✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
رفتن به کانال در Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
193
مشترکین
-224 ساعت
-47 روز
-630 روز
آرشیو پست ها
የሰለፊ ባል ታላቅ ፀጋ ነው
እህቶቼ እዚህ ጋር ልብ ልትሉ የሚገባው አንድ ሰለፊ ባል ያገባች ሴት ለመጀመሪያም ይሁን ለሁለተኛ ለሶስተኛም ይሁን ለአራተኛ ሚስትነት ፣ ያ ሰለፊይ ባሏ መጥፎ ባህሪ ያለው ከሆነ ወይም ብዙ ሚስቶች ካሉትና በመካከላቸው በፍትህ የማያስተዳድር በዳይ ከሆነ… ሌሎችም ችግሮች ካሉበት ሊወቀስ የሚገባው ራሱ ነውጅ ሁሉም ሰለፊዮች በአጠቃላይ አይደሉም ሰለፊዮች በአጠቃላይ መጥፎ ናቸው ማለት አይደለም። በጭራሽ ሁሉንም ሰለፊዮች ባጠቃላይ መውቀስ የለብንም፣ ይህ የሚያሳየው የዚህ ባል ባህሪ መጥፎ መሆኑን ነው እንጂ ከሰለፍያ መንሐጅ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።
ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "ዲኑንና ባህሪውን የምትወዱት ሰው ከመጣላችሁ [ሴት ልጆቻችሁን አጋቡት]።" ዲኑን ብቻ አላለም። ምን ያህል ጥሩ እና ግሩም ምሳሌዎችን አይተናል። ስለዚህ መልካም ባህሪ ያለው ጠንካራ ሰለፊ ባል በዚህች ምድር ላይ የተሰጠ ትልቅ ፀጋ ነው። ወደ ጀነት የሚመራሽ የህይወት አጋር መሆን ቀላል ነገር አይደለም።
ሰለፊይ ባል ተውሂድን ሲያስተምርሽ ታይዋለሽ፣ ሰላቶችሽን ስታዘገዪ ወይም ቁርአንሽን ስትረሺ ይገስፅሻል ያስታውስሻል ፣ አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥምሽ ይረዳሻል፣ ዚክሮችን ያነብልሻል፣ የዲን መጽሃፎችንና የሰለፍ صالح ሰዎችን ታሪክ እንድታነቢ ይመክርሻል፣ አላህ ከእርሱ ጋር በጀነት እንድትሆኑ ይለምናል። ከአጅነብይ ወንዶችና መሰሎች እይታ ይከልልሻል፣ አንቺን ብቻ ነው የሚፈልገው እንጂ ሌላን አይደለም።
በዚህ ዘመን ካሉት አብዛሀኛዎቹ ወንዶች በተለየ መልኩ፣ ከሚስቶቻቸው ጋር ወጥተው ሚስቶቻቸው የተኳኩሉና ያጌጡ ሆነው በመንገድ ላይ ሲንሸራሸሩ፣ እነሱ ምንም ቃል ሳይናገሩ አብረዋቸው የሚሄዱ አልጫ ወንዶች በበዙበት ዘመን ሚስቱን በኒቃብ ሸፍኖ የሚያኖር ሰለፊይ ባል ትልቅ የአላህ ፀጋ ነው ። አላህ እኛንም እነሱንም ይምራ። ስለዚህ እህቴ ሰለፊይ ባል አላህ ከወፈቀሽ ይህ ትልቅ ስጦታ ነውና አጥብቀሽ ያዥው።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ወሬ ከመጀምርህ በፊት…
ረሱል (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَنْ بَدَأَ بالكلامِ قبلَ السلامِ، فلا تُجِيبوهُ﴾
“ከሰላምታ በፊት በወሬ የጀመረን አትመልሱለት።”
ሶሂህ አልጃሚ
በራያ ሙስሊሞች ዙሪያ ለተደቀኑ ችግሮች የመፍትሄ ሐሳብ
መ.የትምህርት ዘመቻ(campaign) ማድረግ
ህዝበ ሙስሊሙ አሁን ላለበት ውጥንቅጥ መንስኤ አንዱ አለመማሩ። በገጠሩ ብቻ ሳይሆን በከተማውም ሙስሊሙ
