ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 664
Suscriptores
+2024 horas
+3787 días
+1 08530 días
Archivo de publicaciones
64ኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድራቸው አካባቢዎች እነማይ እና ሸበል በረንታ ወረዳ ህዝባዊ ውይይቶች እንደቀጠሉ ነው።
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፈለ ጦር ስር የሚገኙት የእነማይ እና ሸበል በረንታ ወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች በእነማይ ወረዳ ማህበረሰላም ቀቸር ቀበሌ እና ሸበል በረንታ በመራፍ ይጨማ ቀበሌ የካቲት 17/2018 ዓ.ም ህዝባዊ ውይይት ተካሄዶል። በውይይቱ መድርኩ:-
🕳 የፋይናስ እና ሀብት አሰባሰብ በተመለከተ
🕳 የወል መሬትን ወረራን መከላከል በተመለከተ
🕳 የፍትህ አሰጣጥን በተመለከተ
🕳 የመልካም አስተዳደር በተመለከተ
🕳 የቀበሌ ፀጥታ በተመለከተ ሰፊ ውይይት ተካሂዶል።
በውይይት መድርኩ የተገኙት የማህበረሰብ ክፍል የእነማይ እና የሸበል በረንታ ወረዳ የጊ/መንግስት አስዳደር አመራሮች ጎን በመሆን የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ የሚገኘውን የአብይ አህመድ አገዛዝ ነቅሎ ለመጣልና ለመቅበር የትኛውንም አይነት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል። በመጨረሻም በስብሰባ መድርኩ የተገኘው የማህበረሰብ ክፍል ላቀረበው ጥያቄ የወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች ሰፋ ያለ ማብራሪያ በመስጠት የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግሉ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ግንዛቤ ሰጥተዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
የቡሬ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት ከ5 ቀበሌወች ጋር ውይይት ተካሔደ
➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
የካቲት 15/2018ዓ.ም
ከዓለም ካርታ ሊያጠፋን የመጣን ጠላት በልኩ ለህዝባችን በየቀኑ ማስረዳት የእኛ የአዲሱ ትውልድ ስራ ነው።
በቡሬ ወረዳ 77ተኛ ክ/ጦር ውስጥ የሚገኝ 5 ቀበሌዎች ( ከጅብ ገደል ቀበሌ ከአግኒ ፈረዳ ከወህኒ ዱርቤቴ ከአርቢሲ መንፈሳዊትና ከወይንማ አምባየ )ቀበሌዎች ጋር የተሳካ ዉይይት ተደረገ
ከጅምሩ የአማራ ትግል ሲጀመር በህዝባዊ እንቢተኝነት የጀመረ የተፈጥሮ ጀግንነት ያለው ማህበረሰብ የሚገኝበት 5ቱን ቀበሌዎች ፍፁማዊ አማራዊ አደረጃጀት ከህዝባዊ ኃይል እስከ አ.ፋ.ጎ እናም እስከ አ.ፋ.ብ.ን የትግል ደረጃ ድረስ የማይዋልል አደረጃጀት ያለበት ቀጠና ነው።
ሆኖም በነበረው የትግል ግለትና አሁናዊውን የትግል ደረጃ ለ5 የቀበሌ ማህበረሰብ ፍፁም ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል።
በስብሰባው ትግልን የወከለና ህዝብን ያማከለ የአካሔድና የስርዓት አጀንዳዎችን አንስተን በጋራ መግባባት አብሮነትን ወንድማማችነትን አሳይተናል።
በስብሰባው የወረዳው ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች በጋራ ሁነው የቀጠናዉን የጮቄነት ግርማ አይደፈሬነት በትናንት ማንነቱ እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል።
ህዝባችንም በዉይይቱ መልካም ሀሳቡን የገለፀበትና ትግላችንን ለመደገፍ በቁርጠኝነት የተነሳ መሆኑንም ከተነሡ ሀሳቦች መረዳት ችለናል።
እኛም ህዝባችን ቀይ መስመራችን ነዉ የምንለዉ በምክንያት ነዉ።
መረጃው የቡሬ ወ/ጊ/መ/ሚዲያ ክፍል ኃላፊ ነው
