ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más4 491
Suscriptores
+1024 horas
+847 días
+87330 días
Archivo de publicaciones
+2
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል የምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ሰብሳቢ ንስሩ አርበኛ ዘመን ተሻለ ‼️
ፅናት፣ቁርጠኝነት፣ጀግንነት፣የመሪነት ጥበብ ሁሉን አሟልቶ የሰጠዉ እንቁ መሪ‼️
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አዲሱ ትውልድ... ራሱን ከውስጣዊ የህልወና አደጋ ካመጡት አካላት እና ባህርይ የጸዳው ትውልድ ነው ‼️
-
(በኮሜንት የቀረበ ጥያቄን መነሻ አድርጎ የተለጠፈ😊)
አዲስ ትውልድ የሚለው አግላይ ነው የሚል ሀሳብ ይነሳል። መልሱ አዎ ያገላል ነው። ሆኖም አለማው ከማግለል አስቀድሞ አዲስነትን ማስረገጥ እና ማስረጽ ነው።
የሚገለለው ማን ነው ከተባለ ፦ የከሰረው፣ ከጎሰቀለው (corrupted) ፣ በአስተሳሰብ ኋላኛው ላይ ተቸንክሮ ዘመኑን ካልዋጀው ፣ ተላላኪነት እና ተለጣፊነት መገለጫው ከሆነው፣ የአስተሳሰብ ጥገኝነት ካለበት፣ ምሁራዊ አድርባይነት ከተጠናወተው፣ ከእውቀት አክፍሎተኛው፣ .... ይህ አይነቱ የፖለቲካ መደብ በትግሉ ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም። ትግሉ "የአዲሱ ትውልድ" ነው።
በሀገር ውስጥ ካሉት ሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች ውስጥም ሆነ በሌላው አለም፣ የፖለቲካ career expiration አለው። የእኛ ትግል ጉበኞች (watchdog's)
ስላልነበሩት እና በደንብ ኦዲት ስለማይደረግ "የከሰረው" ሁሉ ተስቦ መጥቶ ከሞት የሚነሳበት፣ ውስጥ ያለውም ደግሞ ስም እና ግብር እየቀያየረ የሚሸቅጥበት መሆኑ አብቅቷል። ትግሉም ሆነ የፖለቲካ ምህዳሩ ከየት እስከ የት ተብሎ የተሰመረ እና ባለቤት ያለው በመሆኑ እንዲሁ መግባት እና መውጣት የለም። አይኖርምም።
.
.
የአማራ ትግል የትውልዶች ጦርነትን የማሸነፍ ነው። ይህን አረፍተነገር በዚህ ልጥፍ አላብራራም። ነገር ግን በዚህ ሀሳብ መነሻነት የአማራን ጦርነት ውስጣዊ እና ውጫዊ ገጽታ መጥቀስ ግን ይገባል። የአማራ ህልውና ጦርነት አንደኛው አካል ከውጭ ወደ ውስጥ የሚነሳ ነው። ጦርነቱ በአካል በዚህ ዘመን የህልውናችን ዋነኛ ተላብሶ የሆነው አረመኔን የአብይ ብልጽግና ደመኛ ጠላትነት የመነጨ ነው። ሆኖም የዘመኑ ጦርነት ደጋግመን እንደምንለው የራሱ ታሪካዊ መነሻ ያለው የአማራን ሁለንተናዊ ራስ በቅነት የሚገዳደሩ አካላት በተለያዬ ዘመን የጋረጡበት አደጋ የቀጠለ እና ህልውናን ጨርሶ ወደ ማጥፋት የደረሰበት ነው። የአደጋው ሁለተኛ ገጽታ ውስጣዊ ነው። ዋነኛ ውስጣዊ የህልውና አደጋ ባለቤቶች ከአመለካከት እና ባህሪ አንጻር በዋናነት ፦
1) ራስ ጠል ሀሳብ፣ ዕሳቤ እና ባህል
2) የፖሊቲው ድብታ እና ራስን ማግለል
3) ከፋፋይነት እና አቆርቋዥነት
4) ጥገኝነት
5) ያልተደራጀ እና የማይተመማን ፖለቲካዊ ማህበረሰብ
6) በጠላት ፍላጎት ልክ የተቀረጹ ኤሊቶች የስልጣን ወንበር ይዘው፣ አማራን እንዳይደራጅ መከልከል/መከላከል
7) መጥፎ/ደካማ ኤሊት ( corrupted elite )
እነዚህ ውስጣዊ ችግሮች የህልውና አደጋ ምክንያት ከመሆን ባሻገር ከውጭ የመጣብንን ጥቃት ለመከላከልም እንዳንችል አድርገውን ለዛሬው አደጋ ተጋላጭ ሆነናል። አሁንም የህልውና ትግሉ ውስጥ በተለያዩ መልኩ የሚገለጡ ሆነው ይታያሉ። አብዮታችን እነዚህን ውስጣዊ የህልውና አደጋዎች በየምዕራፉ፣ በየአጋጣሚው እና በየደረጃው ሊያጸዳ ይገባል።
👉 አዲስ ትውልድ ስንል ራሱን ከውስጣዊ የህልውና አደጋ ማጽዳት የመጀመሪያው ክፍል ሲሆን ቀጣዩ እና ዋነኛው ስራ በአማራነት የጸና መሠረት ላይ የቆመ ትወልድ መሆንን ይመለከታል። አዲሱ ትውልድ በብሔራዊ ንቃት እና ቁጭት፣ በፍጹም ራስ በቅነት የሚመራ ሀይል ነው። አማራነትን የሚወድ፣ በብሔራዊ ንቃት እና ቁጭት ድብታን እና ትኙነትን ያሸነፈ፣ ጸረ ራስ የሆነውን አቆርቋዥ ከፋፋይነት እንዲሁም ጥገኝነት በአማራነት ያሸነፈ፣ ሁሌም በልህቀት እያደገ የሚሄድ የጸና አደረጃጀትን የሚሻ እና የመጥፎ ልሂቃን የጎሰቀለ የፖለቲካ ባህል ውርስ በቅንነት ያሸነፈ እና የሚያሸንፍ ትውልዱ ነው። አዲሱ ትውልድ እንዲህ ያለ ነው።
አዲስነት ከአሮጌነት ካልተፈታ እና ካልተፋታ ጉዞው አድካሚ ነው!
