es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

Tabor Bible Study (ሐዋሳ ታቦር መካነ ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት)

Tabor Bible Study (ሐዋሳ ታቦር መካነ ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት)

Ir al canal en Telegram

ሐዋሳ ታቦር መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠናበት የቴሌግራም ቻናል

Mostrar más
1 165
Suscriptores
Sin datos24 horas
+107 días
+7430 días
Archivo de publicaciones
#የሰሎሞን_ደጅ የውይይት ርዕስ፦ “በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” ኤፌሶን 2፥20 ሲመተ ሐዋርያና ሲመተ ነቢይ በመጽሐፍ ቅዱስና በቤተ
+9
#የሰሎሞን_ደጅ የውይይት ርዕስ፦ “በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤”              ኤፌሶን 2፥20 ሲመተ ሐዋርያና ሲመተ ነቢይ በመጽሐፍ ቅዱስና በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ምን ይመስላል? 🗒መስከረም 23-24 ፓናሊስት፦ወ/ም  ኢዮስያስ ኢዩኤል በሰሎሞን ደጅ የውይይትና የአስተውሎት መድረክ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይቶች ተደርገዋል፦ 👉የቤተክርስቲያን ዋና አገልግሎት ምንድነው? 👉የትኛው አገልግሎት ዋና የትኛውስ አጋዥ(auxiliary) ነው? 👉በየትኛውስ የአገልግሎት መደብ ላይ ነው ሹመት የሚሰጠው? 👉ሹመት ምንድነው? ሹመት ከጸጋ ስጦታ በምን ይለያል? 👉ነቢያት በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን እንዴት ይታያሉ? 👉ነቢይነት በአዲስ ኪዳን ሹመት ወይስ የጸጋ ስጦታ? 👉ሐዋርያት እነማን ናቸው? የበጉ ሐዋርያትና የጳውሎስ ሐዋርያነት እንዴት ይታያል? 👉ሐዋርያን ማን ይሹመው? (የሚሾም ከሆነ) መስፈርቱ ምንድነው?

.    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨               የዕለቱ ጥቅስ       ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ “ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ።” ሉቃስ 12፥22 በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የዓመቱ የቀን መቁጠሪያ 🗓 አጀንዳ መሠረት #መስከረም_29 የዕለቱ ንባብ ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

#ተሐድሶ #ቀን_8 ርዕስ፦ በእምነት ብቻ ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች" ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

.    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨               የዕለቱ ጥቅስ       ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል። እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው።" ቆላስይስ 1፥17-18 በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የዓመቱ የቀን መቁጠሪያ 🗓 አጀንዳ መሠረት #መስከረም_28 የዕለቱ ንባብ ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

#ተሐድሶ #ቀን_7 ርዕስ፦ ቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ (ቃሉ ብቻ) ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች" ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

#ተሐድሶ #ቀን_7 “ቅዱሳት መጻሕፍትን በተጻፉበት በዚያው መንፈስ መተርጎም አለብን።" ኦሪገን (185-254 ዓ.ም.) ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
#ተሐድሶ #ቀን_7 “ቅዱሳት መጻሕፍትን በተጻፉበት በዚያው መንፈስ መተርጎም አለብን።" ኦሪገን (185-254 ዓ.ም.) ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

.    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨               የዕለቱ ጥቅስ       ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ “. . . በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።” ቆላስይስ 1፥15-16 በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የዓመቱ የቀን መቁጠሪያ 🗓 አጀንዳ መሠረት #መስከረም_27 የዕለቱ ንባብ ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

#ተሐድሶ #ቀን_6 "ቅዱሳት መጻሕፍትን አለማወቅ ክርስቶስን አለማወቅ ነው" ቅዱስ ጀሮም (ከ347-420 ዓ.ም.) ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
#ተሐድሶ #ቀን_6 "ቅዱሳት መጻሕፍትን አለማወቅ ክርስቶስን አለማወቅ ነው"        ቅዱስ  ጀሮም (ከ347-420 ዓ.ም.) ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

.    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨               የዕለቱ ጥቅስ       ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ “. . . ከአሮጌውም እህል ትበላላችሁ፤ ፍሬዋ እስኪገባ፥ እስከ ዘጠነኛው ዓመት ድረስ፥ ከአሮጌው እህል ትበላላችሁ።” ዘሌዋውያን 25፥22 በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የዓመቱ የቀን መቁጠሪያ 🗓 አጀንዳ መሠረት #መስከረም_26 የዕለቱ ንባብ ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

ርዕስ፦ የሐዋርያት ሥራ ትምህርተ መለኮት ማስፋፊያ ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

