es
Feedback
💙..ነጠብጣብ ✨🧩

💙..ነጠብጣብ ✨🧩

Ir al canal en Telegram

✨ትዝታማ አለሽ የለኝም ብትይኝ እኔም አላምንሽም በህይወት መንገድ ላይ ተራምደሽ ሳታልፊ ዛሬ ላይ አልቆምሽም፨ ህይወት ያለ ታሪክ ቀን ያለ ጨለማ መች ቶሎ ይመሻል ሰዉ ስለሆንሽ ብቻ ለሰዉ ምታወጊዉ ቅፅበት ይኖርሻል፨ ትዝታ አለሽ?አዉጊኝ ትዝታ አለኝ!ላዉጋሽ ..እንዲህ ብናወራስ...ቅፅበታት እናዉጋ.. የልብ ንግግሮችም አይታጡም..ግቡ💙 ለአስተያየታችሁ @AnchinayehuGebrie

Mostrar más
2 642
Suscriptores
+324 horas
+247 días
+3030 días
Archivo de publicaciones
✨አበባም ሆነ እፀዋት ተክዬ አላውቅም ነበር፤ምክንያቱ ደግሞ ባይፀድቁልኝስ(ባያድጉስ)ብዬ ስለምፈራ ነው።በአየር ንብረቱ አልያም በአፈሩ አለመስማማት ምክንያት ቢደርቁ እንኳን "አያድጉልኝም" የሚል ትርጉም እንዳይኖረኝ ሽሽት ... አለመቻላቸው ላይ መቀለድ የሚችሉ፤ባይሳካስ'ን ሳይፈሩ የሚሞክሩ ሰዎችን አክባሪ ነኝ።በተለይ ሰዎች ፊት....ብዙ ጊዜዋን ወይ በጣም ችሎ መገኘት አልያም ጭራሽ መተው መሃል እንዳጠፋች ልጅ ውጤትን ከራሳቸው ጋር የማይሰፉ ሰዎች ያስገርሙኛል።ጎበዞች! አንድ ቀን አያቴ የጓሮ አትክልቶቹን ውሃ እያጠጣ ሳለ ላግዘው ሄድኩ።ከግብርና ጣቢያ ያመጣቸውን ችግኞች እየተከለ፣አረሞችን እየነቀለ ውሃ እያጠጣ ነበር ሲያየኝ "ሚጢጢ ነይ እስኪ በመትከል አግዢኝ አለ "እጁ ላይ ያለውን የጤና አዳምና የናና ችግኝ እያቀበለኝ ለመሞከር ጥሩ ቦታ ነው፤አያቴ ነው ባያድጉ እንኳን ይ'ረዳኛል። "አፈሩን በደንብ እየሞላሽ ሥራቸውን በደንብ መሸፈኑን አረጋግጪ።ሥሩን አየር ካገኘው ይደርቃል" እሺ አያቴ! "ቁስል የምትነካኪኮ ነው ሚመስለው በደንብ ትከያቸው ኋላ!ሲያድጉ ማደርግልሽን አታውቂም።" አይ አያቴ ሽልማቱ ቀርቶብኝ ባደጉልኝ!እንደ እኔ ሁሉንም ነገር ቁምነገር እያደረገ ለሚቸገር ሰው ይህ ምን እንደሆነ አታውቅምኮ" በውስጤ እያልጎመጎምኩ ጨረስኩ ቀናት አለፉ...ዓይን ዓይናቸውን ሳያቸው የነበሩት ጤናዳምና ናና በሚያምር መንገድ አደጉ፤ቦረቅሁ...ሌላ ቀን ከአያቴ ጋር ውሃ እያጣን እያለ አያቴ "ሚጢጢ መቀስ አምጪ እስኪ" አለኝ ለምን? አያቴ "አትክልቶችሽ የተወሰነ መቆረጥ ይፈልጋሉ" አይሆንም!  ጩኸቴ ስለ አትክልት አይመስልም አያቴ ደንግጦ እያየኝ"ሚጢጢዬ እፀዋት መትከል፣መንከባከብ እንደሚፈልጉ ሁሉ መቆረጥም የሚፈልጉበት ጊዜ አለ።ይህም ለእድገታቸው ወሳኝ የሚሆንበት ጊዜ አለ ።" ቢደርቁስ? አይደርቁም የኔ ልጅ!ለምሳሌ ይሄንን ጤናዳም ተመልከች።እንዲሁ እንዳለ ብንተወው እንደዚሁ እንደተጣመመ እያደገ እያደገ ይሄድና መጨረሻው አይጠቅምም ነገር ግን በዚህ መንገድ ብናስተካክለው ቆንጆ ይሆናል ግዴለም እመኚኝ ካልወድሽው የእኔን እሰጥሻለሁ።