የብልሽት እና የንቅዝ ውርስ የሆነ ሀሳብ ጀምሮ በተለያየ መልኩ የሚገለጽ ባህል እና ድርጊት በአማራነት አብዮት ሊጸዳ ይገባል። ባንዳን ብቻ ሳይሆን ባንዳዊ አስተሳሰብን፣ ልማድን፣ የዚያ ውርስ ዝንባሌን በጥቅሉ ጸረ-ራስነት ከመላው የአማራ ተዋስኦ፣ የፖለቲካ መድረክ እና አደረጃጀት ሊጸዳ ይገባል። ይህ አዲስነት ነው። ይህ ውስጣዊ የህልውና አደጋ አምጪ ተዋሲያንን ማስወገድ ነው። ይህ የህልውና ጦርነቱ አካል ነው።
አዲሱን ትውልድ ከአሮጌ ሀሳብ፣ ስሌትም፣ ባህል እና አሳለለፍ ጋር ፈንታ የለውም።
እናም ታጋየም ሆነ ደጋፊው ውስጡን በዚህ አብዮታዊ የብሔርተኝነት ሀሳብ ያርም፣ ራሱን ያርቅ (ማረቅ-አውቆ መታረም)። በተለይ ተነቃዩ ( ከፊሉ ዲያስፖራ እና በራስ ጠልነት የተጠመቀው የሀገሬው አማራ ) ከታወረ ራስ ወይም ከራስ እውርታ (the self as a blind spot) ወጥቶ ራሱን ሊፈትን፣ ሊሰልል እና አውቆ በአብዮታዊ መንገድ ከራሱ ጋር ሊተዋወቅ እና ፖለቲካዊ ጉስቁልና ካደበተው ባህል ነጻ ሊወጣ ይገባል።
👉 የወቅቱ የአማራ ትግል ከተለያየ የፖለቲካ መስመር እና የፖለቲካ አሰላለፍ ታሪክ የመጡ ሀይሎች በደጋፊነት አንዳንዴም በታጋይነት ይገኙበታል። ይህ ሀቅ ሆኖ ሳለ ለትግሉ የመስመር ጥራት ሲባል ዝብርቅርቁ መጥራት አለበት፤ ይጠራልም። በተለይ ደጋፊው ሀይል ሚናውን በልኩ ከመመዘን ባሻገር በቀደመ የፖለቲካ አሰላለፉ እና ታሪኩ ምክንያት ትግሉ ላይ ሊመጣ የሚችልን ችግር አውቆ ከወዲሁ ራሱን ማረም ይጠበቅበታል። እኛም ደጋግመን ማሳሰቡን እንቀጥልበታለን። ለማገዝ የሚመጣን አካል መቀበል ተገቢ ነው። ሆኖም ማገዝን ተከትሎ የሚመጣን መበረዝ ግን መታገል አለብን። እንታገላለን።
👉 ፖለቲካችን ከሀቀኛ የራስ ወይም የውስጥ ትንተና'ና እና ግንዛቤ መነሳት የአዲሱ አስተሳሰብ መሠረት ነው። ሆኖም ከዚህ በተቃራኒ የችግር ሁኔታን በማለባበስ ወይም በማስተናነስ እና ያልተፈተነ ራስን ይዞ ለመፍትሄ መቅረብ ተደራራቢ ሸክም ሆኖብናል። የህልውናችን ውስጣዊ አደጋ የሆነው መጥፎ ልሂቅ ዛሬም ለህልውና በምናደርገው ትግል ውስጥም ተከትሎ የትግላችን ውስጣዊ የህልውና አደጋ ሆኖ እንዳይቀጥል መታገል የአዲሱ ትውልድ የአዲስነት ግዴታ ነው። አዲስነት የዕድሜ አይደለም፤ አዲስነት የመስመር ነው። ሆኖም በነባሩ የአማራ ትግል ውስጥ ጥቂት የማይባለው የከረመ ልምድ ያለው አካል በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ባልጠራ ሲያልፍም በተበላሸ መስመር የከረመ መሆኑ ግልጽ ነው። መፍትሄው ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ራስን ማረቅ እና ለመታረም በቅንነት መዘጋጀት ነው።
አብዮታዊ እርማት መውሰድ ለትውልዱ አዲስ አስተሳሰብ ስምረት ብሎም የአዲስ ተስፋው ማህተም ለሆነው አሸናፊነት ወሳኝ ነው።
ህልውናችን በክንዳችን!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!
አማራነት ያሸንፋል!
እስከ ምጽአት አማራ!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!
