ወደ ኢየሱስ ደረት
رفتن به کانال در Telegram
Romans 8÷1 There is therefore now no condemnation to them which are in Christ Jesus, who walk not after the flesh, but after the Spirit.
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
276
مشترکین
-124 ساعت
-27 روز
-630 روز
آرشیو پست ها
276
Repost from ማርከን ዜማ Marken Zema ✟ 🇪🇹
አረስርሰኝ | Singer Bereket Tesfaye
Doriel Ministry
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ማርከን ዜማ @Markenzema_bot
በዚህ ቻናል የማይደመጥ መዝሙር የለም ብቻ ምን አለፋችሁ join ይበሉ
👇
https://t.me/+S2wsmZMSQp3vcGxp
https://t.me/+S2wsmZMSQp3vcGxp
276
በክርስቶስ የተወደዳችሁ🥰 ውድ የእኛ ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ?
አንዳንድ ሀሳቦችን ከእናንተ መቀበልን እንወዳለን እና ዛሬ እስኪ እናንተ የሆነ ነገር ፃፉልን✍ in comment section....👀👇
276
Repost from N/a
ሕዝቡ ግን አበዛ
ከጠላቶች ሁሉ አድኖ ጠብቆ፣
በተጨነቁት ልክ ባርኮ መርቆ፣
ነፃ አውጥቶአቸው ከግብፅ ምድር ከዛ፣
እርሱ ሕዝብ ሲያበዛ፣ ሕዝቡ ግን አበዛ።
✍Alazer Teshome
276
ማቴ 10:32-33 32 ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ 33 በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ። የክርስቶስ አባሳደሮች ነን!! . ➡ለምንድነው በዚህ ምድር ላይ እየኖርን ያለነው? ➡እያንዳንዱ የሚገጥሙን እድሎች ምን እንድናደርግባቸው ነው የተሰጡን? ➡እኛ የማን ተወካዮች ነኝ? ✏️ሰላም እና ፀጋ ከአብ ዘንድ ለእናንተ ይሁን ✏️የክርስቶስ አባሳደር ነኝ የሚለው ሀሳብ እውነት ልቤን ነክቶታል በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ መጥምቆ ዮሐንስን ታቁታላችሁ እና በማርቆስ ወንጌል 2:1-8 ባለው ክፍል ላይ ኢየሱስን እንዴት እንዳገነነው እናያለን ይህ ሰው በሰዎች ዘንድ እጅግ ተቀባይነትን ያገኘ ታላቅ ነብይ ነው ሰዎች እርሱን ለማየት እና ንስሀ ለመግባ ከኢየሩሳሌም ወደ ሚያጠምቅበት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ይመጡ ነበር እና ዮሐንስ ግን እያንዳንዱን የስከትን እና የእውቅናን Opportunity ክርስቶስን ለመናገር ይጠቀማል እራሱን እያሳነሰ ለተጠራበት አላማ ታምኖ የሚኖር ሰው ነው።ምንም በብሉይ ኪዳን ውስጥ በኢሳያስ ትንቢት 40:3 እና በሚልኪያስ 3:1 ላይ የተተነበየለት በበረሀ ነሚጮህ ድምፅ የተባለለት ቢሆንም በእናቱ በኤልሳቤጥ መሀፀን ውስጥ እያለ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ታላቅ ነብይ ሆኖ ሳለም እርሱ ግን ስለ ራሱ ከመናገር ይልቁን የዚህ ሁሉ ስኬት ምንጭ የሆነውን ክርስቶስን የሚያደምቅ ሰው ነው። 📍እኛስ??????????????🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
2ቆሮ 5:20 "እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን"📎ለኢየሱስ ክብር ማለት ስለእኛ በመስቀል ላይ መንጠልጠል ከሆነ ለእየሱስ ደስታ ማለት የእኔን እና የእናንተን በደል ተሸክሞ በአደባባይ እርጉም መባል ከሆነ ይህ ብቻ አይደለም አይጠቅሙሙ የተባሉትን እኛን ከቁምነገር ከቆጠረን በአባቱ ፊት ቆሞ የሚወራ ፅድቅ ሳይኖረን በፅድቁ ወደ አባቱ መንግስት ካስገባን በአባቱ ፊት እኛን የማያሳፍረን ከሆነ..... 📎እኛ ስለፅድቁ ለማውራት በአደባባይ ለመቆም ለምን እንፈራለን በአባቱ ፊት እኔን እና እናንተን የማያሳፍር ከሆነ እኛ ዛሬ በህይወታችን ምክንያት በአነጋገራችን ምክንያት በሰዎች ፊት ለምን ክርስቶስን እናሳፍራለን። 📎አንድ ነገር አንርሳ እኛ የክርስቶስን መንግስት፤ የዳንበትን ደም ፤የሞተልንን ልንናገር የምንኖር የክርስቶስ Ambassador ነን! በኢየሱስ ስም አውነተኛ አባሳደሮች መሆን ይሁንልን🙌 📌ከላይ ያሉትን ጥያቄዎች ለራሳችሁ መልሱ! ክርስቶስን የሚወክል ማንነት እንዲኖረን ምን እናድርግ? next part.....