ወደራሱ ቆንጆ ተክሎች እየጠቆመ... አያቴ ልክ ነበር...ከተቆረጡ በኋላ አማረባቸው።ብርቅ ሆኖብኝ ስተክል ከረምኩ። እንዲሁ ሌላ ጊዜ አያቴ አትክልቶቹ መሃል ተቀምጦ  ረጅም ነጭ ጢሙን ሳብ ሳብ እያደረገ ሲቆዝም መቀሴን ይዤ አጠገቡ ሄድኩ።በግርምት እያየኝ ምንድን ነው ሚጢጢ? አለኝ ዛሬስ አንቆርጥም? አልኩት ክብደቱ እኩያዬ ሊሆን የሚዳዳውን መከርከሚያ እያወዛወዝኩ።ሳቁ እየታገለው ነይ እስኪ ቁጭ በይ አለኝ፤ከጎኑ ተቀመጥኩ። "አየሽ ሚጢጢዬ ከሰማይ በታች ያለ ነገር ሁሉ የጊዜና የሁኔታ ተገዢ ነው።አንድን ትክክል የሆነ ተግባር ትክክል የሚያደርገው በጊዜው ተመርኩዘሽ ስታደርጊው ይሆናል።ለዛም ነው ጠቢቡ ሰሎሞን
መክብብ 3 ¹ ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። ² ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፤ ³ ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመሥራትም ጊዜ አለው፤ ⁴ ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው፤ ⁵ ድንጋይን ለመጣል ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፤ ⁶ ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ⁷ ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ⁸ ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው።"ያለው
"ታዲያ ትክክለኛው ጊዜ በምን ይታወቃል?" "ሚጢጢዬ እያደግሽልኝ ነው!አየሽ ይሄ ነው ህይወትን አጓጊም አስፈሪም የሚያደርጋት።ተጽፎ የተጠረዘ የኑሮ መመሪያ የለም...ሰዎች ነንና የጋራ ብዙ መሠረታዊ ነገሮች ቢኖሩንም የየራሳችን ግለሰባዊ ማንነቶችም አሉን።ከአንቺ የሚጠበቀው ቀዳሚ ነገር ማስተዋል ነው።በፀጥታ ማየት ከቻልሽ መልስሽን የሚነግሩሽ ሁሉ በዙሪያሽ አለ።አንድን ነገር ማድረግ ያለብሸ ስለቻልሽ ብቻ መሆን የለበትም። ምክንያት ሊሸከም ይገባል።ምክንያት አለኝ ተብሎም ሁሉም አይደረግም። መትከል ስለቻልሽ ብቻ የማትንከባከቢውን አትተክይም፤መቁረጥ ስለማይከብድሽ ዕድል የሚሰጠውን አታጠፊም።ከሁሉም የሚበልጠው ግን የምታደርጊውን ሁሉ በፍቅር አድርጊ።ፍቅርን የሚያውቅ ልብ ምኅረት አለው።ፍቅር በውስጥሽ ሲሞላ ዓለምን የምታይበት መነጽር ንፁህ ይሆናል።ያኔ የአንቺ ሰላም ለሌሎችም ይተርፋል።የተከልሽው ብቻ ሳይሆን አንቺም ለሌሎች መጠለያ፣መጠጊያ ትሆናላችሁ።ሌላው ቀስ እያለ ይደርሳል የኔ ቅመም! እሺ አያቴ! ወደ ቤቷ የምታዘግመውን ጀንበር በጋራ ሸኘናት፤ስታምር🤍      𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮 https://t.me/yeesua_queen