እስቲበል ዓለሙ
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የ2018ዓ.ም ትምህርትን በተመለከተ ድርጅታችን አፋብኃ ባወረደው መመሪያ መሰረት የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ኮር ጉና ክፍለጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ የጦር ሰፈር ትምህርት ለማስጀመር መምህራኖችን ለማወያየት እና አቅጣጫ ለመስጠት ሰብስበው እያለ ትምህርት ጠሉ ብልጽግና ትምህርት እንዳይከፈት በመፈለግ ፋኖ ከመምህራኖች ጋር የሚያደርገውን ውይይት ለማደናቀፍ ሙከራ ቢደርግም ደፈጣ በጣሉ ጀግና የፋኖ አባላት በመጣበት አሯሩጠው ውይይቱን ማጠናቀቅ ተችሏል።
በዚህ የተበሳጨው አሸባሪው የብልጽግና ወንበር ጠባቂ አራዊት ሰራዊት ወደኋላ ሲመለስ በብስጭት እስቴ አምጃየ ቀበሌ #ሶስት አርሶ አደሮችን ማለትም:-
✅ጣፈጠ ደሴ እድሜ 50
✅ሙጨ ይርጋ እድሜ 65
✅ወጣት ጌታሰው አጥናፉ እድሜ 20 በማቁሰል በእጃቸው ይዘው ሁሉንም ረሽነዋቸዋል💔!
ይሂን አረመኔ ስርአት ከማስወገድ በቀር ሌላ አማራጭ የለም !
04/ዐ1/2018 ዓ.ም
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ጥቅምት_30_ማይካድራ_ብርጌድ_ጠላትን_ደመሰሰ‼️
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
፬ኛ ደጃዝማች ኮር ጎቤ ክ/ጦር ጥቅምት 30 ማይካድራ ብርጌድ ጠገዴ ወረዳ ከሶሮቃ ወደ ጎንደር ከተማ አቅጣጫ ሲጓዝ በነበረ የጠላት ሰራዊት ላይ ማክሰኝት የተባለ ቦታ በደፈጣ ሁለት ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ የተጫነ ጠላት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።
በርካታ ተሽከርካሪ እና ሰራዊት እያነቃነቀ በነበረበት አንድ ኦራል ወታደራዊ ተሽከርካሪ እና ሌላ አስር ጎማ ሲቪል ተሽከርካሪ ላይ ተሳፍሮ ይጓዝ የነበረው ጠላት ላይ ኢላማ በማድረግ በተሰነዘረበት መብረቃዊ የደፈጣ ጥቃት የኦራሉ አሽከርካሪ በአልሞ ተኳሽ መመታቱን ተከትሎ ኦራሉ ተገልብጦ የወደመ ሲሆን ታጣቂዎቹ በሙሉ ረግፈው ቀርተዋል።አስር ጎማ ተሽከርካሪ ላይ የነበሩት በተከፈተባቸው የተኩስ እሩምታ እሳት ዘንቦባቸው አንድ ለጊዜው በውል ያልታወቀ ወታደራዊ ሻለቃ መሪን ጨምሮ በርካቶች ተደምስሰዋል።
በዚህ የደፈጣ ጥቃት 29 የጠላት ሰራዊት ሲደመሰስ 12 ቁስለኛ ሁነዋል።
የደረሰበትን ምት መቋቋም የተሳነው የጠላት ሰራዊት ንፁሃን ነዋሪዎችን ኢላማ በማድረግ ከፍተኛ እንግልት ፈፅሟል።
ከ5 ቀናት በፊት በእርጎየ አካባቢ ተመሳሳይ ጥቃት የሰነዘረችው ጥቅምት 30 ማይካድራ ብርጌድ በቀጠናው ለመተላለፍ በሚሞክር ጠላት ሰራዊት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት በማድረስ ውጤታማ ተልዕኮ እየፈፀመች ይገኛል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!©አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ
መስከረም 04/2018 ዓ.ም
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
🔥በቅርብ ቀን ባንዳን #እጁን_ቆርጠን ለህዝባችን እፎይታን እናበስራለን‼️
ወደ ትግል ሜዳ የወረድነው የአማራ ህዝብ የትግል ሪዮት ገብቶን እንጅ ቁራሽ ዳቦ ቸግሮን አይደለም የአማራን ህዝብ እፎይታ እምናበስረው የተደረደረው መሳሪያ #በሚተፋው_እርሳስ እንጅ በአብይ አህመድ የቀበሌ ካድሬ #ጭብጨባ አይደለም!!!
በቅርብ ቀን ባንዳን እጁን ቆርጠን ለህዝባችን እፎይታን እናበስራለን።
©የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የጀብደኛው አሳምነው ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ንጉስ አበራ
04/ዐ1/2018 ዓ.ም
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ከ585,882 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች መሀል ያለፉት 48,920፣ የወደቁት ደግሞ 536,962 ሆነዋል። በሌላ አገላለፅ 91.6% ተማሪዎች ወድቀው 8.4% ብቻ አልፈዋል ነው።
ይህ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ትውልድ ምን ሊሆን ነው? ከሰሞኑ እየታፈሰ ወደ ጦር ማሰልጠኛ እንደሚገባው ትውልድ እጣ ፈንታቸው ይሆን?
ያሳዝናል!