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር ህ/ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 17/2018ዓ.ም
ወጣቷ ፖለቲከኛ እና የኢህአፓ ዋና ፀሀፊ ምስጢረ ስላሴ ታምራት።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ብዙም ታይቶ በማይታወቅ ድፍረት፤ በቀጥታ የምርጫ ቅስቀሳ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ የኢህአፓን ጠንካራ የተቃውሞ ሀሳብ በማንጸባረቅ ታሪክ የጻፈችውን ሚስጥረስላሴ ታምራትን ዛሬ እናስተዋውቃችሁ። የኢህአፓ ስራ አስኪያጅ የሆነችው ይህች ደፋር ፖለቲከኛ፤ ትላንት በተደረገ የፓርቲዎች ክርክር ላይ፤ በወቅቱ በመድረኩ ላይ የነበሩትን የብልጽግና ፓርቲ ተወካዮችን ባላሰቡት እና ባልጠበቁት ጠንካራ ሙግት በማስደንገጥ ትልቅ አሻራ ጥሎ ያለፈ ክርክር አድርጋለች።
ይህ በቴሌቪዥን መስኮት ያሳየችው ቆራጥነት እና የሀሳብ ልዕልና አሁን ደግሞ ይበልጥ ወደ ማህበራዊ ሚዲያው ተሸጋግሯል። ሚስጥረስላሴ በአሁኑ ሰዓት በቲክቶክ መድረክ ላይ ከፍተኛ ትኩረት እየሳበች እና የብዙዎችን አድናቆት እያተረፈች ትገኛለች። ወጣቱ ትውልድ የእሷን ንግግሮች እና የፖለቲካ እይታዎች በስፋት እያጋራ ሲሆን፤ ድፍረቷ እና ለምታምንበት አቋም ያላት ጽናት በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ለበርካቶች መነጋገሪያ ሆኗል።
እናንተስ የዚህችን ጠንካራ ፖለቲከኛ የቴሌቪዥን ላይ ታሪካዊ ክርክር እንዴት አያችሁት?
የአቢይ አሕመድ ኮርቻ ጥላኹን ደጀኔ ከደብረ ታቦር ሕዝብ ምን ገጠመው?
ሰውነታቸው ውሸት ከተባለ ንጥረ ነገር የተሰሩት ብልጽግናዎች በሁሉም የሥራ ዘርፍ ያሉ የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎችን ሰብሥበው ደብረ ታቦር ከተማ ሥለነበረው ውጊያና ውጤቱ በጥላኹን ደጀኔ መድረክ መሪነት ለሕዝቡ እንደሚከተለው ተናገረ፦
✅የደብረ ታቦር ተቋማትና የከተማ አሥተዳደር ሰራተኞች ቤት የወደመው በፋኖዎች ነው።
✅የሻዕቢያ ወታደሮችን አሥከሬን ከነሥማቸው አግኝተናል።
✅የሕወሓትን ወታደሮች ማርከናል።
ከሥብሠባው ተሳታፊዎች ከተሰጡ ምላሾች በጥቂቱ፦
✅ አቶ ጥላኹን ደጀኔ ጆሮህን አቁመህ አድምጠን። ከዚህ እንደወጣን ልትገድሉን ትችላላችኹ። ነገር ግን በዓይናችን ያዬነውን ለመመሥከር እገደዳለን። ውጊያው ከመጀመሩ በፊት አዳሩን ሙሉ ከደብረ ሲና እሥከ ሥላሴ፣ ከኪዳነ ምሕረት እሥከ ኮሌጅ፣ ከሚካኤል እሥከ መንፈሥ፣ ከአሣምነው ካምፕ እሥከ መሎ፣ ከኪቢአድ እሥከ 70 ደረጃ፣ ከጎንደር በር እሥከ መለሥተኛ፣ ከመነሐሪያ እሥከ ቴዎድሮሥ አደባባይ እና ሌሎች ቦታዎች በፋኖ ተይዘው አድረዋል። አንድም ጥፋት አልተፈጸመም። ነገር ግን ውጊያው እንደተጀመረ የተቃጠሉ ቤቶችን ፋኖዎች እሣቱን ለማጥፋት ሲረባረቡ በዓይናችን ተመልክተናል። እነሱ ቢያቃጥሉት ኑሮ እኛ እሣቱን ሥናጠፋ ያሥቆሙንና ርምጃ ይወስዱብን ነበር፣ ራሳቸው አቃጥለውስ ለምን ለማጥፋት ሞከሩ? ይሄ የፈጠራ ክሳችኹ ነው። ሽንፈታችሁን ላለመቀበል ያደረጋችሁት ሴራ ነው። በውንብድናና በዘረፋ የተሰማሩ የሥርዓታችኹ የብልጽግና ካድሬዎች ነገም ፋኖ ሲገባ የትናንቱን አውዳሚ ድርጊታቸውን እንደሚፈጽሙ እናውቃለን ብሏቸዋል።
✅በመጀመሪያ ደረጃ የመንግሥት ተቋማት የወደሙት በከፍተኛ የሙሥና ወንጀል በተዘፈቁ በሥርዓቱ አገልጋዮች መሆኑ እየታወቀ ሽንፈትን ላለመቀበል የተደረገ ድግሥ ነው።
✅በ03 ተሽከርካሪ ተጭኖ የገባውን መድኃኒት ተደራጅተው የሸጡ የሕክምና ባለሞያዎች መሆናቸውን(ጥበቃዎቹን አካትቶ) አበክረው ተናግረዋል።
✅በቂም በቀል ካድሬዎች ራሳችኹ አጋጣሚውን ተጠቅማችኹ የጓደኞቻችኹን ቤቶች በእሣት አጋይታችኋል።