ለትምህርት ያለው አመለካከት አሉታዊ ነው። ኢስላማዊና አካዳሚክ ትምህርት ሁሉም የራያ ሙስሊም እንዲማር ሰፊ ቅስቀሳ ዘመቻ በማድረግ ማንቃት ይጠብቅብናል። ከዚህ በተጨማሪ ሙስሊም በሚበዛባቸው የገጠር አከባቢዎች ትምህርት ቤት እንዲሰራ በመንግስት ላይ ጫና በማሳደር የትምህርት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ።
ትምህርት የሚማሩ ልጆችም በትክክል ቱክረት ሰጥተው እንዲማሩ ግንዛቤ መፍጠር፤ በተጨማሪም በመስጂዶች ላይበራሪ በማዘጋጀት እንዲያነቡና እርስበርሳቸው እንዲደጋገፉ ማድረግ።
ትምህርት የመማር ፍላጎት ኑሯቸው በአቅም ማነስ ምክያት ሊማሩ ያልቻሉትን መደገፍ። በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ የራያ ልጆች የደብተር፣እስክርቢሮት፣ፖርሳና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ በማድረግ ህዝበ ሙስሊሙ ልጆቹን እንዲያስተምር ማበረታት።
ሠ.በፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ መሆን
ህዝበ ሙስሊሙ መብቱን ማስከበር የሚችለው በፖለቲካው የሚገባውንና እኩል ውክልና ማግኘት ሲችል ነው። እኩል ውክልና ለማግኘት ደግሞ ንቁ ተሳታፊ መሆን ይኖርበታል።ሁሉም ሙስሊም አንድ አይነት የፖለቲካ አቋም ይኑረው ማለት ባይቻልም በአላማ ግን አንድ መሆን ይኖርባቸዋል።
አንድ ሙስሊሙ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሲሆን የሙስሊሙን ችግር ለመቅረፍና ለህዝበ ሙስሊሙ ድምፅ እንዲያገኝበማሰብ ሊሆን ይገባል። ሙስሊሞች ንቁ ተሳታፊ ሲሆኑ በሚረቁና በሚጸድቁ ህጎችና ድንጋጌዎች የሙስሊሙን አቋም ማንፀባረቅና ሙስሊሙን ሊጎዱ የሚችሉ ወይም ከሙስሊሙ የማይስማሙ ድንጋጌዎች ማሰቀረት ይችላል።
በዚህ ስሌት ከተመለከትነው ሁሉም ሙስሊም አንድ አይነት የፖለቲካ ርዕየተ አለም አራማጅ መሆን አለበት የሚለው ሀሳብ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዛኝ ይሆናል። ምክንያቱም ሙስሊም በሁሉም ፖርቲዎች ንቁ ተሳታፊና በቂ ውክልና ካገኘ ችግሮቹን ምፍታት ይችላል ነገርግን አንድ ፓርቲ ላይ ይሙጥኝ ማለት ከፓርቲው ውድቀት ጋር የሙስሊሙም ውድቀት ማቆራኘት ይሆናል።
ልሂቃኑ ውጭ ያለው ህዝበ ሙስሊሙ መብቱን የሚያስከብርለት፣ በራያ ታሪክ አባቶቹ ያበረከቱትን አስተዋፆኦ እውቅና የሚሰጥ እንዲሁም ለህዝበ ሙስሊሙ የሚገባውን ውክልናና ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚያረጋግጥን የፖለቲካ ድርጅት መደግፍ ይኖርበታል።
ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት በተለይ የተማረው ወጣት በፖለቲካው ዘርፍ በንቃት በመሳተፍ ሙስሊሙን ሊያገሉ ይሚችሉ ዉሳኔዎችን ማሰቀረት ይችላል።
ይህ በእንዲሀ እንዳለ አሁን ላይ የምንመለከታቸው ሹክቻዎች አሳሳቢ ናቸው ፤ የፖለቲካ ጉዳዮች ከመስጂድ ወጭ ማለቅ ይኖርባቸዋል። ህዝበ ሙስሊሙ ባለው ተጨባጭ በፖለቲካ አመለካከቱ የተለያየ ነው ሰለዚህ በሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ፖለቲካን ማስገባት በሙስሊሙ መካከል አንድነት እንዳይመጣ ያደርጋል። ይህንን ስል በገለሰብ ወይም በቡድን ሙስሊሙ በፖለቲካ እንዴት መሳተፍ አለበት የሚለውን መወያየት የለብንም እያልኩ አይደለም። ሙስሊሙ የመጨረሻ ግቡ የሙስሊሞች እኩል ተሳታፊነትና መብት ማሰከበር መሆን ይኖርበታል።