© ኤሊያስ መሠረት
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የግንባር ዜና
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ፩ኛ ኮር የጉና ክ/ጦር አካል የሆነችዉ እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ሻለቃ 2 በዛሬዉ ዕለት መስከረም 04 / 2017 ዓም በወረዳዉ ትምህርት እንዲጀመር ከመምህራን ከሱፐር ቫይዘር ከወመህ እና ከማህበረሰቡ ጋር ለመወያየት ጥሪ አድርገዉ ፕሮግራሙን እየጀመሩ በነበረበት ስሀት ገዳዩ ዘራፊዉ እና ፋሽስቲዝሙ ስርአት ዉይይቱን ለማቋራጥ ለ2 አመት ታግዶ የነበረዉ ትምህርት አሁንም እገዳዉ እና የትዉልዱ ስቃይ እንዲራዘም ለማድረግ ስርአቱ ጥምር ጦር አዘጋጅቶ አምጃየ ቀበሌ ላይ ዉጊያ ከፍቷል። በነበልባሎቹ የሚመራዉ እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ሻለቃ ሁለት፣ መቅደላ አምባ ብርጌድ እና የክፍለ ጦሩ ቃኝና መሀንዲስ በጥምር ጠላት መነሻውን መካነ እየሱስ ከተማ አደርጎ ወደ አምጃዬ ቀበሌ ሲጓዝ በነበረበት ስሀት ነበልባሎቹ ቀድመዉ ደፈጣ በመጣል ከጥዋቱ 4፡00- 8፡10 ሰአት ድረስ ሲወቁት እና ሲለበልቡት ውለዋል። የጠላት ሃይል እጅግ ብዙ እና መጠነ ሰፊ የሆነ አስከሬኑን እና ከ10 በላይ ቁሰለኞቹን ተሸክሞ ወደ ወጣበት የቀበሮ ጉድጎድ ተመልሶ ገብቷል።ነገር ግን ሲመለስ ወደ ስብሰባዉ ሲሄዱ የነበሩ 3 ንፁሀንን ይዞ ረሽኖ 1 ንፁሀንን አቁስለዉ ጭነዉ ወስደዉታል።በእስቴ ወረዳ በብልፅግና ሆድ አደሮች ሰላማዊ ዜጎች ኢላማ ተደርገው ውለዋል። አምጃየ ቀበሌ የተረሸኑ 3አርሶ አደሮች
፩. ጣፈጠ ደሴ እድሜ50
፪. ሙጨ ይርጋ እድሜ65
፫. ጌታሰው አጥናፉ እድሜ20 እና አስቻለው የተባለ ንፁሀን በማቁሰል ሽንፈታቸዉን በንፁሀን ላይ አራግፈዉ ሂደዋል።
መዳረሻዉ ድልና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!!
ድላችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ
ማይካድራ ብርጌድ ጠላትን ደመሰሰ!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
፬ኛ ደጃዝማች ኮር ጎቤ ክ/ጦር ጥቅምት 30 ማይካድራ ብርጌድ ጠገዴ ወረዳ ከሶሮቃ ወደ ጎንደር ከተማ አቅጣጫ ሲጓዝ በነበረ የጠላት ሰራዊት ላይ ማክሰኝት የተባለ ቦታ በደፈጣ ሁለት ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ የተጫነ ጠላት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።
በርካታ ተሽከርካሪ እና ሰራዊት እያነቃነቀ በነበረበት አንድ ኦራል ወታደራዊ ተሽከርካሪ እና ሌላ አስር ጎማ ሲቪል ተሽከርካሪ ላይ ተሳፍሮ ይጓዝ የነበረው ጠላት ላይ ኢላማ በማድረግ በተሰነዘረበት መብረቃዊ የደፈጣ ጥቃት የኦራሉ አሽከርካሪ በአልሞ ተኳሽ መመታቱን ተከትሎ ኦራሉ ተገልብጦ የወደመ ሲሆን ታጣቂዎቹ በሙሉ ረግፈው ቀርተዋል።አስር ጎማ ተሽከርካሪ ላይ የነበሩት በተከፈተባቸው የተኩስ እሩምታ እሳት ዘንቦባቸው አንድ ለጊዜው በውል ያልታወቀ ወታደራዊ ሻለቃ መሪን ጨምሮ በርካቶች ተደምስሰዋል።
በዚህ የደፈጣ ጥቃት 29 የጠላት ሰራዊት ሲደመሰስ 12 ቁስለኛ ሁነዋል።
የደረሰበትን ምት መቋቋም የተሳነው የጠላት ሰራዊት ንፁሃን ነዋሪዎችን ኢላማ በማድረግ ከፍተኛ እንግልት ፈፅሟል።
ከ5 ቀናት በፊት በእርጎየ አካባቢ ተመሳሳይ ጥቃት የሰነዘረችው ጥቅምት 30 ማይካድራ ብርጌድ በቀጠናው ለመተላለፍ በሚሞክር ጠላት ሰራዊት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት በማድረስ ውጤታማ ተልዕኮ እየፈፀመች ይገኛል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ
መስከረም 04/2018 ዓ.ም
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ኢንጅነር ክበር ተመሰገን ማን ነበሩ❓⁉️
🔵ከአባቱ ከአቶ ተመስገን አሰግሀኝ ከእናቱ ክእሙሀይ ሞሲት ምህረቴ ነሀሴ /16/12/1964 ደምበጫ ከተማ ተወለዱ
