653
Suscriptores
Sin datos24 horas
-27 días
+2030 días
Archivo de publicaciones
በ2019 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል እና12ኛ ክፍል ለምትገቡ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትቢሮ በተዘጋጀው የተማሪዎች ውጤት ማላቂያ ስትራቴጂ መሰረት የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት መርሀግበር ላይ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸውማሳሰቢያ መሰጠቱ ይታወቃል፡፡ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርቱ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2018ዓ.ም ተጀምሯል፡፡ ሆኖም በመርሀግብሩመገኘት ያለባቸውን ቁጥር ያክል የት/ቤታችን ተማሪዎች አልተገኙም፡፡ ይህ ደግሞ የተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ እየተደረገ ላለው እንቅስቃሴእንቅፋት ሆኗል፡፡ ስለሆነም በዚህ መርሀግብር እንዲሳተፉ የተመረጡ ልጆች ያላችሁ ወላጆች ቀድሞ በተላለፈው መልእክት መሰረት ልጆቻችሁየት/ቤቱን የደንብ ልብስ አድርገው ከነገ ማክሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ የማጠናከሪያ ትምህርቱ በሚሰጥበት ት/ቤት እንዲገኙእንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ በመርሀግብሩ ላይ ተማሪዎች ባለመሳተፋቸው ለሚገጥማው ችግር ት/ቤቱ ኃፊነቱን የማይወስድ መሆኑንእናሳውቃለን፡፡ ት/ቤቱ
ከ11ኛ ክፍል ወደ 12ኛ ክፍል ለተዘዋወራችሁ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው
በ2018ዓ.ም የክረምት ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በተዘጋጀው የተማሪዎች ውጤት ማላቂያ ስትራቴጂ መሰረት 12ኛ ክፍልን በ2019ዓ.ም የሚቀላቀሉ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት በክላስተር ደረጃ ከሐምሌ 6 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ የሚከታተሉ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት 11ኛ ክፍል በነበራችሁበት ጊዜ ከ1ኛ እስከ 30ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች በሙሉ በማጠናከሪያ ትምህርቱ መሳተፍ ስላለባችሁ ለማጠናከሪያ ትምህርቱ የሚያስፈልገውን ክፍያ ብር 1000.00 (አንድ ሺብር - ለሁለት ወር ክፍያ) በመፈጸም በማጠናከሪያ ትምህርቱ እንድትሳተፉ እናሳስባል፡፡ ትምህርቱ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 አስከ 6፡30 ድረስ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ትምህርቱ የሚሰጠው በሮፋም ት/ቤት ነው፡፡
ት/ቤቱ
Repost from HILLSIDE-CMC-G8
25/07/18
ውድ ተማሪዎች፥መምህራንና የተማሪዎቻችን ወላጆች
በ26/07/18 ሊደረግ የነበረው የሳይንስ ፈጠራና አውደ ርዕይ (science fair) ከበዓል እና ከ3ተኛ ሩብ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ጋር በተገናኘ በልጆቻችን ውጤት ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድር ለቀጣይ ሩብ ዓመት የተላለፈ መሆኑን እየገለፅን የቅዳሜ መደበኛ ትምህርት በነገው እለት የሚቀጥል መሆኑን እንገልፃለን ።