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ደቡብ የመንን ከሰሜኑ ለመገንጠል በሚደረግ አስቀያሚ ፖለቲካ የተነሳ የሃገሪቱ ውስጣዊ ችግር ከድጡ ወደ ማጡ እየሄደ ነው። ወትሮም ሰላም የራቃት የ0ረቡ ዓለም ድሃ ሃገር የመን ከሆነ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ችግሯ ተባብሶ ይበልጥ መንናጥ ይዛለች። የሚያሳዝነው በዚህ ሃገሪቱን ለመገንጠል በሚደረገው ነውረኛ ፊትና ውስጥ ራሳቸውን ወደ ሰለፊያ የሚያስጠጉ አንዳንድ አካላት መኖራቸው ነው።
ብሄርን፣ ጎሳን፣ የፖለቲካ ዝንባሌን መነሻ በማድረግ ህዝብን ከህዝብ የሚያራርቅ "ትግል" በሃገራችንም በሰፊው እንዳለ ይታወቃል። "ዘር ከልጓም ይስባል" እንዲሉ ዘር እየጎተተው ለዲን የማይጠቅሙ የፖለቲካ ኃይሎችን የሚደግፈው ሙስሊም በሰሜንም በደቡብም ብዙ ነው። አንድነት ኃይል ነው። ብርታትና ጥንካሬ ያለው በህብረት ውስጥ ነው። እንኳን እንደ የመን ላሉ እምነትና ባህል ለሚያስተሳስራቸው ህዝቦች ቀርቶ የሃገር መፍረስ ብዙ መልክ ላለን ለኛ እንኳ የሚጠቅም አይደለም። ለአንዳችንም! በሃገር መበተን ውስጥ የሚጠቀም አንድም የኢትዮጵያ ሙስሊም ብሄር የለም። እንዲያውም ይበልጥ ተጎጂዎች ነን። የምናተርፍ የሚመስለን ጉዳዩን ከሁሉም አቅጣጫ ሳይሆን ከሆነች አንግል ብቻ ስለምንመለከት ወይም የቁጭትና የጥላቻ ስብከት ሰለባ ስለምንሆን ነው። አላህ ማስተዋሉን ይስጠን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ወደ ሐራም መመልከት ....
አይንን መስበር እና የቀልብ ድርቀት - ከ ሙሐደራ የተቆረጠ
አጭር ምክር
ሙሐመድ ሲራጅ ሙ/ኑር
https://t.me/msirage4
በራያ ሙስሊሞች ዙሪያ ለተደቀኑ ችግሮች የመፍትሄ ሐሳብ
የዘረዘርኳቸው ችግሮች መፍታት ካልቻልን ህልውናችን የመክሰም አደጋ እንደሚደርሰው ቅንጣት ታክል
የሚያጠራጥር አይደልም። ታሪካችንን በቱክረት ለተመለከተው ሰው ከከፍታ እንዴት ተምዘግዝገን እንደወረድን ይረዳል።
ስለዚህ ለችግሮቻችን መፍትሔ ማበጀት ይደር የማይባል የዛሬ ስራችን ነው። መፍትሔ ይሆናል ብዬ ያመንኳቸው እንደሚከተለው አቀርባለሁ።
1ኛ.ችግሮቻችን ኢስላማዊ በሆነ መንግድ ምፍታት
በሰዎች መካከል ልዩነት መኖር ተፈጥራዊ ነው። ችግሮችን በሀይል ለምፍታት መምከር ግን ኢተፈጥራዊ ብቻ ሳይሆን
የጥፋት መንገድም ጭምር ነው።
ልዩነታችንን ኢስላማዊ በሆነ መንገድ ከመፍታት ይልቅ መንግስታዊ ወዋቅር በመጠቀም የሙስሊሙን አንድነት እንዴት እንደሸረሸሩት፣ መስጂዶችና መድረሳዎችን እንዴት እንዳወደሙት የቅርብ ትዝታችን ነው። ይህንን ግፍ የፈጸሙና የጉዳቱ ሰላባ የሆኑ ወንድሞቻን በህይወት አሉ። አጥፊዎቹ የሄዱበት መንገድ ምን ያክል ኪሳራ ውስጥ እንደከተተን
ለራያ ሙስሊም መንገር ለቀባሪ ማርዳት ነው።
ከዚህ በፊት መንግስታዊ መዋቅር ተጠቅመው ህዝበ ሙስሊሙን የበደሉ፣ተቋሞቹን ያፈራረሱና አሁን ላለበት የመጥፋት አደጋ ያጋለጡት ስዎች ከጥፋተቸው ተምረው ህዝበ ሙስሊሙን ይቅርታ ጠይቀው ችግሮቻቸውን ኢስላማዊ በሆነ
መልኩ ለምፍታት ከውዲሁ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል። የተበደሉ ኡለሞቻችንና ወንድሞቻችን እንዲሁም አጠቃላይ የራያ ሙስሊም ከልቡ ይቅርታው ለመቀበል መዘጋጀት ይኖርብታል።
ኢስላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት ሲባል ሁለት ነገሮችን አካቶ ይይዛል
ሀ) ልዩነትን በቁርአንና ሀዲስ መፍታት
አላህ(ሱ.ወ) በመከካከላችን ልዩነት ሲፈጠር ወደ አላህና መልዕከተኛው በመመለስ መፍትሔ መፈለግ እንዲሚገባን ነግሮናል።
« እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡
በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡» አን-ኒሳእ 59
ልዩነትን ወደ አላህና መልእክተኛው በመመልስ በቁርአንና ሀዲስ መፍታት ውዴታ ሳይሆን መለኮታዊ ትዕዛዝ
ነው።
ስለዚህ በሀሳብ የማይስማማህን «ወሀብያ» የሚል ታፔላ በመስጠትና የመንግስት ደጅ በመጥናት የሚፈታ
ችግር ባለመኖሩ ሁሉም ወደ አላህና ነብዩ መንገድ መመልስ ይኖርበታል።
ይህንን ለማሳካትም በመላ ራያ በተከተታይ የውይይትና የመግባብያ መድረኮች በማድረግ ህዝብም እንዲሳተፍ እድሉን በመስጠት ልዩንታችን በቁርአንና ሀዲስ መፍታት ይኖርብናል።
እኔ ብቻ ነኝ ልክ ሌላው ሙስሊም አይደለም፣ማሰተማር አይችልም የሚለው ህገወጥ አቋም ካሁን ብኋላ ራያ ላይ ቦታ የለዉም።
ለ) የችግር መንሰኤ የሆኑትን ከሀላፊነት ማስወገድ
ከመግስት ጋር በመሆን ህዝበ ሙስሊሙን ያሳሰሩ፣መስጂዶችና መድረሳዎች የዘጉ ወደ መኖርያ ቤት የቀየሩ፣ እድሮች እንዲፈርሱ ያደረጉ፣የሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄ ያኮላሹ የቀድሞ መጅሊስ አመራሮች ለበደሉት ህዝበ ሙስሊም ይቅርታ ጠይቀው ከሀላፊነቸው ሊነሱ ይገባል። በእርግጥ ላጠፉት ጥፋት ፍትህ መረጋገጥ ቢኖርበትም አላህ ይቅርታ እድናደርግ ባዘዘን መሰረት ህዝበ ሙስሊሙ ይቅር ይላቸዋል። እነዚህ ስዎች ከሀላፊነታቸው ከተነሱ ብኋላ በሁሉም የራያ አከባቢዎች ህዝበ ሙስሊሙ የመጅሊስ አመራሮች ፣ኢማሞች በነጻት እንዲመርጥ ማድረግ ቀጣይ ስራ ይሆናል።
በቀጣይ የሚመረጡ ስዎች ህዝበ ሙስሊሙን በእኩል እይን የሚመለከቱ፣ ለሁሉም ነጻነት የሚሰጡ የሙስሊሙን ችግር ስራዬ ብለው እንዲሰሩ ብቃት ያላቸው ስዎች መመርጥ ይኖርባቸዋል። አመራረጡምከኡለሞች፣ ከሙሁራን፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ትፅኖ ፈጣሪ ስዎችን በማካተት የሙስሊሙን መብት ማስከበር የሚችል ተቋም መመስረት ይቻላል።
ሐ) በወጣቱ መካከል መደማመጥ መፍጠር
በወጣቱ መካከል ያለው የሀሳብ ልዩነት በጣም የተጋነነ ባይሆንም እየሰፋ በሄደ ቁጥር አደጋ እንደሚያደርስ ወታወቅ ይኖርበታል።
በወጣቱ መካከል ያሉ ልዩነቶች በሶስት ነጥቦች ሊጠቃለል ይችላል። እነሱም የሀይማኖት ኺላፍ፣የዘርና የፖለቲካ ናቸው። የመጀመርያው ችግር ማለትም የኺላፍ ጉዳይ በ «ሀ» ላይ የተጠቀሰው መፍትሔ ተግባራዊ ከተደረገ ይሄኛው ችግርም
አብሮ የሚቀረፍ ይሆናል።