እድሜቸው ለትምህርት ሲደርስ ከ1-6ኛ ክፍል"ደምበጫ ጁኔር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታተሉ ከ7ኛ-12ኛ በደምበጫ ሙሉ ሳይክል ትምህት ቤት ተከታተሉ (ደምበጫ ሀይስኩል ተከታተሉ)
🔴እንጅነር ክበር 1997 - 2002 ዓ ም በሲቪል እንጅነሪግ በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ የነቁ እና የበቁ በመንፈሳዊ ህይዎታቸው አንቱ የተባሉ በደምበጫ ቅዱሰ ሚካኤል ቤተክርሰቲያን የሰንበት ትምህርት ለትውልዱ አርያ ሁነው ያሰተማሩ የከተማችን ብርቅዬ ልጅ ነበሩ
⚪️የግል ህይወታቸውም ተቋራጭ ግንበኛ ሁነው በግል እየሰሩ እና እያሰሩ ኑረዋል ! ኢንጅነሩ ግፈኛችን ይፀየፋሉ!ግፈኛች እጅግም ይፈሩቸው ነበር እንጅነር አንገታቸውን ደፍተው ሲጓዙ እንጅ ከአንደበታቸው የሚወጣውን እሳት ማንም መመከት አይችልም።ሀሳባቸው ብቻ ተኮሶ ይገላል።
🔵ከ1985 እሰከ 2008 አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ እያውለበለቡ ከፊት ታገኛቸዋለህ ! በዚህ የትግል መሪነታቸው የተነሳ ትክሻቸዉን ከባድ ድብደባ ተፈፅሞባቸው ቆስለዋል ለረጅም ጊዜም ቁሰለኛ ሁነዋል ከደምበጫ አስከ ሞጣ በመሄድ በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ትውልዱን አንቅተዋል። የትግል እንቅስቃሲያቸውም ከወጣቶች ማህበር እስከ ዛሬዉ አቢወት ተሳትፈዋል።
⭕️የጎጃምን ፋኖ በዋናነት በማደራጀት ይታወቃሉ። ከማይረሱኝ ቃሎቻቸው እኔ የምተኩሳት ጥይት የዐምሓራን አቢወት ማፈንዳት አለበት ብለውም ተናግረዋል ቃላቸውም ተከበረ ትውልዱ በሰማቸው ገድል ፈፀመ በሰማቸው ብርጌድ ተመሰረተ በሰማቸው የዐምሓራ ትግል ከፍ አለ ጎመራ አይነኬ አይቀመሴ አደረጃጅት ተወለደ እውነትም ህይዎታቸው እና የተኮሷት ጥይታቸው አቢይዎት ሆነች ለኛ ለቋሚዎች እና በህይወት ላለን ታጋዮች ግን መሰከረም 5 ጨለመችብን
⭕️የደምበጫ ፋኖ ሙሉ የአብይን ጨፍጫፊ ሰራዊት በማፅዳት ላይ የተጠመደ ነበርና ከተማውን አፅድቶ በሰም ሙሉለም በሚባል ጫካ ካንፕ ያደረገው ገዳይ ሰራዊት ጋር መፋለም ተጀመረ
እንጅነርም አብረው ዘለው ምሺግ ገቡ እልህ አሰጨራሺ ውጊያ ተደረገ ሙሉ የጨፍጫፊው ሰራዊት ተደመሰሰ እሬሺን እና ሙሉ ካምቡ በፋኖ እጅ ሆነ ኮለኔል ሰጤ ሚሰቱ ደወለች እጁን ይሰጥ አትግደለብኝ በማለት ለጀግኖች የጦር አዋጊ ፋኖዎች ተደወለ ኮለኔል ሰጤም እጅ ልሰጥ መውጫ መንገድ ሰጡኝ አማራነኝ ወሎዬ ነኝ አትግደሉኝ በማለት ተማፀነ እሩህሩሁ ፋኖም ተኩሰ ቀነሰ ና እጅ ሰጥ ሲባል እጁን አንቀርፎ ከመጣው የሰጤ ጋርድ ጋር ግን ሰጤ አልመጣም
⚪️ሾልኮ በመውጣት ድፍር በተባለ ቦታ የተበተኑ ወታደሮችን ይዞ መሸገ ከፍነተ ሰላም ቢ ኤም እና በታንክ በድሮን ከተማዋን አፈራረሷት ሙሉ ቤተሰብ ከቤት ወጦ ተቀበረ ካህናቶች አሰከሬናቸው ተለቅሞ ተቀበረ ደምበጫ በንፁሀን ደም ታጠበች እንጅነሩም የዛን ቀን ነበር የተሰውት ይህ እንጅነር ክበር በደማቸው የፃፉት የአምራ ትግል ነው። ብዙ ጀግኖችም አብረው ተሰው
⭕️ትግሉ ግን ጎመራ እንደገና እሳት ሆነ የሚያቆማቸው ምድራዊ ሀይል ቀርቶ በድሮንና በመድፍ ቢዋጋም የደምበጫን ፋኖ አንገት ማሰደፋት አልቻለም። እንጅነር ታሪከኛ ናቸው እንጅነር የዚህ ትግል እንደሻማ ቀልጠው አደራጅተው ትውልዱን አንቅተው እሳት የላሱ ልጆቻቸውን ተክተው የተሰው እንቁ ሰው ናቸው
ትውልዱም ያመሰግናቸዋል።
ታሪክም ይዘክራቸዋል።
እኛም ትግላቸውን እናሰቀጥላለን ።
መስከረም 5/2016 ዓ/ም ደምበጫ ክፉ ቀን!
ተበጀ ማተቤ ነኝ (ደመላሺ) የህልሙን የልቡን ደራሺ የጀግኖችን አደራ ወራሺ
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አማራ ዛሬም እየተጨቆነ ነው፤ አማራ ኢትዮጵያን በማለቱ ነው ይህ ሁሉ በደል የደረሰበት፣'' አቶ አብርሃም አለኸኝ'' ይናገራሉ።
ይቅርታ መንጋቱ አይቀርም'' የአማራ ህዝብ ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ እና አለአግባብ በግፍ የተነጠቁበት ዕድሎቹ ብዙ ናቸው፤ የአማራ ህዝብ ተበድሏል መካስ አለበትም ብለዋል!!
