es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 414
Suscriptores
+1324 horas
+277 días
+1 21530 días
Archivo de publicaciones
የአምሓራ ህዝብ ፈተና በዋናነት ሁለት እርስቱን ተቀራምተው ሉዓላዊ ሀገራትን ለማዋለድ በሚቃትቱ ተገንጣይ ወንበዴ ቡድኖች ቅዠት ላይ የታከከ ነው። ለዚህ ህልማቸው ደግሞ ሆድ አደር፣ ምንደኛ የክርስትና እምነት መሪዎች ዝብ በማደንዘዝ ተባባሪ ናቸው። በቤተክርስቲያን መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም" 👉ለቤተክርስቲያን መኖር እንጂ በቤተክርስቲያን መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ለቤተክርስቲያን ራስን አሳልፎ መስጠት እንጂ በቤተክርስቲያን መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ክርስቲያን መሆን እንጂ ክርስቲያን መስሎ መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የሚያምኑትን መኖር እንጂ የሚያምኑትን አስመስሎ መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የቆብ ሕይወትን መኖር እንጂ ቆብ ደፍቶ መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ጺምን መነጨት እንጂ ጺምን እየነቀሱ ቀሚስን እያንሰራፈፉ መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉በመጽሐፍ ሕግ መኖር እንጂ መጽሐፍን እያነበቡ መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የሚሰብኩትን መሆን እንጂ ሰብኮ ከዓውደ ምህረት መውረድ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የሰማዕትነት ደም እንጂ ደሞዝ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የአገልጋዮቿ ንጽህና እንጂ የአገልጋዮቿ ብዛት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የቅንነት አገልገሰሎት እንጂ የእልህ አገልግሎት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ሃይማኖታዊ ቋንቋ እንጂ መንደራዊ ቋንቋ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ኦርቶዶክሳዊ ማኅጸነ ዮርዳኖሳዊ የማይጠፋ ክርስቶሳዊ ዘር ሐረግ እንጂ ሥጋዊ ምድራዊ ጎጣዊ ፈራሽ በስባሻዊ ዘር ሐረግ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉መንግስተ ሰማያዊ ማንነት እንጂ ምድራዊ ማንነት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉መንፈስቅዱሳዊ ጵጵስና እንጂ ኮታዊ ዘርዓዊ ቋንቋዊ ጵጵስና ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ሰማያዊ ጽዮናዊ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቶስ ራስ የሆነለት ሕዋሳዊ አንድነት እንጂ መንደራዊ ጎጣዊ ምድራዊ ጥቅማዊ ኢኮኖሚያዊ ሥጋዊ አንድነት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉አስሩን ሕዋሳት በእግር እርግጥ በእጅ ጭብጥ አድርጎ ለእግዚአብሔር በማስገዛት እንጂ ባለ አስር አውታር በገና መደርደር  ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም ። 👉የሥነ ምግባር ካባን መጎናጸፍ እንጂ የልብስ ካባን መጎናጸፍ ኦርቶዶክሳዊ አስተሳስብን መጠምጠም እንጂ ነጭ ሻሽን መጠምጠም የወንጌልን ጫማ መጫማት እንጂ ቶርሽን ጫማን መጫማት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉እመቤታችንን መምሰል እንጂ ነይ ነይ እምየ ማርያም ማለት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የማርያምን ስራ መስራት እንጂ እኔስ ማርያምን እወዳታለሁ ማለት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉አስቦ መስራት እንጂ ሰርቶ ማሰብ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ሳይሆን መጮኽ እንጂ ከሆነ በኋላ መጮኽ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ደሟ እንዳይፈስ መጠበቅ እንጂ ከፈሰሰ በኋላ ደም መለገስ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። "ነጽር ኀበ አይ መካን አዕረጋ ለቤተክርስቲያን ዘከመ ይእቲ ኵለንታሁ- ቤተክርስቲያንን በዚህን ያህል ክብር እንዳከበራት ዕወቅ ኵለንታ ባህርይዋ ገንዘቡ እንደመሆኑ" ሃይማኖተ አበው ዮሐ አፈ ፷፯÷፴፱ "ቤተክስቲያንን በሕይወታችንም በሞታችንም እንጠብቃለን"

