es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 414
Suscriptores
+1324 horas
+277 días
+1 21530 días
Archivo de publicaciones
በአለም ካሉት ዲያስፖራዎች ሁሉ የለንደን ጉዳያ በፓርላማ ተነሳ ማለት ቤተምንግሰቱን በእንግሊዝ ምድር ያለው እንቅስቃሴ ምን ያክል እንዳስጨነቀው የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ድል በአንድነት የመስራት ውጤት ነው፡፡ ግማሾቻችን በውጪ ሆነን በነጉድጓጋሚ ድምፅ ስናስጨንቃቸው፣ ግማሾቻችን በውስጥ ስናስደነበራቸውና ላብ በላብ ስናደርጋቸው ነበር፡፡ ይህ ድል የበርሚንግሀም አማራ ፋኖዎች ባይመጡ ኖሮ ማን በወንብረ ላይ ይጮህ ነበር፡፡ የአንድነት ማህበሩ አስደንጋጪ እና ድንገተኛ ዱብዳ ድምፅ ባያወጣ ኖሮ ቀጥታ ስርጪት ማን ያቋርጥ ነበር፡፡ በተመሳሳይ በውስጥ የአብይን አውሬነት ተጋልጧል፡፡ ይህ ሁሉ ከውሰጥ የተደረገው ቢደረግም የለንደን ፋኖዎች ማህበራት የመጡትን አማሮች ይዘው በወጭ ሆነው አስጨናቂ ድምፅ ባያጡ ኖሮ የውስጥ ተቃቀሞው ብቻውን ይኮስስ ነበር፡፡ ይህ የአብይ አህምድ ፍርሀት ዋና ምክንያት አንድነታችን እና ህብረታችን ነው፡፡ የትግሉን ውጤታማነት የሚፈልግ ሁሉ ይችን እውነት ይዞ፣ ለእዚህ እውነት ይኑር፡፡ የማሸነፊያ መሳሪያችን እንደ አማራ አንድነት ነው፡፡ ይህ አንድነት መዳኛ መሆኑንም የእነግሊዝ ምድር መስክራለች፡፡ በርቱ እንበርታ፡፡

የበላይነትን በኃይል ወይስ በዲሞክራሲ !? በፀረ-አማራነት ሰልፍ "የአማራን የበላይነት በማሸነፍ" ሲተረክ የኖረውና የቀጠለው የእኩልነትና ዲሞክራሲያዊነት ወግ ሁሉ የራስን የበላይነት የማረጋገጥ ትግል
የበላይነትን በኃይል ወይስ በዲሞክራሲ !? በፀረ-አማራነት ሰልፍ "የአማራን የበላይነት በማሸነፍ" ሲተረክ የኖረውና የቀጠለው የእኩልነትና ዲሞክራሲያዊነት ወግ ሁሉ የራስን የበላይነት የማረጋገጥ ትግል ስለመሆኑ በወያኔ የሩብ ክፍዘ ወቅትም ሆነ የአሁኖቹ ተረኞች ሥራ የሚያረጋግጠው ነው። በወቅቱ የኦሮሞ ልሒቃን መካከል ያለ 'ቅራኔ' የበላይነታችንን ለማረጋገጥ በየትኛው መንገድ እንሒድ የሚል ነው። ስለእኩልነትና "የአማራ የበላይነትን ስለማሸነፍ" አብዝተው ቢያነሱም ዞሮ ፍላጎታቸው በተራችን የበላይነታችንን እናረጋግጥ የሚል ነው። ስልጣን ላይ ያለው የዐቢይ ቡድን ለበላይነታችን ተገዳዳሪዎች የሆኑትን የሰሜን ኃይሎች (አማራና ትግራይ) በጦርነት አንበርክከን እናረጋግጣለን ብሎ ጦርነትን ሥራው ያደረገ ነው። (ይሔ በእርግጥ ጦሱ ለሁሉም መትረፉ ግልፅ ነው።) በእነጃዋር የሚመራው ቡድን ደግሞ የበላይነታችንን ለማረጋገጥ ጦርነት አዋጪ አይደለም፣ መከተል ያለብን "ዲሞክራሲያዊ የበላይነት ነው" እያሉ ነው። ሁለቱም ቡድኖች ለኦሮሞ የበላይነት መሠረት የሚሆኑ የሕዝብ ብዛት የበላይነት፣ የግዛትና ሀብት የበላይነት ፣ ወዘተ እንዳላቸው ያምናሉ። የስልጣን የበላይነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ግን ተገዳዳሪዎችን በኃይል እናንበርክክ ወይስ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የሚለው የልዩነት ምንጭ ሆኖ 'ተቃርነዋል'። በዚህ መሠሉ ክፋት ውስጥ አማራው በሕልውናው ላይ የተቃጣን ጥፋት ለመቀልበስ ይተጋል። ® አንሙት አብርሃም

የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች እየተካሄዱ ባሉ ጦርነቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሰላማዊ ሰዎች እና መሠረተ ልማቶች ጉዳት ይፋ እንዲደረጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠየቁ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም (# አሻራ ሚዲያ) ደሳለኝ(ዶ/ር) የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ያቀረቡት የመክፈቻ ንግግር ብሩህ ተስፋን የተሞላ ቢሆንም በኢትዮጵያውያን ከዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ካለው የሠላምና የጸጥታ መናጋት፣ የኑሮ ውድነትና የዴሞክራሲ ምህዳር መጥበብ አኳያ ከንግግራቸው ይዘት ጋር የሚጣረስ ነው የሚል እምነት አለኝ በማለት ወደ ጥያቄያቸው ተሻግረዋል። ጥያቄያቸውን ከማቅረባቸው በፊት ግን አንድ ማሳሰቢያን ሰጥተዋል። እሱም ዛሬም የማነሳቸው ጥያቄያዎችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጨለምተኛነት እንዳይወስዷቸው ያሳሰቡበት ነው። “ጥያቄዎቹም የሕዝብ በመሆናቸው እንጂ ጨለምተኛ በመሆኔ አይደለም” ብለዋል። በአማራ፣ ኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ጦርነትና ግጭቶች ተባብሰው በመቀጠላቸው ብዙዎች እየተጎዱ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንደ ጸጥታ መሪነትዎ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በእነዚህ ጦርነቶች ምክንያት የተጎዱ ሰላማዊ ሰዎችና የሰለማዊ ሰዎች መሠረተ ልማቶች ቁጥር በግልጽ ይፋ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። “የጸጥታ ችግሮቹን ለመፍታት “ጽንፈኛ” እና “አሸባሪ” የሚላቸውን ቡድኖች ከመውጋት ባለፈ ለሁለቱ ክልሎች ከወታደራዊ አማራጮች ውጪ የተለየ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለመስጠት መንግስት ለምን አይሰራም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል። “የኢትዮጵያ ሕዝብ የእርስ በእርስ ጦርነት አንገፍግፎታል፤ በሀገር ውስጥ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ መብላት ከብዶታል፤ ሀገራችንም እንደ ኮሎምቢያ ከውስጥ ታጣቂዎች ጋር ሀምሳ ዓመታትን እየተዋጋች ልትቀጥል አትችልም” ሲሉ አጽዕኖት ሰጥተው አሳስበዋል። “የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች የተፋጠነ ፍትሕ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም የፖለቲካ አቅጣጫ የተሰጠበት በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ያለ ፍርድ እየተንገላቱ ነው፤ ቤተሰቦቻቸውም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀወዋል” ብለዋል። በሕግ የማስከበር ስም የሚፈጸሙ የዘፈቀደ የፖለቲካ እስሮች፣ ለሚመጣው 7ኛ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ነፃና ተዓማኒነት ያለው እንዳይሆን ላለማድረጉ መንግስት የሚሰጠውን ዋስትናም ጠይቀዋል።

ብልፅግና በአዲስአበባ ከተማ አፈሳ ማካሄዱ ተገለፀ። አገዛዙ በአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችን አፈሳ አጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ኗሪዎች ተናገሩ። ዛሬ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ በርካታ ወ