✅የገጠሟችኹ እዚሁ የምናውቃቸው ልጆች ሆነው እያለ ሶስተኛ ወገን መፈለጋችኹ ምን ማለት ነው? ከጁንታው ጋር በነበረው ውጊያም ግብጻዊ ተገኘ፣ ሱዳናዊ ተገኘ፣ የመኒ ተገኘ...ሥትሉ የነበረው ሁሉ ውሸትና ፈጠራ እንደነበር አሁን አረጋግጣችኹልናል ሲሉ አሥረግጠው ተናግረዋል። ነገር ግን ያቀረባችሁት ፈጠራ ነው ውሸት ነው፤ በሬ ወለደ ነው ሲሉ አሥረግጠው መራራ ዕውነታን ግተዋቸዋል።
የዓምሐራን ደም የጠጣውና እየጠጣ ያለው፣ በሙሥና የተዘፈቀውን ካድሬ የሚመራው ሙሰኛ ካድሬ፣ ሕዝቡን በጎጥ የከፋፈለው፣ ወጣኹበት ለሚለው ጎጥ ተቆረቆርኩ የሚለው፣ የወጣበትን አካባቢ የካድሬ መፈልፈያ ፋብሪካ ያደረገው፣ የሕዝብን ጥቅም አሳልፎ የሚሸጠው፣ የመንግሥት ሰራተኞች እርሥ በርሥ በጥርጣሬ እንዲተያዩ ያደረገውና በጥቅሉ ለኦሕዴድ ብልጽግና ታማኝነቱን በግብር የሚገልጠው ከሃዲውና የአካባቢው ማሕበረሰብ ቁጥር አንድ ካንሰር ጠላታቸው ኦቦ ''ጥላኹን ደጀኔ'' ነው።
ከሕዝብ የተደበቀ ምሥጢር የለም፤ ሕዝብን ያሸነፈ አገዛዝ የለም።
ኃቅ-ዓለው ፀጋ አለባቸው
+1
ጀብደኛው ሲሳይ ታደሰ ዘውዴ 04 ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቅሏል።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
የ25 ክ/ጦር ሞርተር ምድብተኛ ፐርሶኔል ሀላፊ የነበረ ሲሆን ከዚህ በፊት በልዪ ሀይል ሚኒልክ ክፍለጦር ውስጥ የነበረ በአድማ ብተና አሁን ደግሞ በመከላከያ ተቋም ውስጥ የሞርተር ምድብተኛ ፐርሶኔል ሀላፊ የነበረ ሲሆን በአማራ ወገኖቻችን ላይ እየፈፀሙት ያለው ግፍ ያንገበገበው 3 አባላትን እርምጃ በመውሰድ 04 ክላሽ በመያዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅሏል።
አዲስትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የጅጋ ከተማ ከንቲባ በአጃቢው ተሸኝቷል‼️
ሕዝብ ሲዘርፍ፣ ሲያሰቃይ፣ ሲያንገላታ፣ ሲረሽን የነበረው ጥቁር አማራ የጅጋ ከተማ ከንቲባ በትናንትና ዕለት የካቲት 16/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በቅርብ አጃቢው ተገድሏል፡፡
ሲሰርቅ፣ንጹሃንን ሲያሰቃይ እና ሲረሽን ሲታዘብ የነበረው የቅርብ አጃቢው #ግምባሩን ብሎ ሲሸኘው፣ በሀሰት መስካሪውን ጨምሮ መረጃ እና ደህንነቱንም በክፉኛ አቁስሎት በሆስፒታ ይሞታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
የዐማራ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነው አጃቢው ፀረ ዐማራዎችን አስወግዶ ወደ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ከእነ ሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል፡፡የ77ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች እና አባሎችም በደማቅ አቀበባብል ተቀብለውታል፡፡
✅ሟችም ከመሞቱ በፊት በራሱ ወገን ላይ ሰቆቃ ሲጭን፣ፋኖ የለም እያለ በእዬ መድረኩ ሲፎክር እና የዐማራን ታሪክ ሲሰርዝ እና ሲደልዝ መቆየቱ ይታወቃል፡፡በመጨረሻም ወደ አምላኩ ተሸኝቷል፡፡
✅በፍኖተ ሰላም፣በቡሬ፣በቁጭ እና እንዲሁም በ77ኛ ክፍለ ጦር የምትገኙ ጥቁር አማራዎች ''ይዘገያል እንጅ አህያ የጅብ ናት'' እንደሚባለው የጅጋ ከተማ ከንቲባ እጣ ፋንታ እንዳይገጥማችሁ በአስቸኳይ ለ77ኛ ክፍለ ጦር ፋኖዎች እጅ መስጠት አለባችሁ ስንል ወንድማዊ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
የዐማራ ባንዳ አለበት እዳ💪💪
©አፋብን ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 17/06/2018 ዓ.ም
17/ዐ6/2018 ዓ.ም
በመካነሰላም ግንባር ሙደለላ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ በተደረገ ውጊያ ከ20 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ሲደመሰሱ 11 ክላሽንኮብ መሣሪያ ተማረከ!