✨ሁሉም ሰው የየራሱ ቋንቋ አለው።በዘመኑ የከተበው የራሱ መዝገበ ቃላት ይዟል...የምድራችን ቋንቋዎች ብዛት በየነገዳቸው ተከፋፍለው በቁጥር የተቀመጡት ብቻ አይደለም...ይልቁንም ሁላችንም የየራሳችን
✨ሁሉም ሰው የየራሱ ቋንቋ አለው።በዘመኑ የከተበው የራሱ መዝገበ ቃላት ይዟል...የምድራችን ቋንቋዎች ብዛት በየነገዳቸው ተከፋፍለው በቁጥር የተቀመጡት ብቻ አይደለም...ይልቁንም ሁላችንም የየራሳችን ቋንቋ ይዘናል። 🪽የልባችንን ያወጋንበት ቋንቋ ድልድይ ቢሆነንም የሰጠን ስሜትና ትርጉም፤የሚፈጥረው ውጤት ግን የተነጋገሩት ሰዎች ብቻ ይሆናል።ምናልባት ያንን ተመሳሳይ ቋንቋ በሚናገሩ ሰዎች ቢመዘን ሁሉንም አያግባባም። 🍂ቋንቋ ድምር ውጤት ይሆናል...የሰዋሰው፣የሁኔታ፣የሚነጋገሩት ሰዎች ታሪክ፣የፍላጎት፣የጊዜ ...የብዙ ነገር ድምር!ስለዚህም የአንድ ግንኙነት የተሻለው ሚዛን ራሱ ግንኙነቱ ቢሆን ጥሩ አይደለም? ይዘን የመጣነው ብዙ ሚዛን ቢኖረንም የመጨረሻው ልኬት ግን ከልብ የሚሰማ እንጂ ከውጪ የተቀመጡ መዛኝ ነኝ ባዮች ጋር ቢቀመጥ ያለ አ'ገባብ የመቅለልም የመክበድም ችግር ያጋጥመዋል! እናም ያለመግባባት ክፉ ቀናችንን ያሳልፈን ዘንዳ የአጠገባችንን ባለቋንቋ ልንማር ይገባናል።ፍቅሩን፣ሃዘኑን፣ያስጨነቀውን፣ያናደደውን፣እኛ እንድናደርግ የሚፈልገውን፣አድናቆቱን፣አብሮነቱን፣ህይወቱን ሲያስነብበን ያ ሰው ምን ይመስላል የሚለውን ማስተዋል ፤ምናልባትም 'እንዴት እንደዚህ ይባላል?'የሚል መብሰልሰላችንን ጤናማ በሆነ መንገድ ለማስተካከል ይረዳናል.... ሀ ሁ የሚቆጠረው ከየኔታ እግር ስር አልያም ረጅም ዘንግ ጥቁር ሰሌዳ ላይ እያመላለሱ ካስተማሩን የእውቀት አባቶቻችን ብቻ ሳይሆን ህይወታችን ውስጥ ካለፉ ካገደሙት ህያው ፊደላትም መሆኑን ማደግ አስተምሮናል... 𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮 https://t.me/yeesua_queen

Repost from Geraworq Tilaye
ግጥሚያው፦ ሥነ ግጥም ኳስ፦ የቃል ሊቀ መኳስ እስታዲየሙ፦ ወመዘክር ደጋፊው፦ ታዳሚው አሰላለፍ፦ በሰልፍ አሰልጣኝ፦ ኪነት (ለነገ ማክሰኞ ሁላችሁም በነፃ ተጋብዛችኋል)
ግጥሚያው፦ ሥነ ግጥም ኳስ፦ የቃል ሊቀ መኳስ እስታዲየሙ፦ ወመዘክር ደጋፊው፦ ታዳሚው አሰላለፍ፦ በሰልፍ አሰልጣኝ፦ ኪነት (ለነገ ማክሰኞ ሁላችሁም በነፃ ተጋብዛችኋል)

✨"ዴርቶጋዳ"የመጽሐፍ ዳሰሳችንተጠናቋል።ለተሳተፋችሁ ሁሉ ምስጋናችን ከልብ ነው።በቀጣል በሌላ ዳሰሳ እንገናኛለን...ክብረት ይስጥልን🤍

record.ogg24.45 MB

ጀምረናል ግቡ!