ብልፅግና በአዲስአበባ ከተማ አፈሳ ማካሄዱ ተገለፀ። አገዛዙ በአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችን አፈሳ አጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ኗሪዎች ተናገሩ። ዛሬ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ በርካታ ወጣቶች ታፍሰዉ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መወሰዳቸዉ ታዉቋል። በ11 ክፍለከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ታፍሰዉ በሶስት መሰረታዊ ዉትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መወሰዳቸዉን ከአዲስአበባ  ከተማ ኗሪዎች ተናግረዋል። በተለይ እድሚያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለዉ ስለመወሰዳቸዉ ጭምር ኗሪዎች ተናግረዋል። አፈሳው በናዝሬት፣በደብረዘይት፣በሞጆ፣በሀዋሳ፣በይርጋለም፣በኦሮሚያ ክልል በሁሉም አካባቢዎች እንዲሁም በጋሞ እና ወላይታ ብዛት ያላቸዉ ወጣቶች ታፍስዉ በእየ አዳራሹ ታጉረዉ ይገኛሉ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል የሚታፈሱ ወጣቶች ቁጥር ከወትሮው በተለየ መልኩ መጨመሩ የተገለፀ ሲሆን የብልግና ኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ የኦሮሞን ስልጣን እንጠብቅ እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነትን ሊያጠፉ ነዉ በሚል ስብከት ወጣቱ እየታፈሰ ነዉ ተብሏል።

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በፓርላማ ያነሷቸው ነጥቦች መካከል ሁሌ የእኔን ጥያቄ በጨለምተኝነት ይመለከቱታል ለምን? የሰላም እና የፀፅታ መናጋት ዋና መንስኤው መንግስት ነው። የህሌና እስረኞችን ለምን አትፈ
ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በፓርላማ ያነሷቸው ነጥቦች መካከል ሁሌ የእኔን ጥያቄ በጨለምተኝነት ይመለከቱታል ለምን? የሰላም እና የፀፅታ መናጋት ዋና መንስኤው መንግስት ነው። የህሌና እስረኞችን ለምን አትፈቱም፣ በህግ ማስከበር ስም የዘፈቀ እስር ለምን አታቆሙም? መንግስት 10 ድስት ጥዶ አንዱንም አላማሰለውም ፣ ለምን ትኩረት ሰተው የውስጥ ችግሮቻችን አይፈቱም? በጦርነት ስንት ትውልድ እየበላችሁ ትኖራላችሁ ? ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለፓርላማው ያቀረቡት ጥያቄ!

"መንግሥት የቀይ ባሕርን አደንጃ ያነሳበት መንገድ፡ 10 ድስት ጥዶ አንዱንም ሳያማስል ሁሉንም የማሳረር ሂደት ነው" ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ዛሬ ፓርላማ ላይ ካነሱት ጥያቄ የተወሰደ።
"መንግሥት የቀይ ባሕርን አደንጃ ያነሳበት መንገድ፡  10 ድስት ጥዶ አንዱንም ሳያማስል ሁሉንም የማሳረር ሂደት ነው" ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ዛሬ ፓርላማ ላይ ካነሱት ጥያቄ የተወሰደ።

ለአማራ ህዝብ አንድንነት አዛኝ በመምሰል መድረክ አግኝቶ ማይክ በጨበጠ ቁጥር በአማራ ህዝብ የህልውና ታጋይ ፋኖዎች ላይ የስም ማጥፋት የሚያካሂደው ተገንጣዩ እና ነጋዴው ቡድን አሁንም በፋኖዎች ላይ የጥላቻ ንግግሩን ማካሄዱን ቀጥሎበታል። ተገጣዩ እና ነጋደው ቡድን ለአማራ ህዝብ አንድነት አዛኝ አለመሆኑን ማረጋገጥ የሚቻለው ደግሞ በአለም ዙሪያ ያሉ የአማራ ማህበራት ተሰባስበው በመምከር በመሰረቱት አንድ አለም አቀፍ የአማራ ማህበር ውስጥ እንዳልተካተተ እና የተመሰረተውን ማህበርም እንደማያምንበት በድምፅ ቅጅው ሲናገር ይደመጣል አንድነት የሚጠላ ያለ አይመስለኝም!! ሁላችንም አንድነትን እንፈልጋለን ነገር ግን አንድነት ሽፋን አድርጎ ጀግና ፋኖዎቻችንን ለማጥቃት የሚደረግን ዘመቻ ዝም ብለን መመልከት የለብንም ተባብረን ታግለን💪🏽 ማስቆም ይኖርብናል!!