ወደ ጠላት ካምፕ ጥሶ በመግባት እርምጃ የወሰደው የፋኖ ኃይል ሙትና ቁስለኛ ካደረጋቸው የአገዛዙ ወታደሮችና ከማረካቸው መሣሪያዎች በተጨማሪ ቁልፍ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸው የጠላት ይዞታዎችን በቁጥጥሩ ስር ማስገባቱን የመረብ ሚዲያ የቀጠናው ዘጋቢ ለማረጋገጥ ችሏል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ ከነሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ለፋኖ የሰጡ የአገዙ ወታደሮች የተሀድሶ ስልጠና እየተሰጣቸው ሲሆን፡ የምህረት አዋጁን ባልተቀበሉ ወታደሮች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ሰበር ዜና ጅጋ ከተማ!!
የአገዛዙ ቀኝ እጅ የነበረው የጅጋ ከተማ ከንቲባ በ77ኛ ክፍለ ጦር አነፍናፊ አዳኞች ተሸኝቷል የቆሰሉ ብዙ አመራሮችም አሉ ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንቀርባለን፡፡
👉የአማራ ባንዳ አለበት እጅ💪💪
አፋብን ምዕራብ ዐማራ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 16/2/2018 ዓ.ም
ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር እና ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር በጥምረት ጠላት ላይ ድል ተቀዳጁ::
ዛሬ የካቲት 16/2018 ዓ/ም በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ስሪንቃ ቀበሌ መነሻውን ወልድያ ከተማ ያደረገ ጠላት ከሌሊቱ 8:00 ጀምሮ ፋኖ ወዳለበት ቀጠና ማጥቃት ሞክሮ ከፍተኛ ካሳራ ደርሶበት ተመልሷል።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር እንዲሁም ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በተጠቀሰው ቀን ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ወደመጣበት ወልድያ ከተማ መልሰውታል።
በተጋድሎው ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ እየተደረገ እስከ ማታ 11:00 የዋለ ሲሆን በውጊያው ከባድ ኪሳራ ያስተናገደው ጠላት ከባድ መሳሪያ በመወርወር በንብረትና በሰው ሂወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ሞርተር በማስወንጨፍ የማህበረሰቡን ደን ከማቃጠሉም በተጨማሪ ከግለሰብ ቤት ላይ በመወርወር አንድ የቤተሰብ አባል ሙሉ ከባድ ቁስለኛ አድርጎ የተለመደውን ህዝብ የመጨፍጨፍ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 16/2018 ዓ.ም
+2
ባህርዳር ሆይ ተዘጋጅ ልጆችሽ እየመጡ ነው!!!
ባህርዳርን ሲያስጨንቅ የነበረው 22ኛ ክፍለ ጦር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተቀዛቅዞ መቆየቱ ይታወቃል። አሁን ድሮ አስፈሪ ወደነበረበት አቋሙ እየመጣ ነው።💪💪💪
እናመሰግናለን ዝርዝሩን ከሚዳ ሁነን እንመለሳለን በቅርቡ ይወዳጁን!!
88ኛ ክ/ጦር የአርሶ አደርን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ ወደ ገጠር ቀበሌዎች በተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሠራዊት ላይ ከባድ እርምጃ በመውሰድ በርካቶችን ደመሰሰ!