✨ክቡራን ወ ክቡራት ቤተሰቦቻችን ቀጠሯችን ደርሶ ዛሬ እሁድ 10/01/2019 ዓ.ም ከምሽቱ 02:30 ላይ በደራሲ ይስማዕከ ወርቁ የተፃፈውን ተወዳጅ መጽሐፍ "ዴርቶጋዳ"ን እንዳስሳለን! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል🤍

✨አውቃለሁ ምን እንዳለፍኩ፤ከየት ተነስቼ እዚህ እንደደረስኩ አልረሳም።ዋጋ የከፈልኩበት ህይወት ነው ያለኝ፨በቀላሉ ዛሬ ጋር እንዳልመጣሁ አውቃለሁ፤ከፈጣሪ ቸርነት በታች ብዙ ሆኜ ነው ከዚህ የተገኘሁት
✨አውቃለሁ ምን እንዳለፍኩ፤ከየት ተነስቼ እዚህ እንደደረስኩ አልረሳም።ዋጋ የከፈልኩበት ህይወት ነው ያለኝ፨በቀላሉ ዛሬ ጋር እንዳልመጣሁ አውቃለሁ፤ከፈጣሪ ቸርነት በታች ብዙ ሆኜ ነው ከዚህ የተገኘሁት።ትንሿ እኔ ትመኘው የነበረውን ላደርግላት እጥራለሁ፤ቁምነገሬ መሃል ውስጤ ላለችው ህፃን safe adult መሆን ነው። ህይወት ላይ አልቀልድም።ራሴን ወዳታለሁ፤የምወዳቸውም ታድያለሁ....ታድለውኛልም 😋 ስለ ጥበብ፣ስለ ውበት፣ስለ ሳይኮሎጂ፣ስለ ቡና፣ ስለ ጨረቃ፣ስለ ህይወት፣ስለ ዝናብ፣ስለ መጽሐፍ፣ስለ ፍቅር ለሚመስጣቸው ሰዎች አዳላለሁ።መኖር ከሚችሉ ሰዎች ጋር መሆን ደስ ይለኛል። የማባክናት እኔ የለችኝም።ከተገኘሁ አይቀር ከልቤ ብኖር እመርጣለሁ።መሄድ የተማርኩት ብዙ ከፍዬ ቢሆንም የምፀፀትበት አላስቀርም ቢሆን ኖሮ ደስ የሚለኝ እንጂ...'ይመስላል ዘላለም'ቢሆንም  ሁሉም ነገር የሚያበቃበት ቅጽበት ላይቀር ከአሁን ላለመጉደል እጥራለሁ። ሰው መሆኔን አልረሳም።ሰዎችንም ሰውነታቸውን አስታውሳለሁ።የኑሮ ትርጉሜን አስባለሁ።የማመሰግንባቸው ልቦች አውቃለሁ፨መኖር በጣም ቆንጆ ነው...እንደዛ💙 𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮 https://t.me/yeesua_queen

