Sinksar tube(ስንክሳር)
رفتن به کانال در Telegram
እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
3 015
مشترکین
+3324 ساعت
+1177 روز
+28330 روز
آرشیو پست ها
3 015
††† ✝️እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ✝️†††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ✝️ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን ✝️†††††† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ "አውሴ" ይባላል:: ዘመኑ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ : ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር:: ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም:: አውሴን "ኢያሱ" ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ኢያሱ ማለት "መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:- ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ) እንዲሆን ነው:: ቅዱስ ኢያሱ በበርሃ ለ40 ዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዝዞታል (አገልግሎታል):: እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል:: በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ ደብረ ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን : ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር:: ††† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ: ¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ ¤ሕዝቡን አሻግሮ ¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ ¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ ¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ:: የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዚያን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል : በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚያች ዕለትም ለ12ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ:: ሰባት አሕጉራተ ምስካይ (የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ አላቸው:- "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ:: ይህችውም የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ: በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው አባ ሕርያቆስ "ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ) ሲል ያመሰገናት:: ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት:: ††† በወዳጁ በኢያሱ እጅ የአሕዛብን ቅጥር ያፈረሰ እግዚአብሔር የእኛንም የኃጢአታችንን ግንብ በወዳጆቹ ምልጃ ያፍርስልን:: ከቅዱሱ ነቢይም በረከትን ያሳትፈን:: ††† ሰኔ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን 2.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት (ቅዳሴ ቤቱ) ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ 2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ 3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ 4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን 5.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ††† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" ††† (ኢያሱ. 24:14) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† 🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE
3 015
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
3 015
3 015
🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿
🌿 🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🔴የአበባውን ምስል አንድ ጊዜ በመጫን ጠቃሚ ነገር ይመልከቱ አንድ ጊዜ ብቻ ይንኩት፡፡❤
3 015
3 015
3 015
3 015
✞✞✞✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ✝️እንኳን አደረሳችሁ ✝️❖