#ተሐድሶ #ቀን_10 "የክርስቲያን አስተማሪዎች ተግባር በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኘውን እውነት ማወቅ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት እውነትን ማስተማር እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ጥቃት ሲሰነዘርበት መከላ
#ተሐድሶ #ቀን_10 "የክርስቲያን አስተማሪዎች ተግባር በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኘውን እውነት ማወቅ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት እውነትን ማስተማር እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ጥቃት ሲሰነዘርበት መከላከል ነው።"              ቅዱስ አውግስጢኖስ ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

.    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨               የዕለቱ ጥቅስ       ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "እናንተም፦ ካልዘራን፥ እህላችንንም ካላከማቸን በሰባተኛው ዓመት ምን እንበላለን? ብትሉ፥ እኔ በስድስተኛው ዓመት በረከቴን በላያችሁ አዝዛለሁ።" ዘሌ. 25፥20-21 በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የዓመቱ የቀን መቁጠሪያ 🗓 አጀንዳ መሠረት #መስከረም_25 የዕለቱ ንባብ ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

#ተሐድሶ #ቀን_4 ርዕስ፦ እንመርምር ዘማሪ፦ ጌታያውቃል እና ብሩክታዊት ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

#ተሐድሶ #ቀን_4 የአስተምህሮ ጥራት እውነተኛውን ወንጌል የሚሰብኩ ለመጽሐፍ ቅዱስ ዐሳብ በታማኝነት የሚቆሙ፣ ቃለ እግዚአብሔርን በሕይወትም፣ በትምህርታቸውም የሚያከብሩ አገልጋዮች መኖራቸው እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ምክንያት ነው። አሳሳቹን የዘመኑን ነፋስ እየተቋቋሙ እውነተኛይቱን መንገድ ለመጠበቅ የሚጥሩ ቅን ምእመናንም በየስፍራው አሉ። ይህ እንዳለ ሆኖ በአጠቃላይ ሲታይ ግን የቀናና የጠራ ትምህርት እጦት እየተባባሰ መጥቷል።   የክርስቶስ ተከታዮች የተባልን እኛ ይብዛም ይነስም እንጂ በብዙ ረገድ ከመሥመር የወጣን፣ ከደረጃ የወረድን፣ አሳሳች ወለብላባ መልክ ያበጀን እንደ ሆነ ከገባን ቆይቷል። ይህ ብልሽት ሁለንተናችንን ያዳረሰ ቢሆንም የሚጀምረውና የሚጎለብተው በአስተሳሰብና በአስተምህሮ መደብ ላይ መሆኑ ብዙ የሚያነጋግር አይደለም።   ትምህርታችን ከተጣመመ የሕይወት ጉዟችን እንደሚሰነካከል ግልጽ ነው፤ ብልሹ ሕይወትም ተመልሶ አስተምህሮን ይበራራርዛል፤ አስተምህሮ ሲበረዝ ወይም ሲሸቃቀጥ ወይም ባዕድ አስተሳሰብ ሲጫነው ኑሯችን ውልግድግድ ይላል። ሕይወታችንንና አገልግሎታችንን በማነጽ ፈንታ የተገነባውን እየናደ እየፈረካከሰ ይሄዳል ወይም የማያለማ የማያሰማ ከጽድቅ የራቀ ፋይዳ ቢስ እየሆነ ይመጣል፤ አንድነታችን ይናጋል፤ ቅዱሱን የእግዚአብሔርን ስም ያሰድባል፤ ለክብሩ ወንጌል መስፋፋት እንቅፋት ይሆናል።   ባለፉት ሁለት ዐሥርት (ዓመታት) በእኛ በወንጌላውያን መካከል የተከሰተው የእውነት ቃል መንሸራተት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል:: በቤት፣ በቤተ ክርስቲያን ምስባክ፣ በመገናኛ ብዙኀን፣ ይህም ማለት በኅትመት፣ በኤሌክትሮኒክ መገናኛ፣ በኢንተርኔት፣ በስብከት ቃል፣ በትንቢት ቃል፣ በጸሎት አንደበት፣ በመዝሙር ቃል፣ የሚተላለፈው በየመስኩ ሁሉ ላይ የተዘራው፣ የበቀለውና የሚሰበሰበው መከር በርጋታ መበጠር፣ መፈተሽና መጤን አለበት።   