ሁለተኛው ዘረኝነት ነው ፤ ዘረኝነት በኢስላም ፈፅሞ የተወገዘ ከመሆኑም በላይ ሰው ፈልጎና መርጦ ባልተፈጠረበት ሁኔታ የአንተ ዘር ከእኔ ይበልጣል ወይም ዘሩ ከዚህ ስለሆነ አይመራንም፣ ስለኛ ጉድይአያገባውም የሚል ሀሳብ ማራመድ ሰይጣናዊ ነው። አላህ አደምን ፈጥሮ ሱጁድ እንድያደርጉለት ስያዝ ሁሉም መላኢካዎች የታዘዙትን ፈጸሙ ፣ ስይጣን ግን እኔ ከእሳት የተፈጠርኩ ነኝ እሱ ከጭቃ የተፈጠረ ነው ስለዚህ እኔ ከእሱ የተሻልኩ በመሆኔ አልሰግድም በማለት በአለም ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ዘረኝነት ተናገረ በዚህም አላህ ተቆጥቶበት ከጀነት እንዲባረር ተደረገ። ስለዚህ ጀነትን የሚፈልግ ሙስሊም ዘረኛ ሊሆን አይችልም።
ኢስላም ከዘርና ብሔር የሰፋ ዩኒቨርሳል ሀይማኖት ነው። የፊሊስጤም ሙስሊሞች ሲበደሉ የሚከፋን፣ዱዓ የምናደርግላቸው ዘራችን ስለሆኑ ሳይሆን በኢስላም ወንድማማችነት የተሳሰርን ስለሆነ ነው። ስለዚህ የራያ ወጣት ዘረኝነት
ከሙስሊም የማይጠብቅ በመሆኑ ማንኛው ሰው ዘሩ፣ቋንቋውና ሀይማኖቱ ሳንለይ በሰውነቱ ልናከብር ይከባል።
ሶስተኛ የፖለቲካ ልዩነት ነው፤ በእርግጥ ሙስሊሙ በፖለቲካ ያለው ተሳትፎ በጣም ደካማ ቢሆንም አንዳንድ ሙስሊሞችየተለያዩ የፖለቲካ ርዕየተ አለም ሲድግፍ ይስተዋላል። ችግሩ መደገፋቸው ሳይሆን የሚያምኑበት የፖለቲካ አላማ ለማስፈጸመ ጉዳዩን መስጂድ ድረስ ለማምጣት መሞከር፣ የእነሱን ፖለቲካ የማይድግፍን ሰው ማጥላላትና የመሳሰሉት ናቸው።
አድስ ሙሓደራ ለሴቶች
=
ርእስ:{ሱሩቱል ፋቲሐ}ለሴቶች
/////
በ ቢላል መስጂድ ገራዶ እንዶድ በር
https://t.me/abumuazhusenedris
የራያ ሙስሊሞች አሁናዊ ሁኔታ
ከ600 አመታት በፊት ጀምሮ የራያ ሙስሊም ሀይማኖቱናን ማንነቱን ለማስከበር ከፍተኛ ትግል ስያድርግ ቢቆይም በአፄሀይለስላሴ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ተዳክሞ በኢህአዴግ ወደ ከፋ ደረጃ ደርሷል።
ከአፄ ባዕደማርያም ጀምሮ እስከ አፄ ሚኒሊክ ድረስ በራያ ሙስሊም ግልፅ ጦርነት ቢታወጂበትም አንድነቱ ጠብቆ በመቆየቱ ጦርነቱን በመቀልበስ ኢስላማዊ ማንነቱን ለማስጠበቅ ችሏል። በአፄ ሀይለስላሴና ኢህአዴግ ግን ከግልፅ ጦርነት በተጨማሪ በሙስሊሙ መካከል ለዩነት እንዲፈጠርና ሙስሊሙ አንድ ሆኖ ከመታገል ይልቅ እርስ በርሱ እየተባላ ቢዚ እንዲሆን በማድረግ በታሪኩ አይቶት በመያውቀው መልኩ አዳክመውታል።
የሙስሊሙ አሁናዊ ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢና አሳዛኝ ነው። ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ሙስሊሙ በሀይማኖቱና በማህበራዊ ኑሮውና የተዳከመ እንዲሆን አድርጎታል።
በራያ ሙሉ በሙሉ በሚባል ድረጃ የሀይማኖት እንቅስቃሴ የለም። የተዘጉ መድረሳዎችን ስራ አልጀመሩም ፤ ትውልድየሚታነፀው በትምህርት በመሆኑ መድረሳዎች መዘጋታቸው ህዝበ ሙስሊሙ ለከፋ አደጋ አግልጦታል።
የሙስሊሙ ስነ-ምግባር ብንመለከት እጅጉን የወረደ በተለያዩ ሱሶች የተጠቃ፣ለሀይማኖቱ ደንታ የሌለው፣ ሁኔታዎችን ለማስተካከል ከመጣር ይልቅ ማባባስ የሚቀናው ሁኖ እናገኘው አለን። በእርግጥ በተወሰነ ደረጀ የተሻለ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ቢኖሩም አብዘሀኛው ግን ደካማ ነው ማለት ይቻላል።
በሙስሊሙ መካከል ከነበረው ኺላፍ በተጨማሪ የዘርና ፖልቲካ ልዩነት ገብቶበት ሙስሊሙ በተለይ ወጣቱ ከምንም ግዜ በላይ ተከፋፍሎ ይገኛል።