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ያልተሳካለት የብልፅግናው ደህንነት ገመናው ሲጋለጥ
(መስከረም 04/01/2018 ዓ.ም፣ ነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት)
የዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 5ኛ ክፍለ ጦር የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ የብልፅግና መንግስት በተለያየ መንገድ የላከውን ደህንነት ነበልባሎቹ የገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ልጆች ቦታ ባለመስጠት ተልኮውን ሳይፈፅም ወደ መጣበት ተመልሷል።
ያረጋል አያና ይባላል ትውልድ ቦታው ምዕራብ ጎጃም ቋሪት ወረዳ ፈንገጣ ጨጎዴ ቀበሌ ሲሆን አማራ በደሉ ሲበዛ ከሰልፍ ወደ ሰይፍ በይፋ ትግሉን ከጀመረበት ከሀምሌ 25/2015 ዓ.ም ጀምሮ የመንግስት ሰራተኛው ስራውን በመተው፣ነጋዴው የንግድ ቦታውን በመዝጋት፣ ከአ/አደር እስከ ሙሁራን ከህፃናት እስከ አዛውንት በአጠቃላይ የአማራን መበደል የሚያውቁ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የድርሻቸውን እየተወጡ ያሉ ቢሆንም ይህ ከላይ በስም የተጠቀሰው ግለሰብ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ከፌደራል መረጃ ደህንነት ነው የመጣሁ እኔም ከወንድሞቼ ጋር አብሬ ልታገል ብሎ የገረመው ወንዳውክ ብርጌድን በወቅቱ ይጠይቃል፤ ብርጌዱም አቶ ያረጋል አያናን በአይነ ቁራኛ ሲከታል ከዛሬ ነገ አባል ትሆናለህ በማለት ቁጥጥር እና ክትትል ሲደረገበት የቆየ ሲሆን ቁጥጥሩና ክትትሉ ሲበዛበት እውነታው ሊታወቅ ሲል ያሰበው ሳይሳካለት ጠፍቶ ወደ ነበረበት የተላላኪነት ባንዳነቱ ስራ ገብቷል።
የዚህ ግለሰብ ያቀዳቸው ስራዎችና ሳይሳኩ መክነው የቀሩ ጉዳዮች:-
1. ራሱን ለመታመን ራሱ ጽፎ አቶ ያረጋል ይባላል የመረጃና ደህንነት ባለሙያ የነበረ ሲሆን የመንግስትን መረጃ ይዞ የጠፋ ስለሆነ በተገኘበት አጋጣሚ እንዲገደል ብሉ በማይታወቅ ሲም ራሱ ፅፎ ወደ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ አመራሮችና አባለት በስልክ መልዕክት እንዲደርስ በማድረግ ራሱን ታማኝና በመንግስት ተፈላጊ እንደሆነ ለማሳወቅ ቢሞክረም የበለጠ ጥርጣሬና ክትትል እንዲደረግበት በመሆኑ ሳይሳካለት የቀረ፣
2. እኔ ለትግል ነው የመጣሁ መስራት ያለብኝም በሙያየ በደህንነት ነው ብሎ በተለያየ ጊዜ ብርጌዱን ጠይቆ ሙከራ ቢያደርግም ሳይሳካለት የቀረ፣
3. ብር አዳማ አካባቢ ከብት ሲጠብቁና ተሰባስበው ሲጫወቱ የነበሩ 9ኝ ህፃናት በድሮን ሲጨፈጨፉ ወንድማማቾችን የገረመው ወንዳውክና የአንሙት ያዛቸውን ብርጌድን እርስበርስ ለማጋደል የአንሙት ያዛቸው ብርጌድ አመራሮች ናቸው ድሮኑን ያስጣሉት ቢልም ሳይሳካለት የቀረ፣
4. ቤተ ክርስቲያንን ከፋኖ ለመነጠል በፈንገጣ ጨጎዴ ቀበሌ ውስጥ የምትገኘዋን የጨጎዴ ሀና ቤተ ክርስቲያን የቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናቶችን የቤተ ክርስቲያኑን ነዋየ መፅሀፍት ሰርቀዋል ብሉ ለማሳሰር ቢሞክርም ብርጌዱ አጣርቶ በነፃ የለቀቃቸውና ግለሰቡ ያቀረበውን መረጃ ውድቅ በማድረጉ ሳይሳካለት የቀረ፣
5.ባለሀብቱን ከፋኖ ለመነጠልና ባለሀብቶች እንዲማረርሩ ለማድረግ ከአዲስ አበባ ወደ ብር አዳማ ከተማ እህል ለመጫን የመጣን ኦባማ መኪና ለፋኖ 300 ሺህ ብር ድጋፍ ታደርጋለህ ብሎ ቢጠይቅም ሳይሳካለት የቀረ፣ በአጠቃለይ የአብይ አህመድ ተላላኪ የላከው ቅጥረኛ አንተ አማራ ስለሆንህ ብሎም የቋሪት ተወላጅ በመሆንህ እንደሳት የሚፈሩት የገረመው ወንዳውክ ብርጌድን ለማፍረስ ከሌላው አንተ ትሻላለህ በማለት ከአረመኔው የብልፅግና ስርዓት ተልዕኮ ይዞ ቢመጣም ሳይሳካለት ወደ መጣበት አንድም ተግባር ሳይፈፅም በብርጌዱ አመራሮች በኩል የስርዓቱ መረጃና ደህንነት ሆኖ ከመንግስት ጋር ሲሰራ የነበረውን በማጣራት ላይ እንዳሉ ወደ መጣበት ተመልሷል።
የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ ታጋዮችና ደጋፊዎች እየፈራርሰና የፋኖን በትር መቋቋም ያቀተው የብልፅግና ስርዓት በአማራ ትግል ስም በበርካታ ሆድ አደር የአማራ ባንዳዎች ትግሉን ለመጥለፍ ሙከራ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ከተለያየ የመንግስት ተቋማትም ሆነ ድርጅት የሚመጡ ግለሰቦችን ጥንቃቄ በተሞላበት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ይገባችኋል ሲል የገረመው ወንዳወክ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ገልጿል።ይህ የአማራ ህዝብ አብዮት ሽንጉግ የሆነ ግለሰብ የሚዲያ ሽፋን ለማግኘት ሲል የግዙፉ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክፍለ ጦር የመረጃና ደህንነት አመራር ነኝ የሚል የሀሰት ወሬ ሲነዛ የግብር አባቱ ውሸት የማይሰለቸው የአብይ ግርፎች ሲያራግቡት አይተናል። ግዙፉ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክፍለ ጦር እንደሳት በሚፋጁ ብርጌዶቹ አማካኝነት የስርዓቱን ሰርጎ ገብ ሌቦችና ወሬ ለቃሚ ሽንጉጎችን እያራገፋቸው ይገኛል።
፲/አ ኢ/ር ዘመኑ አማረ
የ5ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ሓላፊ
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አማራ የሆነ ሁሉ በጨለማ ውስጥ ነው ። በየትኛውም የፖለቲካ አሰላልፍ ውስጥ ወይም በየትኛውም ሀይማኖት አማኝ ብንሆን መትረፍ አይቻልም ።
ብልፅግና ስለሆንህ ፣ ኢዜማ ስለሆንህ ፣እናት ስለሆንህ ፣አብይ እግር ስር ስለሆንህ፣ ብርሃኑ ነጋ አጠገብ ስለሆንህ ፣ ክርስቲያን ስለሆንህ ፣ሙስሊም ስለሆንህ ወይም ፕሮቴስታንት ስለሆንህ አትድንም ።አማራ የሆነ ሁሉ ጨለማ ውስጥ ነው። ይፈናቀላል፣ ይሰደዳል፣ ሀብት ንብረቱ ይቃጠላል ፣ይገደላል፣ ዘሩ ይፀዳል። ለዚህነው የህልውና ትግል እየታገልን ያለነው።
በአማራነትህ ብቻ ታገል ያኔ በደንብ ይገጋል።
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
🔥#የሀይል_ማፍረሱ_ተጠናክሮ_ቀጥሏል‼️
በአፋብኃ ምዕ/ አ/ ቀ/ ቴ/ዕ 2ተኛ/ተፈራ ዳምጤ/ ክፍለ ጦር የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድን አትኩት ቢተውና ከ303ኛ ኮር፣1ኛ ሻለቃ፣1ኛ ሻምበል ፲ አለቃ አስራት ማርቆስ የተባሉ አንድ ሚሊሻና አንድ የመከላከያ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል።
በሰላም ፋኖን የተቀላቀሉት ሁለቱ የመንግስት ሀይሎች በተለይ የሚሊሻ አባላትን በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች አታለው ካስገቡ በኋላ የፋኖ መረጃ ናችሁ እያሉና ሌሎችንም ተልካሻ ምክንያቶች በመፈለግ ከፍተኛ የሆነ ድብደባና ጭቆና እንደሚፈፅሙባቸው ገልፀዋል።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
©ፋኖ ይላቅ ዳኛው
በአፋብኃ ምዕ/አ/ቀ/ቴ/ዕ 2ተኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት
መስከረም 04/2018 ዓ.ም
04/ዐ1/2018 ዓ.ም
ሰበር ወለጋ‼
፨፨፨፨፨፨
ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ አሹ ኩሳየ ቀበሌ በአገዛዙ ተጠርንፈው የነበሩ ሚኒሾች ካምፕ ላይ ለሊቱን በተፈጸመ ጥቃት 15የኦሮሞና የአማራ ሚኒሾች ሲገደሉ 6ቱ መማረካቸውን የአይን እማኞች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ስዓት ለሊቱን ሀሮ አዲስ አለም ከተማ መከላከያና ማኒሻ ካምፕ ላይ እንዲሁም አስተዳደሩ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ለሊቱን በከባባድ መሳርያ የታገዘ ጦርነት ሲካሄድ ማደሩን የከተማዋ ኗሪዎች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል።
መስከረም 04/2018ዓ.ም
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
❗አይበገሬው እና የፅናት ተምሳሌቱ ወንድማችን ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ በዚያው የፋሽስቱ የግዞት እስር ላይ ሆኖ ምስጋና አቅርቧል❗
በእያላችሁበት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ❗
ቃላችሁን አክብራችሁ ከንጹሃን ወንድም እህቶቻችን ጎን ስለቆማችሁ በሕይወታችሁ ሁሉ እግዝአብሔር ይቁምላችሁ!