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ልዩ ቦታው ዘምባባ አርሴማ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፅሞ 14 ንፁኋኖች መገደላቸው ተነገረ! ጥቃቱ
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ልዩ ቦታው ዘምባባ አርሴማ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፅሞ 14 ንፁኋኖች መገደላቸው ተነገረ! ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ጥቅምት 17/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ገደማ ላይ ሲሆን፡ ከተገደሉት በተጨማሪ በርካቶች ታግተው መወሰዳቸው ተነግሯል። በዚህ ዞን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈፀም ለበርካታ ጊዜ ሲሆን፡ ከሳምንታት በፊትም በተመሣሣይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ታውቋል።

ከደቡብ አፍሪካ ዜና‼️ አስደንጋጭ ክስተት በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ! ጥቁር ቀን ለደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን! በደቡብ አፍሪካ ተወልደው ያደጉ ሁለት እህትማማቾች፣ * ዲቦራ መንግስቴ እና *
+3
ከደቡብ አፍሪካ ዜና‼️ አስደንጋጭ ክስተት በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ! ጥቁር ቀን ለደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን! በደቡብ አፍሪካ ተወልደው ያደጉ ሁለት እህትማማቾች፣ * ዲቦራ መንግስቴ እና * ኦፕራ መንግስቴ፣ ምንነቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሕይወታቸው አልፎ መገኘቱ ታውቋል። * እህትማማቾቹ በራሳቸው ክፍል ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል። * የሞታቸው ምክንያት እስካሁን በግልጽ አልታወቀም። * ይህ አሳዛኝ ክስተት በደቡብ አፍሪካ የሚኖረውን መላውን የኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ በከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ከትቶታል። ቤተሰቡ በጆሃንስበርግ፣ ኪስንግተን በሚገኝ ቦታ ላይ ለሐዘን ተቀምጦ ይገኛል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ሁሉም ወገኖች መጽናናትን እንዲሰጡ ጥሪ እናቀርባለን። አምላክ ለሟቾቹ ቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ለሚኖረው መላው ወገናችን ሁሉ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን። Via የኛ ሰው ሚዲያ ከደቡብ አፍሪካ

ኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት ምዘና ከ143 የዓለም አገራት 132ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች። ከ34 የአፍሪካ አገራት መካከል ደሞ ኢትዮጵያ አራት አገራትን ብቻ በመብለጥ 30ኛ ደረጃ አግኝታለች። ዓለማቀፉ የፍትሕ ፕሮጀክት ባወጣው ሪፖርት፣ በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት የኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ደረጃ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ2 ነጥብ 4 በመቶ ቀንሷል ብሏል።  ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው 16 አገራት መካከል ደሞ፣ ኢትዮጵያ 13ኛ ደረጃ ነው ያገኘችው። በአገሪቱ ለ5 ተከታታይ ዓመታት ተቋማት እየተዳከሙ፣ የሲቪክ ምኅዳሩ እየጠበበና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እየጨመረ መሄዱንም ሪፖርቱ ጠቅሷል። ኢትዮጵያ፣ በተለይ ሃሳብን በነጻነት በመግለጽ፣ በመሰብሰብ ነጻነት እና በሲቪክ ተሳትፎ መስኮች እጅግ ዝቅተኛውን ውጤት አስመዝግባለች።

የካሶኒ ሹፌር የነበረውና ከሰል ጭኖ ሲያሽከረክር ሰከላ ወረዳ አምቢሲ ላይ በጨካኙና በጡት ቆራጩ በአብይ አህመድ ወታደር በአደባባይ በግፍ የተረሸነው የቁጭ ተወላጁ ወጣት ተስፋ አይዞህ!!!
የካሶኒ ሹፌር የነበረውና ከሰል ጭኖ ሲያሽከረክር ሰከላ ወረዳ አምቢሲ ላይ በጨካኙና በጡት ቆራጩ በአብይ አህመድ ወታደር በአደባባይ በግፍ የተረሸነው የቁጭ ተወላጁ ወጣት ተስፋ አይዞህ!!!