ትናንት የካቲት 15/2018 ዓ.ም መነሻውን ከወምበርማ ወረዳ ሽንዲ ከተማ ያደረገው የአብይ አህመድ አገዛዝ ጨፍጫፊ እና ዘራፊ ሠራዊት በቡራፈር ቀበሌ እና በዴንድ ቀበሌ አቅጣጫ ወደ ኸረጥ ቀበሌ ተንቀሳቅሷል።
የጠላት እንቅስቃሴ መረጃ የደረሳቸው በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ስር የ88ኛ ክ/ጦር የስቦ መምታና የቆረጣ ታክቲክ በመጠቀም በወሰዱት እርምጃ በርካታ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ችለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የክ/ጦሩ 1ኛ ሻለቃ ሽንዲ የመሸገው ጠላት ላይ ጥቃት በመክፈት ተወርዋሪ ንስሮቿን ደግሞ መሀል ከተማ አስርጋ በማስገባት ጥቃት የፈፀመች ሲሆን ቀንደኛ የሚሊሻ መሪ የሆነውን እንዳልካቸው መኮነን የተባለ ባንዳን ከእነ ግብረ አበሮቹ በደምሰስ 03 ክላሸንኮቭ መማረክ ተችሏል።
በተያያዘ አማራን በቀጥታ ከመግደል ባለፈ ተቋማቱን በየ ደረሰበት ሁሉ የሚያወድመው የአገዛዙ ሠራዊት በአከባቢው የኸረጥ ቀበሌ ማህበረሰብ ለማህበራዊ ፍትህ፣ ለመልካም አስተዳድር እና መሰል ማህበራዊ ግልጋሎት የሚያካሂድበትን አስተዳድር ፅ/ቤት እንዲሁም ለማህበረሰቡ የህክምና አገልግሎት የሚያገኝበት አነስተኛ ክሊኒክን የህክምና ቁሳቁሶቹን በመዝረፍ ሙሉ በሙሉ በእሳት አውድሞታል።
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ከፍለ ጦር አስር አለቃ ኤፍሪም አጥናፋ ሻለቃ ልዩ ኮማንዶ ምርቃት ላይ በመገኘት ይህን መልዕክት አስተላልፈናል ።
የተከበራችሁ የአፋብን የቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች፤ የተከበራችሁ የቴዎድሮስ ዕዝ 105 ኮር ከፍተኛ አመራሮች፣የተከበራችሁ የቴዎድሮሰ ዕዝ 105 ኮር የ44 ከፍለ ጦር አመራሮቸ፣የተከበራቸሁ የጊዮን ሻለቃ አመራሮች እና የኤፍሬም አጥናፋ ሻለቃ አመራርና አባላት
የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ኮማንድ እጩ የሰራዊት አባላት፣
የተከበራችሁ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ክቡራት እና ክቡራን
በቅድሚያ አድካሚ የሆነውን ወታደራዊ ስልጠና በብቃት በመውሰድ እና የታለፈባቸውን ውጣ ውረዶች በማለፍ ለዚህ የምረቃ እለት የበቃችሁ እጩ የኮማንዶ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
ከሁሉ አስቀድሜ በአጭር ጊዜ ተፀንሶ ፤ ተረግዞና ተወልዶ እንዲሁም ለአቅመ አዳም እድሜ ደርሶ በህዝባችን ላይ የጭቆና ቀንበር ተጭኖ የቆየውን እድሜ ጠገብ እና ጨቋኝ ስርዓት ለመገርሰስና በምትኩ ዘመኑን የዋጀ ትውልዱን የሚመጥን ፤ እኩልነትና ፍትሐዊነትን የዓላማው አልፋና ኦሜጋው አድርጎ ትግል የተነሳው የአማራ ፋኖ ብዙ ውስብውስብ እና ፈተኝ መንገዶችን በከፍተኛ ትግስት፤ እና አርቆ እሳቢነት በመፅናት ወጥ ድርጅት በመሰረትንበት ማግስት እንዲሁም ለአማራ የድል ብርሐን በፈነጠቀበትና በተቃራኒው በጠላቶቻችን ሰፈር የጨለማ ድባብና የሽንፈት መንፈስ በተዘራበት ወቅት ላይ በመመረቃችሁ የዛሬው የእናንተ ምርቃን በአይነቱም ሆነ በይዘቱ ልዩ ስለሆነ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ።
ዛሬ ይህን ታላቅ ቀን ለመድረስ ያደረጋችሁትን ጥረት፣ ያቀረባችሁትን መስዋዕትነት፣ የተጋፈጣችሁትን ከባድ ስልጠናዎችና ውጣ ውረዶች ሁሉ ድርጅታችን በልዩ ክብር እውቅና እንሰጣለን። በሌሊት ተኝታችሁ ተነስታችሁ፣ በዝናብና በፀሐይ፣ በረሃብና በጥማት፣ በአካላዊና በአእምሮአዊ ጫና ሁሉ ተቋቁማችሁ ዛሬ የኮማንዶ ባልደረባ ማዕረግ የተቸራችሁ ሲሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ!