❖ ሰኔ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ✝️ቅዱስ_ሙሴ_ጸሊም (ጥቁሩ ሙሴ) ✝️+"+=>ግብጻውያን ስማቸውን ጠርተው ከማይጠግቧቸው ቅዱሳን መካከል አንዱ ኢትዮዽያዊው አባ ሙሴ ጸሊም ነው:: በእኛ ኢትዮዽያውያን ግን ይቅርና በወርኀዊ በዓሉ (በ24) በዓመታዊ በዓሉ እንኩዋ ሲከበር ብዙም አይታይም:: =>ቅዱሱ ሰው በትውልዱ ኢትዮዽያዊ ሲሆን ያደገውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ እንደሆነ ይታመናል:: ገና በወጣትነቱ አገር የሚያሸብር ሽፍታ ነበር:: ሙሴ ጸሊም ወደ ግብጽ የሔደበት ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም መምለክያነ ጣዖት (ፀሐይን ከሚያመልኩ ሰዎች) ጋር ይኖር ስለ ነበር ምናልባት እነርሱ ወስደውት ሊሆን ይችላል:: +ቅዱስ_ሙሴ በምድረ ግብጽም በኃይለኝነቱ ምክንያት የሚደፍረው አልነበረም:: ፀሐይን ያመልካል: እንደ ፈለገ ቀምቶ ይበላል: ያሻውን ሰው ይደበድባል:: ነገር ግን በኅሊናው ስለ እውነተኛው አምላክ ይመራመር ነበርና አንድ ቀን ፀሐይን "አምላክ ከሆንሽ አናግሪኝ?" አላት:: እርሷ ፍጡር ናትና ዝም አለችው:: +ቅዱስ ሙሴ ምንም አስቸጋሪ ሰው ቢሆንም ፈጣሪን መፈለጉን ግን ቀጥሏልና አንድ ቀን ተሳካለት:: መልካም ክርስቲያኖችን አግኝቶ . . . ወደ ገዳመ_አስቄጥስ ቢሔድ በዛ ያሉ መነኮሳት ወደ እውነት እንደሚመሩት ነገሩት:: እርሱም ሰይፉን እንደታጠቀ ወደ ገዳም ገባ:: መነኮሳቱ ፈርተውት ሲሸሹ ታላቁ አባ_ኤስድሮስ ግን ተቀብለው አሳረፉት:: +"ምን ፈለግህ ልጄ?" አሉት:: "እውነተኛውን አምላክ ፊት ለፊት ማየት እፈልጋለሁ" የሙሴ ጸሊም መልስ ነበር:: አባ ኤስድሮስም "የማዝህን ሁሉ ካደረግህ ታየዋለህ" ብለው ወደ መነኮሳት አለቃ ቅዱስ_መቃርስ_ታላቁ ወሰዱት:: መቃሬም ክርስትናን አስተምረው አጠመቁትና ለአባ ኤስድሮስ መለሱላቸው:: +ከዚህ ሰዓት በሁዋላ ነበር የአባ ሙሴ ጸሊም ሕይወት ፍጹም የተለወጠው:: በጻድቁ እጅ ምንኩስናን ተቀብሎ ይጋደል ጀመር:: በጠባቧ በር ይገባ ዘንድ ወዷልና ያ በሽፍትነት የሞላ አካሉን በገድል አረገፈው:: ከቁመቱ በቀር ከአካሉ አልተረፈለትም:: ወገቡን በአጭር ታጥቆ መነኮሳትን አገለገለ:: አጋንንት በቀደመ ሕይወቱ በሕልም: አንዳንዴም በአካል እየመጡ ይፈትኑት ነበር:: +እንዳልቻሉት ሲረዱ ተሰብስበው መጥተው በእሳት አለንጋ ገርፈው አቆሳስለውት ሔዱ:: እርሱ ግን ታገሰ:: በበርሃ ለሚኖሩ አበው መነኮሳት ሁሉ ብርሃን በሆነ ሕይወቱ ሞገስ ሆነላቸው:: ለኃጥአን ደግሞ መጽናኛ ሆነ:: << በተራራ ላይ ያለች ሃገር ልትሠወር አይቻላትምና ስም አጠራሩ በመላው ዓለም ተሰማ:: ሁሉም "ሙሴ_ጸሊም ይል ጀመር ፡፡ >> +በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያን መኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግን ራሱን "አንተ ጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ: ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር:: ከቆይታ በኋላም በመነኮሳት ላይ እረኛ (አበ ምኔት) ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ:: የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩ አጣፍጦ: ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ:: +ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩ ሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ375 ዓ/ም በርበረሮች (አሕዛብ) ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳት ሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ7 ደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚሕች ቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል:: =>ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ ለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪው ያድለን:: =>ሰኔ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ) 2."7ቱ" ቅዱሳን መነኮሳት (ደቀ መዛሙርቱ) 3.አባ ኤስድሮስ ታላቁ ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት 2፡ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 3፡ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ 4፡ ቅዱስ አጋቢጦስ 5፡ ቅዱስ አብላርዮስ 6፡ አቡነ ዘዮሐንስ ዘክብራን 7፡ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ =>+"+ መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ "የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ" ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል:: +"+ (ሉቃ. 15:3-7) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> 🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE
3 015
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇
https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
3 015
🔴 ኦርቶዶክስ ኖት ❓️
🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹
🌿🌹🌹🌿
🌿🌿
🌿