ይህ ከላይ የምታዩት ግለሰብ ኮማንደር መሐመድ መኮንን ይበላል ከሳምንት በፊት በብልፅግና አማራ ጠሉ ጡት ቆራጩ አብይ አህመድ አረመኔያዊ ሰራዊት በኤፍራታና ግድም ወርዳ በርግቢ ቀበሌ መሸጎ የሚኖረው
ይህ ከላይ የምታዩት ግለሰብ ኮማንደር መሐመድ መኮንን ይበላል ከሳምንት በፊት በብልፅግና አማራ ጠሉ ጡት ቆራጩ አብይ አህመድ አረመኔያዊ ሰራዊት በኤፍራታና ግድም ወርዳ በርግቢ ቀበሌ መሸጎ የሚኖረው መከላከያ በህዝባችን ላይ ለሚያደርሰው እንግልትና ስቃይ አለባብሶ ለማሳለፍ የአገዛዙ የውሽት ፕሮፓጋንዳ መስራቱን ይታወቋል ሆኖም ይል ግለሰብ የኤፍራታና ግድም ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ የሆነው ውሀብይ ኮማንደር መሀመድ መኮንን ከፋኖ ጋር ትዋጋልችሁ መሳሪያችሁን አምጡ በማለት የስድስት ኦርቶዶክስ አርሶአደር አባዎራወችን ማህትባቸውን እየበጠሰ ወደ እስርቤት በማስገባት አላግባብ ግፍና እንግልት እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም ማህተባቸው የተበጠሠባቸዉ ግለሰቦች 1 ለማ ዘዉዴ 2 ሀይሉ አልታዬ 3 ከፈለኝ ተሰማ 4 አስፋዉ አለሜ 5 ገዛኸኝ ሸዋግዘዉ 6 ጠቅል በቀለ ሲሆኑ ግለሰቡ ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ አብዝቶ የሚሰራና የአብይን የሴራ ተልኮ የሚያስፈፅም የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ግለሰብ ስለሆነ ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ ለነፃነት ወጥተን በምንኖርበት ሀገር የበደሉን ድዉያን አፍንጫ አፍንጫቸውን ደፍተን የአማራን ህዝብ ነፃ የምናወጣ መሆኑን በሰማዕታት ስም እንጠይቃለን።

~~~ሰቦ ማስከዳት~~~ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክ/ጦር የስናን አባጂሜ ብርጌድ ከአውደ ውጊያና ከሕዝብ አስተዳደር ጎን ለጎን የጠላ
~~~ሰቦ ማስከዳት~~~ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክ/ጦር የስናን አባጂሜ ብርጌድ ከአውደ ውጊያና ከሕዝብ አስተዳደር ጎን ለጎን የጠላትን ሀይል ስቦ በማስከዳት እያፈራረሰው ይገኛል። ጥቅምት 15 እና ጥቅምት 16/2018ዓ.ም በሁለት ተከታታይ ቀናት ውስጥ አራት የመከላከያው ሠራዊት አባላት  ከረቡዕ ገበያ ከተማ የስናን አባጅሜ ብርጌድን ከነሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል። በዚህም መሠረት 1.መዋስ አባተ 2.መሀመድ ሲራጅ 3.ቦንሳ ፈይሳ እና 4.ሲና ኦብሳ የተባሉ የ25ኛ ክፍለ ጦር  የመከላከያ አባላት የአገዛዙን  ስርዓት ግፍና ጭቆና አንፈልግም በማለት ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ የስናን አባጂሜ ብርጌድ ተቀላቅለዋል። ድል ለአማራ ፋኖ! ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም

🔥የንፁሀን እልቂትና የደረሰው የንፁሃን ሀብት ዉድመት‼️ ====== በቋራ ሳሊያ ከተማ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት የንፁሀን ህይወትን የቀጠፈዉ አካላቸዉን ያጎደለዉ አምባገነኑ አገዛዝ ብዙዎችን መኖሪያ መጠጊያ አልባ አድርጓቸዋል።የብዙዎች ንፁሀን ግለሰቦች ቤት ንብረት ከጥቅም ዉጭ ሆኗል። የአማራ ህዝብ ፋኖ ሆነም አልሆነም ደገፈም አልደገፈም ህፃን ሆነ አዋቂ ሽማግሌ ሆነ ወጣት ሙስሊም ሆነ ክርስቲያ ሸህ ሆነ ቄስ...አማራ እስከሆነ ድረስ በአገዛዙ ከመጨፍጨፍ ከመጥፋት አይድንም።ስለሆነም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከትግሉ ጎን መሆን ብቸኛዉ መፍትሄዉ ነዉ። የአማራ ህዝብ እንደ አማራ ተጠናክሮ ከቀጠለዉ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና የህልዉና ስጋት የባርነት ቀንበር ራሱን ነፃ ለማድረግ በጠላቱ ላይ ገና ብዙ መምረር መጨከን መቁረጥ አንድ ሆኖ ዘመኑን በዋጀ የትግል መዋቅር መታገል ይጠበቅበታል። አማራነት በነፃነት በክብር በእኩልነት ወይም ሞት!!!