እናንተ ዛሬ የተመረቃችሁት የአማራ ህዝብ የነፃነት በሮች የእናት ኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት ጠባቂዎች ናችሁ።
የህዝባችን ነፃነት፤ ሰላምና ደህንነት በእጃችሁ ነው። የድንበራችን ደህንነት፣ የሀገራችን አንድነት፣ የዜጎቻችን ህይወት በእናንተ ብቃትና ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ነው።
ዛሬ የእናንተ ቀን ነው። የብዙ ወራት አድካሚ ስልጠና፣ የማይታመን ጽናት፣ ፍርሃት የሌለበት ልብ፤ የማይሸራረፍ ግብረ ገብነት፤ የማይናወጥ ታማኝነት፤ የማያፈገፍግ ቁርጠኝነት፤ የማይታጠፍ ጀግንነት፤ የማይወላውል የዓላማ ወጥነት ፤ የማይዝረከክ ሰራዊትነት፤ በዘረኝነትና በጎጠኝነት የማይርመጠመጥ በሳልነት፤ ወዘተ ሁሉም ዛሬ በዚህ መድረክ ላይ ፍሬያቸውን አፍርተዋል።
ኮማንዶ መሆን ማለት ቀላል አይደለም። በባህሪው እና በተልእኮ ዝግጁነቱ፤ በስምሪት አሰላለፉ፤ በተግባር አፈፃፀሙ ለየት ያለ ቁመና ያለው ወታደራዊ አደረጃጀት ነው።
ኮማንዶ ማለት ለቆመለትና ለተሰለፈለት ዓላማ ውድ እና መተኪያ የሌላትን ህይወቱን ለመስጠት ዝግጁ መሆን ማለት ነው።
ኮማንዶ ማለት በጨለማ ውስጥ ብርሃን መሆን፣ በፍርሃት ውስጥ ደፍረትን መሆን፣ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ተስፋ መሆን ማለት ነው።
እናንተ ዛሬ ያንን ቃል ኪዳን ገብታችኋል። የአማራ ህዝብ ብሎም መላው ኢትዮጵያውያን ነፃነቱ ያለው በእናንተ እጅ ነው። የልጆቻችን የወደፊት ተስፋ በአጠቃላይ የአዲሱ ትውልድ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በእናንተ እጅ ነው።
ህዝባችን በአቅመ ቢሱ እና በልፍስፍሱ ስርዓት ጊዚያዊ የአፈና መዋቅር ውስጥ ሆኖ ዝም ያለ ቢመስልም እየተነፈሰ ያለው በእናንተ ሳንባ ነው። እየራበው ጠግቦ የሚያድረው በየቀኑ በሚመዘገቡ ጀብድና ድሎቻችን ነው፤ እየቆሰለ የሚያገግመው በየሰከንዱ በምናፈሳት ደምና ላባችን ነው።
እየተፅናና ያለው በእኛ ጀግንነት ነው። ተስፋ አድርጎ እና ተማምኖ እየጠበቀ የሚገኘው የእኛ የትግል ግስጋሴ ነው።
ልፍልስፍሱ የብልፅግና ስርዓት የቆመ የሚመስለው የአማራ ፋኖ የውስጥ መከፋፈልን እንደ ዋና እድል አድርጎ በመቁጠር ነበር፤ ጥንካሬውን እና ድክመቱን የሚለካው በእኛ አንድነትና መከፋፈል ነበር፤ ዛሬ የእኛ አንድነት በእሳት ተፈትኖ እንደ ወርቅ ነጥሮ ምርትና ገለባው ተለይቶ ፍንትው ብሎ ሲወጣ ምርቶ በዝቶ ገለባው አንሶ ሲያገኘው ሳይታዩ አብረው በቅለው የነበሩ ኢምንት እንክርዳዶችን ይዞ በድርድር ታርቂያለሁ እያለ ሲጮህ ህዝቡ አፉን በእጁ ይዞ እየተሳለቀባቸው ነው። የሚናገሩትን ፕሮፖጋንዳ እንኳን ለእኛ ለህፃናት የማይመጥን ነው በማለት ህዝቡ ንቀቱን እያሳያቸው ይገኛል። የቀነጨረ እና የጨነገፈ የፖለቲካ ስልትን ተጠቀምኩ እያለ አምስት የማይሞሉ እንክርዳዶች በሰሩት የባንዳነት ስራ አፍረውና ተሸማቀው ሞታችን ዛሬ ይሆን ነገ እያሉ በየጥሻው እንደ ፍልፈል ሲደበቁ ቆይተው ያገኟትን ቀዳዳ ተጠቅመው እጃቸውን ለምርኮ ፈቅደው ሲሰጡ ለብልፅግናም ለእነሱም እኩል የአፍረተቢስ ፕሮፖጋንዳን ለመጠቀም ተፍጨረጨሩ።
የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ነን ባዮች ነገሩን በውል ሳይረዱ ውሸትን እንደ ፖሊሲ የሚከተለው ብልፅግና አደናግሯቸው ከተሰጣቸው ሃላፊነት ወርደው እንክርዳዶቹ ጋር ቆመው መታየታቸው የህብረቱን ሃላፊነት ጭምር ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል።
