fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Ethiopian University Freshman Information

Ethiopian University Freshman Information

رفتن به کانال در Telegram

Information service for Ethiopian university freshmen. Admissions • Registration • University Updates • Academic Information

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است

📈 تحلیل کانال تلگرام Ethiopian University Freshman Information

کانال Ethiopian University Freshman Information (@freshmanunion) بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 22 647 مشترک است و جایگاه را در دسته متفرقه دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 22 647 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 23 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -646 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -45 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 40.54% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 21.29% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 9 182 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 4 822 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 25 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“Information service for Ethiopian university freshmen. Admissions • Registration • University Updates • Academic Information”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 24 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته متفرقه تبدیل کرده‌اند.

22 647
مشترکین
-4524 ساعت
-1517 روز
-64630 روز
آرشیو پست ها
📣 #KabridaharUniversity የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ማስታወቂያ በ2019 ዓ.ም ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ-ምረቃ (ፍሬሽማን እና ሪሚዲያል) ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 02 እና 03/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። 📍 የምዝገባ ቦታ፦ የዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጂስትራር ጽ/ቤት ለምዝገባ ሲመጡ፦ በተገለጹት ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎችን መያዝ ይኖርባችኋል። ➡️ ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሌሎች ተማሪዎችም መረጃውን እንዲያገኙ ሼር ያድርጉ። @FreshmanUnion✅️

📣 #HaramayaUniversity | የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ በ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርታችሁን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ከጥቅምት 05–08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። 📍 የምዝገባ ቦታ፦ ሐረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ • የ8ኛ ክፍል ሰርቲፍኬት • ከ9ኛ–12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት • የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርቲፍኬት ዋናውና ኮፒው • 6 ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች • ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተገለፁትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ጉርድ ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በሶፍት ኮፒ መያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል። ➡️ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሌሎች ተማሪዎችም መረጃውን እንዲያገኙ ሼር ያድርጉ። @FreshmanUnion ✔️

📣 የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ማስታወቂያ ቀን፦ 25/01/2019 ዓ.ም በ2019 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 03–04/2019 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን። 📍 የምዝገባ ቦታ፦ • የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች — ዋናው ግቢ • የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች — ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለምዝገባ ይዘው መምጣት የሚገባችሁ፦ • የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው • ከ9ኛ–12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው • አራት ጉርድ ፎቶግራፍ • አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ ⚠️ ማሳሰቢያ፦ ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን። ምንጭ፦ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት ➡️ ይህን መረጃ ለሌሎች የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎች ሼር ያድርጉ። @FreshmanUnion ✔️

📌 በመጀመርያ አመት የዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ሊፈትኗችሁ የሚችሉ 3 Freshman Common Courses፦ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ከመጀመራችሁ በፊት የትኞቹ ኮርሶች ከበድ እንደሚሉና ልዩ ትኩረት እንደ
📌 በመጀመርያ አመት የዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ሊፈትኗችሁ የሚችሉ 3 Freshman Common Courses፦ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ከመጀመራችሁ በፊት የትኞቹ ኮርሶች ከበድ እንደሚሉና ልዩ ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው ማወቃችሁ ዝግጅታችሁን ውጤታማ ያደርገዋል። በብዙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የበርካታ ተማሪዎችን GPA ዝቅ የሚያደርጉት 3ቱ ዋና ዋና ኮርሶች እነዚህ ናቸው፦ 1. Mathematics for Natural / Social Science (Math 1011 / 1012) ዋናው ፈተና፡ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት Math ጋር ሲነጻጸር Pace (ፍጥነቱ) እና የትምህርቱ Depth (ጥልቀት) ከፍተኛ ነው። ትኩረት የሚሹ ነጥቦች፡ Propositional Logic, Set Theory, Complex Numbers, Matrices እና Calculus (Limits, Derivatives & Integration) በአንድ Semester ይሸፈናሉ። Midterm እና Final Exam ጥያቄዎች ቀጥታ Computation (ስሌት) ላይ ብቻ ሳይሆን Theoretical Proofs እና Deep Conceptual Understanding ላይ ያተኩራሉ። 2. Logic and Critical Thinking (LoCT 1011) ዋናው ፈተና፡ በHigh School ፈጽሞ አግኝታችሁት የማታውቁት አዲስ የFormal Reasoning እና Philosophical Analysis ዘርፍ ነው። ትኩረት የሚሹ ነጥቦች፡ Ordinary language መግለጫዎችን ወደ Symbolic Logic መቀየር እና Inference Rules መተግበር። በፈተና ወቅት በጣም የሚያደናግሩትን Informal Fallacies መለየትና Formal Deductive Techniques መረዳት። 3. General Physics (Phys 1011) / Introduction to Economics (Econn 1011) (ለNatural Science ተማሪዎች Physics፤ ለSocial Science ተማሪዎች ደግሞ Economics) General Physics (Natural Science): Calculus-based Physics ስለሆነ Vector Analysis እና Differential Formulations ከPhysics ጽንሰ-ሀሳቦች ጋር አዋህዶ መተግበርን ይጠይቃል። Introduction to Economics (Social Science): Graphical Analysis, Mathematical Formulas (Elasticity, Equilibrium) እና Theoretical Models ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መያዝ ይኖርባችኋል። 💡 የእኛ ምክር፡ ያለምንም ክፍያ የሚቀርቡ እንደ ዝግጁ አፕ ያሉ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ለነዚህ ኮርሶች ገና ከቀን 1 ጀምራችሁ በቋሚነት ማስታወሻዎችን አንብቡ እና ፈተና ተኮር ጥያቄዎችን በደንብ ተለማመዱ! @FreshmanUnion ✔️