"አንዳንድ ነገሮችን ሩቅ ያደረጋቸው የኑሮ ዘይቤያችን እንጂ የዋጋቸው ውድነት አይደለም!" ከረጅም ጊዜ ዕቅድና መራዘም በኋላ ዛሬ ከጓደኛዬ ጋር ለጠቅላላ ጤና ምርመራ ወደ አንድ የህክምና ማዕከል ሄድን። ማዕከሉ በልዩነት የኩላሊት ዕጥበት ይከናወንበታል እናም የማየት ዕድል ሰጡን።ሰፊው ክፍል ከህፃናት እስከ አዋቂዎች ተሞልቷል።ህመም በቀላሉ Observe ስለማደርግና ልቤን ስለሚያፍነኝ በፍጥነት ወጣሁ። በየጥጋጥጉ በተሰየሙ ወንበሮች ላይም ብዙ አስታማሚዎች ውዶቻቸውን ደግፈው ተቀምጠዋል። መምጣት ላይቀር ነገር ማርፈድ እጅግ ከሚያስቆጭባቸው ቦታዎች ቀዳሚው የጤና ጉዳይ ይመስለኛል።ምናልባት ከዛሬ ነገ እየተባለ ቸል ማለት መሃል ራስን መክፈል ለራስም ለሌላውም ከማስቆጨት በቀር ምን አለው?! ምናልባት ግማሽ ቀን ብቻ ሊፈጅ በሚችል ጊዜ ውስጥ በሚያልቅ አንድ ምርመራ ገና በጠዋቱ ሊደረስበት የሚችል ዕክል ዘመን አጎልምሶት የማይታከም ደረጃ ላይ ሲደርስ ወዲያ ወዲህ መንከላወስ ያስቆጫል አይደል? እንደ ማኅበረሰብ በተለምዶ ለሌሎች የሆኑ ሰዎች የሰጠነው አልያም"ኧረ መች ደልቶኝ፣አንተ ጊዜ ተርፎሃል እቴ፣ነገ ከነገ ወዲያ ቀስ ብሎ ይደርሳል ዛሬ የኑሮ ባተሌ ነኝ...."የሚሉ ንግግሮቻችን መሃል ችላ ያልነው ራሳችንን ነው ለማለት ነው። መድኃኒት የማይገኝለት ማጣትና ፀፀት ደጃችን ሳይገኝ በፊት ሰውነታችንን እንደ እልፍኝ ልንንከባከብ ይገባል ነው ነገሩ።ጤናማ አኗኗር፣የሰውነትን ቋንቋ መረዳት፣ራሳችንን መንከባከብ፣ሰውነታችን የሚፈልጋቸው እንቅስቃሴዎችና ኑረቶች የሚጠይቁት ራስን መውደድ፣ህይወትን ማድነቅ፣በአስተውሎት መኖርና ከሰውነት በመግባባት  እንጂ ለጤና በሚል ስም በየዲጂታል መስኮቶቻችን በሚተዋወቁ ውድ ነገሮችን አይደለም። "በእርግጥም አንዳንድ ነገሮችን ሩቅ ያደረጋቸው የኑሮ ዘይቤያችን እንጂ የዋጋቸው ውድነት አይደለም!" 𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮 https://t.me/yeesua_queen

photo content

✨የኔ ቆንጆ....ታውቂያለሽ አንቺን ላለማስታወስ የኖርነው አይፈቅድልንም፨ከህይወት ሌላ ገጽ ጋር በዚህ መንገድ በአንቺ በኩል ባንተዋወቅ ጥሩ ነበር፨አንቺ በየማለዳው ምትፈኪ አደይ፣ዕልፍ ሸክሟን በሳቅ ውበቷ የደበቀች ቢራቢሮ፣ልክ እንደእሳት እራት .....ልክ እንደርሷ... የአሻራዎችሽ ምስል ሁሉ የልቤ መዝገብ ውሰጥ ይኖርልሻል፨ስትጎድይ የከበደን ከምርም ስለነበርሽ ነው፨ሰው ከፀፀት አይጎድልም መሰለኝ ያልነገርኩሽ ብዙ መውደድ፣በጋራ ያቀድነው ቡዙ ዛሬ፣የኖርነው ሁሉ እኔ ጋር ቢቀርም እንደ አንቺ አይነት ፀሐይ ሴት ግን አውቅ ነበር ሲያኮራ፨ሁሌም ሁሌም ልቤም ፀሎቴም መኖሪያሽ ነው፨ የዛሬ መልካም ልደትሽ ምኞት አምላክ በእቅፉ በእቅፉ ያኑርሽ ነው፨ምድር አትመጥንሽም ነበር ድሮም...እንደ ሁልጊዜው.....'ወድሻለሁ💙 𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮 ፮/፩/፳፻፲፱

💙ውድ ቤተሰብ ለዛሬ ተቀጣጥረን የነበረው የ"ዴርቶጋዳ"መጽሐፍ ዳሰሳ የጠፋ ዶሮ ፍለጋ ወጥተው ያልተመለሱ፣የጠጡት የማር ጠጅ ሰመመን ያለቀቃቸው፣ የቁርጥ ቢላ ያልሰቀሉ፣የዶሮ ፈረሰኛ አልፎ እግር የሚጠብቁ፣አበባየሆሽ ዙረት ያልጨረሱ....የተሰጣቸውን ስጦታ ያልከፈቱ....ለእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ምላሽ ጽፈው ያልጨረሱ....የአዲስ ዓመት ዕቅዳቸውን ገና በመዘርዘር ላይ ያሉ .....ብዙ ቤተሰቦች ስላሉን ለቀጣይ ሳምንት መዘዋወሩን ስንገልጽ በታላቅ የአዲስ ዓመት ስሜት ነው🥰 ተሰባስበን እንመለሳለን🤍