የሙስሊሙ ሁኔታ አደጋ ውስጥ መሆኑ ከሚያሳዩን መካከል ስርግ ነው። በገጠሩ አከባቢ ሳይቀር በሚያሳዝን ሁኔታ ከኢስላም ያፈነገጡ ሰርጎች መመልከት የተለመደ ሁኗል። ሌላኛው ደግሞ የፍቺ መጠን በሚያስደነግጥ መልኩ ከፍተኛነው። መጋባታቸው ሳንሰማ መለያየታቸውን የሰማን አያሌ ስዎች አሉ። ይህም የሙስሊሙ አስከፊ ሁኔታዎች ማሳያ
ናቸው።
ሌላኛው በዘርና በፖለቲካ የተለያየ አቋም ያላቸው ስዎች ፖለቲካን በቦታው ከማራመድ ይልቅ መስጂድ ድረስ ጎትተው ለማምጣት በመሞከር በሙስሊሙ መካከል የከፋ ልዩነት እንዲፈጥር እያደረጉ ይገኛል።
የራያ ሙስሊመ ሁለንተናዊ ስጋት ላይ እንዳለ የምናውቀውና እያየነው ያለ በመሆኑ መብራርያ ያስፈልገዋል የሚል እምነት
የለኝም።
በዚህ የሚቀጥል ከሆነ የራያ ሙስሊም በጥቂት አመታት ማንነቱን ሊያጣ እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለውም፤ ከ50 ወይም 60 አመታት ብኋላ ቁርአን የሚያስተምር ስው ከሌላ አከባቢ ለማምጣት የምንገደድ ይሆናል።
ዘመነ ኢህአዴግ (ወያኔ) እና የራያ ሙስሊሞች ጭቆና(ከባለፈው የቀጠለ )
ከፖለቲካው ማግለል
የራያ ሙስሊም በፖለቲካ እኩል ተሳታፊ በመሆን መብቱን ማስከብር እንዳይችል ከመጀመርያው ጀምሮ ተሰርቷል።
ሌላው ቀርቶ የራሱ ተቋም መጅሊስ እንኳን በራሱ የተማሩ ልጆች እንዳይተዳደር በማድረግ ተቋሙ የመንግስት ተልዕኮ አስፈፃሚ እንዲሆን አድርጓል።
ሙስሊሙ በፖለቲካ ነቁ ተሳታፊ መሆን የሚችለው ሲማር ነው። ተምሮ ተሳታፊ እንዳይሆን ቀድመው ትምህርት እንዳይማር፣ የሚማረው ደግሞ ተረጋግቶ መማር እንዳይችል ችግሮች በመፍጠር አሰናክለውታል።
ይህን ሁሉ ፈተና አልፎ የተማረው ሙስሊም ደግሞ በሚሰራባቸው መስርያቤቶች የተለያዩ ተፅኖ በመፍጠር የእርከን እድገት እንዳያገኝ አድርጓል። ብብዛት ሙስሊም በሚኖርባቸው አከባቢዎች የተማሩ ሙስሊሞች ቢኖሩም በአመራር
ደረጃ አንድ ሙስሊም እንኳን እንዲካተት አልተደረገም። ይህንን እውነታ በ2010 ዓ/ል ከቆቦ ጀምሮ እስከ ማይጨው ባድረኩት ማጣራት ለማረጋገጥ ችያለሁ።
በመንግስት ሰራተኝነት ስያገልግሉ የነበሩ ሙስሊሞች ከ2000 ዓ/ል ወዲህ በተደጋጋሚ በሚፈፀምባቸው ችግሮች ራያ ለውቀ ስራ ፍለጋ ወደ ሌላ አከባቢ ሄደዋል። ሙስሊሙ በተለያዩ ትፅኖ ስር በማድረግ ከፖለቲካው መድረግ እንዲገለል
በማድረጋቸው መብታችንን ማሰከበር ቀርቶ መጠየቅ አይቻልንም።
ኢኮኖሚያዊ ጥቃት
ሙስሊሙ በሀይማኖቱ፣በትምህርትና ፖለቲካ እንዲገለል ከተድረገ ብኋላ በኢኮኖሚውን ሲስተማቲካሊ ከጫዋታ ውጭ እንዲደረግ ተደርጓል።
በተለ ድህረ 2000 ዓ/ል ሙስሊም ባለሀብቶች የሀብት ምንጫችሁ ምንድነው? ከአረብ ሀገራት ጋር ግኑኝነት አላችሁ! «ወሀብያ» ናችህ በሚል ብዙ ስቃይ አይተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ከቅም በላይ ግብር በመጫን ሙስሊም ነጋዴዎች ከገበያው እንዲወጡ ተደርጓል እንዲሁም በማዳበርያ ስም ገበሬውን አደህይተዉታል።
ድሮ ራያ ላይ ሲታወቁ የነበሩ ሙስሊም ባለሀብቶች ሀገራቸውን ጥለው አዲስ አበባና በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች በመስራት ላይ ይገኛሉ።
" #سؤال_وجواب_في_العقيدة"
س١/ من أين نأخذ عقيدتنا ؟
من القرآن والسنة .
