ELEVATE SKILL
Ir al canal en Telegram
Master Your Skills with us! 🎨Graphics Design 🎞Video Editing 📈 Digital Marketing 🌐 Web Development 📱 Application Development 🤖Robotics Telegram :- @Elevateskillsupport Instagram :- elevateskill.1 📞-+251981807055
Mostrar más1 074
Suscriptores
Sin datos24 horas
+47 días
+630 días
Archivo de publicaciones
1 074
🎓 ወደ ኋላ ተመልሰን እናስብ...
አንድ ደቂቃ ዝም ብለን ወደ ኋላ እንመለስ።
ወደ ዩኒቨርሲቲ የገባንበትን የመጀመሪያ ቀን ታስታውሳላችሁ?
ያ ቀን... እኛ ለአዲስ ሕይወት መጀመሪያ ነበር፤ ለቤተሰቦቻችን ግን የብዙ አመታት ድካምና መስዋዕትነት ፍሬ ነበር።
አንዳንዶቹ ቤተሰቦች በሬ ሸጡ፤ አንዳንዶቹ እህላቸውን ሸጡ፤ ሌሎች ደግሞ መሬታቸውን አስያዙ። ያላቸውን ሁሉ አውጥተው "ልጄ ይማር፣ ሕይወቱ ይለወጥ" ብለው አዲስ ልብስ፣ አዲስ ቦርሳ፣ አዲስ ጫማ ገዝተው በእንባና በፈገግታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሸኙን።
እኛ ግን ያኔ ሁሉንም አላስተዋልንም።
በአዲሱ አለም ተውጠን ነበር።
አዲስ ግቢ... አዲስ ዶርም... አዲስ ጓደኞች... አዲስ ሕይወት...
ከአገር ሁሉ የመጡ ተማሪዎችን አገኘን። የተለያየ ቋንቋ፣ ባህል፣ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ከአንድ ክፍል፣ ከአንድ ዶርም ውስጥ ቤተሰብ ሆኑ።
በመጀመሪያው ሳምንት ግቢውን ስንዞር የነበረው ጉጉት... የመጀመሪያው ክፍለ ትምህርት... የመጀመሪያው ሌክቸር... የመጀመሪያው ሚድ ፈተና... የመጀመሪያው ውጤት...
ሁሉም ዛሬ ትዝታ ሆነዋል።
ምሽት ላይ በዶርም ተሰብስበን የምናወራቸው ወሬዎች... "ነገ እናነባለን" ብለን ሌሊቱን ሙሉ ስናወራ... ከፈተና አንድ ቀን በፊት መጽሐፍ ፈልገን ስንሯሯጥ... Assignment የሚሰራውን ጓደኛ ፈልገን ስንጠራ... Group study ብለን ተሰብስበን ከ10 ደቂቃ በኋላ ወደ ቀልድ ስንገባ... በካፍቴሪያ ረጅም ወረፋ ስንጠብቅ... የወር መጨረሻ ገንዘብ ሲያልቅ "እስከ ሰኞ አበድረኝ" ማለታችን... ሁሉም... ዛሬ የምንስቅባቸው ትዝታዎች ሆነዋል።
አንዳንድ ጓደኞች ከእኛ ሕይወት ውስጥ ወጡ፤ አንዳንዶቹ ግን እስከዛሬ የሕይወት ጓደኞቻችን ሆነው ቀሩ።
አንዳንድ አስተማሪዎች ጠንካራ ነበሩ፤ በወቅቱ አልወደድናቸውም። ዛሬ ግን ብዙ ያስተማሩን እነሱ እንደነበሩ እንረዳለን።
ይቀጥላል .........p2
@elevateskill✅
Via//Amanuel⭐️
.
1 074
Repost from ELEVATE SKILL
ዛሬ ከምሽቱ 3:00 ላይ ይጠብቁን። ከወጣት entrepreneur //CEO-CO FOUNDER //
በተለይ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች //ምክር ብቻ ሳይሆን የስራ እድልንም ይዞ መቷል።ምሽት 3:00 እንዳያመልጣቹህ።