አማራነት ፣ ሰብአዊነት ተሰምቷችሁ ለራሳችሁ የገባችሁትን ቃል በመጠበቅ ከአደራ ልጆቼ ጎን ስለሆናችሁ እግዚአብሔር አምላካችን ቃል ኪዳኑን ይጠብቅላችሁ።
አዲስ ዓመት ሲመጣ በበዓል አልከፋቸውም ፤ በእናንተ ቃል አክባሪ በጎ ፈቃደኛ ወገኖቼ ሁለንተናዊ ድጋፍ በበዓሉ ሳይከፉ ደስ ብሏቸው ስለዋሉ ለእኔ ደስታው እጥፍ ድርብ ነው።
ስለ እውነት እነዚህ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ ተወልደው ካደጉበት አካባቢ በታጠቁ አካላት መሀል ከተማ ላይ በመኖሪያ ቤታቸው መስከረም 7/2014 ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ በዛች ክፉ ቀን ምሽት የሚወዷቸውን ወላጆቻቸውን በአሰቃቂ ግድያ ያጡ አራት ህጻናት ከእኔ መታሰር ጋር ተያይዞ እንዳይከፉ ፣ እንዳይራቡ እና እንዳይጠሙ ፣ የጀመሩት ትምህርትም እንዳይቋረጥ ከጎናቸው እና ከጎኔም ስለሆናችሁ ከፍ ያለ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
እነሆ በእናንተ ቅን አሳቢ እና ተቆርቋሪ ወገኖች ትብብር አማራነት እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ወላጆቻቸውን በግድያ ላጡና ከተቃጣባቸው ጥቃት የተረፉ የአደራ ልጆቼ በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ሁሉም አልፈዋል ፤ አንዳንዶች ደረጃ ይዘው እስከመሸለምም ደርሰዋል፤ አሁንም በመልካም የስነ ልቦና ዝግጅት ላይ ይገኛሉ ፤ ይህም በጣም መልካም ነገር ነው።
በሳይንሳዊ ብቻ ሳይሆን በሀይማኖታዊ- መመንፈሳዊ አስተምህሮ የተቃኘ ተስፋ ሰጭ እና ግብረ ገብነት ያለው ሕይወትን በመምራት ላይ ይገኛሉ።
በእኔ ላይ ልክ እንደ አንድ አማራ በማንነቴ እየተፈፀመ ያለው ሁለንተናዊ ግፍ አሳስቧችሁ ከጎኔ ስለሆናችሁም ልባዊ ምስጋናዬ በእያላችሁበት ይድረሳችሁ ብያለሁ!
በተለይም ከሁለት ዓመት በላይ በታወጀውና እየተካሄደ ባለው መንግስታዊ ጦርነት ፣ ሽብር እና ውንብድና በምድር እና በአየር ኃይል (በድሮንና በከባድ መሳሪያ) ጭምር እየተጠቃችሁ ንጹሃን ቤተሰቦቻችሁን ለተነጠቃችሁ ፣ በስደት ፣ በእስር እና በሰው ሰራሽ ርሃብ እየተሰቃያችሁ ላላችሁ ፣ ትግሉ የሕልውና ነው በሚል የተቀማነውን ሀገር እና መንግስት እናስመልሳለን በማለት ዱር ቤቴ ብላችሁ ውድ ዋጋ እየከፈላችሁ ለምትገኙ አማራዎች (ፋኖዎች) ፣ በውስጥም ሆነ በውጭ ሆናችሁ የንጽሃንን የደም እንባ ለማበስ ደፋ ቀና የምትሉ ተቆርቋሪ ወገኖች በሙሉ የያዝነው አዲስ ዓመት አንድ በመሆን ግፍ እና ግፈኞችን የምታሸንፉበት ዘመን ያድርግላችሁ ፤ ያድርግልን!
ነጻነትና ክብራችን የሚመለሰው
በጥረታችን ልክ ነው!
ዓባይ ዘውዱ
የማንነት ፣ የሕሊና እና የፖለቲካ እስረኛ
መስከረም 04/2018
ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
በእስር ላይ የሚገኙት ክርስቲያን ታደለና ሌሎች ፖለቲከኞች የረሃብ አድማ መጀመራቸው ተነገረ
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት ክርስቲያን ታደለና ሌሎች ፖለቲከኞች እንዲሁም ጋዜጠኞች የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከአዲስ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ በአድማ ላይ የሚገኙት እስረኞች “ለሕይወታቸው እጅጉን አስጊ” በመሆኑ አጣዳፊ እርምጃ በመውሰድ ሕይወታቸውን እንታደግ” ሲል ኢሕአፓ ጥሪውን አቅርቧል።
ተቃዋሚ ፓርቲው ለኢትዮቲዩብ በላከው መግለጫ በማረሚያ ቤቱ የሚገኙት እስረኞች “በደልና ግፍ እየደረሰበት ላለው የአማራና ለቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መብት ነፃነትና ጥቅሞች ከመቆም ውጭ ይህ ነው የሚባል ወንጀል ሳይሰሩ መታሰራቸውን" ገልጿል። እስረኞቹ “ፍትሕ እንዳያገኙ” መደረጋቸውንም ፓርቲው በመግለጫው አስፍሯል።
ኢህአፓ “ወንጀል ሳይሰሩ” በእስር ላይ ይገኛሉ ካላቸው ግለሰቦች መካከል፤የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ አቶ ታዬ ደንደአ፣ ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ይገኙበታል። ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው፣መምህርት መስከረም አበራ፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም፣ ዶ/ር ጫኔ ከበደ፣ መሪጌታ በላይ አዳሙ እና ዶ/ር ካሳ ተሻገር ፓርቲው የጠቀሳቸው ግለሰቦች ናቸው።
ከእስረኞቹ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በሕመም ላይ የቆዩ “በቂና አስፈላጊውን የሕክምና ዕርዳታ የተከለከሉ” መኖራቸውንም ተቃዋሚ ፓርቲው አስታውቋል። በአማራ ክልል እየተካሔደ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለው ታህሳስ 03/2017 ዓ.ም. የአንጀት ድርቀት አጋጥሟቸው በመቅረዝ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ሕክምና ማድረጋቸው አይዘነጋም።