276
Repost from እንዘምር ለጌታ🎤🎸🎹🎧🎤
ለውጥን ምርጫህ አድርግ
✅ለመለወጥ አለመወሰን ላለመለወጥ መወሰን ነውና ለመለወጥ ወስኑ
▶ለውጥን ምርጫ ካደረክ የሚከተሉትን ነጥቦች ተግባራዊ አድርግ :-
➪ አጉል ኩራትህንና ክብርህን ተዉ
➪ ለውጥን አሁኑኑ ጀምር( ለለውጥ ቀጠሮ አትስጥ)
➪ ከትንሹ ጀምር ዝቅ ብለህ
➪ ለውጥን በግል ጀምር ▶ ከሰው ጋር እለውጣለሁ ▶እሱ ሲለወጥ እለውጣለሁ እያልክ ጊዜህን አታባክን
..
..
➪ በትላንት ሕይወትህ አትፈር :- መሳሳትህን አምነ ተቀበልና ንስሐ ግባ
➪ የጎዳሃቸውን ሰዎች ይቅርት ጠይቅ
➪አዕምሮህን ▶ በፍላጐት ሳይሆን በድርጊት ▶ በትላንት ሳይሆን በነገ ▶ በተሸናፍነት ሳይሆን በአሸናፍነት ▶ በጥርጣሬ ሳይሆን በርግጠኝነት ▶በውድቀት ሳይሆን በመነሳት ሙላው።
➪ አቋራጭ መንገድ አትጠቀም
.......#ለመለወጥ_ካልወሰናችሁ_ላለመለወጥ_ወስናችኋል ሰለዚህ ለውጥን ምርጫችሁ አድርጉ..... ወዘተ
▶መልካም ወጣት 2015 ◀
ከቀኑ 6 ሰዓት
#ዮኒ(ዮናታን) ❤❤❤❤🙏🙏
👇 https://t.me/inzemirlegeta call -> +251941873870 comment kalachu 👉 @beka_tm 👈 👆👆Share and Join us
276
Repost from N/a
አይኖቼን አጥፋ
አይታየኝ ቀኑ፣ የቀለሞች ውበት።
ጉድጓዱም፣ ገደሉም፣ እኔ በማልፍበት፤
ምርኩዝም አልያዝ፣ እንድደገፍበት።
ሰውም አይኑረኝ ከቶ፣ እንዳልመካበት።
አይምራኝ ብሌኔ፤ አያምረኝ ገፅታ።
መንገድም አልውጣ፤ አይታወቀኝ ካርታ።
አይኖቼን አጥፋ፤
ሁሉ ጨልሞብኝ፣ በአይንህ ልይ፣ ጌታ።
✍Alazer Teshome
276
ምን ደስታ አለኝ
እኔ ፈገግ የምለው መአዛ ሲከበኝ
ነብሴ የምትረካው በመገኘት ውስጥ ስትገኝ
ምን ደስታ አለኝ ካንተ ውጪ
ሌላ ደስታን የሚያስመኘኝ
ብኮረኮር ፈገግ የማይል ጥርሴ
እንዲሁ ይስቅብኛል ሳገኝህ ወዳጄ
ባልዳስስም እጆችን ባልነካው ልብስህን
ውስጤ ግን ይወቅህ አብረኸኝ እንዳለህ
ምን ደስታ አለኝ
አንተ ካልታወከኝ መተ ካላቀፍከኝ
በሀለዎትህ ውስጥ ዘፍቀህ ካላረሰረስከኝ
ምን ደስታ አለኝ
ሺዎች ቢመጡ ቢያጅቡኝ ያላንተ
እኔ ይከፋኛል መንፈሴም ታወከ
አንድ የሚያረካኝ መገኘትህ ነው
ስስቅ የሚያምርብኝ ካንተ ጋር ስሆን ነው
ምን ደስታ አለኝ
አንተ አዝነህ የምፍለቀለቅበት
ልብ ተሰብሮ የምኩራራበት
አንድም ከፍታ አይኑረኝ የምትከፋት
ይልቁን ወዳጄ ደስታዬ ካንተ ጋር
ፌሽታዬም ከህልውና ጋር