ሜዳውን የሞላው እንክርዳድ፣ ʻየትከብራለህʼ ሰበካ፣ ሣርና ሥራ ሥር አብዛኛው ገዳይ መርዝ ነው፤ ያልገደለም እንደ ሆነ፣ ዐቅም እያሟሸሸ አጥመልምሎ ቤት የሚያውል ወይም ልቦናን እያነሆለለ የሚያስቀባዥር ክፉ ሥራይ (መርዝ) ነው።   መስኩን የሞሉት የግል ገድላ ገድል ትረካ፣ አልፎ አልፎ መስቀሉም ቢነሣ የክርስቶስን መስቀል ትሩፋቱን እንጂ አርአያውን፣ ማለትም መስቀል ተሸክሞ ጒዞን የማይዳስሱ ትምህርቶች ናቸው። ስሙን እያነሡ፣ ያስገኘልንን ጥቅም እየዘከሩ ነገር ግን መስቀሉ የሕይወት ዘይቤ የአካሄድ ፋና የሌለው ይመስል በረከቱን ዘርፎ የራሱን ሩጫ ሰው ሁሉ በየፊናው በመሰለው እንዲሮጥ የሚያበረታቱ አስተሳሰቦች ናቸው። ʻእርሱ መስቀሉን ተሸከመʼ እንልና ʻእኛ መስቀሉን እንሸከምʼ የሚለውን እንዘለዋለን፤ ʻእርሱ ስለ እኛ ሞተʼ እንልና ʻእንግዲያስ እኛም ሞትንʼ የሚለውን እንዘለዋለን:: መስቀሉ ማትረፊያ ብቻ እንጂ መኖሪያ መሆኑን አናወሳውም።   የእግዚአብሔርን መንግሥት አስቀድሞ ከመሻት ከመስበክ ይልቅ የእኛኑ መንግሥት ማስፋፋት፣ ያሁኑንና የዚህን ዕለታዊ ኑሮ ምቾት ምድራዊ ምኞትና ጥማት ለማሟላት ገንዘብ ንብረታዊ ብልጽግናን እንደ ባንዲራ እያውለበለብን ነን። ይሄው እንግዳ ዘር በየመስኩ ላይ በቅሎ እየተኮተኮተለትም ያለ ነው። በክርስቶስ ተከታዮች ልቦና ፍቅረ ንዋይን መዝራት፣ ሃይማኖትን የስግብግብነት ችግኝ ማፍያ መደብ ማድረግ እንዴት አያስጠይቀንም ትላላችሁ? ለጌታ አገልግሎት በራስ ፈቃድና በደስታ ገንዘብ የመስጠትን የልግስና ጥሪን በአጸፋው በሚገኝ አማላይ የደለበ ኪስ ተስፋ እንቁልልጩ እንዴት እንቀሰቅሳለን? የዕለት ጉርስ፣ የዓመት ልብስ እያጡ ወንጌል በሰበኩት ቀዳሚዎቻችን ላይ የምንሳለቀውስ በምን ድፍረት ነው?   “ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው” የሚለው ክቡር ዐዋጅ የፌዝ ቃል እስኪመስል ድረስ ያለ ውስጣዊ ልቡና ተገዥነት ይለፈፋል፤ የእርሱን ጌትነት ከእኛ ሎሌነት ለምን እናፋታዋለን? ይልቁን ይባስብለን በእርሱ ፈንታ ሰዎችን አጌተየን (አነገሥን)፣ ሥጋ ለባሾችን አደመቅን። ይቀጥላል... ምንጭ፦ የተሐድሶ ጥሪ፣ መመርመር - መመለስ - መታደስ ከሚለው ጥናታዊ ጽሁፍ የተወሰደ። (ኢቫንጀሊካል ቲዮሎጂካል ኮሌጅ የቀረበ) ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

ከሥላሴ በኋላ 15ኛ እሑድ ፈጣሪና ፍጥረቱ 👉ዘሌ. 25፥1-5፣ 20-23 👉ቈላ 1፥15-18 👉ሉቃ. 12፥22-27 በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የዓመቱ የቀን መቁጠሪያ 🗓
ከሥላሴ በኋላ 15ኛ እሑድ ፈጣሪና ፍጥረቱ 👉ዘሌ. 25፥1-5፣ 20-23 👉ቈላ 1፥15-18 👉ሉቃ. 12፥22-27 በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የዓመቱ የቀን መቁጠሪያ 🗓 አጀንዳ መሠረት #መስከረም_24 የዕለቱ ንባብ ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

Wherefore_it_is_necessary_for_the_church_to_retain_the_right_of.pdf9.51 KB

.    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨               የዕለቱ ጥቅስ       ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ “. . . ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል።” ማርቆስ 8፥35 በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የዓመቱ የቀን መቁጠሪያ 🗓 አጀንዳ መሠረት #መስከረም_23 የዕለቱ ንባብ ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study