ነባር የፋኖ አባላትን ወደ ማብቃት አድገናል !! በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የአባ ኮስትር ብርጌድ የነባር አባላትን በሶስት ወር ስልጠና በመስጠት ያጠናቀቀ በደማቅ ሁኔታ አስመስቋል ። ትውልድ ግንባታ ሐ
+4
ነባር የፋኖ አባላትን ወደ ማብቃት አድገናል !! በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የአባ ኮስትር ብርጌድ የነባር አባላትን በሶስት ወር ስልጠና በመስጠት ያጠናቀቀ በደማቅ ሁኔታ አስመስቋል ። ትውልድ ግንባታ ሐይል ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!

የሲቪል ደህንነቱ ወጣት በቁጥጥር ስር ውሏል‼️ ያሬድ አስማረ ይባላል የባህርዳር ከተማ የቀበሌ 13 ልጅ ሲሆን በቀን1000 ሽብር አበል እየተከፈለውን ስልክ ተገዝቶ ተሰጥቶት የፋኖን እንቅስቃሴ ለጠላ
የሲቪል ደህንነቱ ወጣት በቁጥጥር ስር ውሏል‼️ ያሬድ አስማረ ይባላል የባህርዳር ከተማ የቀበሌ 13 ልጅ ሲሆን በቀን1000 ሽብር አበል እየተከፈለውን ስልክ ተገዝቶ ተሰጥቶት የፋኖን እንቅስቃሴ ለጠላት በማሳወቅ የመጀመሪያ ዙር ዘጌ ላይ መጥቶ መረጃ ሰብስቦ ለጠላት የሰጠ ሲሆን  ሁለተኛ ተልዕኮውን ፈፅሞ ሲመለስ ደጎስ ያለ 10ዐዐዐብር እንደሚሰጠው ተነግሮት ድጋሜ መረጃ በመሰብሰብ ላይ እያለ ጨንታ ላይ በጣናው መብረቅ ብርጌድ በቁጥጥር ስር ውሏል ። ተመልከቱ ህፃናትን አረመኔው ስርዓት እንዴት መጠቀሚያ አንዳደረጋቸው ሁሉም ማህበረሰብ አዳዲስ ሰወችን ስታገኙ ለፋኖ በመጠቆም እንድትተባበሩን በማለት ብርጌድ መልክት አስተላልፈዋል ። ©ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ወላጆች ልጆቻችንን እንቆጣጠር‼️ 18/ዐ2/2018 ዓ.ም

ከመቄት ወረዳና አካባቢው ህዝብና የፋኖ ሰራዊት ጋር በየ ፈርጁ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የህልውና ትግሉን ለማሳለጥ የሚያግዝ የህዝብ አስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት አመርቂ ስራ እየተሰራ ይገኛል:: የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ኢንጅነር አራጋው ያለው እና ሌሎች በየደረጅው ያሉ አመራሮች በተገኙበት የመቄት ወረዳና የአካባቢውን ማህበረሰብ እንዲሁም የአካባቢውን የፋኖ ሰራዊት በማወያየት የህዝብ አስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት የህዝብ አስተዳደሩን እና የፋኖውን ሚና ለይቶ በማሳወቅና በመስጠት የህልውና ትግሉን ማሳለጥ የሚቻልበት መንገድ ላይ አመርቂ ስራ እየተሰራ ይገኛል:: በዚህም ጥቅምት 15 እና 16/2018 ዓ.ም ከአካባቢው የፋኖ ሰራዊትና አመራር እንዲሁም ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ በየደረጃው ያሉ የሰራዊቱ አመራሮች ከሰራዊቱ የመጣውን ገንቢ ሃሳብና አስተያየት በመቀበል ተበታትኖ እየታገለ ያለውን ሰራዊት ማሰባሰብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተመክሮ ውጤታማ ስራ እየተሰራ ይገኛል:: የህዝብ አስተዳዳሪ ሆነው በህዝብ የተመረጡ አመራሮችም በተመሳሳይ ማህበረሰቡ ያነሳቸውን ሃሳብና አስተያየቶች እንዲሁም ጥያቄዎች በመቀበል በቀጣይ የህዝብ አስተዳደር መዋቅሩ ፋኖ ነፃ ባወጣቸው ቀጠናዎች ታጋዩ ይሰራቸው የነበሩ  ስራዎች በመጋራትና በማቅለል በርካታ የህዝብ  ስራዎችን በመሸከምና በማገልገል ለትግሉ ውጤታማነት የበኩሉን ሃላፊነት መወጣት በሚችልበት ሁኔታ ላይ በመምከር ወደ ተግባር የማስገባት ስራ ተሰርቷል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር በማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ እና ምዕራብ ጎንደር ቋራ የመሸገው ጥምር የአገዛዙ ሰራዊት በሁሉም አቅጣጫ ደለጎ፣አፀደማርያም እና ሻ
+1
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር በማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ እና ምዕራብ ጎንደር ቋራ የመሸገው ጥምር የአገዛዙ ሰራዊት በሁሉም አቅጣጫ ደለጎ፣አፀደማርያም እና ሻሁራ ከተማ በአሁኑ ስዓት ከፍተኛ ሽንፈትን እያስተናገደ ይገኛል።መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ እና ከጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሰራዊት ጋር በመጣመር ደለጎ ከተማ የመሸገውን ፀረ አማራ ሀይል ክፉኛ እየተመታ ሲሆን አድዋ ክ/ጦ አፀደማርያምና ሻሁራ ቀጠናን እየተፋለሙት ይገኛል። ዝርዝር ዜናውን አውደ ውጊያው እንደተጠናቀቀ የምናቀርብ ይሆናል። ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ        ጥቅምት 18/02/2018

አፋብኃ ሰሜን አምሐራ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጥቅምት 17/2018ዓ.ም 01.የአማራ ፋኖ በደራ ምድር ያገኘው ዕንቁ ድል❗ ✅ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር(04 ብርጌዶች፦ አሣምነው ብርጌድ፣ ቴዎድሮሥ ብርጌድ፣ ናኹሰናይ ብርጌድ እና ገብርዬ ብርጌድ) ✅ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የሁሉም ብርጌድ ሥራ አሥፈጻሚዎች እና አፈርዋናት ብርጌድ ✅ጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች እና የገብረ መሥቀል ብርጌድ ተዋጊዋ ጣይቱ ሻለቃ                👉የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት  የአማራ ፋኖን ለማጥቃት ከአርብ ገበያ እሥከ ሳና ዕቅዶችን አውጥቶ በሌሊት ሲንቀሳቀስ መረጃው ቀድሞ የደረሳቸው የጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር/አፈርዋናት ብርጌድ/ውባንተ ሻለቃ ሳና ከተማ መውጫ ላይ ባደረገው ደፈጣ ከሌሊቱ 11:00 ላይ ጠላትን አሳፍሮ መልሷል።የአገዛዙ ጭራቅ አራዊት ሰራዊት በደራ ምድር ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ ሙሉ ቀን እንደ ገብሥ ታጭዶ፣ ተከምሮ ሢወቃ ውሏል።  የጠላትን ቅሥም ቀድማ በሌሊቱ የሰበረችው የትናንቷ ፈረሰኛው ሻለቃ የአሁኗ ውባንተ ሻለቃ ነች። ሳና ሚካኤል ላይ የጠላት ኃይል በነበልባሎቹ ተደምሥሧል፤ ቆሥሏል።              👉የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ከቴሌ እሥከ ቆሚሣ፣ ከሊባኖሥ እሥከ እሥላም መቃብር ደፈጣ ይዞ ነበር። ከቆሚሳና ከእሥላም መቃብር  መካከል ካለው ተራራ''ቸሮ'' ላይ ጭራቁ የአቢይ ወታደር ወደ ቆሚሳ ሲጓዝ በተቃራኒው የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ወደ ገላውዴዎሥ ሢንቀሳቀሥ መሐል መንገድ ላይ ተገናኙ። የአቢይ መከላከያ  ከተራራው አናት የውቤ ልጆች በታች። መብረቅ የመታው የመሰለው የአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አለኝ ያለውን ሁሉ የመሣሪያ ዓይነት አዘነበው። ከሌሊቱ ንጋተ 11:30 ልብና ትጥቅን የታደሉት ውባንታዊያን ጠላትን በጨበጣ እንዳልነበር አድርገውታል። ጨዋታው ወደ ቦምብ ውርዋሮሽ ተቀይሯል። አይበገሬዎቹ አምሐሮች የውባንተ የግብር ልጆች ቦምብን በቦምብ መልሰዋል፣ ጠላትን አምበርክከዋል፣ የጠላትን ምቹ ቦታ ተቆጣጥረዋል። የውጊያው አድማሥ ሰፍቶ በቆሚሳ፣ ቸሮ፣ ደረባ፣ ሊባኖሥ፣እሥላም መቃብር፣ ያያ ሚካኤል ሙሉ ቀናትን ከፍተኛ ተጋድሏን ሢያደርጉ ውለዋል። ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ሥብራትን አድርሷል። ብዛት ያለው ጠላትን ደምሥሧል። ብዛት ያለው ጠላትን አቁሥሏል። መሣሪያዎችን በዓይነት ማርኳል። አያሌ የጠላት ምሽጎችን ሰባብሯል። ከተማውን አሥለቅቋል።                   በዚህ እልህ አሥጨራሽ የጨበጣ ውጊያና መደበኛ ውጊያ ጠላትን ሢፋለሙ ውለውና ሢማርኩ ውለው የጠላት ምሽግ ላይ ጠላትን ተፋልመው በጀግንነት የተሰው ዕንቁ ወንድሞቻችን 02 ናቸው።በጀግንነት ተፋልመው የተሰው ዕንቁ ወንድሞቻችንም አርበኛ መልካሙ ጠጋዬ(ኩርሲ) እና አርበኛ አቢዮት መኳንንት ናቸው።                     👉ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ፣ ንሥር ሻለቃ፣ አፈርዋናት ብርጌድ በአርበኛ ክንዳለምና አርበኛ ታደለ ምሬ እየተመራ፣ ጣና ብርጌድ ሥራ አሥፈጻሚ፣  ጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ/ ገብረ መሥቀል ብርጌድ/አናብሥቷ ጣይቱ ሻለቃ በኢንጅነር አበራ እና በዘመቻ መልሰው  እየተመራ ሁሉም በጥምረት ከገብርዬ ተራራ ጀምረው ያያ ሚካኤል፣ እሥላም መቃብር፣ ሞሻ፣ ገላውዴዎሥ ከተማ እና ዙሪያ ገባው ላይ ጠላትን ከጀርባ በመምታት ለወንድሞቻቸው ደርሰዋል። በዚህ የተናበበ ውጊያ ጠላት አንደኛው ኃይል ለሌላኛው ኃይል እንዳይደርሥ ተደርጎና ሰንሰለታቸው ተቆርጦ በተፈለገው መንገድ ተገርፈው፣ ተደምሥሠውና ቆሥለው ውለዋል። ከቀኑ 11:00 ጀምሮም ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ  ጦር ከገረፈው የተረፈው ኃይል አምልጦ ወደ አርብ ገበያና አምበሣሜ ሢፈረጥጥ የገላውዴዎሥ ቴሌ ላይ ባደረጉት ደፈጣ ጠላት በደምብ እየተመታ ይገኛል።                  👉የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሥራ አሥፈጻሚ በተዋጊው አርበኛ አመኑ ዓለምአንተ እየተመራ፣ የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ በአርበኛ ወንዱ አንተ አሰፋ እየተመራ፣ የጣና ገላውዴዎሥ ሥራ አሥፈጻሚ በአርበኛ ጋሻዬ እንግዳ እየተመራ፣ የጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር/አፈርዋናት ብርጌድ/ውባንተ ሻለቃ በጥምረት ከሳና ከተማ፣ ሐዋርያት አቦ፣ ሚካኤል፣ ቴሌ፣ ኳንኮይ ገብርኤል፣ ቸሮ እና እሥላም መቃብር ድረሥ በፍጹም አንድነትና ቅንጅት ጠላትን ሢገርፉ ውለዋል። ይህኛው የጠላት ኃይልም የውባንተ ጦር ላረገፈው የጠላት ኃይል ድጋፍ እንዳይሰጥ አድርጎታል።  ሳና ከተማ በጀመረው ውጊያ ጠላት የኔ ያለውን አሥከሬን ሳይቀብርና ቁሥለኛ ሣይይዝ ወደ እንጦሮጦሥ ተወርውሯል። የሆድ ዘመዶቹንም ድጋፍ እንዳይሰጥ ተደርጓል። ታሳቢ ያደረጋቸው ዕቅዶቹም በዜሮ ተባዝተውበታል። 