እኛም በእዚህ አጋጣሚ ለአፍሪካ ህብረትም ሆነ ለሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የምናስተላልፈው መልእክት ስራችሁን መሬት ላይ ካለው እውነት ጋር በትክክል መስማማቱን አረጋግጡ፤ አይቶ አልቃሽ አትሁኑ ፤ የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያን እንደ ሐገር ያቆመ እና እስከ አሁን ያቆየ፤ ለመላው አፍሪካ እና የዓለም ጥቁር ህዝቦች ኩራትና የሞራል ከፍታን ያረጋገጠ ፤ የቅኝ ገዥዎች የአለም መጨረሻ እቅዳቸውን በየዘመኑ እያሳፈረ ከዚህ የደረሰ እንደ ሚስማር ሲመቱት እየጠበቀ የሚቀጥል የአድዋ ድል ባለቤት ህዝብ ነው።
ነገ የድል ጮራ ሲፈነጥቅ የአህጉሩን ጥቅሞችና መብቶችን በተመለከተ አብሮ ቆሞ የሚሟገተው የአማራ ፋኖ እንጅ አስመሳዩ ብስልፅግና ስርዓት አለመሆኑን ተረድታችሁ እውነት ላይ እንዲትቆሙ ጥሪ እናስተላልፍለን።
ስለዚህ በአራቱም የአማራ ንፍቀ ክበብ ማለትም ጎንደር፤ጎጃም ወሎና ሸዋ መላው የህዝባችንን ነፃነት ለማረጋገጥ እየተዋደቀ ከሚገኘው ታሪካዊ ሰራዊታችን ጋር ስትቀላቀሉ የእናንተን የጋለ ስሜት ለወንድሞቻችሁና ለእህቶቻችሁ ተጨማሪ ሞራል እንዲሆን አስችሉ!!!
ሁልጊዜ ብቃታችሁን አሳድጉ!!!
ሁልጊዜም ዲሲፕሊናችሁን አትተዉ!!!
ሁልጊዜም የቡድን መንፈስን ጠብቁ!!!
ሁልጊዜም ለሀገርና ለህዝብ ብቻ ታማኝ ሁኑ!!!
ሁልጊዜም በሁሉም ሁኔታ ክብርን ተጎናፀፉ!!
የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ የህዝባችን የብረት አጥሮች፣ የማትበገሩ ጀግኖች! የዛሬ ተመራቂ ልዩ ኮማንዶ አባላት በሙሉ እንኳን ለዚህ ታሪካዊ የምረቃ ቀን አደረሳችሁ።
በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ።
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!!
የካቲት 14/06/2018ዓ/ም
ሰበር ሰበር ሰበር የድል ዜና!
በአለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማ የመሸገው የአገዛዙ ጥምር ሀይል በመደምሰስ የወረዳ ከተማዋን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር በአርበኛ ማንዴላ እያዩ እና ሌሎችም የኮርና የኮር ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ አራቱንም ክ/ጦ በማቀናጀት ካራማራ ክ/ጦ፣ አድዋ ክ/ጦ፣ኦሜድላ ክ/ጦ እና ፊውታራሪ ገበየሁ ክ/ር እንዲሁም አርበኛ ሚኒያስን ጨምሮ የካቲት 15/2018 ከቀኑ 7:00 የጀመረው እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ 5 ስአት በወሰደ አውደ ውጊያ የአገዛዙን ጥምር ሰራዊት በመደምሰስ ከተማዋን መቆጣጠር ተችሏል። በጀግኖች መስዋትነት ከተማዋን ከመቆጣጠር ባሻገር ዲሽቃዎች፣ ብሬኖችን፣ ስናይፐሮችን፣ በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን፣ በርካታ ተተኳሾችን ፣ ተሽከርካሪዎችን፣ እና አገዛዙ የሚጠቀምባቸውን ቁሳቁሶች በቀላሉ በእጃችን ማስገባት ችለናል።
በዚህ እልህ አስጨራሽ አውደውጊያ ነበልባሎቹ የመይሳው ካሳ(፪ኛ) ከ7 በላይ ትልልቅ የቁም ምሽጎችን በመሰባበር በርካታ ቁጥር ያለው የአገዛዙን ሰራዊት አፈር ከድሜ በልቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አገዛዙ ለግል ጥቅም በግዞት የታሰሩ በርካታ እስረኞችን ማስፈታት ተችሏል። ይህ አውደ ውጊያ የተሳካ እንዲሆን አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት የጣናው ብርጌድ ወደ ቀጠናው ተጨማሪ ሀይል እንዳይኖር ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል።