የምዝገባ ጥሪ (Call for Registration) የሚመለከተው አካል፦ በ2019 ዓ.ም. (2026/27) የትምህርት ዘመን ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ (Freshman) ተማሪዎች በሙ
የምዝገባ ጥሪ (Call for Registration) የሚመለከተው አካል፦ በ2019 ዓ.ም. (2026/27) የትምህርት ዘመን ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ (Freshman) ተማሪዎች በሙሉ። የምዝገባ ቀን፦ ጥቅምት 4–5 ቀን 2019 ዓ.ም. (October 14–15, 2026)። የምዝገባ ቦታዎች፦ የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Sciences) ተማሪዎች፦ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (Institute of Technology) ግቢ ውስጥ ትመዘገባላችሁ። የማህበራዊ ሳይንስ (Social Sciences) ተማሪዎች፦ በግብርና እና የእንስሳት ሕክምና ኮሌጅ (College of Agriculture and Veterinary Medicine) ግቢ ውስጥ ትመዘገባላችሁ። ፖርታል ማረጋገጥ (University Portal)፦ የዶርም፣ የካፌ እና የሴክሽን (የክፍል) ምደባችሁን ለማወቅ የመግቢያ ቁጥራችሁን (admission number) በመጠቀም በ https://portal.ju.edu.et ገጽ ላይ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ (መረጃው በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ፖርታሉ ይጫናል)። በምዝገባ ወቅት ልታዟቸው የሚገቡ ነገሮች፦ የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬት (Original እና አንድ ፎቶ ኮፒ)። 4 የፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች። የአልጋ አንሶላ፣ በትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ። ማሳሰቢያ (NB)፦ የአዲስ ሪሜዲያል (Remedial Program) ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ወደፊት የሚገለጽ ስለሆነ ይህ ማስታወቂያ እናንተን አይመለከትም። ተጨማሪ መረጃዎችን በዩኒቨርሲቲው ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ተከታተሉ። @FreshmanUnion ✔️

🌼Baga Ayyaana Irreecha Hora Finfinnee fi Hora Harsadee Bara 2019 Nagaan Geessan! እንኳን ለ2019 ዓ.ም የሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ ሐርሰዴ ኢሬቻ በዓል
🌼Baga Ayyaana Irreecha Hora Finfinnee fi Hora Harsadee Bara 2019 Nagaan Geessan! እንኳን ለ2019 ዓ.ም የሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ ሐርሰዴ ኢሬቻ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! @FreshmanUnion ✔️

📣 ፍሬሽማን ተማሪዎች ተዘጋጁ! በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በዝግጁ (Zegju) አፕሊኬሽን ላይ ጊዜ የማይወስድ ራስ መፈተሻ ውድድር ይጀምራል። እንዴት መሳተፍ ትችላላችሁ? 1⃣ የዝግጁ (Zegju) አፕሊ
📣 ፍሬሽማን ተማሪዎች ተዘጋጁ! በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በዝግጁ (Zegju) አፕሊኬሽን ላይ ጊዜ የማይወስድ ራስ መፈተሻ ውድድር ይጀምራል። እንዴት መሳተፍ ትችላላችሁ? 1⃣ የዝግጁ (Zegju) አፕሊኬሽንን ክፈቱ 2⃣ የፍሬሽማን ጥቅላችሁን ክፈቱ 3⃣ ውድድሩ ሲጀምር Start Challenge የሚለውን ተጫኑ እንዴት እንደምትመዘገቡ ለማየት ማስታወሻ፦ Password የረሳችሁ መመዝገቢያ ቦት ላይ "Change Password" የሚለውን ቁልፍ ተጫኑ ወይም /recover ብላችሁ ይላኩ። ለመመዝገብ - @Zegju_registration_bot ▶️ Android (Play Store) 🛒 iOS (App Store)