ሰበር ዜና ቲርቲራ ከተማ በምኒልክ ዕዝ ቁጥጥር ስር ዋለች!! የንጉሥ ሚላኤል አሊ ኮር ሰራዊት ዛሬ በዕለተ ሰኞ ሌሊት ቲርቲራ ከተማን ተቆጣጥሯል:: ሰራዊቱ በከተማይቱ መሀል እየተንጎማለለ ነው:: ዋርካው ይችላል

ነውረኛው የብልፅግና አገዛዝ የታጋይ ፋኖ ተሰማ ካሳሁን ወላጅ እናት እና የ4 አመት ሕፃን ልጅ ማገቱ ታውቋል ===================================== ሽንፈቱን የፋኖ ቤተሰቦችን በ
+2
ነውረኛው የብልፅግና አገዛዝ የታጋይ ፋኖ ተሰማ ካሳሁን ወላጅ እናት እና የ4 አመት ሕፃን ልጅ ማገቱ ታውቋል ===================================== ሽንፈቱን የፋኖ ቤተሰቦችን በማሰር እና በማገት እየገለፀ የሚገኘው የብልጽግና አገዛዝ ዛሬ ደግሞ የፋኖ አመራሩን እናት እስከነ የልጅ ልጅ አግቶ መሰወሩን ፋኖ ተሰማ ካሳሁን በማህበራዊ የትስስር ገፁ ከዚህ በታች እንደሚከተለው ገልጿል። “እንደ ህዝብ ካልተከበርን እንደግለሰብ አንከበርም፤ ሁላችንም ነፃ ካልሆንን ማናችንም ነፃ አንሆንም! [አሮጊቷ እናቴ ከእነ የልጅ ልጇ በጨለማ ታገተች] በ1983 ዓ/ም ገና እኔኑ በማህፀንሽ ተሸክመሽ በደከምሽበት ወራት አስሮ ያንገላታሽ ጠላት ዛሬ ደግሞ በእኔ ሰበብ ከእነ የልጅ ልጅሽ ህፃን አሜን ዘወትር (የ4-ዓመት ህፃን) እንዳገተሽ ሰማሁ። ያኔ እንዳልወለድ ሞክሯል፤ ሳይሳካለት ቀርቶ ተወልጄም አድጌ አንገቱን አንቄዋለሁ። ይህንን አረመኔ አገዛዝ ጨክነን ማስወገድ እንዳለብን አምነን ወጥተናልና መፍትሔው በእጃችን ነው። የህዝባችንን ጠላት በማስወገድ ህልውናችንን አረጋግጠን ነፃነትን እናመጣለን። አዎ ለሁላችን የሚበጀውን መርጠን መከራውን ታጋዮቹ በተለዬ እንሸከመው ይሆናል እንጂ ወደ ድል ከመገስገስ አንገደብም። ድል ለአማራነት!”

አፋብኃ ሰሜን አምሐራ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጥቅምት 17/2018ዓ.ም 01.የአማራ ፋኖ በደራ ምድር ያገኘው ዕንቁ ድል❗ ✅ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር(04 ብርጌዶች፦ አሣምነው ብርጌድ፣ ቴዎድሮሥ ብርጌድ፣ ናኹሰናይ ብርጌድ እና ገብርዬ ብርጌድ) ✅ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የሁሉም ብርጌድ ሥራ አሥፈጻሚዎች እና አፈርዋናት ብርጌድ ✅ጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች እና የገብረ መሥቀል ብርጌድ ተዋጊዋ ጣይቱ ሻለቃ 👉የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት የአማራ ፋኖን ለማጥቃት ከአርብ ገበያ እሥከ ሳና ዕቅዶችን አውጥቶ በሌሊት ሲንቀሳቀስ መረጃው ቀድሞ የደረሳቸው የጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር/አፈርዋናት ብርጌድ/ውባንተ ሻለቃ ሳና ከተማ መውጫ ላይ ባደረገው ደፈጣ ከሌሊቱ 11:00 ላይ ጠላትን አሳፍሮ መልሷል።የአገዛዙ ጭራቅ አራዊት ሰራዊት በደራ ምድር ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ ሙሉ ቀን እንደ ገብሥ ታጭዶ፣ ተከምሮ ሢወቃ ውሏል። የጠላትን ቅሥም ቀድማ በሌሊቱ የሰበረችው የትናንቷ ፈረሰኛው ሻለቃ የአሁኗ ውባንተ ሻለቃ ነች። ሳና ሚካኤል ላይ የጠላት ኃይል በነበልባሎቹ ተደምሥሧል፤ ቆሥሏል። 