س٢/ أين الله ؟
في السماء على العرش .
س٣/ ما الدليل من القرآن على أن الله على العرش ؟
( الرحمن على العرش استوى) .
س٤/ ما معنى ( استوى) ؟
علا وارتفع .
س٥/ لماذا خلق الله الجن والإنس ؟
لعبادته وحده لاشريك له .
س٦/ ما الدليل من القرآن على أن الله خلق الجن والإنس لعبادته ؟
( وما خلقت الجن والإنس إلا ليعبدون) .
س٧/ ما معنى ( يعبدون ) ؟
يوحدون .
س٨/ ما معنى لا إله إلا الله ؟
لا معبود حق إلا الله .
س٩/ ما أعظم عبادة ؟
التوحيد .
س١٠/ ما أعظم معصية ؟
الشرك .
س١١/ ماهو التوحيد ؟
إفراد الله بالعبادة .
س١٢/ ماهو الشرك ؟
عبادة غير الله مع الله .
س١٣/ كم أقسام التوحيد ؟
ثلاثة .
س١٤/ ماهي أقسام التوحيد ؟
الربوبية والألوهية والأسماء والصفات .
س١٥/ ما تعريف توحيد الربوبية ؟
أفعال الله مثل الخلق والرزق .
س١٦/ ما تعريف توحيد الألوهية ؟
أفعال العباد مثل الدعاء والذبح والسجود .
س١٧/ هل لله أسماء وصفات ؟
نعم .
س١٨/ من أين نأخذ أسماء الله وصفاته ؟
من القرآن والسنة .
س١٩/ هل تشبه صفات الله صفاتنا ؟
لا .
س٢٠/ ما الدليل من القرآن على أن صفات الله لا تشبه صفاتنا ؟
( ليس كمثله شيء وهو السميع البصير) .
س٢١/ القرآن كلام من ؟
الله .
س٢٢/ منزل أم مخلوق ؟
منزل .
س٢٣/ ما هو البعث ؟
إحياء الناس بعد موتهم .
س٢٤/ ما الدليل من القرآن على كفر من أنكر البعث ؟
( زعم الذين كفروا أن لن يبعثوا ) .
س٢٥/ ما الدليل من القرآن على أن الله سيبعثنا ؟
( قل بلى وربي لتبعثن ) .
س٢٦/ كم أركان الإسلام ؟
خمسة .
س٢٧/كم أركان الإيمان ؟
ستة .
س٢٨/كم أركان الإحسان ؟
واحد .
س٢٩/ ماتعريف الإسلام ؟
الاستسلام لله بالتوحيد والانقياد له بالطاعة والبراءة من الشرك وأهله .
س٣٠/ ما تعريف الإيمان ؟
قول باللسان واعتقاد بالقلب وعمل بالجوارح يزيد بالطاعة وينقص بالمعصية .
س٣١/ لمن نذبح ونسجد ؟
لله وحده لاشريك له .
س٣٢/ هل يجوز الذبح والسجود لغير الله ؟
لا .
س٣٣/ ماحكم الذبح والسجود لغير الله ؟
شرك أكبر .
س٣٤/ ماحكم من يحلف ويقول والنبي ، وحياتك ؟
شرك أصغر .
س٣٥/ ما الدليل من القرآن على أن المشرك إذا مات ولم يتب لا يغفر الله له ؟
( إن الله لا يغفر أن يشرك به ) .
س٣٦/ هل يجوز عبادة الشمس والقمر ؟
لا .
س٣٧/ ما الدليل من القرآن على تحريم عبادة الشمس والقمر ؟
( لا تسجدوا للشمس ولا للقمر) .
س ٣٨/ / ما الدليل من القرآن على وجوب عبادة الله وحده وتحريم الشرك بالله ؟
( واعبدوا الله ولا تشركوا به شيئاً) .
