KebronHill Microfinance Official Telegram Channel
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
369
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+630 روز
آرشیو پست ها
የተከበራችሁ ዉድ የኬብሮንሂል ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ አክሲዮን ባለቤቶች( መስራች አባላት), ተቋማችን ኬብሮንሂል ማይክሮ ፋይናንስ አስፈላጊዉንና ሕጋዊ የብሔራዊ ባንክ መስፈርቶችን አሟልቶ በይፋ ሥራ መጀመሩን ስናበስር በታላቅ ደስታ እና አክብሮት ነው::
ኬብሮንሂል ማይክሮፋይናንስ በተለያዩ ምክንያቶች ሥራ ለመጀመር ከታሰበው ጊዜ በላይ የወሰደ ቢሆንም ውሳኝ የሕጋዊነት ምዕራፎችን በማለፍ ሂደት ዉስጥ ባለአክስዮኖች ያሳያችሁትን ትዕግስትና ዓላማ ጽናት በተመለከተ እውነተኛ የባለቤትነት ስሜት በተግባር የታየበት በመሆኑ ቦርዱ በታላቅ አክብሮት ተመልክቶታል::
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ማይክሮፋይናንሱ አዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ቅርንጫፎች ከፍቶ በሥራ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቀጣይም ተቋሙን ትርፋማና ዉጤታማ በሚያደርግ መልኩ የአዋጭነት ጥናቶችን እያደረገ ከአዲስ አበባ ዉጪ ባሉ አከባቢዎች የማስፋፊያ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ለመክፈት ሰፊ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል::
በመሆኑም:- ሁሉም ባለአክስዮኖች በአክሲዮን ሺያጭ ወቅት በገባችሁት ዉል መሰረት ተቋሙ በተሻለ አቅም አገልግሎት እንዲሰጥ ይረዳው ዘንድ ቀሪ ያልተከፈለዉን አክሲዮን መጠን በተቻለ ፍጥነት ለዚህ ዓላማ በተከፈቱ የባንክ ሂሳቦችን ገቢ ማድረግ የሚትችሉ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን::
ኬብሮንሂል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
