ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más4 416
Suscriptores
+1224 horas
+287 días
+1 15930 días
Archivo de publicaciones
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰሞኑ ነፃ በወጣችው ግሸ ራቤል ወረዳ ከሚኖሩ የመንግስት ሰራተኞች ጋር በታሪካዊቷ "ራቤል" ከተማ ውይይት አካሄደ።
===============
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በታሪካዊቷ "ራቤል" ከተማ ያሉ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት መደበኛ ስራቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችል ውይይት ከመንግስት ሰራተኞች ጋር አካሄዷል::
የመወያያ የመነሻ ሐሳብ ያቀረቡት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አርበኛ አሸናፊ ምንዳ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ክፍት ሆነው ለህዝባቸው አገልግሎት እንዲሰጡ የተሰደዱ የብልጽግና የፖሊስና የሚኒሻ አባላት ከነቤተሰቦቻቸው ተመልሰው የበደሉትን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው ህይወታቸውን እንዲመሩ እና የህዝብ ተቋማት ንብረቶች ለግለሰቦች ጥቅም ሳይውሉ በስርዓት ተቆጥረው ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ነው መድረኩ የተዘጋጀው ብለዋል::
በተጨማሪም የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አርበኛ አሸናፊ ምንዳ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከአማራ ህዝብ ጭርፍጫፊ የብልጽግና ስርዓት ጎን ተሰልፈው የነበሩ የብልጽግና አመራሮች ፖሊስና የሚኒሻ አባላት በቀጥታ ከፋኖ አመራሮች ጋር ተነጋግረው ወይም በሀይማኖት አባቶች እና በሀገር ሽማግሌዎች በኩል በቀጣይ ከእንደዚህ አይነቱ የጥፋት ቡድን ጋር ደግመው ላይሰሩ ቃል ገብተው ከመጡ ፋኖ በባለፉት ተግባራቸው እንደማይጠይቃቸው በአቋም እንደተያዘ ማረጋገጫ ሰጥቷል::
በውይይቱ የተሳተፉት የመንግስት ሰራተኞች የፋኖን ተቋማዊ ለውጥ እንደ ተዓምር በመግለጽ አማራን አማራ ላለማፈናቀል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የወሰደው የበሰለ አካሄድ የአማራን አንድነት የሚያመጣ ተግባር ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::
ፋኖ ወደ ታሪካዊቷ "ራቤል" ከተማ የገባበት አግባብ ብስለት በተሞላ መልኩ የተጠና በመሆኑ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ከስግብግብ ዘራፊዎች የታደገ ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ጨምረዋል::
በተጨማሪም እነዚህ የመንግስት ሰራተኞች በቀጣይ ቢስተካከሉ እና በአንክሮ ቢታዩ ያሏቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶች አቅርበዋል::
ከመንግስት ሰራተኞች የተሰጡ አስተያየቶችን በቀጥታ ተቀብለን እናስተካክላለን ያሉት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ህግ አገልግሎት መምሪያ ሀላፊ አርበኛ ተስፋየ ገስጥ የፋኖ አባሎቻችን ዕዙ የሚያስተላልፈውን ትዕዛዝ ከመፈጸም ውጭ በድርጅታዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች የማይገቡ መሆኑን አውቃችሁ በቀጣይ በሚዘረጋው መዋቅር የራሳችሁን አስተዋጽኦ ልታደርጉ ይገባል ሲሉ ማደማደሚያ ሰጥተዋል::
መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግኑኝነት ዜና ክፍል
ጥቅምት 09/02/2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን እና ፊስቡክ ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
https://www.facebook.com/share/p/17FBBgD9xG/
+2
ምሽግ አሰባበር እንዴትና ምን እንደሆነ ለማያውቁት "በመከላከያ ስም" ለሚንቀሳቀሱት ለብልፅግና የመንደር ዱርየዎች አሳዩዋቸው።
ሰሞኑን ፋኖ በሰበራቸው ወሳኝ ምሽጎች ውስጥ በርካታ የጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደር አስከሬን የአሞራ ቀለብ ሆኖ ቀርቷል።
ሕዝባዊ የምክክር መድረክ በኤፍራታ እናግድም ወረዳ ካብሳራምባ ደጉቼ ቀበሌ የተደረገ ውይይት!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ትግሉ ከጀመረ ጀምሮ ብዙህ ቀበሌዎችን በስሩ እያስተዳደረ ይገኛል።
የአሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ፋኖ ያሬድና የኮሩ አመራሮች በተገኘበት ሰፊና ጠለቅ ያለ እርጅም ሰዓት የወሰደ በዚሁ በኤፍራታ እናግድም ወረዳ ካብሳራምባ ደጉቼ ቀበሌ የፖለቲካ ትምህርት እና የህዝብ አደረጃጀት ዙሪያ ከፋኖ አመራሮች በሚያምርና በሚያስደምም መልኩ ለህዝቡ ግንዛቤ የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ማህበርሰቡ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱም ከላይ እንደጠቀስነው አብይ አህመድ በኤፍራታና ግድም ወረዳዎች ላይ በፖለቲካና ትምህርት ጉዳዩ ያለ የሌለውን በትር ከተጠቀመባቸው የአማራ ወረዳዎች አንዱ ነው ።
ሆኖም ብአዴን የአብይ እኩይ ሲራ ተቀብለው በአማራ ህዝብ ላይ ፖሊቲካም ይሁን ትምህረትና የህዝብ አደረጃጃት እንዳይሰራ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ፋኖዎች በሚያስተዳድራቸው ወረዳና ቀበሌ አሁን ባለው የፖለቲካ ትምህርት እና የህዝብ አደረጃጅት ጉዳይ ለህብረተሰቡ ሰፊ ሚና የተጫወተበትና ፋኖች ይህን አረመኔያዊ ስራት ለመጣል ከወጡ ጀምሮ በሰላም መውጣትና መግባት እንደቻሉ አልፎም ተርፎም ተማሪ ልጆቻቸው በሰላም ወደ ትምህርት ቤት ገብተው ተምርው እንዲመለሱ የተደረገበት የህዝብ አደረጃጅትም ሰላማቸውን ያስገኘ ለኮሩ አመራሮች ሰፋ ያለ ገንቤና ሃሳብ ከማህበረሰቡ ያሳዩበት መድረክም ነበር።
በመጨረሻም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር አመራሮች እና የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ፖለቲካ ዘርፍ አርበኛ ያሬድ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ካብሳራምባ ደጉቼ ሸበሌ ከሚኖሩት ማህበረሰብ ጋር በነበራቸው ወይይት እጅጉ ተደስተው ማህበረሰቡም ለፋኖ አመራሮች እናንተ ማለት እኛ ነን እናንተ ስትኖሩ እኛ መኖር እንችላለን ከዚህ በፊት ለፋኖ ድጋፍ ስናደርግ የቆየን ሲሆን ከዚህ በላይ ድጋፋችን እናደርጋለን በማለት ህዝባዊ መድረኩ ተጠናቋል!!
መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ
ጥቅምት 03/02/2018 ዓ.ም
""""""ዘራፊወች ላይ እርምጃ ተወሰደ 👇👇
ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰአት ላይ በመሸንቲ መስመር ልዩ ቦታው መቶ ካብ ተብሎ የሚጠራው ቦታ በፋኖ ስም የተለያዩ ዝርፊያወችን ሲፈፅሙ የነበሩ የአረመኔው ስርዓትና አሽከር ተባባሪ የሆኑ አካላት ላይ የጣናዉ መብረቅ ብርጊድ ቃኝና መሃድስ ባደረጉት የተጠና ልዩ ኦፕሬሽን ደረጀ ሞላ የተባለ ሚሊሻ እስከወዳኛዉ የተሸኘ ሲሆን በዚህ ቀጠና ላይ ያለውን የሚፈፀሙትን ወንጀሎች በመከታተል ቀጣይነት ያለው እርምጃ ለመውሰድ ብርጌድ በትኩረት እየሰራ ሲሆን ህዝቡ ማንኛውን ጥቆማ በመስጠት እንድትተባበሩን በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።
ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም
➾በንፁሐን ላይ የድሮን ጥቃት ደረሰ‼
ፋይሽቱ ኃይል አዴት አቅራቢያ በምትገኘው ሮብገበያ ተብላ በምትጠራ ቦታ ድሮን የጣለ ሲሆን አምስት ንፁሐንን አርሶአደሮች መገደላቸው ታውቋል።
የአሻራ ምንጮች ከቦታው እንዳረጋገጡት ከሆነ ከቀኑ 6:00 ሰዓት አካባቢ ዛሬ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በይልማና ዴንሳ ወረዳ አዴት አቅራቢያ ልዩ ስሟ ሮብገበያ በተባለች ቦታ ድሮን የጣለ ሲሆን አምስት አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ሴቶችና ህፃናት እንዲሁም የቀንድ ከብቶችም የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን የአይን እማኞች ለአሻራ ገልጸዋል።
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ የተለመደ ተግባሩን አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል።
በቀን 02/02/2018 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አብማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 08 ውሀ ጋን ተብሎ በሚጠረው አጥቦ አይለብሴ የሚኒሻ ካንፕ ላይ የንጉሱ ተርቦች ከቀኑ 11:00 ስዓት ባደረጉት ድንገተኛ ኦፕሬሽን የብአዴንን አገልጋዮች ሙት እና ቁስለኛ አድርገውታል። በተመሳሳይ ሌሊት 10:00 በዚሁ ቦታ ላይ በንጉሱ ልጆች በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት ዋርድያዉ እስከ ወዲያኛው ላይመለስ ተሽኝቷል።
ይህንን ጀብድ የተመለከቱት ሲርበን አጉራሽ ሲበርደን አልባሽ የሆነው የደብረ ማርቆስ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ የንጉሱ ጀግኖች ደማችንን እየመለሳችሁት ነው በርቱልን ሲሉ አድናቆታቸውን እና መልዕክታቸውን እየለገሱን ይገኛሉ።
ድላችን በተባበረ ክንዳችን‼️
አዲስ ትውልድ‼️አዲስ አስተሳሰብ‼️አዲስ ተስፋ‼️
የንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት
#ፋኖ_ባዬ_ሽፈራው (ቀኜ)
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ የሰባት ለሰባ ደመላሽ ሻለቃ ተወርዋሪዋ የአሳምነው አናብስቶች
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አፋብኃ ወለጋ ክ/ሀገር ቢዛሞ ዕዝ✊🏽💪🏽
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
"የሰው ልጅ ቅን ሆኖ የከሰረው ክፉ ሆኖ ያተረፈው ነገር የለም‼️"
ቅን እንሁን።
ላንጨርስ የጀመርነው የአማራ ህዝብ ትግል የለም።
ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#የጠላት_እንቅስቃሴ_መረጃ‼️
በዚህ ሰዓት ከቀኑ 5:50 6 አውቶብስ 2 ፒክአፕ እና 1ካሶኒ መከላከያ ከ1 ታንክ እና ዲሽቃ ጋር ወደ ጎጃም በመግባት ላይ ሲሆን አሁን አባይ በረሃ ደርሷል ሲሉ የፍኖተ አማራ ምንጮች ገልፀዋል‼️
03/ዐ2/2018 ዓ.ም
የጥንታዊቷ ደብረ ምዕራፍ ዋሸራ ማርያም(መንክር ኃይላ ) ገዳም ዓመታዊ የንግስ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ፪(ተፈራ ዳምጤ) ክ/ጦር
ዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ በጎንጅ ቆለላ ወረዳ ከሚያስተዳድራቸው ጥንታዊ ገዳማት መካከል በቀዳሚነት የምትቀመጠው
ደብረ ፍዕራፍ ዋሸራ ማርያም ገዳም ( መንክር ኃይላ). #በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት እንደተመሰረተች ይነገራል።
የዚችን ታሪካዊ ገዳም አመታዊ የንግስ በዓል ያለምንም ስጋት እንዲከበር የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ አመራሮችና አባላት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሲሆን
እንደ ዛሬው ዘመናዊ ትምህርት ባልተስፋፋበት በዚያ ዘመን ፊደል ቀርጻ፣ ብዕር አዘጋጅታ እና ብራና ዳምጣ ልጆቿን በማስተማር ብቸኛ የእውቀት መገብያ ማዕከል ሁና ለሺ ዓመታት ስታገለግል ነበር - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፡፡ ቤተክርስቲያኗ በረጅሙ የታሪክ ጉዞዋ ውስጥ የልጆቿን የእውቀት አድማስ የሚያሰፋ እጅግ በጣም የረቀቀና የዳበረ አደረጃጀትና ይዘት ያለው ሥርዓተ ትምህርት ማለትም
የንባብ ቤት (ፊደል መቁጠር፣ ማንበብ /በአቡጊዳና በመልክተ ዮሐንስ/፣ ቁጥር ማወቅ፣ መሰረተ ሃይማኖትን ማጥናት፣ ወዘተ.)፤
የዜማ ቤት (ጾመ ድጓ፣ ምዕራፍ፣ ድጓ፣ ዚቅ፣ አቋቋም፣ ዝማሬ መዋስዕትና ቅዳሴ በ8ቱ የዜማ ምልክቶች በመታገዝ በግዕዝ፣ በእዝልና በአራራይ የሚዜሙበት)፤
የቅኔ ቤት (በግስ እርባታና ሰዋስዋዊ አካሄድ ላይ እንዲሁም በቅኔ አገባብ፣ በቅኔ መንገድ፣ በቅኔ ዓይነት፣ በቅኔ አፈታት፣ በቅኔ አመስጥሮ፣ በቅኔ ዜማልክ፣ በቅኔ አዋጅ፣ በቅኔ ሙያ እውቀት የሚጨበጥበት)፤
መጻሕፍት ቤት (ሰዎችን ለጥናትና ምርምር የሚያዘጋጁ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት፣ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት፣ መጻሕፍተ-ሊቃውንት፣ መጻሕፍተ-መነኮሳት፣…ወዘተ የሚሰጡበት) አደረጃጀት ከማዳበርም አልፋ ዓለምን ያስደመሙ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ቅርሶች እንዲፈጠሩ በማድረግ ተንከባክባና ጠብቃ ለዚህ ትውልድ ያሻገረች ብቸኛ የሀገር ባለውለታ - ደብረ ምዕራፍ ዋሸራ ማርያም ገዳም፣
በሀገራችን ከጥንት እስከ ዛሬ ድረስ ከሚታወቁ የብቃት ማረጋገጫ መስጫ (ማስመስከሪያ) ማዕከላት መካከል ዋሸራ ዋነኛዋ ናት፡፡ የደብረ ምዕራፍ ዋሸራ ማርያም ገዳም በድሮው አጠራር በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር በአሁኑ በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሁለተኛ (ተፈራ ዳምጤ) ክ/ጦር ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ ከአዲስ አበባ በ426 ኪ.ሜትር፣ ከክልሉ ርዕሰ መዲና ባሕር ዳር በ82 ኪ.ሜትር እንዲሁም ከወረዳው ዋና ከተማ አዲስ ዓለም በ31 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።
ደብረ ምዕራፍ ዋሸራ ማርያም ከመመስረቷ በፊት አሁን ገዳሟ ከምትገኝበት በስተምዕራብ አቅጣጫ ‹‹ቁራ ገደል›› እየተባለ በሚጠራው ዋሻ አካባቢ በ10ኛው መ.ክ.ዘ ከአበዳሚት እስከ አበያ እንዲሁም ከግልገል ዳባና ከእናት ዳባ እስከ ዘማ ድረስ በተወሰኑ ሰዎች ይመለኩ የነበሩ ሁለት ዘንዶዎችን በማጥፋት ሕዝቡ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን ያመልክ ዘንድ በወቅቱ በአካባቢው ይኖሩ በነበሩ የሃይማኖት አባቶች ታቦተ ራጉኤል ተተክሎ እንደነበር የገዳሙ ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡
የራጉኤል ቤተክርስቲያን ለ250 ዓመታት ያክል አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በኋላ አምልኮተ ባዕድ በሚፈጽሙ ተቃዋሚዎችና በአካባቢው በነበሩ ጦረኞች ተመዝብሮ ከጠፋ በኋላ እንደገና በአጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግስት በ1260 ዓ/ም የቦታ ለውጥ ተደርጎ ‹‹ጦር መስቀያ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለ2ኛ ጊዜ ተተከለ፡፡ በመቀጠል በአጼ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት በ1304 ዓ/ም ሴቶች የማይገቡበት የወንዶች ገዳም እንዲሆን ተደረገ፡፡ በገዳሙም ገዳማውያን መነኮሳትና ለገዳሙ አገልጋይ የሆኑ ምዕመናን ብቻ በአበምኔቱ እየተመሩ እንዲኖሩ፣ ሀገረ ገዥም ሆነ ሌላ ወራሪ ኃይል ሰራዊት ይዞ ወደ ገዳሙ እንዳይገባ ስርዓት ተሰራ፡፡ በዚህ ስርዓት ከቆየ በኋላ በአጼ ሰይፈ አርዕድ ዘመነ-መንግስት በ1330 ዓ/ም ደግሞ ታቦተ- ጊዮርጊስ እንዲጨመር ተደረገ፡፡
ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ በአጼ ዘርዓ ያቆብ ዘመነ መንግስት ነበር ዋሸራ ማርያም የተመሰረተችው፡፡ አመሰራረቷን በተመለከተ አባቶች እንደሚሉት ከሆነ አሁን ቤተክርስቲያኗ የምትገኝበት ቦታ በወቅቱ ባህር የነበረ ሲሆን ባህሩ ደርቆ ቤተክርስቲያን እንደሚሰራበት ትንቢት ተነግሮ ነበር፡፡ በትንቢቱ መሰረት በተለያዩ ገዳማት ይኖሩ የነበሩ ባህታውያን መነኮሳት ራዕይ ተገልጾላቸው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ታቦተ-ማርያምን ይዘው ወደ ዋሸራ በመምጣት 1ቦታ ላይ አባ ተስፋ ማርያም በሚባሉ አባት ሕንጻ ቤተክርስቲያን አንጸው በ1427 ዓ/ም ታቦተ ማርያም እንደገባች ይናገራሉ፡፡ አያይዘውም የሰረገው ባህር ውስጥ ለውስጥ ተጉዞ በአራቱም ማዕዘናት ወንዞች እንደፈለቁም ይናገራሉ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዋሸራ ማርያም የወንዶችም የሴቶችም ገዳም ሆነች፡፡
---*** በወርኃ ፅጌ በቃል ኪዳኗ መንክር ኃይላ ህዝበ ምዕመኑ(ህዝበ ክርስቲያኑ ) ከጠረፍ እስከ ጠረፍ በመሰብሰብ የሻተውን ሁሉ ጠይቆ የሚያገኝበት)ድንቅ ስፍራ ሆናለች።
---**** የአካባቢው ህብረተሰብ ባህሉን፣እምነቱን ፣ጥበቡን ፣አንድነትና መተሳሰቡን ጠብቆ የሚኖርባት ታሪካዊ ስፍራ ደብረ ምዕራፋ ዋሸራ ማርያም ገዳም(መንክር ኃይላ) ።
ስለ ቦታዋ ስያሜና ሙሉ ታሪኳን ከመጀመሪያዎቹ ቅኔዎች ጋር እያጣቀስን በክፍል ሁለትን በዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ የሚዲያ ክፍል ይከታተሉ
ፅጌ እንዴት በቦታዋ እንደሚከበር በክፍል ሶስት (፫)
ይጠብቁን።
አለሙ መለሰ ብርሃን
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ2ኛ (ተፈራ ዳምጤ)ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ጥቅምት 03/2018 ዓ/ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ቃኚ አናብስቶች በድል ታጅበው እየገሰገሱ ጀብድ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
አብይ አህመድና የእሱን ቀንበር ተሸካሜ የብርሃኑ ጁላ መካላከያ ሰራዊት በአማራ ህዝብ ላያ ያላደረሰው በደል ያልሰራው ሲራ የለም ነገር ግን ህዝብና ማንነታቸው የተነፈጉባቸው የአሳምነው ልጆች ዛሬም እንደትናትና ታሪካዊ ጠላቶቻቸውን ዛሬም እንደ ትናትናው ከመርሐቤቴ ተነስቶ ወደ ለሚ እያመራ ያለውን የ,101 ኛ ክፍለ ጦር አየር ወለድ ኮማንዶ የጠላት ሀይል እንሳሮ ጃሎታ ቀበሌ ላይ ሁለት መኪና የጠላት ሀይል በቦንብና በRPG በመምታት አሰደናቂ ጀብድ ፈፅመዋል!!