02. እሥቴ/መካነ ኢየሱስ ከተማ ጉና ክፍለ ጦር፦ 👉እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ               ጥቋቁር አናብስቶቹ እሥቴ ዴንሳ ብርጌዶች በጉና ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዡ አርበኛ አዛዥ ደሣለኝ እና በብርጌድ መሪዎቹ በአርበኛ ብርቃዬኹ ደምሴ እና አርበኛ አብራራው እየተመራ ከቀኑ 9:30 መካነ ኢየሱስ ከተማ በመግባት የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂዎችን እያምበረከኩ እሥከ ምሽት ድረሥ ውጊያ አድርገዋል። ምሽት 12:10 መካነኢየሱስ ከተማ በእሥቴ ዴንሳ አናብስት ተሞሽራለች። ከተማው ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ሥርም ሆኗል። ቆሪጥ የተባለችው ሆድ አደር ባንዳም እግሬ አውጭኝ ሥትል ወደ ደብረ ታቦር ፈርጥጣለች። 👉አንዳ ቤት ብርጌድ               ጭራቁ የአቢይ አሕመድ አራዊት ሰራዊት ከወለሽ ከተማ ተነሥቶ ወደ ጃራ ገዶ ከተማ ለእኩይ አላማው ሢንቀሳቀሥ በእሳት ተፈትነው ያለፈው አንዳ ቤት ብርጌድ የአገዛዙን ዘመቻ መሪ ጨምሮ 05 የአገዛዙን ዕድሜ አርዛሚዎች ሸኝቷቸዋል። የአንዳ ቤት ብርጌድን ክንድ መቋቋም የተሳነው የአገዛዙ ዕድሜ አርዛሚ ቡድን ንጹሐን አርሶ አደሮችን በጅምላ አሥሯል፣ ገድሏል፣ ሰብላቸውንም አውድሟል።              በመጨረሻም በምሥር ወጥ የተሸጠው በለጠ አንዳርጌ(ቆራጡ)  ከቀኑ 8:00  ወደ እሥቴ የሚወሥደውን ግንዳ ጠመም መድኃኒዓለም  ላይ ያለውን የመብራት ትራንሥፎርመር በሥናይፐር ተኩሶ በመምታት አንድዶታል።  በድርጊቱ የተበሳጨው የእሥቴ ሕዝብም በብሥጭት ወደ አደባባይ ወጥቷል። ድላችን በተባበረ አምሐራዊ ክንዳችን❗ አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ጥቅምት17/2018 ዓም

በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። EOTCMK TV ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ
በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። EOTCMK TV ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገዳላቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል። በደረሰን መረጃ መሠረት በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ  ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፈት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል። የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል። በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ  ከተማ  ሪፈር  መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።  ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ 6ቱ በገገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተገልጿል። በመረጃው እንደተመላከተው በቀበሌው ባለ ከፍተኛ ስጋት በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሀገረ ስብከት ደረጃ ከመንግሥት ጋር በጋራ መሥራት ይገባል ተብሏል። በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ሁኔታዎችን ለማረረጋት የሀገር መከላከያ በስፍራው እንደሚገኝ በመረጃው ተጠቅሷል። ©ማኅበረ ቅዱሳን ቴቪ

"አፋ ብ ኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 💪💪💪 " ትግል ይቀጥላል ........
+2
"አፋ ብ ኃ ቴዎድሮስ ዕዝ  💪💪💪 " ትግል  ይቀጥላል ........

