Genesis Within
رفتن به کانال در Telegram
Thoughts • Life • Everything in between — Literary Works — ◇ Genesis Z.◇ Because a person's life isn't one-dimensional 😉
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
248
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-130 روز
آرشیو پست ها
እኔና የእኔ የስንት አመት ታናሼ ተመሳሳይ 'Feed' እየተመገብን እንዴት ልንሰነብት ነው?! 'የአዋቂ ጨዋታ' እየተባልን እንዳላደግን፤ አሁን እንደዚህ Social Media ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከህጻን እስከ አዛውንት አንድ አይነት ርዕሰ-ጉዳይ ላይ እንድንጠመድ ያድርገን። አወይ ዘመን! ወዴት እየሄድን ይሆን? 🤔
#Thoughts
@GenesisSpeaks
╔═══━━━─── • ───━━━═══╗
👔 HAPPY FATHER'S DAY 👔
╚═══━━━─── • ───━━━═══╝
╭────────────────────╮
│ 𝑆𝑢𝑛𝑑𝑎𝑦, 𝐽𝑢𝑛𝑒 21, 2026 │
╰────────────────────╯
╔═══━━━─── • ───━━━═══╗
👔 HAPPY FATHER'S DAY 👔
╚═══━━━─── • ───━━━═══╝
╭────────────────────╮
│ 𝑆𝑢𝑛𝑑𝑎𝑦, 𝐽𝑢𝑛𝑒 21, 2026 │
╰────────────────────╯
╔═══━━━─── • ───━━━═══╗
👔 HAPPY FATHER'S DAY 👔
╚═══━━━─── • ───━━━═══╝
╭────────────────────╮
│ 𝑆𝑢𝑛𝑑𝑎𝑦, 𝐽𝑢𝑛𝑒 21, 2026 │
╰────────────────────╯
╔═══━━━─── • ───━━━═══╗
👔 HAPPY FATHER'S DAY 👔
╚═══━━━─── • ───━━━═══╝
╭────────────────────╮
│ 𝑆𝑢𝑛𝑑𝑎𝑦, 𝐽𝑢𝑛𝑒 21, 2026 │
╰────────────────────╯
ከሁለት አጉል
ሰው ከሆንክ፣
ሰው የሚጠብቀው፣
ከፍ ካልክ፣
እንድትጠቅመው።
ዝቅ ካልክ፣
እንድትታዘዘው፣
ነው የሚፈልገው።
ከሁለት አጉል፣
ይጠላል፣
ያብጠለጥላል።
✍ ከዘሪሁን ሲሳይ
☞ @GenesisSpeaks
የኛ ሰው በ Anonymous Vent
እኔን የማታዩኝ እኔ ማላያችሁ፣
እንዴት ሰንብታችሁ፣ እንዴት ከረማችሁ?
ከውዱ ጊዜያችሁ በጥቂቱ ልዋስ፣
ስሙኝና እስኪ ብሶቴም ይቀስቀስ።
እኔ ወንድማችሁ፣ የእናንተ ቢጤ ሰው ፣
ሕይወት ገፍታ ገፍታው እዚህ የደረሰው፣
ምንም ሳልሸራርፍ ስብራቴም ይኸው ።
ከዛሬ ነገ ይሻል ብዬ ብታገልም፣
ከእዮብ ተምሬ ብሰክን ዝግ ብልም፣
አውጥቼና አውርጄ ብዙ ብጨነቅም፣
ሌላ መንገድ የለም ላይኔ የሚታየው፣
መዳፍ የእጆቼን ችዬ ካልዘረጋው።
እናም ወገኖቼ...
ስብር ልቤንና ድኩም አዕምሮዬን፣
እዩም ተደነቁ ተጋሩኝ ምስጢሬን፣
የተዘረጋ እጄ እዩ ሳንቲም ሲቃጭል፣
በምናብ አስቡ ያን ጎስቋላ ጉብል፤
ቡጭቅጭቅ ድሪቶ በላዪ የደረተን፣
ካፈር ላይ ተቀምጦ የሚንከላወስን።
በእዝነ ልቦናችሁ በአይነ ህሊናችሁ፣
ልሳለው ያን ምስል ይቀረጽባችሁ፤
ፊታችሁ ይክበደኝ፣ አይናችሁ ይግረፈኝ፣
ብቻ እናንተ እዘኑ፣ ምጽዋት ጣሉልኝ።
#VentOne
#To_be_tested😅
→ @GenesisSpeaks
በሀገራችን የስነ-ፅሁፍ ታሪክ ውስጥ እጅግ ድንቅና ለፊልም ስራ የሚመቹ የፈጠራ ስራዎች፣ በተለይም ልቦለዶች በብዛት ቢኖሩም፣ እነዚህን ስራዎች ወደ ፊልም ስክሪፕት (Screenplay) ቀይሮ የመስራት ልምድ ግን ገና ያልተለመደና ብዙ ያልተኬደበት ነው። እርግጥ ነው፣ ይህ አይነቱ ከልቦለድ ወደ መድረክ የመቀየር (Adaptation) ባህል በቲአትር ቤቶቻችን የተለመደና የተሳካ መስመር ሆኖ ቆይቷል። ይሁንና በፊልሙ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሙከራዎቹ የተወሰኑ ቢሆኑም፣ በተለያዩ ጊዜያት የተሰሩ ጥቂት ስራዎች ግን በተመልካች ዘንድ እጅግ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ማትረፍ እንደሚቻል በተግባር ማሳያ ሆነዋል።
በአሁናዊው የሀገራችን የፊልም ኢንዱስትሪ ተመሳሳይ ይዘት ባላቸው፣ የታሪክ ግጭታቸውና ሴራቸው እርስ በርስ በሚቀራረቡ የፍቅር ታሪኮች የታጠረ ይመስላል። ከዚህ ከተለመደው አዙሪት ወጣ ያሉ፣ ጥልቅ የሰው ልጅ ባህሪንና ማኅበራዊ እውነታን የሚፈትሹ የልቦለድ ታሪኮችን ወደ ፊልም ማምጣቱ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው። ይህ መሆኑ የፊልም ተመልካቾችን የጥበብ ፍላጎት የሚያረካ ብቻ ሳይሆን፣ የኢንዱስትሪውን የፈጠራ ጉልበት እና ብስለት ማሳያ ትልቅ በር ነው።
ይህ በትልልቅ ፊልሞች ላይ ያለው ክፍተት እንዳለ ሆኖ፣ በታሪክ አጭር ግን በይዘት ረቂቅ በሆኑት የአጭር ልቦለድ ድርሰቶች ላይ ግን አንዳንድ ደፋር አዘጋጆችና ዳይሬክተሮች ድንቅ ስራዎችን ሰርተውባቸዋል። አጫጭር ልቦለዶች ለአጭር ፊልሞች (Short Films) ያላቸው አመቺነት ከፍተኛ መሆኑን በተግባር ያረጋገጡ፣ እንደ ማሳያ ሊጠቀሱ የሚችሉ ሁለት ድንቅ አጫጭር ፊልሞች እነሆ፦
"ሽልንጌን" :-
youtu.be/Dov4ajK35nQ
"እናት":-
youtu.be/FXWTMwM2eVo
#Thoughts
☞ @GenesisSpeaks
This is the first Amh–Eng dictionary I've ever come across... hhhm, it's truly one of a kind.
#lexicology #linguistics
☞ @GenesisSpeaks
🔥 New gem incoming from Ezra of Hippo.
Eyes on the channel. Stay tuned! 👀 ☞ @hippozra
#KeepingYouPosted™
#NewRelease
@GenesisSpeaks