👉የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ከቴሌ እሥከ ቆሚሣ፣ ከሊባኖሥ እሥከ እሥላም መቃብር ደፈጣ ይዞ ነበር። ከቆሚሳና ከእሥላም መቃብር መካከል ካለው ተራራ''ቸሮ'' ላይ ጭራቁ የአቢይ ወታደር ወደ ቆሚሳ ሲጓዝ በተቃራኒው የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ወደ ገላውዴዎሥ ሢንቀሳቀሥ መሐል መንገድ ላይ ተገናኙ። የአቢይ መከላከያ ከተራራው አናት የውቤ ልጆች በታች። መብረቅ የመታው የመሰለው የአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አለኝ ያለውን ሁሉ የመሣሪያ ዓይነት አዘነበው። ከሌሊቱ ንጋተ 11:30 ልብና ትጥቅን የታደሉት ውባንታዊያን ጠላትን በጨበጣ እንዳልነበር አድርገውታል። ጨዋታው ወደ ቦምብ ውርዋሮሽ ተቀይሯል። አይበገሬዎቹ አምሐሮች የውባንተ የግብር ልጆች ቦምብን በቦምብ መልሰዋል፣ ጠላትን አምበርክከዋል፣ የጠላትን ምቹ ቦታ ተቆጣጥረዋል። የውጊያው አድማሥ ሰፍቶ በቆሚሳ፣ ቸሮ፣ ደረባ፣ ሊባኖሥ፣እሥላም መቃብር፣ ያያ ሚካኤል ሙሉ ቀናትን ከፍተኛ ተጋድሏን ሢያደርጉ ውለዋል። ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ሥብራትን አድርሷል። ብዛት ያለው ጠላትን ደምሥሧል። ብዛት ያለው ጠላትን አቁሥሏል። መሣሪያዎችን በዓይነት ማርኳል። አያሌ የጠላት ምሽጎችን ሰባብሯል። ከተማውን አሥለቅቋል። በዚህ እልህ አሥጨራሽ የጨበጣ ውጊያና መደበኛ ውጊያ ጠላትን ሢፋለሙ ውለውና ሢማርኩ ውለው የጠላት ምሽግ ላይ ጠላትን ተፋልመው በጀግንነት የተሰው ዕንቁ ወንድሞቻችን 02 ናቸው።በጀግንነት ተፋልመው የተሰው ዕንቁ ወንድሞቻችንም አርበኛ መልካሙ ጠጋዬ(ኩርሲ) እና አርበኛ አቢዮት መኳንንት ናቸው። 👉ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ፣ ንሥር ሻለቃ፣ አፈርዋናት ብርጌድ በአርበኛ ክንዳለምና አርበኛ ታደለ ምሬ እየተመራ፣ ጣና ብርጌድ ሥራ አሥፈጻሚ፣ ጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ/ ገብረ መሥቀል ብርጌድ/አናብሥቷ ጣይቱ ሻለቃ በኢንጅነር አበራ እና በዘመቻ መልሰው እየተመራ ሁሉም በጥምረት ከገብርዬ ተራራ ጀምረው ያያ ሚካኤል፣ እሥላም መቃብር፣ ሞሻ፣ ገላውዴዎሥ ከተማ እና ዙሪያ ገባው ላይ ጠላትን ከጀርባ በመምታት ለወንድሞቻቸው ደርሰዋል። በዚህ የተናበበ ውጊያ ጠላት አንደኛው ኃይል ለሌላኛው ኃይል እንዳይደርሥ ተደርጎና ሰንሰለታቸው ተቆርጦ በተፈለገው መንገድ ተገርፈው፣ ተደምሥሠውና ቆሥለው ውለዋል። ከቀኑ 11:00 ጀምሮም ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ከገረፈው የተረፈው ኃይል አምልጦ ወደ አርብ ገበያና አምበሣሜ ሢፈረጥጥ የገላውዴዎሥ ቴሌ ላይ ባደረጉት ደፈጣ ጠላት በደምብ እየተመታ ይገኛል። 