س٣٩/ ما الدليل من القرآن على وجوب دعاء الله وحده لا شريك له ؟
( وأن المساجد لله فلا تدعوا مع الله أحدا ) .
س٤٠/ ما الدليل من السنة على تحريم الذبح لغير الله ؟
( لعن الله من ذبح لغير الله) .
س٤١/ متى يجوز الاستعانة بغير الله ؟
إذا كان حياً حاضراً قادراً
س٤٢/ متى يحرم الاستعانة بغير الله ؟
إذا كان ميتا أو غائباً أو غير قادر .
س٤٣/ من أول الرسل ؟
نوح عليه السلام .
س٤٤/ من آخر الرسل ؟
محمد صلى الله عليه وسلم .
س٤٥/ ما مهمة الرسل عليهم الصلاة والسلام ؟
يدعون إلى التوحيد وطاعة الله وينهون عن الشرك ومعصية الله .
س٤٦/ ما أول ما فرض الله على ابن آدم ؟
الإيمان بالله والكفر بالطاغوت .
س٤٧/ هل اليهود كفار ؟
نعم .
س٤٨/ لماذا اليهود كفار ؟
يقولون عزير ابن الله .
س٤٩/ هل النصارى كفار ؟
نعم .
س٥٠/ لماذا النصارى كفار ؟
يقولون عيسى بن مريم ابن الله .
س٥١/ هل لله ولد ؟
لا.
س٥٢/ ما الدليل من القرآن على أن الله ليس له ولد ؟
( لم يلد ولم يولد) .
س٥٣/ هل المجوس كفار ؟
نعم .
س٥٤/ لماذا المجوس كفار؟
لأنهم يعبدون النار .
س٥٥/ ما موقفنا من اليهود والنصارى والمجوس ؟
نبغضهم ولا نظلمهم .
س٥٦/ هل نحب الفرقة التي تسب الصحابة؟
لا .
س٥٧/ لماذا لا نحب هذه الفرقة ؟
يشركون بالله ويسبون الصحابة .والصحابة نقلة الدين .
س٥٨/ هل نحب الجهمية والمعتزلة ؟
لا .
س٥٩/ لماذا لا نحب الجهمية والمعتزلة ؟
ينفون صفات الله .
س٦٠/ هل نحب الأشاعرة ؟
لا .
س٦١/ لماذا لا نحب والأشاعرة ؟
يحرفون صفات الله .
س٦٢/ هل نحب جماعة الإخوان المسلمين والأحزاب ؟
لا .
س٦٣/ لماذا لا نحب جماعة الإخوان المسلمين ؟
خوارج يفجرون في المسلمين ويدعون إلى المظاهرات . وقائدها لا ينسب الى الدين .
س٦٤/ هل نحب جماعة التبليغ ؟
لا .
س٦٥/ لماذا لا نحب جماعة التبليغ ؟
صوفية يدعون إلى الشرك والبدع .
س٦٦/ ما طريقة أهل السنة والجماعة في أسماء الله وصفاته ؟
يثبتونها بدون مشابهة ولا ينفونها .
س٦٧/ من هي الطوائف الضالة المخالفة لأهل السنة والجماعة في أسماء الله وصفاته ؟
﴿إِنَّ الَّذينَ تَدعونَ مِن دونِ اللَّهِ عِبادٌ أَمثالُكُم﴾
إن لم يكن هذا شرك فما هو الشرك!!
ስሙኝ ብሏል" አስቸኳይ ጉዞ የምታደርጉ መንገደኞቻችን ሌላ የጉዞ አማራጭ ተጠቀሙ " - የኢትዮጵያ የአየር መንገድ
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ጭጋጋማ እና ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ እንዳጋጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።
አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ይህ የአየር ፀባይ ለተወሰኑ ቀናት ይቀጥላል።
በዚህ ምክንያት ወደተወሰኑ የሀገራችን ክፍሎች የሚያደረጉ በረራዎች ለማቋረጥ መገደዱን አሳውቋል።
" የአየር ፀባዩ እስከሚስተካከል እና በረራዎችን መቀጠል እስከምንችል ድረስ መንገደኞች ታገሱን " ብሏል።
" አስቸኳይ ጉዞ የምታደርጉ መንገደኞቻችን ሌላ የጉዞ አማራጭ እንድትጠቀሙ በአክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን " ሲል ገልጿል።
አየር መንገዱ በአየር ፀባይ ምክንያት የተስተጓጎሉ በረራዎች ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንደተመለሱ ለመንገደኞች እንደሚያሳውቅ ገልጾ በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ መጉላላቶች ይቅርታ ጠይቋል።