በአለም ካሉት ዲያስፖራዎች ሁሉ የለንደን ጉዳያ በፓርላማ ተነሳ ማለት ቤተምንግሰቱን በእንግሊዝ ምድር ያለው እንቅስቃሴ ምን ያክል እንዳስጨነቀው የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ድል በአንድነት የመስራት ውጤት ነው፡፡ ግማሾቻችን በውጪ ሆነን በነጉድጓጋሚ ድምፅ ስናስጨንቃቸው፣ ግማሾቻችን በውስጥ ስናስደነበራቸውና ላብ በላብ ስናደርጋቸው ነበር፡፡ ይህ ድል የበርሚንግሀም አማራ ፋኖዎች ባይመጡ ኖሮ ማን በወንብረ ላይ ይጮህ ነበር፡፡ የአንድነት ማህበሩ አስደንጋጪ እና ድንገተኛ ዱብዳ ድምፅ ባያወጣ ኖሮ ቀጥታ ስርጪት ማን ያቋርጥ ነበር፡፡ በተመሳሳይ በውስጥ የአብይን አውሬነት ተጋልጧል፡፡ ይህ ሁሉ ከውሰጥ የተደረገው ቢደረግም የለንደን ፋኖዎች ማህበራት የመጡትን አማሮች ይዘው በወጭ ሆነው አስጨናቂ ድምፅ ባያጡ ኖሮ የውስጥ ተቃቀሞው ብቻውን ይኮስስ ነበር፡፡ ይህ የአብይ አህምድ ፍርሀት ዋና ምክንያት አንድነታችን እና ህብረታችን ነው፡፡ የትግሉን ውጤታማነት የሚፈልግ ሁሉ ይችን እውነት ይዞ፣ ለእዚህ እውነት ይኑር፡፡ የማሸነፊያ መሳሪያችን እንደ አማራ አንድነት ነው፡፡ ይህ አንድነት መዳኛ መሆኑንም የእነግሊዝ ምድር መስክራለች፡፡ በርቱ እንበርታ፡፡

የበላይነትን በኃይል ወይስ በዲሞክራሲ !? በፀረ-አማራነት ሰልፍ "የአማራን የበላይነት በማሸነፍ" ሲተረክ የኖረውና የቀጠለው የእኩልነትና ዲሞክራሲያዊነት ወግ ሁሉ የራስን የበላይነት የማረጋገጥ ትግል
የበላይነትን በኃይል ወይስ በዲሞክራሲ !? በፀረ-አማራነት ሰልፍ "የአማራን የበላይነት በማሸነፍ" ሲተረክ የኖረውና የቀጠለው የእኩልነትና ዲሞክራሲያዊነት ወግ ሁሉ የራስን የበላይነት የማረጋገጥ ትግል ስለመሆኑ በወያኔ የሩብ ክፍዘ ወቅትም ሆነ የአሁኖቹ ተረኞች ሥራ የሚያረጋግጠው ነው። በወቅቱ የኦሮሞ ልሒቃን መካከል ያለ 'ቅራኔ' የበላይነታችንን ለማረጋገጥ በየትኛው መንገድ እንሒድ የሚል ነው። ስለእኩልነትና "የአማራ የበላይነትን ስለማሸነፍ" አብዝተው ቢያነሱም ዞሮ ፍላጎታቸው በተራችን የበላይነታችንን እናረጋግጥ የሚል ነው። ስልጣን ላይ ያለው የዐቢይ ቡድን ለበላይነታችን ተገዳዳሪዎች የሆኑትን የሰሜን ኃይሎች (አማራና ትግራይ) በጦርነት አንበርክከን እናረጋግጣለን ብሎ ጦርነትን ሥራው ያደረገ ነው። (ይሔ በእርግጥ ጦሱ ለሁሉም መትረፉ ግልፅ ነው።) በእነጃዋር የሚመራው ቡድን ደግሞ የበላይነታችንን ለማረጋገጥ ጦርነት አዋጪ አይደለም፣ መከተል ያለብን "ዲሞክራሲያዊ የበላይነት ነው" እያሉ ነው። ሁለቱም ቡድኖች ለኦሮሞ የበላይነት መሠረት የሚሆኑ የሕዝብ ብዛት የበላይነት፣ የግዛትና ሀብት የበላይነት ፣ ወዘተ እንዳላቸው ያምናሉ። የስልጣን የበላይነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ግን ተገዳዳሪዎችን በኃይል እናንበርክክ ወይስ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የሚለው የልዩነት ምንጭ ሆኖ 'ተቃርነዋል'። በዚህ መሠሉ ክፋት ውስጥ አማራው በሕልውናው ላይ የተቃጣን ጥፋት ለመቀልበስ ይተጋል። ® አንሙት አብርሃም

የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች እየተካሄዱ ባሉ ጦርነቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሰላማዊ ሰዎች እና መሠረተ ልማቶች ጉዳት ይፋ እንዲደረጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠየቁ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም (# አሻራ ሚዲያ) ደሳለኝ(ዶ/ር) የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ያቀረቡት የመክፈቻ ንግግር ብሩህ ተስፋን የተሞላ ቢሆንም በኢትዮጵያውያን ከዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ካለው የሠላምና የጸጥታ መናጋት፣ የኑሮ ውድነትና የዴሞክራሲ ምህዳር መጥበብ አኳያ ከንግግራቸው ይዘት ጋር የሚጣረስ ነው የሚል እምነት አለኝ በማለት ወደ ጥያቄያቸው ተሻግረዋል። ጥያቄያቸውን ከማቅረባቸው በፊት ግን አንድ ማሳሰቢያን ሰጥተዋል። እሱም ዛሬም የማነሳቸው ጥያቄያዎችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጨለምተኛነት እንዳይወስዷቸው