አውደ ውጊያው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ስአት ድረስ እንደ ቀጠለ ይገኛል።ከሞትና ከምርኮ የተረፈው የአገዛዙ ጥምር ሀይል ከከተማው በመውጣት ወደ ኋላ እየፈረጠጠ ፋኖ እየተከተለ ፈቃደኛ የሆነውን እየተማረከ ሰባዊ እንክብካቤ እየተደረገለት ከዚህ ውጭ የሆነውን እየተደመሰሰ ይገኛል።
በዚህ አውደ ውጊያ አገዛዙ የሚተማመንበት የድሮን ቅኝት ከምንም ሊያድነው አልቻለም፣ ከ2 ጊዜ በላይ የድሮን ሙከራ ተደርጎ ምንም ሊፈይድ አልቻለም። አሁን ላይ ግዳጃችን ስላልጨረስን የድል ዜናችን በቁጥርና በአይነት በዝርዝር የምናሳውቅ ይሆናል።
ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር የህ/ግ
የካቲት 16/2018
ለአማራ የነፃነትና የክብርን ጉዞ
የአብይ አህመድ ሥርዓት አስፈፃሚዎች በፈለጉት መንገድ ሲፈነጩ ማየት እጅግ የሚያሳዝን ቢሆንም፣ ይህ ጊዜያዊ መሆኑን መረዳት ይገባል። የአማራን ሕዝብ ወደ ቀድሞ ልዕልናውና ክብሩ መመለስ የሚቻለው በእኛ በልጆቹ ጥረት ብቻ ነው።
የአማራን ሕዝብ ነፃነት ለማረጋገጥ የፋኖ ትግል ወደፊት እንዲገሰግስ ማድረግ የሁላችንም ቀዳሚ ተግባር ነው። የአሁኑ ትውልድ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ የሕዝባችንን የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ የመወሰን ከባድ ኃላፊነት ወድቆበታል።
ዛሬ በቁርጠኝነት ካልሠራን የነገ የታሪክ ተወቃሽ ከመሆን አናመልጥም። መሪዎች በመጠበቅና በታቀደ መንገድ በመጓዝ፣ ለትግሉ ስኬት የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል። ለነፃነታችን የምናሳየው ጽናትና ቁርጠኝነት ለስኬታችን ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ክብራችንን የምናስመልሰው በራሳችን ክንድ እንጂ በሌላ አካል ምጽዋት አይደለም!
88ኛ ክ/ጦር የአርሶ አደርን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ ወደ ገጠር ቀበሌዎች በተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሠራዊት ላይ ከባድ እርምጃ በመውሰድ በርካቶችን ደመሰሰ!
ትናንት የካቲት 15/2018 ዓ.ም መነሻውን ከወምበርማ ወረዳ ሽንዲ ከተማ ያደረገው የአብይ አህመድ አገዛዝ ጨፍጫፊ እና ዘራፊ ሠራዊት በቡራፈር ቀበሌ እና በዴንድ ቀበሌ አቅጣጫ ወደ ኸረጥ ቀበሌ ተንቀሳቅሷል።
የጠላት እንቅስቃሴ መረጃ የደረሳቸው በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ስር የ88ኛ ክ/ጦር የስቦ መምታና የቆረጣ ታክቲክ በመጠቀም በወሰዱት እርምጃ በርካታ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ችለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የክ/ጦሩ 1ኛ ሻለቃ ሽንዲ የመሸገው ጠላት ላይ ጥቃት በመክፈት ተወርዋሪ ንስሮቿን ደግሞ መሀል ከተማ አስርጋ በማስገባት ጥቃት የፈፀመች ሲሆን ቀንደኛ የሚሊሻ መሪ የሆነውን እንዳልካቸው መኮነን የተባለ ባንዳን ከእነ ግብረ አበሮቹ በደምሰስ 03 ክላሸንኮቭ መማረክ ተችሏል።
በተያያዘ አማራን በቀጥታ ከመግደል ባለፈ ተቋማቱን በየ ደረሰበት ሁሉ የሚያወድመው የአገዛዙ ሠራዊት በአከባቢው የኸረጥ ቀበሌ ማህበረሰብ ለማህበራዊ ፍትህ፣ ለመልካም አስተዳድር እና መሰል ማህበራዊ ግልጋሎት የሚያካሂድበትን አስተዳድር ፅ/ቤት እንዲሁም ለማህበረሰቡ የህክምና አገልግሎት የሚያገኝበት አነስተኛ ክሊኒክን የህክምና ቁሳቁሶቹን በመዝረፍ ሙሉ በሙሉ በእሳት አውድሞታል።