#Noteupdates Psychology, Economics, Emerging Technology እና Math ላይ ቀሪ ቻፕተሮች ገብተውላቹሃል። ከነሱ በተጨማሪ፦ ➕Global trends ➕ Inclusivene
#Noteupdates Psychology, Economics, Emerging Technology እና Math ላይ ቀሪ ቻፕተሮች ገብተውላቹሃል። ከነሱ በተጨማሪ፦ ➕Global trends ➕ Inclusiveness ➕ Entrepreneurship ማስታወሻዎች ዝግጁ አፕ ላይ ገብተውላቹሃል። የፈለጋችሁት ዲፓርትመንት ለመግባት የፍሬሽማን ውጤታችሁ ትልቅ ቦታ አለው። ጥናታችሁን ዝግጁ አፕ ላይ በጊዜ በመጀመር ውጤታችሁን አሳምሩ። 🔎 እንዴት እንደምትመዘገቡ ለማየት ማስታወሻ፦ Password የረሳችሁ መመዝገቢያ ቦት ላይ "Change Password" የሚለውን ቁልፍ ተጫኑ ወይም /recover ብላችሁ ይላኩ። ለመመዝገብ - @Zegju_registration_bot ▶️ Android (Play Store) 🛒 iOS (App Store)

#MoE በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከመመደብ ጋር ተያይ
#MoE በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከመመደብ ጋር ተያይዞ የተነሱ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። በምደባው ሒደት የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ ተጠናቆ ተማሪዎቹ በጊዜያዊነት ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡበት ቀን ይፋ እስከሚደረግ ድረስ፣ ተማሪዎቹ ባሉበት ሆነው በትዕግስት እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። @FreshmanUnion ✔️

ከላይ ከቀረቡት ዲፓርትመንቶች በመቀጠል በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተፈላጊነት እና ተስፋ ያላቸው የሚቀጥሉት 10 (ከ11-20) ዋና ዋና የትምህርት ክፍሎች (ዲፓርትመንቶች)፦ 11. ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ (Mechanical Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (BiT) ዲፓርትመንቱ፦ የማሽነሪዎችን፣ የሞተሮችን፣ የኢንዱስትሪ መሳሪያዎችን እና የኃይል ማመንጫ አሰራሮችን ዲዛይን ማድረግ፣ ማምረት እና የመንከባከብ ሳይንስን የሚያጠና ነው። የሥራ እድሎች፦ በአቪዬሽን እና አየር መንገድ (እንደ Ethiopian Airlines) የማሽን ጥገና እና ኦፕሬሽን ኢንጂነር በማኑፋክቸሪንግ እና ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች (የሲሚንቶ፣ የምግብ እና መጠጥ) የምርት ማኔጀር በአውቶሞቲቭ እና ከባድ ማሽነሪ ተቋማት የቴክኒክ ባለሙያ 12. አርክቴክቸር (Architecture / Urban Planning) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (EiABC / 5 ኪሎ) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የህንፃዎችን ውበት፣ ቅርፅ፣ የውስጥ ክፍል አቀማመጥ (Interior Design) እና የከተሞች ማስተር ፕላን ንድፍ በፈጠራና በቴክኖሎጂ አስደግፎ የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በግል እና በድርጅቶች የህንፃ አርክቴክት እና ንድፍ አውጪ (Architect) የውስጥ ዲዛይን እና የቦታ ውበት አማካሪ (Interior Designer) በከተማ ልማት እና ፕላን መሪያ ተቋማት የከተማ ፕላነር (Urban Planner) 13. አግሪካልቸራል ኢንጂነሪንግ እና ባዮሲስተምስ (Agricultural Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የዘመናዊ መስኖ ቴክኖሎጂዎችን፣ የትራክተርና አዝመራ ሰብሳቢ ማሽኖችን እና የውሃ ሀብት አጠቃቀምን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሰፊ የንግድ ግብርና (Commercial Farming) እና የግብርና ፕሮጀክቶች የመስኖ እና ማሽነሪ ኢንጂነር በዓለም አቀፍ የግብርና ድርጅቶች (FAO, USAID) የቴክኒክ እና የምግብ ዋስትና አማካሪ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲሁም በክልል ግብርና ቢሮዎች የውሃ ሀብት ባለሙያ 14. ኢኮኖሚክስ (Economics) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6 ኪሎ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን፣ የገበያ ሁኔታዎችን፣ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን እና የዳታ ትንተናን (Data Analysis) የሚያጠና የማህበራዊ ሳይንስ ንጉስ ነው። የሥራ እድሎች፦ በባንኮች እና ፋይናንስ ተቋማት የኢኮኖሚና ገበያ ተነታኝ (Economic Analyst) በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና በብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ አውጪና ተመራማሪ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች (World Bank, IMF, UN) የልማት ፕሮጀክት አማካሪ 15. አኔስቴዥያ (Anesthesia) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (በቅድሚያ በመጀመር የሚታወቅ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ታካሚዎች ቀዶ ህክምና (Surgery) ከመደረጋቸው በፊት እና በሚደረግበት ወቅት የማደንዘዣ መድኃኒቶችን መስጠት፣ የህመም ማስታገስ እና ምልክቶችን የመከታተል የጤና ሳይንስ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በመንግስት እና የግል ሆስፒታሎች የቀዶ ህክምና ክፍል አኔስቴቲስት (Anesthetist) በአደጋ ጊዜ እና በፅኑ ህሙማን መከታተያ ክፍል (ICU) የህክምና ባለሙያ በህክምና ማሰልጠኛዎች እና ምርምር ማዕከላት አስተማሪና ተመራማሪ 16. ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ (Radiology Technology) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ በዘመናዊ የመመርመሪያ መሳሪያዎች (እንደ X-ray, Ultrasound, CT Scan, MRI) በመጠቀም የበሽታዎችን መንስኤ እና የሰውነት ክፍል ምስሎችን (Medical Imaging) የሚያነሳ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሆስፒታሎች እና በምርመራ ማዕከላት (Diagnostic Centers) የራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂስት በግል ምስል ማንሻ ማዕከላት ስራ አስኪያጅነት እና የኢሜጂንግ ባለሙያ የራዲዮሎጂ መሳሪያዎች አቅርቦት እና ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ 17. ማርኬቲንግ ማኔጅመንት (Marketing Management) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ንግድ ስራ ትምህርት ቤት / Commerce) ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የምርቶችና አገልግሎቶችን ገበያ ማናት፣ የዲጂታል ማርኬቲንግ ስትራቴጂዎችን መንደፍ፣ የደንበኞች ፍላጎት ማናት እና የሽያጭ መጠንን ማሳደግ ላይ የሚያተኩር የቢዝነስ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በቴሌኮም፣ ባንኮች እና ትልልቅ ኩባንያዎች የማርኬቲንግ እና ብራንድ ማኔጀር የዲጂታል ማርኬቲንግ፣ የማህበራዊ ሚዲያ እና የህዝብ ግንኙነት (PR) ስፔሻሊስት በማስታወቂያ እና ፕሮሞሽን ኤጀንሲዎች የፈጠራ እና የስትራቴጂ ዳይሬክተር 18. ኬሚካል ኢንጂነሪንግ (Chemical Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ጥሬ እቃዎችን ወደ ተለያዩ ጠቃሚ ምርቶች (እንደ ፕላስቲክ፣ ሳሙና፣ መድኃኒት፣ መጠጦች) ለመቀየር የሚደረጉ የኬሚካል እና የፊዚካል ሂደቶችን የሚያጠና መስክ ነው። የሥራ እድሎች፦ በምግብና መጠጥ፣ በስኳር፣ በሲሚንቶ እና ሳሙና ፋብሪካዎች የሂደት (Process) ኢንጂነር በፔትሮኬሚካል እና ፕላስቲክ አምራች ድርጅቶች የቴክኒክ ማኔጀር በጥራት ቁጥጥር (Quality Control) እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣናት ተቆጣጣሪ 19. ነርሲንግ / ክሊኒካል ነርሲንግ (BSc Nursing) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ለህሙማን የቅርብ እንክብካቤ መስጠት፣ የህክምና ትዕዛዞችን መፈፀም፣ የታካሚዎችን ሁኔታ መከታተል እና በጤና ኤክስቴንሽን ማህበረሰብን ማገልገልን የሚያጠና ህይወት አድን ሙያ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች ክሊኒካል ነርስ (Clinical Nurse) በአለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች (Red Cross, MSF) የህክምና እንክብካቤ አቅራቢ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ (የውጭ ሀገር የነርሲንግ የሥራ እድሎች) ሰፊ የሥራ እድል ያለው 20. ጋርመንት እና ቴክስታይል ኢንጂነሪንግ (Textile & Garment Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (በቴክስታይል እና ፋሽን ኢንስቲትዩት - EiTEX የሚታወቅ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የጨርቃ ጨርቅ፣ የፈትል፣ የልብስ ስፌት ቴክኖሎጂ እና የፋሽን ዲዛይን ማኑፋክቸሪንግ ሂደትን በኢንዱስትሪ ደረጃ ማምረትን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና አልባሳት ፋብሪካዎች የምርት እና የጥራት ቁጥጥር ኢንጂነር በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዲዛይን ኩባንያዎች የቴክኒክ አማካሪ የራስን የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ማኑፋክቸሪንግ ቢዝነስ መፍጠር @FreshmanUnion ✔️