👉የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሥራ አሥፈጻሚ በተዋጊው አርበኛ አመኑ ዓለምአንተ እየተመራ፣ የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ በአርበኛ ወንዱ አንተ አሰፋ እየተመራ፣ የጣና ገላውዴዎሥ ሥራ አሥፈጻሚ በአርበኛ ጋሻዬ እንግዳ እየተመራ፣ የጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር/አፈርዋናት ብርጌድ/ውባንተ ሻለቃ በጥምረት ከሳና ከተማ፣ ሐዋርያት አቦ፣ ሚካኤል፣ ቴሌ፣ ኳንኮይ ገብርኤል፣ ቸሮ እና እሥላም መቃብር ድረሥ በፍጹም አንድነትና ቅንጅት ጠላትን ሢገርፉ ውለዋል። ይህኛው የጠላት ኃይልም የውባንተ ጦር ላረገፈው የጠላት ኃይል ድጋፍ እንዳይሰጥ አድርጎታል። ሳና ከተማ በጀመረው ውጊያ ጠላት የኔ ያለውን አሥከሬን ሳይቀብርና ቁሥለኛ ሣይይዝ ወደ እንጦሮጦሥ ተወርውሯል። የሆድ ዘመዶቹንም ድጋፍ እንዳይሰጥ ተደርጓል። ታሳቢ ያደረጋቸው ዕቅዶቹም በዜሮ ተባዝተውበታል። 02. እሥቴ/መካነ ኢየሱስ ከተማ ጉና ክፍለ ጦር፦ 👉እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ ጥቋቁር አናብስቶቹ እሥቴ ዴንሳ ብርጌዶች በጉና ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዡ አርበኛ አዛዥ ደሣለኝ እና በብርጌድ መሪዎቹ በአርበኛ ብርቃዬኹ ደምሴ እና አርበኛ አብራራው እየተመራ ከቀኑ 9:30 መካነ ኢየሱስ ከተማ በመግባት የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂዎችን እያምበረከኩ እሥከ ምሽት ድረሥ ውጊያ አድርገዋል። ምሽት 12:10 መካነኢየሱስ ከተማ በእሥቴ ዴንሳ አናብስት ተሞሽራለች። ከተማው ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ሥርም ሆኗል። ቆሪጥ የተባለችው ሆድ አደር ባንዳም እግሬ አውጭኝ ሥትል ወደ ደብረ ታቦር ፈርጥጣለች። 👉አንዳ ቤት ብርጌድ ጭራቁ የአቢይ አሕመድ አራዊት ሰራዊት ከወለሽ ከተማ ተነሥቶ ወደ ጃራ ገዶ ከተማ ለእኩይ አላማው ሢንቀሳቀሥ በእሳት ተፈትነው ያለፈው አንዳ ቤት ብርጌድ የአገዛዙን ዘመቻ መሪ ጨምሮ 05 የአገዛዙን ዕድሜ አርዛሚዎች ሸኝቷቸዋል። የአንዳ ቤት ብርጌድን ክንድ መቋቋም የተሳነው የአገዛዙ ዕድሜ አርዛሚ ቡድን ንጹሐን አርሶ አደሮችን በጅምላ አሥሯል፣ ገድሏል፣ ሰብላቸውንም አውድሟል። በመጨረሻም በምሥር ወጥ የተሸጠው በለጠ አንዳርጌ(ቆራጡ) ከቀኑ 8:00 ግንዳ ጠመም ላይ ያለውን የመብራት ትራንሥፎርመር በሥናይፐር ተኩሶ በመምታት አንድዶታል። በድርጊቱ የተበሳጨው የእሥቴ ሕዝብም በብሥጭት ወደ አደባባይ ወጥቷል። ድላችን በተባበረ አምሐራዊ ክንዳችን❗ አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሀቅአለው ፀጋ አለባቸው