የጉልቻ መቀያየር ወጡን አያጣፍጥም ነውና ብሔሉ ሆኖም አብይ አህመድ ከተላያዩ ቦታዎች ያለ የሌለውን ኃይል በማምጣት በሽዋ መሬት ያልሰራው ስራ ያላሰፈረው ኃይለ የለም ይሁንና የአሳምነው አናብስቶች የጥንት አባቶቻቸው በአወረሷቸው የጦርነት ጠበብት ከቀን ወደ ቀን በብርሃን ፍጥነት ወደ ማይቀረው የአራት ኪሎ ግስጋሴያቸውን እየተራመዱ ይገኛሉ።
የአገዛዙ ስራት አሁን ላይ በአማራ የቁርጥ ቀን ልጆቹ እየፈረሰና እየተንኮታኮተ እየተሽመደመድ ይገኛል። እኛም የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፋኖዎች አንድዬ ነፍሳችን ለአማራ ህዝብ በመስጠት ወደ ፊት የሚዳ ጀብዶችን እየሰራን እንገኛለን።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያቆብ አንደኛ ኮር ህዘብ ግኑኝነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ
ጥቅምት 03/ዐ2/2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
ፔጉን ላይክ አድርጉ ፊስቡክና ቴሌግራም ቻናላችን
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/61581657125998/posts/pfbid02DyzfrHWRucXQaGG3kV2sVYNKH9cyaFcERMv1cGCgtyuE3xYPdS17147SasRNPCHTl/?app=fbl
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
የፋሽስታዊውን ስርዓት እኩይ ሴራ በመረዳት የአገዛዙ ኃይሎች ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
መስከረም 03/2018 ዓ.ም
በፋሽስታዊው ሥርዓት እኩይ ሴራ ተጠልፈው ከጠላቶቻቸው ጋር በመተባበር በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን መንግስታዊ ጭፍጨፋ ሲደግፉና በቀጥታ ሲተገብሩ የነበሩ የአረመኔው ሥርዓት ኃይሎች የሥርዓቱን ጭካኔና ውድቀት በመረዳት በይቅርታ ወደ ፋኖና ወደ ሕዝባቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
ከሰሞኑም ሀሉት የሥርዓቱ አገልጋዮች ወደ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር በረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድና ስናን አባጅሜ ብርጌድ ተቀላቅለዋል።
1/ ዘመኑ ማናየ ..አድማ ብተና.. የስናን አባጅሜ ብርጌድን የተቀላቀለ ሲሆን
2/ መዝገቡ ካሴ ..መከላከያ ..በረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድን ተቀላቅለዋል
"በምሕረት ለሚመጡ የምሕረት በሮቻችን ክፍት ናቸው"
ድል ለአማራ ፋኖ!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!
የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር የሕዝብ ግንኙነት ክፍል
መረጃ_ደብረ_ማርቆስ‼️
በቀን 02/02/18 በደብረ ማርቆስ ከተማ ውሀ ጋን ተብሎ የበሚጠረው የሚኒሻ ካንፕ ላይ ንጉስ ተክለ ሀይማኖት ብርጌድ ከቀኑ 11:00 ስአት ባደረጉት ድንቅ ኦፕሬሽን ሙት እና ቁስለኛ አድርገውታል ሲሉ የአይን እማኞች ለፍኖተ አማራ ገልፀውልናል በተመሳሳይ ለሊት 10:00 ስዓት ውሀ ጋኑ ላዬ በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት ዋርድያ እስከ ወዴኛው እንደተሸኝ ምንጮች አድርሰውናል።
ሰበር ዜና
በሁት ተሽከርካሪ ተጭኖ ከለሚ ወደ ጀማ በመጓዝ ላይ ያለ የአገዛዙ መከላከያ አራዊት ሰራዊት ጃሎታ በተባለች ቦታ ሙሉ ለሙሉ ተደመሰሰ።
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አፄ ዘርዓ-ያዕቆብ 1ኛኮር ቃኝዎች በRPG እና ቦንብ በወሰዱት ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት በሁለት መኪና ተጭኖ ወደ ጀማ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ ጃሎታ በተባለች ቦታ ከነ ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ ማጋየት ተችሏል።
የቀሩትን የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ኃይሎች ሙሉ ለመደምሰስ ከፎተኛ ትንቅንቅ እየተደረገ ሲሆን ዝርርዝሩን የምንመለስበት ይሆናል።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም