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (በቴክስታይል እና ፋሽን ኢንስቲትዩት - EiTEX የሚታወቅ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የጨርቃ ጨርቅ፣ የፈትል፣ የልብስ ስፌት ቴክኖሎጂ እና የፋሽን ዲዛይን ማኑፋክቸሪንግ ሂደትን በኢንዱስትሪ ደረጃ ማምረትን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና አልባሳት ፋብሪካዎች የምርት እና የጥራት ቁጥጥር ኢንጂነር በጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዲዛይን ኩባንያዎች የቴክኒክ አማካሪ የራስን የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ማኑፋክቸሪንግ ቢዝነስ መፍጠር

ከላይ ከቀረቡት ዲፓርትመንቶች በመቀጠል በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተፈላጊነት እና ተስፋ ያላቸው የሚቀጥሉት 10 (ከ11-20) ዋና ዋና የትምህርት ክፍሎች (ዲፓርትመንቶች)፦ 11. ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ (Mechanical Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (BiT) ዲፓርትመንቱ፦ የማሽነሪዎችን፣ የሞተሮችን፣ የኢንዱስትሪ መሳሪያዎችን እና የኃይል ማመንጫ አሰራሮችን ዲዛይን ማድረግ፣ ማምረት እና የመንከባከብ ሳይንስን የሚያጠና ነው። የሥራ እድሎች፦ በአቪዬሽን እና አየር መንገድ (እንደ Ethiopian Airlines) የማሽን ጥገና እና ኦፕሬሽን ኢንጂነር በማኑፋክቸሪንግ እና ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች (የሲሚንቶ፣ የምግብ እና መጠጥ) የምርት ማኔጀር በአውቶሞቲቭ እና ከባድ ማሽነሪ ተቋማት የቴክኒክ ባለሙያ 12. አርክቴክቸር (Architecture / Urban Planning) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (EiABC / 5 ኪሎ) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የህንፃዎችን ውበት፣ ቅርፅ፣ የውስጥ ክፍል አቀማመጥ (Interior Design) እና የከተሞች ማስተር ፕላን ንድፍ በፈጠራና በቴክኖሎጂ አስደግፎ የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በግል እና በድርጅቶች የህንፃ አርክቴክት እና ንድፍ አውጪ (Architect) የውስጥ ዲዛይን እና የቦታ ውበት አማካሪ (Interior Designer) በከተማ ልማት እና ፕላን መሪያ ተቋማት የከተማ ፕላነር (Urban Planner) 13. አግሪካልቸራል ኢንጂነሪንግ እና ባዮሲስተምስ (Agricultural Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የዘመናዊ መስኖ ቴክኖሎጂዎችን፣ የትራክተርና አዝመራ ሰብሳቢ ማሽኖችን እና የውሃ ሀብት አጠቃቀምን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሰፊ የንግድ ግብርና (Commercial Farming) እና የግብርና ፕሮጀክቶች የመስኖ እና ማሽነሪ ኢንጂነር በዓለም አቀፍ የግብርና ድርጅቶች (FAO, USAID) የቴክኒክ እና የምግብ ዋስትና አማካሪ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲሁም በክልል ግብርና ቢሮዎች የውሃ ሀብት ባለሙያ 14. ኢኮኖሚክስ (Economics) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6 ኪሎ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን፣ የገበያ ሁኔታዎችን፣ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን እና የዳታ ትንተናን (Data Analysis) የሚያጠና የማህበራዊ ሳይንስ ንጉስ ነው። የሥራ እድሎች፦ በባንኮች እና ፋይናንስ ተቋማት የኢኮኖሚና ገበያ ተነታኝ (Economic Analyst) በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና በብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ አውጪና ተመራማሪ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች (World Bank, IMF, UN) የልማት ፕሮጀክት አማካሪ 15. አኔስቴዥያ (Anesthesia) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (በቅድሚያ በመጀመር የሚታወቅ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ታካሚዎች ቀዶ ህክምና (Surgery) ከመደረጋቸው በፊት እና በሚደረግበት ወቅት የማደንዘዣ መድኃኒቶችን መስጠት፣ የህመም ማስታገስ እና ምልክቶችን የመከታተል የጤና ሳይንስ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በመንግስት እና የግል ሆስፒታሎች የቀዶ ህክምና ክፍል አኔስቴቲስት (Anesthetist) በአደጋ ጊዜ እና በፅኑ ህሙማን መከታተያ ክፍል (ICU) የህክምና ባለሙያ በህክምና ማሰልጠኛዎች እና ምርምር ማዕከላት አስተማሪና ተመራማሪ 16. ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ (Radiology Technology) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ በዘመናዊ የመመርመሪያ መሳሪያዎች (እንደ X-ray, Ultrasound, CT Scan, MRI) በመጠቀም የበሽታዎችን መንስኤ እና የሰውነት ክፍል ምስሎችን (Medical Imaging) የሚያነሳ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሆስፒታሎች እና በምርመራ ማዕከላት (Diagnostic Centers) የራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂስት በግል ምስል ማንሻ ማዕከላት ስራ አስኪያጅነት እና የኢሜጂንግ ባለሙያ የራዲዮሎጂ መሳሪያዎች አቅርቦት እና ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ 17. ማርኬቲንግ ማኔጅመንት (Marketing Management) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ንግድ ስራ ትምህርት ቤት / Commerce) ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የምርቶችና አገልግሎቶችን ገበያ ማናት፣ የዲጂታል ማርኬቲንግ ስትራቴጂዎችን መንደፍ፣ የደንበኞች ፍላጎት ማናት እና የሽያጭ መጠንን ማሳደግ ላይ የሚያተኩር የቢዝነስ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በቴሌኮም፣ ባንኮች እና ትልልቅ ኩባንያዎች የማርኬቲንግ እና ብራንድ ማኔጀር የዲጂታል ማርኬቲንግ፣ የማህበራዊ ሚዲያ እና የህዝብ ግንኙነት (PR) ስፔሻሊስት በማስታወቂያ እና ፕሮሞሽን ኤጀንሲዎች የፈጠራ እና የስትራቴጂ ዳይሬክተር 18. ኬሚካል ኢንጂነሪንግ (Chemical Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ጥሬ እቃዎችን ወደ ተለያዩ ጠቃሚ ምርቶች (እንደ ፕላስቲክ፣ ሳሙና፣ መድኃኒት፣ መጠጦች) ለመቀየር የሚደረጉ የኬሚካል እና የፊዚካል ሂደቶችን የሚያጠና መስክ ነው። የሥራ እድሎች፦ በምግብና መጠጥ፣ በስኳር፣ በሲሚንቶ እና ሳሙና ፋብሪካዎች የሂደት (Process) ኢንጂነር በፔትሮኬሚካል እና ፕላስቲክ አምራች ድርጅቶች የቴክኒክ ማኔጀር በጥራት ቁጥጥር (Quality Control) እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣናት ተቆጣጣሪ 19. ነርሲንግ / ክሊኒካል ነርሲንግ (BSc Nursing) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ ለህሙማን የቅርብ እንክብካቤ መስጠት፣ የህክምና ትዕዛዞችን መፈፀም፣ የታካሚዎችን ሁኔታ መከታተል እና በጤና ኤክስቴንሽን ማህበረሰብን ማገልገልን የሚያጠና ህይወት አድን ሙያ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች ክሊኒካል ነርስ (Clinical Nurse) በአለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች (Red Cross, MSF) የህክምና እንክብካቤ አቅራቢ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ (የውጭ ሀገር የነርሲንግ የሥራ እድሎች) ሰፊ የሥራ እድል ያለው 20. ጋርመንት እና ቴክስታይል ኢንጂነሪንግ (Textile & Garment Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦

📣 ለ2019 የFreshman ተማሪዎች በሙሉ! በዝግጁ (Zegju) መተግበሪያ ላይ የPhysics እና Anthropology ትምህርቶች ግልጽ፣ ማራኪ እና ለማንበብ እጅግ ምቹ የሆኑ ለፈተና አጋዥ ማስ
📣 ለ2019 የFreshman ተማሪዎች በሙሉ! በዝግጁ (Zegju) መተግበሪያ ላይ የPhysics እና Anthropology ትምህርቶች ግልጽ፣ ማራኪ እና ለማንበብ እጅግ ምቹ የሆኑ ለፈተና አጋዥ ማስታወሻዎች ተካተዋል! የመጀመሪያ ዓመት ኮርሶቻችሁን፣ በየቻፕተሩ የተከፋፈሉ ጥያቄዎችን እና ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎችን በነፃ (FREE) ዝግጁ አፕ ላይ አግኙ። 🔎 እንዴት እንደምትመዘገቡ ለማየት ማስታወሻ፦ Password የረሳችሁ መመዝገቢያ ቦት ላይ "Change Password" የሚለውን ቁልፍ ተጫኑ ወይም /recover ብላችሁ ይላኩ። ለመመዝገብ - @Zegju_registration_bot ▶️ Android (Play Store) 🛒 iOS (App Store)

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ነባርና አዲስ ተማሪዎቹን ለመቀበል አስፈላጊዉን ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳወቀ መስከረም 20/2019 ዓ/ም ላለፉት 50 ዓመታት ተማሪዎችን በተለያዩ የሙ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ነባርና አዲስ ተማሪዎቹን ለመቀበል አስፈላጊዉን ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳወቀ መስከረም 20/2019 ዓ/ም ላለፉት 50 ዓመታት ተማሪዎችን በተለያዩ የሙያ መስኮች ተቀብሎ፣አሰልጥኖ ሲያስመርቅ የቆየዉ አንጋፋዉ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎቹን ለመቀበል ልዩ ዝግጀት ማድረጉን የዩኒቨርሲቲዉ አስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ አሳዉቀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ ክወትሮዉ በተለየ መልኩ ሰፊ ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዉ፣ ሰፋፍ የመማሪያ ክፍሎችና የተማሪዎች መኝታ ቤቶች ዕድሳት መደረጉን ዶ/ር ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ነባርም ሆኑ አዲስ የሚመደቡ ተማሪዎች የተሻሉ መማሪያና መኝታ ክፍሎች ላይ ሆነዉ ትምህርታችዉን እንዲከታተሉ ለማድረግ ያለመ ለትምህርትና ተማሪ ትኩረት የሰጠ መጠነ ሰፊ የዕድሳትና ማስዋብ ስራ መሰራቱ ዩኒቨርሲቲዉ ለትምህርት ጥራትና ለተገልጋዮች እርካታ ልዩ ትኩረት ስለመስጠቱ ተጨባጭ ማሳያ መሆኑን ም/ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡ @FreshmanUnion ✔️

በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው 10 ዋና ዋና የትምህርት ክፍሎች (ዲፓርትመንቶች) ፦ 1. ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና ኮምፒውተር ሳይንስ (Software Engineering / Computer Science) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT / 4 ኪሎ) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (BiT) ዲፓርትመንቱ፦ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን ማልማት፣ የሞባይል መተግበሪያዎችን (Apps) መስራት፣ የዌብሳይት ግንባታ፣ የዳታ አያያዝ እና የዳታቤዝ ደህንነትን የሚያስተምር ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ የሶፍትዌር እና አፕሊኬሽን አልሚ (Software / Mobile App Developer) በፊንቴክ እና በባንኮች (እንደ ቴሌብር፣ ቻፓ፣ ንግድ ባንክ) የሲስተም ኢንጂነር ከሀገር ውጭ ላሉ የውጭ ኩባንያዎች በሩቅ (Remote Work / Freelancing) መስራት 2. ህክምና (Doctor of Medicine - MD) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ (በማህበረሰብ አቀፍ ህክምና የሚታወቅ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የሰው ልጅ አካል አወቃቀርን፣ በሽታዎችን የመመርመር፣ የመታከም፣ የቀዶ ህክምና የማድረግ እና የህክምና ሳይንስ ምርምሮችን የሚያጠና አንጋፋና ጥልቅ የትምህርት ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ የመንግስት እና የግል ሆስፒታሎች ጠቅላላ ሀኪም (General Practitioner) በስፔሻላይዜሽን ትምህርት በመቀጠል የልዩ ህክምና ስፔሻሊስት (እንደ ቀዶ ሀኪም፣ የህጻናት ሀኪም) በአለም አቀፍ የጤና ድርጅቶች (WHO, UNICEF, NGOs) የህክምና አማካሪና ተመራማሪ 3. ኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ (Electrical & Computer Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (BiT) ዲፓርትመንቱ፦ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትና ማሰራጨት፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ኔትወርኮች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የመቆጣጠሪያ ሲስተሞች (Automation/Hardware) ንድፍን የሚያጠና መስክ ነው። የሥራ እድሎች፦ የቴሌኮም ኢንጂነር (በኢትዮ ቴሌኮም፣ ሳፋሪኮም) የኃይል እና ኤሌክትሪክ ኢንጂነር (በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል/አገልግሎት) የኔትወርክ እና የሃርድዌር ሲስተምስ አድሚኒስትሬተር 4. ሲቪል ኢንጂነሪንግ (Civil Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የህንፃዎች፣ የመንገዶች፣ የድልድዮች፣ የደብዳቤና የውሃ ግድቦች ንድፍ (Design)፣ የግንባታ ሂደት እና የፕሮጀክት አስተዳደርን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ኩባንያዎች የሳይት ኢንጂነር (Site Engineer) የመንገድ፣ ውሃ እና ህንጻ ፕሮጀክት መሃንዲስና ዲዛይነር የግንባታ አማካሪ (Consultant) እና የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ 5. ህግ (Law - LL.B.) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6 ኪሎ የህግ ኮሌጅ) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የሀገሪቱንና የአለም አቀፍ ህጎችን፣ የህገ-መንግስት መርሆዎችን፣ የንግድና የወንጀል ህጎችን እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን የሚያጠና ዲፓርትመንት ነው። የሥራ እድሎች፦ የህግ ጠበቃ እና አማካሪ (Attorney / Legal Advisor) ዓቃቤ ህግ (Prosecutor) እና ዳኛ (Judge) በባንኮች፣ በድርጅቶች እና በአለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ተቋማት (NGOs) የህግ ጉዳዮች ኃላፊ 6. ፋርማሲ (Pharmacy) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የመድኃኒቶችን ውህደት፣ ዝግጅት፣ የጎንዮሽ ጉዳት፣ የመድኃኒት አሰራጭነትን እና ለታካሚዎች የሚሰጡ የመድኃኒት ህክምናዎችን የሚያጠና የጤና ሳይንስ ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በግል እና በመንግስት ሆስፒታሎች ክሊኒካል ፋርማሲስት የራስን የግል መድኃኒት ቤት (Community Pharmacy) ወይም የመድኃኒት পাইክስ (Wholesale) ከፍቶ ማስተዳደር በመድኃኒት አምራች ፋብሪካዎች እና አስመጪ ድርጅቶች ውስጥ የመድኃኒት ጥራት ተቆጣጣሪ 7. አካውንቲንግ እና ፋይናንስ (Accounting & Finance) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (የንግድ ስራ ትምህርት ቤት / Commerce) ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የድርጅቶችን የገንዘብ እንቅስቃሴ መመዝገብ፣ የበጀት ዝግጅት፣ የኦዲት ምርመራ፣ የታክስ አሰራር እና የፋይናንስ እቅድ ማውጣትን የሚያስተምር ትምህርት ነው። የሥራ እድሎች፦ በባንኮች፣ በሚክሮፋይናንስ እና በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሂሳብ ሹም/ኦዲተር በግልና የመንግስት መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ ማኔጀር የውጭ ኦዲት እና የታክስ አማካሪ (Tax & Audit Consultant) 8. ባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ (Biomedical Engineering) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) ጅማ ዩኒቨርሲቲ (JiT) ዲፓርትመንቱ፦ የቴክኖሎጂ እና የህክምና ሳይንስ ውህደት ሲሆን፣ የህክምና መሳሪያዎችን (እንደ CT Scan, MRI, Ultrasound) ዲዛይን ማድረግ፣ መገጣጠም እና መጠገንን የሚያጠና ዘርፍ ነው። የሥራ እድሎች፦ በሆስፒታሎች ውስጥ የህክምና መሳሪያዎች ጥገና እና ቁጥጥር ኢንጂነር የህክምና መሳሪያዎችን በሚያስመጡ እና በሚሸጡ ድርጅቶች የቴክኒክ ስፔሻሊስት በምርምር ማዕከላት የሰው ሰራሽ አካላት (Prosthetics) እና የህክምና ቴክኖሎጂዎች አልሚ 9. ቢዝነስ ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ / MIS (Business Information Systems) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ እና በንግድ ስራ ማኔጅመንት መካከል ያለውን ድልድይ የሚያጠና ሲሆን፣ መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ለንግድ ውሳኔዎች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያስተምር ነው። የሥራ እድሎች፦ የቢዝነስ ኤአይ / ዳታ አናሊስት (Data / Business Analyst) በባንኮች እና በድርጅቶች የዳታቤዝ እና የሲስተም አድሚኒስትሬተር የኢአርፒ (ERP) እና የሶፍትዌር ትግበራ አማካሪ (IT Consultant) 10. ሎጅስቲክስ እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት (Logistics & Supply Chain Management) በሙያው የሚታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (የንግድ ስራ ትምህርት ቤት) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዲፓርትመንቱ፦ የዕቃዎች እና አገልግሎቶች እንቅስቃሴ ከጥሬ ዕቃ አቅርቦት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ተጠቃሚ ድረስ ያለውን የትራንስፖርት፣ የመጋዘን፣ የጉምሩክ እና የእቃ አያያዝ ሂደት የሚያስተዳድር ትምህርት ነው። የሥራ እድሎች፦ በወጪና ገቢ (Import/Export) ድርጅቶች የሎጅስቲክስ ማኔጀር በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ፋብሪካዎች የአቅርቦት እቅድ አውጪ (Supply Chain Officer) በጉምሩክ፣ በትራንስፖርት ኩባንያዎች እና በማላኪያ/ሺፒንግ ኤጀንሲዎች የኦፕሬሽን ኃላፊ

📣 ለ2019 የመጀመርያ አመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ! ሙሉ በሙሉ ያለምንም ክፍያ የቀረበው ዝግጁ አፕ አዲስ ገጽታ ይዞላችሁ መጥቷል! ከአሁን ጀምሮ የፍሬሽማን እያንዳንዱን ትምህርት በየቻፕተ
📣 ለ2019 የመጀመርያ አመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ! ሙሉ በሙሉ ያለምንም ክፍያ የቀረበው ዝግጁ አፕ አዲስ ገጽታ ይዞላችሁ መጥቷል! ከአሁን ጀምሮ የፍሬሽማን እያንዳንዱን ትምህርት በየቻፕተሩ የተከፋፈሉ አዳዲስ የልምምድ ጥያቄዎች ተሰብስበው ገብተውላቹኋል። 📣 ይህ አዲስ ገጽታ ምን ይጠቅማቹሃል? ➡️ለፈተና 100% ያዘጋጃችኋል፡ ከትምህርቱ ይዘት ጋር የተጣጣሙ ጥያቄዎችን በመስራት ሙሉ በሙሉ ያዘጋጃቹሃል። ➡️ድክመታችሁን ይለያል፡ ክፍተት ያለባችሁን ቻፕተር በግልጽ በማሳየት ትኩረታችሁን የት ማድረግ እንዳለባችሁ ይጠቁማችኋል። ከዚህ በተጨማሪም ለጥናታችሁ የሚረዱ በርካታ አዳዲስ አገልግሎቶችን በቅርብ ቀናት እናስገባላችኋለን! 🔎 እንዴት እንደምትመዘገቡ ለማየት ማስታወሻ፦ Password የረሳችሁ መመዝገቢያ ቦት ላይ "Change Password" የሚለውን ቁልፍ ተጫኑ ወይም /recover ብላችሁ ይላኩ። ለመመዝገብ - @Zegju_registration_bot ▶️ Android (Play Store) 🛒 iOS (App Store)

📣 የጥሪ ማስታወቂያ ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ለተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፦ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ፣ የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ፦ • ሁሉም ነባር ተማሪዎች • በ2018 ዓ.ም የሪሜዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች • ለ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ የፍሬሽማን እና የሪሜዲያል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው የመግቢያ ጊዜ መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ስለሆነ፣ በተጠቀሰው ቀን በአካል ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታካሂዱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን። የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት

#EPSU የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ መስከረም 20 እና 21/2019 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል። ለምዝገባ
#EPSU የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ መስከረም 20 እና 21/2019 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ 🔵 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ 🔵 ከ9–12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ 🔵 የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ 🔵 አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣ 🔵 የፋይዳ መታወቂያ ዋናውና ኮፒው፣ 🔵 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ 🔵 ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፣ 🔵 የስፖርት ልብስ። (ተጨማሪ መረጃ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።) @FreshmanUnion✔️