ያሳሰቡበት ነው። “ጥያቄዎቹም የሕዝብ በመሆናቸው እንጂ ጨለምተኛ በመሆኔ አይደለም” ብለዋል። በአማራ፣ ኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ጦርነትና ግጭቶች ተባብሰው በመቀጠላቸው ብዙዎች እየተጎዱ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንደ ጸጥታ መሪነትዎ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በእነዚህ ጦርነቶች ምክንያት የተጎዱ ሰላማዊ ሰዎችና የሰለማዊ ሰዎች መሠረተ ልማቶች ቁጥር በግልጽ ይፋ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። “የጸጥታ ችግሮቹን ለመፍታት “ጽንፈኛ” እና “አሸባሪ” የሚላቸውን ቡድኖች ከመውጋት ባለፈ ለሁለቱ ክልሎች ከወታደራዊ አማራጮች ውጪ የተለየ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለመስጠት መንግስት ለምን አይሰራም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል። “የኢትዮጵያ ሕዝብ የእርስ በእርስ ጦርነት አንገፍግፎታል፤ በሀገር ውስጥ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ መብላት ከብዶታል፤ ሀገራችንም እንደ ኮሎምቢያ ከውስጥ ታጣቂዎች ጋር ሀምሳ ዓመታትን እየተዋጋች ልትቀጥል አትችልም” ሲሉ አጽዕኖት ሰጥተው አሳስበዋል። “የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች የተፋጠነ ፍትሕ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም የፖለቲካ አቅጣጫ የተሰጠበት በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ያለ ፍርድ እየተንገላቱ ነው፤ ቤተሰቦቻቸውም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀወዋል” ብለዋል። በሕግ የማስከበር ስም የሚፈጸሙ የዘፈቀደ የፖለቲካ እስሮች፣ ለሚመጣው 7ኛ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ነፃና ተዓማኒነት ያለው እንዳይሆን ላለማድረጉ መንግስት የሚሰጠውን ዋስትናም ጠይቀዋል።

ብልፅግና በአዲስአበባ ከተማ አፈሳ ማካሄዱ ተገለፀ። አገዛዙ በአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችን አፈሳ አጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ኗሪዎች ተናገሩ። ዛሬ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ በርካታ ወ
ብልፅግና በአዲስአበባ ከተማ አፈሳ ማካሄዱ ተገለፀ። አገዛዙ በአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችን አፈሳ አጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ኗሪዎች ተናገሩ። ዛሬ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ በርካታ ወጣቶች ታፍሰዉ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መወሰዳቸዉ ታዉቋል። በ11 ክፍለከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ታፍሰዉ በሶስት መሰረታዊ ዉትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መወሰዳቸዉን ከአዲስአበባ  ከተማ ኗሪዎች ተናግረዋል። በተለይ እድሚያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለዉ ስለመወሰዳቸዉ ጭምር ኗሪዎች ተናግረዋል። አፈሳው በናዝሬት፣በደብረዘይት፣በሞጆ፣በሀዋሳ፣በይርጋለም፣በኦሮሚያ ክልል በሁሉም አካባቢዎች እንዲሁም በጋሞ እና ወላይታ ብዛት ያላቸዉ ወጣቶች ታፍስዉ በእየ አዳራሹ ታጉረዉ ይገኛሉ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል የሚታፈሱ ወጣቶች ቁጥር ከወትሮው በተለየ መልኩ መጨመሩ የተገለፀ ሲሆን የብልግና ኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ የኦሮሞን ስልጣን እንጠብቅ እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነትን ሊያጠፉ ነዉ በሚል ስብከት ወጣቱ እየታፈሰ ነዉ ተብሏል።