ይዝለቅልኝ ከልብህ ደስታ ጋር
✍በፅናት
276
ምንም እንደማይችል
አቅም እንደሌለው
አንችልም እንላለን
አንተው ብቻ እንድትመራን
አንተ ያለህበት ያምራል
የነካኸው ይሰምራል
ብቻ አንድ ነገር እንላለን
ያላንተ አንችልም ምራን እንላለን
መንፈስ ቅዱስ🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
276
ሁሌ ልይ
በትናትናው መረስረስ በትናት ኑሮ
አትችልም ነብሴ ልትኖር ህይወቱዋ ሰምሮ
በቃኝ የማልል የሁልጊዜ ረሀቤ ነህ
አለምድህም ውዴ ዛሬም ሁሌም እንቁዬ ነህ
አይኖቼ አንተን ከማየት አምሮት
እጆቼ አንተን ከመዳሰስ ጉጉት
መቼም አይቆጠቡ እልፍ ጊዜ ይዋትቱ
ሁሌም አይድከሙ ሺ ጊዜ ይዳክሩ
እይታዬ ትኩረቴ አንተ ብቻሁን እና
የምነካሁ ሁሉ አንተን ያስታውሰኝ እና
የምሰማው ድምፅ አንተን ያቅርብልኝ እና
ሁሌ ላይህ እናፍቃለው ፍቅሬ ይብስና
ሁሌ ሁሌ ልይህ ኢየሱሴ
ከአይኔ የአለምን መጋረጃ አንሳና
ለጉልበቶቼ በፊትህ እንዲሆኑ
የትጋትን ፀጋ ጨምርልኝ እና
ድካም ዝለቴን በመንፈስ ጥረገው እና
ሁሌ ላይህ እናፍቃለው የሳሌም አለቃ
✍በፅናት276
Repost from N/a
የውዥንብር ጉዞ
አቤት የኛ ነገር ምነኛ ተሞኘን፣
በለምለሙ ሥፍራ ተርበን ተገኘን።
ማንነታችንን በውል የማናውቀው፣
ቀን ሳያልቅ ለማታ የሚንጨነቀው።
መንገዱ ሳይጠበን አዲስ ስንገነባ፣
በመግቢያው ስንወጣ በመውጫው ስንገባ።
ያየንን ሳናየው የማይታየውን መርጠን፣
ስንለፋ ስንለፋ ድካም ሸነቆጠን።
መራራው ጣፍጦን ጣፋጩ መረረን፣
ወራሪው ሲዳከም ልባችን ወረረን።
መቅበዝበዝ ልምድ ሆኖን ማረፍ አቅቶናል፣
ያገኘንን ጌታ ማግኘት ከብዶናል።
ውሃ እየጠማን ምንጩን ስንደፍን፣
በከንቱ ስንሮጥ ለመጥፋት ተረፍን።
✍Alazer Teshome
276
Repost from N/a
እንገናኝ ነጌ
እንገናኝ ነጌ፣ እንገናኝ ደህና፤
ደቂቃ ይጨመር፣ ልዘገጃጅና።
ቆሽሼ እንዳልገኝ፣ ልተጣጠብ ገላ፤
ቤቴን ላሰናዳ፣ አልወቀስ ኋላ።
ሰጣለሁ ያልኩትን፣ ልስጥና ጠቅልዬ፤
መጣለሁ ያልኩበት፣ ልምጣ ደረስ ብዬ።
ያሳዘንኩት ካለ፣ ልጠይቅ ይቅርታ፤
ያለብኝን ዕዳ፣ ልክፈል እስከማታ።
አልቀጥርም ዛሬ፣ ይድከመኝ ልሥራ፤
ሳልፈፅም ሳልጨርስ፣ ከመሀል አልጠራ።
አንዴ ልረጋጋ፣ ሩጫዬን ልግታና፤
ከመንገድ እንዳይሆን፣ ሳላርፍ በጎዳና።
መንፈሴን ልሰብስብ፣ ከቀልብ ልሁን ላፍታ፤
ንሰሐውን ምስጋናውን፣ ላስይዝ ቦታ ቦታ።
አልሸሽ ነገር ሮጬ፣ አልተርፍ ተሸሽጌ፤