🌿 🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿 🌿🌿🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🌿
🔴የአበባውን ምስል አንድ ጊዜ በመጫን ጠቃሚ ነገር ይመልከቱ አንድ ጊዜ ብቻ ይንኩት፡፡❤
3 015
✞✞✝️ የሰኔ 23 ✝️✞✞
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖✝️ እንኳን አደረሳችሁ✝️ ❖
❖ ✝️ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ✝️ቅዱስ_ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል✝️ +"+=>መፍቀሬ ጥበብ: ¤ጠቢበ ጠቢባን: ¤ንጉሠ እሥራኤል: ¤ነቢየ ጽድቅ: ¤መስተሣልም (ሰላማዊ) . . . እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ሰሎሞን የታላቁ ነቢይና ንጉሥ ልበ አምላክ ቅዱስ_ዳዊትና የቅድስት ቤርሳቤህ (ቤትስባ) ልጅ ነው:: ከ3ሺ ዓመታት በፊት የተወለደው ቅዱስ ሰሎሞን እስከ 12 ዓመቱ ድረስ በቤተ መንግሥት ከአባቱ ጋር አድጉዋል:: +ቅዱስ ዳዊት 70 ዘመን በሞላው ጊዜ የአካሉን መድከም አይቶ አዶንያስ በጉልበት እነግሣለሁ ቢልም አልተሳካለትም:: እግዚአብሔር ሰሎሞንን መርጧልና ገና በ12 ዓመቱ ነገሠ:: ልበ_አምላክ አባቱ ዳዊት ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት መከረው:: "ልጄ ሆይ! ልብህን ስጠኝ:: ፈጣሪህንም አምልክ" አለው:: +ቅዱስ ሰሎሞን እንደ ነገሠ በገባዖን ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቀረበ:: ጌታም ተገልጾ "ምን ትፈልጋለህ?" አለው:: ሰሎሞንም ልክ እንደ አባቱ ማስተዋልን: ልቡናን ለመነ:: በዚህም ጌታ ደስ ስለተሰኘ "አልቦ እምቅድሜከ: ወአልቦ እምድኅሬከ - ከአንተም በፊት: ከአንተም በኋላ እንዳንተ ያለ ጠቢብና ባለጠጋ ሰው የለም: አይኖርም" ብሎት ተሠወረ:: ቅዱስ ሰሎሞን ለ40 ዓመታት በእሥራኤል ላይ ነገሠ:: +ግሩም በሆነ ፍትሑ: በልዩ ጥበቡ ዓለም ተገዛለት:: እግዚአብሔር የመረጣት የእኛዋ ንግስተ_ሳባ /አዜብ/ማክዳም ትፈትነው ዘንድ ሒዳ ምኒልክን (እብነ_መለክን) ጸነሰች:: በኋላም ታቦተ_ጽዮንና ሥርዓተ ኦሪት መጣልን:: ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን ድንግል_ማርያም ከእነሱ ዘር እንደምትወለድ ነግሮት ነበርና ያበጀሁ መስሎት ሴቶችን አብዝቶ ነበር:: +ነገር ግን:- ¤አንደኛ ሰው (ሥጋ ለባሽ) ነውና: ¤ሁለተኛ ደግሞ ከብዙ ሴቶች መካከል ከአንዷ እመ_ብርሃን ትገኛለች መስሎት ነበር:: ነገሩ መንገድ ስቶበት ከአሕዛብ (ከፈርዖን ልጅ) ጋር በመወዳጀቱ ለጣዖት አሰገደችው:: እግዚአብሔር እጅግ አዘነ:: +በራዕይ ተገልጦ "ስለ ወዳጄ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ላይ ክፉን አላደርግም" አለው:: ታላቁ ነቢይ ሰሎሞን ይህንን ሲሰማ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ማቅ ለብሶ: አመድ ነስንሶ በፍጹም ልቡ አለቀሰ:: ንስሃ ገባ:: መፍቀሬ ንስሃ ጌታችንም ንስሃውን ተቀበለው:: +የይቅርታው መገለጫም ተወዳዳሪ የሌላቸውን 5 መጻሕፍት ገለጠለት:: ተናገራቸው:: ጻፋቸው:: እሊሕም:- 1.መጽሐፈ ጥበብ 2.መጽሐፈ ተግሣጽ 3.መጽሐፈ መክብብ 4.መጽሐፈ ምሳሌ 5.መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ናቸው:: +ቅዱስ ሰሎሞን ልዩ የሆነውን ቤተ_መቅደስ በመስራቱም ይደነቃል:: ደጉ ንጉሥ: ጠቢብና ነቢይ ሰሎሞን በዚህች ዕለት በ52 ዓመቱ ዐርፎ ወደ ፈጣሪው ሔዷል::
+"+ አባ_ኖብ +"+=>ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ሰማዕት አባ ኖብ አርፏል:: በዚሕ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን ቢኖሩም ዋናው ይኼው ቅዱስ ነው:: +አባ ኖብ እንደ ገዳማውያን በበርሃ የተጋደለ: እንደ ሊቃውንት መጻሕፍትን ያመሰጠረ: በተለይ ደግሞ በዘመነ ሰማዕታት ጭንቅ ጭንቅ መከራዎችን የተቀበለ አባት ነው:: ስለ ገድሉ ብዛት "ኃያል ሰማዕት": አንገቱን ስላልተቆረጠም "ሰማዕት ዘእንበለ ደም" ይባላል:: ዘመነ ሰማዕታትን ካለፉ 72ቱ ከዋክብትም አንዱ ነው:: =>ከመፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን: ከኃያሉ ሰማዕት አባ ኖብ በረከትን አምላካችን ይክፈለን:: =>ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል) 2.ቅዱስ አባ ኖብ (ሰማዕት ወጻድቅ) 3.ቅዱሳን መርቆሬዎስ: ፊልዾስና ቶማስ (ሰማዕታት) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ 2፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት 3፡ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ 4፡ አባ ሳሙኤል 5፡ አባ ስምዖን 6፡ አባ ገብርኤል 7፡ ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ =>+"+ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ:: ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል:: +"+ (መክ. 12:1-9) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> 🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE
3 015
3 015
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