. . . 😵‍💫 በኖርንበት ጊዜ ሁሉ ሁሉንም አዲስ ዓመቶች የጀመርነው በበጎ ምኞትና በብዙ ምርቃቶች ነበር... ስለ ሰላም ስለ ብልጽግና ስለ መተሳሰብ ስለ መፋቀር . . . ስለ ብዙ ጥሩ ነገሮች
. . . 😵‍💫 በኖርንበት ጊዜ ሁሉ ሁሉንም አዲስ ዓመቶች የጀመርነው በበጎ ምኞትና በብዙ ምርቃቶች ነበር... ስለ ሰላም ስለ ብልጽግና ስለ መተሳሰብ ስለ መፋቀር . . . ስለ ብዙ ጥሩ ነገሮች በዕድሜ ዘመናችን ጸልየናል... በተነገረ ቅጽበት ሁሉ ለምርቃት አሜንታ ሰጥተናል... እጃችንን ዘርግተን፣ ድምፃችንን አጉልተን ይሁንልህ ይሁንልሽ ብለናል...  መሬት ላይ ያለው እውነት ግን በተቃራኒው ነው...  ሰው ከሌላው ጋር ቀርቶ ከራሱም ጋር ሰላም የለውም፤ ከቤቱ በረከት ከማዕዱ ረድኤት አያውቀውም፤ በመንገዱ እረፍት፣ በቀዬው ደህንነት አይሰማውም፤ ከመዝሙራችን በተቃራኒ ሃገር ሰላም ብርቋ ነው፤ ከልፋፌያችን በስተኋላ ወጥቶ መግባት በዕጣ ነው፤ ብቻ - መኖር በብዙ ሕመም የተሞላ አሰልቺ ጉዞ ነው!! እኔ ላንተ ደስታ አላዋጣም... አንተ ለእርሷ መሳቅ ምክንያት አትሆንም... እነርሱ ለእነዚያ የስጋት ምንጭ ናቸው... እኛ ለነከሌ የምቾት ጠንቅ ነን... የሆነ የተሳሳተ ነገር እንዳለ አይሰማችሁም?... ከኑረት Equation ውስጥ ያነጠብነው የሆነ ቁልፍ ማስሊያ እንዳለ አታስቡም?... ያላችሁበት ሁኔታ ተስማምቷችኋል?... ግማሽ ምዕተ ዓመት የሞላው የ “Exodus” (1977) ድምጽ ዛሬም ይጮሃል...
“Open your eyes and look within.  Are you satisfied with the life you're living?”~ Bob Marley
ስለ ሰላም በምንሰብከው ልክ ግንኙነታችን ውስጥ ሰላም አለን?... ስለ ፍቅር በምናወራው ልክ ሰዎች የመወደድ ስሜት እንዲሰማቸው እናደርጋለን?... ስለ ሕብረት በምንደሰኩረው ከፍታ የተለየ ሃሳብ  የማስተናገድ ቀናነት አለን?...
“Be the change that you wish to see in the world.” ~ Mahatma Gandhi
[ልንሆነው ባንፈቅድም መልካሙን በመመኘት አንደኛ ነን...] ⭐️ በልባችን ጥላቻ ሞልቶም ሃገር ሰላም እንድትሆን ከመፈለግ አንቦዝንም... ⭐️ የሌሎችን ስቃይ ባይሰማንም ርሕራሔን ከመስበክ አንታቀብም...  ⭐️ በጥቅማችን ሲመጣ ቃልአባይ ብንሆንም ታማኝነትን መደስኮር አንዘልም...  ⭐️ 'እኛ' እና 'እነርሱ' ከማለት ባንቦዝንም ስለ አንድነት ማውራት አንሰለችም... [ከቶ ለበጎነት መዋጮአችን ምንድነው?...]
"Transformation begins with oneself before it radiates outward." ~ Lao Tzu (Tao Te Ching)
እርግጥ ቃላችን ላይ ላይሆን ይችላል ችግሩ ያለው... ይልቁንም በድንዛዜ የተሞላው ተሳትፎአችን ላይ እንጂ...  ማለቴ... እንደ ግለሰብ ሰላምን ብንመኝም ከንቃት በተፋታ ጉዞ በቁጣ እንመላለሳለን... እንደ ወላጅ ታማኝ ልጆች እንዲኖሩን ብንመኝም በዝንጋኤ ከፊታቸው እንዋሻለን... እንደማሕበረሰብ ኢፍትሐዊነት ብንቃወምም ጠቅሞን ሲገኝ ፍትሕ እንነፍጋለን... አኗኗራችን ቃላችንን አይመስልም... ቀና መሻታችን ተግባራችንን አያክልም...  
“Everyone thinks of changing the world, but no one thinks of changing himself.” ~ Leo Tolstoy
አዎን... ምርቃቱ ሙሉ ነው... የበጎ ቃል ድርድሩ አልጎደለም... የመልካም ምኞት ግትልትሉ ዛሬም አልተለየም... በአካል ብንርቅም... ተደዋውሎ መጠያየቅ፣  Text ልኮ ቃል መጠበቅ፣  በ Emoji ሃሳብ ማርቀቅ - ብዙ አልደበዘዘም... ግና ከቃል የዘለለ እውነት፣ ከመሬት ጠብ ያለ ምልክት፣ በአብሮነት የተገለጸ ብርታት አልታደልንም... የሚያፈላልግ ፊት፣ የሚያስተሳስብ ሰውነት፣ የሚያከባብር ቀናነት እያየን አይደለም...
ያም ሆኖ አንጠይቅም...
መልካም ነገር ከአፋችን እንጂ ከልባችን ባይኖርስ?... ለማለት ያህል እንጂ ከነፍሳችን እያልነው ባይሆንስ?... ለጨዋታው ድምቀት፣ ለልማድ አበርክቶት ብቻ እየተመሳሰልን ቢሆንስ?...
ወይ ደግሞ አንጠረጥርም....
ከእኛ ጋር አብሮ 'አሜን' የማይል ይኖር ይሆን እንዴ?... ከበጎ ምኞታችን Package ውስጥ የጎደለ ነገር ይኖር ይሆን እንዴ?... መፈለጋችን ውስጥ የአፈላለግ ጥይመት፣ መጠየቃችን ውስጥ የአጠያቅ ዝንፈት ይኖር ይሆን እንዴ?... 'ከትናንት' የሚሻል 'ዛሬ' ከሌለን በመሻሻል ውስጥ ነን ልንል አንችልም... ከቁስ ሃብትና ከረብጣ ልቃሚ የሚበልጠውን የመንፈስ ልዕልና ማየት ሳንጀምር ሰላም አለን አንልም... አዎን - ሁሉም ዓመት በበጎ ቃልና በመልካም ምኞት ነው ሲጀመር የኖረው... በሰላም፣ በፍቅር፣ በብልጽግና መሻት ነው መሠረቱ የተዋቀረው... ምኞትና ተግባር ግን በየዓመቱ እልፍ ክንድ እንደተራራቁ ናቸው...  ❓ ይልቅ በዚህ 'አዲስ' ዓመት ይህን ኮስተር ብለን እንጠይቅ... የጎደለን ምንድነው?... ____ @bridgethoughts