የአደረጃጀት ዜና ‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አዲሱን የቡልጋ ክፍለ ጦር መሰረተ ‎=============== ‎በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በከሰም ክ/ጦር ስር የነበሩ ፊት አውራሪ አስማረ ዳኘ ብርጌድና እና ተስፋ ብርጌድ በመቀናጀት የቡልጋ ክፍለ ጦርን መስርተዋል:: ‎ ‎ይህም ክፍለ ጦር የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሴንትራል ኮማንድ የተቋማቱን የሰው ኃይል የፋይናንስ እና መሳሪያ ክምችት መሰረት ያደረገ አደረጃጀት እንዲሰራ ያስተላለፈውን መመሪያ በማሟላታቸው ተረጋግጦ ነው:: ‎ ‎ክፍለ ጦሩ የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሴንትራል ኮማንድ አባል÷ የዕዙ አመራሮች÷ የቀድሞው ከሰም ክፍለ ጦር÷ የነበልባል ክፍለ ጦር ÷ የኃይለ ማሪያም ክፍለ ጦር አመራሮች እና የፋኖ አባላት በተገኘበት ነው:: ‎ ‎በዚህ የቡልጋ ክፍለ ጦር ምስረታ የተገኘ የፋኖ አመራሮች በክፍለ ጦሩ ምስረታ የተሰማቸውን ስሜት÷  የፋኖን የትግል እንቅስቃሴ እና ተቋማዊ ለውጥ የተመለከቱ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል:: ‎ ‎የክፍለ ጦሩ ምስረታ በተለያዩ ዝግጅቶች የተካሄደ ሲሆን ክፍለ ጦሩን የሚመሩ ‎1ኛ ዋና መሪ _ጌታዉ ሻረዉ ‎2ኛ_ወታደራዊ አዛዥ _ይግረማቸዉ ዳምጠዉ ‎3ኛ_ም/አዛዥ ለኦኘሬሽናል_መቶ አለቃ አለሙ ወርቁ ‎4ኛ_ም/ አዛዥ ለአስተዳደር _ አርበኛ ኃይለማርያም ኃይለሴ ‎5ኛ_ም/አዛዥ ለሎጅስቲክ _ አርበኛ    ፍቃደ ወርቁ ‎6ኛ_ዘመቻ _  አርበኛ  ኃይሉ ተፈራ ‎7ኛ_ም/ዘመቻ _ አርበኛ መንገሽ ተፈራ ‎8ኛ_መረጃ እና መሀንዲስ ‎9ኛ_ስልጠና እና ክህሎት-  ሃምሳ አለቃ ሰይፈ ሸዋንግዛዉ ‎10ኛ_ወታደራዊ ህግ አገልግሎት _አርበኛ   ደሞዝ ኃይልዬ  11ኛ-ም/ ወታደራዊ  የህግ አገልግሎት ኃላፊ -አርበኛ  ተገኝ አዳፍሬ ‎12ኛ_ኦርድናስ _አርበኛ   ብሩክ ይልማ ‎13ኛ_ህክምና _መቶ አለቃ ወልዱ ‎     ድርጅት ጉዳይ ፅ/ቤት ‎1ኛ_ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ _አርበኛ   በዛወርቄ ክንፉ ‎2ኛ_የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ _  አርበኛ አቡሽ ኃይሌ ‎3ኛ_ህዝብ ግንኙነት _   አርበኛ ቦጋለ ምንዳ ‎4ኛ_ትምህርት እና ስልጠና _ አርበኛ   ተኮላ ደግፌ ‎5ኛ_ፋይናስ ሀላፊ _   አርበኛ ስዩም ጌታዉ ‎6ኛ_ፋይናስ ም/ኃላፊ_አርበኛ    ዜና ከበደ ‎ ሲቪል አስተዳደር ጉዳዮች    ‎1ኛ_አስተዳደር ጉዳይ ኃላፊ _ሃምሳ አለቃ ገረመዉ ታደሰ ‎2ኛ_አደረጃጀት ኃላፊ_  አርበኛ  ተስፋዬ ጥላሁን ‎3ኛ_ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ _አርበኛ     ፋኒት ቅርሴ ከበደ ‎4ኛ_ሀብት አሰባሳቢ _አርበኛ    አበባየሁ ተስፋዬ ‎5ኛ_ም/ሀብት አሰባሳቢ _ አርበኛ   ጎሽሜ በቀለ ‎5ኛ_ሰላምና የህዝብ ደህንነት ኃላፊ _ አርበኛ  ሻምበል በላቸዉ ‎6ኛ_ሰላምና የህብ ደህንነት ምክትል ኃላፊ  -አርበኛ አህመድ ኢብራሂም ሁነው ተመድበዋል::   መረጃውን ያደረሰን  አርበኛ ቦጋለ ምንዳ የቡልጋ ክ/ጦር ሪፖርተር ነው። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዜና ክፍል    ጥቅምት 17/ዐ2/2018 � ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