እንደማትቀር ባውቅም፣
ደቂቃ ይጨመር እንገናኝ ነጌ።
✍Alazer Teshome
276
ሉቃ17:11-19
አመስጋኝ ልብ
በዚህ ክፍል ኢየሱስን እና አስሩን ለምፃሞችን እናያለን ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በኢያርኮ እና በሰማሪያ መካከል እያለፈ ወደ አንዲት መንደር ይገባል ከሩቅ አስሩ ለምፃሞች እየሱስን አይተው እየሮጡ ሲመጡ እንመለከታለን በዚህ ክፍል ሉቃስ የኢየሱስ ተከታዮች የምስጋና ልብ ሊኖራቸው እንደሚገባ ያስተምራል። ይህንን አሳብ ለማስተማር ኢየሱስ 9 አይሁዶችና 1 ሳምራዊ ያለበትን የለምጻሞች ቡድን ስለፈወሰበት አጋጣሚ ተርኳል። የሚገርመው ከተፈወሰ በኋላ ወደ ኢየሱስ ተመልሶ ምስጋናውን ያቀረበው ሳምራዊው ብቻ ነበር። በእግዚአብሔር ቤት ረዥም ጊዜ የኖርን ሰዎች የአመስጋኝነት ልብ ሊኖረን እንደሚገባ መገንዘብ አለብን። ስለዚህ ስንተነፍስም የእግ/ር እጅ አለበት ስንሄድ ስንመጣ የእግ/ር ምህረት ነው የገነነው በእያንዳንዱ ምልልሳችን እግ/ር ይመሰገናል ምክንያቱም መኖር በእርሱ ስለሆነ።
እንደነዚያ 9ኙ ለምፃሞች ተደርጎልን ከእጁ ተቀብለን የምንኮበልል ሳይሆን ምንም ቢደረግልን መልሰን ለእርሱ የምንሰጥ እንድንሆን ያስፈልጋል
ስለዚህ አስትንፋሳችን እስካለን ድረስ እግ/ርን እናመሰግነዋለን
እስቲ ለ2 ደቂቃ ስልካችሁን አስቀምጣችሁ ወደ ላይ እያያችሁ እግ/ር በህይወታችሁ ስላደረገላችሁ ነገር አመስግኑ.......አሜን
እንደነዚያ 9ኙ ለምፃሞች ተደርጎልን ሳናስተውን በዚያው የምንኮበልል ሳይሆን እግ/ር ያደረገልንን ነገር አስተውለን መልሰን እርሱ እንዲመሰገንበት ወደ እርሱ መቅረብ አለብን ከእጁ የምንቀበል ብቻ ሳይሆን አመስጋኞች ልንሆን ያስፈልጋል
ሀና ልመናዋ የሆነው ሳሙኤል ሲሰጣት መልሳ ለእግ/ር ክብር ሰጠችው ስለዚህ ስለሁሉ ጌታ ይመሰገናል276
Repost from N/a
ወይዘሮ ችግር 👵
፧
፧
የፈጠራ ግብዐት የለውጥ ጉዞ መሪ
የህዳሴ ንግስት ጠንካራ አሠሪ
ቀድማ የሚትፈትን ጎበዝ አስተማሪ
ሁሉም የሚያደምጡአት ቆንጣጭ መካሪ
ፈረቃ የሌላት ሙሉ ግዜ አገልጋይ
የሰው ወኔ ቀስቃሽ እስከሞት አታጋይ
የትጉን ልብ አዳሽ የታካቹን ገዳይ
ጥቁሩን ነጩን እኩል የምታደርግ ደልዳይ
የዕውቀት መሠረት የማስተዋል እናት
የጥበብ መነሻ ወይዘሮ ችግር ናት
"ችግር" አይጥሉአት ለውጥን አርግዛለች
ተስፋ ካልቆረጡ ትወልድልዎታለች።
✍Alazer Teshome