✨✨እነሆ ማለዳችን ነጋልን አሐዱ ብለናል...መስከረም ፩ ,፳፻፲፱🌼 🕰ከጊዜ የከበረ የሰው ልጅ የለውም፨ሁሉነገራችን ጊዜ መሃል የተሰፋ ነው።የምንሰጠው፣የምንቀበለው ውድ ነገር ሁሉ ጊዜ በጊዜ ነው።
✨✨እነሆ ማለዳችን ነጋልን አሐዱ ብለናል...መስከረም ፩ ,፳፻፲፱🌼 🕰ከጊዜ የከበረ የሰው ልጅ የለውም፨ሁሉነገራችን ጊዜ መሃል የተሰፋ ነው።የምንሰጠው፣የምንቀበለው ውድ ነገር ሁሉ ጊዜ በጊዜ ነው።ከጊዜ ጋር ያድሰን! ✨
ባለፉትት 365 ቀናቶች ዉስጥ ብዙ ሁነቶችሆኑ፨ብዙአስተናገድን፨የወደድንዉ:የናፈቅነዉ:የፈራንዉያስከፋን:ያስቦረቀን:ያስተማረን ይህ ዓመት በትዝታ ማኅደር ተከተተ።2018 ምሽት ተኝተን 2019 ማለዳ ነቃን..ተመስገን!!
✨✨🌼🌼🌼 💎ይህ የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ነዉ፨በወርሃ መስከረም አደይ አበባ በነፍስ እንደሚታመን የልብ ወዳጅ ተራራማዋን ሃገር ቀጥሯት አይቀርም፨ ተፈጥሮ ትሰክናለች..ክረምት የሚያገማሽራቸዉ ወንዞች ኩልል:አበቦች ፍክት:ምድር አረንጓዴ ሸማን ልብስ የምታደርግበት ዉብ ጊዜ ነዉ፨ እኛም ራሷን ባስዋበች ተፈጥሮ መሃል በነፍስ በስጋ ተውበን ልንምነሸነሽ ጉዟችንን እንቀጥላለን።ፈገግታ ካረበበበት ገጽታ ጋር... ✨ዓመታችንን ሰላም ያድርግልን፨ብዙ ሆነናልና ለልቦቻችን ዕረፍትን ያድልልን፨ያስማረንን:ያ'ስተማረንን የምንኖርበት ይሁንልን፨የልብ ሥራስ ሰዉን መዉደድ አይደል ከልባችን ያስወድደን፨ለሚወዱን ያብቃን!የአረጋዉያንን ምርቃት:የህፃናትን ደማቅ ሳቅ የምንሰማበት ያድርግልን፨ 🦋ይኼዉ አዲስ ምዕራፍ..አዲስ ዓመት..አዲስ ዘመን...ራሳችንን በሚያስፈልገን መሻታችን ልክ ያስፅፈን!!ያኑረን!!!እንቁ....ለጣጣችን🌼🌼🌼 ✨✨መልካም አዲስ ዓመት ውዶቼ..💙 ✍️𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮 https://t.me/yeesua_queen

🕰ጳጉሜ ❺/❶❸/⓴⓲ዓ.ም

𝖓𝖆𝖍𝖍....𝖒𝖆 𝖊𝖋𝖋𝖊𝖈𝖙 𝖘𝖆𝖛𝖊 𝖚😉..𝖟𝖟𝖟 𝖚𝖗 𝖊𝖋𝖋𝖊𝖈𝖙 𝖐𝖎𝖑𝖑 𝖒𝖊...𝖘𝖙𝖎𝖑𝖑 𝖎 𝖓𝖊𝖊𝖉 𝖚 💃😎

❹/❶❸/⓴⓲ ዓ.ም

ፍ ር ሃ ት ═✦═ ✍ አበራ ለማ ' ያ መረቡ ልቤ - ረገበ እምቢ አለ አንድ ራሱን ማስገር - አቃተው ዋለለ፤ ፍርሃቴ ስጋቴ - በላዬ ነገሠ ውስጥ አንዠቴን ምሶ - ቤቴን አጣረሰ፤ ግና ምነው ፈራሁ
ፍ ር ሃ ት ═✦═ ✍ አበራ ለማ ' ያ መረቡ ልቤ -           ረገበ እምቢ አለ አንድ ራሱን ማስገር -           አቃተው ዋለለ፤ ፍርሃቴ ስጋቴ -           በላዬ ነገሠ ውስጥ አንዠቴን ምሶ -           ቤቴን አጣረሰ፤ ግና ምነው ፈራሁ -           ወኔዬ ባዘቀ በፍርሃት ነቅዤ -           ነፍሴ ተጨነቀ? እድሜ እንደ ብል ሆኖ -           ህይወት ካነተበ ፍርሃት ንጉሥ ሆኖ -           አገር ካስደመመ እናንተም እንደኔው -           ፍርሃት ካባዣችሁ ጠመንዣው፣ ዣንጥላው -           ውሻው ለምናችሁ? ═════════ 🗓 1982 ዓ.ም. 📖 📖 📖 📖 📖

🗓⁰➌/❶❸/⓴⓲ 👣

💙..ነጠብጣብ ✨🧩 - Estadísticas y analítica del canal de Telegram @yeesua_queen